cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

የመከኒሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የስብከተ ወንጌል ክፍል

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
189
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Watch "የ2014 ዓ/ም የመጨረሻ ሰንበት የመካኒሳ ደ/ገ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የጥዋት ጉባኤ ተምህርተ ወንጌል መ/ሐ ሰለሞን ጽጌ ዝማሬ በዘማሪ ገ/አምላክ" on YouTube https://youtu.be/m_n6GIO5CSc
Показати все...
የ2014 ዓ/ም የመጨረሻ ሰንበት የመካኒሳ ደ/ገ ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል የጥዋት ጉባኤ ተምህርተ ወንጌል መ/ሐ ሰለሞን ጽጌ ዝማሬ በዘማሪ ገ/አምላክ

Watch "ነሐሴ 13/2014 ዓ/ም #እርሱን ስሙት## ማቴ 17:5 በመጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፊያለው ኢንጅነር የደብረ ታቦር በዓል ትምህርት" on YouTube https://youtu.be/rC7EQkzMSD8
Показати все...
ነሐሴ 13/2014 ዓ/ም #እርሱን ስሙት## ማቴ 17:5 በመጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፊያለው ኢንጅነር የደብረ ታቦር በዓል ትምህርት

እርሱን ስሙት ማቴ 17:5 በመጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፊያለው

Watch "ሀምሌ 22/11/2014 ዓ/ም ዓመታዊ የቅዱስ ዑራኤል በዐል የማታ ጉባኤ የዝማሬ አገልግሎት" on YouTube https://youtu.be/AHsp_aUVCDM
Показати все...
ሀምሌ 22/11/2014 ዓ/ም ዓመታዊ የቅዱስ ዑራኤል በዐል የማታ ጉባኤ የዝማሬ አገልግሎት

ከሰዎች ጋር በሰላም ለመኖር የሚረዱህ ምክሮች ─ ─━━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─ ─ 👉ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ። “ሁለተኛይቱም፦ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ የምትል እርስዋን የምትመስል ይህች ናት። ከእነዚህ የምትበልጥ ሌላ ትእዛዝ የለችም።” (ማርቆስ 12፥31) 👉ለመስማት እንጂ ለመናገር አትፍጠን፡፡ “ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤” (ያዕ.1:19) 👉ይቅር ስትል ቂም አትያዝ፡፡ "እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ፤ በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት።" (ቆላስይስ 3፡13-14) 👉በሁሉም ነገር ትዕግሥተኛ ሁን። “ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤” (1ኛ ቆሮንቶስ 13፥4) 👉ሳትሰስት ሰጥ። “ኀጥእ ቀኑን ሁሉ ምኞትን ይመኛል፤ ጻድቅ ግን ይሰጣል፥ አይሰስትም።” (ምሳሌ 21፥26) 👉የሰው ንግግር ሳታቋርጥ አዳምጥ። “ሳይሰማ ነገርን በሚመልስ ስንፍናና እፍረት ይሆንበታል።” (ምሳሌ 18፥13) 👉መልስ ስትመልስ አትከራከር። “ጥል ባለበት ዘንድ እርድ ከሞላበት ቤት በጸጥታ ደረቅ ቍራሽ ይሻላል።” (ምሳሌ 17: 1) 👉የገባኽውን ቃል ጠብቅ፡፡ “የምትዘገይ ተስፋ ልብን ታሳዝናለች፤ የተገኘች ፈቃድ ግን የሕይወት ዛፍ ናት።” (ምሳሌ 13፥12) 👉ሰውን ስታምን ካለመጠራጠር ይሁን፡፡ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል።” (1ኛ ቆሮንቶስ 13፥7) 👉ሰዎች ላይ ክፉ አታስብ። “በመጥፎና በጠማማ ትውልድ መካከል ያለ ነቀፋ የዋሆችም ነውርም የሌለባቸው የእግዚአብሔር ልጆች እንድትሆኑ ሳታንጐራጉሩ ክፉም ሳታስቡ ሁሉን አድርጉ፤” (ፊልጵስዩስ 2፥14-15) 👉ይቅር መባባልን ሁሌም አትዘንጋ። መራርነትና ንዴት ቁጣም ጩኸትም መሳደብም ሁሉ ከክፋት ሁሉ ጋር ከእናንተ ዘንድ ይወገድ።እርስ በርሳችሁም ቸሮችና ርኅሩኆች ሁኑ፥ እግዚአብሔርም ደግሞ በክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ ይቅር ተባባሉ። (ኤፌሶን 4:31-32) •••
Показати все...
