cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Yeshua Apologetics Ministry

➟የሹዋ ዐቅበተ እምነት አገልግሎት አላማ ከክርስትና እምነት አንጻር ደርዛቸውን የጠበቁ ስነ መለኮታዊ ፍልስፍና፤ አመክንዮአዊና ታሪካዊ ጽሑፎችን ማቅረብ በክርስትና ላይ የሚነሱ የተቃውሞ ሀሳቦችንና የኑፋቄ ትምህርቶችን መመከት የሌላውን እምነተ መርህ ከሎጂክና ከታሪካዊ ዳራዎች አንጻር መመርመር ▼ @Yeshua_Apologetics_Ministry

Більше
Рекламні дописи
1 494
Підписники
+724 години
+197 днів
+9730 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

መጽሐፍ ቅዱስ አይጋጭም.....![1] 51) ይሁዳ ኢየሱስን በመክዳቱ ያገኘውን ገንዘብ ምን አደረገው? ጥያቄው፡- «ይህም ሰው በዓመፅ ዋጋ መሬት ገዛ በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ።» (ሐዋ1:18) አንቀጹ በግልጽ እንደሚነግረን ይሁዳ በብሩ መሬት እንደገዛ ነው። ነገር ግን በተቃራኒው ሌላ ቦታ ደግሞ ይህንን እናገኛለን፡- «ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ።» (ማቴ 27:5) መልስ፦ "ይህ ሰው..መሬት" ገዛ የሚለው ቃል ይሁዳ መሬቱን በቀጥታ አልገዛም፤ ይሁን እንጂ ለካህናቱ በመለሰው ገንዘብ (ማቴ 27፥3) የሸክላ ሠሪው መሬት ተገዝቶበታል። ከታች ሦስት ቁጥሮች ወረድ ብለን ስናነብ እንዲህ ይላል፦ “ተማክረውም የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት።” — ማቴዎስ 27፥7 ይህ ማለት፦ ይሁዳ ኢየሱስን አሳልፎ በመስጠቱ የተቀበለው የደም ገንዘብ ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደ ማቴ 27:5። ነገር ግን በራሱ በቤተ መቅደስ በጣለው ገንዘብ መሬት ገዙበት። ምክንያቱም በአሁዳውያን ልማድ መሰረት የደም ገንዘብ ለአምላክ ቤት ማዋል ነውር ስለሆነ ሊወስዱት ያልፈለጉት። በራሱ ስም ገዝተው መዘገቡ ምክንያቱ የንፁህ ሰው ደም ገንዘብ ስለሆነ ከወሰዱ የተጨቋኙ ደም ስለሚርብን ብለው በማሰባቸው ምክንያት ማንም አልወሰደውም ነበር። ለዛም ነው እርሱ ቀጥታ ባይገዛም በሐዋርያት ሥራ 1፡18 ላይ ይሁዳ እርሻ እንደገዛ የሚናገረው። በአጠቃላይ ነገሩን በቅርበት ስንመረምረው አንደኛው ምንባብ የሌላኛው ማጠቃለያ እንደሆነ ነው። 52) ይሁዳ እንዴት ሞተ? ጥያቄው፦ «ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ።» (ማቴ 27:5) የይሁዳን አሟሟት ማቴዎስ የሚነግረን ታንቆ እንደሞተ ነው። ነገር ግን በሌላ ቦታ እንዲህ ይላል፡- «ይህም ሰው በዓመፅ ዋጋ መሬት ገዛ በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ።» (ሐዋ 1:18) ይህኛው አንቀጽ ደግሞ በግንባሩ ተደፍቶና አንጀቱ ተዘርግፎ አንደሞተ ይገልጻል። መልስ፡- የሐዋርያት ሥራ 1፡18 ላይ ያለውን ቃል እስኪ እናንብብ፡- “ይህም ሰው በዓመፅ ዋጋ መሬት ገዛ በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ፤ በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ሁሉ ታወቀ፤ ስለዚህም ያ መሬት በቋንቋቸው አኬልዳማ ተብሎ ተጠራ፥ እርሱም የደም መሬት ማለት ነው፡፡” ይህ ጥቅስ አሟሟቱን ሳይሆን ከሞተ በኋላ የሆነውን የሚናገር ነው፡፡ በዚህ ስፍራ ላይ ሞተ የሚል ቃል አልተጠቀሰም፡፡ ነገር ግን በኢየሩሳሌም ይኖሩ ለነበሩት የታወቀውን ነገር፣ ማለትም ይሁዳ በግምባሩ ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰንጥቆ አንጀቱ መዘርገፉን የሚናገር ነው፡፡ ለዚህ ምክንያታዊ ትንታኔ ሊሆን የሚችለው በትውፊት ሲነገር እንደ ኖረው ይሁዳ ገደላማ በሆነው በሄኖም ሸለቆ ላይ ራሱን በሚሰቅልበት ሰዓት ገመዱ ተበጥሶ ወድቆ ሊሆን ይችላል፤ ወይንም ደግሞ ሬሳው ሳይታይ ለረጅም ጊዜ ስለቆየ ገመዱ ተበጥሶ በመውደቅ ፈራርሶ ሊሆን ይችላል የሚል ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ስፍራ ሞተ የሚል ቃል ስለሌለ እነዚህ ሁለቱ ጥቅሶች ይጋጫሉ ብለን ለመደምደም ከመፍጠናችን በፊት ያሉትን ምክንያታዊ ትንታኔዎች ከግምት ውስጥ ማስገባት ያስፈልገናል፡፡ 53) የደም መሬት የተባለው ለምንድን ነው? ጥያቄው፦ «ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ። የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው። የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ። ተማክረውም የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት። ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ።» (ማቴ 27፡5-8) ይህ አንቀጽ እንደሚነግረን የደም መሬት የተባለበት ምክንያት ዋጋው የደም ዋጋ ስለነበር ነው። ከዚህ በተለየ ግን ሌላ ቦታ ደግሞ የተለየ ሀሳብ እናገኛለን፡- «ይህም ሰው በዓመፅ ዋጋ መሬት ገዛ በግንባሩም ተደፍቶ ከመካከሉ ተሰነጠቀ አንጀቱም ሁሉ ተዘረገፈ፤ በኢየሩሳሌምም ለሚኖሩ ሁሉ ታወቀ፤ ስለዚህም ያ መሬት በቋንቋቸው አኬልዳማ ተብሎ ተጠራ፥ እርሱም የደም መሬት ማለት ነው።» (ሐዋ 1፡18-19) ይህ አንቀጽ ደግሞ የሚነግረን ቦታው ላይ ይሁዳ በመሞቱና ደሙ በመፍሰሱ ምክንያት የደም መሬት እንደተባለ ነው። መልስ፦ አሁንም እንደ መጨረሻዎቹ ሁለት ግልጽ ተቃርኖዎች ተመሳሳይ ሁለት ምንባቦችን በማየት ተቃዋሚያን ለምን ይሁዳ የተቀበረበት ቦታ የደም መስክ ተብሎ ይጠራል በማለት ይሟገታሉ። ማቴዎስ 27፡8 በደም ገንዘብ ስለተገዛ ነው ሲል የሐዋርያት ሥራ 1፡19 ላይ ግን በይሁዳ ደም መሞት ምክንያት እንደሆነ ይናገራል። ሁለቱም ምንባቦች በደም-ገንዘብ በመግዛቱ ምክንያት እንደሆነ ይስማማሉ ስለዚህ አንዱ ጋር ስሙን ጠቅሶ አንዱ ጋር ባይጠቅስ ተደራሲያኑ ጋር ሲቀርብ ተቃርኖ ይሆናልን? የሚለውን እንጂ መጠየቅ ያለብን እኛ ጋር ሲቀርብ ተቃረን ማለት አንችልም። በአጭሩ የሐዋርያት ሥራንም ሆነ የማቴዎስ ወንጌልን ላነበበ ሰው ሁለቱም ስለ አንድ ሰው(ስለ ይሁዳ) ጮክ ብለው እንደሚናገሩ ማወቅ እንችላለን ማለት ነው። ....ይቀጥላል 1] መጽሐፍ ቅዱስ ለሙስሊም ሰባኪያን ምላሻ መጽሐፍ የተወሰደ በወንድም David Yeshua Apologetics 🧑‍💻በቅርብ ቀን 🧑‍💻
Показати все...
