cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Lij_Abel ኦርቶዶክሳዊ

የልዑል እግዚአብሔር፣ የቅድስት ድንግል ማርያም ወዳጅ፣ በቅዱሳን ተራዳይነት ያደኩ እኔ የተዋህዶ ልጅ ነኝ:: ሙዚቃ አልሰማም፣ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙር ብቻ እዘምራለሁ !! - ሥርዓተ ቅዳሴ - ስብከት - መዝሙር ጥናት - መፅሐፍ - ገዳማት ይዳሰሱበታል!! እግዚአብሔር ይመስገን:: ሀሳብ አስተያየት በ @abelbeen ማካፈል ይሻላል ።

Більше
Рекламні дописи
1 889
Підписники
-1024 години
+1157 днів
+40230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

⌨ ✅ #ሥላሴ_መታመኛዬ ✅#ዘማሪ_ቀሲስ_ምንዳዬ_ብርሃኑ #ሥላሴ  #Lij_Abel ✍️✍️✍️✍️✍️ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Показати все...
ሥላሴ_መታመኛዬ_ዘማሪ_ቀሲስ_ምንዳዬ_ብርሃኑ.m4a5.79 MB
6🙏 6👌 2
ሐምሌ 7/2016 #አጋእዝተ_ዓለም_ቅድስት_ሥላሴ 👉በስመ #አብ_ወወልድ_ወመንፈስ_ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን በአንድነት በሦስትነት ለሚመለኩ #ለቅድስት_ሥላሴ በአብርሃም ቤት ተገኝተዉ #አንድነታቸዉን_ሦስትነታቸዉን ለገለፁበት አመታዊ ክብረ በአል እንኳን አደረሰን 👉 #ሥላሴን ቅድስት ሥላሴ እያልን የመጥራታችን ምስጢር ምንድን ነው 👉 አንዲት ሴት ወይም እናት ልጆቿን አልወለደችም ተብላ አትጠረጠርም ሥላሴም ይህንን ዓለም ፈጥረዋል እናም አልፈጠሩም ተብለው አይጠረጠሩም 👉አንዲት ሴት በባሕሪይዋ ልጅን ታስገኛለች #ሥላሴም ይህንን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥተው ስለፈጠሩት በሴት አንፃር #ቅድስት ተብለው ይጠራሉ 👉አንድም ሴት አዛኝ ናት ለታናሹም ይሁን ለታላቁ ትራራለች #ሥላሴም እንደዚሁ ለፍጥረት ሁሉ ያዝናሉ ፥ ይራራሉ ፥ ምህረት ይሰጣሉ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ እንዲህ ይላል 👉ምህረታችሁ ከልክም በላይ የበዛ በሴት አንቀፅ #ቅድስት ተብላችሁ የተጠራችሁ #ሥላሴ በማለት ያመሰጥራል ስለዚህ ቅድስት ለምን ተባሉ ቢባል በረከታቸው ፥ ርህራሄያቸውና፥ ይቅር ባይነታቸው መሆኑን ማወቅ አለብን 👉አንድም ሴት ልጇ ቢታመምባት አትወድም #ሥላሴም አንድም ልጅ በዲያብሎስ እጅ ተይዞ በኃጢአት እንዲታመም አይወዱም ፥ አይፈቅዱም በመሆኑም ቅድስት ይባላሉ 👉አንድም ሴት ልጅ የልጇን ነውር አትጠየፍም ልጄ ቆሽሿል ፥ ተበላሽቷል ብላ ፊቷን አታዞርም #ሥላሴም የሰውን በኃጢአት መቆሸሽ ሳይፀየፉ በቸርነታቸው ጎብኝተው #ለንስሐ ያደርሱታል 👉ይህንን የፅድቅ አየር የምንምገው ያማረውንም ብርሃን የለበስነው ስለ ፅድቃችን ሳይሆን #በሥላሴ_ቸርነት ነውና ስለዚህም ሥላሴን በሴት አንቀፅ ቅድስት እንላቸዋለን 👉አንድም ሴት ልጆቿን ፈጭታና ጋግራ ትመግባቸዋለች #ሥላሴም እንደዛው ናቸው በዝናብ አብቅለው በፀሐይ አብሥለው ፍጥረታትን ሁሉ ይመግባሉ ስለዚህ #ሥላሴ እንደ እናት ሁሉንም ይመግባሉና በሴት አንቀጽ ቅድስት ይባላሉ 👉በአብርሃም ቤት ተገኝተዉ በረከታቸዉን ያሣደሩ ቅድስት #ሥላሴ ለሁላችንም በረከታቸዉን ያድሉን የተባረከ የተቀደሰ #ሰንበተ_ክርስቲያን ይሁንልን "አሜን"✝️ 💒 ✝️
Показати все...
🙏 6👏 5👌 3 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
1👌 1😍 1
ጾምና ጾም ፍቺ ✝️ አንዳንድ ገጾች ላይ ለጾም ፍቺ ሥጋ ልንበላ ቀናት ቀሩን ብለው ሲለጥፉ አሜን ሲባልም አይተን ታዘብን ✝️ እውን የጾም ፍቺ ሰዓት ሥጋ ለመብላት የምንጓጓበት ነውን? ✝️ የጾምስ ዓላማ ሥጋን ከቅባት፣ ከእንስሳት ተዋጾኦ ለተወሰነ ጊዜ አርቆ ያንን ለማግኘት መጓጓት፣ መቸኮል ነውን? ❤ የጾም ዓላማ ምንድን ነው? ጾም አንድ ሰው ሐጢያቱን ለማስተሰረይ፣ ዋጋውን ለማብዛት እርሱ ወዶ ፈቅዶ ሕግን ለሠራለት እየታዘዘ የፈቲውን ኃይል ያደክም ዘንድ ሥጋን ለነባቢት ነፍስ ትታዘዝ ዘንድ ማዘጋጀት፣ ማብቃት ነው። ፍት. ነገ. አንቀጽ ፲፭፥፭፻፷፬ /15፥564/ ➻ ጾም ከክፉ ሐሳብ ከክፉ ሥራ ማሰብም መራቅም ነው ➻ ጾም ከመንፈሳዊ ተጋድሎዎች አንዱ ነው ➻ ጾም ለፈቃደ ስጋ መንፈሳዊ ልጓም ነው ➻ ጾም ሰው ፈቃደ ስጋውን እየገታ ነፍሱን የሚያለመልምበት ስንቅ ነው ➻ ጾም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ፣ ኃይለ ፍትወትን የምታደክም፣ የበጎ ምግባራት ሁሉ መጀመሪያ ናት ❤ ስለዚህም መንፈሳዊውን፣ ሰማያዊ ሐብት ለማግኘት እንጓጓ እንጂ ለዓለማዊው፣ ለሚጠፋው መብል፣ መጠጥ መጓጓት አላማችን አይሁን አምላካችን የቀረውን የጾም ጊዜ የተባረከ ያርግልን። በቸርነቱ ይጠብቀን። 🔹🔹🔹🔹🔹🔹
Показати все...
7🙏 6👌 2
ፃድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በተወለዱበት ቤት አልኖሩምና እናት አባታቸው የሥጋ ዘመዶቻቸውም አላወቋቸውም፡፡ በበረሃ ብቻቸውን ኖሩ እንጂ፡፡ ነገር ግን ሰማያውያን ሁሉ ወዳጆቻቸው ሆኑ፤ እመቤታችን ወዳጄ ትላቸዋለች፡፡ ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ወገናችን ይሏቸዋል፡፡ መላእክትም ወዳጃችን እያሉ በክንፋቸው ያቅፏቸዋል፡፡ የአባታችን መዓዛቸው ጫካውን ይሞላው ነበር፡፡ በመንፈስ ቅዱስም ኃይል ወደፈለጉት ቦታ በፍጥነት እንደወፍ ይበራሉ፡፡ ስለተሰጣቸውም ጸጋ የበረሃ እንስሳት (አንበሳና ነብር)  ሁሉ ያገለግሏቸዋል፡፡ አባታችን ሁልጊዜ እንዲህ ይሉ ነበር፡-  
‹‹የሚጣፍጥ ምግብን መውደድ ኃጢአትን ያመጣል፣ ሞትን ያስከትላል፡፡ ክንፍ ያላቸው የሰማይ ወፎች እንኳን በመብል ምክንያት ይጠመዳሉ፣ ምግብ በመሻት ከምድር ላይ ይወድቃሉ በወጥመድም ይያዛሉ፡፡ የሰው ልጅም ምግብን በመውደድ በኃጢአት ይወድቃልና እኔስ ለሰውነቴ ምግብ መጠጥን አልፈልግም፤ ልብስም አልሻም ዕራቁቴን ከእናቴ ማኅፀን እንደወጣሁ እንዲሁ ዕረቁቴን ወደ መቃብር እመለሳለሁ እንጂ፡፡ ከዚህ ከኃላፊው ዓለም በሞት በተለየሁ ጊዜ መብል መጠጥንና ልብስን ማን ያስከትልልኛል?›› 
አሉ፡፡ ዳግመኛም ‹‹ሰው ሊደርስ በማይችልበት በረሃ እኖራለሁ፣ ነጣቂ ተኩላዎችና አራዊቶች ባሉበት እነርሱ እንዲበሉኝ ሥጋዬን እጥላለሁ፤ ዳዊት በመዝሙር 
‹‹የጻድቃን ሥጋቸው ለዱር አራዊት ነው››
 እንዳለ እኔ
ክፉ አውሬዎች፣ ተናዳፊ እባቦችና ዘንዶዎች ወዳሉበት እገባለሁ ምግብም እሆናቸው ዘንድ እወዳለሁ››
