cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Ethio Islamic center

"ያነገሩ ሁላ ስልጣን በእጅ የሆነው ጌታ ጥራት ይገባው" #በዚህ_ቻናል_የምታገኙት ✓የነብያቶችናየሶሀቦችታሪክ ✓እስላማዊ ትምህርቶች ✓ጥያቄና መልስ ✓ጣፋጭ ታሪኮች እና ✓ፈገግታ ለማናቸውም ሀሳብና አስተያየት @Nuredinseha123 #ይቀላቀሉ

Більше
Рекламні дописи
239
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

አል ኢማሙል አውዘዒይ አሏሁ ተዓላ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ፡ "ከዱንያ ሰአቶች ውስጥ አንድም ሰአት የለም የውመል ቂያማ በባሪያ ላይ የሚቀርብ ቢሆን እንጂ ፤ ቀኖች አንድ በአንድ ፤ ሰአቶች አንድ በአንድ (ይቀርባሉ) ፤ አሏሁ ተዓላን ያልዘከረበት አንድም ሰአት አያልፍም ነፍሱ በፀፀት የምትቆራረጥ ቢሆን እንጂ።!" "ከሂልየቱል አውሊያእ ወጦበቃቱል አስፊያ ኪታብ የተወሰደ" Sher&join @Ethio_islamic_center
Показати все...
የአሏህ መልክተኛ ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፡ ((إِذَا جَائَكُمْ مَنْ تَرْضَوْنَ دِينَهُ وُخُلُقَهْ فَزَوِجُوهْ وَإِلَّا تَكُنْ فِتْنَةٌ فِي الْأرْضِ وَفَسَادٌ عَرِيضْ)) ((ዲኑን እና ስነምግባሩን ምትወዱለት ሰው ወደ እናንተ ከመጣ አጋቡት ካልሆነ ምድር ላይ ፊትና እና ብዙ መጥፎ ነገር ይከሰታል)) Sher&join @Ethio_islamic_center
Показати все...
#የዚህ አለም እውነት! ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لم يبقَ منَ الدُّنيا إلّا بلاءٌ وفتنةٌ﴾ “ከዱኒያ የቀረ ነገር የለም መከራና ፈተና ቢሆን እንጂ።” 📚 ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል: 3276 Join join join join @ethio_islamic_center
Показати все...
1
#የህይወት_መርህ ❶. ዱዓ በችግር ጊዜ ብቻ የምትጠቀመው  ሳይሆን በድሎት ሰዓትም የምትጠቀመው መሆን አለበት። ❷. የመኪና እስፖኪዮ ትንሽ የሆነውና የፊት መስታወት ሰፊ የሆነው ለምንድ እንደሆነ ታውቃለህ? በእስፖኪዮው ያለፍከውን በትንሹ እያየህ በሰፊው የወደፊቱ - በደንብ እያየህ፥ አትኩረህ እንድትሄድ ነው። ሰው በዛሬ እንጂ በትዝታ መኖር የለበትም። ከትላንትህ ነገህ ብሩህ ነው። ዛሬ ላይ ኖረህ ነገህን ስራ። ❸. ጓደኝነት እንደ መጽሐፍ ነው። ለማቃጠል ጥቂት ሴኮንዶች ብቻ ይፈጃል። ነገር ግን ለመጻፍ(ለመገንባት)  አመታትን ሊወስድ ይችላል። ❹. በህይወት ውስጥ ያሉ ሁሉም ነገሮች ጊዜያዊ ናቸው። ነገሮች በጥሩ ሁኔታ ከሄዱ፤  ተደሰትበት። ለዘላለም ፀንተው አይቆዩምና።  ነገሮች እንዳልታሰቡት ከተበላሹም፤ አትጨነቅ። እነዚህም ለረጅም ጊዜ ሊቆዩ አይችሉምና ያልፋሉ፤ ይረሳሉ። ❺. የድሮ ጓደኞች ወርቅ ናቸው! አዲስ ጓደኞች አልማዝ ናቸው! አልማዝ ካገኘህ ወርቁን አትርሳ! ምክንያቱም አልማዝ ለመያዝ ሁል ጊዜ የወርቅ መሰረት ያስፈልግሃልና! ❻. ብዙ ጊዜ ተስፋ ስንቆርጥ መጨረሻው  ይህ ነዉ ብለህ አታስብ  ይህ መታጠፊያ ኩርባ እንጂ መጨረሻው አይደለም!" አሏህ ታጋሽ ነዉ በትግስትና በዱዓ በርታ..! ❼. አሏህ ችግርህን ሲፈታ፤ በችሎታው፤ ሁሉ ቻይ ስለመሆኑ ማመን ይኖርብሃል።  አሏሁተዓላ  ችግሮችህን እስከሚፈታልህ ባለህ ልምድ ላይ ጠንክር ስራ፣ዱዓ አድርግ ተስፋ አትቁረጥ የአሏህ እዝነቱ ሰፉ ነዉ። #ኮፒ ቴሌግራም 👇👇 https://t.me/ethio_islamic_center
Показати все...
