uk
Feedback
Yoni Motivation

Yoni Motivation

Відкрити в Telegram

ከማንም አትጠብቅ

Показати більше
698
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
🌑 FIAS ማን ነው? ( Who is FIAS) best explanation in amharic language FIAS በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚሰራ platform ነው። የኩባንያው አሰራር ከፌስቡክ እና ከዩቲዩብ ጋር የተገናኘ ነው። አንድን ተግባር ለመቀበል ጠቅ ባደረጉ ቁጥር ስርዓቱ በራስ-ሰር ያጠናቅቃል። ሁሉም የቪዲዮ ተወዳጅነት የኩባንያው መድረክ እገዛ ያስፈልገዋል. ለእያንዳንዱ ተጨማሪ ለታዋቂዎች እና የኔትዎርክ ገበያተኞች መሰል እና ተከታይ ነጋዴው መድረኩን ከ10 እስከ 35 ብር ሶል ይሰጦታል፣ መድረኩ ከ5 እስከ 25 ብር ይሰጠናል፣ መድረኩ ከ5 እስከ 10ብር ገቢ ያስገኛል። ኩባንያው ወደ ኢትዮጵያ ገበያ ከገባ ወዲህ አዲሱ የገንዘብ ማግኛ ሞዴል በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ፍቅርና ድጋፍ የተደረገለት ሲሆን መድረኩም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየዳበረ መጥቷል። ነገር ግን አንዳንድ ህግ ተላላፊዎች የኛን የንግድ ስራ ሞዴል በመኮረጅ ወሬዎችን በማሰራጨት ድርጅታችንን አበላሽተውታል። የኩባንያው የህግ ክፍል በምርመራ እና ማስረጃ ማሰባሰብ ጊዜ ከተረጋገጠ ለፖሊስ ተላልፎ ይሰጣል! በተመሳሳይ ጊዜ አባላት፣ እባክዎ ልብ ይበሉ፣ የኩባንያውን ብቸኛ LOGO እና ይፋዊ የማውረጃ ማገናኛን ይፈልጉ። አንድ ሰው ሌሎች መተግበሪያዎችን እንዲያወርዱ ለመፍቀድ መልእክት ከላከለት አትመኑት። በሌሎች መተግበሪያዎች ውስጥ ከተታለሉ ከኩባንያው ጋር ምንም ግንኙነት የለውም! ችግሮች ካጋጠሙዎት፣ እባክዎ የኩባንያውን የደንበኞች አገልግሎት እና የቡድንዎን አስተዳዳሪ ያነጋግሩ። VIP ስያሜ ሲሆን ማንኛውም አባል FIAS ላይ ሲመዘገብ የሚሰጠው መጠሪያ ነው ሲሆን 6 አይነት VIP አሉ። እነሱም VIP0, VIP1, VIP2, VIP3, VIP4, VIP5 ናቸው። ስለዚህ አባላት አንድዬ አቅማቸው መጠሪያቸው መግዛት ይችላሉ። ይህም ሲባል ሁሉም አባል መጀመሪያ ሲመዘገብ VIP0 ሆኖ ሲሆን አንደፍላጎቱ የመረጠውን የVIP ስያሜ መግዛት ይችላል። 1.VIp0: 3 ተግባራትን ብቻ ማጠናቀቅ ይችላል እና ገንዘብ ማውጣት የሚችለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው (100ብር) 2.VIp1 :1000ብር ይከፍላል። በየቀኑ 4 ተግባራትን ያጠናቅቁ ፣ እያንዳንዱ ተግባር 6ብር ፣ የቀን ገቢው 24ብር ፣ ዓመታዊ ገቢው 8640ብር ነው። 3. vip2 3000ብር ይከፍላል። በየቀኑ 6 ተግባራትን ያጠናቅቁ ፣ እያንዳንዱ ተግባር 14 ብር ፣ የቀን ገቢው 84 ብር ፣ ዓመታዊ ገቢው 30240 ብር ነው። 4. vip3 6000ብር ይከፍላል። በየእለቱ 11 ስራዎችን ያጠናቅቁ ፣ እያንዳንዱ ስራ 16ብር ፣ የቀን ገቢው 176ብር ፣ ዓመታዊ ገቢው 63360ብር ነው። 5. vip4 10000ብር ይከፍላል። በየእለቱ 17 ስራዎችን ያጠናቅቁ ፣ እያንዳንዱ ስራ 18ብር ፣ የቀን ገቢው 306ብር ፣ ዓመታዊ ገቢው 110160ብር ነው። 6. vip5 30000ብር ይከፍላል። በየቀኑ 38 ስራዎችን ያጠናቅቁ ፣ እያንዳንዱ ተግባር 25ብር ፣ የቀን ገቢው 950ብር ነው። አመታዊ ገቢ 342000ብር ማሳሰቢያ፡-VIp0 3ተግባራትን ብቻ ማጠናቀቅ ይችላል እና ገንዘብ ማውጣት የሚችለው አንድ ጊዜ ብቻ ነው (100ብር) የVIp ደረጃን ያሻሽሉ ፣ በየቀኑ ተጨማሪ ኮሚሽኖችን ማግኘት ይችላሉ ፣ የVIp ደረጃው በየቀኑ የሚወጣውን መጠን ሳይገድብ ሊወጣ ይችላል ፣ የVIp ደረጃውን ያሳድጉ ፣ ተቀባይነት ያለው ጊዜ 365 ቀናት ነው ፣ እና ጊዜው ሲያበቃ ሊታደስ ይችላል:: #_መልካም_እድል!!! https://fias777.com/#/pages/register?invite_code=4fsT2ZyL&t=1651737934677

