cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ታላቁ ተልዕኮ አገልግሎት 🌍

ማቴዎስ 28 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁸ ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ። ¹⁹-²⁰ እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤ እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። @Goldenmission @Goldenmission1

Більше
Рекламні дописи
198
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

.....“አንተ ግን ነገርን ሁሉ በልክ አድርግ፥ መከራን ተቀበል፥ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ አድርግ፥ አገልግሎትህን ፈጽም።”   — 2ኛ ጢሞቴዎስ 4፥5 “But be self-controlled in all things, do without comfort, go on preaching the good news, completing the work which has been given you to do.”   — 2 Timothy 4፥5 (BBE)
Показати все...
"ኃጢአትህን ለማጽደቅ መሞከርህን አቁም ኢየሱስ የሚፈልገው ይህን አይደለም። እና ለማንኛውም ማመካኘት አይችሉም። ለምን እንደሰራህ እግዚአብሔር ያውቃል፣ እና ምንም ማለት አትችልም ምንም አዲስ መረጃ ወደዚያ ሊጨምር አይችልም። ለዚህ ነው ኢየሱስ ንስሀ እንድትገቡ፣ ከእግርህ እንድትወርድ እና በምትኩ እሱን እንድትከተል የሚፈልገው። የክርስትና ሕይወት ኃጢአት አለመሥራት አይደለም; የክርስትና ሕይወት ኃጢአት ስትሠራ በምትሠራው ነገር ላይ ነው... ክርስቲያኖችም ሲበድሉ ንስሐ ግቡ። ‹ንስሐ መግባት› ማለት አእምሮህን መለወጥ እና በእግዚአብሔር ነገሮች፣ በእግዚአብሔር መንገድ እና በእግዚአብሔር ተፈጥሮ ላይ ማተኮር ነው። በሌላ አገላለጽ፣ በእውነት ንስሐ መግባት ማለት ለሠራችሁት ኃጢአት ሀሳባችሁን በመቀየር ስለዚያ ኃጢአት ያለዎት እምነት ይለወጣል፣ ይህም ወደ ባህሪ ለውጥ ያመራል። ኃጢአት መሥራታችሁን ትቀጥላላችሁ፣ ነገር ግን ንስሐ መግባታችሁን ስትቀጥሉ፣ በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ኃጢአትን እየቀነሰ ትሠራላችሁ። “ኃጢአት አልባነት” ሳይሆን ኃጢአት-አልባነት። ፴፭ እናም ይህ ወደ ዘላለማዊነት ያበቃል፣ ኃጢአታችን ሁሉ ሲታጠብ እና በአዲስ ምድር ከኢየሱስ ጋር የጽድቅ ህይወት ለመኖር ስንመርጥ (ራዕይ 21፡1-4)። ስለዚህ ኃጢአትህን ማጽደቅ አቁም። ይልቁንስ ንስሀ ግባ፣ ሃሳብህን ቀይር እና ከኢየሱስ ጋር እንደገና ተጓዝ። ማሰብዎን ይቀጥሉ! ..."
Показати все...
