cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ኦርቶዶክሳዊ ስብከት | ORTHODOX SIBKET

በዚህ ቻናል የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ወጣቶችን በሥርዓተ ቤተከርስቲያን ለማነጽ ታስቦ የተከፈተ ቻናል ነው የስነልቦና ማማከር ከፈለጉ በ @binigirmachew ላይ ያናግሩን

Більше
Рекламні дописи
16 199
Підписники
-124 години
+307 днів
+36030 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
53🙏 25👍 10
ግን… እግዚአብሔር እንደሚያደርግልን እንጂ እንዴት እንደሚያደርግልን አናውቅም፡፡ እንዴት የሚለውን መጠይቅ ያልተሻገረ እምነት አይደለም ፡፡ አምናለሁ ግን… የሚል አስመሳይ ከሃዲ ነው ፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ነው “ግን” አይባልም ፡፡ አፍራሽ የሌለው “ግን” የማይከተለው እግዚአብሔር ፍቅር ነው ፡፡ በርግጥ እንደ ወደድነው ባናውቅም በርግጥ እንደ ወደደን እናውቃለን ፡፡ ራሳችንን እንደ ሰጠነው እርግጠኛ ባንሆንም ራሱን ግን ሰጥቶናል ፡፡ እንዳገለገልነው በሙሉ አፍ ባንናገርም ፣ እንዳገለገለን ግን እንመሰክራለን ፡፡ እርሱ ከፍ ባለው ዙፋን ፣ ዝቅ ባለው በረት ፤ ከፍ ባለው ንግሥና ፣ ዝቅ ባለው እግር ማጠብ ፤ በደሙ በመግዛት በይሁዳ በመሸጥ ሁሉ በሁሉ ሁኖ ይታያል ፡፡ የሰው ፍቅር ሂደት ነው ፣ የእግዚአብሔር ፍቅር የተፈጸመ ነው ፡፡ የምንወደውን ባንሆንም የሆነውን መውደድ የተፈጥሮ ግዴታችን ነው ፡፡ የእግዚአብሔር ፍቅር ግን ግራ በገባን ነገር ላይ መልስ ነው፡፡ ክርስቲያን ነኝ ግን… አይባልም ፡፡ ግን ከተጨመረበት ክርስትና የለም ፡፡ እግዚአብሔርን ማመን ፣ ትእዛዙን መፈጸም ፣ ምሥጢራትን ማክበር ፣ ከሌሎች ጋር በፍቅር መኖር ፣ የተጨነቁትን ማረጋጋት ፣ ሥጋዊ ደስታን መጠየፍ የክርስትናው ግዴታ ነው ፡፡ በመሥዋዕት እዚህ የደረሰ ክርስትና ያለ መሥዋዕትነት አይቀጥልም ፡፡ በዛሬው ዘመን ትልቁ ሰማዕትነት ዓለምን እንቢ ማለት ነው ፡፡ ዓለምንና እግዚአብሔርን ለማስታረቅ መሞከር እግዚአብሔርን ያለ ማወቅ ውጤት ነው ፡፡ ክርስቲያን ዘመናዊ ሳይሆን ዘላለማዊ ነው ፡፡ አንድ ጊዜ ተመሥርቶ ዘመኑን በሙሉ ግን የሚታነጽ ነው፡፡ እርሱን የሚመስሉትን አማንያን የሚወድ ነው ፡፡ ላላመኑ የፍቅርና የአዘኔታ ልብ ያለው ነው ፡፡ በድሀ የማይጨክን ፣ ድምፅ ለሌላቸው ድምፅ የሚሆን ነው ፡፡ ኦርቶዶክስን እወዳታለሁ ግን … አይባልም ፡፡ ቤተ ክርስቲያን እናት ናትና ያለ “ግን” ልትወደድ ይገባታል ፡፡ እናቱን የሚሰድብ እንደሌለ ካለም የተረገመ እንደሆነ ሃይማኖቱንም የሚያቃልል የቀለለ ነው ፡፡ በዓለም ላይ ፍጹም ቤተ ክርስቲያን የለችም ፡፡ ፍጹሙ እግዚአብሔር ያላት ቤተ ክርስቲያን ግን አለችን ፡፡ ፍጹም ነገር መፈለግ አንደኛ ስቃይ ነው ፤ ምክንያቱም አይገኝምና ፡፡ ሁለተኛ፡- ቢገኝም እኛ መግባት አንችልም ፤ ምክንያም ፍጹም አይደለንምና ፡፡ ሦስተኛ፡- ፈቅደው ቢያስገቡን እንኳ እኛ የገባን ቀን ፍጹምነቱ ያበቃል ፡፡ አዎ በአስተዳደሩ ሃይማኖትን ፣ በአገልጋዮቹ እግዚአብሔርን መጥላት ተገቢ አይደለም፡፡ ክርስቲያኖችን እወዳለሁ ግን… የሚል ቀድሞም አይወድም ፡፡ ፍቅር ፍጹም ነገርን ከፈለገ ፍቅር አይደለም ፡፡ ፍቅር ጎዶሎውን ፍጹም አድርጎ ሲመለከት ያን ጊዜ ፍቅር ነው ፡፡ ገና ዘላለም አብረነው የምንኖረውን አማኒ ዛሬ በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አብረነው መኖር ካቃተን በራሳችን ላይ መንግሥተ ሰማያትን እየዘጋን ነው ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ተስማምቶ ከሰዎች ጋር በጠብ የሚኖር ገና ከእግዚአብሔር ጋር አልተስማማም ፡፡ ምክንያቱም በፍቅር ኑሩ ያለውን የእግዚአብሔርን ቃል አላከበረምና ፡፡ ትዳሬን እወዳለሁ ግን… የሚል ሐሰተኛ ነው ፡፡ ትዳር ማለት ሠርግ ማለት አይደለም ፣ ስለዚህ ሁልጊዜ ደስታ አይጠበቅም ፡፡ የትዳር ጓደኛ ማለትም ተማሪ አይደለም ፣ ስለዚህ በሁለት ዓይን አያዩትም ፡፡ ትዳር ልዩነት የታረቀበት እንጂ የተጨፈለቀበት አይደለም ፡፡ የትዳር ውበቱ የተለያየ ጾታ ፣ መልክና ፍላጎት መሆኑ ነው ፡፡ ትዳርን ለዜና ፍጆታ አሳልፎ መስጠት ተገቢ አይደለም ፡፡ “ሰው አባቱና እናቱን ይተዋል ፣ ከሚስቱም ጋር ይተባበራል” ማለት የትዳሩን ምሥጢር ከቤተሰቡም ጋርም አይማከርም ማለት ነው ፡፡ ለቤተሰብ የማይነገረው የትዳር ምሥጢር ዛሬ የሕዝብ ማጫወቻ መሆኑ ያሳዝናል ፡፡ እግዚአብሔርም ይቀጣል ፣ ዝም አይልም ፡፡ መንፈሳዊ አባቴን እወዳቸዋለሁ ግን… ማለት ስህተት ነው ፡፡ ከአገልጋዮች ጋር ያለን ግንኙነት ከግል ሕይወታቸው ጋር ሳይሆን ከተሰጣቸው ቃሉና ጸጋው ጋር ነው ፡፡ በተገቢው ርቀት ከኖርን መልካም ግንኙነት ይኖረናል ፡፡ እፍ ካልን ግን ልንጠፋ ፣ ልናጠፋ ፣ ልንጠፋፋ እንችላለን ፡፡ እፍ ያጠፋልና፡፡ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ሊመረቁ ይገባል እንጂ ሊረገሙ አይገባም ፡፡ በጸሎት ማገዝ እንጂ ቁመት መለካካት ተገቢ አይደለም ፡፡ እግዚአብሔር አፈኛውን አሮንን ሳይሆን አፈ ትቡን ሙሴን መርጧል ፡፡ እግዚአብሔር አገልጋዩን ማንም አይመርጥለትም ፡፡ አገሬን እወዳታለሁ ግን… ማለት ቀድሞም አለመውደድ ነው ፡፡ አገር የእግዚአብሔር ስጦታ ናት ፡፡ እኛን ከዚህ ወገንና አገር ሲፈጥረን እግዚአብሔር አልተሳሳተም ፡፡ አገርን በፓርቲ ፣ ሕዝብን በመሪዎች ማየት ስህተት ነው ፡፡ አገዛዝ ይወድቃል ፤ አገርና ሕዝብ ግን ቋሚ ሁኖ ይኖራል፡፡ ደግሞም “ጋን ቢለቀለቅ ጭልፋ ይሞላል” ይባላልና አነሰ በዛ ሳይሉ አገርን መርዳት ፣ ድሆቿን ከራብ ማሳረፍ ይገባል ፡፡ ያለ “ግን” መውደድ ይሁንልን ፡፡
Показати все...
