cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ዜና ቲቪ 2

የዜና ቻናል ነው

Більше
Рекламні дописи
758
Підписники
-124 години
-57 днів
-2330 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
ድርጅት መፍጠርና መልሶ መሸጥ የተካነችውን ትውልደ ኢትዮጵያዊት እንተዋወቃት፤ ኬነሳ ሙሉነህ ትባላለች። ትውልዷ ድሬዳዋ ሲሆን፣ ገና በሶስት ዓመቷ ነው ከወላጆቿ ጋር ወደ ኔዘርላንድስ ያመራችው። ከወላጆቿ ጋር መሄዷ አማርኛ ቋንቋን ጨምሮ የኢትዮጵያ ወግና ባሕልን እንድትማር አስችሏታል። ያደገችበት የኔዘርላንድስ ባህልም ሌላ ማንነትን አላብሷታል። በሁለት ባህሎች ውስጥ ማደጓም ለስራዋ እንደጠቀማት ኬነሳ ትናገራለች። ወላጆቿ ልጃቸው የህክምና ዶክተር እንድትሆን ይፈልጉ ስለነበር እነሱን ለማስደሰት ህክምናን አጥንታለች። ነገር ግን በሕክምና ሙያው ከምርቃት በኋላ አንድም ቀን ሐኪም ሆና አልሰራችበትም። ‘የወላጆቼን ፍላጎት አሟልቻለሁ፤ አሁን ደግሞ የአኔን ፍላጎት ላሟላ ብዬ የራሴን ሥራ ጀመርኩ’ በማለት ሙሉ በሙሉ ከሕክምና ሥራ የተለየ ሥራ መጀመሯን ኬነሳ ትናገራለች። በተመረቀችበት የሕክምና ሙያ ባትሠራበትም ሕክምና መሟሯ ግን ቀጣይ ሕይወቷን የሚቀይር አጋጣሚ ፈጥሮላታል። በህክምና ትምህርቷ ወቅት ባዘጋጀችው የምርምር ጽሑፍ ላይ በመመስረት ምርምሩን ወደ ተግባር ቀይራ የራሷን የመጀመሪያ ድርጅት መመስረት ችላለች። ድርጅቱን አንድ አመት ከሰራችበት በኋላ ለአንድ የኢንሹራንስ ኩባንያ በመሸጥ በሚሊዮን ዶላር የሚቆጠር ገንዘብ ወደ ካዝናዋ አስገብታለች። የድርጅቱ መመሥረትና መሸጥ ለኬነሳ ችግርን በማጥናት መፍትሔ ማፈላለግና ሃብት ማፍራት እንደሚቻል አሳይቷታል። ሌላ ድርጅት ለመፍጠር ያነሳሳት ደግሞ የምትወደው ስፖርት ነው። አይኗ ያረፈውም በኔዘርላንድስ ሴቶች ዘንድ ያልተለመደውን የሴቶች የአሜሪካ ፉትቦል ማስተዋወቅ ላይ ነበር። በመሆኑም በተለያዩ ከተሞች ቡድን መሥርታ ሴቶች መደበኛ ጨዋታ እያካሄዱ በማድረግ የሴቶች የአሜሪካ ፉትቦል አንድ የመዝናኛ ስፖርት እንዲሆን አስቻለች። ጨዋታው ታዋቂነቱ አደገ፣ በሊግ ደረጃም ተመሰረተ፤ ባለቤትነቱንም መስራቿ ከኔሳ ጠቀለለች። እንደመጀመሪያው ድርጅቷ ሁሉ ይህንንም ሸጠችው። የህይወቷን አጋጣሚዎች ለስራ መፍጠሪያነት የምትጠቀመው ባለትዳርና የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ኬነሳ በተለይም ሁለተኛ ልጇን ስትወልድ ክብደቷ በመጨመሩ የምትፈልገውን አይነት ልብስ በቀላሉ ገበያ ውስጥ ማግኘት ባለመቻሏ ‘ሙሉ’ የፋሽን ብራንድን እንድትመሰርት መነሻ ሆናትና ሶስተኛ ድርጅቷን አቋቋመች። ለፋሽን ሥራዎቿ የሚሆን ልብስ የምታመርትበት የራሷን ፋብሪካ ፓኪስታን ውስጥ ገንብታለች። ፋብሪካው ከሙሉ ብራንድ በተጨማሪ ለሌሎች የልብስ ፋሽን ኩባንያች ጭምር ልብስ ያመርታል። ኑሮዋን ዱባይ አድርጋ የፋሽን መለያ ልብሶቿን በእስያ፣ አፍሪካና አውሮፓ ገበያዎች እየሸጠች ነው። በአፍሪካ ጋና እና ናይጄሪያ በብዛት የፋሽን ልብሶቿን የምትሸጥባቸው ሀገራት ሲሆኑ፣ በኢትዮጵያም በቅርቡ መጀመሯን ተናግራለች። በቀጣይም ወደ ሕንድና ፓኪስታን የማስፋት እቅድ አላት። አውሮፓና አሜሪካ ከመጀመሪያው ጀምሮ የገበያ አማራጮቿ ናቸው። ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ ሀገራት ተቀጥረው የሚሠሩ ከ50 በላይ ሠራተኞች አሏት። የማኅበራዊ ሚዲያ ንቁ ተሳታፊና ‘ተጠቃሚ’ ናት። ለስኬቴ ማህበራዊ ሚዲያ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል የምትለው ኬነሳ፣ አብዛዎቹን ስራዎቿንም የምትሰራው በማህበራዊ ሚዲያዎች አማካኝነት ነው። ከንግድ ሥራዋ በተጨማሪ አስተማሪ ነኝ የምትለው ኬነሳ የምታስተምረው ዩኒቨርሲቲ ወይም ኮሌጅ ውስጥ ተቀጥራ ሳይሆን በኦንላየን ነው። በኦንላየን ተማሪዎችን መዝግባ የሕይወት ጉዞዋንና የቢዝነስ ፈጠራን በተመለከተ ትምህርት ትሰጣለች። ብዙ ተማሪዎቿም አዳዲስ ቢዝነስ ጀምረው ለውጥ እያመጡ መሆኑን ትናገራለች። ኬነሳ ከሥራ ፈጠራ ክኅሎቷና የአስተማሪነት ሥራዋ በተጨማሪም የኦንላየን ይዘት ፈጠራ ላይ ትሠራለች። በቅርቡ ‘አድዋ’ የተሰኘ የኢንተርኔት ጨዋታ [ጌም] ይፋ አድርጋለች። ጨዋታው ታሪካዊውን የኢትዮጵያ የአድዋ ድል የሚዘክር ነው። በጨዋታው የወከለቻቸው ገጸ ባህሪያትና አጠቃላይ የጨዋታው ሂደትም በጦርነቱ ኢትዮጵያውያን የነበራቸውን ሚና የሚያስታውስ፣ አልበገር ባይነታቸውንና ጀብደኝነታቸውን የሚዘክር ነው። ስራ ፈጣሪዋ ኬነሳ ድርጅት ፈጥሮ መሸጥ ዋነኛ መገለጫዋ ነው። ከዚህ በኋላም ክፍተቶችን የሚሞላ ግኝት በማምጣት ሥራዎቿን እንደምትቀጥል መግለጿን ጠቅሶ ታሪኳን ያቀረበው ቢቢሲ አማርኛ ነው።
Показати все...
👍 1
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የእስር ማዘዣ ወጣባቸው፡፡ ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት በዚህ የንጹሃን ዜጎች ግድያ ተጠያቂ ናቸው ባላቸው መሪዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ አስተላልፏል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡ እንደዘገባው ከሆነ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና ዮዓቭ ጋላንት ከእስራኤል በኩል ከሐማስ በኩል ደግሞ ሶስት አመራሮች የእስር ማዘዣው የወጣባቸው አመራሪች ናቸው፡፡በሐማስ በኩል ደግሞ የሐማስ ሀላፊ ያህያ ሲነዋር፣ የሐማስ ጦር አዛዥ መሀመድ አል ማስሪ እንዲሁም የሐማስ ታጣቂዎች ኮማንደር እስማኤል ሀኒያህ የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸዋል፡፡ ደቡብ አፍሪካ፣ ቱርክ እና ሌሎችም ሀገራት እስራኤል ንጹሀንን በመግደል እና ሌሎች የከፋ ጥቃት አድርሳለች በሚል በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት እንድትጠየቅ ግፊቶች ሲያደርጉ የነበሩ ሀገራት ናቸው፡፡እስራኤልም ሆነች ሐማስ የጦር ወንጀሎችን እንዳልፈጸሙ ተናግረው በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት ያወጣውን የእስር ማዘዣ ውድቅ አድርገዋል፡፡ @Addis_News
Показати все...
