cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ቅዱስ ፋኑኤል አባቴ✝️✝️✝️⛪️⛪️⛪️ 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። የእግዚአብሔር ቤተሰቦች እዚህ ቻናል ላይ ስርዓትን የጠበቁ ትምህርቶች, መዝሙራት ከነዜማቸው, የስብከት video እና መንፈሳዊ ፎቶዎችን ያገኛሉ።

Більше
Рекламні дописи
694
Підписники
Немає даних24 години
+107 днів
+1630 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏
Показати все...
በዕቅበተ እምነት ጥንቃቄ የሚሹ ተግባራት (ከብርሃኑ አድማስ ጽሑፍ በምኅጻር የተወሰደ) -- 1.የዕቅበተ አምነትን ሁለት ዋና ዋና ጠባያት መረዳት፡- (1) ሃይማኖት/እምነት ከአምላክ የተገለጠ እውነት መሆኑን ተረድቶ ማጽናትና (2) በእምነት የደከሙትን/የሳቱትን ሰዎች ራሳን እንደ ደጉ ሳምራዊ አድርጎ በርኅራኄ ቁስላቸውን አክሞ ለማዳን መፋጠን ሁለቱ የቅበተ እምነት መሠረታውያን ጠባዕያት ናቸው፡፡ -- 2. በዕቅበተ እምነት ውስጥ የማይታለፉ ጉዳዮች፡- (1)ዐቂበ እምነት፡- የሃይማኖትን ምንነት በቤተ ክርስቲያናዊ አስተምህሮ ላይ ተመሥርቶ መግለጥና ያንን የሚቃወም ስሑት ትምህርት በየዘመናቱ ሲመጣ ትምህርቱ የአባቶች አለመሆኑን ማሳየት፡፡ (2)እውነት ላይ ማተኮር፡- ዐቃቤ እምነት ትኩረቱ እውነት እንጂ አሸናፊነት አይደለም፣ ትኩረቱ ወደተሳሳተው አስተምህሮ እንጂ ወደተሳሳተው ግለሰብ አይደለም- ልክ መድኃኒት በሽታን እንጂ በሽተኛን ለማጥቃት እንደማይሰጠው፡፡ (3)አሳማኝነት፡- ጭብጥ አቀራረጹና አቀራረቡ ሐሳብን ሊያስተላልፍና የተለያየ ዕውቀትና ግንዛቤ ላላላቸው ሰዎች ተደራሽና ሰዎች ሐሳቡን ሊጋሩት በሚችል መልኩ ሆኖ መቅረብ አለበት፡፡ (4)ክርክርን በተገቢው መንገድ ማቅረብ፡- የዕቅበተ እምነት ሥራ ዐላማው አማኞችን ከመጠራጠር መጠበቅና የሔዱትን መመለስ እንደመሆኑ መጠን አቀራረቡ የሚያቀርቡትን ጭብጥ መረዳት (understanding)ንና ተደራስያን ሊረዱ በሚችሉበት ቋንቋ የማቅረብ አቅምን፣ ያልተድበሰበሰ ውሳኔን (judgment)ና የሚሟገታቸውን ሐሳቦች ስሑትነት የሚያሳይና የሚያቀርበውን ሐሳብ ከትችት ያራቀ አጠይቆት(reasoning)ን ማማከል ይገባዋል፡፡ -- 3.