cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

FutureX

The future starts here!

Більше
Рекламні дописи
8 464
Підписники
+824 години
+617 днів
+55930 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ጥረትህን አታቁም! ከጓደኞችህ ወይ በዙሪያህ ካሉ ሁሉ ኋላ መቅረትህን አትጥላው፤ ምክንያቱም ረጅም ርቀት ለመወርወር ወደ ኋላ በደምብ መንደርደር ወሳኝ ነው። እየታሸህ ያለኸው በደምብ እንድትበስል ነው፤ እድል ጓዟን ጠቅልላ እጅህ እስክትገባ ጥረትህን እንዳታቆም! የዚህ አለም እድለኞች አብዝተው የሚለፉ እንጂ አብዝተው የሚመኙ አይደሉም። ሰናይ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @FutureXethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Показати все...
🔥 49👍 26 11🙏 9😁 2🥰 1
ያንተ ጥንካሬ! አይንህ ወደ ብርሀኑ አቅጣጫ ከሆነ ሊጋርድህ የሚፈልግ ጥላ ከኋላህ ያርፋል፤ ሀሳብህ መልካም ነገር ላይ ብቻ ካረፈ መጥፎ ነገሮች አንተ ጋር ሳይደርሱ ከጀርባህ ይወድቃሉ። ጨለማው ላይ ማፍጠጥ ብርሀን አይሰጥም፤ ድክመትህን ብቻ አጉልተህ አትይ! አንተ ባትሆን የማታልፋቸው ብዙ ችግሮች ነበሩ፤ አንተ ግን ለዛሬ ደርሰሀል፤ ወዳጄ አሁን ያለህ ጥንካሬ የምታስበውን ሁሉ ለማሳካት ከበቂ በላይ ነው! ውብ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @FutureXethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Показати все...
👍 84🙏 20 15🔥 1
ቆራጥ ሁን! የትም አያደርስህም እንጂ የስሜትህ ባሪያ መሆን ቀላል ነው፤ ጊዜያዊ ደስታ የሚሰጡህን ነገሮች በጥበብ እለፋቸው፤ ለእውነተኛ ደስታህ ስትል አሁን የማይጠቅሙህን ሰዎች፣ ነገሮች፣ ሁኔታዎች፣ ቦታዎች ሁሉ ከህይወትህ አውጣቸው! የተመረዘ እጅ ወይም እግር የሚቆረጠው ባለቤቱ ስለማያስፈልገው አይደለም ግን ሌሎቹን የሰውነት ክፍሎች ስለሚመርዝ ነው፤ ስኬትና ደስታ መስዋዕትነት ይጠይቃል! ወዳጄ የሚጠቅምህን አሳምረህ ታውቃለህ ቆራጥ ሁን! ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @FutureXethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Показати все...
👍 73 34🙏 5🤩 1
ትችላለህ! ወዳጄ 'አልችልም' ካልክ ልክ ነህ አትችልም፤ 'እችላለሁ'ም ካልክ ልክ ነህ ትችላለህ! ሁሉም በመዳፍህ ነው! ውስጥህ ካመነበት የምትፈልገውን እንዳታገኝ የሚያስቆምህ ማነው?! እንደምትችል ማንም እስኪነግርህ አጠብቅ! አንተ የምትችለውን ሁሉ ስታደርግ ፈጣሪ ደግሞ የማይቻል የሚመስለውን አድርጎ ያሳይሀል! ድንቅ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @FutureXethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Показати все...
👍 88🥰 14 11🙏 11🕊 2
አሁን ጀምር! ምንም ነገር ቁጭ ባልክበት ሊሳካ አይችልም፤ ስልክህ ላይ ተጥደህ፣ ቲቪ ላይ አፍጥጠህ ወይ አልጋ ላይ ጋደም ብለህ ጣሪያ ጣሪያ እያየህ ምንም ነገር መጀመርም ሆነ መቀየር አትችልም! ይህ ምድር ያንተን ላብ ይፈልጋል፤ ያንተን ጥረት ይፈልጋል፤ ለነገ መድረሻህ አሁን መዘጋጀት፣ ማቀድ እና ወደ ድርጊት መግባት አለብህ! ወዳጄ ለመጀመር ታላቅ መሆን አይጠበቅብህም፤ ታላቅ ለመሆን ግን አሁኑኑ መጀመር አለብህ! የለውጥ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @FutureXethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Показати все...
👍 85 25🙏 3🤝 2
ልክ ነህ! ሁሌም የምትችለውን ሁሉ አድርግ! አሁን የዘራኸውን ነው ነገ የምታጭደው። አሁን ስትለፋ ወይ አላማህን ስታስቀድም እንደ ሞኝ ሊያዩህ ይችላሉ፤ አንተም ለጊዜው የተሸወድክ ይመስልሀል፤ ልክ ነህ አልተሳሳትክም። ሰዎችን በብልጠት ሳይሆን በልፋትህ ብለጣቸው ምክንያቱም በልፋትህ ከፍ ስትል ብልጡን ሰው ቀጥረህ ታሰራዋለህ። ደስ የሚል ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @FutureXethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Показати все...
👍 100🥰 6🙏 6 4😢 3🔥 2
ለራስህ ቃል ግባ! ነገሮች በፈለከው መንገድ ላይሄዱ ይችላሉ፣ ሰዎች ጀርባቸውን ሊያዞሩብህ ይችላሉ፣ በዚህ አለም ለመኖር የሚያጓጉህን ነገሮች ሁሉ ልታጣ ትችላለህ፤ ግን ሁላችንም በዚህ ስሜት ውስጥ አልፈን እናውቃለን ወደፊትም እናልፍ ይሆናል። ታላቅነት ግን በዚህ ከባድ ጊዜ መቼም ተሰፋ ቆርጠህ ጥረትህን እንደማታቆም ለራስህ ቃል መግባት ነው! ተስፋ የሞላበት ምሽት ተመኘሁላችሁ🙏 @Futurexethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Показати все...
👍 91🙏 14🔥 7👏 5 3
ስንፍናን ማሸነፍ! በህይወት ውስጥ ትልቁን ለውጥ የሚፈጥሩት ትናንሽ ነገሮች ናቸው፤ ዝሆን ገጭቶት የሞተ ሰው ታውቃላችሁ? በትንሿ የወባ ትንኝ ግን ተነክሶ የሞተ ነፍ ነው። ታዲያ እንደ ቀላል የምታየው ቸልተኛ ፀባይህ ምን እንደሚያሳጣህ የምታውቀው ዘግይተህ ነው። በቀን ውስጥ አደርጋለው ያልከውን ሳታደርግ ቀጣዩን ቀን አትጀምር! አለዛ ከነገ ላይ እየሰረክ ነው፤ ስንፍናን ማሸነፍ የምትችለው በየቀኑ ካንተ የሚጠበቀውን ሁሉ በማድረግ ነው። ልዩ ምሽት ተመኘንላችሁ🙏 @FutureXethiopia የእናንተው ምርጥ ጓደኛ!
Показати все...
👍 81 17🔥 4😁 2🫡 2🙏 1
ከባዱን አሁን ስራ! ታሪክ በአንድ ጀምበር አይሰራም! ሁሌም የማይቆም ጥረት ማድረግ አለብህ፤ የምትፈልጋቸው ነገሮች በነፃ አይገኙም ዋጋ ያስከፍላሉ ዋጋ ለመክፈል ራስህን አዘጋጅ! ወዳጄ አሁን ከባዱን ካደረክ ህይወት ቀላል ትሆናለች፤ ቀላሉን ካደረክ ግን ህይወት ትከብድሀለች! አጀብ የሚያሰኝ ስኬት ተመኘንላችሁ🙏 @FutureXethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Показати все...
👍 81 20🫡 8🕊 3🥰 2🙏 1
🛑በፅናት ማሸነፍ! ሰነፍ የምትባለው ውጤትህ ዝቅ ሲል አይደለም፤ ምርጥ ውጤት ለማምጣት የምታደርገውን ጥረት ስታቆም ነው። አሸናፊዎች አያቆሙም፤ የሚያቆሙም አያሸንፉም! @futureXethiopia ለውጥ አሁን ይጀምራል!
Показати все...
👍 105🔥 9🥰 5👏 2