#እነዚህን_5_ምልክቶች_ካሳዩህ_ግንኙነትህን_አቁም! #አንደኛ_ገንዘብ_የማያወጡ_ሰዎችን_ራቅ ሁሌም ካንተ የሚጠብቁ ምንም ያህል ይሉኝታ የሌላቸውን ሰዎች መራቅ ይኖርብሃል። በርግጥ ሰዎች በአጋጣሚ ገንዘብ ላይኖራቸው ስራም ላይሰሩ ይችላሉ። ነገር ግን እንዳንተው ሰርተው እየገቡ ብዙ ችግርተኛነትን በማውራት ወጪህ የሚሆኑ ሰዎች አደጋህ እንደሆኑ ከወዲሁ እወቅ። #ሁለተኛ_ብዙ_ጊዜ_የሚጨቃጨቁ_ሰዎች ሁሌም ጠብ የማያቋርጡ ሰዎች ለህይወት ሰላም አስቸጋሪ ናቸው። ወይ በየምክንያቱ ነገር ይፈልጉሃል፤ አሊያም ስህተትህን በፍጹም ማለፍ እና ይቅር ማለት አይፈልጉም። ይህ አይነቱ ፀባይ ያላቸው ሰዎች ህይወት አጭር መሆኗን የማይረዱና ዘላለም ይኖሩ ይመስል ሁሉን ነገር በጭቅጭቅና በጸብ መፍታት የሚመርጡ ናቸው። #ሶስተኛ_ሁሌም_ከሚያማርሩ በህይወት ሰው ተስፋ ሊቆርጥ ሲወድቅ ሊያማርር ሲነሳ ሊያመሰግን ተፈጥሮ አለበት ነገር ግን። ሁሌም በማግኘት ውስጥ አልጠግብ ባይና አማራሪ ከሆነ ሰው በዘዴ ሽሽ። ሲያገኝም ሲያጣም ያው ከሆነ ሰው ወዳጅ አትሁን። #አራተኛ_መዝናናት_ከሚያበዙ_ሰዎች እውነት ነው ሁሌም ሰው በስራ መጠመድ የለበትም። ሁሌም ግን እንዝናና፤ እንጠጣ ከሚሉና ነገ ከዛሬ ጋር ከማይታያቸው ሰዎች አብረሀቸው ከመውደቅህ በፊት ራቅ። ብዙ ሰርቶ በጥቂቱ መዝናናት እንጂ፣ ጥቂትም ሳይሰሩ ብዙ መዝናናት በዚህች የውድድር ዘመን ውጤታማ አያደርግም። #አምስተኛ_ሁሌም_ከሚወቅሱህ_ሰዎች_ራቅ። ሁሉንም ጥፋት ባንተ ላይ ከሚደመድሙ ሰዎች ገለል በል። ላንተ ቦታ ያለው ሰው ራስህን በጸጸት እና በአይረቤነት እንድታገኘው አይሻም። ነገር ግን እነሱም ሲያጠፉ አንተም ስታጠፋ ጣታቸውን ወደ አንተ የሚጠቁሙ ሰዎች ለህይወትህ አደጋ ናቸው። ☑️ ሰውን ትለምደዋለህ፣ ታውቀዋለህ ምንም ያህል ሀብትና ዝና ይኑረው ካንተ ጋር የማይጣጣም ከሆነ ልትርቀው አትቸገር። የሮበርት ኪዮሳኪ ምርጥ መጽሐፍት በገበያ ላይ:- #የባለጸጋነት_መንገድ 2ኛ ዕትም #ሐብት_የመገንባት_ጥበብ #Cashflow_Quadrant በእንግሊዘኛ #ሐብታም_የመሆን_ጥበብ 8ኛ ዕትም ከተክሉ ጥላሁን የቴሌግራም ገፅ የተወሰደ
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
😎😎😎 ልጅ ያሬድ ከ8 ወር እስር በኃላ ከእስር ተፈቷል::
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
“ በየጊዜው ወጣቶች የምገብርበት የጦርነት ምዕራፍ መዘጋት አለበት “ - አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በኩል መልዕክት አሰራጭተው ነበር። በዚህም ፤ “ የህዝባችን ሁለንተናዊ መብትና ጥቅም ከማረጋገጥና አስተማማኝ ከማድረግ የሚቀድም ሌላ አጀንዳ የለንም “ ብለዋል። “ የህዝባችን ጥቅምና መብት የሚያረጋግጥ መንገድ ሁሉ እንጓዘዋለን “ ያሉት አቶ ጌታቸው “ ጉዞው እንዲሳካ የህዝቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው “ ሲሉ አክለዋል። ፕሬዜዳንቱ ፤ “ ከሚገባው በላይ ያበረከተ ህዝብ በቅንነትና ታማኝነት ማገለገል ይገባል “ ሲሉም ገልጸዋል። “ ህዝቡ ከጦርነትና ጦርነት ወለድ ችግሮች በማላቀቅ ወደ አስተማማኝ ሰላም እንዲሸጋገር መስራት ይገባል “ ሲሉም አስገንዝበዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ “ በየጊዜው ትኩስ ሃይል የሆኑትን ወጣቶች የምንገብርበት የጦርነት ምዕራፍ ተዘግቶ ፤ የልማትና የእድገት ፍላጎታችን እንዲሳካ መስራት አለብን “ ብለዋል።
Показати все...
