cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ኦርቶዶክሳዊ 📖📖📖 መጻሕፍት ✝️✝️✝️

በዚህ channel ውስጥ መንፈሳዊ መጻሕፍትንና የየዕለቱን ስንክሳር ያገኛሉ።

Більше
Рекламні дописи
1 102
Підписники
Немає даних24 години
+147 днів
+7130 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

17/09/2016                        የዕለቱ የወንጌል ክፍል                           ሉቃስ 19:11-28     እነርሱም ይህን ሲሰሙ፥ ወደ ኢየሩሳሌም መቅረቡ ስለ ሆነ የእግዚአብሔርም መንግሥት ፈጥኖ ሊገለጥ እንዳለው ስለ መሰላቸው ምሳሌ ጭምር ተናገረ።ስለዚህም እንዲህ አላቸው፦ “አንድ መኰንን ለራሱ መንግሥትን ይዞ ሊመለሰ ወደ ሩቅ አገር ሄደ። አሥር ባሪያዎችንም ጠርቶ አሥር ምናን ሰጣቸውና፦ ‘እስክመጣ ድረስ ነግዱ፡’ አላቸው። የአገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ነበርና፦ ‘ይህ በላያችን ሊነግሥ አንወድም፡’ ብለው በኋላው መልክተኞችን ላኩ። መንግሥትንም ይዞ በተመለሰ ጊዜ፥ ገንዘብ የሰጣቸውን እነዚህን ባሪያዎች ነግደው ምን ያህል እንዳተረፉ ያውቅ ዘንድ እንዲጠሩለት አዘዘ። የፊተኛውም ደርሶ፦ ‘ጌታ ሆይ፥ ምናንህ አሥር ምናን አተረፈ፡’ አለው። እርሱም፦ ‘መልካም፥ አንተ በጎ ባሪያ፥ በጥቂት የታመንህ ስለ ሆንህ በአሥር ከተማዎች ላይ ሥልጣን ይሁንልህ፡’ አለው። ሁለተኛውም መጥቶ፦ ‘ጌታ ሆይ፥ ምናንህ አምስት ምናን አተረፈ፡’ አለው። ይህንም ደግሞ፦ ‘አንተም በአምስት ከተማዎች ላይ ሁን፡’ አለው። ሌላውም መጥቶ፦ ‘ጌታ ሆይ፥ በጨርቅ ጠቅልዬ የጠበቅኋት ምናንህ እነሆ፤ ፈርቼሃለሁና፥ ጨካኝ ሰው ስለ ሆንህ፤ ያላኖርኸውን ትወስዳለህ ያልዘራኸውንም ታጭዳለህ፡’ አለው። እርሱም፦ ‘አንተ ክፉ ባሪያ፥ አፍህ በተናገረው እፈርድብሃለሁ። እኔ ያላኖርሁትን የምወስድና ያልዘራሁትን የማጭድ ጨካኝ ሰው እንደ ሆንሁ አወቅህ፤ ምን ነው ገንዘቤን ለለዋጮች አደራ ያልሰጠኸው? እኔም መጥቼ ከትርፉ ጋር እወስደው ነበር፡’ አለው። በዚያም ቆመው የነበሩትን፦ ‘ምናኑን ውሰዱበት አሥሩ ምናን ላለውም ስጡት፡’ አላቸው። እነርሱም፦ ‘ጌታ ሆይ፥ አሥር ምናን አለው፡’ አሉት። ‘እላችኋለሁ፥ ላለው ሁሉ ይሰጠዋል፥ ከሌለው ግን ያው ያለው ስንኳ ይወሰድበታል። ነገር ግን እነዚያን በላያቸው ልነግሥ ያልወደዱትን ጠላቶቼን ወደዚህ አምጡአቸው በፊቴም እረዱአቸው’።”             የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ መልእክት                      1 ጢሞቴዎስ 3:1-8     ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል የሚለው ቃል የታመነ ነው። እንግዲህ ኤጲስ ቆጶስ እንዲህ ሊሆን ይገባዋል፤ የማይነቀፍ፥ የአንዲት ሚስት ባል፥ ልከኛ፥ ራሱን የሚገዛ፥ እንደሚገባው የሚሰራ፥ እንግዳ ተቀባይ፥ ለማስተማር የሚበቃ፥ የማይሰክር፥ የማይጨቃጨቅ ነገር ግን ገር የሆነ፥ የማይከራከር፥ ገንዘብን የማይወድ፥ ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር፤ ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል? በትዕቢት ተነፍቶ በዲያቢሎስ ፍርድ እንዳይወድቅ፥ አዲስ ክርስቲያን አይሁን። በዲያቢሎስ ነቀፋና ወጥመድም እንዳይወድቅ፥ በውጭ ካሉት ሰዎች ደግሞ መልካም ምስክር ሊኖረው ይገባዋል።                   