uk
Feedback
የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

የገ/ጉ/ወ/ወ/የመ/ኮ/ጉ/ጽ/ቤት

Відкрити в Telegram
918
Підписники
Немає даних24 години
+27 днів
+930 днів
Архів дописів
ጥር 09/2018 ዓ.ም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የ2018 በጀት አመት የፓርቲ ስራዎች የግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም የግምገማ መድረክ በጉራጌ ዞን ጉመር ወረዳ ጉልቾ ጀፎረ ላይ እየተካሄደ ይገኛል። "በመስፈንጠር ከፍታ ወደ ላቀ እምርታ" በሚል መሪ ቃል በጉራጌ ዞን፣ ጉመር ወረዳና አረቅጥ ከተማ አስተናጋጅነት በመካሄድ ላይ ነው። በክልሉ በ2018 በጀት አመት በግማሽ አመቱ የፓርቲ ስራዎችን በላቀ ደረጃ በመፈጸም የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ አበረታች ተግባራት መከናወናቸውን ተገልጿል። በክልሉ የመንግስት ዋና ተጠሪ በዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ የተመራ ልዑክ በዞኑ የጉመር ወረዳ አበኬ ቀበሌ የጉልቾ ውብ ጀፎረ ጉብኝት አድርገዋል። በመድረኩም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ ዶ/ር ዲላሞ ኦቶሬ፣ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪዎች፣ የዞኑ የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ አለማየሁ ገብረመስቀል ጨምሮ ከሁሉም ዞንና ልዩ ወረዳ የተወጣጡ የመንግስት ዋናና ረዳት ተጠሪዎች፣ የጽህፈት ቤቱ የማናጅመንት አካላት፣ የዞኑ ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የመንግስት ረዳት ተጠሪዎች፣ የወረዳውና የአረቅጥ ከተማ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ጥር 8/2018 ዓ.ም በጉራጌ ዞን ገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ በህብረተሰብ፣ በተወላጅ ባለሀብቶችና በመንግስት እየተከናወኑ ያሉ የመንገድ ልማት ስራ የመስክ ምልከታ እየተካሄደ ይገኛል። በዞኑ በተያዘው በጀት አመት ማህበረሰቡ፣ ተወላጅ ባለሀብቶችና መንግስት በመቀናጀት 4 መቶ 39 ሚሊዮን ብር ሀብት በማሰባሰብ 3 መቶ ኪሎ ሜትር የመንገድ ልማት ስራ በመስራት ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው። በወረዳው በተወላጅ ባለሀብት፣ በማህበረሰቡና በመንግስት 94 ሚሊዮን ብር ሀብት በማሰባሰብና በመበጀት 46 ኪሎ ሜትር የመንገድ ግንባታ ስራ፣ ድልድዮችና ሌሎችም ተግባራት እየተከናወነ ይገኛል። በመስክ ምልከታውም የጉራጌ ዞን ምክር ቤት የኢኮኖሚ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ክብርት ወይዘሮ ጠጄ ደነቀ፣ የጉራጌ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ የህያ ሱልጣን ጨምሮ የመምሪያው ምክትል ኃላፊ፣ የወረዳው ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሸብር ረጋና የጽህፈት ቤቱ የማናጅመንት አካላት ተገኝተዋል።

በጉቲ ኢቶቢየ ክልል በጉራጌ ዞን በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረደ ይትረኸባነይ የሱሙኜ ጎ አድ