ሐምሌ ፯ የአብርሃሙ ሥላሴ በዚህች ቀን አጋዕዝተ ዓለም ስላሴ በአብርሃም ቤት ተገኝተው ቤቱን የባረኩበት የአንድነታቸውንና ሶስትነታቸው ሚስጢር የገለጹበት ታላቅ በዓል ነው። ወበዛቲ ዕለት ቦኡ ሥሉስ ቅዱስ ውስተ ቤተ አብርሃም ወተሴሰዩ ዘአቅረቦ ሎሙ፡፡ በከመ መጽሐፍ ውስተ ኦሪት ወአብሠርዎ ልደቶ ለይስሐቅ ወባረክዎ፡፡ በዚችም ቀን ልዩ የሆኑ ሦስቱ አካላት /ቅድስት ሥላሴ/ በኦሪት መጽሐፍ እንደ ተጻፈ ወደ አብርሃም ቤት ገቡ ያቀረበላቸውንም ተመገቡ፡፡ የይስሐቅንም ልደት አበሠሩት ባረኩት አከበሩትም፡፡ መጽሐፈ ስንክሳር ዘሐምሌ ሰባት ሥላሴ ማለት በቅዱሳት መጻሕፍት መሠረት አንድ አምላክ በሦስት አካላት እንዳለ ለአበው ለነቢያትና ለሐዋርያት መገለጡን አምነን የምንማረው ትምህርት ነው፡፡ ፨ ሥላሴ ማለት የግእዝ ቃል ሲሆን ሦስት፤ ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ፨ የአንድ አምላክ በሦስትነት መገለጥን ለመረዳት በኦሪት ዘፍጥረት 1፡26 ላይ በተገለጠው መሠረት “እግዚአብሔርም አለ ሰውን በመልካችን እንደምሳሌችን እንፍጠር” ይላል ይህ አገላለጽ “እግዚአብሔርም አለ” ሲል አንድነትን (አንድነታቸውን) “እንፍጠር” ሲል ከአንድ በላይ (ሦስትነትን) መሆንን ያስረዳል፡፡ ፨ በኦሪት ዘፍጥረት 3፡22 ላይ “አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ” የሚለው አገላለጽ ከአንድ በላይ መሆንን የሚያስረዳ ነው፡፡ ፨ በኦሪት ዘፍጥረት 11፡5-7 የተጠቀሰው “ኑ እንውረድ ቋንቋቸውን እንደባልቅ”በማለት ሥላሴ የተናገሩት ከአንድ በላይ (ሦስትነት) መሆንን የሚያመለክት ነው፡፡ ፨ በኦሪት ዘፍጥረት18 ላይ ሥላሴ ለአብርሃም እንደተገጹለት የሚያስረዳ ሀሳብ የያዘ አገላለጽ ሲሆን ሥላሴ ለአብርሃም በመገለጻቸው አብርሃም ሥላሴን በእንግድነት አሰተናግዷል፡፡ አብርሃምም የሥላሴ ባለሟል መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ እንዲሁም በእርጅናው ጊዜ ልጅ እንደሚያገኝ ተበስሮለታል፡፡ ዘሩም እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደ ምድር አሸዋ እንደሚበዛ በሥላሴ ቃል ተገብቶለታል፡፡ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሚጠመቅበት ጊዜም የሥላሴ ምስጢር ተገልጧል፡፡ “እግዚአብሔር አብ የምወደው ልጄ ይህ ነው” ሲል እግዚአብሔር ወልድ ሲጠመቅ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል ተገልጧል፡፡ ማቴ.3፡13 አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያትን "ሂዱና በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ ደቀመዛሙርቴ አድርጉ” ማቴ. 14፡28 ሲል ሦስትነት የሚገልጽ መልእክት አስተላልፏል፡፡ እንግዲህ ሥላሴ ስንል በስም በአካል፣ በግብር የተለዩ መሆናቸውን ያስረዳል፡፡ ይኸውም፡- የአካል ሦስትነት፡- አብ የራሱ መልክ፣ ገጽ፣ አካል አለው፡፡ ወልድ የራሱ መልክ፣ ገጽ፣ አካል አለው፡፡ መንፈስ ቅዱስ፡- የራሱ መልክ፣ ገጽ አካል አለው፡፡ የስም ሦስትነት ስንል፡- የአንዱ ስም ለአንዱ የማይሆን አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ በመባል ይጠራሉ፡፡ የግብር ሦስትነት ስንል፡- አብ ወላዲ፣ አስራጺ ሲሆን ወልድ ተወላዲ ነው የተወለደውም ከአብ ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ሰራጺ ነው፡፡ የሰረጸውም ከአብ ነው፡፡ የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት ለመረዳት በሥላሴ ፈቃድ መጻሕፍት እንዳስተማሩ ሊቃውንት እንደተረጉሙልን እንጂ ማንም በገዛ ፈቃዱ ተመራምሮ አይደርስበትም፡፡ በዓለ ሥላሴ በዓላት የሰው ልጅ በእግዚአብሔር የተደረገለትን የቸርነት ሥራ በማሰብ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታት ያደረጉትን ተጋድሎና ተአምራት በመስማትና በማሰማት የተደረገውን ድንቅ ነገር በመዘከር በደስታ የሚከበሩ ዕለታት ናቸው፡፡ “በቃለ አሜን ወበትፍስሕት ድምፁ እለ ይገብሩ በዓለ፡- በዓለ የሚያደርጉ ሰዎች የደስታና የምስጋና ቃል አለው” እንዳለ ቅዱስ ዳዊት መዝ.41፡5 የበዓል መከበርን ያሳወቁት ሥላሴ ሲሆኑ፤ ሥላሴ ፍጥረታትን ስድስት ቀናት ፈጥረው ሰባተኛውን ቀን ቀዳሚትን አርፈውበታል፡፡ “በሰባተኛውም ቀን ከሥራው ሁሉ ዐረፈ፡፡ እግዚአብሔር ሰባተኛውን ቀን ባርከውም ቀድሰውም እግዚአብሔር ሊያደርገው ከፈጠረው ሥራ ሁሉ በእርሱ ዐርፏልና” ዘፍ.1፡1-3 እንዲል በዚህ መሠረትነት በዓል እንዲከበር የመደቡት ሥላሴ ሲሆኑ የመጀመሪያው የሥላሴ መታሰቢያና የበዓል አከባበር መጀመሪያ የሆነችው ቀዳሚት ናት፡፡ የሐምሌ ፯ ቀንም ሥላሴ በአብርሃም ቤት ገብተው ቸርነታቸውና ፍቅራቸውን የገለጹበት፣ አብርሃምን የባረኩትና ልጅ እንደሚወልድ፣ መጻዒው ሕይወቱን የነገሩት ዕለት ስለሆነ በዓሉን ስናዘክር ሥላሴን እናመሰግናለን፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም ሐምሌ ፯ ቀን በታላቅ በዓል ከእኛ ከልጆችዋ ጋር በመሆን ስታከብረው ትኖራለች። የቅድስት ሥላሴ ቸርነት አይለየን፡፡ አሜን!!!
Показати все...
