cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Teqwa islamic channal

Рекламні дописи
345
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
አብሽሪ እህቴ ውስጥሽ አይከፋ፤ ዱኒያ እንዲሁ ናት አትፈስም ተርፋ፤ አንድ ችግር ሲቀል ሌላኛው ይመጣል፤ ቆሞ የነበረው በተራው ይወድቃል፤ የወደቀው ሲቆም የቆመው ይደቃል፤ እንዲህ እንዲህ ብለው ጊዜዎች ሲነጉዱ፤ በድንገት ከች ይላል ሞትም ከነጉዱ፤ ቆይ ይሄ ቀርቶኛል ደቂቃ ጠብቀኝ፤ ብትይ አይሰማሽም አያይም ግራ ቀኝ፤ ስለዚህ መሸበር መጨነቅ ከንቱ ነው፤ ላንጨምር ነገር ወይ ላንቀንሰው፤ ባለን እናመስግን በሌለን እንሶብር፤ የባሰም አለና ባዶ መና ሚያስቀር፤ ለዚህ ሁሉ ችግር የመፍትሄ ካዝናው፤ ሸክሙ የማይከብደው አልሀምዱሊላህ ነው።!! ¶=== @Sekinaislamicchannal
Показати все...
#ሶስት ቦታዎች ላይ #ልብህን ፈልግ #ኢብኑል ቀይም رحمه الله ፈዋኢድ በተባለው ኪታባቸው አብደላህ ኢብኑ አባስ رضى الله عنه እንዲህ ማለታቸውን ይጠቅሳሉ ሶስት ቦታዎች ላይ #ልብህን ፈልግ ፦ #አንደኛ፦ ቁርአንን በምትቀራበት ወይም በምታዳምጥበት ወቅት #ሁለተኛ፦ ኢልም በሚቀሰምበትና አላህ በሚወሳበት ስፍራ #ሶስተኛ፦ ብቻህን በምትሆንበትና ነፍስህን በምትተሳሰብበት ወቅት በነዚህ ቦታዎች #ልብህን (ህያው ሆኖ) ካገኘህ አላህን አመስግን፤ በሶስቱ ቦታዎች #ልብህን( ህያው ሆኖ) ካላገኘህ #ልብ የለህምና አላህ #ልብ እንዲሰጥህ ተማፀነው
Показати все...
የሂባዋ ናርዶስ ክፍል ሀያ (ፉአድ ሙና) . ቀመር የኢምራን ነገር ተስፋ እያስቆረጣት የመጣ ይመስላል፡፡ ከሱ የጠበቀችውን ክብር እያገኘች አይደለም፡፡ ዶርም ውስጥ ተኝታ በደንብ ስታሰላስለው የነበረው ኢምራንን የምታስገድድበትን አዲስ መንገድ ነበር፡፡ ምንም አይነት አዲስ መንገድ አላገኘችም፡፡ ከዶርም ወጥታ በቀጥታ እየተንደረደረች ወደ ኢምራን ቢሮ ሄደች፡፡ ኢምራን ቢሮው ውስጥ ተቀምጦ እያነበበ ነበር፡፡ ሳታንኳኳ ቢሮውን በርግዳው ገባች፡፡ ኢምራን ሁኔታዋ በጣሙን አስደንግጦታል፡፡ ጠረጴዛውን አልፋ ሄዳ ጭኖቹ ላይ ተቀመጠች፡፡ ‹‹ደህና ነሽ ግን?›› በግርምት እያየ ጠየቃት፡፡ ‹‹ኢምሩ በአላህ ይሁንብህ አግባኝ! ካንተ ሌላ ጥብቅ የነበርኩ መሆኔን የሚያውቅ የለም! አዲስ ሰው መልመድ አልችልም እባክህ!›› ‹‹ቀመር ይኼ እኮ በልመና የሚሆን አይደለም! ውስጤ ላይ ላንቺ ያለኝ ፍላጎት ተንኗል፡፡ ተረጂኝ!›› ‹‹የመጨረሻ ውሳኔህ ነው?›› ‹‹አዎ አዝናለሁ!›› ‹‹በቃ መጥጠህ ወረወርከኝ? ስሜትህን አረካህብኝ በቃ?›› ቀመር ማልቀስ ጀመረች፡፡ ኢምራን ለቅሶዋ ሰልችቶታል፡፡ ‹‹ለሰራሽው ስራ ሀላፊነቱን ራስሽ ውሰጂ! አስገድደሽኝ እንጂ አስገድጄሽ ያደረግኩት ነገር የለም!›› ቀመር ተፈናጥራ ቢሮውን ለቅቃ ወጣች፡፡ ልቧ ውስጥ የነበረው ተስፋ ሙሉ ለሙሉ ሲተንን ተሰማት፡፡ * ልክ እንደ ፅጌረዳ አበባ …. የፍካቷ ቀን በመጣ ጊዜ አይኖች እንደሚቃብዙባት …. ብዙዎች እንደሚመኟት ….. አዎን ልክ እንደ አበባዋ ፍካት አክሳሚ እጆች እንደሚሽቀዳደሙባት ….. የተቀጠፈች ቀን ከቀናት የዘለለ እድሜ እንደማይኖራት …. እንደምትሟሽሸው እንደሷ እንደአበባዋ ….. ናርዶስም ፈክታ ፣ ሂባም አብረቅርቃ ነበር፡፡ የሂባ ትዳር ጎርባጣ መሆን ሁለቱንም ሲያሳዝናቸው ፣ ማምለጫ ሲያስፈልጋቸው …. ስሜቱን እኩል ሲጋሩት ያኔ የመጀመሪያው ስብራታቸው ነበር፡፡ ዛሬ ግን ከብዶ የሚከብድ …. እንዲሁ በቃኝ ተብሎ የማይመለጥበት የጭንቀት አጥር ውስጥ ታጭቀዋል፡፡ ዛሬ ማንንም ለመውቀስ የማይመች ሁኔታ ላይ ወድቀዋል፡፡ ‹‹እና ምርመራውን ምን አሰብሽ?›› ሂባ የናርዶስ አልጋ ላይ እግሮቿን በልቅጣ ትራሷን ተደግፋ አልጋው ላይ በፊቷ ተደፍታ የደነዘዘችውን ናርዶስን ጠየቀቻት፡፡ ‹‹አላውቅም›› ‹‹ናርዲዬ እንዲሁ ክፍልሽ ውስጥ ታሽገሽ ሳምንት ሊያልፍ እኮ ነው! ቢያንስ ለመፍትሄ ይረዳናል ተመርመሪ!›› ‹‹ለየቱ መፍትሄ? ቀን ከሌት ክኒን ለመዋጥ? ንገሪኛ ለምኑ ነው የሚረዳን?›› ናርዶስ ለቅሶዋን ቀጠለች፡፡ የናርዶስ ፊት ጠውልጓል፡፡ በለቅሶ ብዛት አይኖቿ አባብጠዋል፡፡ ለቤተሰቦቿ ስራዋን እርግፍ አድርጋ ትታ መኝታ ቤቷ መታሸጓ ትልቅ ዱብዳ ሆኖባቸዋል፡፡ ምግብም በብዙ ልመና ጥቂት ብትወስድ ነው፡፡ ሁሉም ነገር በአንድ ቀን ተገለባብጧል፡፡ ሳቂታዋ ናርዶስ ለቅሶ ቤት ሆናለች፡፡ ሂባ ሁኔታዋ እጅጉን እያሸበራት ነው፡፡ በዚህ ከቀጠለች አቅም አንሷት መሞቷ ነው፡፡ ሂባ ልመናዋን ቀጥላለች፡፡ ‹‹ናርዲዬ አሁን እኮ እሱ ስላለበት ነው ይዞሽ ሊሆን ይችላል ብለን ያሰብነው! ምን ይታወቃል ይዞሽ ባይሆንስ? መመርመሩ ይሻላል ተይ!?