ሰዋስው ☘☘☘☘
Відкрити в Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
Показати більше1 161
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
1 161
ከጥቅምት ፳፩ ጀምሮ ለሰባት ቀናት ሲከናወን የቆየው ሥርዓተ ፍልሃተ ቅብዐ ሜሮን በጸሎተ ቅዳሴ ተጠናቀቀ።
©ኢኦተቤ ቴቪ ጥቅምት ፳፯/፳፻፲፭ ዓ/ም
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በታሪክ ለሦስተኛ ጊዜ ከጥቅምት ፳፩ እስከ ፳፯/፳፻፲፭ ዓ/ም ለሰባት ቀናት የተከናወነው የሥርዓተ ፍልሀተ ቅብዐ ሜሮን በጸሎተ ቅዳሴ ፍጻሜው ሆኗል።
የሥርዓተ ቅብዐ ሜሮን ማጠናቀቂያ የሆነው ጸሎተ ቅዳሴ በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ሲከናወን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ቅዳሴውን በመምራት ፣ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የኒውዮርክና አካቢቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ቁጥራቸው በርከት ያሉ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳስ ተገኝተውበታል።
ጸሎተ ቅዳሴው እንደሥርዓቱ ከተከናወነ በኋላ በስተመጨረሻ ቅብዐ ሜሩን እንዲያዘጋጁ በኮሚቴነት ከተዋቀሩት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት መካከል አንዱ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ በትግራይ ክልል የደቡባዊ ዞን ማይጨው ሀገረ ስብከትና የቅርስ መምሪያ እንዲሁም አዲስ የተቋቋመው የማኅበራት ምዝገባና ቁጥጥር መምሪያ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ ስለ ፍልሀተ ቅብዐ ሜሮን ለምዕመናን ገለጻ አድርገዋል።
ብፁዕነታቸው ስለተከናወነው ጉዳይ ሲያብራሩ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት ለሰባት ቀናት ሥርዓተ ጸሎቱ ሲከናወን ስለነበረው ስለቅብዐ ሜሮን ጥንተ ታሪክ፣ አስፈላጊነትና አዘገጃጀት እንዲሁም ሁሉም አማኝ የመንፈስ ቅዱስ ማኅተም የሆነው ቅብዐ ሜሮን በትክክል ማወቅና ሥርዓቱን ማክበር እንዳለባቸው መልእክት አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም ቅዱስነታቸው በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቀረበውን ቅብዐ ሜሮን በቤተ መቅዱሱ በምዕመናን ፊት የባረኩ ሲሆን ቀጥሎም ለሰባት ቀናት ሥርዓቱ ሲከናወንበት ወደ ነበረው ቦታ በመምጣት በቅዳሴ የከበረውን ቅብዐ ሜሮን በብዛት ከተዘጋጀው ሜሮን ጋር አዋሕደዋል።
ይህንን ሥርዓትም በቦታው የተገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንዲሁ አድርገዋል።