የሙታን በአጸደ ሥጋ መነሳት ናቸው (ማቴ.27፤45-46)፡፡ እነዚህ ተአምራት በመስቀል ላይ የተሰቀለው ወልደ እግዚአብሔር መሆኑን ለሰው ልጆች ያረጋገጡ ምልክቶች ነበሩ፡፡ እነዚህን ተዓምራት አይተው በጌታችን ያመኑ ነበሩ፡፡ ከሰቃዮቹ ወገን የሆኑት እንኳ በትህትናው፣ በተዓምራቱ ተማርከው አምነው ምስክሮቹ (ሰማዕታት) ሆነዋል፡፡ ዕርቀ ሰላም፡ ሰባቱ መስተፃርራን (ጠበኞች) የታረቁበት ዕለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት ሰባት መስተፃርራን (ጠበኞች) ታረቁ፤ ተስማሙ፡፡ እነዚህም፡- ሰውና እግዚአብሔር፣ ሰውና መላእክት፣ ሕዝብና አሕዛብ፣ ነፍስና ሥጋ ናቸው (ኤፌ. 2፥10 ቈላ. 1፥20)፡፡ የስቅለት ቀን የገነት በር የተከፈተበት በአንጻሩ ደግሞ ሲኦል የተበረበረበችበት ነው፡፡ በአዳም በደል ምክንያት አምስት ሺህ አምስት መቶ ዘመን ተዘግታ የነበረችው ገነት የተከፈተችበት፣ በአንጻሩ ደግሞ ሰልጥና የነበረችው ሲኦል የተበረበረችበት፣ ነፍሳት ከሲኦል ወጥተው ወደ ገነት የገቡበት ነው፡፡ የስቅለት ዕለት የገነት መዘጋት ያበቃበት፣ የሲኦልም መሰልጠን ያከተመበት ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ «ጥልን በመስቀሉ ገደለ» ሲል የገለጸው (ኤፌ. 2፥16) በእነዚህ መካከል የነበረው ጥል ማብቃቱንና ፍጹም ሰላም መስፈኑን ያሳያል፡፡ የሰው ልጅ ድኅነት፡ የሰው ልጅ ከዲያብሎስ እሥራት የተፈታበት ዕለት ነው፡፡ የስቅለት ዓርብ የሰው ልጆች በዘር ኃጢአት /ቁራኝነት/ ይኖሩበት የነበረው የጨለማ ሕይወት ያከተመበት ፍጹም ድኅነት ያገኙባት ታላቅ ዕለት ናት፡፡ የስቅለት ዓርብ የሲኦል አበጋዝ ዲያብሎስ በንፋስ አውታር የታሠረበትና ስልጣኑ የተሻረበት፣ በአንጻሩ ደግሞ ታስሮ የነበረው አዳም የተፈታበትና ወደ ገነት የተመለሰበት ናት፡፡ በመጀመሪያ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲፈረድበት ወንጀለኛ የነበረው በርባን ተፈታ፡፡ ጌታችን በሥጋው ሲሞት ደግሞ አዳምና ልጆቹ በሙሉ ተፈቱ፡፡ ቅዱስ አትናቴዎስ “በምድር ላይ ኃጢአትን አሳፈረ፤ መርገምን በመስቀል ላይ ሻረ፤ ሞተ ነፍስን በሲዖል አጠፋ፤ ፈርሶ በስብሶ መቅረትን በመቃብር አፈራረሰ” እንዳለ፡፡ እንዲሁም ቅዱስ ጴጥሮስ “ሞተ በሥጋ ወሐይወ በመንፈስ ወወረደ ኀበ እለ ሙቅሕታ ትነብር ነፍሶሙ ወሰበከ ሎሙ ግዕዛነ” በሥጋ ሞተ በመንፈስ /በመለኮት/ ግን ሕያው ነው እርሱም