cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ተውሂድ የመልዕክተኞች ሁሉ ጥሪ

منهاج السلف منهاج الحق والنجة في الدنية والأخرة

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
182
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

📮ዓቂደቱል አህሊ ሱናቲ ወልጀማዓሕ 4️⃣4️⃣ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ኬሚሴ (አቡ ጁወይሪያ) ➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/1696 📮አቂደቱ ሰለፍ አዓስሓቡል ሓዲስ 4️⃣5️⃣ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ኬሚሴ (አቡ ጁወይሪያ) ➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/1714 📮 ስላሰቱል ኡሱል 4️⃣6️⃣ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ኬሚሴ (አቡ ጁወይሪያ ➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/1764 📮ፈትሁ ረቡል በሪያ ቢተልኺሲል ሃመዊያ (ተልኺስ) 4️⃣7️⃣ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ኬሚሴ (አቡ ጁወይሪያ ➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/1790 📮 ኪታቡ ተውሒድ ሙሓመድ አብዱል ወሓብ 4️⃣8️⃣ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ኬሚሴ (አቡ ጁወይሪያ) ➴➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/1879 📮 ሸርህ አቂደቱል ዋሲጢያ ሊል ኻሊል ኻራስ 4️⃣9️⃣ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ኬሚሴ ➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/1958 📮 ሸርሑ መንዙመቱል ሓኢያ ሊሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን " 5️⃣0️⃣ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ኬሚሴ ➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/2145 📮አል ኡሱል ሚን ኢልመል ኡሱል ሸይኽ ሷሊህ አል ኡሰይሚን " 5️⃣1️⃣ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ኬሚሴ ➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/2238 📮" ሙስጠለሑል ሓዲስ ሊሸይኽ አል ኡሰይሚን " 5️⃣2️⃣ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ኬሚሴ ➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/2268 📮 ኹዝ አቂደተከ ሚነል ኪታቢ ወሱነቲ ሰሒሓ" 5️⃣3️⃣ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ኬሚሴ ➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/2359 📮ኢና ኩና ፊ ጃሒሊያ 5️⃣4️⃣ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ኬሚሴ ➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/2386 📮 ሙምቲዕ ሸርሁ አጅሩሚያ 5️⃣5️⃣ ኡስታዝ ኸድር አሕመድ አል ኬሚሴ ➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/2419 📮ሸርሑ ሉምዓቱል ኢዕቲቃድ 5️⃣6️⃣ በኡስታዝ ኸድር አህመድ ➴➴➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/2632 📮 ተብሲሩል ኸለፍ" 5️⃣7️⃣ በኡስታዝ ኸድር አህመድ ➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/2704 📮መጃሊሱ ሸህሪ ረመዳን 5️⃣8️⃣ በኡስታዝ ኸድር አህመድ ➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/2733 📮 ሚንሓጁ ፊርቀቱ ናጂያህ 5️⃣9️⃣ በኡስታዝ ኸድር አህመድ ➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/2744 📮 ኹላሰቱ ኑሪል የቂን 6️⃣0️⃣ በኡስታዝ ኸድር አህመድ ➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/2800 📮ተብሲሩል ባዲዒን ቢስጢላሓት አል ሙሓዲሲን 6️⃣1️⃣በኡስታዝ ኸድር አህመድ ➴➴➴➴➴➴➴➴ https://t.me/ye_Selefey_Ustazoch_Durus/2830 ይቀጥላል የሌሎችም ኡስታዞች አለ አልተለቀቀም አልተጨረሰም
Показати все...
ተቀርተው ያለቁ ደርሶች ስብስብ ቻናል