ተቋርጧል? ወይስ የለም? የሁለቱ ቪድዮዎች አሳብ በአጭሩ። ባለፉት ሁለት ቪድዮዎች ስለ ሴሴሽኒዝም ጉዳይ ባልታሰበ መንገድ ተጀምሮ ብዙ አወዛገበ። የኔ የመጀመሪያ ልጣፍ November 22 የለጠፍኩት ወደፊታዊ ትንበያን ብቻ የተመለከተ ነበር። ኋላ፥ የጸጋ ስጦታዎች ቀርተዋል የምል አድርገው አንድ ሁለት ሰዎች በርዘው አቀረቡትና ጉዳዩ ወደ ‘ተቋርጧል? አልተቋረጠም?’ ንትርክ አመራ። ንትርክ ትክክለኛ ቃል ይመስለኛል። ነገሩ ተባብሶ ጥቂት ነገሮችን ጨምሬ እንድጽፍና ሁለት ቪድዮዎችን እንድሠራ ሆነ። በመጀመሪያ አሳቤን በጽሑፍ ብቻ ለማካፈል ነበር አሳቤ። ብዙ ጊዜ ስለሚወስድና ከሥራ ጋር ስለማይመቸኝ አቆየሁት።ቪድዮው ተጨማሪ ሰዎችን ስለሚደርስ በማለት በቪድዮ አደረግሁት። ስለ ‘ተቋርጧል? አልተቋረጠም?’ ጉዳይ የሁለቱ ቪድዮዎች ዋና አሳብና የመጨረሻ ማጠቃለያዬ በጣም አጭር በሆነ ጽሑፍ ይህ ነው። ቪድዮው ወደ ጽሑፍ እየተቀየረ ነው፤ ሲያልቅ በቴሌግራም ገጼ አስቀምጠዋለሁ። ተቋርጠዋል የተባሉት አራት ተአምራውያን ስጦታዎች፥ #ፈውስ፥ #ልሳን፥ የልሳን #ትርጉም፥ እና #ትንቢት ናቸው። የተቋርጧላውያን መነሻዎች አራት መሆናቸውንና፥ አራቱ መነሻዎች፥ ስጦታዎቹ አሉታዊና አፍራሽ ሚና መጫወታቸው፥ ቃሉ ሙሉና በቂ መሆኑ፥ ምልክቶች ከሐዋርያት ጋር መቅረታቸው፥ እና ቃሉ ይቀራሉ ይሻራሉ ማለቱ ናቸው። አራቱም ሕጋውያን መነሻዎች ቢሆኑም አራቱም መቋረጣቸውን አረጋጋጭ አለመሆናቸውን አብራርቻለሁ። ይሁን እንጂ ቃሉ ጥቂቱን፥ ‘ይሻራሉ ይቀራሉ’ ስለሚል፥ ‘ተሽረዋል እና ቀርተዋል’ የሚሉ ክርስቲያኖች ከቃሉ ስለሚንደረደሩ የሳቱ ወይም የተሳሳቱ አይደሉም። በሁሉ ነገር እገሌ እኔን መምሰል የለበትም። እኔም እርሱን መምሰል የለብኝም። ወደ ስጦታዎቹ በመግባት አራቱንም ስጦታዎች በዝርዝር ተመልክቼአቸዋለሁ። 1. ፈውስ ቀርቷል? ተቋርጧል? አልቀረም፤ አልተቋረጠም። ነገር ግን ፈውስ እንደ ጌታ ፈቃድ የሚሆን እንጂ ሰዎች ብልጭ ድርግም የሚያደርጉት ነገር አይደለም። ደግሞም ፈውስ ሲኖር የሚታይና የሚታወቅ ክስተት ነው። የውሸት ፈውሶች ቢኖሩም፥ በፈውስ ስም ብዙ ማጭበርበሮች ቢደረጉም፥ ፈውስ አልተቋረጠም። 2 እና 3. ልሳንና ትርጉም ተቋርጠዋል? ቀርተዋል? አልቀሩም፤ አልተቋረጡም። ተለማምደውና አለማምደው የሚናገሩት ልሳን እርሱ ጸጋ አይደለም። እውነተኛው ልሳን እንደ ሐዋ. 2 ያለው ተናጋሪዎች የማያውቁት፥ ሰሚዎች የሚያውቁት ቋንቋ ነው። እውነተኛው የጉባኤ ልሳንና ትርጉም ደግሞ በ1ቆሮ. 14 እንደተጻፈው ያለው ነው። በተጻፈበት መልኩ ከተደረገ ይህ ዛሬም ያለ ጸጋ ነው። ልሳን የመንፈስ ጥምቀት ወይም ሙላት ምልክት ተብሎ ጉባኤ ሁሉ የሚናገርበት ጫጫታ፥ ጳውሎስ እብደት ያለው ልምምድ ነው። ይህ የሰው ሥራ ነው። እውነተኛው ልሳንና ትርጉም ግን አልቀረም፤ አልተቋረጠም። 