cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት

ሥነ ጽሑፍና፡ ንባብን ለማዳበር በማሰብ የሚዘጋጅ ዓመታዊ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ነው።

Більше
Рекламні дописи
714
Підписники
Немає даних24 години
-57 днів
-830 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
የሆሄ ሥነ ጽሑፍ ሽልማት፡ በረጅም ልብወለድ ዘርፍ ሁለት ግዜ የዓመቱ ምርጥ መጽሐፍ አሸናፊ ዓለማየሁ ገላጋይ በአዲስ መጽሐፍ እየመጣ ነው። #Ethiopia
Показати все...
👍 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የኢትዮጵያ ቡክ ፎረም ወዳጆች አዲስ የሕዝብ ቤተ-መጻሕፍት በማደራጀት ላይ ይገኛሉ። ለዚህም ቤተ-መጻሕፍት የመጽሐፍ ማሰባሰብ ሥራ እየሠራን እንገኛለን። ተያያዥ ዝርዝሮችን ከታች የምናስቀምጥላችሁ ሲሆን የመጻሕፍት እና ሌሎችም ድጋፎች ማድረግ የምትችሉ  @TheDawit እና @Ahmedteyib98 ላይ አግኙን። በጊዜያዊነት ለመጻሕፍት መሰብሰቢያ ያሰብናቸው ቦታዎች: 1. ሜክሲኮ - ቡና እና ሻይ ባለሥልጣን ሕንጻ ምድር ቤት የሚገኘው ፊሊ ኮፊ 2. መስቀል አደባባይ - እስጢፋኖስ ቤተ-ክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ከቤት እስከ ከተማ፤ የከተማ ማዕከል ቤተ-መጻሕፍቱ ምን ሊመስል እንደሚችል ለመረዳት ትችሉ ዘንድ: ቦታ: ሜክሲኮ አደባባይ፣ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ሕንጻ ምድር ቤት የሚገኘው ፊሊ ቡና አባላት ለመመዝገብ ሁለት መጻሕፍት ማበርከት ይኖርባቸዋል። እነዚህ መጻሕፍት ያሉንን የመጻሕፍት ስብስብ ለማብዛት እንዲሁም ለአባላትም በዋስትናነት ያገለግላሉ። (ያው ከሁለት መጻሕፍት በላይ እንሰጣለን ካላችሁም እምቢ አንልም።) የቤተ-መጻሕፍቱ አሠራር - የአባልነት መታወቂያ የምናዘጋጅ ሲሆን፤ አባላት መጽሐፍ በሚዋሱበት ጊዜ ከመጽሐፉ ጋር ባለው ኪስ ውስጥ መታወቂያቸውን ያስቀምጣሉ። ሌላ አዲስ መጽሐፍ ለመዋስ የሚፈልጉ አባላት በቅድሚያ የተዋሱትን መጽሐፍ መመለስ ይኖርባቸዋል።
Показати все...
👏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
መጋቤ ሀዲስ እሸቱ አለማየሁ በሰዋሰው ብርሀን መንፈሳዊ ኮሌጅ የሀዲስ ኪዳን አንድምታ መምህር ናቸው፡፡ የብሉይ ፣ የቅኔ እና ሌሎች የቤተክርስቲያን ትምህርቶችንም ያስተምራሉ፡፡በተለያዩ መድረኮች ተገኝተው ስለአብሮነት፣ ስለኢትዮጵያዊነት፣ ስለባህል እና ታሪክ በሚሰጧቸው ገለፃዎች የብዙዎችን ልብ መማረክ ችለዋል፡፡ ትውልዱ ለንባብ ቅድሚያ በመስጠት የሌሎች መጠቀሚያ ከመሆን መዳን አለበት የሚሉት መምህሩ ‹‹ያነበበ ሰው ያልተጣራ ሀሳብ ሌላ ሰው ላይ አይጭንም፡፡ እሱም ላይ ያልተጣራ ሀሳብ አይጫንበትም፡፡ አዕምሮውን ሲያስፈልግ እንጂ የሚከፍተው ለትንኝም ለበረሮም አዕምሮውን አይከፍትም ›› ሲሉ ይናገራሉ፡፡ ‹‹ትውልዱ ያነባል ብዬ እገምትና በሌላ በኩል ደግሞ እንዴት ነው ማንም እየመጣ የሀሳብ መስጫ ሳጥን ያደረገው ብዬ እደነግጣለሁ፡፡ እናም ንባብ የአዕምሮ ወርሀው አስቤዛ ነው እላለሁ፡፡ የነፍስ ቀለብ የህሊና ደመወዝ ነው እላለሁ፡፡ እርቃን ነፍስ ይርባታል፣ ይጠማታል፣ ይበርዳታል፡፡ ስለዚህ ቀለቧ፣ መጠጧ ልብሷ መፅሀፍ ንባብ ነው ፡፡ የተራበች ፣የተጠማች እና የተራቆተች ነፍስ ይዞ ከመንቀሳቀስ ማንበብ ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ ›› ሲሉ ያክላሉ፡፡ ያለሁበት ሙያ የቤተክርስቲያን ሙያ እንደመሆኑ ሀዲስ ኪዳን ለማስተማር ተዛማጅ መፅሀፍት አሉ፡፡ ብሉይ ኪዳን ፣ መፅሀፍተ ሊቃውንት፣ መፅሀፈ መነኮሳት የሚባሉ አሉ፡፡ እነዚህ በመጀመሪያው መስመር የማነባቸው ናቸው፡፡ ሁለተኛው ፡- በየዘመኑ የተነሱ ገድላት ፣ ድርሳናት እና ተአምራትን አነባለሁ፡፡ ሶስተኛ፡- በዘመናችን የተፃፉ መፅሀፍትን አነባለሁ፡፡ አራተኛ፡- ፍልስፍና ፣ታሪክ እና አለም ላይ ያሉ የተለያዩ መፅሀፍትን አነባለሁ አምስተኛ፡- ጋዜጦች መፅሄቶች እና በራሪ ወረቀቶችን አነባለሁ፡፡ ስለዚህ ንባብ ያለፈ ትዝታችንን የምንገመግምበት፤ የነገ አለኝታችንን የምናልምበት፤ የዛሬ ተግባራችንን የምንፈፅምበት፤ የህሊና እርካታ ፤የአዕምሮ እረፍት የምናገኝበት መንገድ ነው፡፡ በመሆኑም የኔ የምንግዜም ምርጥ መፅሀፍ መፅሀፍ ቅዱስ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር ምርጥ ናቸው የምላቸውና ያላነበባቸው ሰው እንዲያነባቸው ምርጫዎቼ የሚከተሉት ናቸው • ፍኖተ አዕምሮ - ራስ ካሳ ሀይሉ • የሀያኛው ክፍለዘመን ትዝታዬ - መርስኤ ሀዘን ወ/ቂርቆስ • ሰበዝ እና ችቦ - ዶ/ር አለማየሁ ዋሴ • የሻሞላ ትውልድ - ፋሲካ ሲደልል
Показати все...
👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ረዳት ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን (ሰዓሊ፣ ቀራጺ እና ገጣሚ) በቀለ መኮንን (ረዳት ፕሮፌሰር) የብዙ ሙያዎች ባለቤት ነው፡፡ ሰዓሊ፣ ቀራጺ እና ገጣሚ፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ ፈለገሰላም የሥነ ጥበባት ትምህር ቤት በረዳት ፕሮፌሰርነት እያስተማረ የሚገኘው በቀለ መኮንን ለተሻለ ነገ እናንብብ የ100 ቀናት ንባብ ዘመቻን ምክንያት በማድረግ የንባብ ልምዱን አካፍሎናል፡፡ ‹‹እኔ ቀበኛ አንባቢ የምባል ሰው ዓይነት አይደለሁም፡፡ ሁሉን ነገር ማንበብ ብወድም ንባቤ ውስንነት አለው፡፡ በአብዛኛው የሥነ ጥበብ፣ የሙያ የሆኑ መጻሕፍን ነው የማነበው፡፡ በርግጥ ሌሎችንም አነባለሁ፡፡» ብሏል። ''የኔ የምንጊዜም ምርጥ ሦስት መጻሕፍት'' ያላቸውን አስተዋውቋል። ደማሙ ብዕረኛ፡ መንግሥቱ ለማ The Feature of Knowledge & Culture: Edited By Vinay lal & Ashis Nandy Art & Physics: Leonard Shlain
Показати все...
👏 1
#የ100ቀናትየንባብዘመቻ
Показати все...
3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በአምባሳደር በቀለ እንደሻው፡ በቀኃሥ ዘመነ መንግስት የንግድ ሚኒስቴር የነበሩ “ሕይወቴና የአገልግሎት ትዝታዬ” በሚል ያዘጋጁት መጽሐፍ፡ ቅዳሜ መጋቢት 7 2016 ዓ.ም. በአአዩ ራስ መኮንን አዳራሽ 4 ሰዓት ላይ ይመረቃል። ሁላችሁም ተጋብዛችኋል። የ1966ቱ አብዮት 50 ዓመት በሚዘከርበት ግዜ፡ ለነበረው ለውጥ መነሻ ከሆኑ ነገሮች አንዱ በነዳጅ ዋጋ ላይ የተደረገው የ10 ሳንቲም ጭማሪ እንደነበረ ይታወሳል። በግዜው የንግድ ሚኒስቴር የነበሩት አምባሳደር በቀለ እንደሻው ስለሁኔታው ይነግሩናል።
Показати все...
