cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

የ ኦርቶዶክስ ስብከት

Рекламні дописи
604
Підписники
Немає даних24 години
+137 днів
+3330 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

አቤቱ ባንተ ታምኛለሁና አትጣለኝ✝                                                     Size:- 36.3MB Length:-1:44:20              በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ http://t.me/orthodox_sebket http://t.me/orthodox_sebket
Показати все...
አቤቱ_ባንተ_ታምኛለሁና_አትጣለኝ_እጅግ_ድንቅ_ትምህርት_በርእሰ_ሊቃውንት_የኔታ_አባ_ገብ_QBS9jYPUZ8A.m4a36.34 MB
👍 1
የንግሥት ልጆች ለክብርህ ይገዛሉ✝                                                     Size:- 25.9MB Length:-1:14:18              በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ http://t.me/orthodox_sebket http://t.me/orthodox_sebket
Показати все...
_የንግስት_ልጆች_ለክብርህ_ይገዛሉ_እጅግ_ድንቅ_ትምህርት_በርእሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረኪዳ_wEIuhr6Ojsk.m4a25.88 MB
ሰላም የክርስቶስ ቤተሰቦች በቅድምያ እንኳን ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዩሀንስ በሰላም አሸጋገረን። እኛም እንግዲ በተለያዩ ምክንያቶች ጠፍተን ዝም ብለን ነበር ለዚህም ትልቅ ይቅርታ እየጠየቅን 🙏 በቀጣይ በተቻለን አቅም ለመስራት አስበናል፤ የናንተም ድጋፍ አይለየን ዘንድ በ እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።🙏
Показати все...
​​✞ እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ ✞ #ደብረ_ታቦር #ደብረ_ታቦር በቁሙ እሥራኤል ውስጥ ከሚገኙ ተራሮች አንዱ ነው። ተራራው ብዙ ታሪካዊ ዳራዎች ቢኖሩትም ክብሩ ከፍ ከፍ ያለው ግን ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን ስለ ገለጸበት ነው። #ይሕስ_እንደ_ምን_ነው_ቢሉ:- አካላዊ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን በተዋሐደባት በዚያች በተወደደች ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ስለ እግዚአብሔር መንግስት ምሥጢርን ይማሩ ነበር። በጊዜው ግን አበው ሐዋርያት ምሥጢር ባይገባቸው አንድም ገና መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ አልወረደም ነበርና እምነታቸው ሙሉ አልነበረም ጌታም አምላክነቱን በየጊዜው በቃልም በተግባርም ይገልጥላቸው ነበር። በርግጥ ያንን ነደ እሳት ሰማያት የማይቸሉትን ግሩማዊ አምላክ በትሑት ሰብዕና መመልከቱ ሊከብድ እንደሚችል መገመት አያዳግትም። ጌታችን ብዙ ተአምራትን በአምላካዊ ጥበቡ ሠርቷል። እጅግ ድንቅ ከሆኑት መካከል ደግሞ ቅድሚያውን ደብረ ታቦር ይይዛል። ጌታ ስለ ምን መለኮታዊ ክብሩን በደብረ ታቦር ገለጸ ቢሉ:- 1.ትንቢቱ ሊፈጸም (መዝ. 88:12) 2.ምሳሌው ሊፈጸም (ባርቅና ዲቦራ በሢሣራ ላይ ድልን ተቀዳጅተዋልና) 3.ሊቀ ነቢያት ሙሴ "ልይህ" ብሎ ከ1,500 ዓመታት በፊት ጠይቆ ነበርና እርሱን ለመፈጸም 4.አንድነቱን: ሦስትነቱን ለመግለጽ 5.ቤተ ክርስቲያንን በምሳሌ ለማሳየት 6.ተራራውን ለመቀደስ 7.የሐዋርያቱን ልብ ለማጽናት . . . ወዘተ ነው። ነሐሴ 7 ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቂሣርያ ፊልዾስ ወስዶ "የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?" ብሎ ጠይቁዋቸው ነበር። እነርሱም የራሳቸውን ሐሳብ የሌላ እያስመሰሉ "አንዳንዶቹ ኤልያስ: አንዳንዶቹም ሙሴ: ሌሎቹም ከነቢያት አንዱ ነው ይሉሃል" አሉት። ኩላሊትን የሚመረምር ፈጣሪ ነውና "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ቢላቸው ደንግጠው ዝም አሉ። የሃይማኖት አባት: ባለ በጐ ሽምግልና ቅዱስ ዼጥሮስ ግን በመካከላቸው ቆሞ "አንተ ውዕቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው - የሕያው እግዚአብሔር አንድያ የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ አንተ ነህ" አለው:: በዚያን ጊዜ ቃለ-ብጽዓን እና የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ተሰጠው። (ማቴ. 16:13) መጽሐፍ እንደሚል ደግሞ እንዲህ ከሆነ ከ6ኛው ቀን በሁዋላ ጌታችን 12ቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ደብረ ታቦር ወሰዳቸው። ዘጠኙን በእግረ ደብር (ከተራራው ሥር) ትቶ 3ቱን (ዼጥሮስን: ዮሐንስንና ያዕቆብን) ይዟቸው ወጣ። እኒሕ ሐዋርያት "አዕማድ: አርዕስት: ሐዋርያተ ምሥጢርም" ይባላሉ:: በተራራው ላይ ሳሉም ድንገት የጌታችን መልኩ ከፀሐይ 7 እጅ አበራ: ከመብረቅም 7 እጅ አበረቀ። "ወኮነ ልብሱ ጸዐዳ ከመ በረድ" እንዲል ከታቦር የተነሳው ብርሃነ ገጹ አርሞንኤም ደርሷል። ያንን ተመልክተው መቆም ያልቻሉት ሐዋርያቱ ፈጥነው መሬት ላይ እንደ ሻሽ ተነጠፉ:: በዚያች ሰዓት ሙሴ ከመቃብር: ኤልያስም ከብሔረ ሕያዋን መጡ። አንዳንዶቹ ጌታን 'ነቢይ' (ሎቱ ስብሐት) ብለውታልና ሙሴና ኤልያስ ተናገሩ:- "ስለ ምን አንተን ነቢይ ይሉሃል: እግዚአ ነቢያት - የነቢያት ፈጣሪ ነህ እንጂ" እያሉ ተገዙለት: አመሰገኑት። ነገር ግን በቦታው ጸንተው መቆየት አልቻሉም። መለኮታዊ ብርሃኑ ቢበዘብዛቸው ቅዱስ ሙሴም ወደ መቃብሩ: ቅዱስ ኤልያስም ወደ ማደሪያው በድንጋጤ ሩጠዋል። በዚያች ሰዓት ሊቀ ሐዋርያት ጌታን "ሠናይ ለነ ኀልዎ ዝየ: ንግበር ሠለስተ ማሕደረ: አሐደ ለከ: ወአሐደ ለሙሴ: ወአሐደ ለኤልያስ - ጌታ ሆይ! በዚህ መኖር ለኛ መልካም ነው። በዚህም 3 ዳስ እንሥራ። አንዱን ላንተ: አንዱንም ለሙሴ: አንዱን ለኤልያስ" ብሎታል። ቅዱስ ዼጥሮስ ለራሱ ሳያስብ ለጌታና ለቅዱሳን ነቢያቱ "ቤት እንሥራ" በማለቱ ሲመሰገን ጌታን የመጣበትን የማዳን ሥራ የሚያስተው ጥያቄ በማቅረቡ ከድካም ተቆጥሮበታል። ለሁሉም ግን ሐሳቡ ድንቅና መንፈሳዊ ነው። እርሱ ይሕንን ሲናገር መንፈስ ቅዱስ በደመና አምሳል ወረደና ከበባቸው። አብ ከሰማይ ሆኖ "ዝንቱ ውዕቱ ወልድየ ዘአፈቅር: ወሎቱ ስምዕዎ - የምወደው: የምወልደው: ሕልው ሆኘ የምመለክበት የባሕርይ ልጄ እርሱ ነውና ስሙት" ሲል ተናገረ። ደቀ መዛሙርቱም ከፍርሃት የተነሳ በዚያች ሰዓት እንደ በድን ሁነው ነበርና ጌታችን ቀርቦ ቀሰቀሳቸው:: በተነሱ ጊዜ ግን ሁሉም ነገር ወደ ነበረበት ተመልሶ ነበር። (ማቴ. ማር. ሉቃ. ) በደብረ ታቦር የጌታችን ብርሃነ መለኮት ያዩ 3ቱ ሐዋርያት ብቻ አይደሉም:: እመ ብርሃን ካለችበት ሆና ስትመለከት 12ቱ ሐዋርያትh ደግሞ በተራራው ሥር ሆነው በተደሞ ተመልክተዋል:: ይሕንን ድንቅ ብርሃነ መለኮት ያላየ ይሁዳ ብቻ ሲሆን እርሱም ስለ ክፋቱ የኢሳይያስ ትንቢት ተፈጽሞበታል። ኃጢአተኛው የእግዚአብሔርን ክብር እንደማያይ ተነግሮበታልና:: "ያአትትዎ ለኃጥእ ከመ ኢይርዐይ ስብሐተ እግዚአብሔር" እንዲል:: (ኢሳ.) ሊቁም የደብረ ታቦርን ምሥጢር ሲያደንቅ እንዲህ ብሏል:- "ጸርሐ አብ ኪያከ በውዳሴ: ወበርእስከ ጸለለ መንፈሰ ቅዳሴ: አመ ገበርከ እግዚኦ በታቦር ምስለ ሐዋርያት ክናሴ: መንገለ ሀሎ ኤልያስ ወኀበ ሐለወ ሙሴ: ዘመለኮትከ ወልድ ከሠትከ ሥላሴ::" ለወዳጆቹ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠ ጌታ የእኛንም ዐይነ ልቡናችንን ያብራልን። ከበዓሉ በረከትም ያሳትፈን።
Показати все...