የዕቅበተ እምነት ጸያፎች፡- (1)ሐሰተኛ ትርጉም መስጠት (Proselytism)፡- ማለትም የምንሞግተውን ሐሳብ ተሞጋቹ በሚለው ሳይሆን እኛ በሰጠነው ትርጉም ሰይሞ ምላሽ ለማዘጋጀት መሞከር፡፡ ለምሳሌ፡- ኦርቶዶክሳውያን እመቤታችንን እናከብራታለን እንጂ አናመልካትም፡፡ ተቃዋሚዎች ግን ማክበራችንን ማምለክ ብለው ተርጉመው የዕቅበተ እምነት ሥራ ሠራን ይላሉ፡፡ በእኛም ቤት ካቶሊካውያን እመቤታችንን ኃይል አርያማዊት ይላሉ የሚል ልማድ ያገነነው ስሑት አበባል አለ፡፡ ይኼ ሐሰተኛ ትርጉም መስጠት ይባላል፡፡ (2)ሥነ ልቡናዊ ርግጠኝነት (Psychological Certainity)፡- የሰማዕያን/አንባብያንን ድክመት ተጠቅሞ የማያውቁትን ሐሳብ ወይም ቋንቋ ከዐውድ ውጪ በመውሰድ ለማሳመን መሞከር ነው፡፡ ምሳሌ፡- ኦርቶዶክሳውያን ለሥዕል የምንሰጠውን ክብር ዘፀ.20፡4 ላይ ያለውን ‹‹የተቀረጸውን ምስል ለአንተ አታድርግ›› የሚል ጥቅስ ተጠቅሞ ቅዱሳት ሥዕላትን ጣዖት አድርጎና የጥቅሱ መተርጎሚያ አድርጎ መጠቀም፡፡ ያላነበቡትን እንዳነበቡ፣ የማያውቁትን ግእዝ ወይም እንግሊዝኛ ወይም ደግሞ ሌላ ቋቋ የሚያውቁ መስሎ ለማሳመን መሞከርም በሰማዒው/አንባቢው ላይ የሥነ ልቡና ርግጠኝነትን ፈጥሮ ለመቀሰጥ ሙከራ የሚደረግበት የዕቅበተ እምነት ጸያፍ ነው፡፡ (3)መንሸራተት (Deviation)፡- ከጭብጥ መሸሽ ወይም ጭብጥን ለራስ በሚመች መልኩ ቀርጾ መዳከር፡፡ (4)ከአመክንዮ በተቃርኖ መቆም (Logical fallacy)፡- ምንም እንኳ ነገረ ሃይማኖት ከአመክንዮ ባሻገር ቢሆንም አንድን የፍሬ ነገር መለኪያ ለተለያየ መደምደሚያ መጠቀም፡፡ ምሳሌ፡- ተሐድሶዎች የደቂቀ እስጢፋስ ገድላት ላይ መፍቀርያነ ገድል መስለው ሲያበቁ በሌሎች ቅዱሳን ላይ ሲሆን የምናውቀውንና እዚህ የማንናገረውን ጸያፍ አንደበት እንደሚጠቀሙት፡፡ (5)ሁሉን ጠልነት (Negativism)፡- የሚቃወሙት ሰው/ቡድን የተናገረውን ሁሉ በጅምላ ማነወር፡፡ አውንታዊ ምሳሌ ብንጠቅስ፡- መልአከ ብርሃን አድማሱ ምላሽ የጻፉላቸው ሰዎች ትክክለኛ ነገር ሲጽፉ እንዳላዩ አያልፉም፤ እዚህ ላይ ትክክል ነህ ይላሉ፣ ሁሉን ጠል ስላልሆኑ፡፡ (6)አድሏዊነት (Inclination/Bias)፡- በአንድ ስሕተት የሚያውቁትን ሰው እንደሚሳሳት አስቦ ሥራዎቹን ማየት ወይም በስሕተት የወደቁ ሰዎችን በአካባቢ ወይም በተማሩበት ት/ቤት ፈርጆ ‹‹ወትሮስ ከዚያ የወጡ!›› እያሉ መፈረጅ ጸያፍ ነው፡፡ -- ምንጭ፡- አድማሱ ጀንበሬ፡ ሕይወቱ ወሐተታ መጻሕፍቱ፣ 2011፣ ገጽ 12-39 (በምኅፃር ተጨምቆ የቀረበ፡፡)
Показати все...
ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት እልልታ ባለው ጸናጽል አመስግኑት። መዝ 150፡5
Показати все...
ድክመትህን እና ጥፋትህን የሚነግሩህን ሰዎቸ ቃላት እንደ ስድብ  ወይም እንደ ጸያፍ ቃል ለምን ትቆጥራለህ ? እንዲህ አይነት የተግሳጽ ቃላት አንተነትህን ለማስተካከል የተሰነዘሩ ገንቢ ቃላት እንደሆኑ አድርገህ ለምን  አትቆጥራቸውም ?