›› ‹‹ሂባ ለምን አጉል ተስፋ ትሰጪኛለሽ? በየቀኑ ያለምንም መከላከያ ነበር እኮ ስንፋተግ የነበረው! ……ምናለ ቢያንስ እንኳ ትንሽ ቢያስብልኝ? ደደብ! ….. ራስ ወዳድ ነው!›› ሂባ የናርዶስን ስልክ ከአጠገቧ አንስታ ልታስነሳው ሞከረች፡፡ ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ሳምንቱን ሙሉ ተዘግቶ ነበር፡፡ ቻርጅ ከሰካችው በኋላ ድጋሚ አስነሳችው፡፡ ስልኩ በርቶ ትንሽ እንደቆየ በርካታ መልዕክቶች ገቡ፡፡ የኤርሚያስን መልዕክት ከፈተችው፡፡ ‹‹ለተፈጠረው ነገር አዝናለሁ፡፡ እኔም ለራሴ ማሰብ ስለነበረብኝ ነው፡፡ መከላከያ ለምን እንድንጠቀም አላደረግክም ላልሽኝ ….. ሎሊፖፕ ከነልጣጩ መምጠጥ እንደማለት ነው፡፡ ስሜት አይሰጠኝም! አዝናለሁ!›› ይላል፡፡ ሂባ ማንበብ የፈለገችውን ስላገኘች ስልኩን መልሳ አጠፋችው፡፡ ‹‹እና ናርዲዬ እስከመቼ ነው በዚህ ሁኔታ የምትቀጥይው?›› ‹‹እስከምሞት ነዋ! ከዚህ የአታላዮች አለም እስክገላገል!›› ብላ ወደ ሂባ ፊቷን መለሰችና ንግግሯን ቀጠለች፡፡ ‹‹ሂባዬ ታውቂያለሽ አይደል? እኔ ያላንቺ … አንቺ ያለኔ ደካማ እንደሆንን? …. እ ሂቡ ታውቂያለሽ አይደል ከልጅነታችን ጀምሮ በሁሉም የህይወታችን ጉዳዮች ላይ በጋራ ተማክረን ስንወስን በራሳችን መወሰን እንዳልለመድን? ….. አየሽ ያኔ ሳይረፍድ በፊት ስለ ኤርሚያስ ላማክርሽ ስፈልግ አንቺ በዚያድ ምክንያት ጊዜ አልነበረሽም፡፡ ስንገናኝም ስለ ዚያድ በደል እንጂ ስለ አዲስ ፍቅር ለማውራት ሁኔታዎች ምቹ አልነበሩም፡፡ ያኔ አንቺን አማክሬሽ ቢሆን ኖሮ እንዲህ አልሆንም ነበር፡፡ …. ሂቡዬ ያኔ ብነግርሽ ኖሮ…›› ለቅሶዋ በርትቶ ከንግግሯ ገታት፡፡ ሂባ በናርዶስ ተስፋ መቁረጥ ውስጧ ተረበሸ፡፡ ዳግም ወደ ተወችው መነፋረቋ ተመለሰች፡፡ * በእንባ እና በጭንቅ እንደተሞሉ በርካታ ቀናት ነጎዱ …. ሂባ ለእርግዝና ክትትሏ ወደ ህክምና ተቋም በሚሄዱበት ጊዜ ሁሉ ናርዶስን እንድትመረመር ብትለምናትም ልትሰማት አልቻለችም፡፡ ምርመራ የሚባለው ቃል እጅጉን ቀፏታል፡፡ ስራዋን ትታ ቤቷ ውስጥ ከታሸገች ወር አለፈ፡፡ ቤተሰቦቿ መጨነቃቸው ሲበረታ ሂባ ‹‹ፍቅረኛዋ ከድቷት ነው›› በሚል ምክንያት ልባቸውን ለማሳረፍ ትሞክራለች፡፡ አሁን አሁን ግን እነሱም አልመስል እያላቸው ነው፡፡ የሚያዚያ ወር ገብቶ ጥቂት ቀናት ሄደዋል፡፡ ሂባ እና ናርዶስ የሂባ መኝታ ክፍል ውስጥ ተቀምጠው ስለኢምራን እያወሩ ነበር፡፡ ናርዶስ ስልኳን አንስታ ኢምራን ጋር ደወለችለት፡፡ ‹‹ምን እያደረግሽ ነው?›› ሂባ ደንግጣለች፡፡ ‹‹አታካብጂ ባክሽ የምን መንቀጥቀጥ ነው!›› ስልኩ ተነሳ፡፡ ኢምራን የቀድሞ ጓደኛውን ስልክ ከረዥም ጊዜ በኋላ ሲያይ ተገርሟል፡፡ ‹‹ናርዲ ቀውሷ!›› ‹‹ትሰማለህ ኢምራን! ሂባ ከባሏ ጋር ተፋታለች፡፡ ከአንድ ልጇ ጋር ተቀብለህ ልታገባት ከፈለግክ ፈቃደኛ ስለሆነች ደውልላት! ቻው!›› ስልኩን ጆሮው ላይ ጠረቀመችው፡፡ ‹‹ናርዲ ምንድነው ያደረግሽው?›› ‹‹በቃ ከፈለገሽ ይደውላል፡፡ አለቀ!›› እየተጨዋወቱ ብዙም ሳይቆይ ሂባ ማቃሰት ጀመረች፡፡ ምጧ መጥቶ ነበር፡፡ ናርዶስ ሮጥ ብላ ወ/ሮ ዘምዘምን ጠራቻቸው፡፡ ጎረቤት ተሰበሰበ፡፡ እናቷ እንደደገፏት ናርዶስ የምታውቀው ባለላዳ ጋር ደውላ ይዘዋት ወደ ጤና ጣቢያ ሄዱ፡፡ ጤና ጣቢያ ደርሰው ሂባን ለነርሶቹ ካስረከቡ በኋላ ውጪ ላይ ቆመው እየተቁነጠነጡ የመውለዷን ብስራት መጠበቅ ጀመሩ፡፡ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ የሂባ አባት ስለተደወለላቸው ከስራ ቦታቸው መጡ፡፡ ሁሉም በጉጉት የሚጠብቀው የሂባን ልጅ በሰላም ወደዚህ አለም መቀላቀል ነው፡፡ ናርዶስ በሩ ላይ ከተሰበሰቡት ሰዎች መሀከል ተነጥላ ወደ ፎቅ ወጣች፡፡ የላይኛው ፎቅ ከታች ወደ ላይ እስከጣራው ድረስ ደረጃው ዙሪያውን ክፍት ነው፡፡ ታች ሆና የላይኛው ፎቅ ላይ ያየችው ነገር አለ፡፡ ራመድ ….. ራመድ …. አንደኛ ፎቅ ….. ሁለተኛ ፎቅ ….. ሶስተኛ ፎቅ ….. አንድ ቀይ ቀለም የበዛበት ማስታወቂያ የተለጠፈበት ቢሮ ውስጥ ገባች፡፡ እጇን ከጠረጴዛው ወዲያ ተቀምጣ ስትቦዝን ለነበረችው ነርስ ዘረጋችላት፡፡ ደሟን ወስዳ ጥቂት ደቂቃዎችን እንድትታገሳት ጠየቀቻት፡፡ ናርዶስ ተስፋ መቁረጧ ፊቷ ላይ እየተነበበ ከቢሮው ወጥታ ወደ ታች ቁልቁል ተመለከተች፡፡ የማዋለጃ ክፍሉ በር ላይ ወላጆቿ እና ጎረቤቶቿ ሲቁነጠነጡ ተመለከተች፡፡ ሁሉም የሂባን መውለድ በተስፋ እ ንደ
Показати все...
ሚጠብቁ ገመተች፡፡ የሂባ ልጅ የመጣው ከወንድ ጋር ተኝታ ነው፡፡ የናርዶስም ስብራት የተፈጠረው ከወንድ ጋር ተኝታ ነው፡፡ ልዩነቱ ግን በጋብቻ እና በዝሙት መሀል ነው፡፡ ከጋብቻው ልጅ ….. ከዝሙቱ ደግሞ በሽታ! ጋብቻ ምንም ያህል የተመቻቸ ባይሆን እንኳ ፍሬው እንደዝሙት አይከፋም ስትል አሰበች፡፡ ጋብቻ ያስከተለው ህይወትን ….. ዝሙቷ የሸለማት ሞትን እንደሆነ ስታስብ እንባዋ ቀደማት፡፡ ናርዶስን የመረመረቻት ነርስ ከላብራቶሪ የመጣላትን ውጤት ከተመለከተች በኋላ ወደ ተረኛው የስነ ልቦና ባለሙያ ደወለች፡፡ ካፌ ውስጥ እያውደለደለ ነበር፡፡ እየሮጠ መጥቶ ወደ ቢሮው ገባ፡፡ ነርሷ ወደ ውጪ ወጥታ ናርዶስን ጠራቻት፡፡ ናርዶስ ቢሮው ውስጥ እንደገባች ነርሷ ቢሮውን ዘግታ ወጣች፡፡ ቀጫጫው የስነ ልቦና ባለሙያ እንድትቀመጥ ከጋበዛት በኋላ ለምን መመርመር እንደፈለገች ጠየቃት፡፡ ነገረችው፡፡ ከጅምሩ ምክር ማብዛት ሲጀምር ሰለቻት፡፡ ‹‹ቫይረሱ ቢኖርብሽ እንኳ በህይወት መኖር አትችይም ማለት አይደለም! ከቫይረሱ ጋር አብሮ መኖር ይቻላል …..›› ወሬው ሰለቻት፡፡ ‹‹ይቅርታ …… የምትለውን ሁሉ አውቀዋለሁ፡፡ አሁን ውጤቴን ብቻ ንገረኝ!›› ተበሳጨች፡፡ ‹‹ካልሽ መልካም ….. ውጤቱ የሚያሳየው ቫይረሱ በደምሽ ውስጥ እንዳለ ነው ይህ ማለት ግን ….›› ‹‹እልልልልልልልል›› የሚል የደስታ ጩኸት ጤና ጣቢያውን አናጋው፡፡ ሂባ በሰላም የመገላገሏን ብስራት የሰሙ ቤተሰቦቿ እና ጎረቤቶቿ ያወጡት ድምፅ ነበር፡፡ ናርዶስ የስነ ልቦና ባለሙያውን ሳታስጨርሰው ትታው ወጣች፡፡ የጠበቀችውን ውጤት መስማቷ ብዙም አላስደነገጣትም ነበር፡፡ ከመተላለፊያው ላይ ቆማ ማዋለጃ ክፍል በር ላይ እየተካሄደ ያለውን የደስታ ትዕይንት ተመልክታ ፈገግ አለች፡፡ ፈገግ ለሂባ ….. ፈገግ ለጓደኛዋ ደስታ …. ፈገግ ለአብሮአደጓ የአብራክ ክፋይ ….. ፈገግ! የቤተሰቡን …. የራሷንም እናት ደስታ ስታይ ለቤተሰቧ ውርደት መሆንን ፈራች፡፡ ከረፈደ በኋላ መንቃቷ እያመማት ቀስ ብላ በሌላኛው የፎቁ መውረጃ በኩል ወርዳ ወደ ውጪ ወጣች፡፡ ወዴት እንደምትሄድ አታውቅም …. ቦርሳዋን ብቻ እንደያዘች ….. ማንም ወደ ማያውቃት ….. ማንንም ወደማታሰድብበት ቦታ ለመሰደድ ወሰነች፡፡ ታክሲ ውስጥ ….. ከዛም መናኸሪያ …… ከዛም አንድ አባዱላ መኪና ውስጥ እንዱ ደላላ ጎትቶ ሲያስገባት …. መኪናው ወዴት እንደሚሄድ እንኳ አታውቅም! ብቻ ከአዲስ አበባ ውጪ መሆኑን ብቻ ነው የፈለገችው …… ከብዙ ደቂቃዎች በኋላ ….. ናርዶስ አዲስ አበባን ለቅቃ ወደማታውቀው ስፍራ ተጓዘች፡፡ ሂባ ከሆስፒታል ከወጣች ጀምሮ ጥያቄ የሆነባት ናርዶስን አለማየቷ ነበር፡፡ ቤተሰቦቿ ተጨንቀው ስልክ በተደጋጋሚ ቢሞክሩም ….. ስልኳ ዝግ ነው፡፡ ሳምንት … ናርዶስ የሌለችበት ባዶ ቤት ውስጥ አለፈ፡፡ ዚያድ ልጁን ለማየት ብቅ ባለበት እግረ መንገዱን አባቷ ባዘዙት መሰረት ‹‹ፈትቼሻለሁ›› ብሏት አዲስ የሰርግ ጥሪ ካርድ ሰጥቷቸው ሄደ፡፡ ተፈላጊ ነኝ ለማለት ይመስላል፡፡ ገንዘብ አለው …… ሴት ለእርሱ የምትገዛ እቃ ናት፡፡ * ቀመር የነበራት ተስፋ ሲሟጠጥ ለመጨረሻ ጊዜ ኢምራንን አገኘችው፡፡ ሻንጣዋን ይዛ ነበር፡፡ በጣም ደንግጧል፡፡ ‹‹ወዴት ነው?›› ‹‹ወደ ቤት …. በቃኝ ባክህ እዛው የግል እማራለሁ … ወንጀል ከለመድኩበት ቦታ ልሽሽ!›› ‹‹እንዴ ቀመር ጎበዝ ተማሪ እኮ ነሽ …›› ‹‹እሱን ተወው ለማንኛውም አሁን ላገኝህ የፈለግኩት ባለፈው ሂባ ያማከረችህ ጉዳይ ስለራሷ እንደሆነ ልንገርህ ብዬ ነው፡፡ ፈትታለች … ሲመስለኝ ልጅም አርግዛለች … አግባት›› ‹‹ጓደኛዋ ደውላ ስትነግረኝ ወዲያው ነው የነገረችኝ ስለራሷ እንደነበር የገባኝ …. ግን ለእማማ ስነግራት የወለደች ሴት አታገባም … ያኔ እንደዛ አድርጋህ ምናምን አለች …. እዛው ደሴ ቤተሰብ የሚያመጣውን  ለማግባት ወስኛለሁ ባክሽ!›› ‹‹እሷ የወለደችው እኮ አግብታ ነው አይደል እንዴ ….. አንተ ሳታገባ በዝሙት የረከስክ መሆንህን እንደውም ለሂባ ንፅህና የማትመጥን መሆኑን አትነግራቸውም ነበር? …… ያው ለነገሩ ፍርዳችን ሁሌም ሚዛናዊ አይደለም፡፡ ወንድ እንዳሻው ቢቆሽሽ አይታወቅበትም …. አይታወቅበትም ብቻ ሳይሆን ቢታወቅም እሱ ወንድ ስለሆነ ችግር የለውም አይደል? …. ሴት አግብታ ስትወልድ ግን ….. ›› ንግግሯን መጨረስ ከበዳት፡፡ ‹‹እንዴ ጥብቅና መቆም›› ሳቀ፡፡ ‹‹በቃ ቻው የምትመጥንህን ይስጥህ ብያለሁ!›› ‹‹ይቅርታ ለዚህ ውሳኔሽ ምክንያት ስለሆንኩ!›› የፌዝ ፈገግታ ፈገግ ብላ ሻንጣዋን እየጎተተች ትታው ሄደች፡፡ የዩኒቨርሲቲውን ግቢ ለቅቃ እስክትወጣ በአይኑ ሸኛት፡፡ የሂባን በደል ቀመር ላይ የተወጣ መሰለው፡፡ በልቡ ‹‹ሁሉም ዕድሉን ሲያገኝ በደለኛ ነው!›› ሲል አሰበ፡፡ ዋናው በር ላይ በእርሱ አነሳሽነት የተመሰረተው የሴቶች መብት ላይ የሚሰራው ቢሮ ክፍለ ሀገር ለሚኖሩ ሴት ተማሪዎች የሞዴስ ወጪያቸውን ለመሸፈን በማሰብ ላሰናዳው የባለድርሻ አካላት የተሳትፎ ምክረ ሀሳብ ማጎልበቻ ኮንፈረንስ የመጥሪያ ባነር ተሰቅሎ ነበር፡፡ * ተፈፀመ፡፡ ✨✨✨✨✨🔰🔰🔰🔰🔰🔰 ✨✨✨✨✨🔰🔰🔰🔰🔰🔰 #share_share_share @Sekinaislamicchannal
Показати все...
የሂባዋ ናርዶስ ዘ መጠናቀቅ (ፉአድ ሙና) . ለተከታታይ አስራዘጠኝ ቀናት ሳስነብባችሁ የነበረው ‹‹የሂባዋ ናርዶስ›› የተሰኘ ልብወለድ ነገ በክፍል ሀያ ይጠናቀቃል፡፡ ፅሁፉ ከተጠናቀቀ በኋላ እንደተለመደው ምስጋና የሚገባቸውን አመስግነን የናንተን አሰተያየት እቀበላለሁ፡፡ ዛሬ እና ከዚህ በፊትም ለሁለት ቀናት ፅሁፉ በሰዓቱ ስላልተለቀቀ ከልብ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡ ከቁጥጥር ውጪ የሆነ ጉዳይ ገጥሞን ስለሆነ ይቅርታችሁን አትንፈጉን! ❗️❗️የመጨረሻው ክፍል ቶሎ እንዲለቀቅ @sekinagroupግሩፕ ለይ Add ማድረግ አለባችሁ🙏🙏🙏🙏 @sekinaislamicchannal 😊😊 ከጥልቅ መውደድ ጋር! ፉአድ ሙና የማይታይ ፊርማ ✨✨✨✨✨🔰🔰🔰🔰🔰🔰 ✨✨✨✨✨🔰🔰🔰🔰🔰🔰 #share_share_share @fuadislamic  @fuadislamic
Показати все...