📌 በዚህ ቻናል ፦ በ ❶- ኡስታዝ ኢብኑ ሙነወር ❷- ኡስታዝ ኸድር አል-ኬሚሴ ❸- ኡስታዝ ሳዳት ከማል ❹- አቡ ዐብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ ❺- ዐብዱ ሽኩር አቡ ፈውዛን ❻- ኡስታዝ ሑሴን ዐሊይ ❼- ኡስታዝ አቡ ሙስሊም አል-አሩሲ ❽- ኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ ❾- አቡ ሙዓዊያ ሰዒድ ሙኑር ❿- አቡል ዐባስ ናስር ሙሐመድ ⓫- ሸይኽ ሙሐመድ ዘይን ኣደም ⓬- ኡስታዝ አቡ ሙዓዝ ሐሰን ኢድሪስ ⓭- ኢብኑ ሙሐመድዘይን ⓮- ሸይኽ አወል አሕመድ አል-ኬሚሴ ⓯- አቡ ረይስ ሙሐመድ ኢማም ⓰- ዐብዱል ጀባር ሙኑር ⓱- አቡ ማሂር ሙባረክ ኢድሪስ ⓲- ዶ/ር ሰዒድ ሙሳ አቡል ቡኻሪ ⓳- አጫጭር የዐረብኛ ደርሶችን እና ⑳- በሌሎች ኡስታዞችና ወንድሞች ተቀርተው የተጠናቀቁ ኪታቦችን 📚 ፣ ሙሓዶራዎችን 🔊 ፣ መፅሐፎችን 📖 ፣ ፈትዋዎችንና❔✔️ ፈዋኢዶችን 🍏 ያገኛሉ። “መገጠሜም በአላህ እንጂ በሌላ አይደለም፡፡ በእርሱ ላይ ተመካሁ፡፡ ወደእርሱም እመለሳለሁ።” [ሁድ: 88] https://t.me/MOhamedAljawi
Показати все...
◾️ይድረስ ለኢድ ሶላት ለሚወጡ ሴቶች ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ ↪️ የኢድ ሶላት ለወንድም ሆነ ለሴት የተደነገገ ኢባዳ ነው። ሴቶች ልክ እንደ ወንዶቹ ለኢድ ሰላት መውጣታቸው የተወደደ ተግባር ነው። የአላህ መልእክተኛ ሀይድ ላይ ያሉት ሳይቀር እንዲወጡ አዘዋል። ነገር ግን ወደ ኢድ መውጣት የሚፈቀድላቸው ሌሎች የተቀመጠላቸውን መስፈርቶች ማሟላት ሲችሉ ብቻ ነው። ⭕️👉አንድ ሴት ወደ ኢድ ሶላት በምትወጣበት ጊዜ እነዚህን ነገሮች ልትጠብቅ ይገባታል። 1⃣ ወፍራም፣ ሰፊ፣ ረጅምና ሁሉ የሰውነት አካሏ የሚሸፍን አለባበስ መልበስ አለባት። 2⃣ ሽቶ የሚባል ነገር አካሏም ሆነ ልብሷ በፍፁም ሊነካት አይገባም። 3⃣ አቅሟ በቻለው ሁሉ ከወንዶች መራቅና ከነሱ ጋር ሳትጋፋ የመንገዱን መሀል ሳይሆን ጫፍ ጫፋን ይዛ መሄድ ይጠበቅባታል። 4⃣ በተክቢራም ይሁን በሌላ ፅምፇን ከፍ ከማድረግ መቆጠብ ይኖርባታል። 5⃣ የለበሰችው ጫማ ከፍ ያለ ሆኖ ስትራመድ ሲንቋቋ ሰውን እይታ የሚጣራ መሆን የለበትም። 6⃣ የልብሷ ከለር ደመቅ ብሎ የሰውን አይን የሚስብና ጌጣ ጌጦች ያሉበት መሆን የለበትም። 7⃣ እራሷ ተፈትና ሌሎችን ፊትና ላይ ከመጣል ጥንቃቄ ልታደርግ ይገባል። 8⃣ በአረማመዷ፣ በአነጋገሯና በእይታዋ ሀያእ የተላበሰች ልትሆን ይገባል። 👉ምክንያቱም ባለማወቅ ኸይር እሰራለሁ ብላ ወንጀል እንዳትሸከም፣ አላህን አስደስታለሁ ብላ የሱን ቁጣ እንዳትሸምት፣ ወደ ጌታዋ መቅረብ ፈልጋ የባሰ ከጌታዋ እንዳትርቅ፣ የጀነት መንገድ መስሏት የጀሀነም መንገድ እንዳትሄድ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርባታል። ↪️ በአሁን ሰአት ግን ለኢድ ሶላት ብለው በሚመጡ አንዳንድ ሙስሊም እህቶች ላይ እያፈርንና አንገታችን እየደፋን ነው። ሀያእ የሚባል ጭራሽ የላቸውም። እስልምና እንዲሁም ሙስሊሞችን እያሰደቡ ነው። ካፊሮች እስልምናን በተሳሳተና ትክክል ባልሆነ መልኩ እንዲገነዘቡት እያደረጉ ነው። የኢድ እንደፈለጋችሁ ሁኑ የተባለ ይመስል ብዙ ክልከላዎችን ይፈፅማሉ። ለምሳሌ፦ ✅ ከራሷ የተጣበቀ ጠባብ ልብስ ለብሳ፣ ሰውነቷን በጉርድ ወጣጥራ፣ ፊቶቿ እግሮቿና እዶቻን ገልጣ፣ ሽቶ ተለቅልቃ፣ ቻፕስቲክ ተቀብታ፣ ቅንድቧን ተቀንድባ፣ የተቀባችውን ሂና እያሳየች፣ የእጅ የእግርና የጆሮ ጌጧን ከፍታ፣ ግራና ቀኝ የሚያወዛውዝ ጫማ ለብሳ፣ ድምፇ ከፍ አድርጋ እየሳቀች፣ ከወንዶች እኩል እየተጋፋች፣ ወንዶችን አፍጣ እያየች፣ በየሱቁና መደብሩ እየተዘዋወረችና ሌሎችም ስህተቶች በመፈፀም እራሷ ተፈትና ሌላውንም ፈተና ላይ ጥላ፣ እራሷ ወንጀል ውስጥ ወድቃ ሌላውንም ዘፍቃ፣ አላህን በማመፅ ሸይጧንን በማስደሰት፣ የወንጀል መአት ተሸክማ ወደ ቤቷ የምትመለስ አለች። ➡️ ሴቶች ሆይ አላህን ፍሩ። ለአንድ ቀን ብላችሁ አሄራ ዱንያችሁን አታበላሹ። 👉እንዲህ አይነት ሴቶች እቤት መቀመጣቸው በላጭ ነው። 👉ለኢድ መውጣትሽ ብቻ ሳይሆን አደብ ስርአቱ የጠበቅሽ መሆንሽ አረጋግጪ። በድጋሚ የተለቀቀhttp://t.me/Sadik_Ibnu_Heyru