4. ትንቢት ቀርቷል? ተቋርጧል? አልቀረም፤ አልተቋረጠም። ትንቢት ያለንበትን ዘመንና ሁኔታ መናገር ነው። ትንቢት ቅዱስ ቃሉን መግለጥ ነው። ትንቢት እንደ ጸጋ፥ ነቢያትም እንደ ስጦታ ለቤተ ክርስቲያን እነጻ ተሰጥተዋል። ትንቢት ወደፊት ስለሚሆኑ ነገሮችም የተነገረበት መሆኑ በታሪኮች ውስጥ ተጽፎአል። በታሪኮች ውስጥ የተጻፉ ነገሮች ሁሉ ትእዛዛት አይደሉምና አይደጋገሙም። በትንቢት ጸጋ ስም ስለ ወደፊቱ መጻኢ ዘመን መናገር እንደ ጸጋ ስጦታ በቃሉ ውስጥ አልተጻፈም። ነቢያትና ትንቢቶች በአዲስ ኪዳን ቤተ ክርስቲያናት ውስጥ ምን እንዳደረጉ ስንመረምር በቀጣይ ዓመታት የሚሆኑትን ክስተቶች ሳይሆን መምከር፥ ማጽናት፥ መላክ፥ ቅዱሳንን ማነጽ እና የመሳሰሉትን ተግባራት ሲፈጽሙ እንጂ ወደፊታዊ ትንበያዎችን ከመንፈሳዊ ዓለም እየተቀበሉ ሲያድሉና ሲነሰንሱ አይታዩም። ትንቢት ቀርቷል? ተቋርጧል? አልቀረም፤ አልተቋረጠም። ወደፊታዊ ትንበያ ግን ሲጀመርም የጸጋ ስጦታ አይደለም። ደግሜ እላለሁ፤ አይደለም። እኛ ስለ ነገ እንድናውቅ ወይም እንድንጨነቅ ሳይሆን ስለ ነገ በጌታ እንድንታመን ነው የተነገረን። ይህ ስለ ነገ ማወቅ የሚባለው ነገር ጸጋ እንዳልሆነ ሲነገር እጅግ የሚያስጨንቃቸውና የሚረብሻቸው ሰዎች አሉ። እነማን ናቸው? ቢባል፥ ሀ) ዋናዎቹ ስለ ነገ ከመንፈስ ዓለም እየቀዱ የመናገር ስጦታ ያላቸው የሚያስመስሉ እየጠነቆሉ ገንዘብና ዝና የሚሠሩ ‘ነቢያት ነን’ የሚሉ ነጋዴዎች እና ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ናቸው። ወደፊታዊ ትንበያን በትንቢት ስም ስለሚነግዱበት። ለ) ነገን አስይዘው ቁማር መጫወት የሚወዱ፥ ከተበሉ (ሁሌም የተበሉ ሰዎች ናቸው) ‘ወየሁ ከሰርኩ!’ የሚሉ እያስጠነቆሉ በአቋራጭ መበልጸግ የሚወድዱ ሰዎች፤ ሐ) ቃሉን በማንበብና ደቀ መዝሙር በመሆን ፈንታ ዋጋ ባለመክፈል መጓዝ እና ያደጉ ለመምሰል የሚፍጨረጨሩ እየተማሩ እውነትን ለማወቅ ያልወደዱ ሰዎች ናቸው። እነዚህ ስጦታዎች ባይቋረጡም በአካሉ ውስጥ ጉዳት ፈጣሪዎች በመሆናቸው፥ ስጦታዎቹንም ቀውሶቹንም ከመንፈስ ቅዱስና ካሪዝማዊ ቀውሶች መጽሐፌ ጀምሮ ቀደም ባሉት በርካታ ዓመታት በብዙ መጣጥፎችና ትምህርቶች ዳስሻቸዋለሁ። እዚህም ያንኑ አድርጌአለሁ። የለወጥኩት ምንም ነገር የለም። ብለውጥ፥ ‘ለወጥኩ’ ለማለት ወይም ብሳሳት፥ ‘ተሳስቼ ነበር’ ለማለት አልፈራም፤ አላፍርምም። ተቋርጧላዊ ብሆን፥ ‘ነኝ’ ለማለትም ምንም አይከለክለኝም። ብዙዎች በአንዳንድ ጉዳዮች ደፍረው መጻፍ ባይሆንላቸውም አይገርመኝም። አንዱ ለስሕተት አሠራር ከሌላው ይበልጥ የተጋለጠ ቢሆንም ቅሉ፥ ሁለቱም ወገኖች (ተቋርጧላውያንም፥ ቀጥሏላውያንም) ክርስቲያኖች መሆናቸውን አልጠረጥርም። እንደገና ስደመድም፥ አራቱም ስጦታዎች ቀርተዋል? ተቋርጠዋል? አልቀሩም፤ አልተቋረጡም። የተቋረጠ ጸጋ የለም። በአንዳንዶች ዘንድ እንዳለ የሚቆጠርና የሌለ ወደፊታዊ ትንበያን መከተል ግን ላም ባዋለበት ኩበት ለቀማ ነው። ይህንን ጉዳይ አንጠፍጥፌ ጨርሻለሁ። ዘላለም ነኝ።
Показати все...