ጥር 07/2018 ዓ.ም የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራን በማጠናከር ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል :-ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር) በሀዲያ ዞን በምስራቅ ባደዋቾ ወረዳ የ2018 ዓ.ም ክልላዊ የተቀናጀ የተፋሰስ ልማት ስራ አስጀምረዋል። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻዉ ጣሰዉ (ዶ/ር)በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በክልሉ በተቀናጀ ተፋሰስ ልማት የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራን በማጠናከር ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል ብለዋል። በክልሉ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት መላው ህዝብ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪ አቅርበዋል። የክልሉ መንግስት በሁሉም ዘርፍ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራም ርዕሰ መስተዳድሩ አብራርተዋል። በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ እና የክልሉ ግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ኡስማን ሱሩር እንደገለጹት በክልሉ በሚቀጥሉት 25 ቀናት በ 1ሺ294 ንኡስ ተፋሰሶች፣ ከ290 ሺህ ሄ/ር በሊይ የሚሸፍን መሬት እንደሚለማ ተናግረዋል። በተፋሰስ ልማት ስራው ከ1 ነጥብ 94 ሚሊየን በላይ ህዝብ ተሳታፊ እንደሚሆን ጠቁመዋል። በክልሉ ግብርናን በማዘመን ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ በተጀመሩ ንቅናቄዎች ተጨባጭ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል። በክልሉ ስድስቱን የግብርና ሴክተር ምሶሶዎች ለማሳደግ በተቀመጡ አቅጣጫዎች ውጤታማነት የተስፋ ብርሃን ማየት ጀምረናል ሲሉም አቶ ኡስማን አብራርተዋል። የግብርና ዘርፍን በማዘመንና የግብርና ሽግግር ማረጋገጥ የሚያስችል መፍጠንና መፍጠርን መነሻ ያደረጉ በርካታ አዳዲስ ኢኒሼቲቮች ተቀርጸው ተግባራዊ ማዴረግ ጀምረናል ብለዋል። ባለፉት ዓመታት የክልሉ መንግስት መላውን ህዝብ በማስተባበር ክልላዊ ጸጋዎችን መሰረት በማድረግ የልማት አቅጣጫዎችን ቀይሶ የጋራ ተግባቦት በመፍጠር ወደ ተግባር በመገባቱ የላቀ ውጤት ስለመመዝገቡም ኃላፊው አመላክተዋል። የክልሉ መንግስት ያስቀመጣቸው አቅጣጫዎች በተገቢው ተግባራዊ በመደረጋቸው ዘርፈ ብዙ ውጤቶች ተመዝግቧል ሲሉም አቶ ኡስማን በአብነት ጠቅሰዋል። በክልሉ የቴክኖልጂ አጠቃቀም ባህል ማደግ፣ከዚህ ቀደም ያልተለመዱ አዳዲስ የምርት አይነቶችን ማምረት መጀመሩን ኃላፊው አብራርተዋል። የኩታ ገጠም ልማት፣የግብርና ሜካናይዜሽን አጠቃቀም ፍላጎትና እያደገ ነው ያሉት አቶ ኡስማን ውሀ ተኮር የአመራረት ባህል እያደገ ስለመሆኑም ጠቁመዋል። በክልሉ ምርታማነት እየጨመረ ነው ያሉት አቶ ኡስማን በ2016 በጀት ዓመት 142 ሚሊየን ኩንታል ከነበረበት በ2017 ዓም ይህን አሀዝ ወደ 159 ሚሊየን ኩንታል ማሳደግ መቻሉን በአብነት