uk
Feedback
😘❤️ፍቅር እና ፍልስፍና

😘❤️ፍቅር እና ፍልስፍና

Відкрити в Telegram

አርት ነክ የሆኑ ጉዳዮችን ግጥም እጥር ምጥን ያሉ አጫጭር ፁሑፎች ስለ ደራሲያ እና ፈላስፋዋች

Показати більше
4 417
Підписники
+1024 години
+457 днів
+15530 день
Архів дописів
በግጥም ተውበው በዘነጡ ቃላት አስሰው ገርበው ትዝታን ሲያነቋት እንባ ተናነቀኝ እሄድበት ጠፋኝ ድሮም ትዝታ ሲነቃ ከምሽጉ ከርሞ እንዲው አይመለስም የሰው ግምባር ስሞ 121

"የድሮ ደብተሬን ስገለጥ፣ 'ፍቅር እያደር ወጣት ይሆናል እንጂ እንደ ሰው አያረጅም' የሚል ጽሁፍ አገኘሁ። የኔስ ፍቅር የት ደረሰ? እንደ እድሜ ጠገብ አዛውንት መቋሚያ ተደግፎ ይሆን ወይ? 'ገና አልሞትኩም' እያለ ለማትረፍ የሚታገል... አንዳንዴ በውስጥ ያለን ስሜት አለመናገር፣ ከልብ የማይጠፋ የዘወትር ጠባሳ ሆኖ ይቀራል። እናንተስ? የውስጣቹን ሳትናገሩ ግዜ የሸበለለባቹ ነገር አለ?" 121

ሬድዮ አዳምጬ ማቅባቸው ቀናቶች በጣት የሚቆጠሩ ትንሽ ናችው ዛሬ ግን መክፈት ፈለኩ መስማት ፈለኩ የሆነ ምስሉን የማላየው ድምጽ ፈለኩ እሱነቱን በለበሰው ጨርቅ ሳይሆን በንግግሩ መመዝን ፈለኩ አንዳንዴ ምናለ የዘመኑ social mediaዋች በድምጽ በሆኑ እላለሁ ብቻ ከፈትኩት አንድ ሰው በደስታ ተሞልቶ ዛሬ ታሪካዊ ቀን ነው ሲል ይደመጣል ታሪካዊ ቀን ማለት የማይረሳ በጥሩ ም በመጥፎም የሚታወስ አደል እንዲ ካልን ስንቱ በልቡ ከትቦ የያዘው ታሪካዊ ቀን አለው የማይረሳው. . . የማይዘክረው. . . የማይረግመው. . . ሊፍቀው ቢሞክር የማይፋቅ በልቡ የተነቀሰው ጥቁቁር የጠለሹ የህይወቱ ቅንጥብጣቢዋች ሆነው ለመንቀል ያዳገቱ ብቻ እግዜር መቶ ለሁሉም ብእር ወርቀት የታሪካዊ ቀናቹን ገጠመኝ አስፍሩ ቢል ወረቀቱ ይበቃቸዋል? እንጃ የኔዋ ታሪካዊ ቀን ግን ታሪከ ብዙ ናት ቢጨልፏት የማታልቅ ውቅያኖስ የናተስ? ስንት ታሪካዊ ቀን . . . አላቹ ? አኮብ(121)

ሬድዮ አዳምጬ ማቅባቸው ቀናቶች በጣት የሚቆጠሩ ትንሽ ናችው ዛሬ ግን መክፈት ፈለኩ መስማት ፈለኩ የሆነ ምስሉን የማላየው ድምጽ ፈለኩ እሱነቱን በለበሰው ጨርቅ ሳይሆን በንግግሩ መመዝን ፈለኩ አንዳንዴ ምናለ የዘመኑ social mediaዋች በድምጽ በሆኑ እላለሁ ብቻ ከፈትኩት አንድ ሰው በደስታ ተሞልቶ ዛሬ ታሪካዊ ቀን ነው ሲል ይደመጣል ታሪካዊ ቀን ማለት የማይረሳ በጥሩ ም በመጥፎም የሚታወስ አደል እንዲ ካልን ስንቱ በልቡ ከትቦ የያዘው ታሪካዊ ቀን አለው የማይረሳው. . . የማይዘክረው. . . የማይረግመው. . . ሊፍቀው ቢሞክር የማይፋቅ በልቡ የተነቀሰው ጥቁቁር የጠለሹ የህይወቱ ቅንጥብጣቢዋች ሆነው ለመንቀል ያዳገቱ ብቻ እግዜር መቶ ለሁሉም ብእር ወርቀት የታሪካዊ ቀናቹን ገጠመኝ አስፍሩ ቢል ወረቀቱ ይበቃቸዋል? እንጃ የኔዋ ታሪካዊ ቀን ግን ታሪከ ብዙ ናት ቢጨልፏት የማታልቅ ውቅያኖስ የናተስ? ስንት ታሪካዊ ቀን . . . አላቹ ?