የምታገኘው እርካታ በምትኖረው እወነታ ውስጥ ነው ። ባልሆንከው ጉዳይ ፣ በማይገልፅህ አስመሳይነት ከምትወደድ ፣ በሆንከው በእውነተኛ ማንነትህ ፣ በትክክለኛው ስብዕናህ ብትጠላ ፣ ብትገፋ ይሻልሃል ። ንግስናህን የሚያቆየው አስመሳይነትህ ሳይሆን እውነተኛነትህና አንተነትህ ነው ። በሆንከው ብትጠላ አንድ ቀን ልትወደድ ትችላለህ ፤ ባልሆንከው ብትወደድ ግን እውነታው ሲታወቅ ዳግም የመወደድና የመታመን እድልህ ያበቃል ። አዎ! ጀግናዬ..! እራስህን ሆነህ ተጠላ ፤ አስመስለህ አትወደድ ። ታማኝ ሆነህ ተገፋ ፤ ከሃዲ ሆነህ አትመረጥ ። እውነተኛ ሆነህ ተጎዳ ፤ ክሰር ፤( አጭበርብረህ አትጠቀም ፤ አታትርፍ ። እውነተኛው እርካታ በምትኖረው እወነታ እንጅ ባስመሰልከው ውሸት ውስጥ አይገኝምና ። Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

ድምፅህን አጥፍተህ ተለወጥ! የራስህን ዋጋ ስታውቀው ዋጋቸውን ያልተረዱ ሰዎች ያሳዝኑሀል ፤ አንተ ከልብህ መለወጥ ስትጀምር ሌሎች እንደፈዘዙ ታያለህ ፤ መሮጥ ስትጀምር ብዙዎች ቆመው እንደቀሩ ትታዘባለህ ። ብትነግራቸው ግን አይሰሙህም ፤ ሰዎች ብዙ ርቀት ላልተጓዘ ጆሮ አይሰጡም ፤ ለዛ ነው ድምፅህን አጥፈተህ እስከጥግ መለወጥ ያለብህ ። መጀመሪያ አንተ ሳትቀየር ሌሎች እንዲቀየሩ አጠብቅ! ለምትወዳቸው የምትደርሰው አንተ ቆራጥ ሆነህ ያመንክበትን ስታሳካ ነው ፤ ያኔ ስኬትህ ጮክ ብሎ ይናገራል! Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