1 ጴጥሮስ 5:1-ፍጻሜ       እንግዲህ እኔ፥ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤ በእናንተ ዘንድ ያለውን የእግዚአብሔርን መንጋ ጠብቁ፤ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ በውድ እንጂ በግድ ሳይሆን፥ በበጎ ፈቃድ እንጂ መጥፎውን ረብ በመመኘት ሳይሆን ጐብኙት፤ ለመንጋው ምሳሌ ሁኑ እንጂ ማኅበሮቻችሁን በኃይል አትግዙ፤ የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ። እንዲሁም፥ ጐበዞች ሆይ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል። እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ፤ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። በመጠን ኑሩ ንቁም፥ ባላጋራችሁ ዲያብሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሣ አንበሳ ይዞራልና፤ በዓለም ያሉት ወንድሞቻችሁ ያን መከራ በሙሉ እንዲቀበሉ እያወቃችሁ በእምነት ጸንታችሁ ተቃወሙት። በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁምል ያበረታችሁማል። ለእርሱ ክብርና ኃይል እስከዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን። እየመከርኋችሁና የምትቆሙባት ጸጋ እውነትኛ የእግዚአብሔር ጸጋ እንድትሆን እየመሰከርሁላችሁ፥ የታመነ ወንድም እንደ ሆነ በቈጠርሁት በስልዋኖስ እጅ በአጭሩ ጽፌላችኋለሁ። ከእናንተ ጋር ተመርጣ በባቢሎን ያለች ቤተ ክርስቲያን ልጄም ማርቆስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል። በፍቅር አሳሳም እርስ በርሳችሁ ሰላምታ ተሰጣጡ። በክርስቶስ ላላችሁ ለሁላችሁ ሰላም ይሁን። አሜን...                 ሐዋ. ሥራ 20:28-31     በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ። “ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ፥ ደቀ መዛሙርትንም ወደ ኋላቸው ይስቡ ዘንድ ጠማማ ነገርን የሚናገሩ ሰዎች በመካከላችሁ እንዲነሡ እኔ አውቃለሁ።                        ምስባክ                     መዝሙር 83:6 እስመ መምህረ ህግ ይሁብ በረከተ ወየኃውር እምኃይል ውስተ ኃይል ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን                ትርጉም የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል @religious_books_lover
Показати все...