👍 29 12🙏 9
ጊዜና ማጣት “ሰው ከጊዜና ከማጣት ብዙ ይማራል ።” እግዚአብሔር አስተማሪ ነው ። እግዚአብሔር የሚያስተምረውም በተለያየ መንገድ ነው ። ተማሪው በመረጠው መንገድ ሳይሆን አስተማሪው በመረጠው መንገድ ያስተምራል ። “እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው ? በሚመርጠው መንገድ ያስተምረዋል” ይላል ። መዝ. 24 ፡12 ። ለእኛ የመረጠልን ምን ይሆን ? ብለን መጠየቅ መልካም ነው ። ለአንዳንድ ሰው የተመረጠለት ሕመም ሊሆን ይችላል ። አንዳንድ ሰውም የተመረጠለት ስደት ነው ። ለሌላውም የተመረጠለት እስር ቤት ይሆናል ። እግዚአብሔር በመረጠው መንገድ ያስተምራል ። ተግባራዊ የሕይወት ትምህርት የሚገኘው ከእግዚአብሔር ዘንድ ብቻ ነው ። እግዚአብሔር በሕይወት እያሳለፈ የማስተማር ሥልጣን አለው ። እግዚአብሔር የሚያስተምርበት ዓላማ እርሱን እንድናውቀውና ከትዕቢት እስራት እንድንፈታ ነው ። የሰው ልጅ የሌለውን ነገር እንዳለው አድርጎ ማሰቡ ትዕቢት ሲሆን በእርግጥ አለኝ እንዲለው የተፈቀደለትን እግዚአብሔርን አለኝ አለማለቱ ደግሞ አለማመኑ ነው ። እግዚአብሔር የሚያስተምረው ለምስክር ወረቀት ሳይሆን ለሕይወት ለውጥ ነው ። በመስቀል ላይ የተሰቀሉት ሁለት ወንበዴዎችን ስናይ መከራ አንደኛውን እንዲያምን ሲያደርገው ሌላኛውን ደግሞ እንዲክድ አደረገው ። መከራ በራሱ አይለውጥም ። ትሑት ልብ ላላቸው ግን መከራ ሰማይን የሚያዩበት ሽንቁር/ቀዳዳ ነው ። ራሳችንን የምናውቀው ይመስለናል ፣ ግን አናውቀውም ። ሰዎችን የምናውቃቸው ይመስለናል ፣ ግን አናውቃቸውም ። ዓለሙን የምናውቀው ይመስለናል ፣ ግን አናውቀውም ። እየኖርንበት ያለውን ይህን ቀን የምናውቀው ይመስለናል ፣ ግን አናውቀውም ። ራሳችንን ከፍ አለ ስንል ሲዘቅጥብን እናገኘዋለን ። ሰዎች ገቡ ስንል ሲወጡ እንመለከታለን ። ዓለሙ ተሻሻለ ስንል ወደ ድንጋይ ዘመን ሲጓዝ እናስተውላለን ። ቀኑን በሰላም ጨረስኩት ስንል ምሽት ላይ ጣጣ ይዞ ይመጣብናል ። የዛሬው ስሜታችንም ፣ የሰዎች ተለዋዋጭነትም ፣ የዓለሙ መውረድም ፣ የቀኑ ክፋትም ሁሉም ያልፋሉ ። የማያልፍ አንድ ነገር ቢኖር እግዚአብሔር በዚህ ሁሉ ውስጥ የሚያስቀርልን ትምህርት ነው ። እርዳታ የሚያደርጉልን ሰዎች ስለመስጠታቸው እንጂ ስለ ትምህርታችን አይጨነቁም ። የሚያክሙን ሐኪሞች ስለሕክምናቸው እንጂ ስለ ትምህርታችን አይጨነቁም ። የሚዳኙን ዳኞች ስለ ሕጉ እንጂ ስለትምህርታችን አይጨነቁም