🌙 ኢድ አል-አድሃ ሙባረክ ለመላው የሙስሊም ወንድሞቻችን ና እህቶቻችን መልካም እና የተባረከ 1447ኛ ኢድ አል-አድሃ ቀን ይሁንላችሁ!

የብቸኝነት ካባ ሰውነቴን ሲጫጫነኝ ተስቼ ወጣው ሰማዩ ሰዋችኝ በጎርናና ድምጹ ካሁን ካሁን ዘነብኩ እያለ ማስፈራራት ጀምሯል. . . . በዚ መሀል ሰው መራራጥ ጀመረ የዛኔ ወድሃለው ያለቺኝ ልጅ በፍጥነት ብስክሌት ስነዳ አየዋት በዛው ቅጽበት ትዝታዎቼ መጣን መጣን ማለት ጀመሩ ለመጀመሪያ ግዜ ወድሀለው ያለቺኝ ቀን የሳልኳት ቀን ምናምን ምናምን ትርኪሚርኪ ትዝታ . . . ግራ ተጋባው የተዳፈነው ፍቅሬ አፈር ልሶ ሲነሳ ይታወቀኛል ሰው እንዴት የላፈ ታሪኩን መርሳት ባይችል መተው ያቅተዋል እላለው ዝም እልና ደግሞ "የተፋቀረ ሁሉ አብሮ አይዘልቅም" በሚለው ቢሂል እጽናናለው ትንሽ ጋብ ሲልልኝ ደሞ ምን አልባት ትወደኝ ይሆናል ምን አልባት እረስታኝ ይሆናል ምን አልባት ታቂዋለሽ ብትባል አላቀውም ብላ ትክድ ይሆናል እንዴት ሰው ከ8 አመት ቢፊት ስላሳለፈው ግይሰጠዋል እላለው ብቻ . . . አንዳድ ፍቅር ልተውህ ሲሉት አተን ለማ ትቼ ሚል የሚል ይመስለኛል 121

ፍቅር ግን ልክ እንደማያድግ ሰው ዘወትር መሸንገያ እና ማባበያ ሚፈልግ ህጻን ይሁን? . . . . ብቻ ያማል እየተዋደዱ መለያየት ያማል . . . ያላንቺ አልኖርም ያላንተ አልኖርም እየተባባሉ መለያተት ያማል . . . ሆነው እንዳለ ሆኖ ማፍቀር ምን አልባት ለሁሉ አልተፈቀደ ይሆናል 121

ስልኬን እዘጋለሁ ፤ እስልኬን እከፍታለሁ ከጣፍሽልኝ ብዬ ፤ አስሬ አፈጣለሁ አይኔ እስኪቀላ ፤አስኪጠፋኝ መላ ስጠብቅ ቃልሽን ፤ የዋላ የሀዋላ በዋዛ ፈዛዛ ፤ ዘመኑ ነጎደ ነፍሴ በቃልሽ ጥም ፤ ላይሽር ነደደ በትዝታሽ እቶን አቅሉን እየሳተ ዛሬም ስፅፍልሽ አንድም አልታከተ ​ዳሩ ... ኩራት በሚሉት ፤ ቃል ልቦናሽ ታውሮ አመጤፍ አትቆጥሪ ፤ የውጤን ሮሮ ቢገባሽ ኖሮማ አውቀሽ ቢሆንማ ትይኝ አልነበረ ! መጣፍ አይኑ ይጥፋ ይጣ ኢሚንት ተስፋ እኔስ እመጣለሁ ካለህበት ስፍራ እራስህን ጠብቅ የኔ ውድ አደራ ምናምን... ምናምን... ብቻ... የአንደበትሽን ዜማ ፤ ስሻልሽ ዳክሬ ዝምታሽ ገደለኝ ፤ ተዘረርኩኝ ዛሬ። 121

በወሬ መሀል እንደቀልድ በዋዛ ፈዛዛ ስምሽን ሲያነሱ ድንገት ነበር ሳቄ ከገፄ ላይ የተራገፈው... ድንገት ነበር ጨዋታ የጠፋብኝ... ድንገት ነበር በዝምታ ባህር ውስጥ የሰጠምኩት... ብቻ ከምሸሸው እኔነቴ ጋር ነው ያላተሙኝ.. አላወቁትም እንጂ ማባርያ ከሌለው ዶፍ ትዝታ ውስጥ ነው የዘፈቁኝ... "!አንዳንዴ የተዳፈነ ትዝታ ሰው ፊት ሲነቃ አንገት ያስደፋል '' 121