👏 1
📌 ግንቦት 17 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ) ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ (ዘደሴተ ቆዽሮስ) 2.ቅዱስ ኢላርዮን ገዳማዊ 3.አባ ሉክያኖስ ጻድቅ 4.ቅዱስ ፊላታዎስ ክርስቲያናዊ 📌 ወርኀዊ በዓላት 1.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት (ቀዳሜ ሰማዕት) 2.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ ዘብዴዎስ) 3.ቅዱሳን አበው መክሲሞስና ዱማቴዎስ 4.አባ ገሪማ ዘመደራ 5.አባ ዸላሞን ፈላሢ 6.አባ ለትጹን የዋህ ✍️"የሚታገል ሁሉ በሁሉ ነገር ይታገሣል እነርሱስ የሚጠፋውንና የሚያልፈውን የምስጋናቸውን ዋጋ አክሊል ሊያገኙ ያገኙ ዘንድ ይበረታሉ እኛ ግን የማያልፈውን አክሊል ለማግኘት እንታገሣለን፤ እኔ ያለ አሳብ እንደሚሮጥ ሁሉ እንዲሁ አልሮጥም፤ ነፋስን እንደሚጐስም ሁሉ እንዲሁ አልጋደልም፤ ነገር ግን ለሌላ ሳስተምር እኔ ለራሴ የተናቅሁ እንዳልሆን ሰውነቴን አስጨንቃታለሁ ሥጋዬንም አስገዛዋለሁ" 📖1ኛ ቆሮ 9፥25 ዘአቅረብኩ ማኅሌተ አዘኪርየ አእላፈ። እምእለ ተጸምዱከ ዘልፈ። ለለአነብብ ተወከፍ ዘንዴትየ መጽሐፈ። እንተ ረሰይከ እግዚኦ ጸሪቀ መበለት ውኩፈ። እምእለ አብኡ ብዑላን ዘተርፈ። ነቢያት ቅዱሳን ወሐዋርያት ሰባኪያን። ሰማዕት ወጻድቃን ወመላእክት ትጉሃን። ደናግል ዓዲ ወመነኰሳት ኄራን። ባርኩ ባርኮ ጉባኤ ዛቲ መካን። እስከ አረጋዊ ልሒቅ ወንኡስ ሕፃን። ለዘጸሐፎ በክርታስ ወለዘአጽሐፎ እንዘ ይደርስ። ለዘአንበቦ ወለዘተርጐሞ በልሳን ሐዲስ። ወለዘሰምዐ ቃሎ በዕዝነ መንፈስ። በጸሎተ እሙ ማርያም ዐራቂተ ኵሉ እምባእስ። ኅቡረ ይምሐረነ ኢየሱስ ክርስቶስ።
Показати все...

👍 3
❖"ቅዱስ ኤጲፋንዮስም ፈጽሞ እያዘነ ከእርሷ ዘንድ ወጣ፤ ምን እንደሚአደርግም ያስብና ይጨነቅ ነበር፤ የንግሥት ባሮቿ ግን እነሆ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ዮሐንስ አፈወርቅን ከሹመቱ ሻረው እያሉ በቊስጥንጥንያ ከተማ በሐሰት አወሩ፤ ቅዱስ ዮሐንስም ይህን ወሬ በሰማ ጊዜ ወደ ኤጲፋንዮስ እንዲህ ሲል ላከ፤ ለምን ያለ ፍርድ በእኔ ላይ ይህን አደረግህ አንተ ወደ መንበረ ሢመትህ እንደማትደርስ ዕወቅ፤ ኤጲፋንዮስም ለመልእክቱ መልስ እንዲህ ሲል ጻፈ፤ ስለ አንተ ምንም ምን የጻፍኩትና ከንግሥት ጋራ የተስማማሁት ነገር የለም አንተም ከስደት እንደማትመለስ ዕወቅ። ❖"ከዚህ በኋላም ወደ መንበረ ሢመቱ ሊሔድ ሽቶ ከቊስጥንጥንያ ወጥቶ በመርከብ ተሳፈረ እግዚአብሔርም የዮሐንስን ጽድቅ ሊገልጽ ከመንበረ ሢመቱ ሳይደርስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ በመርከብ ውስጥ አረፈ፤ እንዲሁም የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ክብር እንዲገለጥ ቅዱስ ዮሐንስ በተሰደደበት አረፈ፤ የከበረ ኤጲፋንዮስም የሚያርፍበትን ጊዜ አውቆ ተነሥቶ ጸለየ፤ ለደቀ መዛሙርቱም እነርሱ ኤጲስቆጶሳት እንዲሆኑ ነገራቸው በሰላምታም ተሰናብቷቸው ከዚህ በኋላ በሰላም አረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።                 አርኬ ✍️ሰላም ዕብል በቃለ ስብሐት ወይባቤ። ለከናፍሪሁ ሙኀዘ ከርቤ። ኤጲፋንዮስ ከዊኖ በመንፈስ ቅዱስ ነባቤ። እም አመ ረሰይኩ አስኬማ መላእክት ግልባቤ። ውስተ ልብየ እኪተ ኢያኅደርኩ ይቤ። ✍️ሰላም ለአባ ሉክያኖስ ኤጲፋንዮስ ዘዴገኖ። ሕገ አበዊሁ መኒኖ። ሶበ ነጸረ ገሀደ እምኀበ ልዑል አምላከ አድኅኖ። ልብሰ ክብር ፀዐዳ እንዘ ላዕሌሁ ይትፌኖ። ህየንተ ወሀበ ለዕሩቅ ክዳኖ። 📜 አቡነ ገብረ ሚካኤል ❖ እኚህ ኢትዮጵያዊ ጻድቅ በታላቅ ተጋድሎአቸው ይታወቃሉ፤ የትውልድ ሀገራቸው ትግራይ ገርዓልታ ነው፡፡ ❖ ከገርዓልታ በደቡባዊ አቅጣጫ የሚገኘው ይህ የአቡነ ገብረ ሚካኤል አስደናቂ ገዳም እንደ ደብረ ዳሞ በገመድ ብቻ ከሚወጣው ከአቡነ ገብረ ናዝራዊ ገዳም ጋር የሚዋሰን ሲሆን ገዳሙ ለመድረስ የመኪናውን መንገድ ከጨረሱ በኋላ በእግር አንድ ሰዓት ይፈጃል፡፡ ❖ በገዳሙ ውስጥ ጻድቁ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ብዙ ቅርሶች ይገኛሉ፤ የጌታችን የሾህ አክሊል ምሳሌ የሆነውና ጻድቁ ያደርጉት የነበረው የድንጋይ ቆብ፣ መቋሚያቸው፣ የእጅ መስቀላቸውና መጻሕፍቶቻቸው ይገኛሉ፡፡ ❖ ሌላው አስደናቂ ነገር ሀገሩ በረሃ ቢሆንም ጻድቁ ከኢየሩሳሌም ዮርዳኖስ ያመጡትና ዋሻው ውስጥ ጉድጓድ ቆፍረው ያጠራቀሙትን ውኃ መነኮሳቱ ሁልጊዜ የሚጠቀሙበት ቢሆንም ውኃው ግን ከዓመት እስከ ዓመት መጠኑ አይቀንስም፡፡ ❖ ሊቀ ብርሃናት መርቆርዎስ አረጋ የቅዱሳን ታሪክና ኢትዮጵያውያን ቅዱሳን በሚሉት ሁለት መጽሐፎቻቸው ላይ እንደጠቀሱት በገዳሙ ውስጥ ከዓመት እስከ ዓመት የምትበራው አንዲት ጧፍ ብቻ ናት፤ ጧፏ ነዳ የማታልቅ ስትሆን አለቀች ትቀየር ሳትባል አስገራሚ በሆነ ተአምር ከዓመት እስከ ዓመት ትበራለች፡፡ የአቡነ ገብረ ሚካኤል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፤ በጸሎታቸው ይማረን።
Показати все...