ስለነዚህ ቃላት ብለህ የምትቆጣና የምትበሳጭ ከሆንህ ግን ውዳሴን የምትሻና ሰዎች ሁሌ ስለ አንተ መልካም የሆነውን ብቻ እንዲናገሩልህ  የምትወድ ሰው ነህ ማለት ነው፡፡ ወንድሜ ሆይ! ሰዎች ሲገስጹህ ደስ ሊልህ  ይገባል። ይህ ለአንተ መልካም ነውና። ለምትጠባበቀው የዘላለም ሕይወት  ያነጥርሃል ያበቃሃልም፡፡ አንድ ሰው በወቀሰህ ጊዜ ምናልባት የዚያ ሰው ወቀሳ የእግዚአብሔር  ወቀሳ ሊሆን ስለሚችል አመስግነው፡፡ ለማለት የፈለኩት የሚወድህ  እግዚአብሔር ያን ሰው ወዳንተ ልኮ ሊመራህና ክፉ ሥራህን በመግለጥ  ዳግመኛ እንዳታደርገው ሊከለክልህ ወዶ ይሆናልና፡፡ ምናልባትም  እግዚአብሔር በቅርቡ ወይም ከብዙ ጊዜ በፊት ስለፈጸምካቸው ኃጢአቶች  በእነዚህ የዘለፋ ቃላት ሊቀጣህ ፈልጎ ይሆናል። ነቢዩ ዳዊት የስድብ ቃላትን  በሰማ ጊዜ በትህትና በመሆን እንዲህ ነበር ያለው፡፡ “እግዚአብሔር ዳዊትን  ስደበው ብሎ አዝዞታልና ይርገመኝ፡፡...” (2ኛ ሳሙ 16፥10) ስለዚህ አንድ ሰው ሲገስጽህ የቀደመ ኃጢአትህን በማስታወስ ከተግሳጽ  በላይ መሆን የማትችልና ብቃት የሚጎድልህ ሰው መሆንህን አስብ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር በአንተ አድሮ የተዋጣለት ሥራ ይሠራል  አንተ ግን ይህን ራሰህን ለማመጻደቅና ለማጽደቅ ዓይነተኛ መሣሪያ አድርገህ  ትጠቀምበታለህ፡፡ በዚህ ጊዜ ይህ ትዕቢትህና ኩራትህ ለውድቀት  እንዳይዳርግህ እግዚአብሔር እርሱ በፈቀደ አንድ የሚዘልፍህ ሰው  ይልክብሃል፡፡ ይህ ኩራትና ትዕቢትህን በመጠኑም ቢሆን በመቅረፍ በቆይታ  ሊያስተካክልህ ይችላል።  እንዲህ ያሉት የተግሳጽ ቃላት ፍቅርና መታገስን  ስለሚያስተምሩህ ላንተ ትምህርት ነውና ደስ ይበልህ፡፡ #ለሌሎች_ሼር_ማድረግ_አትዘንጉ 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏
Показати все...
"ማንነትህን ማወቅ" ተወዳጁ ወንድሜ ሆይ! ኃይለኛ ነኝ ብለህ ታስባለህን? ካሰብህ ይህን ኃይልህን ከየት አመጣኸው? አንተ አመድና ትቢያ ጎስቋላና ምስኪን ስለሆንህ ይህ ኃይል የአንተ አይደለም። ይህ ኃይል ከሌላ ሰው ያገኘኸውም አይደለም ከእግዚአብሔር እንጂ። ክብርና ምሥጋና ለእርሱ ይሁንና ኃያል እርሱ ብቻ ነው፡ ኃይልም ሁሉ የሚገኘው ከእርሱ ብቻ ነው። ያንተስ ኃይል ከእግዚአብሔር አይደለምን? ከሆነ ለምን ትታበያለህ? ለምንስ ትኩራራለህ? የእግዚአብሔርንስ ኃይል እርሱን ለማገልገል ካልሆነ ለሌላ ለምን ታውለዋለህ? ስለዚህ ሊከበር የሚፈልግ ቢኖር በእግዚአብሔር ይክበር። እርሱ ከክብር ሁሉ በላይ የሆነና ለምንከብርበት ነገር ሁሉ ምንጩ ነውና። በእግዚአብሔር ኃይለኛ ሆነህ በተፈጥሮህ ደካማ ብትሆን ከሐዋርያው ከቅዱስ ጳውሎስ ጋር እንዲህ በል። "እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ። ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና።" 2ኛ ቆሮ 12:9-10 (ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ) 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏
Показати все...