Показати все...
ውዷ_እህቴ_ሆይ_ህይወትሽ_የሚደምቀው በዲንፍቅርእንጂ_በብር_አይደለም! እናም ገንዘብን በማንኛውም ሰዓት ከሰራሽ ልታገኝው ትችያለሽ! የዲን__ፍቅር ግን ከፈጣሪ ነውና የሚገኘው አብዝተሽ አምላክሽን ለምኝ………………! እናም በትዳር ዙሪያ ላስታውስሽ ፈልጌ ነው! ውዷ እህቴ ወንድን ልጅ ከወደደሽ ራሱን ይሰጥሻል! ይህ ማለት ደግሞ አንቺ አንደፈለግሽ አንገት ሆነሽ ታዞሪዋለሽ ...……………… ብዙ ሀብት ኖሮት ስለ ዲን ምንም የማያውቅ + ስብዕና + ላንቺ ክብር ከጎደለው ሰው ጋር አይደለም ትዳር___ለአንድ ቀን አብሮ ለመዋል እንዳትመኝ... …………………………! በማስመሰል እራሱን ደብቆ ከሚመጣ አስመሳይ ወንድ ወጥመድ እንዳትገቢ ጥንቃቄ ይኑርሽ...………! ብዙ ወንድ በማስመሰል የሚፈልገውን እስኪያገኝ የማይፈልገውን ያደርጋልና! እንዲህ አይነቱን ወንድ በኑሮ ሂደት እንደ ዕስስት____ሲቀያየር ትመለከችዋለሽ! በውሳኔው__የማይፀና_አቋም የሌለው ሰው ላይ ብትወድቂ እድሜሽን በሙሉ ስትንከራተቺ ትኖሪያለሽና! እንደዚህ አይነቱን ወንድ ለማስተካከል ካልችልሽ በትዳር እንዳትታሰሪ ጠንቃቃ ሁኝ!!! ደስታ የሚገኘው የውስጥን ፍላጎት በነፃነት መግለፅ ሲቻል ነውና ነፃነትሽን የሚነፍግ ፍልጎትሽን የማይጠይቅ ወንድ ገና ሲጀመር አትቅረቢው! እንደህ አይነቱ ወንድ ምንጊዜም ራሱ የሚያወራውን እንጂ አንቺ የምታወሪውን አይሰማም!+ ቢሰማም ቦታ አይሰጠውም! እርሱ በወደደው እንጂ አንቺ በመረጥሽው መንገድም አይጓዝምና! አንቺ ለምትናገሪው + ለምታደርጊው ነገር ስህተት ቢመስለው እንኳ! በቀስታ እንጂ ጮሆ የሚናገር ወዳጅ አታበጂ! ዛሬ ከጮኸብሽ ነገ ሊመታሽ እጁን የማያነሳበት ምንም ምክያት የለውምና! ከሀብት ከቁሳቁስ በላይ ዲን ላይ + ዓባዳ ላይ የሚያጠናክርሽ + ንፁህ ልቡን+ ንፁህ ፍቅርን የሚሰጥሽን ወንድ ተመኝ!! የወንድን ልጅ ያለውን ሀብት ወይም ኪሱን ሳይሆን! በዲን ሊያጠናክርሽ ይዞ የመጣውን ንፁህ ፍቅር ተመልከች! እንደዚህ አይነቱን ወንድ ትልቅ ዛፍ ሆኖ ሊጠልልሽ ፍሬ ሊሰጥሽ ይችላልና! ምክንያቱም የሁሉም መሰረቱ *ዲን ነውና* ! ደስተኛ የሆነ ህይወት ከፈለግሽ! እህቴ ሁል ጊዜም አስተውይ ብር ሳይሆን ለአንቺ ክብር ያለው ወንድ በዲኑ ጠንካራውን አግቢ!!! እህቴ ሆይ የትዳርአጋርሽን ስትመርጭ በድብ እስቢበት የልጆችሽ አባት የሚሆን ግማሽ አካልሽ ምን አይነት የትዳር አጋሪ መምርጥ አለብሽ ገንዘብ። ያልቃል ውበት ይርግፍል ዘርም አይተሽ ብትገቢ ዘርኝነት ጥብናት ዘሩ ለጀነት። አያበቃሽም እናማ ምንማድርግ አለብኝ ትይኝ ይሆናል ተከታተይኝ ልብሽ ስጭኝ ጆሮሽን። አውሽኝ ዲኑን አኽላቁን ስነምግባሩን አይተሽ ግቢ!!! ደግሞ ልብ በይ ቁርዓን ያሀፍዘ ሁሉ ሀድስ የሽመደደ ሁሉ ጥሩ ስነምግባር አለው ማለት አይቻልም!! አሏህ ያዘነለት ቢሆን እንጅ ስንት አለ በውጭ ዑስታዝ። በቤት። እና ከስውች ሲስውር ሙንከር ላይ የሚውል!! በውጭ ጢሙን አስርዝሞ +ቶፕውን አሳጥሮ። ከላይ ሱንይ መስሎ። በተግባር ግን ዜሮ። በቤት ሚስቱን እያስለቀስ :ሚስት የለኝም እያለ የእህቶችን ሂጃብ የሚገፍ። ::ህይውታቸውን የሚያበላሽ!!እናማ ተጠንቀቂ። ለትዳር የቤት እመቤት። መሆን ቢናፍቅሽም። ፣ለስውች ውሬ ለምን አታገቢም የሚሉ ስውች እንዳይሽውድሽ!!ለስው ውሬ ቦታ አትስጭ። ስምሽን እንጅ ምኞትሽን መቸ ያውቃሉ !! ታገሽ ወበሽር አሷብሪን ብሏል ጌታሽን አንች እውነተኛ የአሏህ ባሪያ ሁነሽ ሷሊህ መልካም ሴት ሁነሽ ሷሊሁን ጠብቂ!!! الْخَبِيثَاتُ لِلْخَبِيثِينَ وَالْخَبِيثُونَ لِلْخَبِيثَاتِ ۖ وَالطَّيِّبَاتُ لِلطَّيِّبِينَ وَالطَّيِّبُونَ لِلطَّيِّبَاتِ ۚ أُولَـٰئِكَ مُبَرَّءُونَ مِمَّا يَقُولُونَ ۖ لَهُم مَّغْفِرَةٌ وَرِزْقٌ كَرِيمٌ (ሱረት አል-ኑር፣ - 26) መጥፎዎቹ ሴቶች ለመጥፎዎች ወንዶች መጥፎዎቹ ወንዶችም ለመጥፎዎቹ ሴቶች የተገቡ ናቸው፡፡ ጥሩዎቹ ሴቶችም ለጥሩዎቹ ወንዶች ጥሩዎቹ ወንዶችም ለጥሩዎቹ ሴቶች የሚገቡ ናቸው፡፡ እነዚያ (መጥፎዎቹ) ከሚሉት ነገር ንጹሕ የተደረጉ ናቸው፡፡ ለእነርሱ ምህረትና መልካም ሲሳይ አላቸው፡፡ በርሽን ላንኳኳልሽ። ሁሉ። ልብሽን አትክፍች !!ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ አንች እኮ።ውድ ነሽ አሏህ በኢስላም ትልቅ ደርጃ ስቶሻል!!! قُل لِّلْمُؤْمِنِينَ يَغُضُّوا مِنْ أَبْصَارِهِمْ وَيَحْفَظُوا فُرُوجَهُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَزْكَىٰ لَهُمْ ۗ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا يَصْنَعُونَ (ሱረት አል-ኑር፣ - 30) ለምእመናን ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን (ያልተፈቀደን ከማየት) ይከልክሉ፤ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፤ ይህ ለነሱ የተሻለ ነው፤ አላህ በሚሠሩት ሁሉ ውስጥ ዐዋቂ ነው፡፡ እናማ ውደዋ የኔ ከርታታ የስው ቤት ያስመርርሽ አብሽሪ። አንገትሽን አትድፊ!! ቀና በይ ከአሏህ ጋር ሆኖ አዘን የለም!! وَلَسَوْفَ يُعْطِيكَ رَبُّكَ فَتَرْضَىٰ (ሱረቱ አል ዱሃ - 5) ጌታህም ወደ ፊት (ብዙን ስጦታ) በእርግጥ ይሰጥሃል፡፡ ትደሰታለህም፡፡ ምንግዜም ከአሏህ ተስፍ አትቁርጭ ሙእሚን ተስፍ አይቆርጥም!! እራስሽን ከሀራም ነገር ጠብቂوَقُل لِّلْمُؤْمِنَاتِ يَغْضُضْنَ مِنْ أَبْصَارِهِنَّ وَيَحْفَظْنَ فُرُوجَهُنَّ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا مَا ظَهَرَ مِنْهَا ۖ وَلْيَضْرِبْنَ بِخُمُرِهِنَّ عَلَىٰ جُيُوبِهِنَّ ۖ وَلَا يُبْدِينَ زِينَتَهُنَّ إِلَّا لِبُعُولَتِهِنَّ أَوْ آبَائِهِنَّ أَوْ آبَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ أَبْنَائِهِنَّ أَوْ أَبْنَاءِ بُعُولَتِهِنَّ أَوْ إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي إِخْوَانِهِنَّ أَوْ بَنِي أَخَوَاتِهِنَّ أَوْ نِسَائِهِنَّ أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُهُنَّ أَوِ التَّابِعِينَ غَيْرِ أُولِي الْإِرْبَةِ مِنَ الرِّجَالِ أَوِ الطِّفْلِ الَّذِينَ لَمْ يَظْهَرُوا عَلَىٰ عَوْرَاتِ النِّسَاءِ ۖ وَلَا يَضْرِبْنَ بِأَرْجُلِهِنَّ لِيُعْلَمَ مَا يُخْفِينَ مِن زِينَتِهِنَّ ۚ وَتُوبُوا إِلَى اللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ الْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ (ሱረት አል-ኑር፣ - 31) ለምእምናትም ንገራቸው፡- ዓይኖቻቸውን ይከልክሉ፡፡ ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ፡፡ ጌጣቸውንም ከእርሷ ግልጽ ከኾነው በስተቀር አይግለጡ፡፡ ጉፍታዎቻቸውንም በአንገትጌዎቻቸው ላይ ያጣፉ፡፡ (የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንዶች ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለሴቶቻቸው ወይም እጆቻቸው ለያዙት (ባሪያ) ወይም ከወንዶች ለሴት ጉዳይ የሌላቸው ለኾኑ ተከታዮች ወይም ለነዚያ በሴቶች ሐፍረተ ገላ Cp https://t.me/+jFuPUP7QXbs3MzI0
Показати все...
💐👑كــــو نــــي امــرأة صـــالــحـــة وتـــقـــيـــــة 💐

· ━━━━•𖡼•⟨ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ ⟩•𖡼• ━━━━· ·⟣ ┈┈┈┈┉┉⊏ □⊐ ┉┉┈┈┈┈⟢· | التَّوْحِيدُ كَالسَّيْفِ الصَّارِمِ يَقْطَعُ رُؤُوسَ الضَّلَالِ | ·⟣ ┈┈┈┈┉┉⊏ □⊐ ┉┉┈┈┈┈⟢· ·· ━━━•𖡼•⟨ مُحَمَّدُ رَسُولُ اللَّهِ ⟩•𖡼• ━━━·

https://t.me/+jFuPUP7QXbs3MzI0

▃▄▅▆▇ የቀልብ በሽታ ▇▆▅▄▃▂▁ ሸይኽ ኡሰይሚን (አሏህ ይዘንላቸውና)እንዲህ ብለዋል:- "አሏህ ይጠብቀን እና የቀልብ በሽታ ማለት የዱንያ እና የ አኼራ ክስረት ነው!! ቀልብ በሸክ(በጥርጣሬ)በሽርክ፤በኒፋቅ፤ ከታመመ፤አሏህ ያወረደዉን ህግጋት(ቁርዐን)የሚጠላ ፡እንዲሁም የ አሏህ ወዳጆችንና መሰል የአሆኑ ነገሮችን የሚጠላ ከሆነ በዱንያውም ሆነ በአኼራውም ላይ ታላቅ ክስረት ገጥሞታል ማለት ነው !! ለዚህም ሲባል አሏህን አፊያ(ፈውስ)እንዲሰጥህ ስትለምን የቀልብህን እና የ አካልህን በሽታ እንዲፈውስልህ ልብህን፡ በኢኽላስ ዱዐ ማድረግ ይኖርብሀል።" ========================= ሸይኽ ኡሰይሚን[ሸርህ ሪያዱ ሷሊሂን ቅፅ 6/ገፅ 21] https://t.me/+jFuPUP7QXbs3MzI0 https://t.me/+jFuPUP7QXbs3MzI0
Показати все...
💐👑كــــو نــــي امــرأة صـــالــحـــة وتـــقـــيـــــة 💐

· ━━━━•𖡼•⟨ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ ⟩•𖡼• ━━━━· ·⟣ ┈┈┈┈┉┉⊏ □⊐ ┉┉┈┈┈┈⟢· | التَّوْحِيدُ كَالسَّيْفِ الصَّارِمِ يَقْطَعُ رُؤُوسَ الضَّلَالِ | ·⟣ ┈┈┈┈┉┉⊏ □⊐ ┉┉┈┈┈┈⟢· ·· ━━━•𖡼•⟨ مُحَمَّدُ رَسُولُ اللَّهِ ⟩•𖡼• ━━━·

https://t.me/+jFuPUP7QXbs3MzI0

የማያባራ እልቂት። የማይገደብ የደም ጅረት። ሰሚ ያጣ ዋይታ። ለመሆኑ ደካሞችን፣ ጨቅላዎችን በጅምላ በመፍጀት የሚገኘው ትርፍ ምን ይሆን? ግን እስከ መቼ? ጌታዬ ሆይ! ከሰው ያለን ተስፋ ተሟጧል። ሽሽታችን፣ ለቅሷችን፣ ጩኸታችን ወዳንተ ብቻ ነው። አንተው መላ በለን። አንተው ወገኖቻችንን ፈርጅልን። ለርካሽ አላፊ ትርፍ ሲሉ የደካሞችን ነፍስ በማጥፋት ላይ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ድርሻ ያላቸውን ሁሉ የሚገባቸውን ስጣቸው። https://t.me/IbnuMunewor
Показати все...
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)