ቅዱስነታቸው በቃለ በረከታቸው ሥርዓተ ጸሎተ ቅብዐ ሜሮን ከጅምሩ እስከ ፍጻሜው በነበረው ሁሉ እጅግ እንደተደሰቱ ገልጸው ይህ ልዩ የሆነ ሥርዓት እንዲከናወን ላደረጉ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባት ጀምሮና ለዚህ ጉዳይ በኮሚቴነት ተዋቅረው ሲደክሙ ለነበሩ ብፁዓን አባቶችና ወንድሞች እንዲሁም ይህ እንዲሆን መንገድ ለጠረጉ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅብዓ ሜሮን ዝግጅት ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜያት የተከናወነ ሲሆን እነሱም በአምስተኛው ፓትርያርክ በነበሩት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ዘመነ ፕትርክና በ፲፱፻፺፰ ዓ/ምና በ፳፻፪ ዓ/ም እንደነበር የሚታወስ ነው።
መ/ር ኃይሉ በላይ
1 161
29/2/2013 ዓ.ም (፳፱/፪/፳፻፲፫ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
ዐፀደ ወይን አፍለስከ እምግብጽ።
ሰደድከ አሕዛብ ወተከልከ ኪያሃ።
ወፄሕከ ፍኖተ ቅድሜሃ። መዝ 79፥8
🕯 ትርጉም
ከግብጽ የወይን ግንድ አመጣህ።
አሕዛብን አባረርህ።
እርሷንም ተከልህ።
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯1 161
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
ማቴ. 27:20-57፡ "ወእምዝ መስተራትዐተ ሐራ" - "የካህናት፡አለቃዎችና፡ሽማግሌዎች፡ግን፡በርባንን፡እንዲለምኑ፡ኢየሱስን፡ግን፡እንዲያጠፉ፡ሕዝቡን፡
አባበሉ። ገዢውም፡መልሶ፦ከሁለቱ፡ማንኛውን፡ልፈታላችኹ፡ትወዳላችኹ? አላቸው፤ እነርሱም፦በርባንን፡አሉ። ጲላጦስ፦ክርስቶስ፡የተባለውን፡ኢየሱስን፡እንግዲህ፡ምን፡ላድርገው? አላቸው፤ሁሉም፦ይሰቀል፡አሉ። ገዢውም፦ምን፡ነው፧ያደረገው፡ክፋት፡ምንድር፡ነው? አለ፤እነርሱ፡ግን፦ይሰቀል፡እያሉ፡ጩኸት፡አበዙ። ጲላጦስም፡ሁከት፡እንዲዠመር፡እንጂ፡አንዳች፡እንዳይረባ፡ባየ፡ጊዜ፥ውሃ፡አንሥቶ፦እኔ፡ከዚህ፡ጻድቅ፡ሰው፡ደም፡ንጹሕ፡ነኝ፤እናንተ፡ተጠንቀቁ፡ሲል፡በሕዝቡ፡ፊት፡እጁን፡ታጠበ፡ሕዝቡም፡ዅሉ፡መልሰው፦ደሙ፡በእኛና፡በልጆቻችን፡ላይ፡ይኹን፡አሉ። በዚያን፡ጊዜ፡በርባንን፡ፈታላቸው፥ኢየሱስን፡ግን፡ገርፎ፡ሊሰቀል፡አሳልፎ፡ሰጠ። በዚያን፡ጊዜ፡የገዢው፡ወታደሮች፡ኢየሱስን፡ወደገዢው፡ግቢ፡ውስጥ፡ወሰዱት፡ጭፍራውንም፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡አከማቹ። ልብሱንም፡ገፈው፡ቀይ፡ልብስ፡አለበሱት፥ ከሾኽም፡አክሊል፡ጎንጉነው፡በራሱ፡ላይ፥በቀኝ፡እጁም፡መቃ፡አኖሩ፥በፊቱም፡ተንበርክከው፦የአይሁድ፡ንጉሥ፡ሆይ፥ሰላም፡ለአንተ፡ይኹን፡እያሉ፡ዘበቱበት፤ ተፉበትም፡መቃውንም፡ይዘው፡ራሱን፡መቱት። ከዘበቱበትም፡በዃላ፡ቀዩን፡ልብስ፡ገፈፉት፥ ልብሱንም፡አለበሱት፡ሊሰቅሉትም፡ወሰዱት። ሲወጡም፡ስምዖን፡የተባለው፡የቀሬናን፡ሰው፡አገኙ፤ርሱንም፡መስቀሉን፡ይሸከም፡ዘንድ፡አስገደዱት። ትርጓሜው፡የራስ፡ቅል፡ስፍራ፡ወደሚኾን፥ጎልጎታ፡ወደሚባለው፡ስፍራ፡በደረሱ፡ጊዜም፥ በሐሞት፡የተደባለቀ፡የወይን፡ጠጅ፡ሊጠጣ፡አቀረቡለት፤ቀምሶም፡ሊጠጣው፡አልወደደም። ከሰቀሉትም፡በኋላ፡ልብሱን፡ዕጣ፡ጥለው፡ተካፈሉ፥ በዚያም፡ተቀምጠው፡ይጠብቁት፡ነበር። ይህ፡ኢየሱስ፡የአይሁድ፡ንጉሥ፡ነው፡የሚል፡የክሱን፡ጽሕፈት፡ከራሱ፡በላይ፡አኖሩ። በዚያን፡ጊዜ፡ኹለት፡ወንበዴዎች፡አንዱ፡በቀኝ፡አንዱም፡በግራ፡ከርሱ፡ጋራ፡ተሰቀሉ። የሚያልፉትም፡ራሳቸውን፡እየነቀነቁ፡ይሰድቡት፡ነበርና። ቤተ፡መቅደስን፡የምታፈርስ፡በሦስት፡ቀንም፡የምትሠራው፥ራስህን፡አድን፤የእግዚአብሔር፡ልጅስ፡ከሆንህ፡ከመስቀል፡ውረድ፡አሉት። እንዲሁም፡ደግሞ፡የካህናት፡አለቃዎች፡ከጻፊዎችና፡ከሽማግሌዎች፡ጋራ፡እየዘበቱበት፡እንዲህ፡አሉ። ሌላዎችን፡አዳነ፥ራሱን፡ሊያድን፡አይችልም፤የእስራኤል፡ንጉሥ፡ከኾነ፥አኹን፡ከመስቀል፡ይውረድ፡እኛም፡እናምንበታለን። በእግዚአብሔር፡ታምኗል፤የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ነኝ፡ብሏልና፥ከወደደውስ፡አሁን፡ያድነው። ከእርሱ፡ጋራ፡የተሰቀሉት፡ወንበዴዎች፡ደግሞ፡ያንኑ፡እያሉ፡ይነቅፉት፡ነበር። ከስድስት፡ሰዓትም፡ጀምሮ፡እስከ፡ዘጠኝ፡ሰዓት፡ድረስ፡በምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ጨለማ፡ሆነ። በዘጠኝ፡ሰዓትም፡ኢየሱስ፦ ኤሎሄ፥ኤሎሄ፥ላማ፡ሰበቅታኒ፧ብሎ፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኸ።ይህም፦አምላኬ፡አምላኬ፥ስለ፡ምን፡ተውኸኝ፧ማለት፡ነው። በዚያም፡ከቆሙት፡ሰዎች፡ሰምተው፦ይህስ፡ኤልያስን፡ይጠራል፡አሉ። ወዲያውም፡ከነርሱ፡አንዱ፡ሮጠ፤ሰፍነግም፡ይዞ፡ሖምጣጤ፡ሞላበት፥በመቃም፡አድርጎ፡አጠጣው። ሌላዎቹ፡ግን፦ተው፥ኤልያስ፡መጥቶ፡ያድነው፡እንደ፡ሆነ፡እንይ፡አሉ። ኢየሱስም፡ሁለተኛ፡በታላቅ፡ድምፅ፡ጮኾ፡ነፍሱን፡ተወ። እነሆም፥የቤተ፡መቅደስ፡መጋረጃ፡ከላይ፡እስከ፡ታች፡ከሁለት፡ተቀደደ፥ምድርም፡ተናወጠች፥አለቶችም፡ተሰነጠቁ፤ መቃብሮችም፡ተከፈቱ፥ተኝተው፡ከነበሩትም፡ከቅዱሳን፡ብዙ፡ሥጋዎች፡ተነሡ፤ ከትንሣኤውም፡በኋላ፡ከመቃብሮች፡ወጥተው፡ወደ፡ቅድስት፡ከተማ፡ገቡና፡ለብዙዎች፡ታዩ። የመቶ፡አለቃም፡ከእርሱም፡ጋራ፡ኢየሱስን፡የሚጠብቁ፡መናወጡንና፡የሆነውን፡ነገር፡አይተው፦ይህ፡በእውነት፡የእግዚአብሔር፡ልጅ፡ነበረ፡ብለው፡እጅግ፡ፈሩ። ኢየሱስን፡እያገለገሉ፡ከገሊላ፡የተከተሉት፡ብዙ፡ሴቶች፡በሩቅ፡ሆነው፡ሲመለከቱ፡በዚያ፡ነበሩ፤ ከእነርሱም፡መግደላዊት፡ማርያምና፡የያዕቆብና፡የዮሳ፡እናት፡ማርያም፡የዘብዴዎስም፡የልጆቹ፡እናት፡ነበሩ። በመሸም፡ጊዜ፡ዮሴፍ፡የተባለው፡ባለጠጋ፡ሰው፡ከአርማትያስ፡መጣ፥እርሱም፡ደግሞ፡የኢየሱስ፡ደቀ፡መዝሙር፡ነበረ።"
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨
1 161
27/2/2015 ዓ.ም (፳፯/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም)
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
እግዚአብሔርሰ ንጉሥ ውእቱ እምቅድመ ዓለም
ወገብረ መድኃኒተ በማዕከለ ምድር
አንተ አጽናዕካ ለባሕር በኃይልከ፡፡ መዝ. 73:12
🕯 ትርጉም
እግዚአብሔር ግን ከዓለም አስቀድሞ ንጉሥ ነው።
በምድርም መካከል መድኀኒትን አደረገ።
አንተ ባሕርን በኃይልህ አጸናሃት፡፡
🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯
1 161
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
የጥቅምት ፳፯ ምስባክ
፭ መዝሙር ጸገየ ወይን
🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺🌺
ዘቅዳሴ ምስባክ
ሮሜ፦፲፩፥፲፫-፳፭
ራእ .ዮሐ ፦፲፪፥፲፫-ፍ
ግብ.ሐዋ፦፲፩፥፩-፲፪
ወንጌል ፦ ማቴ ፳፩፥፴፫-ፍ
ቅዳሴ ፦ዘእግዚእትነ
ዐፀደ ወይን አፍለስከ እምግብጽ፣
ሰደድከ አሕዛበ ወተከልከ ኪያሃ፣
ወፄሕከ ፍኖተ ቅድሜሃ።
✝
✝🇪🇹✝ መዝ ፸፱፤፰
✝
1 161
💖 🕊 💖
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞
✞ ጥቅምት ፳፯ [27] ✞
✞ እንኩዋን ለፈጣሪያችን "መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ" እና ለቅዱሳኑ "አባ መቃርስ": "አቡነ መብዓ ጽዮን" "ወአባ ጽጌ ድንግል" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞
🕊 መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ 🕊
ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ለእኛ ሲል በፈጸመው የማዳን ሥራ ክፉዎች አይሁድ ከምሽቱ ፫ ሰዓት ጌቴሴማኒ ውስጥ ያዙት::
ሙሉውን ሌሊት ከቀያፋ ወደ ሐና ፥ ከሐና ወደ ቀያፋ ሲያመላልሱት ፥ አስረው ሲደበድቡት አድረዋል::
ዝም ቢላቸው ዓይኑን ሸፍነው በጥፊ መቱት::
✞ ምራቃቸውን ተፉበት:: ዘበቱበት::
✞ ራሱንም በዘንግ መቱት::
✞ እርሱ ግን ሁሉን ታገሰ::
✞ በጧት ከገዢው ዘንድ ሞት እንዲፈረድበት አቀረቡት::
✞ በሠለስት ፫ ሰዓት ላይ አካሉ እስኪያልቅ እየተዘባበቱ ስድስት ሺህ ስድሳ ስድስት ገረፉት::
✞ ሊቶስጥሮስ አደባባይ ላይ እርጥብ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ ወሰዱት::
✞ ፮ ሰዓት ላይ በረዣዥም ብረቶች ፭ ቦታ ላይ ቸንክረው ሰቀሉት::
✞
፯ ታላላቅ ተአምራት በምድርና በሰማይ ታዩ::
✞ ዓለም በጨለማ ሳለች ጌታ በመስቀል ላይ ፯ ቃላትን ተናገረ::
✞ ከቀኑ ፱ ሰዓት አካባቢ በባሕርይ ስልጣኑ ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው ለየ::
✞ በዚያች ሰዓትም ወደ ሲዖል ወርዶ የታሠሩትን ሁሉ ፈታ::
✞ በ ፲፩ ሰዓት ላይ ደጋጎቹ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ከታላቅ ክብርና ሐዘን ጋር በአዲስ መቃብር ቀበሩት::
በዚአች ቀን ድንግል ማርያም ልቧ በሐዘን ተቃጠለ:: ወዳጁ ቅዱስ ዮሐንስም ፍፁም ለቅሶን አለቀሰ:: ቅዱሳት አንስት በዋይታ ዋሉ::
🕊
" ጌታዬና መድሃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ የደረሰበትን ጉስቁልና ሊተካከል የሚችል ጉስቁልና እንደምን ያለ ነው? ቀላያት ፊቱን በተመለከቱ ጊዜ የሚንቀጠቀጡለት ፀሐይ ብርሃኗን የምትከለክልለት : ጨረቃ የምታለቅስለት : ከዋክብት የሚረግፉለት : ክፉዎች አይሁድ ተፉበት : እጃቸውን አክርረው መቱት : ከስድብ ሁሉ የከፋ ስድብ ሰደቡት:: ስድባቸው እንዲሁ የቃላት ብቻ አልነበረምና ምራቅና ቡጢም አለበት እንጂ : ይህ ብቻ አይደለም : - ክርስቶስ ሆይ በጥፊ የመታህ ማን ነው? ትንቢት ተናገርልን ¡ የሚል ስላቅም አለበትና::
