917
Підписники
Немає даних24 години
+27 днів
+930 днів
Архів дописів
የሳምንቱ አበይት ዜናዎች
ታህሳስ 26/2018 ዓ.ም
🎤 በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረደ በጅመ ወለኔ ከተመ በኡን ኢንቨስትመነት ዘርፍ ታቶትከ የትፈጄ ፔንሲዮን።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት የመሀል አምባ የስራ ማዕከል ከፌደራል ስራና ክህሎት ሚኒስቴር በመጡ ከፍተኛ ኤክስፐርቶች የስራ ማእከሉ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ምልከታና ድጋፍና ክትትል ተደረገለት።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 ገዥ ትርክት ሀገራዊ ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ለማጠናከር አይነተኛ መሳሪያ መሆኑን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ክንፍ ጽ/ቤት አስታወቀ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 በጉራጌ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርት ውድድር ሻምፒዮና በስድስት የስፖርት አይነቶች እየተሳተፈ የሚገኘው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ እስካሁን በተደረጉ ውድድሮች በተለያዩ የስፖርት አይነቶች 7 ሜዳሊያዎችን ማግኘት ችሏል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የጉራጌ ዞን ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ቡድን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌያት ድጋፍና ክትትል አደረጉ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 በትምህርት ዘርፋ ያጋጠመንን የውጤት ስብራት በተቀናጀና በተባበረ መንገድ መጠገን ይገባል ሲሉ
የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ መብራቴ ወ/ማርያም ገለጹ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
🎤 በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በሙስሊም ኤይድ ዩ ኤስ ኤ እና በኬር ዘንጊ ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ድርጅት የተገነባው የአበልታ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማስፋፈያ ፕሮጀክት ተመረቀ።
ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረደ በጅመ ወለኔ ከተመ በኡን ኢንቨስትመነት ዘርፍ ታቶትከ የትፈጄ ፔንሲዮን።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረደ በጅመ ወለኔ ከተመ በኡን ኢንቨስትመንት ዎገን የታተ የትፈጄ ፔንሲዮን ቢቢ እንግር ላኞት የጄጄኮ የወዳን።
በኡን ኢንቨስትማነት ዘርፍ የትረሼ ፔንሲዮን የከተማይ ሊኦት ባቢዦትወ የገደረ ጥኧሞት ይነብሪያንኮ ይጥቄራን።
ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ደነብ ቀበሌ የለማ በርበሬ ምርት አሰባሰብ በምስል በከፊሉ፦
ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም
በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት የመሀል አምባ የስራ ማዕከል ከፌደራል ስራና ክህሎት ሚኒስቴር በመጡ ከፍተኛ ኤክስፐርቶች የስራ ማእከሉ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ምልከታና ድጋፍና ክትትል ተደረገለት።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በድጋፍና ክትትሉ በቀጣይ በዘርፉ በሚሰሩ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ወይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ተችሏል።
በወረዳ ደረጃ ያገኘነውን እድል በአግባቡ በመጠቀም የሚታይና ውጤታማ እንደሚሰራ ጽ/ቤቱ አክሎ ገልጿል።
ይህንን እድል እንድናገኝ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ላደረጉ
የክልል እና የዞን የስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ተቋማት በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ስራ እድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ስም ምስጋና አቅረቧል።
ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርት ውድድር ሻምፒዮና
ዛሬም ቀጥሎ ተካሄዷል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርት ውድድር ሻምፒዮና በ6 የስፖርት አይነቶች እየተሳተፈ የሚገኘው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ስፖርት ልዑክ እስካሁን በተደረጉ ውድድሮች በተለያዩ የስፖርት አይነቶች 12 ሜዳሊያዎችን ማስመዝገብ ችሏል።
@ ዛሬ በተደረገ ውድድር በአትሌቲክስ አራት መቶ ሜትር ዱላ ቅብብል ሩጫ ጋሊብ አ/መጅድ፣ ሱአሊ ካሳ፣መሀመድ በሽር እና በታዬ አስፋ የነሀስ ሜዳልያ
@ በአሎሎ ውርወራ አብድረሂም ባልቻ የብር ሜዳልያ
@ በጠረፔዛ ቴነስ በግል ይስሃቅ ብርሀኑ የነሀስ ሜዳልያ እና በጠርፔዛ ቴነስ በግሩፕ መንሱር ብርሀኑ፣ ይስሃቅ ብርሀኑ፣ አህመድ መሀመድ አማካኝነት የነሀስ ሜዳልያ ማስመዝገብ የተቻለ ሲሆን
በፓራሊምፒክ በእጅ ጉዳት 100 ሜትር ሩጫ በሳዳም ሰኢድ የነሀስ ሜዳልያ ተመዝገቧል።
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ እስካሁን በተደረጉ ውድድሮች 5 የብር ሜዳልያ እና 7 የነሀስ ሜዳልያ በድምሩ 12 ሜዳልያዎች ማስመዝገብ ተችሏል።
ውድድሩ በነገው እለትም የሚቀጥል ሲሆን በወንዶች ቮሊቮል ከጠዋቱ 4:30 ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ከእዣ አቻው ጋር ይጫወታል።
መልካም እድል!!!