እንዴት ይኼን ያህል ራስ ወዳድ ትሆናለህ? ትንሽ እንኳ አላሳዝንህም?›› ተነፋረቀች፡፡ ‹‹ናርዲዬ ምንድነው የምትዪው? የምን ራስ ወዳድነት ነው? ምን ሆንሽብኝ?›› ‹‹ቢያንስ እንኳ ምናለ በኮንዶም እንድንወጣ ብታደረግ? እህት ባይኖርህ እንኳ እናት የለህም?›› ‹‹ናርዲ እባክሽ ግራ አታጋቢኝ! ምንድነው አረገዝሽ እንዴ?›› ‹‹እሱማ በምን እድሌ! ስማ! ዛሬ የሄድክበት ሀኪም ቤት እኔም ክትትል ስጀምር እንገናኝ ይሆናል! አንተ ግን ሰብዓዊነት የማይሰማህ …… ደደብ ነህ እሺ!›› ስልኩን ጆሮው ላይ ጠረቀመችበት፡፡ ትንሽ ካነባች በኋላ ሂባ ጋር ልትደውል እንደነበር ትዝ አላት፡፡ ሂባ ጋር ስትደውል ሜላት ወደ መቀመጫዋ እየተመለሰች ነበር፡፡ ሜላት ወንበሯ ላይ እንደተመቻቸች ስልኳን ጆሮዋ ላይ የለጠፈችውን ናርዶስን እየተመለከተች ‹‹ናርዲዬ ይኼ ማለት እኮ አንቺን ይዞሻል ማለት ላይሆን ይችላል፡፡ አይታወቅም እኮ የፈጣሪ ነገር ላይዝሽ ይችላል ብዙ አትረበሺ!›› አለች፡፡ ናርዶስ የደወለችው ስልክ ተነስቶ ስለነበር ምላሽ ሳትሰጣት እያለቀሰች ‹‹ሂባዬ …. ›› አለች፡፡ ‹‹ወዬ ናርዲዬ ምንድነው ድምፅሽ? ምን ሆነሻል?›› ‹‹ጉድ ሆንኩልሽ ሂባዬ! ጉድ ሆንኩልሽ!›› ‹‹የት ነሽ? ምን ተፈጠረ?›› ድንጋጤዋ ንግግሯን የመርበትበት ወዘና አልብሶታል፡፡ ያለችበትን ቦታ ነገረቻት፡፡ የአብሮ አደግ ጓደኛዋ ጭንቅ ላይ መሆን ሆዷ በጣሙን መግፋቱንና በታክሲ ለመሳፈር በጣሙን የሚከብዳት መሆኑን አስረስቷታል፡፡ ከቤቷ ወጥታ ታክሲ ጋር እስከምትደርስ የሆዷን መግፋት ረስታው ነበር፡፡ ሰዓቱ መምሸቱ ደግሞ ታክሲ እንደልብ እንደማታገኝ ሲያረዳት ኮንትራት ታክሲ አናገረች፡፡ የናርዶስ መስሪያ ቤት አቅራቢያ ስትደርስ ደወለችላት፡፡ ከካፌው በር ላይ ወጥታ ተቀበለቻት፡፡ ሜላት ናርዶስን ለሂባ አስረክባ በተደጋጋሚ ሲደውል ወደነበረው ባሏ ሄደች፡፡ ናርዶስ ሂባን ስታይ ለቅሶዋ ቅጥ አጣ፡፡ ክፉኛ አነባች፡፡ ከልብ ለማንባት ምቹ መደገፊያ ያሻል የሚባለው እውነት ለመሆኑ ምስክር ይመስላሉ፡፡ ሂባ ምን እንደሆነች እንኳ ሳታውቅ ደረቷ ላይ አስደግፋት አብራት ታለቅሳለች፡፡ በቃ ዝም ብሎ ማልቀስ! ዝም ብሎ ማንባት!  ‹‹የኔ ቆንጆ ምንድነው የሆንሽብኝ?›› ሂባ ፊቷ በእንባ እንደታጠበ የናርዶስን እንባ ለመጥረግ እየሞከረች ጠየቀቻት፡፡ ከንፈሮቿ እየተንቀጠቀጡ ፣ ሳግ ባጎረበጠው ድምፅ ‹‹ኤርሚ ኤች አይ ቪ አለበት›› አለች፡፡ ሂባ የሰማችውን ለማመን አልቻለችም፡፡ በቀጥታ አዕምሮዋ ውስጥ የተፈጠረው ምስል የናርዶስ ሞት ነው፡፡ ለጥቂት ደቂቃ ከደነዘዘች በኋላ መንሰቅሰቅ ጀመረች፡፡ ለቅሶዋ ናርዶስን ይበልጥ እያስለቀሳት ነው፡፡ አፅናኝ የለም፡፡ ሁለቱም ህመሙን እኩል የቀመሱት ይመስላሉ፡፡ ያነባሉ …. እንባ ግን አይፈውስም፡፡ *** ይቀጥላል… ✨✨✨✨✨🔰🔰🔰🔰🔰🔰 ✨✨✨✨✨🔰🔰🔰🔰🔰🔰 #share_share_share @Sekinaislamicchannal
Показати все...
የሂባዋ ናርዶስ ክፍል አስራዘጠኝ (ፉአድ ሙና) . ናርዶስ ከቢሮዋ ወጥታ በፍጥነት ደረጃውን ስትወርድ የኤርሚያስ ባልደረባ ተከተለቻት፡፡ ባለፈው ሰፈር ውስጥ አብረው አግኝታቸው ነበር፡፡ ናርዶስ ዛሬ ኤርሚያስ ለስብሰባ ወደ ሰበታ ሄጃለሁ ስላላት ከነጋ አላገኘችውም፡፡ እድሜዋ ከሀያ አራት የማይበልጠው አጠር ያለችው የኤርሚያስ ባልደረባ እየተፍለቀለቀች ቀረበቻት፡፡ ‹‹hey ናርዲ እንዴት ነሽ?›› ‹‹አለሁልሽ ሜላትዬ ሁሉ አማን ነው!›› ‹‹ኤርሚ ዛሬ የለም ብቻሽን ነሽ!›› ‹‹አዎ ስብሰባ ነው አይደል? እናንተም ዛሬ ብቻችሁን ዋላችሁ!›› ‹‹ስብሰባ? የምን ስብሰባ?›› ‹‹የቀረው ስብሰባ ሄዶ አይደለም እንዴ?›› ‹‹ምናልባት አዲስ ነገር መጥቶ በዛው ከላኩት አላውቅም እንጂ ዛሬ የቀረው ለህክምና አስፈቅዶ ነው!›› ‹‹የምን ህክምና ነው? አሞታል እንዴ?›› ‹‹ ናርዲ ግር እያልሽኝ ነው! ይቅርታና ፍቅረኛው ነሽ አይደል?›› ‹‹አዎ እንደዛ ነገር ነኝ፡፡ ምነው?›› ‹‹ምንም አይነት የሚከታተለው ህክምና እንዳለ አታውቂም?›› ‹‹እኔ አንድም ቀን አሞት አይቼው አላውቅም!›› ሜላት ነገሩ ግራ ስለገባት ረጋ ብላ ልታወራት ፈለገች፡፡ ደረጃውን ወርደው ወደ ውጪ ከወጡ በኋላ ወደ ቀኝ ታጥፈው ትንሽ እንደተራመዱ ያገኟት ትንሽዬ ካፌ ገብተው ተቀመጡ፡፡ አስተናጋጁ ከመቅፅበት ከፊታቸው መጥቶ ተገተረ፡፡ ማስተናገድ ናፍቆት የነበረ ይመስላል፡፡ ትኩስ ነገር ካዘዙ በኋላ ጨዋታቸውን ቀጠሉ፡፡ ‹‹ናርዲዬ ከኤርሚ ጋር ምን ያህል ጊዜ ሆናችኋል?›› ‹‹በቃ እዚህ ከተቀጠርኩ በኋላ ነው እንደ ጓደኛ ቀረበኝ ቀስ በቀስ ወደዛ ቀየርነው፡፡›› ‹‹እኔ እኮ ከዛም በፊት የምትተዋወቁ ነበር የሚመስለኝ! እንደውም በሱ ጥረት ነው የተቀጠረችው ምናምን ይባል ነበር እኮ!›› ‹‹አጎቴ ነው ያስቀጠረኝ! ኤርሚያስን ከመቀጠሬ በፊት እንኳን ልግባባው አይቼውም አላውቅም!›› ሜላት አቀረቀረች፡፡ እንባ አይኗን ታገለው፡፡ በውሸት ፈገግታ እንባዋን ለማባረር እየሞከረች ቀና አለች፡፡ ‹‹መስሪያ ቤት ውስጥ ስለናንተ የሚወራውን ሰምተሽ አታውቂም?›› ‹‹ስለኛ ይወራል?›› ናርዶስ ቢሮ ውስጥ ያደረጉት ነገር የታወቀ መስሏት ልቧ በፍርሀት ራደ፡፡ ‹‹በጣም ነው የሚወራው!