ጌታዬና ንጉሴ መከራ ያልደረሰበት አካል አልነበረውም:: ጭንቅላቱ ላይ የእሾኽ አክሊል ደፉበት : ፊቱን በጥፊ መቱት ፡ ትከሻውን መስቀል አሸከሙት : እጁን በችንካር ቸነከሩት : እግሩን በምስማር ቸነከሩት : አፉን ኮምጣጤ አጠጡት : መላ አካልቱን በጅራፍ ገረፉት :: ወዮ ! እንዲህ ያለ መውደድ እንደምን ያለ ፍቅር ነው፡፡ "
[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ]
🕊
"አቤቱ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፥ ወደ ጕድጓድም እንዳልወርድ አዳንኸኝ።" [መዝ.፴፥፫]
💖 🕊 💖
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ጥቅምት ፳፯ (27) ቀን።
❤ እንኳን ለመድኃኔዓለም ለስቅለቱ ዓመታዊ መታሰቢያ በዓልና ለሀገረ ቃው ኤጲስ ቆጶስ ለአባ መቃርስ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ በዋሻ ከሚኖር ከጳውሎስና ከዮልያኖስ ከእነርሱም ጋር ላሉ ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ "እስመ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን፤ መድኃኒቶሙ ለጻድቃን አሠርገዋ ለምድር በጽጌ ሮማን፤ ስብሐት ዋህድ ዘምስለ ምሕረት፤ በመስቀሉ ወበቃሉ አዕበዮሙ ለአበዊነ። ትርጉም፦ እርሱ የቅዱሳን ክብራቸው፤ የጻድቃን መድኃኒታቸው ነው፤ ምድርን በሮማን አበባ አስጌጣት፤ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ከምሕረት ጋር ያለ የወልድ ምስጋና በመስቀሉና በቃሉ አባቶቻችንን ከፍ ከፍ አደረጋቸው።
+ + +
❤ "ሰላም ለሕማሙ ወሰላም ለሞቱ። ሰላም ለገቦሁ ቅድስት ዘውኅዘ እምኔሃ ደመ ወማይ፡ፅሙር። አንቅዕተ ብዕል ወክብር። ሰላም ለግንዘቱ በዘጠብለልዎ ሰላም ለመቃብሩ ኀበ ቀበርዎ"። ትርጉም፦ ለሕማሙ ሰላምታ ይገባል፤ ለሞቱም ሰላምታ ይገባል። የሀብት (የብልጥግና) የክብር ምንጮች የኾነ ደምና ውሃ አንድነት (ተባብሮ) ከርሷ የፈሰሰ ለኾነች ለቅድስትጐኑ ሰላምታ ይገባል። በሚጠቀልሉት ገንዘብ ለኾነ ለግንዘቱ ሰላምታ ይገባል፤ በቀበሩት ዘንድ ላለ መቃብሩ ሰላምታ ይገባል። አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ አባ መቃርስ ዘሀገረ ቃው፡- ለዚህም ቅዱስ የዝንጉዎችን ምክር ተከትሎ ያልሔደ በኃጢአተኞችም ጎዳና ያልተጓዘ በዘባቾችም መቀመጫ ያልተቀመጠ የእግዚአብሔርን ሕግ መጠበቅ ፈቃዱ የሆነ እንጂ ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያነብ የሚያስተምር ብፁዕ ነው የሚለው የነቢይ ዳዊት ቃል ተፈጽሞለታል።