የእምነት አቋም 1. በሶስትነትና በአንድነት በሚኖር በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ ቅዱስ አንድ አምላክ እናምናለን። 2. ሰው በእግዚአብሔር አምሳል መፈጠሩን በኃጢአት መውደቁን እና በኢየሱስ ክርስቶስ እስከሚያምን ድረስ የእግዚአብሔር ቁጣና ፍርድ ያለበት በደለኛ መሆኑን እናምናለን፡፡ ከኃጢአት ዕዳ ኃይልና ቅጣት ሰው ሊድን የሚችለው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ እንደሆነ እናምናለን፡፡ 3. መጽሐፍ ቅዱስ ዘላለማዊና የማይሻር የእግዚአብሔር ቃል እንደሆነ እናምናለን፡፡  4. ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ፤ ፍፁም አምላክ ፍፁም ሰው መሆኑን፤ እኛን ለማዳን ከድንግል ማሪያም መወለዱን፤ ለአዳም ዘር ሁሉ ስለ ኃጢአታቸው ሲል ሞቶ መቀበሩን፤ በአካል ከሙታን ተነስቶ በክብር ማረጉን፤ በአብ ቀኝ መቀመጡን፤ ዳግመኛም በታላቅ ክብርና ኃይል ለፍርድ እንደሚመለስ እናምናለን፡፡ 5. መንፈስ ቅዱስ በዚህ ዘመን በአማኞች ሕይወት እንደሚሰራ ለአገልግሎታቸውም ኃይልን እንደሚያለብስ እናምናለን፡፡ 6. ቅዱሳን መላዕክት ሕያዋን መሆናቸውን፤ በእግዚአብሔር ፊት እንዳሉ፤ ቅዱሳንን እንደሚያገለግሉ፡፡ ሰይጣን በእግዚአብሔር ያመጸ የውሸት አባት መሆኑን እና በመጨረሻም ወደ ተዘጋጀለት ወደ ገሃነም እሳት እንደሚጣል እናምናለን። 8. በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያምኑ በቅድስና መመላለስ እንዳለባቸው እናምናለን፡፡ በክርስቶስ ኢየሱስ ያመነ ሰው፣ በክርስቶስ ሞት እና ትንሳኤ መተባበሩን ለመግለጽ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በውሃ ውስጥ በመጥለቅ መጠመቅ እንዳለበት እናምናለን፡፡ 9. የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋ እና ደም ዳግመኛ ልደት የተቀበሉ የውኃ ጥምቀት ሥርዓት የፈፀሙና ራሳቸውን መርምረውና ፈትነው ያዘጋጁ ምዕመናን መውሰድ እንደሚችሉ እናምናለን፡፡ 10.የክርስቶስ አካል በሆነች ከእግዚአብሔር መንፈስ ዳግም የተወለዱ ሁሉ በሚገኙባት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን፡፡ 11. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር እንደገና ሲመጣ፣ በእርሱ አምነው የሞቱት ቀድመው እንደሚነሱ ሕያዋን የሆኑት ደግሞ እርሱን ለመቀበል እንደሚነጠቁ ኃጥአን ግን ወደ ዘላለማዊ ስቃይ እንደሚሄዱ እናምናለን:: @Goldenmission
Показати все...
Repost from Zelalem Mengistu
መልእክተ ይሁዳ
Показати все...
መልእክተ ይሁዳ.pdf9.85 KB
ኢየሱስ በዕብራውያን መፅሃፍ ልጅ የዕብራውናን መፅሃፍ ኢየሱስ እርሱ የእግዚብሄር ልጅ እንደሆነ ይናገራል። “በዚህ መጨረሻ ዘመን ግን ሁሉን ወራሽ ባደረገውና ዓለማትን በፈጠረበት #በልጁ ለእኛ ተናገረን።”    ዕብራውያን 1፥2 (አዲሱ መ.ት)          ይህ ልጅ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ አለማትን የፈጠረ የእግዚአብሄር አብ የክብሩ ነፀብራቅና የባህሪው ምሳሌ ሆኖ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እንደሚደግፍ መላዕክት እንደሚሰግዱለት ሰማይና ምድርን እንደሚጠቀልላቸው ደግሞም ሃጢያታችንን በራሱ ማንፃቱን ተገልጿል።