ደግሞ ሄደ በወህኒ /በሲዖል/ ለነበሩ ነፍሳት ነጻነትን ሰበከላቸው” (1ጴጥ.3፡18) እንዳለው ጌታችን በሲኦል እስራት የነበሩትን ነፍሳት ነፃ አወጣቸው፡፡ የመስቀል ስጦታዎች፡ የምንጠመቅበት ማየ ገቦ፣ የምንድንበት ሥጋውና ደሙን እንዲሁም የምታማልድ እናት የተሰጠንበት ነው፡፡ በዘጠኝ ሰዓት ጌታችን በውኃው ተጠምቀን፣ ደሙን ተቀብለን የእግዚአብሔር ልጆች እንኾን ዘንድ ከቀኝ ጎድኑ ጥሩ ውኃ፣ ትኩስ ደም አፈሰሰልን (ዮሐ. 19፥34)፡፡ ዕለተ ዓርብ ተጠምቀን ድኅነት የምናገኝበት ውኃ ከጎኑ የፈሰሰበት፣ የዘላለም ሕይወት የምናገኝበት ቅዱስ ሥጋውና ክቡር ደሙን ያገኘንበት ዕለት ነው፡፡ ‹‹ በነገው ዕለት ስለ ዓለም የሚቆረሰው ሥጋዬ የሚፈሰው ደሜ ይህ ነው›› እንዳለ (ማቴ 27፡27)፡፡ ቤተክርስቲያንም የተዋጀችው በዚሁ በዕለተ ዓርብ በፈሰሰው ደሙ ነው፡፡ በዚህ ዕለት አርማችን መስቀሉ፣ ማኅተማችን ደሙ፣ ሕይወታችን እርሱ ሆነዋል፡፡ ሥጋውንና ደሙን በመስቀሉ ላይ አግኝተናል፡፡ ከመስቀሉ ሥር ድንግል ማርያም በዮሐንስ አማካኝነት እናት እንድትሆነን፣ እኛም ልጅ እንድንሆን የተሰጠንበት ቀን ነው፡፡ እናቱ እናት እንድትሆነን በይፋ የተሰጠንበት ቀን ነው፡፡ ‹‹እነኋት እናትህ፤ እነሆ ልጅሽ›› (ዮሐ 19፡36) ብሎ ሰጠን፡፡ ርህርህት እናት ከመሰቀል ሥር በዕለተ ዓርብ አግኝተናል፡፡ በአጠቃላይ የስቅለት ዓርብ ጌታችን የቤዛነቱን ሥራ የፈጸመበት ነው፡፡ በቤተልሔም የተጀመረው የሰውን ልጅ የማዳኑ ሥራ የተጠናቀቀበት፣ ጌታም ስለ ሰው ልጆች ፍቅር ሲል በቀራኒዮ አደባባይ ራሱን አሳልፎ በመስጠት የቤዛነቱን ሥራ የሠራበት ዕለት ነው፡፡ ዕለተ ዓርብ “እግዚአብሔር አንድያ ልጁን አሳልፎ እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዷልና” የተባለው የተፈጸመበት ነው፡፡ ለዚህም ነው ጌታችን በመስቀል ላይ ‹‹ተፈጸመ›› ያለው (ዮሐ 19፡30)፡፡ እኛም በዚህ ታላቅ ዕለት ጌታችን ስለ እኛ የተቀበለውን መከራ እያሰብን፣ ስለ ኃጢአታችንም እያዘንንና እያለቀስን፣ ስለ ማዳኑም ሥራ ምስጋናን እያቀረብን ስንሰግድ እንውላለን፡፡ እንደ ፈያታዊ ዘየማን ‹‹አቤቱ በመንግስትህ በመጣህ ጊዜ አስበን›› እያልን እንማፀናለን፡፡ እርሱም ዳግመኛ በመጣ ጊዜ እንዲያስበን የጾማችንን ፍጻሜ በቅዱስ ሥጋው በክቡር ደሙ ማኅተምነት ማተም ይኖርብናል፡፡ ለዚህም የእርሱ ቸርነት የቅድስት ድንግል እመቤታችን አማላጅነት አይለየን፡፡ አሜን
Показати все...