ውሳኔ ህይወትክ ውስጥ ምን ትፈልጋለክ ? ምን ማግኘት ? ምን እንዲሆንልክ ትፈልጋለክ ? መጀመሪያ የምትፈልገውን በግልፅ አስቀምጥ ቀጣይ ምን እንደሚያስፈልክ ምን እንደሚጠበቅብክ ለይ መቁረጥ መተው ያለብክንም ለይ መጨረሻ ላይ ወስን በህይወትክ 📌 መመኘት ነው ማግኘት ነው የምትፈልገው ? 📌ማለም ነው መኖር ? 📌ማሰብ ነው መተግበር ? ታድያ ወስና "ውሳኔ የተግባር አባት ነው ያልወሰነ አይተገብርም" Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

የነጋበት ጅብ ሰዎችን በብዛት ሲያይ መደነባበርና መሯሯጥ ይጀምራል፤ ምንም ያኽል ጠንካራ ቢሆንም በዛ ሰዓት ግን የሱ መገኛ ስላልሆነ አቅሙ ይከዳዋል! እናም መሸሸጊያ ፍለጋ ይራወጣል! የሰው ፍጥረትስ መሆን እና መኖር ባለበት ጊዜና ቦታ ጎድሎ ቢኖር በንጋቱ ሰዓት ማሟላትና መሆን የነበረበትን ስላልሆነ ምሽግ ይፈልግ ይሆን??? ለሱ የተፈቀደለትን ጊዜ ሳይጠቀምበት ከሌሎቹ ላይም ሰርቆ ሲኖር ምድር በተተኪዎች ስትመላ አቅሙን ማጣት ይጀምር ይሆን??? ለሀሉም ፍጥረት ተሰፍሮ የተሰጠው ጊዜ አለ፡ በመጀመሪያ ያን ጊዜ አስቀድሞ ማወቅ መልካም ነው። ሲቀጥል ያቺን ጊዜ መከፋፈልና እንደአስፈላጊነቱ መመደብም አስፈላጊ ነው። 'ሚጠበቅብንን ከሰራን የንጋት ጸሐይ ስትፈነጥቅ ምንሸሽ ሳይሆን በሐሴት የምንጎማለልባትና የምንሞቃት ነው ሚሆን!!! Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

ታሪክህን የሚቀይረው ከፈጣሪ ቀጥሎ የራስህ አመለካከትህ ነው ። ወዳጄ ደስተኛ መሆን ራስህን ወደ ጥሩ መንፈስ መውሰድ ከፈለክ መልካም ነገሮች አስብ ፤ የተሰጠህን ተመልከት ፣ ጤናህን ፣ ቤተሰቦችህን ፣ ሀይማኖትህን በዙሪያህ ያለውን ነገር ተመልከት ። ተስፋ መቁረጥ ባንተ አያምርም! ማዘን መከፋት ባንተ አያምርም! ህይወት አጭር ናት እንኳን ለማዘን ለመደሰትም እኮ አትበቃህም ፤ ወዳጄ ሁልጊዜም ሰላም ከሚሰጡህ ነገሮች ውጪ ሌላ ነገር ማሰብ የለብህም ። Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

#_ወዳጄ_ሆይ #ላም ለመንደሩ ሙሉ የሚሆን #ወተት ታልባ እንኳ ምንም #አትጮህም ። #ዶሮ ግን ለአንድ ህፃን ልጅ ቁርስ እንኳን የማይሆን #እንቁላል ጥላ ሀገር ምድሩን በእወቁልኝ #ጩኸት ታናጋዋለች ። ስለዚህ ወንድሜ #የሚጮህ ሁሉ ቁም ነገር የሰራ አይምሰልህ ። #በዝምታ ከጎናችን ሆነዉ ትልልቅ ነገሮችን የሚሰሩ ትልልቅ ሰዎች አሉ ። አስተዉለን እንጓዝ !! Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