Ethio Islamic center

"ያነገሩ ሁላ ስልጣን በእጅ የሆነው ጌታ ጥራት ይገባው" #በዚህ_ቻናል_የምታገኙት ✓የነብያቶችናየሶሀቦችታሪክ ✓እስላማዊ ትምህርቶች ✓ጥያቄና መልስ ✓ጣፋጭ ታሪኮች እና ✓ፈገግታ ለማናቸውም ሀሳብና አስተያየት @Nuredinseha123 #ይቀላቀሉ

👍 1
👇
የኢድ ተክቢራ _…__……… 😍አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር . አሏሁ አክበር አሏህ አክበር . አሏሁ አክበር . ላኢላሃ ኢለሏህ . አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር . ወሊላሂል ሃምድ . አሏሁ አክበር ከቢራ . ወልሃምዱሊላሂ ከሲራ . ወሱብሃነላሂ ቡክረተን ወአሲላ . ላኢላሃ ኢለሏህ . ወላ ነእቡዱ ኢላ ኢያሁ ሙኽሊሲነ ለሁ ዲነ ወለው ከሪሀል ካፊሩን . ላኢላሀ ኢለሏህ . ሰደቀ ወአደህ . ወነሰረ አብደህ . ወአዓዘ ጁንደህ . ወሃዘመል አህዛበ ወህደህ . ላኢላሃ ኢለሏህ . አላሁ አክበር . አሏሁመ ሶሊ አላ ሰዪዲና ሙሐመድ . ወአላ አሊ ሰዪዲና ሙሐመድ . ወአላ አስሃቢ ሰዪዲና ሙሐመድ . ወአላ አንሷሪ ሰዪዲና ሙሐመድ . ወአላ አዝዋጂ ሰዪዲና ሙሐመድ . ወአላ ዙሪየቲ ሰዪዲና ሙሐመድ . ወሰለም ተስሊመን ከሲራ! . ♡ዒድ ሙባረክ♡ https://t.me/ethio_islamic_center
Показати все...
Ethio Islamic center

"ያነገሩ ሁላ ስልጣን በእጅ የሆነው ጌታ ጥራት ይገባው" #በዚህ_ቻናል_የምታገኙት ✓የነብያቶችናየሶሀቦችታሪክ ✓እስላማዊ ትምህርቶች ✓ጥያቄና መልስ ✓ጣፋጭ ታሪኮች እና ✓ፈገግታ ለማናቸውም ሀሳብና አስተያየት @Nuredinseha123 #ይቀላቀሉ

👏 2
የዐረፋ ቀን عن عائشة رضي الله عنها قالت : إن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال : ( ما مِن يوم أكثر من أن يعتق الله فيه عبداً من النار من يوم عرفة አዒሻ ረ•ዐ እንደተረከችው የአላህ መልዕክተኛ(ﷺ) እንዲህ ብሏል ከቀናቶች ሁሉ አሏህ ብዙ ባሮቹን ከእሳት የሚያወጣበት ቀን ቢኖር የዐረፋ ቀን ነው። (ሰሂህ ሙሥሊም 1348) وعن عبد الله بن عمرو بن العاص رضي الله عنهما أن النبي صلى الله عليه وسلم قال : ( خير الدعاء دعاء يوم عرفة ، وخير ما قلت أنا والنبيّون من قبلي : لا إله إلا الله وحده لا شريك له ، له الملك ، وله الحمد ، وهو على كل شيء قدير ) رواه الترمذي ( 3585 ) وحسَّنه الألباني في " صحيح الترغيب " ( 1536 ) . አብደሏህ ኢብኑ ዐምር {ረ•ዐ} እንደተረከው የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብሏል የዐረፋ ቀን በላጩ ዱዓህ እኔና ከእኔ በፊት የነበሩ ነቢያት ከተናገርነው ዱዓህ በላጩ ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም: አንድ ነው: አጋር የለውም: ንግሥና የእርሱ ብቻ ነው። ምስጋና የእርሱ ነው: እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው። {ቲርሚዚ, 3585} አልባኒ ሐዲሱን ሰሂህ ነው ብሎታል። (ሷሂህ አል-ተርጊብ, 1536)
Показати все...