ፍቅር አልባው እኔነቴ አለት ልቡ ማንነቴ እንዳልበር ድሮ ገና ስትመጪ አልል ቀና ይሰማኛል እፍረት ቢጤ እደነካው እልፍ ቃጤ ቀናት አልፎ ቀን ሲተካ አለት ልቤ ፈርሷል ለካ 121

እውነት ነው መለያየት ያማል ያቆስላል ብቻ አንዳንድ ግዜ በወጉ እራሱ መለያየት ይናፍቃል አለ አደል ብዙ ግዜ ምናለ ከዚ በዋላ እንዳታወራኝ... ምናም ብትለኝ ብዬ አስቤ አቃለው.... ብቻ ስንብት ከሌለው መለያየት ይጠብቃቹ😊

አንዲት እኳ ቀን የሌለው    ለመፈገግ ለመጫወት ካላደለው መዳፍ ጥሎሽ ብትከፊ         ከእግዜሩ ደጅ ብታኮርፊ ፈዋሽ የለው አንዳች መድን       ከትዝታሽ እልፍ እርቆ ለሚመንን 121

ከፈገግታህና ከኔ የቱን ትመርጣለህ አለቺኝ አንቺን አልኳት.. እንዴ ለምን አለቺኝ ምክንያቱም ያለአቺ መሳቅ ስለማልችል አልኳት..

ትግስተኛ ሰው አደለሁም ግን እስካሁን የአንቺን ምላሾች እየተጠበኩ ነው... እመኚኝ አንቺ ለኔ መተኪያ የሌለው ልዩ ሰው ነሽ

photo content

የዚህች አለም የአሸናፊነት ሚስጢር ሴት ልጅ ጋር ብቻ ነው!! የትኛው ሀብታም ነው ፣ የትኛው ባለ ስልጣን፣ የትኛው ባለ ዝና ፣ የትኛው ጀግና፣ የትኛው ተዋጊ ነው በሴት ልጅ ፍቅር ያልተሸነፈ? ወንድ ልጅን ያለ ጦር መሳሪያ መማረክ የምትችል ፍጥረት ሴተ ልጅ ብቻ ነች!! ...Masayoshi Kobayashi ይባላል ታዋቂ የጃፖናዊ ቢሊየነር ነው...የስራ ሰው እንደሆነ አለም ይመሰክርለታል...ለጃፖናዊያን ህብረተሰብ ለሚሊዮኖች የስራ እድልም ፈጥሯል እየፈጠረም ይገኛል። ፍቅር ግን ጅ'ል ያረጋል መሰለኝ Masayoshi Kobayashi ከአንዲት ቀበጥ ወጣት ፍቅር ያዘው...ልጅቷ በጣም ቀበጥ ከመሆኖ የተነሳ በቀን ውስጥ የመኪና ውድድር የሚካሄድበት ቦታ ሄዳ መኪኖች ሲወዳደሩ ካላየች ቀኑን ሙሉ ይደብራታል ዘመድ እንደሞ''ተበት ሰው ቤቷን ዘግታ ስቅስቅ ብላ ታለቅሳለች የመኪና ውድድር እንኳን ባይኖር ለመኪና ውድድር ልምምድ ሲያረጉ ማየት ትወዳለች😂😂 ጃፖናዊው ባለ ሀብት እሷን ከሚያገኝበት ቀን የማያገኝበት ቀን በለጠበት ለእሷ ብሎ አንድ ሁለት ቀን የመኪና ውድድር የሚካሄድበት ቦታ ላይ ተገኝቶ ነበር ነገር ግን ሰዎቹ እሱን ሲያዩ የሰጡት ከፍ ያለ ቦታ ነፃነቱን ገደበውና አልተመቸውም ስለዚህ መሄድ አቆመ። ፍቅረኛውን ደሞ አትሂጂ ቢላት ተነጫንጫ አኩርፋ በሯን ዘግታ እያለቀሰችበት ተቸገረ....ተጨነቀ በመጨረሻም አንድ ሀሳብ አመጣ ከቅርብ ሰዎቹ ጋርም ተነጋግሮ ተገበረው ቤቱ ግቢ ውስጥ 200ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር አውጥቶ መኪና መወዳደሪያ ትራክ ሰራና ፍቅረኛውን ሰርፕራይዝ አረጋት😂😂😂 እውነትም ሀብታም ቀልብ የለውም የሚባለው እውነት ነው አስቡት 200ሚሊየን ዶላር አውጥቶ ቤቱን አፈራርሶ የመኪና መወዳደሪያ ሰርቶላት ከፍቅረኛው ጋር ቢለያይ ከብሩም፣ ከቤቱም፣ ከፍቅረኛዎም ሳይሆን መሀል ላይ ቀረ ማለት አይደል😂😂😂 አረ እባካችሁ ወንዶች ፍቅር ሲ ይዘን የምናረገውን እንወቅ ስሜታዊ አንሁን😂😂😂😂😂

