cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ኦርቶዶክሳዊነት 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

እዚህ Channel ላይ ኦርቶዶክሳዊ ስብከት ፣መዝሙር ፣ኬነጥበቦች እና መፅሕፍት ይለቀቁበታል "ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??" ቅዱስ ኤፍሬም

Більше
Рекламні дописи
1 638
Підписники
+7524 години
+2257 днів
+76230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

01:08
Відео недоступнеДивитись в Telegram
                         †                         ሰው ራሱን አገኘ የሚባለው መቼ ነው ?          †              †               † ▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
Показати все...
7.92 MB
[ + እውነተኛ ፍቅር + ] .mp36.53 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
💛 ▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬ 🕊     ም ክ ረ     ቅ ዱ ሳ ን     🕊 ▷  " ከቅጣት የሚያወጣን እውነተኛ ፍቅር !  " [    " ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ "    ] [                        🕊                        ] ----------------------------------------------- ❝ ዋላ ወደ ውኃ ምንጭ እንደሚናፍቅ ፥ አቤቱ ፥ እንዲሁ ነፍሴ ወደ አንተ ትናፍቃለች። ነፍሴ ወደ ሕያው አምላክ ተጠማች ፤ መቼ እደርሳለሁ ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ? ❞ [  መዝ . ፵፪ ፥ ፩  ] 🕊                        💖                     🕊                              👇
Показати все...
[ + ውለታህ ከበደኝ + ] .mp34.73 MB
                       †                          [     🕊  ፍኖተ ቅዱሳን   🕊     ] [  የቅዱሳን አባቶቻችን የቅድስናና የተጋድሎ ሕይወት ] †                       †                       † [        በሌላ ላይ አለ መፍረድ !        ] 🕊 " በታቦቱ አጠገብ ቁጭ ብዬ እጠብቃለሁ .. " ........ ጠቢብ የሆነ አንድ አረጋዊ ነበር፡፡ የአገሩ ሰዎች ወደ ኤጴስ ቆጶሱ ሄዱና ፦ “ይህ ካህን እያሳዘነን ስለሆነ ይባረርልን” ሲሉ ጠየቁት። ኤጲስ ቆጶሱም ፦ "ያሳዘናችሁ በምን ምክንያት ነው?" አላቸው። እነሱም ፦ "ቅዳሴ በሦስት ሰዓት የሚገባበት ጊዜ አለ ፣ በስድስት ሰዓትም የሚቀድስበት ጊዜ አለ ፣ ሰንበታትን አይጠብቅም ፣ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ያፈርሳል" አሉት፡፡ ኤጲስ ቆጶሱም ብቻውን ወሰደውና ፦ "ለምን እንዲህ ታደርጋለህ? የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓትስ ለምን ታፈርሳለህ?" አለው፡፡ አረጋዊውም ፦ "አባቴ ሆይ ፣ ይቅርታ አድርግልኝ ፣ የማደርገውን አላውቅምና፡፡ በእሁድ ጠዋት አገልግሎት ከመፈጸም በኋላ መንፈስ ቅዱስ በመስዋዕቱ ላይ እስኪታይ ድረስ በታቦቱ አጠገብ ቁጭ ብዬ እጠብቃለሁ ፣ ያን ጊዜ በፍርሃትና በረዓድ ሆኜ ቅዳሴውን አከናውናለሁ" አለው:: ኤጲስ ቆጶሱም ይህን ሲሰማ እጅግ አደነቀ ፣ ሕዝቡንም "በሰላም ሂዱ" ብሎ አሰናበታቸው:: ለዚሁ ቅዱስ አረጋዊ ሌላ ግሑስ አረጋዊ ሦስት የእሳት ፍሞችን በጨርቅ ቋጥሮ ላከለት ፣ ከዚህ አረጋዊ ካህን ዘንድም እሳቱም ሳይጠፋ ፣ ጨርቁም ሳይቃጠል ደረሰ፡፡ እርሱም ውኃ በጨርቅ አስሮ ላከለት ፣ በመካከላቸው ያለው ርቀት ሃያ አምስት ምዕራፍ ያህል ነበር። ቢሆንም ውኃው ሳይፈስ ደረሰ ፤ እግዚአብሔርንም አመሰገነ፡፡ የአባቶቻችን ጸሎትና በረከት ይደርብን፡፡ †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