#ግንቦት_26 ዝ ክ ረ - ቅ ዱ ሳ ን በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ : አሐዱ አምላክ . . . አሜን። 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 እንኳን ለታላቁ ጻድቅ አቡነ ሃብተ ማርያም አመታዊ ክበረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 ✞ አቡነ ሃብተ ማርያም ጻድቅ ✞ እኒህ ጻድቅ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው። "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው። ባሕር ከሆነ ጣዕመ ሕይወታቸው ጥቂቱን ለበረከት እንካፈል። ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ : እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች። በተለይ ቅድስት ዮስቴና እጅግ ደመ ግቡ : ምጽዋትን ወዳጅ : ቡርክት ሴት ነበረች። እንዲያውም ከጻድቁ መወለድ በፊት መንና ጭው ካለ በርሃ ገብታ ነበር። ግን የበቃ ግኁስ አግኝቷት "ከማሕጸንሽ ደግ የሥላሴ ባርያ አለና ተመለሽ" ብሏት እንደ ገና ተመልሳለች። ጻድቁን ወልዳ አሳድጋም እንደ ገና መንና በተጋድሎ ኑራ 7 አክሊላትን ተቀብላ ዐርፋለች። ወደ ጻድቁ ዜና ሕይወት ስንመለስ አቡነ ሃብተ ማርያም ገና ሕጻን እያሉ ከእናታቸው ጋር ቆመው ሲያስቀድሱ "እግዚኦ መሐረነ ክርስቶስ" ሲባል ይሰማሉ። ይሕችን ጸሎት በሕጻን አንደበታቸው ይዘው ሌሊት ሌሊት እየተነሱ "ማረን እባክህን?" እያሉ ይሰግዱ ነበር። የ5 ዓመት ሕጻን እንዲህ ሲያደርግ ማየቱ በእውነት ይደንቃል። ትንሽ ከፍ ብለው በእረኝነት ሳሉም ፍጹም ተሐራሚና ጸዋሚ ነበሩ። ጸጋው ስለ በዛላቸውም ልጅ ሆነው ብዙ ተአምራትን ሰርተዋል። የፈጣሪውን ስም ያቃለውን አንድ እረኛም በዓየር ላይ ሰቅለው አውለውታል። ከዚያ ግን ለአካለ መጠን ሲደርሱ ወደ ት/ቤት ገብተው : መጻሕፍትንም አጥንተው መንነዋል። በአባ መልከ ጼዴቅ እጅ ከመነኮሱ በሁዋላ የሠሩትን ትሩፋትና የነበራቸውን ተጋድሎ ግን የኔ ብጤ ደካማ ሰው ሊዘረዝረው አይችልም። ➠ ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ። ➠ በየቀኑ 4ቱን ወንጌልና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ። (መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ታላቅ ጸሎት ነው) ➠ በ40 ቀናት : ቀጥሎም በ80 ቀን አንዴ ብቻ ይመገባሉ። ➠ ምግባቸው ደግሞ ሣርና ቅጠል ብቻ ነው። ➠ በየዕለቱ ያለ ማስታጐል ማዕጠንት ያሳርጋሉ። (ካህን ናቸውና) ➠ ዘወትር በንጽሕና ቅዱስ ሥጋውን ይበላሉ : ክቡር ደሙን ይጠጣሉ። ➠ በፍጹም በልባቸው ውስጥ ቂምን : መከፋትን አላሳደሩም። በእነዚህና በሌሎች ትሩፋቶቻቸው ደስ የተሰኘ ጌታም ለጻድቁ የእሳትና የብርሃን ሠረገላን ሰጥቷቸው በዚያ እየበረሩ ኢየሩሳሌም ይሔዱ ነበር። ከብዙ የተጋድሎ ዘመናት በሁዋላም የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አዕላፍ መላእክትን አስከተትሎ መጥቶ አላቸው። "1.ስለ እኔ ረሃብና ጥምን ስለ ታገስክ: 2.ስለ ምናኔሕ: 3.ስለ ተባረከ ምንኩስናህ: 4.ስለ ንጹሕ ድንግልናህ: 5.ቂምና በቀልን ስላለመያዝህ: 6.ስለ ንጹሕ ክህነትህና ማዕጠንትህ: 7.