👍 3👏 2
በአራቱ ወንጌሎች ግጭት ተብለው የሚነሱ እንዴት እንያቸው? ጥንታዊ ግለ ታሪኮች ለዚህ ዘመን እንከን የለሽነት የታለሙ አይደሉም። ለምሳሌ በአጭሩ እንዴት ማለት መሰላቹ፦ ➥ ስለ አንድ በጣም ጠቃሚ ስለ ሆነ ሰው ግለ ታሪክ ለመፃፍ ብታስቡ ምን አይነት የስነፅሁፍ ዘውግ ትጠቀማላችሁ? የሆረር አፈታሪክ ያለበት ግጥም ወይስ ግለ ታሪክ? በአንደኛው ምዕተ አመት ያለ ግለ ታሪክ ፀሀፊ ብትሆን እና የምትፅፈው በአንደኛው ምዕታመት ላሉ ተደራሲያን ቢሆን እና የግለ ታሪኩ ባለቤትም በአንደኛው ምዕተ ዓመት ያለ ቢሆን በዛን ዘመን የነበረው የአፃፃፍ ሂደት ትከተላለህ ወይስ ከ 1500 አመት በኃላ የመጡ ዘመነኛ የአፃፃፍ ሂደቶችን ትከተላለህ? ለእነዚህ ጥያቄዎች መልሱ ግልፅ ነው። ➥ አራቱ ወንጌላት የተፃፉት በግሪኩ ሮማ ግለ ታሪክ ዘውግ ውስጥ ነው። የግሪኩ ሮማ ግለ ታሪኮች የራሳቸው የሆነ የስነ ፅሁፋዊ ዘውግ አላቸው። እሱም፦ 1) ስለ ገፀ ባህሪው የልጅነት ጊዜ ብዙም ትኩረት አይሰጥም ይልቅ ወደ አገልግሎት ህይወቱ በቶሎ ይገባሉ። ይህም በአራቱ ወንጌላት ላይ ፍንትው ብሎ ይታያላል 2) Compostional device ይጠቀማሉ ማለትም በተለያዩ መተግበሪያዎች ፀሀፊው አንድን ታሪክ በማለያየት ይዘግባል። ለምሳሌ ፕሉታርክ አንድ ቦታ ላይ የዘገበውን ታሪክ በተለየ ዘውግ እራሱን ታሪኩን ይዘግባል። ይህም በወንጌላት ምንም ፍንትው ብሎ የታየ ነው፤ አብዛኞቹ ሰዎች ግጭት እያሉ የሚሮጡበትም ጉዳይ ይህ ነው። 3) ቃላት ቁጥር እንኳን መጠን አለው። ይህም በአራቱ ወንጌላት የቃላት ቁጥር የመቀራረቡ ምክንያት ይህ ነው። እንያንዳንዱን ግጭት በዚህ ትርጓሜውን ሂደት ከሄድን፥ ቀላል ነው ማለት በእርግጥ እንችላለን!! @Yeshua_Apologetics_Ministry
Показати все...
4👏 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ይህቺን መጽሐፍ ለ3ኛ ዕትም ለማብቃት እንቅስቃሴ ጀምረናል። በዚህ መልካም ሥራ መሳተፍ የምትፈልጉ ወገኖች ቴሌግራም ላይ ወንድማችን ማሜን ማናገር ትችላላችሁ። ይህንን መልካም ሥራ ከግብ ለማድረስ አንድ ጥራዝ ከማሳተም ጀምሮ ሁላችንም የአቅማችንን እንለግስ። እግዚአብሔር አምላክ ይባርካችሁ! ቴሌግራም t.me/Muhammad_Ewnetlehulu
Показати все...
😇 4 3
ሰላም። ተመልሰናል ጠፍተን ነበር። እዚህ መንደር ምን አዲስ ነገር አለ?😁
Показати все...
4😁 4👍 2
"ክርስትናን በክርስቶስ መነጽር ማየቱ እግዚአብሔር ወደ መምሰል ለማደግ የመጀመሪያውም የመጨረሻውም መንፈሳዊ መብል ነው። አንዳንድ አላዋቂያን እብሪት ጋልቧቸው ክርስትናን ከክርስቶስ ውጪ ሆነው ለመመዘን መሞከራቸው እብደት እንጂ ሌላ አይደለም። ምክንያቱም ክርስትና የሚለውም ስም ወደ ማን ጠቋሚ መሆኑን እስኪዘነጉ ድረስ ብዙ ይለፋሉና። በእኒህ ዕቡያን ልብ የተከበባችሁ ሰዎች ካላችሁ ተጠበቁ።"
Показати все...
21👍 1
ከእኔ አብ ይበልጣል? ብዙ አርዮሳውያን ሆነ ሙስሊም ወገኖቻችን ይህንን ጥቅስ መሠረት አድርገው ኢየሱስ ፍጡር ነው ከአብ ያንሳል ይሉናል። እስኪ እንቃኘው! “የምትወዱኝስ ብትሆኑ ከእኔ አብ #ይበልጣልና ወደ አብ በመሄዴ ደስ ባላችሁ ነበር።”   — ዮሐንስ 14፥28 ክርስትና አንድ አምላክ ብቻ መኖሩን ቢያስተምርም ይህ አንዱ አምለክ ሦስት አካላት እንዳሉት ስለሚያስተምር በነዚህ አካላት መካከል የሥራ ድርሻ (function) ወይም የደረጃ (rank) ብልጫ ሊኖር ይችላል፡፡ ይህ በእግዚአብሔር በራሱ ሕላዌ ውስጥ የሚገኝ እንጂ ከእርሱ ውጪ የሚገኝ ባለመሆኑ በሥላሴነት ከሚኖረው ከአንዱ አምላክ ውጪ የሚገኝ አካል ብልጫ እንዳለው እስካልተነገረ ድረስ ምንም የሚፈጥረው ችግር የለም፡፡ በነዚህ ቦታዎች የተጠቀሰው μείζων(ሜይዞን)  የሚለው የግሪክ ቃል ደረጃን እንጂ የግድ የባሕርይ ብልጫን የሚያመለክት አይደለም፡፡ ማሳያ አንድ፦ “እውነት እላችኋለሁ፤ ከሴት ከተወለዱት መካከል እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ያለ አልተነሣም፤ ሆኖም በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚያንሰው #ይበልጠዋልμείζων[ሜይዞን]።   — ማቴዎስ 11፥11 ይህ ማለት በመንግሥተ ሰማይ ያለው አካል በባሕርይ ይበልጠዋል ማለትም በመንግሥተ ሰማይ ያለው ፈጣሪ ዮሐንስ ፍጡር ነው ማለት ማለት አይደለም። ሁለቱም ፍጡሮች ናቸውና ነገር ግን በሥራ ድርሻ የደረጃ ብልጫን ነው የሚያሳየው። ማሳያ ሁለት፦“እውነት እላችኋለሁ፤ በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ ይሠራል፤ እንዲያውም እኔ ወደ አብ ስለምሄድ፣ ከእነዚህም #የሚበልጥ ሜይዞን[μείζων]  ያደርጋል።”   — ዮሐንስ 14፥12 ይህም ማለት እኛ በባሕሪያችን ከክርስቶስ እንበልጣለን ማለት አይደለም። በአጭሩ አንድ አካል ከሌላው በሥራ ድርሻ፣ በሥልጣን ወይም በደረጃ ይበልጣል ማለት የባሕርይ ብልጫ አለው ማለት እንዳልሆነ ልብ ሊባል ይገባል፡፡ ለምሳሌ ያህል የአንድ አገር መሪ በሥራ ድርሻ፣ በሥልጣንም ሆነ በደረጃ በስሩ ከሚተዳደሩት ዜጎች ይበልጣል፡፡ ይህ ማለት ግን እንደ ሰው ያለው ዋጋ (Value) ከማንም ይበልጣል ማለት አይደለም፡፡ ባል የቤተሰብ ራስ እንደመሆኑ መጠን ከላይ በተጠቀሱት መንገዶች ከሚስቱ ሊበልጥ ይችላል ነገር ግን ወንድ እንደ ሰውነቱ ከሴት ይበልጣል ወይም ሴት ከወንድ ታንሳለች ማለት ግን አይደለም፡፡ የግሪክ አዲስ ኪዳን የባሕርይ ብልጫን ለማመልከት “ዲያፎሮስ”[διάφορος] የሚል ሌላ ቃል የሚጠቀም ሲሆን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በባሕርዩ ከመላእክት የላቀ መሆኑን ለማመልከት ዕብራውያን 1፡4 ላይ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ከመላእክት ይልቅ እጅግ የሚበልጥ ስምን በወረሰ መጠን እንዲሁ ከእነርሱ አብዝቶ #ይበልጣል[διαφορώτερον]።   — ዕብራውያን 1፥4 በሥላሴ አካላት መካከል የሚገኘውን ግንኙነት ለማመልከት ግን ይህ ቃል ጥቅም ላይ ውሎ አናገኝም፡፡ ስለዚህ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አብ ከወልድ መብለጡ መነገሩ የመለኮታዊ ባሕርይ ብልጫን ሳይሆን የሥራ ክፍፍልን እና ወልድ ሥጋን በመልበስ መለኮታዊ ክብሩን ትቶ ወደ ምድር እንደመምጣቱ መጠን (ፈልጵስዩስ 2፡5-11) የደረጃ ብልጫን ብቻ የሚያመለክት በመሆኑ የኢየሱስን አምላካዊ ባሕርይ ከአብ የሚያሳንስ አይደለም፡፡
Показати все...
👍 14 11👏 4
ኢየሱስ አምላክ ነውን? እስኪ ይህቺን ቪዲዮ እንጋብዛችሁ። ብዙዎቹን በቻናላችን ላይ ዳሰሳ አድርገናል ወደ ላይ ከፍ ስትሉ ታገኙዋቸዋላችሁ። ይቺን ቪዲዮ ተጋበዙ፦ https://vm.tiktok.com/ZMrdWgekn/
Показати все...
👍 6
ኢየሱስ አምላክ ነውን? እስኪ ይህቺን ቪዲዮ እንጋብዛችሁ። ብዙዎቹን በቻናላችን ላይ ዳሰሳ አድርገናል ወደ ላይ ከፍ ስትሉ ታገኙዋቸዋላችሁ። ይቺን ቪዲዮ ተጋበዙ፦ https://vm.tiktok.com/ZMrdWgekn/
Показати все...
👍 3
🚩 ይህ የወንድማችን የመሐመድ አበባው YouTube ገጽ ነው። ይህ ወንድማችን በእስልምና ዙሪያ የሚያገለግል የተወደደ ወንድም ነው። Subscribe እና Share በማድረግ አግዙት!
Показати все...
12👍 5
Показати все...
በእስልምና የድነት ዋስትና አለን?

Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.