የተከተለውን ጥሮፊሞስን ወደ መቅደስ ያስገባው ስለመሰላቸው ተቃውሞአቸው በረታ፡፡ የሐዋ. 22.29፡፡ ከተማውንም አወኩት፤ ይህ ነበር ቅዱስ ጳውሎስን በ58 ዓ.ም ለሮም እሥር የዳረገው፡፡ከብዙ መከራና ስቃይ በኋላ ታሥሮ ሮም ገባ፡፡ በዚያም በቁም እሥር ሆኖ ለሁለት ዓመታት ያህል ወንጌል ሰበከ፡፡ የሁለቱን ዓመት የቁም እሥር እንደጨረሰ ወደ ኔሮን ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ ይህም በ60ዎቹ ዓ.ም ነው፡፡ በፍርድ ቤቱ በተደረገው ምርመራ የሮሜን ሕግ የሚቃወም ምንም ወንጀል ስላልተገኘበት በነፃ ተለቀቀ አራተኛው የቅዱስ ጳውሎስ ጉዞ ከዚህ በኋላ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ አራተኛውንና የሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ያልመዘገበውን ጉዞውን ያደረገው፡፡ ይህ ጉዞው በመታሠሩ አዝነው ተክዘው የነበሩ ክርስቲያኖችን ለማጽናናት የጀመራቸውን ሥራዎች ፍጻሜ ለማየት የተደረገ ጉዞ ነው፡፡ በዚህም ጉዞው ኢየሩሳሌምን፣ ኤፌሶንን፣ ሎዶቅያን፣ መቄዶንያን፣ ቀርጤስን፣ ጢሮአዳን፣ ድልማጥያን፣ እልዋሪቆን፣ ኒቆጵልዮን፣ ብረንዲስን፣ ጐብኝቷል፡፡ በዚህ የመጨረሻ የስብከት ጉዞው ለአራት ዓመታት ያህል ቆይቷል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ የመጀመሪያው ስነ መለኮትንና ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን አምልቶ አስፍቶ የጻፈ በትምህርቱ እጅግ ተጽእኖ ማሳደር የቻለ የቤተክርስቲያን ታላቅ መምህር ነው እርሱ የክርስቶስ ቤተክስርቲያን የአሕዛብ ሐዋርያ ነው። ግብረ ሐዋርያት የሚጀምረው በቅዱስ ጴጥሮስ ሥራ ሲሆን የምዕራፉም መጨረሻ የሚጠናቀቀውበቅዱስ ጳዉሎስ አገልግሎት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ቅዱስ ጴጥሮስ አይሁድን /የተገረዙትን/ በአባትነት እንዲጠብቅ ሲሾም በተመሳሳይ መልኩ ደግሞ ቅዱስ ጳዉሎስ አሕዛብን /ያልተገረዙትን/ እንዲጠብቅና እንዲያስተምር ተሹሞ ነበር፡፡ ስለዚህም ነገር ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለገላትያ ሰዎች በጻፈው መልእክቱ «… ጴጥሮስ ለተገረዙት የሆነው ወንጌል አደራ እንደተሰጠው እንዲሁ ለእኔ ላልተገረዙት የሆነው ወንጌል አደራ እንደተሰጠኝ እዩ፤ ለተገረዙት ሐዋርያ እንድሆን ለጴጥሮስ የሠራለት ለእኔ ደግሞ ለአሕዛብ ሐዋርያ እንድሆን ሠርቶአልና፡፡» በማለት ነው የገለጸው፡፡/የሐዋ.2.7-9/ ሰማዕትነት ቅዱስ ጳውሎስ ና ኔሮን ቄሳር በ ማናቸውም ነገር የማይስማሙ አጥፊና ጠፊ ነበሩ ኔሮን ቄሣር ክፉና አመጸኛ ነበር ቅ/ጳውሎስ ግን ደግና ፈቃደኛ ነበር ኔሮን ቄሳር ከኀዲና ጨለማ በቃኝ የማይል ንፉግ የሠይጣን ማደርያ ነበር ቅ.ጳውሎስ ግን ሃይማኖታዊና ብርሃን ፣ በቃኝ የሚል ቸር የመንፈስቅዱስ ማደርያ ነበር በመጨረሻ በ64 ዓ.ም ኔሮን በጥጋቡ የሮማ ከተማ ስትቃጠል ምን እንደምትመስል ማየት እፈልጋለሁ ብሎ አቃጠላት፡፡ የሮም ሕዝብ በከተማው መቃጠል በማዘኑና በማመፁ ነገሩን ሁሉ በክርስቲያኖች ላይ አሳበበ፡፡ በዚህም የተነሣ ክርስቲያን የተባለ ሁሉ መሰደድ፣ መሠየፍ፣ መታረድ፣ ዕጣ ፈንታው ሆነ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በኒቆጵልዮን ከተማ ሲያስተምር በ65 ዓ.ም ተይዞ ወደ ወኅኒ ገባ፡፡ ለሁለት ዓመት ከስድስት ወር በጨለማ ቤት ታሥሮ ቆየ ቅዱስ ጳውሎስ በኔሮን ቄሳር ፊት በቀረበ ጊዜ በቀኝ እጁ ከሰንሰለቱ ጋር መስቀሉን ይዞ ሳይፈራ የክርስቶስን ነገር መሰከረ ኔሮን ቄሳርም በቁጣ ቃል ይሙት በቃ ፈረደበት ለልማዱ ሮማውያን በወንጀለኛ የሞት ፍርድ ሲፈርዱ የተፈረደበት ሰው የውጭ ሀገር ዜጋ የሆነ እንደሆነ አስቀድሞ በግርፋትና በሌላም በልዩ ልዩ ሥቃይ ካሠቃዩት በኋላ በመስቀል ወይም በሰይፍ ይገድሉት ነበር ቅዱስ ጳውሎስ ግን በጠርሴስ ተወላጅነቱ የሮማውያን ዜጋ ስለሆነ ሥቃዩ ቀርቶለት ባንድ ሥቃይ ብቻ በሠይፍ እንዲሞት ተፈረደበት ወደ መሞቻው ስፍራ ሲወስዱት በንግግሩና በአስተዬቱ ሁሉ ምንም ፍርሃት አልነበረበትም እንዲያውም በጦርነት ላይ ድል አድርጎ ገድሎና ማርኮ እየፎከረ በደስታ ወደ ቤቱ የሚመለስ ወታደር ይመስል ነበር፡፡ በመጨረሻም በ74 ዓመት ዕድሜው በሮማ ከተማ በኦስትያ መንገድ አንገቱን ተሠይፎ በ67 ዓ.