ይህን ያኽል የኔ ስራ መጥፎነት እና ከአንተ መሸሽ ሆኗል። ፍቃድህን ከመፈጸም ይልቅ ለራሴ መሸት ከልክ በላይ ተጋው። ውለታህን ትቼ ለስጋዬ ጩኸት አቤት አልኩኝ። የአንተ ድምጽ እንዳልሰማ ሰው ሆኜ ለራሴ ድምጽ ግን ታዘዝኩኝ። ከሚጮኸው ከፍቅርህ ድምጽ ይልቅ ለስሜቴ ሹሹክታ ጆሮ ሰጠው። ተው ልጄ እያልከኝ ተወኝ እስኪ ብዬ ሸሸውህ። አይበጅህም እያልከኝ መስሎኝ ከሞቴ መንደር ሰነበትኩኝ። ልጄ ይሄ አይመጥንህም ይቅርብህ እያልከኝ ያለውሎዬ ውዬ ቀለልኩኝ። የምከብር መስሎኝ ክብርህ በሌለበት ክብሬን ጣልኩኝ። የምዝናና መስሎኝ በራሴ ድርጊት አዝኜ ተገኘው። የተዘረጋውን መዳፍህን በመያዝ ፈንታ በፍላጎቴ መዳፍ ላይ ወደኩኝ። አንተን እንደሚያሳዝን እያወኩኝ ደስታ በመሰለኝ ነገር ግን ደስታ ባልሆነ ተግባር ተነኘው። አንዳንዴ እንኳን እሺ የማልልህ ለምን ይሆን ብዬ እራሴን እጠይቃለሁ። እሳት ነው ያቃጥላል ያልከኝ የታወሰኝ እሳቱ ሲነካኝ ነው። አንተን መስማት ትርፌ ነበር አንተ እኮ ህይወቴ ነህ። ያለንታ ሁሉ ነገር ጨለማ እና ነበልባል ነው። ከነፍሴ ይልቅ ለምንስ ለስጋዬ አደላሁ? ለምንስ ከአንተ ይልቅ ለራሴ ቆምኩኝ። ለምን አኖርከኝ፣ በቃ ግደለኝ፣ እኔ በደለኛ ነኝ ፍረደብኝ... ብዬ አለምንህም ምክንያቱም ምህረትህ ብዙ ነውና መመለሴን እንጂ መሞቴን አትሻም። የበደልኩህን ፍለጋ ከሰማያት መጥተህ በበደሌ ምክንያት ብቻዬን አትተወኝም። ምክንያቱም አንተ ኃጢያቴን እንጂ እኔን የመጥላት ባህሪ የለህም። ለራሴ አስልፈህ አልሰጠኸኝምና ዛሬም የምህረትህ ጥላ በላዬ ላይ አርፎ በህይወት ቆሜያለሁ። መውደድህ ማርጀት የለበትምና በአንተ ዘንድ መወደዴ በዝቷል። ግን ይህን ያኽል ምህረት እንዴት አይነት ምህረት ነው። ይህን ያኽል ይቅር የምትለኝ ምን አይተህብኝ ነው? አባ ..... ምህረትህ በዝቶ ከማሰቤ ልቋል፣ ከህሊናዬም ረቋል። እኔ የምበድልህ እንኳን ሰልችቶኝ ለውጤን ስናፍቅ እኔን መማር እንዳልሰለቸህ ሳስብ የማሰቤ አቅም ውስን ይሆንብኛል። ምህረትህ ግነ ወሰኑ ምኑ ጋር ነው? እኔ የኃጢያት ወሰኑን አልፌም የአንተ ምህረት ግን ወሰን አልባነቱ ጎልቶብኛል። ሁሌ መበደል እኮ ይሰለቻል፣ ሁሌ ማስከፋት ይታክታል። እየተበደሉ ያለመታከት ማመር ደግሞ ከሁሉ ይልቅ ያደክማል። አንተ እኮ ግን ደከመኝ አላልከኝም ሰለቸኝ አልወጣህም ዝም ብለህ ትምረኛለህ። ይቅር እያልክ ታኖረኛለህ። ምህረትህን ተደግፌ እንዳልበድልህ፣ ይቅርታህን ተማምኜ እንዳላጠፋ፣ አቃፊነትሀን አስቤ እንዳልኮበልል፣ ተቀባይነትህን አንግቤ ለኃጢያት እንዳልዘምት፣ እንደማትጥለኝ እያወኩኝ እንዳልወድቅ በጸጋህ ደግፈኝ። ይምረኛል ብዬ በኃጢያት አንዳልመላለስ አንተ ጠብቀኝ። አሜን ✍️ ዲያቆን ተስፋ መሠረት ይቀላቀሉ ➟ @orthodox_sebket ለሌሎች ያጋሩ ➟ @orthodox_sebket
Показати все...