#ድክመቶቻቸውን የሚያሸንፍ ጠላቶቹን ከሚያሸንፍ ይልቅ ጀግኖች ስኬታሞች ናቸው ! ምክንያቱም በጣም አስቸጋሪው #ትግል ራስን ማሸነፍ ነው ..! ለዚህም ራሱን ነፍሱን ታግሎ ያሸነፈ በዱኒያም በአኬራም ባለ ትልቅ የድል ባለቤት ሆነ!!! አስቢበት ድክመትሽን ተዋጊው!!! አስብበት ድክመትህን ተዋጋ !!! @Ethio_islamic_center
Показати все...
1
👍 2
👇
የሆነ ግዜ አንዲት ወጣት ወደ አያቷ ዚያራ ትሄድና ድሮ ያለ ሚዲያ እንዴት ነበር ምትኖሩት አለቻቸዉ ???🤷‍♀ እርሳቸዉም፣ ዛሬ እናንተ ያለ አዝካር፣ ያለ ሱና ሶላት፣ ያለ አዉራድ እንደምትኖሩት ብለዉ መለሱላት🤦
Показати все...
3
👍 5
👇
#ታላቁ_ሶሃባ_አሊ_ቢን_አቢጧሊብ_ከልጅነት_እስከ_ሞት ! ታላቁ ሶሃባ አራተኛው የሙስሊሞች ኺላፋ አሊ ቢን አቢጧሊብ  በ ጥር 26 , 661 እ.ኤ.አ ወይንም በረመዷን 19 , 40 ኛው አመተ ሂጅራ ላይ ነበር በተረገመው አብዱረህማን ኢብኑ ሙልጂም የተገደሉት ። ታላቁ ኸሊፋ አልይ የተገደሉት በታላቁ የኩፋ መስጅድ የሱብሂ ሶላትን እየሰገዱ በነበረበት ወቅት ነው። ሙጅሪሙ ኢብኑ ሙልጂም አልይን የገደላቸው በተመረዘ ሰይፍ ከወጋቸው በሗላ ነበረ። ኢብኑ ሙልጂም ኸዋሪጅ ነበረ። አብዱረህማን ኢብኑ ሙልጂም ተይዞ አልይ ፊት በቀረበ ጊዜ አሊ " አንተ የአላህ ጠላት ሆይ እኔ ላንተ መልካምን አላደረኩም ነበር ?" በማለት ጠየቁት ኢብኑ ሙልጀም በዚህ ጊዜ " አዎ በሚገባ መልካምን አድርገህልኛል እንጅ !" አላቸው። በዚህ ጊዜ አሊ " ታዲያ ይህንን በኔ ላይ እንድትፈፅም ምን ገፋፋህ "አሉት ። እርጉሙ ኢብኑ ሙልጂምም በዚህ ጊዜ " እኔ ሰይፌን ለአርባ ቀን ንጋቶች ያክል ስየዋለሁ( ሞርጄዋለሁ ) ፤ እርሱ ከፈጠራቸው ፍጡራኖች ሁሉ አስቀያሚ የሆንከውን አንተን የመግደል እድል ይሰጠኝም ዘንዳ ለምኘዋለሁ ለዚያም ነው የዋጋሁህ " አላቸው። አሊ ቢን አቢጧሊብ በመርዛማው የኢብኑ ሙልጂም ሰይፍ ከተወጉ ከሁለት ቀን በሗላ ጌታቸውን ተገናኙ። © 5 Minute History አልይ ቢን አቢጧሊብ አስር በጀነት ከተበሰሩ ሶሃባዎች አንዱ ናቸው ። አልይ አላህን አብዝተው የሚፈሩ ዛሂድ ፤ ጠላት የፈለገውን ያክል አስፈሪ ቢሆን ቅንጣት ታክል ፍርሃት የሌለባቸው ጀግና ፤ እጅግ ጥበበኛ የሆኑ አዋቂ ፤ እጅግ አዛኝ የሆኑ መሪ ፤ አንድትንም ቀን ካለ ጂሃድ አሳልፈው የማያውቁ ሙጃሂድ ነበሩ። አሊ ቢን አቢጧሊብ ከወንዶች እስልምናን በመቀበል የሚቀድማቸው የለም። ረሱላችን ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም የአላህ ነብይና መልእክተኛ ሆነው በተላኩ ጊዜ ከሴቶች ኸድጃ ከወንዶች ደግሞ አሊ ናቸው ለመጀመሪያ ጊዜ የተቀበሏቸው ። ከዚያ አቡበክር አሲዲቅ ይከተላሉ። አሊ እስልምናን ሲቀበሉ ገና የ 10 አመት ህፃን ነበሩ ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እስከለተ ህልፈታቸው ድረስ እስልምናን በሁሉም ነገራቸው ህይወታቸውን ቤተሰቦቻቸውን ንብረታቸውን ሰውተው አገልግለዋል። አሊ ያልተሳተፉበት አንድም ዘመቻ የለም -የተቡክ ዘመቻ ሲቀር ። በዚያ ዘመቻ ላይ ነብያችን አሊን መድናን ከተማዋን እንዲጠብቅ አዘዙት ። አሊ ግን ቅር አላቸው ። በዚህ ጊዜ ነብያችን ሶ.አ.ወ ለአሊ " ሀሩን ለሙሳ እንደሆነው ሁሉ አንተ ለእኔ መሆንን አትወድም? " አሉት ። አልይም ደስ አላቸውና መድናን ሲጠብቁ ቆዪዋቸው። አልይ ለነብያችን ሀሩን ለሙሳ እንደሆኑት ናቸው ። አንድ ጊዜ ነብያችን ሶ.ዓ.ወ " ይህችን ባንድራ አላህና መልእክተኛውን ለሚወድ፤ አላህና መልእክተኛውም ለማወዱት ፤ አላህ በእርሱ አማካኝነት ከተሞችን የሚከፍትበት ለሆነ ሰው እሰጣታለሁ " ሲሉ ተናገሩ ። ሁሉም ሶሃቦች "እኔ እሆን ? " እኔ እሆን " በማለት ጓጉ ። ኡመር ኢብኑልኸጧብ እንደዚህ ይላሉ " ወላሂ በህይወቴ አንድም ቀን ሹመትን ተመኝቼ አላውቅም የዚያችን ቀን ቢሆን እንጅ " አሉ ። ረሱላችን ሰ.ዐ.ወ " አሊ የታል ? " ሲሉ ጠየቁ ። ሶሃቦችም " አይኑን አሞታል " በማለት መለሱላቸው ። ነብያችንም " ጥሩት " አሉና አሊ መጣ ። ከዚያም ነብያችን የአሊን አይን ዳበስ ዳበስ አደረጉለት ። ወዲያ አይኖቹ ፍፁም ጤነኛ ሆኑ ። ለአሊም ያችን ባንድራ ሰጡት ። አሊም የዘመተባትን ከተማ ከፈታት። ነብያችን አሊን #አሳዱሏህ የአላህ አንበሳ በማለት ነበር የሚጠሩት። ሙስሊሞች በየዘመቻው ሀይለኛ ተፋላሚ በገጠማቸው ጊዜ ከፊት የሚሰለፈው አልይ ነበር። አልይን ተፋልሞ ያሸነፈ አንድም ተዋጊ የለም። አልይ የሙጃሂዶች ሁሉ አርአያ እና ሞደል ነው ። ምናልባትም ምድር የአሊን ያክል ጀግና ሰው አይታ አታውቅም ። አሊ ጀግና ብቻ አይደለም ። እጅግ አዋቂ አሊምም ጭምር እንጅ ። ነብያችን በአንድ ንግግራቸው " እኔ የእውቀት ከተማ ነኝ መግቢያ በሩ ደግሞ አሊ ነው " ብለውታል ። ይህ ማእረግ ለአሊ እንጅ ለማንም አልተሰጠም። አሊ ጥበባዊ ንግግሮቹ እስከ የውመል ቂያማ ውስጥን ሲያናግሩ ይዘልቃሉ። ፍትሃዊነት በአልይ በቃ! እርሱ ታላቁን ኸሊፋ ኡመር ኢብነልኸጧብን " ምስክር የማታቀርብ ከሆነ እስር ቤት አስገባሃለሁ " ያለ ፍትሃዊ ሰው ነበር። ታላቁ አሊም ኢማም አህመድ ስለ አሊ ሲናገሩ " አሊ የተሰጠውን ትሩፋት ያክል ማንም አልተሰጠውም " ብለዋል። አሊ የነብያችን እጅግ ቅርቡ ሰው ነበር ። ነብያችን አሊን " ወንድሜ " በማለት ነው የሚጠሩት ። ይህን