ም ሐምሌ አምስት ቀን በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡ በአጠቃላይ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ :-ፀባዩ ቅዱስ ጳውሎስ ለእውነት ነገር ይሉኝታና ፍርሃት የሌለበት ደፋር ነበር (ሮሜ1፡16) ለ ጊዜውም በሚሆነው ንቁ ወደፊትም በሚሆነው አሳቢና ጠርጣሪ ነበር (ሐዋ27፡30) በድንገተኛ ነገር ምላሽ ለመስጠት የሚችል ና ንግግር አሳማሪ ነበር(ሐዋ26፡1-7) መጻሕፍትንም ለማንበብና ለመተርጎም መልዕክትን ለመጻፍና የሰውን ልብ በፍቅር ለመሳብ ሁሉንም ለመምሰልና ደስ ለማሰኘት ከመንፈስ ቅዱስ ሥጦታ ነበረው የስሙ ትርጓሜ ቅዱስ ጳውሎስ የስሙ ትርጓሜ ብርሃን ማለት ነው፥ ሰርግዮስ ጳውሎስ የተባለ ሀገረ ገዥ የገዛ ስሙን ሰጥቶት ነው፥ የቀደመ ስሙ ሳውል ነበር። ይህ ሀገረ ገዥ አስተዋይ ሰው ስለነበር፡- የእግዚአብሔርን ቃል ሊሰማ ወድዶ፥ በርናባስንና ሳውልን ወደ እርሱ አስጠራቸው። ኤልማስ የተባለው ጠንቋይ ግን አገረ ገዥውን ከማመን ለማጣመም ፈልጐ ተቃወማቸው። ሳውል ግን መንፈስ ቅዱስ ባደረበት ሰውነት ሆኖ ትኩር ብሎ በመመልከት ጋኔኑን ነሠጸው አይኑንም አሳወረው በዚያን ጊዜ አገረ ገዥው የተደረገውን ባየ ጊዜ ከጌታ ትምህርት የተነሣ ተገርሞ አመነ። የጠንቋዩን ዓይነ ሥጋ በተአምራት ሲያጠፋበት፥ የእርሱን ደግሞ ዓይነ ኅሊናውን ሲያበራለት አይቶ ጳውሎስ (ብርሃን) የሚለው ስም ለአንተ ይገባሃል አለው። የሐዋ ፲፫፥፮።ጳውሎስ ማለት ንዋይ ኅሩይ (ምርጥ ዕቃ) ማለትም ነው። ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ጳውሎስ ለሐናንያ በመሰከረለት ጊዜ፡- «ይህ በአሕዛብም፥ በነገሥታትም፥ በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤» ብሎታል። የሐዋ ፱፥፲፭። ምርጥ ዕቃ የተባለው መዶሻ ነው። እርሱም ሰባት የማዕድን አይነቶችን ቀጥቅጦ አንድ የሚያደርግ ነው፤ ቅዱስ ጳውሎስም እግዚአብሔርን እና ሰውን፥ሰውን እና መላእክትን፥ ሕዝብን እና አሕዛብን፥ ነፍስን እና ሥጋን አስታርቆ አንድ ያደርጋል። አንድም ምርጥ ዕቃ የተባሉ ወርቅና ብር ናቸው። ወርቅና ብር ለንዋያት ሁሉ ጌጥ እንደሆኑ፡- እርሱም የቤተ ክርስቲያን ጌጥ ነው። አንድም፡- ጳውሎስ ማለት፡- አመስጋኝ፥ ደስታ፥ ምዑዝ ነገር የሚናገር፥ ልሳነ ክርስቶስ፥ ሰላም፥ ፍቅር ማለት ነው።ዕውቀትን ከትህትና ደርቦ የያዘ ነበር፡- ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በኢየሩሳሌም በሚገኘው በታላቁ የአይሁድ ትምህርት ቤት በሊቁ በገማልያል እግር ሥር ብሉይ ኪዳንን የተማረ ነበር፡፡ በኋላም ትምህርተ ክርስትናን ከሐዋርያት አግኝቷል፡፡ ይህን ሁሉ ዕውቀት ይዞ ሁል ጊዜ ኑሮው የትህትና ነበር፡፡ እኔ ጭንጋፍ ነኝ እስከማለትም ደርሶ ነበር፡፡ (1ቆሮ. 15.8)ትጉህና ታታሪ ነበረ፡- ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስለ42 ዓመታት ያህል በሐዋርያነት አገልግሎአል፡፡ እስከ እስጳኝ ድረስ ሄዶም አስተምሯል፡፡ በባሕር እና በእግር፣ ተመላልሷል፡፡ በ12ቱም ሐዋርያት ሀገረ ስብከት እየገባ ወንድሞቹን አግዞአቸዋል፡፡ ትዕሥተኛ ነበረ፡- ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች በላከው ቀዳማዊ መልእክቱ እንደገለጠው (11.25-33) ብዙ ፈተናዎችን አልፏል፡፡ ሁለት ጊዜ ታሥሯል ተደብድቧል፣ በረሃብ ተገርፏል ይህ ሁሉ ቢሆንም በኑሮው ደስተኛ ነበር፡፡ በሮሜ ታሥሮ እያለ ለፊልጵስዩስ ሰዎች መልእክት ስጽፍ በደስታ የተሞላ ነበረ፡፡ በመጀመሪያ ጉዞው ያልተቀበሉትን ከተሞች በሁለተኛው አልያም በሦስተኛ ጉዞው ጎብኛቸው እንጂ እምቢ አሉኝ ብሎ ተስፋ አልቆረጠም፡፡ ጥበበኛ ነበረ፡- ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን የቤተ ክርስቲያን አበው (መዶሻ) ይሉታል፡፡ መዶሻ ማዕድናቱን ቀጥቅጦ አንደ
Показати все...
ያደርጋቸዋል፤ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም በትምህርቱ ሕዝብንና አሕዛብን አንድ ያደረገ ሐዋርያ ነው፡፡ በ50 ዓ.ም አካባቢ ወደ ኢየሩሳሌም ሲወጣ ቲቶንና በርናባስን አስከትሎ ነበር፡፡ ቲቶን ከአሕዛብ ወገን በርናባስን ደግሞ ከአይሁድ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ሰውን እንዴት መቅረብ እንደሚቻል የሚያውቅ ሰው ነበረ፡- ከተራ ሰዎች እስከ ነገሥታት ቤተሰቦች በፍቅር እየሳበ ክርስቲያን አድርጓቸዋል፡፡ በመልእክቱ መጨረሻ የቤተክርስቲያን ልጆች በስማቸው እየጠራ ሰላምታ ማቅረብ የዘወትር ልማዱ ነበረ፡፡ ይህም ሁሉም በልቡ እንደታተሙ ያውቁ ዘንድ ነው፡፡ ጸሐፊ ነበር፡- ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቃል ያለ ይረሳል በጽሑፍ ያለ ይወረሳል ነውና ያስተማራቸውን ክርስቲያኖች እንዲሁ አይተዋቸውም፡፡ ለሃይማኖታቸው ማጽኛ ለመንፈሳዊ ሕይወታቸው መመሪያ የሚሆኑ መልእክታትን ጽፎላቸዋል፡፡ አብዛኛዎቹ መልእክታት በእሥር ቤት ውስጥ ነው፡፡ ለመጓዝ የሚያስችለው አመቺ ጊዜ ሲያገኝ በአካል፣ በቃል፣ ያስተምራቸዋል፡፡ ሲታሠር መንቀሳቀስ ሲከለከል ደግሞ ጣቶቹ ብዕር ይጨብጣሉ፡፡ መልእክቶቹ በየሀገረ ስብከቱ ይላካሉ፡፡ ሥራ ወዳድ ነበር፡- ቅዱስ ጳውሎስ ሌት ተቀን ለስብከተ ወንጌል ቢባክንም ለምእመናን እንዳይከብድባቸው ድንኳን እየሰፋ የዕለት ጉርሱን የዓመት ልብሱን ያገኝ ነበር፡፡ የሐዋ. 18.3፣4 ለዚህም ነው ‹ሊሠራ የማይወድ ቢኖር አይብላ› እያለ ያስተምር የነበረው፡፡ 2ተሰ.3.10፡፡ ሐዋርያው ጳውሎስ በዘመናት ውስጥ 33 ዓ.