›› ‹‹ምን ተብሎ?›› ‹‹በብዛት የሚወራው ከድሮም እንደምትተዋወቁ ፣ በጣም ራሳችሁን ስለምትጠብቁ እንደማያስታውቅባችሁ ምናምን ነው፡፡›› ‹‹ምኑ ነው የማያስታውቅብን? ፍቅረኛ መሆናችን?›› ሜላት ራሷን ለማደፋፈር ሞከረችና ቀጠለች፡፡ ‹‹የእድሜ ማራዘሚያ ትወስጂያለሽ አይደል?›› ‹‹ፈጣሪ ራሱ ያርዝምልኝ እንጂ እኔ ምን እወስዳለሁ?›› ካለች በኋላ ሳቋን ለቀቀችው፡፡ ‹‹ግልፅ አድርጌ ልጠይቅሽ! አንቺ ቫይረሱ በደምሽ ውስጥ እንዳለ ካወቅሽ ምን ያህል ጊዜ ነው?›› ‹‹የምን ቫይረስ?›› ናርዶስ ሳታስበው ከመቀመጫዋ ተነሳች፡፡ ‹‹አረ ቁጭ በይ ተረጋግተን እናውራ! እኔም ይሄን ስለገመትኩ እኮ ነው ላወራሽ የፈለግኩት!›› ናርዶስ በዝግታ ተመልሳ ተቀመጠች፡፡ ‹‹ይኸውልሽ ናርዶስ ታውቂ ይሆን አይሆን ለማረጋገጥ ነበር ዙሪያ ጥምጥም እየሄድኩ ጥያቄዎችን ስጠይቅሽ የነበረው፡፡ አሁን እንደገባኝ ከሆነ ምንም የምታውቂው ነገር የለም፡፡ በአጭሩ ልልሽ የፈለግኩት ኤርሚያስ HIV career ነው፡፡ ይኼን ሳታውቂ ከሆነ የገባሽበት ከአሁኑ መንገድሽን እንድታስተካክዪ ነው፡፡ ያው ግንኙነታችሁ የአጭር ጊዜ ስለሆነ ሌላ ነገር ውስጥ የገባችሁ አይመስለኝም፡፡›› ‹‹ቆይ ግን አንቺ እንዴት አወቅሽ? ማለቴ እሱ እንደዛ እንደሆነ!›› ‹‹ይኸውልሽ እሱ እዚህ መስሪያ ቤት ወጣት ሆና የገባች ሴት አንድም አታልፈውም ነበር፡፡ ሲበዛ ሴሰኛ ነገር ነው፡፡ እኔም ስቀጠር እንደዚሁ ሊያሰምጠኝ ሞክሮ ነበር፡፡ ግን እኔ የዛኔም ቀለበት አስሬ ለማግባት የቀረኝ ጥቂት ቀን ስለነበር ፊት አልሰጠሁትም፡፡ እሱም ቀለበት እንዳሰርኩ ሲያውቅ ተፋታኝ! እና የገባውን ሰራተኛ ሁሉ በአጉል ጀብደኝነት ካልቀመስኩ ሲል ውጪም ጠጥቶ ከሴተኛ አዳሪዎች ጋር ሲልከሰከስ ነው የያዘው! አንዷን ከኔ በፊት የገባች ፋይናንስ ክፍል የምትሰራ ልጅ እንደዚሁ አሰማምጦ ቤቱ ወስዷት ቤቱ ውስጥ የእድሜ ማራዘሚያ መድሀኒት ምናምን አየች፡፡ ከዛ ደግሞ ስትበረብር የኤች አይ ቪ ህሙማን ማህበር የአባልነት መታወቂያውን አገኘች፡፡ ከዛ መታወቂያውን ፎቶ አነሳችና ለግቢው ሰራተኞች ለምታውቃቸው ላከችላቸው፡፡ እያለ እያለ ሙሉ ግቢው አወቀ፡፡ እሱም ከዛ በኋላ በግልጽ የኤች አይ ቪ ቀን እዚህ ግቢ ሲከበር ምናምን ያስተምራል ነገር! አሁን አሁን እየቆየ ሲመጣ ሰዉ ተላመደውና ተረሳ እንጂ የገባ ሰራተኛ ቀድሞ የሚነገረው ይኼ ነበር፡፡ ያንቺን ግን ገና እንደገባሽ ፍቅረኛዬን አስቀጠርኳት ብሎ ቀድሞ ነበር ያስወራው፡፡ ደግሞም ትመስሉ ነበር፡፡›› ናርዶስ ሰማይ ከአናቷ ላይ የተደፋባት ያህል አዘመመች፡፡ ዝም ፣ ጭጭ! አስር ደቂቃ ፣ አስራ አምስት ደቂቃ ፣ ሀያ ደቂቃ! ዝም እንዳሉ ነጎደ፡፡ በእነዚህ ደቂቃዎች ላለፉት ስድስት ወራት የተካሄደውን ሁሉ እየተመለከተችው ነበር፡፡ ሜላት ትዕግስቷ ሲያልቅ ዝምታውን ለመስበር ሞከረች፡፡ ወንበሯን ወደ ናርዶስ በደንብ አስጠግታ አይኖቿን እያየች ማውራት ጀመረች፡፡ ‹‹ናርዲዬ አብራችሁ ተኝታችኋል እንዴ?›› ‹‹በጣም ብዙ ጊዜ!›› ናርዶስ ፊቷ ፍም መስሏል፡፡ እንባ እንኳን ማፍሰስ አልቻለችም፡፡ ‹‹በጣም ቸኮልሽ ናርዲዬ! Whatever ግን በኮንዶም ነበር የምትወጡት አይደል?›› ‹‹አይደለም ሁሉንም ቀን በባዶ ነበር ያደረግነው!›› አሁን ፊቷ በእንባ መራስ ሰውነቷ መንዘፍዘፍ ጀምሯል፡፡ ሜላትም አቅፋት ማንባት ጀመረች፡፡ ‹‹አንቺ የተማርሽ አይደለሽ እንዴ ናርዲዬ እንዴት ሳትመረመሩ ያለኮንዶም አብረሽው ትወጪያለሽ?›› ‹‹እኔ …… (ተንሰቀሰቀች) ….. HIV? …. የጠፋ ነበር የሚመስለኝ! አንድም ቀን ትዝ ብሎኝ አያውቅም!›› ‹‹ከሚዲያ ላይ ጠፋ እንጂ እኮ ሀገራችን ውስጥ ወረርሽኝ በሚመስል መልኩ እየተስፋፋ ነው፡፡ ለማንኛውም ቶሎ ብትመረመሪ ነው የሚሻለው!›› ‹‹እና ምን በድዬው ነው እኔን ማስያዝ የፈለገው? እንዴት ያለ ራስወዳድነት ነው ይኼ?›› ረዥም ሰዓት ናርዶስ እየተንሰቀሰቀች ሜላት ስታባብላት ከቆየች በኋላ ናርዶስ አልቅሳ ሲደክማት ጥያቄ መጠየቅ ጀመረች፡፡ ‹‹እናንተ ታዲያ ለምን እስካሁን አልነገራችሁኝም?›› ‹‹አንቺም እንዳለብሽ ነው የነገረን ደግሞ ገና መቀጠርሽን ሳናውቅ ማውራት ስለጀመረ አመንነው፡፡ እንጂ እንዲሁ ከገበያ ጥናት ክፍል ተነስቶ ኢንጅነሪንግ ሴክሽን ድረስ የሄደ አልመሰለንም ነበር፡፡›› ‹‹እና አሁን ምንድነው የሚሻለኝ?›› እንባዋን በመዳፏ በጠረገችበት ቅፅበት ተመልሶ ይፈስሳል፡፡ ‹‹መተኛት ከጀመራችሁ ሶስት ወር ይሆናል?›› ናርዶስ ጥቂት እንደማሰብ ካለች በኋላ ‹‹ይሆናል!›› አለች፡፡ ‹‹ይኼን ያህል ጊዜ ከሆነው ብትመረመሪ ጥሩ ነው፡፡ ከጅምሩ የሆነ እርምጃ መውሰድ ትችያለሽ!›› ሜላት ስልኳ በተደጋጋሚ ይጠራ ነበር፡፡ ‹‹ባሌ ጋ ልደውልለት አንዴ!›› አለችና ስልኳን አንስታ እየደወለች ወደ ውጪ ወጣች፡፡ ናርዶስ ይኼን ጭንቅ ለማን እንደምታዋየው ግራ ገብቷት ስታሰላስል ብትቆይም ከሂባ ውጪ የመጣላት ሰው አልነበረም፡፡ እንባዋን ለመጥረግ እየሞከረች ሂባ ጋር ለመደወል ስልኳን ስታነሳ ኤርሚያስ ደወለ፡፡ ውስጧ እልህ እየተንቀለቀለ ስልኩን አነሳችው፡፡ ‹‹ሄሎ የኔ ማር ሰላም ዋልሽልኝ?›› ኤርሚያስ እንደሁሌው እየተቅለሰለሰ ንግግሩን ጀመረ፡፡ ‹‹ምን በድዬህ ነው ግን ኤርሚ?