ይሆናል ። እግዚአብሔር ግን በደረሰብን ነገር ሁሉ ትምህርቱ እንዳያመልጠን ስለ እኛ ያስባል ። እግዚአብሔር የማይረሳ ትምህርት ፣ በዓለት ላይ የተጻፈ ፊደል የሚቀርጽልን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንድናልፍ በመፍቀድም ነው ። አብርሃም ሁሉን አጥቶ ሁሉን አገኘ ። ሁሉን ለማግኘት ሁሉን ማጣት ያስፈልጋል ። አንድ የአገር መሪ ሲነግሥ የመኖሪያ ቤቱን ፣ ማኅበራዊ እሴቱን … ሁሉን ነገሩን ያጣና ሁሉም የእርሱ ይሆናል ። ሙሴ ከቤተ መንግሥት እየበላ ወደ ድሆች ይውጥ ነበር ። ከባዕድ ሰብስቦ ከዘመድ ጋር ለመብላት ይጨነቅ ነበር ። እግዚአብሔር ግን በልዑልነቱ ሳይሆን በእረኛነቱ ለታላቅ ራእይ አበቃው ። ነቢዩ ዳዊት በብዙ መንከራተት ውስጥ ፣ ነቢዩ ዳንኤል በስደት አገር ፣ ሠለስቱ ደቂቅ በነደ እሳት ፣ ሶስና በረበናት ክስ እግዚአብሔርን ይበልጥ አዩት ። ከዚህ በፊት የማናውቀውን የእግዚአብሔር ጣት የምናየው ጠመዝማዛ መንገድ ውስጥ በማለፍ ነው ። ራሳችን ብርቱ መስሎ ይሰማን ነበር ። ችግር ሲመጣ ግን ደካማ መሆናችንን አሳወቀን ። እግዚአብሔርን ያሳወቀን ችግር ፣ ቀጥሎ ራሳችንን አሳወቀን ። በሰላም ቀን ካንተ በፊት ያድርገኝ ይሉ የነበሩ ሰዎች ችግር ሲመጣ አላውቀውም ብለው እንደ ጴጥሮስ ሲክዱን ሰዎችን አወቅን ። ስንመነዝረው የማያልቅ የመሰለን ነገር ሲሟጠጥ ገንዘብ ሥር እንደሌለው ተረዳን ። አናታችን ላይ መንበራችሁን ሥሩ ሲሉን የነበሩት ሲያዋርዱን ዓለም ወረተኛ የወረት ቤት መሆኗ ተረዳን ። ጊዜ ብዙ ያስተምራል ። ጊዜ የተባለውም እግዚአብሔር የሚሰጠው ዘመንና ዕድል ነው ። በጊዜ ውስጥ የእግዚአብሔር ፍርድ ይታያል ። በጊዜ ውስጥ እታች ያለው ሲወጣ ፣ እላይ ያለው ሲወርድ መሐል ላይ ይገናኛል ። በጊዜ ውስጥ ቀዩ ሲጠቁር ፣ ጥቁሩ ሲቀላ ፣ ማሩ ሲመርር ፣ ወተቱ ሲጠቁት ይስተዋላል ። ጊዜ የእግዚአብሔር ባሪያ ነውና ጣል ሲለው ይጥላል ፣ አንሣ ሲለው ያነሣል ። ሰው ግን በዚህ ሁሉ ውስጥ ከመማር ወሬ ያሯሩጣል ። በእነ እገሌ የመሸ ዓለም በእርሱ የሚመሽ አይመስለውም ፣ ወዳጁንና ልጁን ቀብሮ እየተመለሰ እርሱ የሚሞት አይመስለውም ። ዛሬ በሌላው ይስቃል ፣ ነገ በእርሱ እንደሚሳቅበት አይረዳም ። በጊዜ ውስጥ ብርቱ ጉልበታችን ሲደክም ፣ የሰጠ እጃችን ሲነጥፍ ፣ ያማረ መልካችን ሲረግፍ ፣ የከበቡን ሠራዊቶች ሲበተኑ ፣ ያቀፉን እጆች ሲገፈትሩን እናያለን ። ባንኖር ይህን ሁሉ አንማርም ነበርና መኖር ደግ ነው ። ማጣት የማይለመድ የሰው ልጆች የእሳት ጅራፍ ነው ። ማጣት ቀና ያለውን አንገቱን ይሰብረዋል ። ማጣት የከበረውን ያዋርደዋል ። ማጣት ትላንት በሰጣቸው ሰዎች እንዲሰደብ ያደርገዋል ። ያጣ ሰው ጥበብ ቢናገር አበደ ይባላል ። እውቀት ቢናገር ምነው ዝም ባለ ይባላል ። ሰው የእውነት ሳይሆን የገንዘብ አገልጋይ በሆነበት ዓለም ፣ ያጡት ላይ ድንጋይ መጫን ይቀናዋል ። የመሸው ቀን ይነጋል ፣ የጠፋውም ሀብት ይመጣል ። ወዳጄ ሆይ በሚያልፍ ቀን ውስጥ የማያልፈውን እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ ። “ጊዜ የማይሽረው ቍስል የለም ። በችግር በመከራ ውስጥ የመትረፉ ነገር ያስፈራው ጸሎተኛ እንዲህ አለ፡- “አብም ያንተ ስም ነው ፣ ወልድም ያንተ ስም ነው ፣ መንፈስ ቅዱስም ያንተ ስም ነው ፤ ብጠራህ ብጠራህ አቤት አላልህም ምነው ።” እግዚአብሔር ሦስት ስም ፣ አንድ አምላክነት እንዳለው አወጀ ። ዳግመኛም ዘገየህብኝ ብሎ ጮኸ ። አቤት የሚል ታናሽ ነውና አቤት አላልህም ፣ አንተ ጌታ ነህ ብሎ መሰከረ ። አዎ በጊዜና በማጣት ውስጥ ያስተማረን እግዚአብሔር ስሙ የተቀደሰ ይሁን ! ያጣ ወዳጃችሁን እስቲ ዛሬ አስቡት ፣ አለሁ በሉት ።
Показати все...
👍 30 23🙏 23
“ወደማልመለስበት ሳልሄድ ዐርፍ ዘንድ ተወኝ ።” (መዝ. 38፡13) ።
Показати все...
32👍 3🙏 2
      ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር ሼር 🙏🙏 የአስተባባሪው ኮሜቴ መልእክት 🙏🙏🙏 ✍️✍️ አስቀድመን ከጅማሬ እስከ ፍፃሜ በነገር ሁሉ የረዳን አምላካችንን እናመሰግናለን።          በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገራት ላላችሁ በነገሮች ሁሉ ከጎናችን ለነበራችሁ ወገኖቻችን በሙሉ እግዚአብሔር ብድራቱን ይክፈላችሁ እያልን ....   የወንድማችንን የብንያም አበራን ኩላሊት ንቅለ ተከላ አስመልክቶ የተቋቋመው አስተባባሪ ኮሚቴ  ለአለፉት ሁለት ወር ከአስራ አምስት ቀናት ስናደርግ የነበረውን የገንዘብ ማሰባሰብ በይፋ አቁመን ወንድማችንን ዛሬ ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ ም ወደ ህንድ ሀገር ለህክምና ልከናል።        በቀጣይ ለምስጋና ለመገናኘት ያብቃን። = = = = += = = = = = + = = = + = = + = = =     
Показати все...