Показати все...
                          †                           [    🕊    ገ ድ ለ   ቅ ዱ ሳ ን   🕊     ] ▬▬▬▬▬▬   †    ▬▬▬▬▬▬ [  የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ የተጋድሎ ሕይወቱና ትምህርቱ  ] [    ክፍል ሰባት     ] 💛 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ [ የመቃርዮስ ራእይ ] ❝ በዚያን ዘመን ሽፍቶችን ከመፍራት የተነሣ ነጋዴዎች የሚጓዙት በአንድ ላይ ብዙ ሆነው ነበር፡፡ ሽፍቶች ቀስ በቀስ ወደ ምሥራቅ በኩል በመምጣት ያስቸግሯቸውና ማርከው ወደ ሀገራቸው ይወስዷቸው ነበርና፡፡ ስለዚህ እርስ በእርሳቸው በመጠባበቅና በመረዳዳት ብዙ ግመል ይዘው ይሄዱ ነበር፡፡ መቃርዮስም ከብዙ የግብጽ ነጋዴዎች ጋር በመሆን ሲሄድ አስቄጥስ ከሚባል ቦታ ከወንዝ አጠገብ በሚደርሱበት ጊዜ መሽቶ ስለ ነበር ለማረፍ ፈለጉና ቦታ ይዘው ተኙ፡፡ ወጣቱ መቃርዮስም በጣም ደክሞት ስለ ነበር በዚያ ተኝቶ እያለ ስድስት ክንፍ ያለው ኪሩብ ታላቅ ብርሃናዊ መብረቅን የተጎናጸፈ ሰው ሆኖ ተገልጾ እጁን ይዞ ወደ ተራራ ላይ አወጣውና የአስቄጥስን በረሃ ምሥራቁንና ምዕራቡን በአራቱም ማዕዘን አሳይቶ ፦ "ተነሥና ተመልከት ፣ ይህን ራእይ ልብ አድርግ ፣ ይህን ተራራ ዙረው ፣ ውስጡን አስተውለው" አለው፡፡ መቃርዮስም ለሚናገረው ፦ "ጌታዬ ሆይ ፦ እኔስ ከሚታየው ጫካና በቀኙ ካለው ተራራ በስተቀር ምንም አይታየኝም" አለው፡፡ ያ ኪሩባዊም መልሶ እንዲህ አለው ፦ "እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ፦ 'ይህን ተራራ ለአንተ ርስት አድርጌ እሰጥሃለሁ ፣ ለአንተም ለከምልኮቴ ጽኑዓን የሚሆኑ ብዙ ልጆች ይኖሩሃል ፤ ከአንተም ታላላቆች ሰዎች ይገኛሉ፡፡ በትምህርትህና በፍቅርህ ለአሕዛብ ሁሉ ጽኑዕ መሠረት ትሆናለህ ፤ እኔም ቅርንጫፍህ ብዙ ፍሬን እንዲያፈራ አደርጋለሁ ፤ እነርሱም በምድር ሁሉ ያመሰግኑኛል፡፡ የአንተንም ስም ይዘክራሉ፡፡' አሁንም ከእንቅልፍህ ተነሥ ፣ ወደ ቤትህም በሰላም ተመለስ ፣ ይህን ያየኸውንና የነገርኩህን በልብህ ጠብቅ ፣ ፍጹም ስትሆን እገልጽልሃለሁ ፣ እግዚአብሔር የሚልከኝንም እነግርሃለሁ ፣ ይህን የነገርኩህን ግን እስክትታዘዝ ድረስ ለማንም አትንገር" አለው፡፡ ኪሩባዊው ይህን ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ ሲነጋ መቃርዮስ ከእንቅልፉ በሚነቃበት ጊዜ እንዲህ ዓይነት ተአምራት አይቶ ስለማያውቅ ስላየው ራእይና ስለተነገረው ነገር ሁሉ እያሰበ እያለ አብሮት የነበረው ሰው ፦ "እንዲህ የሚያስደንቅህ የተፈጠረው ነገር ምንድን ነው?" አለው፡፡ እርሱ ግን ምንም ነገር አላለውም፡፡ ከሦስት ቀን በኋላ መቃርዮስ ባየው ራእይ እየተገረመ ከአስቄጥስ በረሃ ወደ ቤቱ በተመለሰ ጊዜ ያቺ ሚስት ትሆነው ዘንድ ብለው ያመጡለት ብላቴና በጽኑ ታማ አገኛት ፣ ጥቂት ቆይታም ወዲያው በድንግልናዋ እንዳለች በሰላም ዐረፈች ፤ የክብር ባለቤት እግዚአብሔርንም አመሠገነው፡፡ እርሱም ለራሱ ፦ 'መቃርዮስ ሆይ ! ከእንግዲህ ወዲህ ለነፍስህ ድኅነት በሚሆን ትጋት በመትጋት መንፈሳዊ ፍሬን ለማፍራት ታጠቅ ፤ አንተም እንዲሁ ትወሰዳለህና' እያለ ራሱን ይገሥጽ ጀመር፡፡ ❞ የአባታችን የቅዱስ መቃርዮስ ምልጃና ጸሎቱ አይለየን፡፡ ይቆየን ! †                       †                         † 💖                    🕊                     💖
Показати все...
[ ስንክሳር ሰኔ - ፳፭ - ] .mp37.36 MB
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.