sticker.webp0.62 KB
#የሐሙስ_ውዳሴ_ማርያም_ትርጓሜ ይህ ዕለት ለምስጋና አራተኛ ለፍጥረት አምስተኛ ቀን ነው፡፡ በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣለች፤ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል፤ የብርሃን ዙፋን ይነጸፋል፡፡ ከዚያ ላይ ኹናም ሊቁን ባርካው ምስጋናዉን ጀምሯል፡፡ ከወትሮ ይልቅም ነቢያትንና ሐዋርያትን አስከትላ መጥታለች፡፡ ፩. ነደ እሳት ሰፍሮባት፣ በነደ እሳት ተከባ፣ ጫፎቿ ሳይቃጠሉ ሙሴ በደብረ ሲና ያያት ዕፅ ድንግል ማርያምን ትመስላለች /ዘጸ.፫፡፩-፫/፡፡ አካላዊ ቃል ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ሰው ኹኗልና፤ ባሕርየ (እሳተ) መለኮቱም አልለወጣትምና (አላቃጠላትምና) ሐመልማላዊቱ ዕፅ እመቤታችንን ትመስላለች፡፡ ዳግመኛም እርሱን ከወለደችው በኋላ ማኀተመ ድንግልናዋ አልተለወጠምና ሐመልማላዊቱ ዕፅ እመቤታችንን ትመስላለች፡፡ እርሱም ምንም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷም ነፍስ ነስቶ ፍጹም ሰው ቢኾንም ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠምና እሳቱን ይመስላል፡፡ ሰውም ቢኾን ባሕርየ መለኮቱ አልተለወጠምና ሰው ኾኖ ያዳነን የባሕርይ አምላክ ነው፡፡ ሰው ኾኖ ካዳነን ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋዉን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኚልን፡፡ ፪. ይቅርታሽ (ምልጃሽ) ለኹላችን ይኾን ዘንድ አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ! ኹላችን እናከብርሻለን፤ እናገንሻለን፡፡ ሔዋን ባደረገችው ዐመፅ በባሕርያችን ጸንቶ የነበረ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ በእርሷ ምክንያት የጠፋልን አምላክን የወለደች ድንግል ማርያም የኹላችን መመኪያ ናት፡፡ “ሔዋን ምን አደረገች?” ትለኝ እንደኾነም ዕፀ በለስን በልታለች እልሃለሁ፡፡ “ወአዘዞሙ ለኪሩቤል ወሱራፌል ዘውስተ እደዊሆሙ ሰይፈ እሳት እንተ ትትመያየጥ ከመ ይዕቀቡ ፍኖተ ዕፀ ሕይወት - ወደ ሕይወት ዛፍ የሚወስደውንም መንገድ ለመጠበቅ ኪሩቤልንና የምትገለባበጥ የነበልባል ሰይፍን በዔድን ገነት ምሥራቅ አስቀመጠ” እንዲል /ዘፍ.፫፡፳፬/ በሔዋን ምክንያት የገነት ደጅ ተዘጋ፡፡ “ወአግኃሦ ለሱራፊ ዘየዐቅብ ፍና ዕፀ ሕይወት፤ ወአእተተ እምእዴሁ ኵናተ እሳት - ” እንዲልም በድንግል ማርያም ምክንያት ዳግመኛ ተከፈተልን፡፡ ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግም፡- “አዳምን እንዲሞት ያደረገች ያቺ ቀን ተለወጠች፡፡ እርሱም ከሞት የሚድንባት ሌላ ቀን መጣች፡፡ እባቧ ሳትኾን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ይናገር ዘንድ ተነሣ፡፡ ሔዋን ሳትኾን ድንግል ማርያምም ቃሉን ትቀበል ዘንድ ተዘጋጀች፡፡ በተንኰል የሚያስተው ሳይኾን ሕይወትን የሚያውጀው ቃል ወጣ፡፡ በሞት ዛፍ መካከል የሞት ዕዳዋን በጻፈችው ሔዋን ፈንታ ልጇ (ማርያም) የአባቷን ዕዳ ኹሉ ከፈለች፡፡ ሔዋንና እባቡ በቅድስት ድንግል ማርያምና በቅዱስ ገብርኤል ተተኩ፡፡ ያ ከመጀመርያው የተበላሸው ነገር አሁን ተስተካከለ፡፡ የሔዋን ጀሮና ቀልብ አታላዩ በሚናገርበት ጊዜ እንደምን እንዳዘነበለ አስተውሉ፤ ያ በገነት ሲመለከታቸው የነበረው መልአክ አሁን በድንግል ማርያም ጀሮ የድኅነትን ተስፋ ሲያሰርጽና የእባቡን ከፉና መርዛማ ቃል ሲያጠፋ ደግሞ አስተውሉ፡፡ ሔዋን ያፈረሰችው ሕንፃ ገብርኤል ገነባው፡፡ በዔደን ገነት ውስጥ ኹና ሔዋን ያፈረሰችውን መሠረት ዳግሚት ሔዋን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር ኹና ገነባችው፡፡ ከኹለት መልእክተኞች መልእክት የተቀበሉ ኹለት ደናግላን ኹለት ትውልድን ቀጠሉ፡፡ አንዱም የአንዱ ተቃራኒ ኾነ፡፡ በእባብ ምክንያት ሰይጣን ምሥጢርን ለሔዋን ላከ፡፡ በሌላ ቅዱስ መልአክ አማካኝነት ደግሞ ጌታ የምሥራቹን ወደ ቅድስት ድንግል ማርያም ላከ፡፡ እባብ ለሔዋን የሐሰትን ቃል ለሔዋን ስትናገር ቅዱስ ገብርኤል ግን የእውነትን ቃል ለቅድስት ድንግል ማርያም ተናገረ፡፡ እውነትን በሚናገር አንደበቱ የቀደመውን የእባብ ቃል አደሰው፡፡ እውነትን ተናገረና ሐሰቱን አስወገደው፡፡ አስቀድሞ ሐሰትን ከራሱ አንቅቶ ሰይጣን ሔዋንን በዔደን ገነት አታለላት፡፡ ይህንንም ታላቅ ስሕተት በጀሮዋ አልፎ እንዲሰማት ፈቀደች፡፡ አሁን ግን በመጀመርያዋ ድንግል ፈንታ ሌላ ድንግል ተመረጠች፡፡ በዚህች ድንግል ጀሮም ከአርያም የተላከ የእውነት ቃል ገባ፡፡ ሞት በገባበት በዚያ በር (ጀሮ) ሕይወት ገባ፡፡ ክፉው (ዲያብሎስ) ያጠበቀው ጽኑ የሞት ማሰርያም ተፈታ፡፡ ኀጢአትና ሞት ሠልጥነውበት በነበረ ቦታ ጸጋ ከመጠን ይልቅ በዝቶ ታየ፡፡ … እባብ የስሕተትን ዜማ ለሔዋን ዘመረላት፤ ሐሰትንም ረጨባት፡፡ በተፈጥሮዋ ገና ድንግል በምትኾን በሔዋን ላይ ክፉ ምክርና ስሕተት አፈሰሰባት፡፡ በመርዝ የተለወሰና ደምን የተጠማ ክፉ ምክር በአዳም ቤት ውስጥ አስገባ፡፡ ኃይለ ልዑል የላከው መልአክ ግን እነዚህን የክፋት ሰይፎች ለመቆራረጥ ክንፉን እያማታ እየበረረ መጣ፡፡ ለሰው ኹሉ የሚኾን የድኅነት ሰነድ ይዞ መጥቶም ለድንግሊቱ (ለማርያም) አበሠራት፡፡ ሰገደላት፡፡ ሕይወትን በውስጧ አሰረጸ፡፡ ሰላም ዐወጀ፡፡ በፍቅር ቀረባት፡፡ የቀድሞውን የሞት ዳባ በጣጠሰው፡፡ እባብ የገነባውን የማታለል ግንብ ዳግም ላይገነባ በወልደ እግዚአብሔር እንደሚናድ ነገራት፡፡ በእባብ የታጠረው የሞት ቅጽር በወልድ መውረድ እንደሚሰባበር ቀጠሮው እንደደረሰ ነግሮ የምሥራች አላት” በማለት ከማር የጣፈጠ ትምህርቱን እያነጻጸረ አስተምሯል፡፡ ከዕፀ ሕይወትም እንበላ ዘንድ አደለን፡፡ ይኸውም እኛን ስለ መውደድ ሰው ኾኖ ያዳነን የክርስቶስ ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙ ነው፡፡ ወዮ! ሰውን የሚወድ ሰውም የሚወደው እግዚአብሔር፣ ማኅደርም ኀዳሪም ያይደለ አካላዊ ቃል፣ ሳይለወጥ ቅድመ ዓለም የነበረ እግዚአብሔር ወልድ፣ ከአብ አንድነት ሳይለይ መጥቶ ንዕድ ክብርት ከምትኾን ከእመቤታችን ሰው ኾኗልና፤ እርሱንም ከወለደችው በኋላ እንደ ቀድሞ ማኅተመ ድንግልናዋ ሳይለወጥ ኑራለችና፤ ስለዚህም ነገር አምላክን የወለደች እንደኾነች በጎላ በተረዳ ነገር ታውቃለችና ለርሷ ድንቅ ኾኖ የሚነገረውን ነገር መናገር የሚቻለው ምን አንደበት ነው? መስማትስ የሚቻለው ምን ጆሮ ነው? ማወቅስ የሚቻለው ምን አእምሮ ነው? የእግዚአብሔር የጥበቡ ምላት ስፋትስ ምን ይረቅ? ምን ይጠልቅ? አንድም ለእግዚአብሔር ለጥበቡ ምላት ስፋት አንክሮ ይገባል፡፡ “በፀነስሽ ጊዜ ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፤ በጭንቅ ትወልጃለሽ፤ ፈቃድሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል” /ዘፍ.፫፡፲፮/ ብሎ የፈረደባት ማኀፀን የሕይወት፣ የድኅነት መገኛ ኾነች፡፡ ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇                 •➢ ሼር // SHARE @retua_haymanot @retua_haymanot @retua_haymanot @retua_haymanot
Показати все...