እውነትም እርሱ መፅሃፍ እንዳለው እንዲሁ ነው ብለን አምነናል። የእግዚአብሔር ልጅ ማለት ምን ማለት ነው?          ጳውሎስ ፍቃዱ  የእግዚአብሔር ልጅ በተሰኙ የዳጎሰ መፅሃፉ እንዲህ ብሏል ።           "አብ አባት ካለመሆን ወደ መሆን አልተለወጠም ።ወልድም ልጅ ካለመሆን ወደ መሆን አልመጣም ።የአብ አባትነትና የወልድ ልጅነት ወልድ ሰው ሲሆን የጀመረ አይደለም።ወልድ ሁሌም ሰው አልነበረም ።በታሪክ ወስጥ ነው ሰው የሆነው የዛሬ ሁለት ሺ አመት ።ነገር ግን ወልድ ሁሌም የእግዚብሄር ልጅ ነበር።ሰው ይሆን ዘንድ የተላከውና ታዞ የመጣው ልጅነት ግብሩ ስለሆነ ነው መታዘዙ ልጅነቱን  ያንፀባርቃል።አብ ልጁን ወደ አለም የላከው የአባትነት ግብሩ ስለሆነ ነው።ተልእኮ መስጠቱ አባትነቱን ያንፀባርቃል።ወልድ ሰው ከሆነ በኋላ አይደለም ታዞ ነው ሰው ወደ መሆን የመጣው።ሰው የሚሆነው አምላክ ነው ።አምላክ ነው የታዘዘው ሰው የሆነው አምላክ ነው የታዘዘው! ከዚህ በቀር ወልድ  ከሌላ ማንነት ወደ ወልድነት (ልጅነት) አልመጣም።ሰው ሳይሆን በፊት የእግዚአብሄር ልጅ የእግዚአብሔር ልጅ ነበር ።ሰው መሆን (በታሪክ ውስጥ)ለእግዚአብሔር አዲስ ነገር ነው።ልጅነት እና አባትነት ግን አለም ሳይፈጠር የነበረ ነው።"       አሁንም ፀሃፊው ጳውሎስ ፍቃዱ ሰለ ልጁ ዘላለማዊ  ማንነት  ቀጠል አድርጎ እንዲህ ያብራራል!!           "የእግዚአብሔር ቃል የሆነው  ኢየሱስ አለምን ስለ መፍጠሩ  ሐዋሪያው ዮሃንስ ሲናገር ሙሉ በሙሉ አዲስ ሃሳብ እያስተዋወቀን አይደለም።የእግዚአብሄር ቃል ያለውን የመፍጠር ሚና አይሁዳውያን በደንብ ያውቁ ነበርና ።ይህም በዘፍጥረት ምዕራፍ አንድ ከተፀባረቀው በተጨማሪ በሌሎች ብሉይ ኪዳን ክፍሎች ተጠቅሷል። ለምሳሌ “በእግዚአብሔር ቃል ሰማዮች ጸኑ፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በአፉ እስትንፋስ”   መዝሙር 33፥6 “እርሱ ተናግሮአልና፥ ሆኑም፤ እርሱ አዘዘ፥ ጸኑም።”   መዝሙር 33፥9 “እርሱ ብሎአልና፥ ሆኑም፤ እርሱም አዝዞአልና፥ ተፈጠሩም፤ የእግዚአብሔርን ስም ያመስግኑት።”   መዝሙር 148፥5 (ተጨማሪ መዝ 147:15-18) በአይሁድ ዘንድ የሚታወቀው የቃል ፈጣሪነት በአዲስ ኪዳንም ተንፀባርቋል።  የዕብራውያን ፀሃፊ “ዓለሞች በእግዚአብሔር ቃል እንደ ተዘጋጁ፥ ስለዚህም የሚታየው ነገር ከሚታዩት እንዳልሆነ በእምነት እናስተውላለን።”   — ዕብራውያን 11፥3          እግዚአብሔር አለማትን በልጁ መፍጠሩ በመልክቱ ጅማሬ ላይም ጠቅሷል ዕብራውያን 1 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹⁰ ደግሞ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤ ¹¹ እነርሱም ይጠፋሉ አንተ ግን ጸንተህ ትኖራለህ፤ ሁሉም እንደ ልብስ ያረጃሉ፥ ¹² እንደ መጎናጸፊያም ትጠቀልላቸዋለህ ይለወጡማል፤ አንተ ግን አንተ ነህ፥ ዓመቶችህም ከቶ አያልቁም ይላል።           በማለት የልጁን ፈጣሪነት አስረድቷል።.......ዮሃንስም የእግዚአብሔር ቃል ሲል የተነገረ ቃል ማለቱ አይደለም  የተፈጠረ ቃልም አይደለም ። "ቃልም እግዚአብሔር ነበር ብሏልና"            አብ አለማትን በልጁ የፈጠረው ሃይል አንሶት እንዳልሆነ ሁሉ........"እያለ ፀሃፊው  ስለ መንፈስ ቅዱስም ማብራራት  ይጀምራል። እውነት ነው ይህ ልጅ ከዘላለም ዘመናት የነበረ አልፋ ደግሞም የማይኖርበት ዘመን የሌለው ኦሜጋ ነው ። ፀጋ ይብዛላቹ በግሩሜ ድፈቅ አሜን🙏
Показати все...