መረጃው የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ነው።
ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም
የጉራጌ ዞን ኢንስፔክሽንና ስነ-ምግባር ኮሚሽን ቡድን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የተለያዩ ቀበሌያት ድጋፍና ክትትል አካሄደ።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
የኢንስፔክሸንና ሱፐርቪዥን ቡድኑ በወረዳው ደነብ ቀበሌ እና አስዳደር ዘርፍ የብልጽግና ፓርቲ ህብረት እና ብልጽግና ፓርቲ ቤተሰብ የነበረውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ለወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ግብረ-መልስ ሰጥቷል።
የኢንስፔክሽን ቡድኑ የ2018 በጀት ዓመት ሁለተኛ ሩብ ዓመት የተከናወኑ የኢንስፔክሽንና የሥነ-ምግባር ኮሚሽን ተግባራትና የፓርቲ ተግባር ያሉበትን ደረጃ
እንዲሁም ደነብ ቀበሌ በመስኖ የተከናወኑ ተግባራት የመስክ ምልከታ በማድረግ በጥንካሬና በጉድለት ግብረ መልስ ሰጥቷል።
ታህሳስ 21/2018 ዓ.ም
የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ እግር ኳስ ቡድን ከ እኖር ወረዳ እግር ኳ ቡድን የመጀመሪያውን የምድብ ጫወታ ተጀምሯል።
መልካም እድል ለእግር ኳስ ቡድናችን!!!
ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም
በጉራጌ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርት ውድድር ሻምፒዮና በስድስት የስፖርት አይነቶች እየተሳተፈ የሚገኘው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ እስካሁን በተደረጉ ውድድሮች በተለያዩ የስፖርት አይነቶች 7 ሜዳሊያዎችን ማግኘት ችሏል።
፨፨፨፨፨///፨፨፨፨፨
በጉራጌ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርት ውድድር ሻምፒዮና በ6 የስፖርት አይነቶች እየተሳተፈ የሚገኘው የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ ስፖርት ልዑክ እስካሁን በተደረጉ ውድድሮች በተለያዩ የስፖርት አይነቶች 7 ሜዳሊያዎችን ማስመዝገብ ችሏል።
በዚህ መሰረት በፓራሊምፒክ በእጅ ጉዳት አሎሎ ውርወራ በሳዳም ሰኢድ የብር ሜዳልያና በአብዶ ሽኩሬ የነሀስ ሜዳልያ ማግኘት የተቻለ ሲሆን በእግር ጉዳት በረቢቅ መኪ የብር ሜዳልያ ተመዝግቧል እንዲሁም የጦር ውርወራ በእጅ ጉዳት በአብዶ ሽኩሬ የብር ሜዳልያና በሳዳም ሰኢድ የነሀስ ሜዳልያ ሲመዘገብ በእግር ጉዳት በረቢቅ መኪ የብር ሜዳልያ ማሳካት ተችሏል።
በተያያዘም በአትሌቲክስ በ100 ሜትር ጋሊብ አ/መጅድ የብር ሜዳሊያ ለወረዳው ማምጣት የቻለ ሲሆን ዛሬ በተደረገ የወንዶች ቮሊቮል የምድብ ጫወታ ገ/ጉ/ወ/ወረዳ የሙህር አክሊል አቻውን አስተናግዶ 3ለ1 በማሸነፍ የመጀመሪያውን 3 ነጥብ ማሳካት ችሏል።
በነገው እለትም በጉራጌ ዞን ልዩ ልዩ ስፖርት ውድድር ሻምፒዮና የሚቀጥል ሲሆን ከረፋዱ 5፡00 ሰዓት በወንዶች እግር ኳስ ውድድር ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ከ እኖር አቻው ጋር የመጀመሪያውን የምድብ ጫወታ የሚያኪሄድ ይሆናል።
የነገውን የእግር ኳስ ጫወታ ትክክለኛውን ውጤት ለሚገምቱ 3 የመጀመሪያዎቹ የፔጃችን ቤተሰቦች የሞባይል ካርድ የምንሸልም ይሆናል!!!
ለእግር ኳስ ቡድናችን መልካም እድል እንመኛለን!!!
መረጃው የወረዳው ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት ነው።