ስቅለት፡ ሕይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ሰቀሉት! Posted by Astemhro Ze Tewahdo  ሰሙነ ሕማማት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  የሰውን ልጅ ከዲያብሎስ ባርነት ነፃ ለማውጣት በፈቃዱ የተቀበላቸው ጸዋትወ መከራዎች የሚታሰቡበት ሳምንት ነው፡፡ የሰሙነ ሕማማት ዕለታት የዓመተ ኩነኔ ወይም የዓመተ ፍዳ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ክርስቲያኖች ክርስቶስ የዋለልንን ውለታ እያሰብን እጅግ የምናዝንበት፣ የምናለቅስበት፣ የምንሰግድበት ከሌሎች ቀናትና ጊዜያት በተለየ መልኩ አምላካችንን የምንማጸንበት፤ ጧት ማታ ደጅ የምንጠናበት፤ የክርስቶስን ተስፋ ትንሣኤ ከመቼውም ጊዜ በላይ በእምነትና በተስፋ የምንጠብቅበት  በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚገኝ ልዩ ተምሣሌታዊ ምስጢራትና አዘክሮ የሚፈጸምበት ሳምንት ነው፡፡ በዚህ  ሳምንት ያሉ እያንዳንዳቸው ቀናት ስያሜና ከስያሜው ጋር የተያያዘ ምስጢር አላቸው፡፡ ይህም፡- ሰኞ: አንጽሆተ ቤተመቅደስ፣ መርገመ በለስ ማክሰኞ:  የጥያቄ ቀን፣ የትምህርት ቀን ረቡዕ:    የምክር ቀን፣መልካም መዓዛ ያለው ቀን፣ የእንባ ቀን ሐሙስ:   ጸሎተ ሐሙስ፣ ሕፅበተ ሐሙስ፣ የምስጢር_ቀን፣ የሐዲስ ኪዳን ሐሙስ፣ የነፃነት ሐሙስ ዓርብ:    የስቅለት ዓርብ፤ የድኅነት ቀን፣ መልካም ዓርብ ቅዳሜ:    ቅዳም ሥዑር፣ ለምለም ቅዳሜ፣ ቅዱስ ቅዳሜ ከእነዚህ ሁሉ ግን ዓርብ የስቅለት (crucifixion) ቀን እጅግ ልዩ ናት፡፡ የስቅለት ዕለት የዕዳ ደብዳቤያችን በጌታችን በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ለመጨረሻ ጊዜ የተደመሰሰበት፤ ከአጋንንት አገዛዝ ነጻ የወጣንበት ዕለት ስለኾነ “የድኅነት ቀን” ወይም ‹‹መልካም ዓርብ›› ይባላል፡፡ ጌታችን ከተያዘባት ሰዓት አንሥቶ አይሁድ ከቀያፋ ወደ ሐና፣ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት አደሩ፡፡ ሲነጋ ከቀያፋ ወደ ጲላጦስ አደባባይ አስረው ወሰዱት (ማቴ. 27፥1-57)፡፡ ይህን አጥፍቶአል የሚሉት ነገር ሳይኖራቸው ጌታችንን ለፍርድ ያቀረቡት አይሁድ ጲላጦስ እነርሱ ወደ ተሰባሰቡበት ቦታ ወጥቶ ‹‹ይህን ሰው ወደ እኔ ያመጣችሁበት በደል ምንድን ነው?›› ሲል በጠየቃቸው ጊዜ በቂ ምላሽ አላቀረቡም፡፡ በግብረ ሕማማት‹‹የማይሞት መለኮት ስለ እኛ የሞትን ጽዋ ተቀብሎ በሰውነቱ ሞተ! ወዮ ለዚህ አንክሮ ይገባል፡፡›› እንደተባለ ስለኛ በፈቃዱ ይሞት ዘንድ ፈቃዱ ነበርና በአይሁድ ጭካኔ ምክንያትነት ሞት ተፈረደበት፡፡ ይህ የስቅለት ዕለት ሙሉ ምስጢሩና ሥርዓቱ በግብረ ሕማማቱ በስፋትና በጥልቀት እንደሰፈረው ነው፡፡ በዚህች አጭር ጽሑፍ የተወሰኑ ነጥቦችን ለማንሳት ያህል ይህ የስቅለት ቀን የሚከተሉት የተከናወኑበት ነው፡፡ ፍኖተ መስቀል፡ ጌታችን 15ቱን ምዕራፎች መከራ እየተቀበለ የተጓዘበት ነው፡፡ ጌታ በጲላጦስ ፊት ከቆመበት ቦታ ጀምሮ እስከ መካነ ትንሣኤው ድረስ በዕለተ ዓርብ የሆነው ዐሥራ አምስት የመከራ መስቀል መንገድ ምዕራፎች (ፍኖተ መስቀል) አሉ፡፡ እነዚህም የጲላጦስ ዐደባባይ (ለፍርድ የቆመበት)፣ የተገረፈበት፣ በመጀመሪያ የወደቀበት ቦታ፣ እመቤታችን እያለቀሰች ልጇን ያገኘችበት ቦታ፣ ቀሬናዊ ስምዖን የጌታን መስቀል የተሸከመበት ቦታ፣  ቤሮና /ስራጵታ/ በመሐረብ የጌታን ፊት የጠረገችበት ቦታ፣ የጎልጎታ መቃረቢያ፣ የጌታችንን ሥቃይ ሴቶች አይተው ያለቀሱበት ቦታ፣ መስቀል ይዞ የወደቀበት፣ ልብሱን የገፈፉበት፣ጌታን የቸነከሩበት፣ የተሰቀለበት ቦታ፣ ቅዱስ ሥጋውን ያወረዱበት ቦታ፣ ቅዱስ ሥጋውን የገነዙበት ቦታ፣ ቅዱስ ሥጋው የተቀበረበት ቦታ ናቸው፡፡ እነዚህም ምዕራፎች የጌታችንን መከራና የማዳኑን ሥራ ሲያሳስቡን ይኖራሉ፡፡ ሕማማተ መስቀል፡ ጌታችን 13ቱን ሕማማተ መስቀል የተቀበለበት ዕለት ነው፡፡ ዕለተ ዓርብ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ መተላለፋችን የቆሰለበት፣ ስለ በደላችንም የደቀቀበት፣ ስለ ሁላችን ኃጢአት ራሱን መስዋዕት ያደረገበት፤ በእርሱም ቁስል እኛ የተፈወስንበት፤ በሞቱም የሞት ስልጣን የተሻረበት ዕለት ነው፡፡ የሕይወት ባለቤት፣ የሕያዋን ሁሉ አምላክ በፈቃዱ በሥጋ ሞቷልና የሞትን ስልጣን አጠፋልን፡፡ ይህ ዕለት አስራ ሦስቱን ሕማማተ መስቀል የተቀበለበት፣ እኛም እነዚህን እያሰብን የምንሰግድበት፣ በተደረገልን ቤዛነት እየተደነቅን ፍቅራችንን አምልኮታችንን የምንገልጥበት ዕለት ነው፡፡ የበረቱ ቅዱሳን ሙሉ ሕይወታቸውን፣ ትዳራቸውን ደስታቸውን ትተው ዕለት ዕለት የሚያስቡትን መከራ መስቀል፣ ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችንም በየዕለቱ የምታስበውን፣ የምታዘክረውን መከራ መስቀል እኛ ደካሞች ደግሞ ቢያንስ ለአንድ ሣምንት በልዩ ሁኔታ የምናስብበት ልዩ ወቅት ነው፡፡ በዚህ ልዩ ወቅት ስለበደላችን እያነባን መድኃኒት የሆነንን የክርስቶስን 13ቱን ሕማማተ መስቀል እናስባለን፡፡ እነዚህም 13ቱ ሕማማተ መስቀል የሚባሉት፡ አስሮተ ድኅሪት (ወደኋላ መታሰር)፣ ተስሕቦ በሐብል (በገመድ መሳብ)፣ ወዲቅ ውስተ ምድር (በምድር ላይ መውደቅ)፣ ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በእግረ አይሁድ መረገጥ)፣ ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሶሶ ጋር መላተም)፣ ተጽፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)፣ ተቀሰፎ ዘባን (ጀርባን በጅራፍ መገረፍ)፣ ተኰርዖተ ርእስ (ራስን በዱላ መመታት)፣ አክሊለ ሦክ (የሾህ አክሊል መድፋት)፣ ፀዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)፣ ተቀንዎ በቅንዎት (ሳዶር፣ አላዶር፣ ዳናት፣ ሮዳስና አዴራ በተባሉት ችንካሮች መቸንከር)፣ ተሰቅሎ በዕፅ (በመስቀል ላይ መሰቀል) እና ሰትየ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት) ናቸው፡፡ በስቅለት ዕለት ለእኛ ሲል እነዚህን ሕማማተ መስቀል መቀበሉን እያሰብን የአምልኮ ስግደት እንሰግድለታለን፡፡ አጽርሐ መስቀል፡ ጌታችን በመስቀል ላይ ሆኖ ሰባቱን አጽርሐ መስቀል የተናገረበት ነው፡፡ ይህ ዕለት ጌታችን በመስቀል ላይ ሆኖ ሰባቱን አጽርሐ መስቀል (የፍቅር ቃላት) የተናገረበት ዕለት ነው፡፡ እነዚህም ቃላት በየራሳቸው ጥልቅ ምስጢር ያላቸው ሲሆኑ የማዳኑ ሥራም አካል ናቸው፡፡ ሰባቱ ቃላትም:  ኤሎሄ ኤሎሄ ኤልማስላማ ሰበቅታኒ/አምላኬ አምላኬ ለምን ተውከኝ (ማቴ.27፤46)፣ አማን ዕብለከ እሙን ፈድፋደ ከመ ዮም ትሄሉ ምስሌየ ውስተ ገነት (እውነት እውነት እልሃለሁ ዛሬ በገነት ከእኔ ጋር ትኖራለህ)(ሉቃ.23፤43)፣ አባ አማሐፅን ነፍስየ ውስተ እዴከ (አባት ሆይ ነፍሴን በእጅህ አደራ እሰጣለሁ) (ሉቃ.23፤46)፣ አባ ሥረይ ሎሙ እስመ በዘኢየአምሩ ይገብሩ (አባት ሆይየሚያደርጉትን አየውቁምና ይቅር በላቸው) (ሉቃ.2334)፣ ነዋ ወልድኪ ወነያ እምከ (እናትህ እነኋት፤ እነሆ ልጅሽ) (ዮሐ.19፤26-27)፣ ጸማዕኩ (ተጠማሁ) (ዮሐ.19፤30) እና ተፈጸመ ኩሉ (ተፈጸመ) (ዮሐ.19፤30) የሚሉት ናቸው፡፡ እነዚህን ሰባቱን በመስቀል ላይ ሆኖ ተናግሮ እራሱን ወደቀኝ ዘንበል አድርጎ ነፍሱን ከሥጋው በገዛ ሥላጣኑ ለየ፡፡ በስቅለት ዕለት እነዚህ በንባብና በዜማ እያልን እንሰግድለታለን፡፡ የስቅለት ተአምራት፡ በሰማይና በምድር ሰባት ተአምራት የተከናወኑበት ነው፡፡ በዕለተ ዓርብ በሰማይ ሦስት ተአምራት ተከናውነዋል፡፡ እነዚህም የፀሐይ መጨለም፣ የጨረቃ ደም መልበስ፣ የክዋክብት መርገፍ ናቸው፡፡ ይህም የሆነው በመስቀል ላይ ያለውን የአምላካቸውን እርቃን ላለማሳየት ነው፡፡ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ይህንን ‹‹ፀሐይ ፀልመ ወወርኅ ደመ ኮነ ወክዋክብት ወድቁ ፍጡነ ከመ አይርአዩ ዕርቃኖ ለዘአልበሶሙ ብርሃነ›› ሲል ገልጾታል፡፡ እንዲሁም በምድር አራት ተአምራት ታይተዋል፡፡ እነዚህም የቤተ መቅደስ መጋረጃ መቀደድ፣ የዐለቶች መሰንጠቅ፣ የመቃብሮች መከፈት፣
Показати все...
ስቅለት፡ ሕይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ሰቀሉት!

ሰሙነ ሕማማት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  የሰውን ልጅ ከዲያብሎስ ባርነት ነፃ ለማውጣት በፈቃዱ የተቀበላቸው ጸዋትወ መከራዎች የሚታሰቡበት ሳምንት ነው፡፡ የሰሙነ ሕማማት ዕለታት የዓመተ ኩነኔ ወይም የዓመተ ፍዳ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ክርስቲያኖች ክርስቶስ የዋለልንን ውለታ እያሰብን እጅግ የምናዝንበት፣ የምናለቅስበት…

Фото недоступнеДивитись в Telegram
የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል)ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ። የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሐምሌ 3-5  ለማህበራዊ ሳይንስ ሐምሌ  9-11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት ይሰጣል። በወረቀት ላይ የሚፈተኑ የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ሰኔ 30-ሐምሌ 01/2016 ዓ/ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ሐምሌ  6-7/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ይሆናል። ስለሆነም ተፈታኞች እና የሚመለከታቸው ሁሉ ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ተብሏል።
Показати все...