uk
Feedback
ዳዊት ጌታቸው።(እይታ)

ዳዊት ጌታቸው።(እይታ)

Відкрити в Telegram

ፍቅር!ሰላም!ግጥም!እይታ! sad! ለ አስተያየት @addemiinilik

Показати більше
452
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
እንባዬ እንደ አዋሽ.... በዚ ለጋ እድሜዬ... አራት ግዜ አነባዉ ፅና ትከሻዬ!! ሳንቀላፋ ነበር ብዬ ሀገር አማን መርዶዋን ስሰማ የብኩኗ እናቴን (የካቲት 12፣አለቀስኩ፣ለቅሶ አንድ) እሷን በማጣቱ ጉልበቱ እንደ ጤዛ በማለዳ ተኖ እርፍ መጨበጡ ዛሬ ታሪክ ሆኖ ናፍቆት አብሰልስሎ እንደ ጤፍ ቢወቃው አባቴም ተረታ ሞትን ተዳበለው!! ባለእንጀራ ሆነው!! (እዩዋቸው አብረው እሳት ሲሞቁ) (ግንቦት 20 አነባው ሁለተኛው ለቅሶ) በ እንባዪ ብዛት ለራሴ አዝኜ ሙሾዬ ቢበዛ ፀሎቴ ቢረሳ ፈጣሪን ለምኜ... (መጋቢት24...ሶስተኛው እዬዬ) ወንድም በጠፋበት በዚ ጥቁር ዘመን እንደ እህቴ ሳይሽ የገዛ ፎቶዬን ሊያውም ከንፈሩ ለይ ስትስሚ አየውሽ.... ቅስሜን ሰበርሽው (ዛሬ፥አሁን...አራተኛው ለቅሶ) @addemiinilik ዳዊት ጌታቸው✍️✍️✍️

አሪፍ ግጥም እየመጣ ነው ግማሹ አልቋል😂

RED8 ትችላለህ
RED8 ትችላለህ

እኔን መሳይ እንዴት መጣች ወደዚ አለም?? እኔን መሳይ ልትሸለም!! ልሆንላት ሜዳሊያ🥇 ልጠልቅ ነው ከሷ ጉያ... ለየቱ ታቦት ብታለቅሽ ከ እጅሽ ጣለኝ እንደ ሻሽ?! ሸብ አድርጊኝ ልጠርሽ እንኳን መጣሽ እልል እልል ሞገስ ሆንሽኝ እንድሸልል 💪 እንደ ዘበት ቶሞቦላ ፋቅሽ 1ኛ እጣ ወጣሁልሽ😂 ቆፍጣና ነኝ የማልፈራ! ጠበቅ አርጊኝ እንደ ስራ ይመኙኛል በ ሆዳቸው ምን ዋጋ አለው ቀደምሻቸው። ሰምሯል ሆዴ ስለትሽ ስጠኝ አልሽው ያው ሰጠሽ... ...እኔን መሳይ... @addemiinilik ዳዊት ጌታቸው

ረቂቅ ሙዚቃ ነበር የምትፈትለው...ያረጋጋል ሰላም ይሰጣል መንኩሱ መንኩሱ ያሰኛል..#እማሆይ_ፅጌ_ማርያም_ገብሩ ምት አይቀርም እና አረፈች!!! ሳትሞት በፊት ግን በተወሰኑ ስራዎቿ ስራዎቼን አጅቤ ነበር!!አመሠግናለው!!!

አንዲት ወዳዴ ለ ፍቅረኛዋ ሁለት ስንኝ ግጥም እንድፅፍላት ጠየቀችኝ ከዛ...... መስፈርት አልነበረም አንተን ያስመረጠኝ እግዜሩ ነው እንጂ መልአክ ውደጅ ያለኝ:: አልኳት።ለ ፍቅረኛችሁ ለባሎቻችሁ share በማድረግ አበርቱአቸው!!!! @addemiinilik ዳዊት ጌታቸው