👍 23 16🙏 10
የባከነው ሰዓት                                                                                           ጥሪ አልባ ጉዞ ምሪት አልባ ሩጫ ራዕይ አልባ እቅድ ግብ አልባ ፍጥጫ ሠላም አልባ ህይወት ጎብጦ መንከራተት ክብር ያጣ ማንነት ንቀት የበዛበት ከጭንቀት ለመራቅ ከንቱ የዋልኩበት ቃሉ አይነበብ ድምጹ አይሰማኝ ዕውቀቴ ብዙ ነው ምንስ አዲስ ላገኝ? ባለኝ እውቀት መጠን መንፈሣዊ ሰው ነኝ፤ ክፉ በሚመስል ቦታ በመዋሌ አትበሉኝ ጠፍተሀል ሆነሀል አለሌ፤ በማለት ራሴን እንዲሁ ሸንግዬ በክፉ ሀሳቤ ውስጤን አታልዬ ክፉ ሆኖ ሳለ መልካሜ ነው ባልኩት ከንቱ ወዳጅነት የነገሰበት ቃሉ ቦታ አጥቶ የከረምኩበት ዝማሬ ተገፍቶ ዘፈን ከፍ ያለበት እልልታ ተውጦ ጩኸት የበዛበት ያ የያኔው ጉዞ ያ የያኔው መንገድ አሁን ጌታን ይዤ ቀጥ ብዬ ስሄድ የሰጠኝን ሰላም ፍቅሩን ስመለከት ያደረገልኝን መልካም ነገር ብዛት የሰጠኝን ሞገስ በብዙ በረከት የፍቅር እጁ ዳሶኝ ጥቅሜን ስመዝናት በዘፈን በስካር እንዲሁም በዝሙት አሁን ይቆጨኛል የባከነው ሰዓት
Показати все...
23👍 10🙏 2
‹‹የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን? ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ›› (፩ኛቆሮ.፫፥፲፮)።
Показати все...
23🙏 5👍 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
49👍 9🙏 4
የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤን ጥቂት እናስታውሰው /ክፍል 1 የክርስቶስ ትንሣኤ ምስጋና ይገባዋል ። ውዱስ ፣ ቅዱስ መባል ያስፈልገዋል ። ታላላቅ ነገሥታት ቢነሡ ከድሀ ሰፈር ነው ፣ ክርስቶስ ግን ከሞት መንደር ተነሥቷል ። በቤተ ልሔም እጅግ ዝቅ ያለው ፣ በትንሣኤው እጅግ የገነነው አንዱ ክርስቶስ ነው ። ታላላቅ ሰዎች ከፍ ቢሉ በምክንያቶች ነው ፣ ክርስቶስ ግን በኃይሉ የተነሣ ነው ። ተነሥተው የነበሩ ኃያላን በመውደቃቸው መተረቻ ሁነዋል ፣ የክርስቶስ ትንሣኤ ግን ዳግም ድካምና ሞት የለበትምና ሲደነቅ ይኖራል ። ሌሎች ቢነሡ ለበቀል ፣ ለጥፋት ነው ፣ የክርስቶስ ትንሣኤ ግን ቅዱስ ነው ። ገንዘብ ላጡ ገንዘብ የሰጡ ቸር ተብለው ይመሰገናሉ ፣ ሕይወት ላጡ ሕይወት የሰጠ ክርስቶስ ሲመለክ ይኖራል ። ሁሉ ቢነሡ እርሱን ሥልጣንና በኵር አድርገው ነው ። እርሱ ግን በራሱ ሥልጣን ተነሥቷል ፣ በኵረ ትንሣኤ ሲባል ይኖራል ። ሳይንስ ፍልስፍና ገና ያላለቀ ነውና አይታመንም ፣ የክርስቶስ ትንሣኤ ግን የተፈጸመ ነውና ሊያምኑት ይገባል ። ክርስቶስ ተነሣ ! ምእመን ሆይ ለበጎ ተግባር ተነሣ ! ማስታወሻ ማዕዶት፦ ማለት መሻገር ማለት ነው። ከትንሳኤ ማግስት ያለው ሰኞ ማዕዶት ይባላል። ይኸውም ክርስቶስ ከጨለማ ወደ ሚደነቅ  ብርሃን ያሸጋገረን ዕለት ነው።
Показати все...