Показати все...
ርታ! ግን አሁን የተሻለ ነገር እንገንባ! ተረዳኝ! አፈቅርሀለሁ!›› ‹‹ብረዳሽ ደስ ይለኝ ነበር ግን አልችልም!›› ‹‹ማለት?›› ከእቅፉ ተመንጭቃ ወጣችና አፈጠጠችበት፡፡ ‹‹ማለት ማለት?›› ‹‹አታገባኝም?›› ‹‹ውስጤ አልተረጋጋም በዚህ ሰዓት ምንም ልልሽ አልችልም!›› ቀመር እንባዋ ፊቷ ላይ እየተንዠቀዠቀ ቀጠለች፡፡ ‹‹ወንድ ሁሉ አንድ ነው ሲባል ውሸት ይመስለኝ ነበር፡፡ አንተም ከሌሎቹ በምንም አትሻልም፡፡ ስሜትህን ካረካህብኝ በኋላ ልትወረውረኝ ነው ፍላጎትህ!›› ‹‹እኔ ከጅምሩ ስሜቴን ላረካ አልቀረብኩሽም! ከገባሽ አንቺው ነሽ የደፈርሽኝ! ማልቀስ ደግሞ መፍትሄ አይሆንም!›› ‹‹በጣም ጥሩ ስህተታችንን እንድናርም ፈቃደኛ ካልሆንክ ሌላ ስህተት እንቀጥላለን! አየህ አይደል በፍቅር እጅ አትሰጥም ሀይል ብቻ ነው የሚገዛህ! እኔማ የፍቅር ሰው ትመስለኝ ነበር፡፡›› ‹‹እሱን ለመመስከር ካንቺ ይልቅ ሂባ ትሻላለች! ሳፈቅር የምታውቀኝ እሷ ናት!›› የተፈጠረውን የመካረር ስሜት ለማብረድ ፈለገች፡፡ ተመልሳ ወደ እቅፉ ገባች፡፡ ‹‹ስለማፈቅርህ እኮ ነው! እሺ በለኝ እና ደስተኛ ሆነን እንኑር!›› ‹‹ቀመር እኔ አብረን እንድንተኛ እንኳ አልፈልግም እኮ! ግን አንቺ ስትመጪ እምቢ ማለት አይሆንልኝም! ራሴን እንደዚህ ያለ ቆሻሻ ቦታ አገኘዋለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም! ለዚህ ደግሞ ምክንያቷ አንቺ ነሽ! ልንገርሽ አይደል እንደውም ከዚህ በኋላ ቤቴ እንድትመጪ አልፈልግም! ከዚህ በላይ መቆሸሽ አልፈልግም በቃኝ! በቃኝ!›› ለመጀመሪያ ጊዜ ስትስመውም ሆነ ወደ ቀጣዩ ደረጃ ስትገፋፋው ወዲያው ተፀፅቶ ያገባኛል የሚል እሳቤ ነበራት፡፡ ነገሩ ግን የተገላቢጦሽ እየሆነ ፣ ኢምራን ትዳርን እየሸሸ ፣ ለሷ የነበረው መውደድ እንኳ ተሸርሽሮ ቤቴ ድርሽ እንዳትይ ማለት ጀመረ፡፡ በፈጣሪዋ ዘንድ ድንበር አልፋ ልታገኝ ያሰበችው የደስታ ህይወት ገና ከጅምሩ እየራቃት ነው፡፡ እቅፉ ውስጥ እንዳለች ከዚህ ቀደም የሰማችው የነብዩ ሙሀመድ (ሰዐወ) ንግግር ትዝ አላት፡፡ ‹‹አላህ አንድን ባሪያውን ሲወደው ለጅብሪል ጅብሪል ሆይ እኔ ይኼን ባሪያዬን ወድጄዋለሁ አንተም ውደደው ይለዋል፡፡ ጅብሪል ደግሞ ለመልዓክቱ ጌታችሁ ይኼን ባሪያ ወዶታል እናንተም ውደዱት ይላል፡፡ ከዚያም አላህ በምድር ያሉ ሁሉ እንዲወዱት ያደርጋል፡፡ ሲጠላም በተመሳሳዩ ነው›› እናም ምናልባት በነበረችበት ጌታዋን የማስደሰትና ወንጀልን የመራቅ መንገድ ላይ ቀጥላ ቢሆን ለሷ ያለውን ጊዜው ሲደርስ ታገኝ ነበር፡፡ ጌታዋን አስከፍታ ከኢምራን ልታገኝ የፈለገችው ፍቅር በጌታዋ ይሁንታን ያገኘ አይመስልም! ‹‹እሺ ጥሩ …. (እንባዋ አይኗን እየሞላ ይፈሳል) … እስኪ ኢምሩ ንገረኝ ከኔ ምኔን ነው የጠላኸው?›› ውስጧ ላይ የርካሽነት ንፋስ ይነፍሳል፡፡ ‹‹አንቺን በአንቺነትሽ አልጠላሽም፡፡ አንቺን የምጠላሽ የወንጀለኛው እኔነቴ አካል በመሆንሽ ብቻ ነው፡፡›› ‹‹አተርፍ ባይ አጉዳይ ነዋ የሆንኩት!›› እንባዋ ፊቷን ማርጠቡን ቀጠለ፡፡ ድሮ ገና ፊቷ ሲቀየር እንኳ ይደነግጥ ነበር፡፡ አሁን ግን እንባዋ ሲንዠቀዠቅ እንኳ ግድ አይሰጠው ጀምሯል፡፡ *** ይቀጥላል… ✨✨✨✨✨🔰🔰🔰🔰🔰🔰 ✨✨✨✨✨🔰🔰🔰🔰🔰🔰 #share_share_share @Sekinaislamicchannal
Показати все...
የሂባዋ ናርዶስ ክፍል አስራስምንት (ፉአድ ሙና) . ናርዶስ የወሲብ ፊልም የማየት ሱሷን ለመግታት እጅጉን ከራሷ ጋር ትግል እየገጠመች ነው፡፡ ሂባ ፊልም በፍላሽ የሚጭኑ ቤቶች እየሄደች የሆሊዉድ ኮሜዲ ፊልሞችን እያስጫነች ታመጣላታለች፡፡ ናርዶስ ብትጨክን ብትጨክን በሳቅ አትጨክንምና የወሲብ ቪዲዮ በምታይባቸው ጊዜዎች ኮሜዲ ፊልሞችን ማየት ጀምራለች፡፡ ግን እንዲሁ በአንዴ እርግፍ አድርጋ ልትተወው ከብዷታል፡፡ ሂባ ሁሉንም ነገር ችላ ብላ ናርዶስን መልሶ በመስራቱ ጉዳይ ላይ ትኩረቷን አድርጋለች፡፡ የናርዶስ ስልክ እና ላፕቶፕ ላይ የነበሩትን የወሲብ ፊልሞች ሂባ ሙሉ ለሙሉ ስላጠፋቻቸውና በየቀኑም ስልኳን ስለምትፈትሽባት ማየት ብትፈልግ እንኳ ቢሮ ስትሄድ በኤርሚያስ ስልክ የማየት እድል ብቻ ነው ያላት፡፡ እጅጉን ከብዶ የከበዳት ከኤርሚያስ ጋር ያላትን የአልጋ ግንኙነት የመቋጨቱ ጉዳይ ነው፡፡ ልትጠላው አልቻለችም፡፡ ወንዳ ወንድ ቁመናውን ….. ያስለመዳትን አጓጉል ነገር … ብቻ በቃኸኝ ለማለት ብትፈልግም አልቻለችም፡፡ ቢሮ እየመጣ ከአንገት በላይ ሰርቷት ይሄዳል፡፡ በእርግጥ እንደድሮው ፊልሞችን አያመጣላትም፡፡ ምክንያቱም ፊልሞቹ እንዲያደርሷት የፈለገበት ቦታ ደርሳለታለች፡፡ እንደቀድሞው በየቀኑ ባይሆንም በሳምንት ሁለት ቀን እሱ ቤት ሄዳ የለመዱትን ይፈፅማሉ፡፡ ለሂባ ግን እሱ ቤት እንደምትሄድ አትነግራትም፡፡ ዛሬ ከስራ እንደወጣች ከኤርሚያስ ጋር ተያይዘው እሱ ቤት ሄዱ፡፡ ሰዓቱ መሸት ወደማለቱ እየተጠጋ ነበር፡፡ መንፈራገጡ ሲያበቃ አልጋው ላይ እንደተጋደሙ ማውራታቸውን ቀጠሉ፡፡ እሷ በጊዜ መሄድ አለባት፡፡ ‹‹ስማ postpill አላለቀም አይደል?›› ‹‹እስኪ እሱ መሳቢያ ውስጥ ፈልጊ!›› ማርገዝን እጅጉን ትፈራዋለች፡፡ አረገዘች ማለት ጉዷ ሁሉ ተዘረገፈ ማለት ነው፡፡ የአልጋውን ኮመዲኖ ስትከፍተው ብዙ አይነት ክኒኖች ተመለከተች፡፡ ጫፍ ላይ pospill ስላገኘች ኮመዲኖውን ዘጋችና የመኝታ ክፍሉ በር አካባቢ መሬት ላይ ከተቀመጡት የታሸጉ ውሀዎች አንዱን አንስታ ክኒኑን ዋጠች፡፡ ‹‹አንተም የወሊድ መቆጣጠሪያ ትወስዳለህ እንዴ? ምንድነው ይሄ ሁሉ ክኒን?›› ‹‹ባክሽ የቆዩ ናቸው፡፡ ዛሬ ለምን እዚህ አታድሪም?›› ‹‹ያምሀል እንዴ! አሁን ራሱ ላመሸሁበት ሰበብ መፈለግ አለብኝ!›› ‹‹አንቺ ደግሞ ስታካብጂ ነው እንጂ አሁን እኮ ብዙ አልቆየሽም፡፡ ሰበብ የሚያስፈልገው አይነት አይደለም፡፡›› ልብሷን ለባብሳ ስትጨርስ ሊሸኛት ተከትሏት ወጣ፡፡ የውስጥ ለውስጥ መንገዱን ጨርሰው ሜክሲኮ ጋር ሲደርሱ አንድ የስራ ባልደረባቸውን አገኙ፡፡ የኤርሚያስ ቢሮ ውስጥ ነው የምትሰራው፡፡ ከልጅቷ ጋር ሰላም ተባብለው ከተሰነባበቱ በኋላ የፒያሳ ታክሲ ተሰለፉ፡፡ ሰልፉ ረዥም ነበር፡፡ ግን ማለቁ አይቀርም፡፡ ህይወትም እንደዛው ናት፡፡ ረዥም ብትመስልም ማለቋ አይቀርም፡፡ * ሂባ የናርዶስ ነገር ራስምታት እየሆነባት ነው፡፡ ቀን ከሌት የቀድሞዋ ናርዶስን ለመገንባት የሚያስችሏትን መንገዶች ታሰላስላለች፡፡ ናርዶስ አብዛኛውን ሰዓቷን መስሪያ ቤት ማሳለፏ ደግሞ ለሂባ ትልቅ እንቅፋት እየሆነባት ነው፡፡ በሂባ እጅ ትነፃና እዛ ሄዳ በኤርሚያስ እጅ ትጨቀያለች፡፡ ሂባ ቤት ተቀምጣ ቴሌቪዥን እያየች ነበር፡፡ ከእነርሱ ቤት ፊት ለፊት ያለው ቤት የሚኖሩት ጎረቤታቸው ወ/ሮ ገነት መጡ፡፡ የሂባን ለመፋታት መንገድ ላይ መሆን ከራሷ እና ከናርዶስ ቤተሰቦች በቀር የሚያውቅ አልነበረም፡፡ ገና እንደገቡ ሰላምታ እንኳ ሳያስቀድሙ ‹‹ወይኔ ሂባዬ ለካ ከባልሽ ጋር ተጣልተሽ ነው የመጣሽው! እኔ እኮ ስለደረስሽ ልትታረሺ መስሎኝ ነበር፡፡›› አሉ፡፡ ሂባ ከየት እንደሰሙ ግራ ገባት፡፡ ‹‹ማነው እንደዛ ያለው?›› ‹‹ውይ አሁንማ ሁሉም አውቆ የለ እንዴ! አንቺ ግን ምነው ከኛ ይደበቃል ይኼ? እኔስ ብሆን እናትሽ አይደለሁ!›› ‹‹ይኼ እኮ ደስ የሚል ነገር አይደለም! ደግሞ ጊዜው ሲደርስ ማወቅዎ አይቀርም ነበር፡፡›› ‹‹ይሁን እስኪ! እና መች ነው የፍርድ ቤት ቀጠሮው? ያለውን ንብረት ሙሉ ለሙሉ ነው አይደል የሚያካፍሏችሁ?›› ‹‹ኧረ ገንዬ የምን የፍርድ ቤት ቀጠሮ ፣ የምን ንብረት ነው?›› ‹‹እንዴ የሰፈሩ ሴት ሁሉ ቤተሰቦቿን ልታስከብራቸው ነው ስላረገዘች የመኪና መሸጫው ለሷ ሊፈረድ ይችላል እያለ አይደል እንዴ?›› ‹‹እንደሱ ብሎ ነገር የለም፡፡ ወሬ ነው፡፡›› ሂባ ውስጧ እያረረ ነው፡፡ ‹‹አዪ ተይው ተይው! ገና ለገና የሆነ ገንዘብ ትጠይቀኛለች ብለሽ ነው አይደል? ድሮም ሰው እኮ ገንዘብ ሲያገኝ መቀየሩ አዲስ አይደለም!›› ወ/ሮ ገነት ከተቀመጡበት ተነስተው ቤቱን ለቀው ወጡ፡፡ ሂባ የወሬው መናፈስ ግርም እያላት ትኩረቷን እየተመለከተችው ወደነበረው የቴሌቪዥን ዝግጅት ለመመለስ ሞከረች ግን አልቻለችም፡፡ ገንዘቡን ፈልጋ ተፋታች ይሉኛል የሚለው ስጋት ውስጧን ይረብሸው ነበር፡፡ ሰው የራሱን ህይወት ትቶ በሌሎች ሰዎች ህይወት ዙሪያ የማያውቀውን ሲቀባጥር ስትመለከት ቀፈፋት፡፡ * ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሁለተኛው መንፈቅ አመት የትምህርት መርሀ ግብር ተጀምሯል፡፡ ቀመር ቀደም ብላ ለኢምራን ገብታው በነበረው ቃል መሰረት civil engeenering ከመግባት ተቆጥባ biomedical engeeneringን መርጣ ተመድባለች፡፡ የየካቲት ወር ተጠናቆ የመጋቢት ወር ስለተጋመሰ ትምህርቱም በአግባቡ እየተሰጠ ነው፡፡ ቀመር እና ኢምራን ሳያስቡት የወደቁበት የስሜት አረር በዘላቂነት እየተንቀለቀለ ነው፡፡ አብረው ከተኙ በኋላ በጣሙን ተፀፅቶ ነበር፡፡ እሷም ያጠፋችው ጥፋት አሟታል፡፡ ግን ሁለቱም ሲገናኙ ፀፀታቸውን ረስተው ድጋሚ ስሜታቸውን ይከተላሉ፡፡ ኢምራን የማያውቀውን መጥፎ ነገር ለምዶ ያቅበጠብጠዋል፡፡ አንዳንዴ ደግሞ ፀፀቱ መፈጠሩን እስኪጠላ ድረስ ያይልበታል፡፡ ከመጀመሪያዋ መንፈራገጥ ወዲያ ቀመር አብዛኛውን ቀን እሱ ጋር ማደር ጀምራለች፡፡ ዛሬም ምሽቱን አብረው ናቸው፡፡ ትግሉ በሁለቱም አሸናፊነት ሲጠናቀቅ እቅፉ ውስጥ እንዳለች አንሾካሾከች፡፡ ‹‹ኢምሩዬ!