አንተ ብቻ ታገስ ! ነገሮች ባሰብናቸው መንገድ አልሄድ ሲሉን ፤ ሁሉ ነገር አልሳካ ያለን ሲመስለን ፤ ጥቃት ደረሰብኝ ስንል ሁሌም ለምን እኔ ላይ ይህ ሁሉ ሆነ ፈጣሪን ምን ብበድለው ነው እንዲህ ያደረገኝ እንላለን ችግር ውስጥ ነን ብለን ባሰብንበት ወቅት ነገሮች መቼም ቢሆን ታሪካቸው እንደሚቀየር አናስብም ወንድሜ እስኪ አስታውስ ከዚህ ቀደም በህይወትህ ላይ የገጠሙህን ችግሮች አስባቸው የሚያልፋ የማይመስሉ ከባድ ጊዜያትህን አስታውሳቸው መቼ እንደተቀየሩ እንኳን ሳታውቅ ከህይወት ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ተወግደዋል አይደል ዛሬም ልክ እንደዛው ነው ያሉብህ እያንዳንዱ ችግሮችህ መቼ እንደሆነ በማታውቀው ሰዐት ከህይወትህ ሙሉ ለሙሉ ይወገዳሉ አንተ ብቻ ታግሰህ ጠብቅ። Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

"የደፈረሰን ውሃ ማንፃት የምትችለው ስትተወው ብቻ ነው" በሁላችንም ህይወት እጅግ ለፍተንበትና ደክመንበት አልሳካ ያለ አንድ ነገር አለ ፡፡ እናም አልሳካ ያለን ነገር የሆነ እኛ ወይ ፈጣሪ ያጎደልነው ነገር ስላለ መስሎ የሚሰማን ጥቂቶች አይደለንም ፡፡ በዚህም የተነሳ በመማረርና በማማረር ከእራሳችን ጀምሮ በዙሪያችን ያሉ ሰዎችን አልፎም "ነገር ሁሉ በግዜው ውብ አድርግ የሰራን" ፈጣሪ እናሳዝናለን ፤ እናስከፋለን ፡፡ ነገር ግን እያንዳንዱ ክስተት በእኛ የእውቀት ደረጃና ብልጠት የሚሆን ቢመስለንም ግን አይደለም ፤ ሁሉም የሚሆነው እሱ እንዲሆን በፈቀደበት ግዜ ነው ፡፡ ስለሆነም በተደጋጋሚ ሞክረን ከእኛ አቅም ውጪ የሆነ ነገሮችን አንዳንዴም መተው ብልኸነት ነው ፡፡ እዚህ ጋር ግን "መተው" ሲባል ተስፋ መቁረጥ ማለት አይደለም ፡፡ እኛ አቅማችን ያልቻለውን ነገር አሳልፎ ለፈጣሪ መስጠት እንጂ ፡፡ Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

አንቴን ሊያቆም የምችል አንዳች ሀይል የለም። ራስህን እመን ወዳጄ በዝህ አሌም ላይ የማይቻል ነገር የለም ነገር ግን ችሌ እስክታሳያቸው የሚቻል አይመስልም ስለዝህ አድርገህ አሳያቸው መልካም እሁድ ተመኝው Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