ጠቅሰዋል። በክልሉ በወተት፣በእንቁላል፣በማር፣በዓሳ፣በቡናና ቅመማ ቅመም በሌሎችም አያሌ የግብርና ልማት ስራዎች የላቀ ውጤት መመዝገቡን አቶ ኡስማን አብራርተዋል። የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቲዎስ አኒዮ እንደገለጹት በዞኑ ባለፈው አመት በግብርናው ዘርፍ ውጤታማ ስራ ማከናወን ተችሏል ብለዋል። በቡናና ቅመማ ቅመም፣በአትክልና ፍራፍሬ ልማት ፣በእንስሳት ሀብት ልማት እና በሌለሎችም ቀጣይነት ያለው እድገት እንዲመዘገብ እየተሰራ ስለመሆኑም ዋና አስተዳዳሪው አብራርተዋል።

ጥር 06/2018 ዓ.ም በአከባቢያችን ያሉ ጸጋዎቻችንን በአግባቡ በመለየት ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ በተጨባጭ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት አስታወቀ። ፨፨፨፨፨///፨፨፨፨ በ2018 በጀት አመት ለ 5ሺህ 4 መቶ 60 ስራ ፈላጊ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ ባለፉት 6 ወራት  በቋሚና ጊዜያዊ 3 ሺህ 2 መቶ 38 ወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር የእቅዱ 60% ማሳካት መቻሉን በጉራጌ ዞን የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት አክሎ ገልጿል። የገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረዳ የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጅላሉ ወራቄ ያለፉት 6ወራት አፈጻጸም አስመልክተው እንደገለጹት ወጣቶች ጊዜያቸው፣ ጉልበታቸው፣ እውቀታቸው እና ገንዘባቸውን እንዲቆጥቡ በማድረግ እንዲሁም መንግስታዊ ድጋፍ በማድረግ ተደራጅተው ውጤታማ እንዲሆኑ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል። ባለፉት 6 ወራት 6624 በላይ ስራ ፈላጊ ወጣቶችን ለመለየት ታቅዶ በከተማና በገጠር አጠቃላይ 6844 ወጣቶችን በመለየት ከእቅዱ በላይ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል። ለተለዩ ስራ ፈላጊ ወጣቶች የተለያዩ አጫጭር፣ የክህሎት እና የኢንዱስትሪ ኢክስቴንሽን ስልጠናዎችን በመስጠት ወደ ስራ ለማስገባት ጥረት መደረጉን ጠቅሰው በ2018 በጀት አመት ለ5460 ስራ ፈላጊ ወጣቶች የስራ እድል ለመፍጠር ታቅዶ ባለፉት 6ወራት  በቋሚና ጊዜያዊ 3238  ወጣቶች የስራ ዕድል በመፍጠር የእቅዱ 60% ማሳካት መቻሉን አቶ ጅላሉ ወራቄ አክለው አስታውቀዋል። በሂደቱም በከተማና በገጠር የመስሪያና መሸጫ ቦታ 174 ሄክታር መሬት ለማስተላለፍ ታቅዶ ባለፉት 6ወራት ከ115 ሄክታር መሬት ለወጣቶች መተላለፉን እንዲሁም በከተሞች 6 ሼዶችን በመገንባት ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ መቻሉን የጠቀሱት አቶ ጅላሉ 10 ሚሊየን ብር በላይ የብድር አቅርቦት ለማመቻቸት ታቅዶ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት 5,080,505  ብር ብድር ለወጣቱ ተደራሽ ማድረግ እንደተቻለ አስገንዝበዋል። ወጣቶቹ ወደ ስራ የገቡት በግብርና ዘርፍ በመኸር ሠብል ልማት ፣መስኖ ማደለብና ማሟከት እንዲሁም በዶሮ ሃብት እና በንግድ ዘርፍ እና በእንጨትና ብረታ ብረት ተሰማርተው እንደሚገኙ ገልጸው 9,769,240 ብድር ለማስመለስ ታቅዶ ባለፉት 6 ወራት 4,795,417.79 ብር ማስመለስ መቻሉ እንዲሁም በባለሙያ ደረጃ የሚሰሩ የሂሳብ ዝርጋታ፣ የገቢያ ድጋፍ፣ ኦዲት እና ሽግግር ስራዎች በልዩ ሁኔታ እየተሰሩ መሆኑን  አስታውቋል። በመጨረሻም አቶ ጅላሉ ባስተላለፉት መልዕክት ቋሚ ስራ ዕድል ፈጠራ ፣ ብድር አመለለስ ፣ ብድር ስርጭት፣ቁጣባ እና ኢንተርፕራይዞችን በELMIS ምዝገባ ተግባራት በጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር መተግበር እንዳለበት ገልጸው በአከባቢያችን ያሉ ጸጋዎቻችንን በአግባቡ በመለየት ወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ በተጨባጭ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ ሶሆን ዜጎች በሚፈጠሩት የስራ ዕድሎች ከራሳቸው ባለፈ ሌሎችንም ተጠቃሚ በማድረግ የስራ አጥነትን ችግር መቅረፍ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ፓርቲዉ በወሰደዉ ቁርጠኝነት ክልሉ በአጭር ጊዜ የብልጽግና ተምሳሌት መሆን ችሏል- አቶ አደም ፋራህ በብልፅግና ፓርቲ የ2018 በጀት ዓመት የ6 ወራት የፓርቲ ስራዎች አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንትና የዋና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ እንደገለጹት የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በሁለት ዓመት ከአምስት ወራት የምስረታ ታሪክ ተምሳሌት የሆነ ዉጤት ማስመዝገብ የቻለዉ ፓርቲዉ በወሰደዉ ቁርጠኛ አቋም ነዉ፡፡ የተቋማትን ዝግጁነት በቅንጅት መምራት፣ ያለምንም የሰላምና የጸጥታ ችግር ወደ ስራ መግባት፣ መደበኛ አገልግሎቶች ሳይቆራረጡ መቀጠላቸዉ፣ ክልሉ በፋይናንስ ራሱን መቻሉ፣ ፈጥኖ ወደ ስራ መግባትና የማስፈጸም አቅም መገንባት መቻሉ አሁን ለተመዘገቡ ስኬቶች መሰረት መሆናቸዉን አብራርተዋል፡፡ ብልፅግና ፓርቲ ሁሉን አቃፊና ሁሉን አሳታፊ ህብረ ብሄራዊ ፓርቲ መሆኑን የተናገሩት አቶ አደም ፋራህ በሙሉ እይታና በጥራት የመደመር ዕሳቤን መሰረት በማድረግ አሰባሳቢ ትርክት መፍጠር መቻሉን ገልጸዋል፡፡ ሁሉን አባላት ማብቃትና ብቁ አደረጃጀት መፍጠር ያለዉን ፋይዳ በመረዳት ለዚህ ስኬት በትኩረት ተሰርቷል ዉጤትም ተገኝቶበታል ብለዋል፡፡ በየደረጃዉ ብቁ የሆኑ ስትራቴጂያዊ አመራሮችን ለማፍራት በርካታ ስልጠናዎችን በመስጠት ሀገራዊ ለዉጡን መሸከምና ማስቀጠል የቻለ አመራር መፍጠር እንደተቻለ አንስተዋል፡፡ እንደ ፓርቲ በሁሉም መስኮች በተመዘገቡ ስኬቶችና ድሎች የህዝብ ቅቡልነት ማረጋገጥ እንደተቻለ ያብራሩት አቶ አደም ወጥነት ያለዉ ተቋማዊ ስርዓት መዘርጋት መቻሉንም ተናግረዋል፡፡ የአመራሩንና የአባሉን አቅም በስልጠና በመገንባት ወጥነት ያለዉን ተቋማዊ አሰራር መዘርጋት ተችሏል ብለዋል፡፡ ዲጂታል ኢትዮጵያ እዉን ለማድረግ በሚደረግ ጥረት ዉስጥ እንደ ፓርቲ አርዓያ ለመሆን ዲጂታል ብልጽግናን ማረጋገጥ መቻሉን ተናግረዋል፡፡ በግምገማ መድረኩ በፓርቲ ስራዎች ባለፉት ስድስት ወራት በተመዘገቡ ስኬቶችና ዉስንነቶች እንዲሁም በቀጣይነት ትኩረት በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ላይ በስፋት ዉይይት እየተደረገ ነዉ፡፡

የራዘር 5/2018 ኢትቶብየ ዘማን ሂልቅ በገደባኖ ጉታዘር ወለኔ ወረደ በኢንጌ ከተመ በአውጄነይ አያም ሙሊ ገበየ ተጄመረ።