ቅዱስ ወንጌልን በፍቅር ስለ ማንበብህ 7 አክሊላትን እሰጥሃለሁ።" "በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጐን : 500 የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ። በስምህ የሚለምኑ : በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው። ቅዱሳን መላእክትም "ሃብተ ማርያም ወንድማችን" ሲሉ አቀፏቸው። ጌታ ግን በዚያች ሰዓት አንድም ሦስትም ሆኖ ታያቸውና አቅፎ 3 ጊዜ ሳማቸው። ከፍቅሩ ጽናትም የተነሳ ነፍሳቸው ከሥጋቸው ተለየች። በዝማሬም ወሰዷት። {ይህች ቀን (ግንቦት 26) ለጻድቁ ዕለተ ልደታቸው ናት።} አምላከ አበው ወሰማዕት ጣዕመ ፍቅራቸውን: ክብራቸውን: ጸጋ በረከታቸውንም ይክፈለን። --------------------------------------------- "እግዚአብሔር ፍርድን ይወድዳልና። ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና። ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል . . . ጻድቃን ምድርን ይወርሳሉ። በእርስዋም ለዘላለም ይኖራሉ። የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል። አንደበቱም ፍርድን ይናገራል። የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው። በእርምጃውም አይሰናከልም።" (መዝ. 36:28-31) <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>> #ስንክሳር_ዘወርሃ_ህዳር ለወዳጅዎ ያካፍሉ!! @Tsehaye_Tsidk @Tsehaye_Tsidk
Показати все...
1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏
Показати все...
👍 1
“ክርስቲያን” ተብለህ መጠራትህ ዋስትና አይኾንህም፤ ዋስትና የሚኾንህ … በመንገድ ዳር ላይ ዘርን የሚዘሩ ሰዎች ምንም የሚያገኙት ጥቅም እንደ ሌለ ኹሉ፥ እኛም ለልጅነታችን የሚገባ’ ምግባር ከሌለን ክርስቲያኖች ተብለን ከመጠራት የምናገኘው በቁዔት የለም፡፡ ይህ እንዴት ይኾናል የምትለኝ ከኾነም የጌታችን ወንድም የተባለው ያዕቆብን ምስክር አድርጌ እነግርሃለሁ፡፡ እርሱ፡- “ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው” ብሎአልና (ያዕ.2፡17)፡፡ ስለዚህ ለእኛ (ለክርስቲያኖች) ምግባር መያዝ ግዴታ ነው፡፡ ምግባር ከሌለን ግን “ክርስቲያን” የሚለው ስም ለእኛ የሚፈይደው ምንም ነገር የለም፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እንኪያስ ንገረኝ ! በዓውደ ውጊያ የማይሳተፍ፣ ለሚመግበው ንጉሥም የማይዋጋ ከኾነ አንድ ወታደር ወታደር ተብሎ ቢጠራ ምን ጥቅም አለው? ለንጉሡ ክብር የማይዋጋ ከኾነስ ወታደር ተብሎ ባይጠራ ይሻለዋል፡፡ ይህ ሰው በንጉሡ የሚመገብ ኾኖ እያለ፥ ነገር ግን ንጉሡ በጠላቱ ላይ ድል እንዲያደርግ የማይዋጋ ከኾነ እንዴት ከቅጣት ሊያመልጥ ይችላል? ንጉሡን ምሳሌ አድርጌ ልናገረው የፈለግሁትስ ምንድን ነው? ልለው የፈልገሁት እግዚአብሔር በትንሹ ስለ ገዛ ነፍሳችን እንድንጠነቀቅ (ምግባር መያዝ እንድንችል) ኃይል (ዓቅም) ሰጥቶናል ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ንስሐና ምጽዋት መጽሐፍ #ይቀላቀሉ 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏
Показати все...