ማእረግም ከአሊይ ውጭ ያገኘ የለም። ነብያችን መድናን ለቀው ሊወጡ ባሰቡ ጊዜ ቁረይሾች በተኙበት ሊገድሏቸው እያሴሩ ነበር ። እናም ነብያችን እርሳቸው መኝታ ላይ አስተኝተውት የሄዱት የጀግኖቹን ጀግና አሊን ነበር። አሊ ስለዚያ ክስተት ሲያወሩ " እንደዚያ የሚያስደስትና ሰላም ያለው ሌሊት አሳልፌ አላውቅም"  ይላሉ። አሊን የወደደ አላህንና ነብያችንን ይወዳል። አሊን የሚጠላ ደግሞ አላህንና ነብያችንን ይጠላል !! አንድ ጁሙአ ላይ ነብያችን ሶ.ዐ.ወ የአሊን እጅ ያዙና ኹጥባ ማድረግ ጀመሩ ። ነብያችን " እናንተ ሰዎች ሆይ እኔ የናንተ ወሊያችሁ ( ወዳጃችሁ ) ነኝ " አሏቸው ። ሶሃቦችም " የአላህ መልእከተኛ ሆይ እውነትን ተናገሩ " አሏቸው ። ነብያችን ከዚያም የአልይን እጅ ከፍ አድርገው ያዙና "  ይሄ የኔ ወሊይ ነው ፤ ይሄ እዳየን የሚመልስልኝ ነው !! እርሱን የወደደው ወዳጄ ነው እርሱን የጠላው ደግሞ ጠላቴ ነው !!!" በማለት በዚያ ለተሰበሰቡት ሶሃቦች ነገሯቸው። ሱብሃን አሏህ! ምንኛ እጅግ የገዘፈ ደረጃ ነው!!! ነብያችን ሶ.ዐ.ወ በሌላ ንግግራቸው " አልይን የወደዱው በርግጥ እኔን ወደደኝ ! እኔን የወደዱኝ ደግሞ አላህን ወደደ ! ፤ አላይን ያስከፋ እኔን አስከፋኝ ፤ እኔን ያስከፋ ደግሞ አላህን አስከፋ " በማለት ተናግረዋል ። አልይን አለመውድ አላህንና መልእክተኛውን አለመውደድ ነው!!! ነብያችን አልይን ከመውዱዳቸው የተነሳ እጅግ የሚወዷትን ልጃቸውን ፋጢማን ድረውለታል።  አንድ ቀን ነብያችን አሊን ፣ ባለቤቱን ፋጢመትን እንዲሁም ልጆቹን ሀሰንና ሀሰይንን አንድ ላይ ጠሯቸውና አድስ ልብስ አለበሷቸው ። ከዚያ ነብያችን እንደዚህ አሉ " አሏህ ሆይ እነዚህ ቤተሰቦቼ ናቸው ! ከእነርሱ ላይ አስቀያሚን ነገር ሁሉ አስወግድላቸው ፤ ማጥራትንም አጥራቸው " በማለት ዱአ አደረጉላቸው ። አላህም ዱአቸውን ሰማ ። በቁርአን ቃሉም " አላህ የሚሻው ከናንተ ላይ ቆሻሻን ነገር ሊያስወግድላችሁ ነው " በማለት አወረደ። ነብያችን ሶ.ዐ.ወ እንደዚህ አሉ " ሰዎች ሁሉ ጀነትን ይናፍቃሉ  ጀነት ግን ሶስት ሰዎችን ትናፍቃለች #አሊን #አማርን እና #ቢላልን " አሉ!! የአሏህ ምንኛ መበለጥ ነው! ምንኛ ከፍታ ነው!! እረ join @Ethio_islamic_center
Показати все...
👍 1 1
የ #ዙል_ሂጃ  ፆም ኒያ  👇 ነወይቱ ሶውመ غ ዲን አን አዳኢ ሱነተል ዙል ሂጃ ሊላሂ ተዓላ ኒያው ይሄ ነው 👆 ዋናው እደምትፆሙ  በቀልባችሁ መጣድ ነው :: ይሄን የማያውቁ ብዙ ሰዎች ስላሉ ሁላችሁም #ሼር እያደረጋችሁ ላኩላቸው ሊላሂ ተዐላ
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.