photo content

photo content

photo content

ወጣቱ አንድ አዛውንት አግኝቶ መጠየቅ ጀመረ: "አስታወስከኝ?" አዛውንቱ "አይ" አለ። ወጣቱ "ያንተ ተማሪ ነበርኩኝ" አለው። መምህሩ አዛውንትም "አሁን ከምን ደረስክ?" ሲል ጠየቀው። ወጣቱም "መምህር ሆንኩኝ" ሲል መለሰለት። "ዋው! ደስ ይላል። እንደ እኔ?" "አዎን! በእርግጥ መምህር የሆንኩት አንተን አርዕያ አድርጌ ነው" አዛውንቱም ወጣቱ መቼ መምህር ለመሆን እንደወሰነ ለማወቅ ስለጓጓ ጠየቀው። ወጣቱም የሚከተለው አጭር ታሪክ ያጫውተው ጀመር። "አንድ ዕለት ጓደኛዬ አሪፍ ሰዓት ይዞ ትምህርት ቤት መጣ። በጣም ስለወደድኳት መውሰድ ፈለኩኝ እና ከኪሱ ወስድኳት። ብዙም ሳይዘገይ ጓደኛዬ ሰአቱ እንደተወሰደበት ስላወቀ ወዲያው ለመምህር አመለከተ። መምህሩም አንተ ነበርክ። "እናም አንተ ለክፍሉ ተማሪዎች 'ይሄ ልጅ ዛሬ ሰአቱ ተሰዘርፎበታል። የሰረቃችሁበት በቶሎ መልሱለት' ስትል ተናገርክ። መመለስ ስላልፈለኩኝ ዝም አልኩኝ። እናም ማንም የሚወጣ ሰው ሲጠፋ በሩን ዘጋኸውና ተነስተን ክብ እንድንሰራ አሳሰብከን። "ሰአቱ እስኪገኝ አንድ በአንድ ኪሳችንን ልትፈትሽ እንደሆነ፣ ነገር ግን ከዛ በፊት አይናችንን መጨፈን እንደሚገባን ነገርከን። "እንዳዘዝከንም አደረግን። "ከአንዱ ኪስ ወደሌላው መፈተሽክ ጀመርክ። የኔም ኪስ ስትበረብር ጊዜ ሰአቱን አገኝተኸው ወሰድክ። ዳሩ ግን መፈተሽህን አላቆምክም ነበር። ስትጨርስም 'አይናችንን እንድንከፍት እና ሰአቱም እንደተገኘ' ነገርከን። "ቢሆንም ግን አልጠቆምክብኝም ወይም አሳልፈህ አልሰጠኸኝም ነበር። ሌባው ማን እንደነበር ፈፅሞ አልተናገርክም። ወይም ወደ ቢሮ ጠርተኸኝም ምክር ቢጤም አልሰጠኸኝም። በዛች ቀን ክብሬን ጠበክልኝ። የሕይወቴ በጣም አሳፋሪ ቀኔም ነበር። ቢሆንም ግን ዕለቱ ሌባ፣ መጥፎ ሰው ላለመሆን ቃል የገባሁበትም ነበር። "በሚገባ ነበር መልዕክቱን የተረዳሁት። እውነተኛ መምህር ምን ማድረግ እንደሚገባው ገብቶኛል። አመሰግንሃለሁ። ይሄንን አጋጣሚ ታስታውሰዋለህ?" አዛውንቱ መምህርም "እንዴታ አስታውሰዋለሁ እንጂ! የሁላችሁንም ኪስ የፈተሽኩበት እንዴት ይዘነጋኛል? ነገር ግን አንተን አላስታውስህም ምክንያቱም እኔም አይኔን ጨፍኜ ነበር ስፈትሻችሁ የነበረው። አየህ! እንዲህ ነው፤ መምህርነት። ሌላውን እስከጥግ ለመረዳት መሞከር፤ በጭፍንነት ከመፈረጅ መቆጠብ። እንዲህ ነው ረቡኒነት፤ የምታስተምረውን በጥልቀት ማወቅ፣ መውደድ፣ መኖር። ስታስተምር በግብዝብነት፣ በእብሪት፣ በመታበይ፣ በችኩልነት አይደለም፤ በትህትና ነው፤ በመተናነስ ነው፤ በትዕግስት ነው፣ በማክበር ነው። ይሄ ነው፤ የአዛውንቱ መምህር ትልቅነት… ማስተዋል… ጥበብ፤ ሰውኛውነቱ ተፅኖ እንዳያደርግብት ለመጠንቀቅ ሲል አይኑን ሸፈነ። ባይሆን ግን ሌባውን ተማሪ ስለእውነት፣ ስለመርህ፣ ስለፍትህ ሲል አሳልፎ እንዲሰጠው ይፈትነው፣ ይገፋፋው ነበር።