ተወዳጆች ሆይ አንድ የልብ ምክር አለኝና አድምጡኝ፦ ወዳጄ የቤተሰብ ሓላፊ ከሆንህ፡- እኔ ለቤተሰቤ እንደ ኢዮብ ካህን ነኝ ስለዚህ በመንፈስ ሁል ጊዜ፤ በአካል ደግሞ እንደ ችሎታዬ መጠን ስለራሴ ምክንያቱም በመልካም ማስተዋል ቤተሰቤን እመራ ዘንድ ስለቤተሰቤ ምክንያቱም ቤተሰቤ በኃጢአት ምክንያት አእምሮው እንዳይቆሽሽ በራስ መተማመን እንዳያጣ በማስተዋልና እግዚአብሔርን በመፍራት እንዲመላለሱ ስለሀገሬ ሰዎች ደግሞ በሰላም ወጥተው በሰላም እንዲገቡ ማስተዋልንና እርስ በእርስ መግባባትን እንዲሰጣቸው ፍቅር እንድትነግሥ ስለዓለሙ ሁሉ ደግሞ “ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን” እንድንል ጌታ እንዳስተማረን የምንኖርባት ዓለም ፈቃዱን ለማድረግ እንደሚተጉ መላእክት ለመልካም ሥራ እንዲበረቱ በጸሎት መትጋት አለብኝ ብለህ ለልብህ ንገረው፡፡ ለቤተሰባቸው እማወራ ለሆኑ እናቶችና ሚስቶች ደግሞ ለልባቸው እንዲህ ብለው ይንገሩ፡- እኔ ለቤተሰቤ አካሉ ነኝ፡፡ በእርግጥም ባለቤቴ ራሴ ነው እኔም አካሉ ነኝ ልጆቼም ከእኔ የወጡ የአካሌ ክፋዮች ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ሳራን “ካንቺ ሕዝብና አሕዛብ ይወጣሉ” እንደተባለች ከእኔ ማኅበረሱ ተገኝቶአል ይገኛልም፡፡ እኔ ለማኅበረሰቡ ፣ እንደ ሀገር ለሚቆጠረው ሕዝብና ለዓለሙ ሁሉ እንደ መሠረት ነኝ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ “ቡሆው ቅዱስ ከሆነ ሊጡም ቅዱስ ይሆናል” እንዲል የእኔ ቅድስና ለእነርሱ ቅድስና መሠረት ነው፡፡ ይህን ሁሌም ላስበው ይገባል ትበል፡፡ ሁሌም ይህን አስቤ እንደ ተምሳሌቴ እንደ ቤተ ክርስቲያን ማስተዋልን ያድለኝ ዘንድ ስለሀገሬ ስለ ዓለሙ ሁሉ ሰላም በመንፈስ ሁልጊዜ ፤ በአካል እንደ ችሎታዬ መጠን በጸሎትና ራሴን በማስተዋል ለማነጽ ልተጋ ይገባኛል ትበል፡፡ ልጅም እንደ ክርስቶስ በመንፈስም በአካልም በጥበብም በእግዚአብሔርም በሰው ፊት ሊያድግ እንዲገባው ዘወትር ያስብ የእርሱ ወጣትነት ዘመን ክርስቶስ ዓለምን ለማስተማር በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት የተመላለሰበት ዘመን እንደሆነ ያስብ፡፡ ስለዚህም ሰውነቱን በኃጢአት ሳይተደደፍ ወጣትነቱን በንጽሕና ይጠብቃት ዘንድ ክርስቶስን ማወቅ ከቅዱሳን ጋር ማኅበርተኛ መሆንን ሊለማመድ እንደሚገባው ቆጥሮ በጸሎትም በምንባብም በተመስጦም ሊተጋ እንዲገባው ለልቡ ይንገረው፡፡ ሁሉ ነገር ከራስ ሲጀመር እጅግ መልካም ነው፡፡ የቅድስና መንገዱም ይህ ነው፡፡ ጌታስ ቢሆን ያስተማረው ይሄንኑ አይደለምን? አንተ ግብዝ አስቀድመህ በዓይንህ ውስጥ ያለውን ግንድ አውጣ በኋላ የወንድምህን ጉድፍ ማየት ይቻልሃል” ብሎ አላስተማረንምን? ወገኖቼ በጸሎት አንዳችንለአንዳችን እንትጋ፡፡ (ከዲ/ን ሽመልስ መርጊያ) 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏 🙏@fanuel333🙏
Показати все...