›› ‹‹ወዬ›› ‹‹ትወደኛለህ?›› ‹‹እኔንጃ! ይመስለኛል!›› ‹‹ጉረኛ እኮ ነህ!›› ‹‹አይመስለኝም!›› ‹‹እስከመቼ ነው በዚህ ሁኔታ የምንቀጥለው? ለምን ኒካህ አናስርም?›› ‹‹ለምንድነው የምናስረው?›› ‹‹እንዴ! እኔ የማውቀው ኢምራን እንደዚህ አይልም! አሁን የምንሰራው እኮ ወንጀል ሆኖ ይመዘገብብናል፡፡ ሚስትህ ስሆን ግን እንደውም ምንዳ እናገኝበታለን፡፡ ደግሞ ልጅም እወልድልሀለሁ፡፡›› ‹‹ተይ ይሄ ባንቺ አፍ አያምርም፡፡ ራሴን ከዝሙት በብዙ ርቀት ጠብቄ የነበርኩትን ልጅ ገፍትረሽ ካሰመጥሽኝ በኋላ እጅሽን ተጣጥበሽ ልትሰብኪኝ አትሞክሪ!›› ‹‹ለምን ተስፋ ትቆርጣለህ? ተፀፅተን መንገዳችንን ካረምን እኮ አላህ ይቅር ይለናል!›› ‹‹ወንጀል ውስጥ ሆነ ብለሽ እንድንገባ ካደረግሽ በኋላ ይምረናል ስትዪ ትንሽ አይሸክክሽም? ይምረኛል ብሎ ወንጀል መስራት በጣም ያስቃል፡፡›› ‹‹ከዚህ በፊት ለነበረው እኔ ተጠያቂ ልሆን እችላለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ ላለው ግን ተጠያቂው አንተ ነህ! ህጋዊ እንድናደርገው እየለመንኩህ ነው፡፡›› ‹‹ታውቂያለሽ ….. ድሮ እንደ ትዳር የሚያጓጓኝ ነገር አልነበረም፡፡ አሁን ግን ያስፈራኛል፡፡ ደግሞ …….. መሰረቱ ወንጀል የሆነ ትዳር እንዲኖረኝ አልፈልግም፡፡›› ‹‹ገብቶኛል የትም መሄጃ እንደሌለኝ ስለምታውቅ ነው እንደዚህ የምትንጠባረርብኝ! …………. አዎ አጥፍቻለሁ አልኩኝ እኮ! …… የኔ ላደርግህ ጓጉቼ መሄድ ባልነበረብኝ መንገድ ሄጃለሁ! ለሱ ይቅ
Показати все...
ላ አንስታ ለበሰች፡፡ ሙሉ ለሙሉ ራቁቷን ነበረች፡፡ አንሶላውን ተጋራት፡፡ ዝም እንዳሉ መሸ፡፡ አስር የለ፣ መግሪብ የለ ፣ ኢሻ የለ ….. ዝም! ሁለቱም ልብ ውስጥ በዚህ ሁኔታ ፈጣሪ ፊት የመቆም ድፍረት የለም፡፡ ዝምታው ሲደክማት ተጠግታ ተለጠፈችበት፡፡ አቀፋት፡፡ ‹‹ኢምሩዬ አፈቅርሀለሁ እሺ!›› ‹‹እኔም እወድሻለሁ!›› ‹‹የምርህን ነው?›› ‹‹ይመስለኛል! ባልወድሽ ይህን ያህል አልቀርብሽም ነበር፡፡›› ፊቷ ላይ የደስታ ብርሀን በራ፡፡ እንዳታልፈው እስኪሰጋ ድረስ ተለጠፈችበት፡፡ የወደደችውን ስላገኘች ….. ህይወቷን ልትሰጠው የምትፈልገው ሰው ስለተቀበላት ….. ደስ ብሏታል፡፡ ‹‹ግን ቀሙ ትክክል ያልሆነ ነገር አለ አይደል?›› ‹‹የቱ?›› ‹‹አሁን ካንቺ ጋር መተኛቴ!›› ‹‹በጣም ይቅርታ ኢምሩዬ! አማራጭ የነበረኝ አልመሰለኝም!›› ቀና ብላ ከንፈሩን ሳመችው፡፡ መፀፀት የጀመረው ያገኘው እርካታ አልቆበት ከሆነ ብላ ማደንዘዣዋን ደገመችው ….. ሳመችው፡፡ በጣም ደካማ ነበር፡፡ ስትስመው ተመልሶ ስሜቱ ውስጥ ሰጠመ፡፡ የፍራሿ ስቃይ ቀጠለ፡፡ እሱም ሆነ እሷ በፍፁም ራሳቸውን በዚህ አይነት ወራዳ ተግባር ውስጥ እናገኛለን ብለው አስበው አያውቁም፡፡ ጭንቅላቷን ተጠቅማ እያሸነፈች ነበር፡፡ አሁን ግን በአቋራጭ ለማሸነፍ ብላ ሴትነቷን ተጠቀመች፡፡ ሴት ልጅ መሸነፍ የምትጀምረው ሴትነቷን መጠቀም ስትጀምር ነው፡፡ ዛሬ ኢምራን ተደፈረ ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ መድፈር በጉልበት ማነቅ ብቻ አይደለም፡፡ እንዲህ በውበት ሀይል …. እንዲህ በስሜት ሀይል አስገድዶ እጅ እንዲሰጥ ማድረግም መድፈር ነው፡፡ ጠዋቱን ከእንቅልፋቸው ሲነቁ ሁለት ሰዓት አልፎ ነበር፡፡ ቀመር የወር አበባ ላይ ሆና ሰላት የማትሰግድባቸው ቀናትን እንኳ ልምድ ሆኖባት በንጋት ስግደት ሰዓት ትባንን ነበር፡፡ ኢምራንም የሷው ቢጤ ነው፡፡ ወንጀል ፤ ሰሪውን ከመልካም ስራ እንደምትከለክል ለመረዳት የሻ ሰው ሁለቱን መመልከት ይበቃዋል፡፡ የትናንትናው ወንጀላቸው ከስግደት ሲከለክላቸው … ደነገጡ፡፡ ‹‹ሁለት ሰዓት ሆኖ ነው?›› ቀመር ሰውነቷን በአንሶላው እንደጠቀለለች ስልኳን ፈልጋ ስትመለከት ማመን ከብዷት የጠየቀችው ነበር፡፡ ‹‹ማለት ነዋ እንግዲህ! ምነው ደነገጥሽ?›› ‹‹ፈጅር ሳንሰግድ ብዬ ነዋ!›› ፈጅር ጎህ ሲቀድ የሚሰገደው የንጋት ስግደት መሆኑ ነው፡፡ ‹‹ትናንት አስር ፣ መግሪብ እና ኢሻም አልሰገድንም ከረሳሽው ላስታውስሽ!›› ቅስሟ ስብር እንዳለ ወደ ፍራሹ ተመለሰች፡፡ ገና ለስግደት ብቁ ለመሆን ጀናባ ማውረድ የሚባለው መስፈርት ይቀራቸዋል፡፡ ገላቸውን መታጠብ አለባቸው፡፡ ያኔ ጀናባቸው ወረደ ይባላል፡፡ ኢምራን ከወ/ሮ አርሴ መዘፍዘፊያ ተውሶ ቀመር ቤቱ ውስጥ ገላዋን እንድትታጠብ እሱ ደግሞ ግቢው ውስጥ እንደነገሩ በቆርቆሮ የታጠረችው ክፍል ውሀ ይዞ ሄዶ ለመታጠብ አሰበ፡፡ ቱታውን ለብሶ ወደ ወ/ሮ አርሴ ቤት ሲሄድ ወ/ሮ አርሴ እና ሌሎች ተከራዮች ቤቱ ውስጥ ሲሰራ የነበረውን ወንጀል ያወቁ ፣ ያወቁ እየመሰለው ያፍር ነበር …. እነሱ ግድ ይሰጣቸው ይመስል ይጠራጠራቸዋል! የሚመለከተው ….. ከመመልከት ምንም የማይጋርደው ጌታው ግን ያልተፈቀደለትን ቀለበት በማህተሙ ሲዘጋ እየተመለከተው ነበር፡፡ እሱ ያውቃል …. እሱ ተወንጅሏል ….. ግን ምንም አላለም! አይቸኩልማ! . ይቀጥላል … ✨✨✨✨✨🔰🔰🔰🔰🔰🔰 ✨✨✨✨✨🔰🔰🔰🔰🔰🔰 #share_share_share @Sekinaislamicchannal
Показати все...