ማመስገን አታቁም ! የጎደለህን አትቁጠር የተሰጠህን አስብ ፤ ብዙ ያልጠበካቸዉ መልካም ነገሮች በህይወትህ ብዙ ጊዜ ደጋግመዉ ተከስተዋል ፤ የዛሬዉ ቀን አንዱ ስጦታ ነዉ ። ትናት ሲስቁ ዉለዉ ዛሬ ጠዋት ግን ከእንቅልፍቸዉ ያልነቁ ብዙ ሰዎች አሉ ፤ ይሄንን ፅሁፍ ለማንበብ ቢያንስ መተንፈስ አለብህ ፤ በህይወት እስካለህ ደግሞ የማይስተካከል ነገር የለም ። ወዳጄ መስጠት በማይሰለቸዉ ፈጣሪህ ማመስገን አትሰልች ! Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

👉 ተወዳጁ FIAS777 ከ 1,000 ብር ቦነስ ስጦታ ጋር በቴሌግራም መቷል አሁኑኑ ይቀላቀሉን ስልኮን ብቻ በመጠቀም በወር እስከ 30,000 ብር ተከፋይ ይሆናሉ 👉 የFIAS777 ቦትን ተጠቅመው ሲመዘገቡ የ 1,000 ብር ስጦታ በተጨማሪም 1 ሰዉ ወደ ቦቱ ሲጋብዙ በየቀኑ የ 100 ብር ቋሚ ክፍያ 👉ዛሬውኑ ይጀምሩ ስኬትን ከ Fias777 ጋር ያጣጥሙ!! https://fias777.com/#/pages/register?invite_code=4fsT2ZyL&t=1651737934677 https://fias777.com/#/pages/register?invite_code=4fsT2ZyL&t=1651737934677

ተመስገን በል! ካጣነው ይበልጥ ያገኘነው ይበልጣል፤ ከተደረገብን ይበልጥ የተደረገልን ይበልጣል! እጅህ ላይ ያሉትን ነገሮች አላየህም እንጂ ካንተ በላይ እድለኛ የለም! አጠገብህ ያሉት ቤተሰቦችህ ባይኖሩ የሚሰማህን ባዶነት አስበው እስኪ፣ መተንፈስ ባትችልና ራስህን ማወቅ አቅቶህ በአልጋ ብትቀር ምን እንደሚሰማህ አስበው እስኪ? አየህ ይሄን ስታስብ ነው የፈጣሪ ቸርነትና ላንተ ያደረገው ግልጥ ብሎ የሚታይህ! ተመስገን በል ወዳጄ! Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

👉ጠላታችን ያለው አይምሯችን ውስጥ ነው፤ እስክንሞት የሚያስጨንቀን...የሚያንገበግበን... ሊሰብረን ሊያቆመን የሚታገለን...ህልማችንን ሊያዳፍን የሚዋጋን...በቃ ፍልሚያው ጭንቅላት ውስጥ ነው! ባንክ የቆጠብናት አካውንት ውስጥ አይደለም! ስራችን ውስጥ አይደለም! ግንኙነት ትዳራችን ውስጥ አይደለም! ወዳጄ በሰዎች አዝነህ ልብህ እንዳይሰበር ውጊያው አይምሯችን ውስጥ ነው! Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

"ዛሬን ተጨነቅና ቀሪ ዘመንህን በደስታ ኑር እለዋለው ራሴን" ይለናል ታላቁ ስፖርተኛ መሀመድ አሊ። አንተም አሁኑኑ ልደሰት አትበል! ለገንዘብ መስራት አቁመህ ገንዘብ ላንተ መስራት እስኪጀምር ጠንክረህ ስራ። የዚህ አለም ስኬት ትንፋሹን ለረጅም ጊዜ ተቆጣጥሮ ደስታውን ለሚያዘገይ ነው። Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

ሁሉም ነገሮች የሚሆኑት በምክንያት ነው፤ ስለማትቀይራቸው ነገሮች አትጨነቅ! እንደዛ እያደረክ ከሆነ ንፋስን እየተከተልክ ነው፤ ስለዚህ የትም አትደርስም! ወዳጄ ሌላውን ትተህ ወደራስህ ተመልከት! እህቴ የሚያዋጣሽ ስለምትቀይሪው ነገር ማሰቡ ነው! Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