Repost from N/a
የፖላንድ መንግስት ሙሉ ወጪዎችን ሸፍኖ ያቀረበው እና ያለምንም ክፍያ ራሳችሁ በነፃ ማመልከት የምትችሉት የስኮላርሺፕ እድል ሌሎች በነፃ ራሳችሁ ማመልከት የምትችሉትን ስኮላርሺፖች እድሎች ለማግኘት የ
የፖላንድ መንግስት ሙሉ ወጪዎችን ሸፍኖ ያቀረበው እና ያለምንም ክፍያ ራሳችሁ በነፃ ማመልከት የምትችሉት የስኮላርሺፕ እድል ሌሎች በነፃ ራሳችሁ ማመልከት የምትችሉትን ስኮላርሺፖች እድሎች ለማግኘት የቴሌግራም ቻናላችንን @edmap_community ይቀላቀሉ። #Betty🦋 | #13

በጣም አሪፍ የምላትን 1ገፅ ከወደድኩት መፅሀፍ ለይ በ ድምፅ የማንበብ ዘመቻ ልጀምር ነው

እንዲህ ስል አሰብሁ.... ህይወት ሰለሜ ሰለሜ ናት ግና ገራፊም ተገራፊም መሆን በእኛ እጅ ነው። ተገራፊ ከሆንህ ቢያንስ ከ ገራፊው ሁዋላ ሁን...ገራፊውን ማሸነፍ ባትችል እንኳ የሞተ ቀን ተተኪው አንተ ነህ...

ልክ የለው ለማሰብ አይበጅለት ኬላ የማፈቅርሽ እኔ ምታፈቅሪው ሌላ። ስቃይ ነው.... መኖር እያለሙ የፍቅርን ወጋገን ፍሬ አልባ ቅዠት ፍቅር ካንድ ወገን። ዮኒ ኣታን @yonatoz Share @Yonny_Athan Share @Yonny_Athan

ወደ ቻናላችን አዲስ የምትቀላቀሉ ወገኖች ከላይ ጀምራችሁ ስራዎችን ተከታተሉ go to the first message

ለ ሙስሊም ወገኖች እና ወዳጆቼ ህይወት ተደራርቦ ከ ግራዋ ቢመር በፆማችሁ ብቻ ይጣፍጥ እንደ ቴምር በ አላህ ተአምር!! ችግሮች ይለፉ እንደ አምና ካቻምና የ ጎበጠው ሁሉ በ ፀሎት ይቃና ፆማችሁን ያርገው ፀሀይ የበራበት መቀበያችሁ ነው የ ጀነትን ትኬት አፍጥርን ጠብቆ ይንኳኳ ደጃፌ ግብዣ ይዝነብብኝ ልግባ ተደግፌ (በ ጥጋብ)😂 @addeiinmilik ዳዊት ጌታቸው 24 ሰአት የ ቴምር ሾርባ እና የ ኩኪስ gift ለመቀበል ዝግጁ ነኝ😂

ለምን ብለሽ ተጨብጠሽ ኩርምት ከፋ እኔን ስሚኝ ቀን ሲከፋ እኔን ሳሚኝ ሌት ሲያካፋ እቅፍ አርጊኝ ተሸሸጊኝ አለሁልሽ እኔ ወንዱ ሰው መሀል ነው ሰው መንገዱ ተጠምጠሚ እንደጋቢ ተጣበቂ ተቃቀፊኝ ቆዳዬንም ሂጅ እለፊኝ ተሰተሪ እንደአጥር ክትት በይ እንደሚስጥር ኤልያስ ሽታኹን

ግጥሜን post ሳደርግ ጥቂት ሰው ነው የሚያይልኝ።የራሴን ፎቶ post ሳደርግ ግን ብዙ ሰው ያደንቀዋል አለች በቅሬታ። ያው ካንቺ ግጥም የእግዜሩ ግጥም ስለሚሻል ይሆናላ.... @redietassefa T.me/yefkrgtmdawit

ስታወሩልኝ ፊቴን ወደ እናንተ እያዞራቹ አገጬን እየጠመዘዛቹ አታውሩልኝ እኔ እሰማቹአለው በቃ ሳትነኩኝ አውሩ😁

መኖር ሊከብድ ይችላል ግን ከመሞት አይብስም። @addemiinilik ዳዊት ጌታቸው

የእናት ውለታዋን ላወሳ ወዳለው:- ትውለድ መንታ መንታ ሳትሰለች እናት ላግባ መንታ መንታ ወኔዬ ሳይታክት ቆንጆ እንደ ሹሩባ ከ ጀርባዋ ትደር ስታድግ ሚስቴ ናት በተስፋ አለም ልኑር የእናት ውለታዋን ላወሳ ወዳለው!!! @addemiinilik ዳዊት ጌታቸው!!