ም ለሐዋርያነት ተጠራ:: ወደ ዓረብ ምድር ሄደ በዚያም ፫ ዓመት ቆየ 35 ዓ.ም ወደ ኢየሩሳሌም ለአጭር ጉብኝት ሄደ 35-45 ዓ.ም ኪልቅያ ሶርያ አንጾኪያ 46 ዓ.ም ከአዕማድ መሪዎች ጋር በኢየሩሳሌም መገናኘቱ (ገላ 2:1-10) ከአንጾኪያ ይዞት የሄደውን እርዳታ ለኢየሩሳሌም ቅዱሳን ማድረሱ (ሐዋ 11:27-30) 47-48ዓ.ም ጳውሎስ እና በርናባስ የመጀመሪያውን ሐዋርያዊ ጉዞ ማድረጋቸው (ሐዋ 13:4-14:28) 48/49ዓ.ም የሐዋርያት ጉባኤና ውሳኔ (ሐዋ 15፡1-20) 49-51/52 ዓ.ም ጳውሎስና ሲላስ በመቄዶንያና በአካይያ:: የፊልጵስዩስ በተሰሎንቄ በቤሪያ እና በቆሮንቶስ አብያተ ክርስቲያናት ተመሠረቱ፡፡ (ሐዋ 16:9-18:18) 51/52 ዓ.ም ጳውሎስ በኢየሩሳሌም አስቸኳይ ጉብኝት አደረገ 52-55 ዓ.ም ጳውሎስ በኤፌሶን (ሐዋ 19:1-20:1) 55-57 ዓ.ም ጳውሎስ በመቄዶንያ በእልዋሪቆን እና በቆሮንቶስ 57 ዓ.ም ጳውሎስ ለመጨረሻ ጊዜ ኢየሩሳሌምን መጎብኘቱ:: መያዙ እና መታሠሩ:: 57-59ዓ.ም በቂሳርያ መታሠሩ (ሐዋ23:35-26:32) 59-60ዓ.ም ወደ ኢጣሊያ ጉዞ 60-62ዓ.ም በቁም እስር በሮም መቀመጡ 62 ዓ.ም ጳውሎስ በቄሳር ፊት 64 ዓ.ም የሮም መቃጠል 65ዓ.ም ቅዱስ ጳውሎስ በቄሳር ወታደሮች ተያዘ 65-66ዓ.ም በሮም እስር ቤት ቆየ 67 ዓ.ም በኔሮን ቄሳር ትዕዛዝ በሰማዕትነት አረፈ የአባታቶቻችን የቅዱስ ጴጥሮስና ቅዱስ ጳውሎስ ጸሎትና በረከት በሁላችን ይደርብን አሜን ወስብሐት ለእግዚአብሔር
Показати все...
ይህን የሚያውቀው ሐናንያ በቅድሚያ ከእግዚአብሔር ጋር መከራከር ጀምሮ ነበር፡፡ እግዚአብሔር አያውቀው ይመስል ስለ ቅዱስ ጳውሎስ ማስረዳት ጀመረ፡፡ በመጨረሻ ግን ‹ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእሥራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤ ስለ ስሜ ስንት መከራ ሊቀበል እንዲያስፈልገው እኔ አመለክተዋለሁና› በማለት እግዚአብሔር ሐናንያን ላከው፡፡ ይህንንም እርሱ ራሱ በሐዋ22፡12 ላይ ተናግሮታል ሐናንያ ቅዱስ ጳውሎስን ካጠመቀውና ካስተማረውም በኋላ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ዓረብ ሀገር መሄዱን ራሱ ተናግሮአል፡፡ ገላ 1.17፡፡ ቅዱስ ጳወሎስ የተጠራው ሦስት ጊዜ ነው፡፡ የተጠራው በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ነው፡፡ የእርሱ ጥሪ በአብ ስም የተከናወነው በእናቱ ማኅፀን ነው፡፡ ይህንንም ራሱ ቅዱስ ጳዉሎስ ሲገልጽ «ነገር ግን በእናቴ ማኅጸን ሳለሁ የለየኝ፤ በጸጋውም የጠራኝ፤ እግዚአብሔር በአሕዛብ መካከል ስለ እርሱ ወንጌልን እሰብክ ዘንድ በእኔ ልጁን በእኔ ሁኔታ ሊገልጥ በወደደ ጊዜ ወዲያው ከሥጋና ከደም ጋር አልተማከርሁም፤» በማለት ነው፡፡ በዚህም አብ እግዚአብሔር በሚለው አምላካዊ ስሙ እንዳጠራው በምስጢር እንረዳለን፡፡ /ገላ.1.15-16/ ሌላኛው ጥሪ ደግሞ በወልድ የተከናወነው ነው፡፡ አስቀድመን እንደገለጽነው እግዚአብሔር ወልድ በደማስቆ ጎዳና ላይ «ሳውል ሳውል ለምን ታሳድደኛለህ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ» ብሎ ከገሰጸው በኋላ ወደ ካህኑ ሐናንያ በላከው ወቅት ነው፡፡ በዚህ ወቅትም ጌታ ቅዱስ ጳዉሎስን ለምን እንደመረጠው ለካህኑ ሐናንያም ሲያስረዳ «ይህ በአሕዛብምበነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃነውና፤»በማለት ነው፡፡/የሐዋ.9.15/ ቅዱስ ጳዉሎስ ከአብና ከወልድ ባሻገር በመንፈስ ቅዱስም ለአገልግሎት የተመረጠ ነው፡፡ ይህም የሆነው መንፈስ ቅዱስ ለአባቶቻችን «በርናባስንና ሳዉልን ለጠራኋቸው ሥራ ለዩልኝ» /ሐዋ.13.21/ ባለበት ወቅት እና እንዲሁም «በዚያን ጊዜም ከጦሙ፤ ከጸለዩም፤ እጃቸውንም ከጫኑ በኋላ አሰናበቱ በመንፈስ ቅዱስ ተልከውወደ ሰሌውቅያ ወረዱ፤አቸው፡፡ እነርሱም» በሚለው አምላካዊ ቃል መሠረት ነው፡፡ /የሐዋ.13.3-4/ በመሆኑም የቅዱስ ጳዉሎስመጠራት ከጥሪነት ባሻገር ምሥጢረ ሥላሴ የተገለጠበት ነው፡፡ በእርሱ መመረጥ ውስጥ የቅድስት ሥላሴ ልዩ አንድነትና ሦስትነት ተገልጧል፤ /ተመስክሯል/፡ ፡ የቅዱስ ጳውሎስ ወደ ክርስትና መመለስ ለ3 ዓመታት በዓረቢያ በረሃ ከቆየ በኋላ ወደ ደማስቆ ከተማ ተመለሰ፡፡ በዚያም በነበሩ አይሁድ መካከል በፊት ያሳድደው የነበረውነን ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ጀመረ፡፡ ከዚያ በፊት በፈሪሳዊነቱ ለአይሁድ ሕግ በነበረው ቅንዓት የሚታወቀው ጳውሎስ ዛሬ ወንጌል ሲሰብክ በማየታቸው አይሁድ ተነሡበት፡፡ በዚህም የተነሣ የደማስቆ ክርስቲያኖች በቅርጫት አውርደው ወደ ኢየሩሳሌም ላኩት፡፡ቅዱስ ጳውሎስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ የገጠመው ሁለት ችግር ነበር፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ወደ ክርስትና መመለስ ለ3 ዓመታት በዓረቢያ በረሃ ከቆየ በኋላ ወደ ደማስቆ ከተማ ተመለሰ፡፡ በዚያም በነበሩ አይሁድ መካከል በፊት ያሳድደው የነበረውነን ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ጀመረ፡፡ ከዚያ በፊት በፈሪሳዊነቱ ለአይሁድ ሕግ በነበረው ቅንዓት የሚታወቀው ጳውሎስ ዛሬ ወንጌል ሲሰብክ በማየታቸው አይሁድ ተነሡበት፡፡ በዚህም የተነሣ የደማስቆ ክርስቲያኖች በቅርጫት አውርደው ወደ ኢየሩሳሌም ላኩት፡፡ቅዱስ ጳውሎስ ኢየሩሳሌም ሲደርስ የገጠመው ሁለት ችግር ነበር፡፡ 1- አይሁድ ጳውሎስን እንደሚያውቁት እና እንደለመዱት ሆኖ ስላላገኙት ሊገድሉት ተነሡ፡፡ 2- ክርስቲያኖች የቅዱስ ጳውሎስን መመለስ ሊያምኑ አልቻሉም፡፡ በመጨረሻ ግን በርናባስ ወደ ሐዋርያት ዘንድ ወስዶ የጳውሎስን መመለስ በመተረክ እንዲያምኑት አደረጋቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎሰ በኢየሩሳሌም በድፍረት በማስተማሩ አይሁድ ስለተቃወሙት ከተማዋን ትቶ በቂሳርያ በኩል ወደ ትውልድ ሀገሩ ጠርሴስ ተመለሰ፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በጠርሴስ ከተማ ለዘጠኝ ዓመታት ቆይቷል፡፡ ከኢየሩሳሌም ውጭ የአሕዛብ ከተማ በነበረችው በአንጾኪያ የክርስትና ሃይማኖት ተስፋፋ፡፡ ከኢየሩሳሌም የተሰደዱት ክርስቲያኖች የአንጾኪያን ሕዝብ ተግተው በማስተማራቸው ዝናው እስከ ኢየሩሳሌም ደረሰ፡፡ በዚህም ምክንያት በኢየሩሳሌም የነበሩት ሐዋርያት በርናባስን ወደ አንጾኪያ ላኩት፡፡ በርናባስ የግሪክ ቋንቋ ችሎታ ያለውን፣ ከማንኛውም ሰው ጋር መግባባት የሚችለውን፣ ደግሞም እግዚአብሔር ለአሕዛብ ሐዋርያ እንዲሆን የመረጠውን ቅዱስ ጳውሎስን ከጠርሴስ በማምጣት በአንጾኪያ ሥራቸውን ጀመሩ፡፡ በገላትያ መልእክቱ ምዕራፍ 2 ላይ ራሱ እንደገለጠው ከአሥራ አራት ዓመት በኋላ ወደ ኢየሩሳሌም ከአንጾኪያ ክርስቲያኖች የሰበሰበውን ርዳታ ይዞ ወጣ፡፡ በዚህም በአይሁድ በአሕዛብ መካከል የነበረውን መለያየት ክርስትና አንድ እንዳደረገው አስመስክሮአል፡፡ የቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያዊ ሥራ የመጀመሪያው የቅዱስ ጳውሎስ ጉዞ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ከኢየሩሳሌም ወደ አንጾኪያ ከተመለሰ በኋላ በልዑል እግዚአብሔር ጥሪ (የሐዋ. 13.1-3) በአሕዛብ ሀገር ወንጌልን ለመስበክ ከበርናባስ ጋር ወጡ፡፡ በዚህ ጉዞቸው በጠቅላላ ወደ 2000 ኪ.ሜ የሚደርስ መንገድ በእግር ተጉዟል፡፡ ይህም ጉዞ የተከናወነው በ46 ዓ.ም አካባቢ ነው፡፡ የተሸፈኑትም ሀገሮች ሲሊንውቂያ፣ ቆጵሮስ፣ ስልማና፣ ጳፋ፣ ጰርጌን፣ ገላትያ፣ ጵስድያ፣ ኢቆንዮን፣ ሊቃኦንያ፣ ልስጥራ፣ ደርቤን፣ ጵንፍልያ፣ አታልያ እና አንጾኪያ ናቸው፡፡ ሁለተኛ የሐዋርያው የቅዱስ ጳውሎስ ጉዞ ሁለተኛው ጉዞ የተከናወው በ50 ዓ.ም ገደማ ነው፡፡ በመጀመሪያው ጉዞ ማርቆስ አብሮ ተጉዞ ነበር፡፡ ነገር ግን ጵንፍልያ ከተማ ሲደርስ እናቱ ስለናፈቀችው መመለስ በመፈለጉ በርናባስ ወደ ኢየሩሳሌም ይዞት መጣ፡፡ ስለዚህም በሁለተኛው ጉዞው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ሲላስን ይዞ ወደ ኪልቋያ ሶርያ ሲጓዝ በርናባስ ደግሞ ማርቆስን አስከትሎ ወደ ቆጵሮስ ሄደ፡፡ በዚህ ጉዞው ቅዱስ ጳውሎስ እስከ ግሪክ ደርሶአል፡፡ የተጓዘባቸውና ያስተማረባቸው ከተሞችም፡- ደርብያ፣ ልስጥራ፣ ፍርግያ፣ ገላትያ፣ ሚስያ፣ ጢሮአዳ፣ ሳሞትራቄ፣ ናፒሊ፣ ፊልጵስዩስ፣ ተሰሎንቄ፣ በርያ፣ አቴና፣ ቆሮን፣ ቶስ፣ አንክራኦስ፣ ኤፌሶን፣ ቂሳርያ፣ ኢየሩሳሌም እና አንጾኪያ ናቸው፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የመንፈስ ልጁ ጢሞቴዎስን ያገኘው በዚሁ ጉዞው በልስጥራ ከተማ ነው፡፡ ሦስተኛው የቅዱስ ጳውሎስ ጉዞ ይህ ጉዞ የተከናወነው በ54 ዓ.ም ሲሆን የተሸፈኑትም ሀገሮች የሚከተሉት ናቸው፡፡ ገላትያ፣ ፍርግያ፣ ኤፌሶን፣ መቄዶንያ፣ ፊልጵስዩስ፣ ቆሮንቶስ፣ ጢሮአዳ፣ አሶን፣ ሚሊጢኒን፣ አንጠቀከስዩ፣ ትሮጊሊዩም፣ መስጡ፣ ቆስ፣ ሩድ፣ ጳጥራ፣ ጢሮስ፣ ጵቶልማይስ፣ ቂሳርያ፣ ኢየሩሳሌም፡፡ ክርስቲያኖች የሰበሰበውን ዕርዳታ ለኢየሩሳሌም ቤተ ክርስቲያኖች በመያዝ ሦስተኛውን ጉዞ አጠናቅቆ ኢየሩሳሌም ገባ፡፡ ነገር ግን ኢየሩሳሌም የገባበት ጊዜ የፋሲካ በዓል ስለነበር ከልዩ ልዩ ሀገሮች የተሰበሰቡ አይሁድ በከተማዋ ነበሩ፡፡ እነዚህ በዝርወት የሚኖሩ አይሁድ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን በየሀገራቸው በትምህርቱ የተነሣ ሲቃወሙት የነበሩ ናቸው፡፡ እኒህ አይሁድ ቅዱስ ጳውሎስን በኢየሩሳሌም ሲያዩት ታላቅ ተቃውሞ አነሡበት፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም ተቃውሞአቸውን ለመግታት እንደ አይሁድ ሕግ በቤተ መቅደስ የመንጻት ሥርዓት መፈጸም ጀመረ፡፡ ነገር ግን ከኤፌሶን
Показати все...
አንተ እግሬን አታጥበኝም”አለው። በዚህ ጊዜ ፈጽሞ እንቢ ማለቱን ባየ ጊዜ “እውነት እውነት እልሃለሁ እኔ እግርህን ካላጠብሁህ፥ ከእኔ ጋር ዕድል ፋንታ የለህም”ብሎ መለሰለት። በዚህ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ሁሉን ትቶ የተከተለውን ጌታ ከማጣት የሚበልጥ ምንም ነገር እንደሌለ ስለሚያውቅ “አቤቱ፥ እንኪያስየምታጥበኝእጆቼንና ራሴንም እንጂ እግሮቼን ብቻ አይደለም አለው።ጌታችን ኢየሱስም፦ ፈጽሞ የታጠበ ከእግሩ በቀር ሊታጠብአያስፈልገውም፥ ሁለንተናው ንጹሕ ነውና፤እናንተማ ንጹሐን ናችሁ፥ ነገር ግን ሁላችሁ አይደላችሁም አለው።” /ዮሐ. ፲፫ ፥ ፩- ፲፩/። የቅዱስ ጴጥሮስ ንስሐ 7. ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በካህናት አለቆችና በአይሁድ ሽማግሌዎችተላልፎ የሚሰጥበትና መከራ የሚቀበልበት ሰዓት ሲደርስ ይህንን መራራእውነት ለደቀመዛሙርቱ ሲነገራቸው እጅግ ተረብሸው ነበር። ይባስ ብሎ ደግሞ በመጨረሻው ሰዓት ሁሉም ደቀ መዛሙርት እንደሚክዱትበነገራቸው ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ “ሌሎች ቢክዱህ እንኳን እኔ በፍጹም አልክድህም” አለው። ጌታችን እርሱ ባወቀ ዶሮሳ የጮህ ሦስት ጊዜ ትክደኛለህ ቢለውም እርሱ “በፍጹም” አለ። ነገር ግን አይሁድጌታችንንይዘው መከራ ሲያጸኑበት አይቶ እርሱን ያገኘ ያገኘኛል ብሎ “አንተ ከእርሱ ወገን ነህ” ሲሉት “በፍጹም አይደለሁም” እያለ መማል ጀመረ። ወዲያው ዶሮ ሲጮክ ጌታ የተናገረውን ቃል አስታውሶ በዚያችው ቃል“አላበጀሁም”በማለት በፍጹም ጸጸት ማንባት ጀመረ(ንስሓ ገባ) /ማቴ. ፳፮ ፥ ፳፱-ፍጻሜ/።ቅዱስ ጴጥሮስ ለጌታችን ካለው ፍቅርና ቀረቤታ ታሪኩ በቅዱስ ወንጌል በስፋትተገልጿል፤ሁሉንም ዘርዝሮ መጥቀስ ባይቻልም። ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችንበእውነት ከሙታን ተለይቶመነሣቱን መቃብሩን በማየት ያረጋገጠ፣ ጌታችንግልገሎቼን ጠቦቶቼንና በጎቼን ጠብቅ ብሎ እንደሾመው እርሱም ልክ እንደጌታው ለበጎቹ መልካም እረኛ በመሆን የታመነ፣ መንፈስቅዱስ ከወረደላቸው በኋላበመንፈስ ቅዱስ ታድሶ በአንድ ጊዜ ሦስት ሺህ ነፍሳትን አሳምኖያጠመቀ፣ ብዙተአምራትን በጌታችን ኃይል ያደረገ፣ የሐናንያንና የሰጲራን ድብቅ ሥራ በመንፈስ የመረመረ፣ በሰማርያ በኢዮጴና በልዳ ዞሮ ወንጌልን ያስተማረ፣ በመጨሻምበሮማወንጌልን ሲሰብክ በአደባባይ የቁልቁሊት ተሰቅሎ ፍጹም ጌታውን የመሰለ ታላቅ ሐዋርያ ነው። ቅዱስ ጴጥሮስ ስለ ክርስትና ሃይማኖት የአይሁድ መሪዎችንና ሊቃነ ካህናቱን ይሞግት፤ ከእነርሱም ፊትምስክርነት ይሰጥ ነበር፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ የአይሁድን ሊቃነ ካህናት «ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል» እያለ በሸንጎ ይሟገት ነበር፡፡ /የሐዋ.5.29/ በዚህም ብዙውን ጊዜ ይገረፍ ይታሰር ነበር ቅዱስ ጴጥሮስ እየተዘዋወረ ሲያስተምር በወንጌል የወለዳቸውን ክርስቲያኖች ከልዩ ልዩ ፈተናዎች ለማጽናት ሲል ሁለት መልእክታትን ጽፏል። የመጀመሪያመልእክቱን የጻፈውአይሁድ ለሚያሳድዷቸውና መከራ ለጸኑባቸው ከእስጢፋኖስ ሰማዕትነት በኋላ በስደትለተበተኑ ክርስቲያኖች ነው። ሁለተኛውን መልእክቱንየጻፈበት ምክንያት ደግሞ በወቅቱ የሮማ ግዛት መሪ የነበረው ኔሮን ቄሣር ክርስቲያኖች ሁሉ እየተያዙ እንዲፈረድባቸው አዋጅነግሮ ነበርና በዚሁ ምክንያት ለተጨነቁ በእስያ ላሉ ክርስቲያኖች ነው። ከዚህም በተጨማሪ ሐሰተኞች መምህራን ተነሥተው በሐሰተኛ ትምህርታቸው ስላስጨነቋቸው ለማጽናት ጽፎላቸዋል። ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም የወንጌል አርበኛ ሆኖ የቃለ እግዚአብሔርን ዝናር በወገቡ ታጥቆ ርኩሳን መናፍስትን በቃለ ወንጌል እያሳደደ ክርስትናን ባእድ አምልኮ ቀስፎ በያዛት በሮም ምድር እያስፋፋ ሳለ አንድ ያልታሰበ ነገር ተከሰተ፡፡ታላቋን የሮም ከተማ የፅልመት ሠራዊት ከቧታል በሰማይ ላይ የፈሰሱት ከዋክብት እርስ በእርሳቸው ከመጠቃቀስ በስተቀር ለከተማዋ ብርሃናቸውን በመለገስ ጨለማውን በመጠኑም አላስወገዱላትም፡፡ ሞቃቱ የምሽት ነፋስ የሮም ከተማን ይዞራል።