دروس وفوائد ابن منور

📣ጥቂት ምክሮች ለአረፋ ወደ ገጠር ሁጃጆች፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ቤተሰብን ለማስደሰት ብላችሁ ጊዜያችሁን፣ገንዘባችሁና ስራችሁ መሰዋት በማድረግ ከቤተሰባችሁ ጋር ለመገናኘትና እነሱን ለማስደሰት ብላችሁ የምታደርጉት ጉዞ አሏህ ይቀበላችሁ ከመጥፎ ነገርም ይጠብቃችሁ፡፡ለዚህ ለአማረ ስራ ይበልጥ ያምር ዘንድ የሚከተሉትን ነጥቦች እንደወንድምነት ተመከሩልኝ፡፡   ክፍል አንድ ከጉዞ ጋር በተያያዘ 1ኛ ከጉዞ ቀን በተመለከተ፡- የምትሄዱበት ቀን ብትመርጡ መልካም ነው በተለይ የዙልሂጃ ዘጠነኛው ቀን(የአረፋ ቀን)ጉዞን ባታደርጉ ይመረጣል፡፡ምክንያቱ የአረፋ ቀን ትልቅ ቀን በመሆኑ የአሏህ መልክተኛ የአሏህ ሰላምና እዝነት በሳቸው ላይ ይሁንና ያንን ቀን በመፆም አዘውናል፡፡ምንዳውንም የሚመጣውና የአለፈው ወንጀል ያስምራል ብዬ ኧከጅላለሁ ብለዋልና ያንን ቀን መንገድ ላይ ሳይሆን በፆምና በተለያዩ ኢባዳዎችን ብናሳልፍ መልካም ነው፡፡ 2ኛ ጉዞ ላይ በሚስታወሉ ችግሮች ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ከችግሮችም ለአብነት፡-    A/በዘፈን፣በመንዙማዎችና በነሺዳዎችን እየጨፈሩ መኪና እየደበደቡ መጓዝ፡፡ውድ አንባቢያኖቼ በመጀመሪያ ለሁሉም ነገር ልክ አለው በደስታችን ጊዜ የዚህን የደስታ ጊዜ ያደረሰንን ጌታችን የማመስገን ፋንታ እንዴት እሱን እናምፀዋለን? ሁለተኛ ሰው የበለጠ በአስቸጋሪ ላይ ሲሆን እንዴት ወንጀልን ይዳፈራል?የመካ ሙሽሪኮች እኮ በባህር ላይ ሲሳፈሩ ያንን አስፈሪውን ማዕበል ሲያዩ እኮ አሏህን በቢቸኝነት ያመልኩት ይጣሩት ነበረ ወደ የብሱ ወይም ወደ ምድሩ ሲወርዱ ያኔ ወደ ሽርካቸው ይመለሳሉ ታዳ እኛ ከእነሱ መሻል ሲገባን እንዴት እንብሳለን?በመኪና ውስጥ እኮ አሏህ ይጠብቀንና መኪና መገልበጥ፣መጋጨትና የተለያዩ አደጋዎች የመጋለጥ ዕድል ሰፊ በሆነበት ሁኔታ የእኛ ጭፈራ ምን የሚሉት ነው?ሰው በአውሮፕላን፣በመርከብና በመኪና ሲጓዝ ይበልጥ ሊፈራና ሊሰጋ ይገባዋል ምክንያቱም ለአደጋ ቅርብ ስለሆነ ስለዚህ ጌታውን ሊለምነው ሊያወሳው ይገባል፡፡እንዲሁም ደግሞ የሰው ልጅ ሲሞት በነበረበት ሁኔታ ላይ ሆኖ ነው ሚቀሰቀሰው የሚለው ሀዲስስ አስተውለነው እናውቃለን እንዴ?ሙዚቃ እየሰማን እየጨመርን የሆነ ነገር ብንሆን እንኳን ነገ የምንቀሰቀሰው ሙዚቃና ዘፈን እየሰማን ነው የምንቀሰቀሰው ይልቁንስ ዚክር እያደረግን፣ቁራዐንና ጠቃሚ የሆኑ ሙሀደራዎች እየሰማን ብንሄድ ተጠቃሚ ከመሆን አልፎ ኒያው ከአለን ኢባዐዳ እያደረግ እየሄድን መሆኑን አሏህ ዘንድ ይመዘግብልናል፡፡ B/የሴቶች ጉዞ ሴት እህቶቻችን ከወንዶቹ ይልቅ ቤተሰብን በመንከባከብ የተለዩ መሆናቸው ለማን የማይሰወር ሀቅ ነው አሏህ በዱኒያም በአኼራ መልካምን ነገር ይግጠማቸውና፡፡ነገር ግን ቤተሰብ ለማስደሰት ነው ብለሽ ግን ድንበር አትጣሺ፡፡ድንበር ከሚጣስባቸው ነገራቶች አንዱ ጉዞን ያለመህረም መጓዝ ነው፡፡ መህረሞች ማን ናቸው በጥቂቱ አባትሽ፣አያትሽ፣ባዐልሽ፣የስጋ ወንድሞች(በእናትም ፣በአባትም ወይንም ከሁለት አንዱ የምትገናኚው)ልጅሽ፣አጎትሽ...