የጠፋውን በግ ፈላጊ ገጣሚ : Betselot (Beki) User name : @Betsitaye ቀን : 29/02/2015 ዓ.ም መቶ በጎች ያለው፣ አንድ በግ ቢጠፋው፣ ዘጠና ዘጠኙን በግ ትቶ፣ አንዱን ሲፈልግ ሁሉን ትቶ፣ . . እስኪያገኘው ቢፈልገው ከመንገድ፣ በዱር በገደል ሲፈልግ ከጉርጓድ፣ ሳይሰለቸው እስኪገኝ በሁሉ ቢባዝን፣ መልካም እረኛ በጎቹን ስለሚያድን፣ ይፈልጋል በጉን እንዳይገኝ በጠላት፣ እንዳይበላ በራባቸው በክፉ አውሬያት፣ . . እረኛው ሳይታክት ፈልጎ ሲያገኘው፣ በጉን ተሸክሞ አድርጎ በጫንቃው፣ ወደ ቤቱ ይሄዳል ሲገባ ከቤትም፣ ወዳጅ ጎረቤቱን ጠርቶ ሲያበቃም፣ ይነግራችዋል ስለበጉ አበርትቶ፣ እረኛው በደስታ በሀሴት ፊቱ አብርቶ፣ . . የጠፋውን በጌን አግንቼዋለሁ እያለ፣ ከእኔ ጋራ ደግሞ ደስ ይበላችሁ አለ፣ የጠፋውን በግ ፈላጊ ሁሉን ትቶ፣ አንዱን በግ ፍለጋ ወጥቶ፣ ዘጠና ዘጠኙን በጎች ጥሎ፣ ፍቅሩ ያስገርማል በልብ ተንጣሎ፣ . . ከዘጠና ዘጠኙ ፃድቃን አንዱን ቢፈልግ፣ እረኛው ፍቅሩ ልዩ ነው ለጠፋው በግ፣ ከፃድቃኖቹ ይልቅ ለአንዱ ሀጢያተኛ፣ ንስሃ ቢገባ በሰማይ ታላቅ ደስታ ሁነኛ፣ አዎ ይገኛል እና ከአርያም ደስታ፣ መዳን ለአንዲት ነፍስ ከሆነ አሌንታ፣ . . ምንኛ መታደል ነው እረኛውን መከተል፣ ከጥፋት ከአለም በጌታ ሸሽቶ መከለል፣ መልካሙን እረኛ ማድረግ ሊቀ ካህኑ፣ ይሻላል አዎ ከዘላለም ሞት መዳኑ፣ በእረኛው መጠበቅ ከአዳኝ ማምለጥ፣ ደቀመዝሙር መሆን በጌታ መለወጥ፣ መኖር እንደ ቃሉ መስቀል ተሸክሞ፣ ሁሉን ትቶ መከተል ትዛዙን ፍፅሞ።
Показати все...
መበርቻዬ ገጣሚ : Betselot (Beki) User name : @Betsitaye ቀን : 26/02/2015 ዓ.ም ዞር ብዬ ስቃኝ የኋላዬን፣ ስመለከት ያን ያለፈ ዘመኔን፣ ሳስተውለው ይህ ያሁን ህይወቴን፣ ስሰማው ደግሞ አጥብቄ ነፍሴን፣ ከረመጥ ከድጡ መውጣቴን ስመለከት፣ ያኔ ነፍሴ ሲመስላት ተስፋ የሌላት፣ . . . ባቅም ማጣት ውሃ ሲሆን ሰውነቴ፣ የሀዘኔ ጥላ በልጦም ነበር ከህይወቴ፣ እንደ ደረቅ አበባ አቅም እንዳነሳት፣ ሲጠወልግ ነፍሴን ልምላሜ ሲያሳጣት፣ ሀሉ ሲጨልም ማይነጋ ሲመስል፣ የመኖር ትርገሙ ጠፍቶኝ ስታገል፣ . . . ጌታ ለደረቀች ነፍሴ ተስፋ ሰጣት፣ እንደ ደረቀ አበባ አቅም እንዳያንሳት፣ አጠጣኝ ከምንጩ ህይወት ከሚሰጠው፣ እሱ የደረቀውን ደርሶ የሚያለልመው፣ ስሬ አቋጥቁጦ ውበት እንዲሞላኝ፣ በዙሪያዬ ቋሞ ሁሌ እየጠበቀኝ፣ . . . አጠጣኝ ከምንጩ ከዘላለም ህይወት፣ የፈጠራት ነፍሴ ድርቀት እንዳያያት፣ ያጠጣት እርሱ ነው ለተጠማች ነፍሴ፣ ደግሞ በከበረው ፍቅሩ እኔ መዳሰሴ፣ . . . የህይወቴ ቤዛ ሆኖኝ መበርቻዬ፣ እንዳልወድቅ ደግፎ ሆኖ ከለላዬ፣ በህይወቴ ላይ አዲስ ቀን ጨምሮ፣ አዎ አድኖኛል ጌታ ታሪኬን ቀይሮ።
Показати все...
ግን ነብሱን ቢያጎድል ምን ይጠቅመዋል ገጣሚ : Betselot (Beki) User name : @Betsitaye ቀን : 16/02/2015 ዓ.ም በአምላክ ከፍጥረት የተመረጠ ህዝብ፣ በሀጥያት መንገድ ተሳፍሮ በመርከብ፣ ሲዋዥቅ ለነበረው ደርሶ የዋሁ በግ፣ ከማዕበል ሳይጠልቅ ሳይሰርግ፣ የበጎቹ እረኛ ለሰዎች ሀጢያት፣ ከፈለ የበጉ ደም ሆኖ መስዕዋት፣ ወጣን በኢየሱስ ከሀጢአት ቀንበር፣ አሁን ምን ይሰራል የአለም ፍቅር፣ ማጌጥ መዋብ በአለም ኩል፣ እኩላለሁ ብላ አይን እምጠነቁል፣ በሀጥያት ቅርሻት ስትጥል ጉድጓድ፣ ቅሌት መዝናኛዋ ሳቋ የሌለው እግድ፣ ውድቀት ክብሯ ሙት ነው አላማዋ፣ የመከራዋ ሙጫ መርዝ መስጠትዋ፣ አለም ይህች ናት ከራቀች ከጌታ፣ በድምቀት ስሌት በሰይጣን ስትረታ፣ መአዛዋ ግማት የጌጧ ኮተትዋ፣ ገዳይ ነው ጢሷ ሞት ገንዳዋ፣ ይሄ እንዴት ይስባል ምን ያጓጓል፣ ነፍስን ሰጥቶ ለመሸጥ ለሲኦል፣ ምን ይረባል ጌታ በሌለበት ክብር፣ የአለም ክብር ዝና ጊዜያዊ ፍቅር፣ አሮጌ ኮተት ይዞ ማንዣበብ፣ በአዲስ ካባ እንደ ማበብ፣ ሽርጉድ ለአለም በጥቂት ጭላንጭል፣ በዚህ ሁሉ ግን ነፍሱን ቢያጎድል ፣ ምን ይጠቅመዋል አለምን ማንገስ፣ ስሟ እንዳይጠፈ ስሟን ማደስስ፣ እያለ የማይታይ አምላክ ምሳሌ የሆነን፣ ወደ ፍቅሩ ልጅ መንግስት ያፈለሰን፣ እሱ የፍጥረት ሁሉ በኩር ነው፣ ሁሉ በእርሱ ለእርሱ ፈጣሪ የሆነው፣ ከጨለማ ስልጣን ሁሉን ያዳነ፣ ቤዛነቱን ለሰው ልጅ ያገነነ፣ የሞትን ቀንበር የሰበረ ጌታ፣ ከሀጢአት አረንቋ ቋጠሮን የፈታ፣ ከሁሉ አብልጦ ሰውን የወደደ፣ ጌታ እኮ ነው ፍቅሩን ያላገደ፣ ታዲያ በበጎ ስራ ፍሬ እያፈሩ፣ በመፅናት በትግስት ለክብሩ፣ ላዳነን ለአብ ምስጋና እየሰጡ፣ በነገር ሁሉ ለአለም ሳይሮጡ፣ እሱን እየመሰከሩ ወንጌል እያወጁ፣ ሳይርቁ ከጌታ በአለም ሳይጃጁ፣ መመለስ በቤቱ በጌታ መሆን፣ ልብን ለእርሱ መስጠት ሁሉን።
Показати все...
ስለ ኢየሱስ ማወቅ ለምን አስፈለገ? ክፍል አንድ መግቢያ "እውነተኛ አምላክ የሆንኸውን አንተንና የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች #የዘላለም_ሕይወት ናት።” — ዮሐንስ 17፥3 (አዲሱ መ.ት) ይህ ክፍል ብንመለከተው የሚነግረን መሰረታዊ እውነታ አለ ። እርሱም እውነተኛ የሆነው አምላክ አብን ማወቅ እና አብ የላከውን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ የዘላለም ሕይወት ጉዳይ እንደሆነ ነው ። አንዳንዶች እውነተኛ አምላክ የተባለው አብ ነው እንጂ የተላከው ኢየሱስ አይደለም ይላሉ ።በእርግጥ ይህ ምን ያህል እውነት ነው ብለን ብንጠይቅ ምንም ያህል እውነት አለመሆኑን እንረዳለን።ምክንያቱም አብ ተብሎ የፃፈውን ማወቅ ብቻ ሳይሆን አብ የላከውን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅም የዘላለም ሕይወትን ይወሰናል እና ነው። የዘላለም ሕይወት ጉዳይ ሁለቱን በማወቅ ላይ የተመሰረ ተደርጎ ከቀረበ የሁለቱን አካላት አቻነት (እኩል መሆን) ከግንዛቤ ልናስገባ እንችላለን ። በሌላ ስፍራ የእዚሁ መፅሃፍ ፀሃፊ ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር ቅዱስ ዮሃንስ በመልዕክቱ እንዲህ ብሎናል። “የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ #እውነተኛ_አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።” 