የሮም ከተማ እሳት ቃጠሎ ከመሃል ከተማው የፈነጠቀው ውጋገን በአንድ ጊዜ እንደ ሞት ከብዶ የነበረውን ጨለማ ገፎ ከተማዋን በብርሃን ጎርፍ እንድትጥለቀለቅ አደረገ ፡፡ የእሳቱ ነበልባል እየተጎረደ፣ እየተጎረደ ግዛቱን ያሰፋል የእሳቱ ቃጠሎ መላ የሮም ከተማን ባጭር ጊዜ አጥለቀለቃት ፡፡ ከተማዋ በእሳት ባህር ተከበበች፡፡ ታላላቅ ቤቶች የእሳት ራት ሆኑ፡፡ ቤተ መቅደሶቹ ፈራረሱ ሱቆች በውስጣቸው ከያዙት ዕቃ ጋር አመድ ሆኑ፡፡ ነገር ግን የእሳቱን አደጋ በቁጥጥር ሥር ማዋል አልተቻለም፡፡ አንድ ጊዜ ፎክሮ የመጣ ይመስል የነበረውን እንዳልነበር አድርጎ አፍርሶና አወዳድሞ ከስድስት ቀን በኋላ ፀጥ ረጭ አለ፡፡ የሮም ከተማ ሕዝብ የብርቅየ ከተማውን አሳዛኝ ፍፃሜ በሐዘን ተውጦ ተመለከተው ፡፡ ከበርቴዎች ባዶ እጃቸውን አጨብጭበው ቀሩ ፡፡ ብዙ የሮሜ ሰዎች ቤት አልባ ሆኑ፡፡ የእሳት ቃጠሎው መንስዔ ምን እንደሆነ በውል ባይታወቅም የሮም ሕዝብ ግን በይሆናል ማውራት የጀመረው ወዲያውኑ ነበር ፡፡ በስፋት ይወራ የነበረው የእሳት አደጋ በተነሳበት ወቅት ኔሮን ቄሳር በቤተ መንግስቱ ሠገነት ላይ የተዋናይ ልብስ ለብሶ በገናውን እየደረደረ ሲዘፍን ታይቷል የሚለው ሲሆን በዚህም በእሳቱ ቃጠሎ የኔሮን እጅ አለበት እየተባለ ስለተወራም ምንም እንኳን ኔሮን በዚያ ምሽት ከሮም ከተማ ብዙ ርቆ በሚገኘው ባማረ ቤተ መንግስቱ የነበር ቢሆንም ይህን የሕዝቡን ሐሜት ለማስለወጥ ዘዴ ያውጠነጥን ጀመር፡፡ ኔሮን ቄሣር የእሳቱን ቃጠሎም በሚጠላቸው ክርስቲያኖች ላይ አሳበበ አማልክቶች በክርስቲያኖች ሥራ ስላልተደሰቱ በቁጣ ሮምን ኣቃጠሏት ብሎ አስወራ፡፡ ይህንንም ለሕዝቡ እንዲሠራጭ አደረገ፡፡ በዚህ የተነሣ ብዙ ክርስቲያኖች ከያሉበት ታድነው በአሠቃቂ ሁኔታ መሥዋዕት ሆኑ ፡፡የኔሮን ቄሣር የቅርብ ባልንጀሮች የሆኑት የአልቢኖስና አግሪጳ ሚስቶች በቅዱስ ጴጥሮስ ስብከት ተማርከው ክርስቲያን ሆነው ስለነበር ባሎቻቸው በእርሱ ላይ የሸረቡበትን ሤራ ሄደው በመንገር ከሀገር እንዲወጣ ቅዱስ ጴጥሮስን ግድ አሉት፡፡ እርሱም ለክርስቶስ ታማኝ ወታደር ሆኖ በወንጌል ተጋድሎው ጸንቶ በሰማዕትነት ማለፍ እንዳለበት ቢነገራቸውም እነርሱ ግን ስለ እነርሱና ስለሌሎች ክርስቲያኖች ሲል ለጥቂት ጊዜ በሕይወት መኖሩ ለወንጌል አገልግሎት እንደሚጠቅም ገልጸውለት መሸሹ አማራጭ የሌለው መሆኑን በማሰብ ከሮም ከተማ ወጥቶ ሲሄድ በሮም መግቢያ መውጫ በር ወደ እሱ እየተራመደ የሚመጣ ሰው አየ፡፡ ያም ስው ወደ ሮም ቅጥር እየተጠጋ መጣ፡፡ ለካስ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ኑሮአል፡፡ ጴጥሮስም ደንግጦ ጌታዬ ወዴት ነው የምትሄደው? ብሎ ጠየቀው ጌታም ጴጥሮስ፣ ዳግመኛ በሮም ልሰቀል መሄዴ ነው ብሎ መለሰለት፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም የራእዩ ምስጢር ስለገባው ወደ ሮም ከተማ ተመልሶ ድምፁን ከፍ አድርጎ ስለተሰቀለው ጌታ ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ማስተማር ጀመረ ኔሮን ቄሣርም ወደ አካይያ ዘምቶ ነበርና በዘመቻው ድል አድርጎና ደስ ብሎት ወደ ሮሜ ሲመለስ አረማውያን የሆኑ መኳንንቱን ደስ ለማሰኘትና አማልክቱን ለማክበር ሲል በቅ.ጴጥሮስና በሌሎች ክርስቲያኖች ሁሉ የሞት ፍርድ ፈረደባቸው የቅዱስ ጴጥሮስንም ሞት በመስቀል እንዲሆን አዘዘ ቅዱስ ጴጥሮስ በመስቀል ተሰቅሎ እንዲሞት መፈረዱን በሰማ ጊዜ ጌታችን፡- “በሸመገልህ ጊዜ እጆችህን ትዘረጋለህ፤ ሌላውም ያስታጥቅሃል ወደማትወደውም ይወስድሃል” ያለውን ቃል /ዮሐ.21፡18/ ትዝ አለውና “አላውቀውም ብዬ መካዴን ሳያስብብኝ በዚህ ፍጹም ይቅርታ ያደርግልኛል” በማለት እጅግ ደስ አለው፡፡ የሚሰቀልበትም ሰዓት በደረሰ ጊዜ ከኔሮን ቄሣር የታዘዙ አራት
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.