❤ ይህም አባ መቃርስ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቅ በመክሊት ነግዶ ዕጥፍ አድርጎ አትርፎአልና እግዚአብሔርም በእጆቹ ያደረጋቸውን ታላላቆች ድንቆች ተአምራት ስንቱን እናገራለን። ስለርሱም እንዲህ ተባለ እርሱ በአገረ ቃው ተሾሞ በወንበር ተቀምጦ ሕዝቡን በሚያስተምራቸው ጊዜ ዘወትር ያለቅሳል ከደቀ መዛሙርቶቻቸውም አንዱ በእግዚአብሔር ስም ካማላቸው በኋላ ለምን ሁልጊዜ እንደሚያለቅሱ በመሐላው አምሎ ጠየቃቸው፡፡ እርሳቸውም ስለመሐላቸው ፈርተው ነገሩት "ዘይት በብርሌ ውስጥ ጎልቶ እንደሚታይ የወገኖቼም ኃጢአት እንዲሁ በታየኝ ጊዜ አለቅሳለሁ" አሉት፡፡ በሌላም ጊዜ ጌታችን በመሠዊያው ላይ ሆኖ ተገልጦላቸው የእያንዳንዱን ሰው ኃጢአት መላእክት ሲያቀርቡለት አሳያቸው፡፡ ቀጥሎም "ሕዝቡን አስተምረህ ከክፋታቸው መልሳቸው" አላቸው፡፡ እሳቸውም "አይሰሙኝም" ቢሉት ጌታችንም "አስተምረሃቸው ከክፋታቸው ባይመለሱ ደማቸው በራሳቸው ላይ ይሆናል" አላቸው፡፡
❤ መናፍቁ ንጉሥ መርቅያኖስና ተከታዮቹ ክብር ይግባውና ጌታችንን "ሁለት ባሕርይ" በማለታቸው ጉባዔ ሠርተው አባቶች ሲሰበሰቡ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ አባ መቃርስን አስከትሎ በጉባዔው ተገኘ፡፡ አባ ዲዮስቆሮስና አባ መቃርስም ሁለት ባሕርይ ባዮችን አስተምረዋቸው እምቢ ቢሏቸው አውግዘውና እረግመው ከቤተ ክርስቲያን ለዩአቸው፡፡ ለመከራም የተዘጋጁ ሆነው ራሳቸውን አሳልፈው ሰጧቸው፡፡ ከሃዲው ንጉሥም ወደ ጋግራ ደሴት አጋዛቸው፡፡ አባ ዲዮስቆሮስም ለአባ መቃርስ "አንተ በእስክንድርያ ሀገር ሰማዕትነት ትቀበላለህ" በማለት ትንቢት ነግረዋቸው ከአንድ ነጋዴ ጋር ወደ እስክንድርያ ላኳቸው፡፡ እዚያም ሲደርሱ መናፍቁ ንጉሥ መርቅያኖስ አባ መቃርስን ይዞ ብዙ ካሠቃያቸው በኋላ ኩላሊታቸውን ብሎ ገደላቸውና የሰማዕትነታቸው ፍጻሜ ጥቅምት 27 ቀን ሆነ፡፡ ክርስቲያኖችም ሥጋቸውን ወስደው ከነቢዩ ኤልሳዕና ከመጥምቁ ዮሐንስ ሥጋ ጋር በአንድነት አኖሩት፡፡ ከሥጋቸውም ብዙ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛን በአባ መቃርስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት27 ስንክሳርና መዝገበ ቅዱሳን።
https://t.me/Eotcw
1 161
ሥቃይን አያያትም"፡፡
❤ የአቡነ መብዓ ጽዮን በዓለ ዕረፍታቸውም እጅግ አብዝተው በሚዘክሩበትና ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ታስቦ በሚውለው በመድኃኔዓለም ቀን ጥቅምት ሃያ ሰባት ነው፡፡ ከአባታችን አቡነ መብዓ ጽዮን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን!።
+ + +
❤ አቡነ ጽጌ ድንግል፡- ደራሲና ማኅሌታዊ ሲሆኑ የላመ የጣፈጠ ከመብላት ተቆጥበው ጥሬ ቆርጥመው 9 ዓመት ከቆዩ በኋላ የእመቤታችንን ስደት በጣም በጥልቀት የሚተርከውን "ማኅሌተ ጽጌን" የደረሱ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ውኃም በሦስት ቀን አንድ ጊዜ ብቻ ነበር የሚጠጡት፡፡
❤ አቡነ ጽጌ ድንግል ከደብረ ሐንታው ከአቡነ ገብረ ማርያም ጋር እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው እመቤታችንንና ፈጣሪ ልጇን በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ድርሰቱን በመዝሙረ ዳዊት መጠን 150 አድገው ደርሰዋል፡፡ አቡነ ገብረ ማርያምና አቡነ ጽጌ ድንግል ማኅሌተ ጽጌን በጥምረት ሊደርሱት የቻሉት አቡነ ገብረ ማርያም በወሎ ክፍለ ሀገር በወረኢሉ አውራጃ ልዩ ስሙ ደብረ ሐንታ በሚባለው ገዳም የሕግ መምሕር ሆነው በተሾሙበት ወቅት ነው፡፡ እነዚህም ሁለት ቅዱሳን የዘመነ ጽጌ የማኅሌት አገልግሎትን ሳይለያዩ በሰላምና በፍቅር በአንድነት አግልግለዋል፡፡ ይኸውም የሆነው እንዲህ ነው፡-