8👍 6🙏 4
#ልብስህን ማን ወሰደው  ❖❖❖❖ •••በአንድ ወቅት አባ ሰራብዮን ወደ እስክንድርያ በሄደ ጊዜ በገበያም ስፍራ አንድ ከልብስ የተራቆተ ነዳይ አገኘ፡፡ ለራሱም "ይህ ደሃ ሰው ታርዞ መነኩሴ የተባልኩ እኔ እንዴት ለብሼ እታያለሁ? በእውነት ይህ 'ታርዤ አልብሳችሁኛልና' ብሎ የተናገረው ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አይደለምን? በዚህ ብርድ እየተሰቃየ እንዴት አልፌው እሄዳለኹ?" ብሎ ፈጥኖ ልብሱን በማውለቅ ይለብሰው ዘንድ ለዚያ ደሃ ሰጠው፡፡ ከዚያም በእጁ ያለውን መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ያዘ እርቃኑን በጎዳናው ዳር ተቀመጠ፡፡ እርሱን የሚያውቀው አንድ የከተማው ባለጠጋ ሰው አባ ሰራብዮን ባለበት ሥፍራ ሲያልፍ ተመልክቶት ወደ እርሱ ቀረበና ‹አባ ሰራብዮን ሆይ ልብስህን ማን ወሰደው?› ሲል ጠየቀው፡፡ ቅዱሱም በእጁ ወደ ያዘው መጽሐፍ ቅዱስ እየጠቆመ ‹ልብሴን የወሰደው ይህ ነው!› አለው፡፡ ያም ባለጠጋ አዲስ ልብስ ገዝቶ አለበሰው። ከዚህም በኋላ አባ ሰራብዮን ከእርሱ እንደ ተለየ በመንገድ ሲሄድ ዕዳውን መክፈል ባለመቻሉ እያንገላቱ ወደ ወኅኒ ቤት የሚወስዱትን አንድ ምስኪን ሰው ተመለከተ፡፡ እርሱም የያዘውን መጽሐፍ ቅዱስ ፈጥኖ በመሸጥ የዚያን ሰው ዕዳ ከፍሎ ነጻ አደረገው፡፡ ይህንንም አድርጎ ጉዞውን ሲጀምር እንደ ገና ሌላ የታረዘ ነዳይ ሲለምን ተመለከተ። አባ ሰራብዮንም እንደ ቀድሞው የለበሰውን ልብስ አውልቆ ለነዳዩ በመስጠት እርሱ እርቃኑን ወደ በአቱ ተመለሰ፡፡ ደቀ መዛሙርቱም መምህራቸውን እርቃኑን ባዩት ጊዜ ደንግጠው ‹መምህር! ልብስህ ወዴት አለ?› ብለው ጠየቁት፡፡ እርሱም ‹መጸወትኩት› አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም መልሰው ‹እኛን የምታጽናናበት መጽሐፍ ቅዱስህስ አባታችን?› ሲሉ ደግመው ጠየቁት፡፡ አባ ሰራብዮንም ‹በእጄ የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ ሁል ጊዜ ‹ሂድ ያለህን ሽጠህ ለድሆች ስጥ› ይለኛል፤ ስለዚህ ያለኝ እርሱ ነበር እርሱንም ሸጥኩት› አላቸው፡፡ ኢትዮጵያዊው ቄርሎስ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንደሚናገረው ምጽዋት የፊት መብራት ናት፡፡ አንድ ሰው በጨለማ ሲጓዝ ከኋላው መብራት ቢያበሩለትም እንኳ ከፊቱ የሚቀድመው የገዛ የአካሉ ጥላ እንቅፋት እየሆነበት ይጥለዋል፡፡ ወደ ፊት ያለውን መንገድ አጥርቶ እያየ ያለ ስጋት ለመሄድ እንዲችል የግድ የፊት መብራት ያስፈልገዋል፡፡ ጾም ፣ጸሎት እና ሌሎች መንፈሳዊ ትሩፋት እንደ ኋላ መብራት ናቸው፡፡ የፊት መብራት የተሰኘች ምጽዋት ካልታከለችባቸው እነዚህ ብቻቸውን ዋጋን አያሰጡንም፡፡ የምጽዋትን ታላቅነት ልንረዳ ይገባል፡፡ ዓለም ሁሉ ከወደቀበት የሕግ እርግማን የዳነው ቸር እረኛ በሆነው በመድኃኔ ዓለም በአካሉ ምጽዋትነት (በሥጋው በደሙ መሰጠት) ነውና!!!
Показати все...
18🙏 13👍 12