ሁሉም ነገሮች የሚሆኑት በምክንያት ነው፤ ስለማትቀይራቸው ነገሮች አትጨነቅ! እንደዛ እያደረክ ከሆነ ንፋስን እየተከተልክ ነው፤ ስለዚህ የትም አትደርስም! ወዳጄ ሌላውን ትተህ ወደራስህ ተመልከት! እህቴ የሚያዋጣሽ ስለምትቀይሪው ነገር ማሰቡ ነው! Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

ማዘን ከፈለክ ብዙ ምክንያቶች መደርደር ትችላለህ፣ ብዙ የጎደሉህ ነገሮችን እያሰብክ መብሰልሰል ትችላለህ፤ ልደሰት ስትል ግን በምን እንደምደሰት እንኳን አላውቅም ልትል ትችላለህ። እኔ ግን ልንገርህ እየተነፈስክ መሆኑ ብቻ ሊያስደስትህ ይገባል ምክንያቱም ትንፋሽህ እስካልቆመ ድረስ ምንም ነገር ለማሳካት እድሉ አለህ። ድጋሚ ለመማር፣ ድጋሚ ለመስራት፣ ድጋሚ ንግድ ለመሞከር፣ ድጋሚ ለማፍቀር ብቻ ብዙ እድሎች አሉህ። ታዲያ ከዚህ በላይ ምን ደስ የሚል ነገር አለ? ከሁሉ በላይ ደግሞ የሚጠብቅህ የሚወድህ በመንገድህ ሁሉ የሚቀድም ፈጣሪ አለ። ተደሰት ወዳጄ! Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

አስተውላችሁ ከሆነ በአንድ ቀስት ብዙ ኢላማ መምታት አትችሉም፤ ምክንያቱም አንድ ቀስት ለአንድ ኢላማ ብቻ ነው የሚሆነው እሱንም አሪፍ አድርጋችሁ ማነጣጠር ከቻላችሁ። በህይወትም ብዙ ስራ ብዙ ቢዝነስ ስለሞከራችሁ ስኬታማ ትሆናላችሁ ማለት አይደለም፤ ደስ የሚለው ብዙ በሞከራችሁ ቁጥር ስኬታማ የሚያደርጋችሁን ዘርፍ እየለያችሁ ትመጣላችሁ። በተቻለን አቅም አንድ ስራ ከዳር ሳናደርስ ሌላ መጀመር የለብንም አለዛ ጎዶሎ ነገር ይበዛብንና ከአንዱም ሳንሆን እንቀራለን። Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni4600

አንድ ነገር አስታውስ ሰዎች የሚሰጡህ ዋጋ ራስህ ባወጣኸው መሰረት ነው፤ ውድ ነኝ ብለህ አስበህ ራስህን አክብረህ ከኖርክ ሁሉም ውድ እንደሆንክ አምኖ ያከብርሀል። ራስህን ካራከስክ እና ለራስህ ያለህ ግምት ዝቅ ያለ ከሆነ ምን ትጠብቃለህ ሁሉም ሰው ዝቅ አርጎ ያይሀል፤ ምርጫው ያንተ ነው። ራስህን ከፍ አርገህ ሰዎች ባይቀበሉህ እንኳን ላንተ ያላቸው ክብር አይቀንስም እንደውም በውጣቸው "እሱ ግን ራሱን እንደማን ነው ሚያስበው? እኔ የእሱ ድፍረትና በራስ መተማመን ቢኖረኝ የት እደርስ ነበር" ይላሉ። ወዳጄ አይነግሩህም እንጂ ድብን አርገው ነው የሚቀኑብህ። ራስህን አክብረው ወዳጄ! Yoni motivation ለአነቃቂ ጽሑፎች የቴሌግራም ቻናላችንን ግቡና Join አድርጉ ከተመቻችሁ share አርጉ !! Yoni https://t.me/yoni4600 https://t.me/yoni460