ከእነዚህ ከተገኙት ካልሆነ በስተቀር ሸሪያዐችን ሴት ልጅ ሩቅ ቦታ ቢቻዋን መሄድን ከልክሎዋል፡፡ሰውን አስደስታለሁ ነፍሴያዬ ደስ ይበላት ብለሽ አሏህን አታምፂው፡፡ፉጡርን አሏህን በሚታመፅበት ነገር መታዘዝ ክልክል ነው፡፡በሚያሳዝነው መልኩ ጂልባብሽ ኒቃዐብሽ ለብሰሽ የሰፈር ልጆች ናቸው የአጎቴ ልጆች እያልሽ ተተራምሰሽ ስትሄጂ እንዴት ያማል፡፡እህቴ ለአንቺ እኮ አይሆንሽም፡፡መኪና ውስጥ ተቀምጠሽ ከእነዛ ጨፋሪና ቃሚዎች ጋ እንዴት ሆኖ?ደግሞ ምንም ያህል ኢማን አለኝ፣አቋም አለኝ፣በራስ የመተማመን አቅሜ ከፍ ያለ ነው ብቲይም ያንን ያህል ርቀት ያለው ቦታ እንዴት ሆኖ ቢቻሽ?አንቺ እኮ ሰው ነሽ ደካማ ለዛውም ነፍሲያና ሸይጧን የሚፈታተኑት ሰው የሚሉት ፉጡር ስለዚህ ኧቆጣጠረዋለሁ ችግር የለውም አትበይ፡፡     ክፍል ሁለት እዛ ከደረስንስ በኀላ 1ኛ እናት አባታችን(ቤተሰባችን አለማስቸገር ከአዲስ አበባ መጥተሀል ማሻአሏህ አንተ ቤት የተለያዩ ጓደኞችህ እያመጣህ እናትህ አንዴ ቡና አንዴ ሻይህ እያፈላች ወገብዋ ቀና ሳይል ሽርጉድ እያለች እንድትውል አታድርጋት፡፡ያ ብሎ ማለት ጓደኛህ ቤት መጥቶ አይዘይር አትዘያየሩ ለማለት ሳይሆን በልኩ ይሁን እንዲሁም ወንድ እንግዳ ሲመጣ ራስህ ለማስተናገድ ሞክር 2ኛ ወደ ውጪ መውጣት አታብዛ ቤተሰብህ ማሻአሏህ ልጃችን ከአዲስ አበባ መጥቶዋል ብለው ብዙ ነገር ከአንተ መጨዋወትን ይፈልጋሉ፣ከአንተ ማሳለፍን ይወዳሉ፣ቡና እንኳን ቢፈላ አይናቸው የአንተ መምጣት በመጠባበቅ ወደ ውጪ ያማትራል እና ቀልባቸውን ከመስበር ተጠንቀቅ 3ኛ ቤተሰብህ ከጎረቤታቸውና ከዘመዶቻቸው ጋር ያላቸው ቁርኝት ቃኘው፡፡ተጣልተውም ከሆነ አስታርቃቸው በተለይ ጉርብትና እንዳይበላሽ አስተካክል 4ኛ የዲናቸው ጉዳይ ላይ ትኩረት ስጣቸው፡፡በአገኘህ ቁጥር አስታውሳቸው ሸሪያዐን የሚቃረን ነገር ቤት ውስጥ ሲሰራ ከአየህ በጥበባዊ መልክ በጥሩ ዕዘዝ ከመጥፎ ከልክል 5ኛ በቻልከው መጠን የቤት ስራ እናትህም አባት አግዝ እነዚህ ጥቂት ጥቆማዎቼ ነው ከተሳሳትኩኝ አርሙኝ ያሰባችሁትን ቤተሰብ ዝያራ አሏህ ያሳምርላችሁ፣አሏህ ይቀበላችሁ፣ምንዳችሁ እጥፍ ድርብ አድርጎ ይተካላችሁ፣ከአደጋም ይጠብቃችሁ አሏሁመ አሚን ሰላምና እዝነት እንዲሁም በረካ በአሏህ መልዕክተኛና እሳቸውን በተከተለ ላይ ይሁን፡፡    ከወንድማችሁ ኢብኑ ሲራጅ    በየቻናላችሁና ግሩፕ አሰራጩልኝ    share.............. https://t.me/kurantejwid
Показати все...
[] مركز أبي موسى الأشعري []