👏 3
📖 ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት ፲፯ አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥራ ሰባት በዚች ቀን የከበረ አባት ታላቅና የተመሰገነ የቆጵሮስ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ አረፈ። 📜 ቅዱስ ኤዺፋንዮስ ሊቅ ❖ ይህም ቅዱስ ከቤተ ገብርኤል ዐፀድ አቅራቢያ ነው ወላጆቹም በኦሪት ሕግ የጸኑ አይሁድ ናቸው፤ እነርሱም ድኆች ናቸው አባቱም ገባር ስለ ነበረ ይህን ቅዱስና አንዲት እኅቱን ሳያሳድጋቸው ሞተ እርሱም አንድ ክፉ አህያ ነበረውና የተወላቸው እርሱን ነው እናታቸውም የኦሪትን ትምህርት በማስተማር አሳደገቻቸው። ❖ እናቱም አህያውን እንዲሸጠውና ከእርሱም እንዲያርፍ በሺያጩም እንዲረዳ ኤጲፋንዮስን መከረችው፤ ሊሸጠውም ከአህያው ጋራ ሲጓዝ አንድ ክርስቲያን ጻድቅ ሰው ስሙ ፊላታዎስ የሚባል ተገናኘው ያንን አህያ ሊገዛ ወዶ ከኤጲፋንዮስ ጋራ ቁሞ ሲነጋገር ያን ጊዜ አህያው ኤጲፋንዮስን ኵላሊቱን ረገጠው በምድር ላይ ወድቆ ለመሞት ደረሰ። ❖ አባ ፊላታዎስም በመስቀል ምልክት ኵላሊቱ ላይ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ብሎ አማተበ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም ያን ጊዜ ከሕማሙ ድኖ ተነሣ ከቶ ምንም ሕማም እንዳልነካው ሆነ። ❖ ከዚህ በኋላም አባ ፊላታዎስ በዚያ ክፉ አህያ ላይ እንዲህ ብሎ ጮኸ ስለ እኛ በተሰቀለው በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ትሞት ዘንድ ይገባል ወዲያውኑ ያ አህያ ወድቆ ሞተ፤ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም እሊህን ሁለት ተአምራት አይቶ በስሙ ተአምራት የምታደርግበት የተሰቀለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማነው ብሎ አባ ፊላታዎስን ጠየቀው፤ እርሱም እንዲህ ብሎ መለሰለት የክብር ባለቤት የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ በኢየሩሳሌም አይሁድ የሰቀሉት ነው አለው ይህም ነገር በቅዱስ ኤጲፋንዮስ ልብ ተቀረጸ። ❖ በዚያም ወራት አንድ ባለጠጋ አይሁዳዊ ነበር ኤጲፋንዮስንም ወሰደው የኦሪትንም ሕግ በማስተማር አሳደገው፤ የሚሞትበትም በቀረበ ጊዜ ልጅ ስለሌለው ጥሪቱን ሁሉ አወረሰው የኦሪትንም ሕግ ትምህርት ሁሉ ተማረ። ❖ በአንዲት ዕለትም ስሙ ሉክያኖስ ከሚባል መነኰስ ጋራ ተገናኘ እርሱም የተማረና የእግዚአብሔር ጸጋ ያደረበት ነው ከእርሱ ጋር ተጓዘ፤ ሁለቱም