1ኛ ዮሐንስ 5፥20 ስለዚህ ስለ ኢየሱስ ማወቅ እጅግ መሰረታዊ ነገር ነው ማለት ነው። በክርስትና ስለ ክርስቶስ ለማወቅ ስንሞክር የክርስትና መሰረታዊ አስተምህሮ ላይ እንደርሳለን ።ሁሉ ትምርቶች ክርስቶስን ማዕከል አድርገው የሚሽከረከሩ ናቸው ። ለእዚህ ነው ኢየሱስ በመዋለ ስጋዌው (በስጋ በምድር በተመላለሰበት ጊዜ) መፅሐፍት ሁሉ ስለ እርሱ እንደሚናገሩ የገለፀው። “እናንተ በመጻሕፍት የዘላለም ሕይወት እንዳላችሁ ይመስላችኋልና እነርሱን ትመረምራላችሁ፤ እነርሱም ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው፤” — ዮሐንስ 5፥39 ከእለታት አንድ ቀን ኢየሱስ ለፈሪሳውያን እንዲህ አላቸው ። “እንግዲህ፦ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ አልኋችሁ፤ እኔ እንደሆንሁ ባታምኑ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁና አላቸው።” — ዮሐንስ 8፥24 እውነት ይህ የማለት ስልጣን ፍጡር ሊኖረው ይችላልን? እኔ እንደሆን ባታምኑ በኃጢአታችሁ ትሞታላችሁ። እሱን ማመን እና አለማመን ከሞት ወይም ከሕይወት ጋር ተጋምዷል (ተያይዟል) ታዲያ ይህ አካል ማን ነው? ኢየሱስ ላይ ያለን መረዳት የዘላለም ሕይወት ጉዳያችንን ሊወስን ያስቻለው ኢየሱስ ማን ቢሆን ነው? ይህ ጥያቄ ዛሬ የጀመረ አይደለም ። ኢየሱስ እና ጥያቄ ያልተቆራኙበት ጊዜ የለም ።ሲፀነስ ለዮሴፍ ጥያቄ ነው። ሲወለድ ለንጉሱ ሄሮድስ ጥያቄ ነው ። በሕይወቱ ለደቀመዛሙርቱ ለቤተሰቦቹ ጥያቄ ነው ።ሲሰቀል ለነገስታቱ አብረው ለተሰቀሉትም ጥያቄ ነው ።ሲነሳም ለሐዋርያቱ ጥያቄ ነው ።ሊያርግ ሲልም መንግትህን መቼ ትመሰርታለህ በሚል ጥያቄ ነበር ያቀረቡት! ለጠየቁ ሁሉ መልስ ሆኗቸው እስከሞት ታምነው አለገልግለውታል ! ከእለታት በአንዱ ቀን ወደ ፊሊጶስ ቂሳርያ ወደ እስራኤል ሰሜናዊ ጫፍ ፀጥተኛ እና ቀዝቃዛ ወደ ሆነችው አከባቢ ወስዷቸው የተጠየቃቸው ይህንኑ ነው። “ኢየሱስም ወደ ፊልጶስ ቂሣርያ አገር በደረሰ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱን፦ ሰዎች የሰውን ልጅ ማን እንደ ሆነ ይሉታል? ብሎ ጠየቀ።” ማቴዎስ 16፥13 የእዚህ ጥያቄ መልስ እጅግ ወሳኝና የሕይወትና የሞት መለያ ስለሆነ በጥንቃቄ መመለስ ነበረበት ።ግን ብዙዎች በቅጡ ሊመልሱት አልቻሉም። ኢየሱስ ወደ ደቀመዛሙርቱ በድጋሚ ጥያቄውን ሰነዘረ ። “እርሱም፦ እናንተስ እኔን ማን እንደ ሆንሁ ትላላችሁ? አላቸው።” — ማቴዎስ 16፥15 ይህ ጥያቄ መገለጥን ይፈልጋል ። ለእነዚህ ነው መልሱን ለመለሰው ለጴጥሮስ እንዲህ የተባለው ። “ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለው፦ የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና ብፁዕ ነህ።” — ማቴዎስ 16፥17 አብ እርሱ የገለጠው ኢየሱስ ይህ ነው። “ስምዖን ጴጥሮስም መልሶ፦ አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ አለ።” — ማቴዎስ 16፥16 ስለዚህ ይህ የተገለጠውን የእግዚአብሔር ልጄ የሆነውን ኢየሱስ ማወቅ አማራጭ የሌለው ምርጫ ነው ።ከግዴታዎች ሁሉ ግዴታ ነው ። ግን ለምን ኢየሱስን ማወቅ አስፈለገ ? በዝርዝር ወደ ማየት እንለፍ!! ይቀጥላል ... ፀጋና ሰላም ይብዛላችሁ ። ✍️✍️✍️✍️✍️✍️ Girum Difek Girum difek page የክርስትና እውነቶች - Christian Truths @Goldenmission
Показати все...