 በማለት አባታችን ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው ይሰጡ ነበር ነገር ግን አራዊቱ ሁሉ እየሰገዱላቸው ይገዙላቸው ከእግራቸውም በታች ይተኙ ነበር፡፡ እንደሚታዘዝ ደቀ መዝሙርም ይታዙላቸው ነበር፤ ለጸሎትም በሚቆሙበት ጊዜ አብረዋቸው ይቆማሉ፡፡ በፊታቸውም ይጫወታሉ፡፡ በአንደኛው ዕለት አባታችን ጸሎታቸውን እንደጨረሱ ሰማይ ተከፍቶ የእሳት ድንኳን ተገልጦ አርባእቱ እንስሳ የእግዚአብሔርን ዙፋን ተሸክመው ፳፬ቱ ካህናተ ሰማይ ማዕጠንት ይዘው፣ ቅዱሳን መላእክትና አለቆቻቸው በየነገዳቸው በዙሪያው ቆመው ጌታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአንድነት በሦስትነት እንዳለ ተገለጠላቸው፡፡ አባታችንም ይህንን ባዩ ጊዜ እጅግ ፈርተውና ደንግጠው መሬት ላይ ወደቁ፡፡ ጌታችንም ካጸናቸውና ካበረታቸው በኋላ ‹‹ዮሐንስ ቀለምሲስ እኔን እንዳየኝ አንተም እኔን ማየት የምትችልበትን ኃይል እሰጥሃለሁ፤ ወዳጄ ሆይ ምን ትሻለህ? የምትጠይቀኝስ ነገር ምንድነው? ልይህ ብለህ በለመንከኝ ጊዜ ተገልጥኩልህ፡፡ ሰማንያ ዓመት በጫካ ኖርክ፤ በረሃዎችን ዞርክ፤ ከአንበሶችና ነብሮች ከአራዊትም ጋር መኖርን አልፈራህም፤ ጨክነህ እስከ ሞት ድረስ ታገሥህ፡፡ የመረጥኩህ ወዳጄ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! ምን አደርግልህ ዘንድ ትወዳለህ?›› አላቸው፡፡ አባታችንም ይህንን ቃል ከጌታችን ሲሰሙ 
‹‹አምላኬ ሆይ ይህን ልታደርግልኝ አይገባኝም፡፡ በፊትህስ ሞገስን ካገኘሁ የገቦታን ሰዎች ማርልኝ፤ እነርሱ ኃጥአን ናቸውና አንተ ንስሓን ለማይሹ ጻድቃን አልመጣህምና ኃጥአንን ወደ ንስሓ ልትመልስ ነው እንጂ›› አሉት፡፡ ዳግመኛም ‹‹አቤቱ እንደ ክረምት ውኃ እንባቸውን እያፈሰሱ ጥርሳቸውን እያፋጩ በደይን የሚኖሩትን አስባቸው፤ ሰይጣን አስቷቸዋልና፤ በማወቅ ባለማወቅ በሠሩት ማራቸው፤ ይቅር በላቸው›› እያሉ ለመኑት፡፡ ጌታችንም ‹‹ወዳጄ ሆይ የለመንከኝን አልከለክልህም፣ እንደቸርነቴም ስምህን የጠሩትን መታሰቢያህን ያደረጉትን ኃጥአንን ምሬልሃለሁ፤ የለመንከኝንም ሁሉ አደርግልህ ዘንድ ቃል ኪዳንን ሰጥቼሃለሁ›› 
አላቸው፡፡ አባታችንም እጅግ ደስ ብሏቸው በግንባራቸው መሬት ላይ ወድቀው ጌታችንን ሲያመሰግኑት ቅዱሳን መላአክትና ሰማያውያን ቅዱሳን ሁሉም አብረው ተደስተው እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡
Показати все...
🙏 12👏 4😍 3👌 2
✅ #የእምነትሽ_ፅናት ➡️ #ዘማሪት_ሲስተር_ሊድያ
@LijAbelOrthodoxawibot ይጋብዙ።
#Mezmur #መዝሙር #ቅድስት_አርሴማ ✅✅✅✅✅ ✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
Показати все...
ዘማሪት_ሲስተር_ልድያ_New_Ethiopian_Orthodox_Mezmur_2022.m4a5.67 MB
9🙏 6😍 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሐምሌ ፮ እንኳን አደረሰን አደረሳችሁ ለቅድስት አርሴማ በዓል በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን።
Показати все...
🙏 13 10👌 3
00:30
Відео недоступнеДивитись в Telegram
ይሄን ማለፍ አልቻልኩም❤
Показати все...
6.89 MB
22🙏 8🥰 3👌 2👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ከፀድቁ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስዕለ አድኖ ስር ነብር እና አንበሳ ይታያል። ለመሆኑ ትርጉሙ ምንድነው ? እያሰላሰላችሁ እደሩ። ነገ ትንሽ ፅሁፍ ለማስቀመጥ እሞክረሰለሁ፣ እግዚአብሔር ይርዳን🙏🙏 መልካም አዳር
Показати все...
🙏 11 6🤔 6👌 2🥰 1
🔹🔹🔹🔹🔹 ፆመ ሐዋርያት ዛሬ ተፈፀመ። ፆም ፀሎታችንን እግዚአብሔር ይቀበለን። አሜን🙏🙏
የምንናፍቃት ፆመ ፍልሰታ ነሐሴ ፩ ትጀምራለች።
Показати все...
13🙏 7👌 3👏 2
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.