924
Підписники
Немає даних24 години
+57 днів
+930 днів
Архів дописів
የጨረቃ ግርዶሹን እየተመለከቱ ነው?
በኢትዮጵያ ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽ እየታየ ነው።
ዛሬ ከምሽቱ 12፡28 መሬት ጨረቃን መከለል ስትጀምር ጀምሮ ግርዶሽ መታየት ጀምሯል።
ከምሽቱ 2፡30 ላይ ተጠባቂው ሙሉ የጨረቃ ግርዶሽን ወይም ጨረቃ ደም የምትመስልበት ሰዓት መሆኑን የሥነ ፈለግ ባለሙያ መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር) ተናግረዋል።
ግርዶሹ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ በአፍሪካ፤ አውስትራሊያ እና እስያ የተወሰኑ አካባቢዎች እንደሚታይ ይጠበቃል።
#ኢቢሲ
ቢቢሲ የሕዳሴ ግድብን ግዙፍነት እንዴት ገለጸው?
ቢቢሲ ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግዙፍነት በገለጸበት ዘገባው፣ “ኢትዮጵያ በአፍሪካ በግዙፍነቱ ቀዳሚ የሆነውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድቧን በያዝነው የፈረንጆቹ መስከረም ወር ታስመርቃለች” ብሏል።
በዓባይ ወንዝ ላይ በ4.6 ቢሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከ5 ሺህ በላይ ሜጋ ዋት ኃይል እንደሚያመነጭም ጠቁሟል።
በንፅፅር ሲያስቀምጠውም፣ የግብጹ አስዋን ግድብ እና የአሜሪካው ሁቨር ግድብ ከሚያመነጩት ኃይል ከእጥፍ በላይ የማመንጨት አቅም እንዳለውም ጠቅሷል።
በዘገባው ‘ዊቢዩልድ ግሩፕ’ን ጠቅሶ ስለግድቡ የሚገልፁ የኢንፎግራፊክስ ቁጥራዊ መረጃዎች አስቀምጧል።
5 ሺህ 150 ሜጋ ዋት ኃይል እንዲያመነጭ ሆኖ የተገነባ፤ በዓመት 15 ሺህ 700 ጊጋዋት ሰዓት በአማካይ የሚያመነጭ እንዲሁም 74 ቢሊዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ የያዘ መሆኑንም አመላክቷል።
13 ተርባይኖች እንዳሉት፣ ቁመቱ 170 ሜትር፣ ርዝመቱ 1.8 ኪሎ ሜትር እንደሆነ ነው ቢቢሲ በዘገባው የጠቀሰው።
የግድቡን ውኃ የያዘው ንጋት ሐይቅ 246 ኪሎ ሜትር ርዝመት እንዳለው ቢቢሲ በቁጥራዊ መረጃዎቹ ውስጥ አካትቷል።
ኢትዮጵያውን ቦንድ በመግዛት እና በስጦታ መልክ ከ2.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ማዋጣታቸውን፣ የግድቡን ግንባታ ለማጠናቀቅ 14 ዓመታት መውሰዱን እንዲሁም በየዓመቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በግንባታው ላይ መሳተፋቸውንም ቁጥራዊ መረጃው ያሳያል።
ኢትዮጵያ ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ በየዓመቱ አንድ ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደምታገኝ ይጠበቃል።
ግድብ ታዳሽ ኃይልን የሚጠቀም በመሆኑ በዓመት ሁለት ሚሊዮን ቶን ካርቦን ዳይኦክሳይድ ወደ ከባቢ አየር እንዳይገባ ያደርጋል።
#EBC #ebcdotstream #GERD #largestdaminafrica #resilience
ጳጉሜ 01/2017 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባር ተጠናክሮ እንደቀጠለ ይገኛል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በዛሬው ዕለት የወረዳው የክረምት በጎ ፍቃድ አብይ ኮሚቴ አባላት በወረዳው ጅማ፣አስፈዲን እና ከንትዋት ቀበሌዎች በመገኘት እየተገነቡ ለሚገኙ የአቅመ ደካማና የዘማች ቤተሠብ ቤቶች 120 ቆርቆሮና 9 ፓኬት ሚስማር ድጋፍ አድርገዋል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የብልፅግና ፓርቲ ፅ/ቤት የፓለቲካ እና የአቅም ግንባታ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ሚፍታ አረቦ የቤት ቆርቆሮ ድጋፍ ባደረጉት ወቅት እንደተናገሩት የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት በሁሉም ቀበሌ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀው ተግባሩ አብሮነታችን የሚያጠናክር የህሊና እርካታ የሚያስገኝ ስው ተኮር ተግባር ነው ብለዋል።