በአንድነት ሲጓዙ ድኃ ሰው አገኛቸውና ምጽዋትን እንዲሰጠው ያንን መነኰስ ለመነው፤ ገንዘብም ስለሌለው የሚለብሰውን የጸጉር ዐጽፍ አውልቆ ለድኃው ሰጠው በዚያን ጊዜ ለዚያ መነኰስ የብርሃን ልብስ ከሰማይ ሲወርድለት ኤጲፋንዮስ አየ። ❖ ስለዚህም ድንቅ ተአምር አደነቀ ከመነኰስ እግር በታች ሰግዶ አንተ ማነህ ሃይማኖትህስ ምንድ ነው ብሎ ጠየቀው እርሱም ክርስቲያን እንደሆነ ነገረው፤ ደግሞ ክርስቲያን እንዲያደርገው ለመነው መነኵሴውም ኤጲፋንዮስን ወስዶ ወደ አንድ ኤጲስቆጶስ አደረሰው፤ እርሱም የክርስትና ጥምቀትን አጥምቆ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሥርዓቷንም ሁሉ አስተማረው። ❖ ኤጲፋንዮስም ኤጲስቆጶሱን እኔ መነኰስ መሆን እፈልጋለሁ አለው ኤጲስቆጶሱም ብዙ ገንዘብ እያለህ መነኰስ መሆን አይገባም አለው፤ ኤጲፋንዮስም ሒዶ እኅቱን አምጥቶ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቃት ገንዘቡን ሁሉ ለድኆችና ለምስኪኖች ለባልቴቶችና ለሙት ልጆች ለአብያተ ክርስቲያናትም ሰጠ መጻሕፍትንም ከእርሱ ገዛ። ❖ ከዚህ በኋላ መነኰሰ ለእርሱም ለእኅቱም ለጥምቀት ምክንያት ወደሆነው ስሙ ሉክያኖስ ወደተባለው መነኰስ ገዳም ገባ ዕድሜውም ዐሥራ ስድስት ዓመታት ነበረ፤ ከዚህም በኋላ ታላቁን አባ ኢላርዮስን አገኘው እርሱም በዕድሜው ጐልማሳ በገድልም ሽማግሌ ነው፤ ቅዱስ ኤጲፋንዮስንም ተቀብሎ የምንኵስናን ሕግና የክርስትናን ሥርዓት አስተማረው የእግዚአብሔርም ጸጋ አድሮበት የቤተ ክርስቲያንን ሕግና ሥርዓት የምንኵስናንም ሕግ በጥቂት ቀኖች አጠና። ❖ ከዚህ በኋላ ታላላቅ ተአምራቶችን በመሥራት ሙታንን እስከሚአስነሣቸው ሰይጣናትን ከሰዎች ላይ እስከሚያስወጣቸው ውኃ ከሌለበት ከደረቅ ቦታ ውኃን እስከሚአፈልቅ ያለ ጊዜውም ብዙ ዝናምን እስከ ማውረድ ደርሶ በገድልና በትሩፋት ፍጹም ሆነ፤ የትሩፋቱም ወሬ አዋቂነቱም ተሰማ ከእርሱ ጋራም ሊከራከሩ ብዙ አይሁድ ወደ እርሱ መጡ፤ ስሕተታቸውንም ገለጠላቸው በእርሱ ትምህርት አምነው የክርስትናን ጥምቀት አጠመቃቸው፤ እንዲሁም ጥበበኞች ዮናናውያን በትምህርቱ ተመለሱ ወደ ክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖትም ውስጥ ገቡ። ❖ መምህሩ ቅዱስ ኢላርዮስም በቆጵሮስ ሀገር ኤጲስቆጶስነት እንደሚሾም ትንቢት ተናገረለት፤ ወደዚያም ሒዶ በታዘዘለት ቦታ በዚያ እንዲኖር አዘዘው፤ እንዲህም አለው ኤጲስቆጶስነት ሊሾሙህ በፈለጉህ ጊዜ እምቢ አትበል ይህ በእግዚአብሔር ፍቃድ ሆኖአልና፤ ቅዱስ ኤጲፋንዮስም ወደ ቆጵሮስ ሒዶ መምህሩ ቅዱስ ኢላርዮስ በአዘዘው ቦታ ተቀመጠ። ❖ የቆጵሮስ ደሴት ኤጲስቆጶስም በአረፈ ጊዜ በዚያን ሰሞን ቅዱስ ኤጲፋንዮስ ምግቡን ሊገዛ ወደ ገበያ ገባ፤ ከእርሱም ጋራ ሁለት መነኰሳት አሉ፤ ደግሞም በዚያች ገዳም ጻድቅ የሆነ ሽማግሌ ኤጲስቆጶስ ነበረ ለእርሱም የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲህ ብሎ ነገረው፤ ወደ ገበያም ሒድ በእጁም ሁለት የወይን ዘለላ የያዘ መነኰስ ታገኛለህ ከእርሱ ጋራም ሁለት መነኰሳት አሉ ስሙንም ጠይቀው፤ ስሜ ኤጲፋንዮስ ነው ይልሃል እርሱን ያዝ በእጁ ያለውንም አስጥለህ ከአንተ ጋራ አምጣው፤ ያ ኤጲስቆጶስም የክበር ባለቤት ጌታችን እንደ አዘዘው አደረገ በአመለከተውም ቦታ አግኝቶት ይዞ ወደ ቤተ ክርስቲያን ወስዶ ዲቁና ሾመው፤ በሦስተኛውም ቀን ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። ❖ ከዚህም በኋላ ሽማግሌው ኤጲስቆጶስ የኤጲፋንዮስን ልብ ደስ ለማሰኘት ሽቶ ስለ ኤጲፋንዮስ ያየውን ራእይ ለሕዝቡ ገለጠላቸው፤ ስለ ርሱም ታላቅ ደስታ ሆነላቸው፤ ይህም ቅዱስ እግዚአብሔር በሚወድለት በሹመቱ ሁኖ በበጎ ሥራ ላይ ጸና፤ ጥቅም ያላቸውን ብዙ ድርሳኖችንም ደረሰ፤ ርኅራኄ ስለ ሌለው ሰው በሚሰማ ጊዜ ተመልሶ ቸር እስከሚሆን ድረስ ሁልጊዜ ይገሥጸዋል ይመክረዋል። ❖ በኢየሩሳሌም ኤጲስቆጶስ በአባ ዮሐንስ ላይ ምክንያት ፈጠረ ስለ ርሱ ርኅራኄ እንደሌለው በሰማ ጊዜ ከወርቅ የተሠሩ የማዕዱን ዕቃዎች የሚመገብባቸውን በውሰት ወሰደ፤ እነርሱም ወርቅና ብር ናቸው ቅዱስ ኤጲፋንዮስም ሸጣቸውና ለድኆችና ለምስኪኖችም መጸወታቸው። ❖ አባ ዮሐንስም እንዲመልስለት በሻ ጊዜ ምንም ምን አልሰጠውም፤ በክብር ባለቤት ጌታ መቃብር ቤተክርስቲያን ውስጥ ቅዱስ ኤጲፋንዮስን የልብሱን ጫፍ ስጠኝ ብሎ ያዘው፤ ቅድስ ኤጲፋንዮስም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ የአባ ዮሐንስም ዐይኖቹ ያንጊዜ ታወሩ፤ ከዚህ በኋላም ይምረው ዘንድ በብዙ ልቅሶ ወደርሱ ፈጽሞ ማለደ ዐይኖቹንም ይገልጥለት ዘንድ ለመነው። ❖ ሁለተኛም ቅድስ ኢጲፋንዮስ ጸለየ አንድ ዐይኑንም ገለጠለት የማዕዱንም ዕቃዎች ሸጦ ለድኆችና ለምስኪኖች እንደሰጣቸው ነገረው፤ ስለ ዮሐንስ አፈወርቅ መሻርና መሰደድ ወደርሷ መጥቶ ይራዳት ዘንድ አውዶክስያ ንግሥት ጽፋ ወደርሱ በላከች ጊዜ ሊአስታርቃቸውና በመካከላቸው ሰላምን ሊአደርግ ሽቶ ወደ ቊስጥንጥንያ ሔደ፤ ነገር ግን ቅዱስ ኤጲፋንዮስን አልሰማችውም ዮሐንስን ከሹመቱ ካልሻርከው ይህ ካልሆነ አብያተ ክርስቲያናትን እዘጋለሁ የጣዖታትንም ቤቶች እከፍታለሁ አለችው። ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር አሜን ይቆየን።
Показати все...

👏 1