✝️ሐዋርያዊነት✝️ Size:-37.8MB Length:-1:48:31 በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ http://t.me/orthodox_sebket http://t.me/orthodox_sebket
Показати все...
_ሐዋርያዊነት_በህልማችሁ_አትታመኑ_እጅግ_ድንቅ_ትምህርት_በርእሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረኪዳ_UOho8TsY9Ko.m4a37.80 MB
*መልካም ጾመ ፍልስታ* ✝️ *እነሆ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የእረፍቷ እና የትንሣኤዋ መታሰቢያ የሆነው እና በ 12ቱ ቅዱሳን ሐዋርያት የተጀመረው ታላቅ የበረከት ጾም ነገ ነሐሴ 1 ቀን 2015 ቀን ይጀምራል:: እንኳን አደረሳችሁ!!!* ✝️  *አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ።   ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቁጣው የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ* ። ' ኢዮኤል 2 :12- 13 ✝️ *ሱባኤውን በሚገባ ስለ ቤተክርስቲያናችን፣ ስለ ሀገራችን፣ ሀብት ንብረታቸውን ቤተሰቦቻቸውን በአንድ ጀምበር አጥተው በዚህ ብርቱ ክረምት በሀዘን እና በረሀብ ተቆራምደው በየቤተክርስቲያኑ እና በየጎዳናው ተጠልለው ያሉ ወገኖቻችንን፣ ነፍስ እና ሥጋችንን፣ መንፈሳዊ ህይወታችንን እያሰብን እያለቀስን እና እየሰገድን ምህረት እየለመንን እንድንጠቀምበት እመብርሃን ትርዳን* :: ✝️ *በቀጣዩ መንፈሳዊ ምክር በዚሁ ገጽ የምንገናኘው እግዚአብሔር አምላክ በሰላም ቢያደርሰን ሱባኤው ሲጠናቀቅ ይሆናል:: በሱባኤው ወቅት ሁሉ ዘአክሎግ እያላችሁ ታናሽ ወንድማችሁን በጸሎታችሁ አስቡኝ:: ሁላችንንም በሰላም ያድርሰን::* ✝️ *መልካም ጾመ ፍልሰታ ✝️*
Показати все...
ክርስቲያን እና ፈተና በመ/ር ምህረተአብ አሰፋ ክፍል አንድ #share ╭══•|❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╮ ✥ 💚 @orthodox_sebket 💚 ✥ ✥ 💛 @orthodox_sebket 💛 ✥ ✥ ❤️ @orthodox_sebket ❤️ ✥ ╰══•❀:✧๑✞✞๑✧❀|:══╯ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Показати все...
ክርስቲያን_እና_ፈተና_በመ_ር_ምህረተአብ_አሰፋ_ክፍል_አንድ_s4ZMIdhkKB8_139.m4a19.08 MB
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.