ይህንን በጎ ተግባር የሚያስተባብሩ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት እገዛቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ አቶ ሚፍታ አሳስበዋል።
በድጋፉ ወቅት የተገኙት የወረዳው ሚሊሻ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አምዲሳ ከበደ የጅማ ቀበሌ ለሚገኙ የመኖሪያ ቤት ችግር ውስጥ ለነበሩ ለአንድ የዘማች ቤተሰብ ድጋፍ መደረጉን ገልጸው ሀገር በደሙና በላቡ ሌትተቀን ያለ እረፍት እየጠበቀና እያጸና ላለው ለሀገር መከላከያ ቤተሰብ የማገዝና የመንከባከብ የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት አንዱ ዘርፍ በማድረግ በወረዳችን በርካታ ስራዎች እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሸምሱ ኢብራሂም በበኩላቸው በወረዳው የክረምት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተግባር በሁሉም ዘርፍ ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸው በዛሬው እለት በወረዳው ጅማ፣አስፈዲን እና ከንትዋት ቀበሌዎች በመገኘት ለአቅመ ደካሞችና ለዘማች ቤተሠብ ግማታቸው 107 ሺህ ብር በላይ የሚገመት 120 የቆርቆሮ እና 9 ፓኬት ሚስማር ድጋፍ መደረጎን አስታውቀዋል።
ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ
"ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር በተሻገረ ህልም፣ በላቀ ትጋት፣ አስተማማኝ ነገን መስራት! በሚል መሪ ቃል ባለፉት የለውጥ ዓመታት ድሎችና እና ቀጣይ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገው በየማህበራዊ መሠረቱ ለሚገኙ ለብልፅግና ፓርቲ ህብረት አባላት ለሁለት ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በኮንፍረንስ በማካሄድ በዛሬው እለት ተጠናቀቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በስልጠናው ምጠቃለያ ወቅት የተለያዩ የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ስራዎች የአረጋዊያን ቤት መገንባትና እድሳት፣ለወላጅ ህጻናት ዩኒፎርም እና ደብተር ማሰባሰብ፣ለአቅመ ደካሞች ገንዘብ የመሰብሰብ ስራዎች ተሠርተዋል።
ናሴ 29 2 ክም 17 ኢ/ዘማን
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረደ
ተታገዞት አሙርቶት ቢላን ቡር ሁስብ በመንግስት ክትበት ጋርቸ ጋሬረ በመኸር ከስብ ስርም በሬደኮ ፋረ ርኸቦት ተቻላን።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በወረዳይ ፈረንክ ክትበት ጋር ጋሬረ የኧበሩዪ ቱመ፣ቲማቲም፣ሹንኩርት ገናም ገናም ግዝቸ ወ ቦቆሎ የከተመ ግብርነ ስርም ያኦምሳን።
የከተመ ግብርነ የንብር ጩምነት ላስክኖት የገደረ ፋረ ያለይ ለዎነዬት ክትበት ጋርቸ በጋሬረኒም ባለይም ጎፍ ደቼ ፈየኮ ቁመርወ ቢያኙ ስርም በሬደኮ የንብር ጩምነቲ ጥወሮት ያኧትሉዋን።
ተወክቼ ወክቼ ቲደብል ዪመጫነይ የንብር ጩምነት ላኧኖት ወ እነምኮንገ ለከተማይ ሰብ ወ ለመንግስት ብለተኜነይ የገደረ ፋረ ላለዬት ፈየኮ ኪስቦት ያትኬሻን።