"አቡ ሙሳ የቁርአን ሒፍዝ ማእከል" በአካል ለመማር በነዚህ አድራሻዎች ይደውሉ +251911249457 +251901175562 +251908986697 +251914033324 +251930547776 በ Online ለመማር እነዚህን 2 ዩዘሮች ይጠቀሙ 👇👇👇 @MerkezAbumusa @MERKEZ_Abumusaa

Фото недоступнеДивитись в Telegram
➲ልብ ያለው ልብ ይበል ➱➱➱➱➱➱➱➱➱➱ እህቴ ሆይ ስሚኝ ላስታውስሽ አንድ አፍታ የሚል አይቻለሁ ይጠቅማል ትውስታ እናም እህቴ ሆይ በርቺ በመማር ላይ የዲን እውቀት መማር ግድ ነው ባንች ላይ አንገትሽን ደፍተሽ ወዳ ወዲህ ሳትይ ዲንሽን ተማሪ ሁኚ ጽኑ ታጋይ እንዳትበገሪ ለሰዎች ኡኡታ ስምሽን ቢያነሡት ባልዋልሽበት ቦታ በጽናት ተጓዥ ተራመጅ ወደፊት እንዳያዘናጋሽ የጯሂወች ጩኸት። ጸንተሽ ከተራመድሽ ካልሆንሽ ወላዋይ ሀቅ ወደጠቆመው ከሆንሽ ተዘንባይ ያኔ ትሆኛለሽ የአጥር ውስጥ አበባ ሁሉ የማይቀጥፋት ደፍሯት የማይገባ !! ያኔ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 በእውቀት ስትበረች ስትሆኚ ጠንካራ ተሠልፈሽ ሲያይሽ ከጀግኖቹ ጎራ ጠላትሽ ይበሽቃል ያኔ አይኑ ይቀላል ምኞቱ ነውና እንድትሆኚ ተራ እንድትሆኚ ቀላል ታዳ ይህ ምኞቱን ተገንዝበሽ በጥልቅ ክብርሽን ጠብቂው ቆመሽ በተጠንቀቅ !! አንች ውዷ እህቴ ብልጥ ሁኚ አደራ ጎትቶ እንዳይጥልሽ የጠላትሽ ሤራ!! ሁሌም ሁኝ ከፊቱ ቀድመሽው ተገኝ እሱ አይተኛም እና አንችም አትተኝ ከቶ አትዘናጊ አትርሽው ለቅጽበት አይጥ ካልፈጠነ ይበላዋል ድመት!! 〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰 የጠላትን ሤራ ሽርቡን ለማክሸፍ ቁጥሩን ለማምከን ተንኮሉን ለመግፈፍ ዋናው ቁልፍ ነገር ወዲህ ነው እወቂ የሸሪዓ እውቀት ነው እህቴ ሆይ ንቂ !! እኔም ለዚሁ ነው የምልሽ ተማሪ ከዚያም በመቀጠል በተማርሽው ስሪ አማኝ ጥቆማ እንጂ አያሻውም ዝርዝር እኔም በዚህ ይብቃኝ ልብ ያለው ልብ ይበል። ◉◉◉◉✍ cpe https://t.me/+jFuPUP7QXbs3MzI0 https://t.me/+jFuPUP7QXbs3MzI0 https://t.me/+jFuPUP7QXbs3MzI0
Показати все...
Repost from Ibnu Muhammedzeyn
ውጫችንን ለማሳመርና ለማስተካከል እንደምንጥረው ውስጣችንንም ለማስተካከል እንጣር የውስጥ መበላሸት መጨረሻን(ኻቲማን) ያበላሻል። ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን እንድህ ይላሉ:- «ብዙው ሰው በሙስሊሞች፣በዑለሞችና በኸይር ባለቤቶች ላይ ቀልቡ በምቀኝነት የተሞላ ሆኖ ሳለ ከላይ በሚታይ ስራ እንዳይሳሳት ይጓጓል(ይጥራል)። እንድህ አይነቱ ሰው –በአላህ እንጠበቃለን– በመጥፎ ኻቲማ ይጨረስለታል።ምክኒያቱም ቀልብ ውስጧ ቆሻሻ ከሆነች እርሷ ባልተቤቷን እሩቅ ስፍራ ትጥላለች።» [መጅሙዑ አል ፈታዋ ወረሳኢል (5/138)] ‏🔸 قال الشَّيخ ابن عثيمين - رحمه الله - : "كثير من النَّاس يحرص ألاَّ يخطئ في العمل الظَّاهر، وقلبه مليء بالحقد على المسلمين وعلمائهم وعلى أهل الخير، وهذا يختم له بسوء الخاتمة والعياذ بالله، لأنَّ القلب إذا كان فيه سريرة خبيثة، فإنَّها تهوي بصاحبه في مكان سحيق". ‏📔المصدر: [مجموع الفتاوى والرَّسائل (238/5)] ✍ ኢብኑ ሙሐመድዘይን ​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈• t.me/IbnuMuhammedzeyn
Показати все...
Ibnu Muhammedzeyn

ይህ ቻናል በአላህ ፍቃድ አቅም በፈቀደ መልኩ ትክክለኛው ኢስላማዊ አስተምህሮት፦ ① ከቁርኣን፣ ② ከሐዲሥ √ በሰለፎች አረዳድ እንድሁም ③ ከቀደምት እና በዘመኑ ካሉ የሱናህ ዑለሞች ይቀርብበታል።

جمعة مباركة بدعة ✋🏻 الله يخليك لا يجوز قولها✋🏻 إنشاء الله ❌ إن شاء الله☑️ الله يعطيك لعمى❌ الله يعطيك كل خير ويحفظك ☑️ ولو فعلت كذا وكذا ❌ قدر الله وماشاء فعل ☑️ عطك الله كلشي شكون بحالك ❌ اللهم بارك وزد في ذلك والحمد الله اللهم اعطيني كما عطيت فلان وأرزقني من حيث لا أحتسب☑️ اللهم أرزقني الشباب فقط ❌ اللهم أرزقني الذرية الصالحة ☑️ علاش هذيك مزوجة وأنا لا✋🏻❌ اللهم أكمل لها على الخير وأرزقني ايضا زوجا صالحاً ☑️ هذيك ديرة المكياج او زوينة نمشي حتى انا ندير بحالها❌ أختاه إتقي الله فإذن ذلك حرام الجمال الحقيقي هو في قلبنا وأخلاقنا ☑️ كتسمع الأغاني وو زوين هذا صوت يلا نشطوح ❌ أختاه ذلك حرام فلا تسمعي له☑️ زوين فيك ذك سروال المزير تبارك الله ❌ أختاه هي بنا لي نلبسو الحجاب الشرعي وماأجمل الستر ☑️ هذيك خايبة او مكتعرف تمشي زيد زيد ❌ أختاه لا يجوز أن نتكلم على عورات الناس إتقي الله في اختكي ☑️ الأخوات الله يجزاكم بالخير ملي تشوف بحال هذشي خصكم تنهو عنه مشي تمشوا معهم وهكذا الصحبة الصالحة ☑️☑️ https://t.me/+jFuPUP7QXbs3MzI0
Показати все...
💐👑كــــو نــــي امــرأة صـــالــحـــة وتـــقـــيـــــة 💐

· ━━━━•𖡼•⟨ لَا إِلَهَ إِلَّا اللَّهُ ⟩•𖡼• ━━━━· ·⟣ ┈┈┈┈┉┉⊏ □⊐ ┉┉┈┈┈┈⟢· | التَّوْحِيدُ كَالسَّيْفِ الصَّارِمِ يَقْطَعُ رُؤُوسَ الضَّلَالِ | ·⟣ ┈┈┈┈┉┉⊏ □⊐ ┉┉┈┈┈┈⟢· ·· ━━━•𖡼•⟨ مُحَمَّدُ رَسُولُ اللَّهِ ⟩•𖡼• ━━━·

https://t.me/+jFuPUP7QXbs3MzI0

Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.