👍 2 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#ነገረ_መጻሕፍት - ፲፰ ሁላችሁም በነጻ ተጋብዛችኋል! የካቲት 16 2016 ዓ.ም. ቅዳሜ: ከ8:00 - 10:30 ቆይታ:- ከብ/ጄ ካሳዬ ጨመዳ ጋር ርዕሰ ጉዳይ፡-  የጦር ሜዳ ውሎዎች ሲቃ አወያይ:-  እንዳለጌታ ከበደ። አዘጋጅ:- ዛጎል የመጻሕፍት ባንክ። አስተባባሪ ፦ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል የዝግጅቱ ቦታ:- በኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የብላቴን ጌታ ኅሩይ ወልደ ሥላሴ የሥነጥበባት ማዕከል፡፡ ከቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል አካባቢ (በንግድ ባንክ ጉለሌ ቅርንጫፍ በኩል ገባ ብሎ)፡፡ https://maps.app.goo.gl/yb1LFT7PDTwLUP217 ለበለጠ መረጃ እና መገኘትዎን ለማረጋገጥ የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡፡ https://t.me/+VZQIhKm-NoAwYjM0 ቦታውን ለማያውቁ እና የትራንስፖርት  አገልግሎት ለሚሹ አቡነ ጴጥሮስ አደባባይ አወልያ ት/ት ቤት አጠገብ ከ7:30-7:50 ጠብቆ የሚነሳ ትራንስፖርት ተዘጋጅቷል። በሰአቱ በመገኘት ነጻ የትራንስፖርት አገልግሎቱን ለመጠቀም +251 91044 2989 ላይ ይደውሉ። በራሳችሁ ለምትመጡ አድራሻው Ethiopian Academy of Sciences https://maps.app.goo.gl/GwKfjcwg1jmqsfG76 🔴 ያለፋችሁን ዝግጅቶች ለመከታተል   https://youtube.com/@endalegetamultimedia?si=hEO0egZkKPtR1mv0 ቴሌግራም:-  https://t.me/ZagolBookBank1     https://t.me/zagolbookbank እንዲሁም 0900651010 ወይም 0777664020 (ሳፋሪ) ይደውሉ፡፡
Показати все...
1
አንድ መቶ ዓመት የሞላው የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የህፃናት መጽሐፍ መታሰቢያ ዝግጅት ተካሄደ በ1916 ዓ.ም የታተመው የመጀመሪያው “የፍቅር መላክት ለኢትዮጵያ ልጆች” በሚል ርዕስ በብላታ በቀለ ሀብተማርያም የተጻፈው የልጆች መጽሐፍ 100ኛ ዓመት መታሰቢያ ዝግጅት ዛሬ የካቲት 14 2016 ዓ.ም በኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት (መወዘክር) ተካሄደ ። በዝግጅቱም ላይ የህፃናት መጻሕፍት ላይ ረጅም ዓመታት የሰሩ ባለሞያዎችን የምስጋና እና እውቅና የመስጠት ሥነሥርዓት ተካሄዷል። ጥቅምት 6 ቀን 1916 ዓ.ም በብላታ በቀለ ሀብተሚካኤል የተፃፈችው «የፍቅር መላዕክት›› ለኢትዮጵያ ልጆች “የተሰኘችው የልጆች መጸሐፍ ዘንድሮ መቶ ዓመት ሞልቷታል፡፡ ይህ የመታሰቢያ መርሐግብር ሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ከኢትዮዽያ ሪድስ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ነው። "ሆሄ የስነ-ጽሑፍ ሽልማት" በሀገራችን ኢትዮጵያ የንባብ ባህል እንዲጎለብትና የድርስት ፈጠራ ሥራዎች እንዲበረታቱ ለማድረግ በየዓመቱ የሚዘጋጅ የስነ-ጽሑፍ ሽልማት እና የእውቅና መስጫ ነው፡፡ በ2009 ዓ.ም የተቋቋመው ሆሄ የስነ-ጽሑፍ ሽልማት እስከአሁን ድረስ አራት ጊዜ ዓመታዊ የሽልማትና የዕውቅና ዝግጅት አሰናድቷል፡፡ ፎቶ: ተክሌ ማርኮን Website:https://eventaddis.com/ Telegram: https://t.me/EventAddis1
Показати все...
👍 2