አንድ ዓመት አቡነ ገብረ ማርያም የክረምት መውጫና የዘመነ ጽጌ ዋዜማ በሆነው መስከረም 25 ቀን ከደብረ ሐንታ መጥተው ደብረ ብሥራት አቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም ገብተው ከመስከረም 25 ቀን እስከ ኅዳር 5 ቀን ያለውን የዘመነ ጽጌ የ40 ቀን አገልግሎት ከአቡነ ጽጌ ድንግል ጋር ፈጽመው ኅዳር 8 ቀን ወደ ደብራቸው ደብረ ሐንታ ይመለሳሉ፡፡ በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ አቡነ ጽጌ ድንግል ከገዳማቸው ከደብረ ብሥራት ተነሥተው ወደ ደብረ ሐንታ ሄደው እንዲሁ እንደ አቡነ ገብረ ማርያም 40ውን ቀን አግልግለው ይመለሳሉ፡፡ እነዚህ ሁለት ቅዱሳን እንደዚህ እያደረጉ በየተራ አንደኛው ወደ ሌላኛው ገዳም እየሄዱ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ በፍጹም ፍቅርና በትሕትና አብረው እመቤታችንን ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ ይኸውም በራሳቸው በአቡነ ገብረ ማርያም ገድል ላይ እና በአቡነ ዜና ማርቆስ ገድል ገጽ 72-73 ላይ በሰፊው ተጠቅሶ ይገኛል፡፡ የሁለቱ ድርሰታቸው የሆነው "ማኅሌተ ጽጌ" ድርሰት የእመቤታችንንና የልጇን የጌታችንን ሥጋዊ ስደት የሚገልጽ ሲሆን በጨማሪም ስደት የማይገባው አምላካችን ወደ አህጉራችን አፍሪካ ተሰዶ የሠራቸውን ድንቅ ድንቅ ተአምራትና የእመቤታችንን ንጽሕናዋን ቅድስናዋን አማላጅነቷን የሚያስረዳ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡
❤ አባ ጽጌ ድንግል ከማኅሌተ ጽጌ በተጨማሪ ሌሎች በርካታ አስደናቂ ድርሰቶችን ደርሰዋል፡፡ የጻድቁ ቅዱስ ዐፅማቸው፣ ታቦታቸውና የደረሷቸው በርካታ ድርሰቶች በገዳማቸው ደብረ ጽጌ ውስጥ በክብር ተጠብቀው ይገኛሉ፡፡ አምሃራ ሳይንት ቦረና ከአቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም የ5 ሰዓት የእግር መንገድ ከተሄደ በኋላ የሚገኘው ገዳማቸው "ደብረ ጽጌ" ከአንድ ወጥ ዓለት ተፈልፍሎ የተሠራው ሲሆን አሠራሩም እጅግ ድንቅ ነው፡፡
❤ የአቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም ከአቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ጋር የሚያገናኘው "የእግዜር ድልድይ" የተባለ አስገራሚ ታሪክ ያለው ድልድይ አለው፡፡ ሁለቱ ቅዱሳን በመንፈስ ተጠራርተው ለመገናኘት ቢያስቡም የወለቃ ወንዝ ሞልቶ በአካል ሳይገናኙ ቀሩ፡፡ በዚህም በጣም አዝነው ከወንዙ ወዲያና ወዲህ ሆነው ተላቅሰው አፈር ተራጭተው ወደየገዳማቸው ቢመለሱም ያ ተላቅሰው የተራጩት አፈር በተአምር ትልቅ ድልድይ ሆነ፡፡ ድልድዩን ሁለቱም በበዓታቸው ሆነው በመንፈስ አዩት፡፡ የበጎ ነገር ጠላት ሰይጣንም ይህንን ሲመለከት ድልድዩን በትልቅ ሹል ድንጋይ በስቶ ሊያፈርሰው ሲል አቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመንፈስ አዩትና ከጋስጫ ተነሥተው በደመና ተጭነው በመሄድ ሰይጣኑን በግዘፈ ሥጋ ገዝተው ያንን ድልድዩን አፈርስበታለሁ ያለውን ትልቅ ሹል ድንጋይ አሸክመውት በዓታቸው ጋስጫ ድረስ ወስደውታል፡፡ ያ ድንጋይ ዛሬ በጋስጫ አቡነ ጊዮርጊስ ገዳም ለመነኮሳቱ ደወል ሆኖ እያገለገለ ይኛል፡፡ ድልድዩም እስከ አሁን ድረስ ለአካባቢው ኢስላም ማኅበረሰብ ብቸኛው የወለቃ ወንዝ መሻገሪያቸው ሆኖ እያገለገላቸው ነው፡፡
ከአባታች አቡነ ጽጌ ድንግል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ይሳትፈን፣ በጸሎታቸው ይማረን! ምንጭ፦ገድለ አቡነ መባዓ ጽዮን፣ መዝገበ ቅዱሳን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ጥቅምት ፳፯ (27) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያውያኑ ጻድቃን ማኅሌተ ጽጌን ከአባ ገብረ ማርያም ጋር በመሆን ለደረሱት ለታላቁ አባት ለአቡነ ጽጌ ድንግል፣ ጌታችን በዕለተ አርብ የጠጣው መራራ ሐሞት እያሰብ ሁል ጊዜ አርብ አርብ ኮሶ ይጠጡና የመድኃኔዓለም ዝክር ይዘክሩ ለነበሩት ለታላቁ አባት ለአቡነ መብዓ ጽዮንና በዋሻ ውስጥ አርባ ዓመት ለኖሩ መና ሲመገቡ ለነበሩት ለታላቁ አባት ለአቡነ ጊዮርጊስ ዘጣና ለዕረፍታቸው በዓል መታሰቢያ በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አቡነ ጊዮርጊስ ዘጣና፦ አገራቸው ጣና ዘጌ ነው። በዋሻ ውስጥ አርባ ዘመን ሙሉ ዘግተው ሲኖሩ መና ከሰማይ እየወረደላቸው ውሃም በዋሻ ውስጥ ፈልቆላቸው ይኖሩ ነበር። አንድ ቀን መልአክ መጥቶ ምን ቢጋደሉ የጌታችንን ስጋውን በልተው ደሙን ካልጠጡ እንደ ማይድኑ ነገራቸው። በመልአኩም ትዕዛዝ መሰረት ከዋሻው ወጥተው ሊቆርቡ ቤተ ክርስቲያን ገቡ በቅዳሴም ላይ ሳሉ አንድ ድንቅ ምስጢር ተመለከቱ ይህም በጸሎተ ሐሙስ ዕለት ካህኑ "ሀበነ" ሲል ጌታችን በዕለተ አርብ እንተ ተሰቀለ ሆኖ ደሙ ሲፈስ የካህኑ እጅ በደም ተነክሮ በመንበሩ ቆሞ ቢያዩት በድንጋጤ ሳይቀሳቀሱ አርባ ዓመት ተኝተዋል ይህም በሰው አቆጣጠር በጌታችን ዘንድ ግን ምን ያይህል ጊዜ እንደ ሆነ እራሱ ባለቤቱ ያውቀዋል። በመጨረሻም ጻድቁ በዐረፉ ጊዜ መቃብራቸውን አራዊት ቆፍረውላቸው መነኰሳቱ ገንዘው ቀብረዋቸዋል። ታቦታቸው በጣና ይገኝል። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳንና ቅዱሳን በዓላት።
+ + +
❤ አቡነ መብዓ ጽዮን፡- አባታቸው ንቡረ ዕድ እናታቸው ደግሞ ሀብተ ጽዮን ይባላሉ፡፡ በሌላኛው ስማቸው ተክለ ማርያም ይባላሉ፡፡ ይህንንም ስም ያወጣችላቸው እመቤታችን ናት፡፡ እመቤታችንን ከሕፃንነታቸው ጀምረው እጅግ ይወዷት ነበር፡፡ ትንሽ ልጅ ሳሉ አንድ ካህን ወደ ሀገራቸው በእግድነት መጣና አባታቸው ሀብተ ጽዮን አሳደሩት፡፡
❤ እንግዳውም ካህን የእመቤታችንን ሥዕል ምስለ ፍቁር ወልዳን ይዞ ነበር፡፡ ሲተኛም በራስጌው ያኖራት ስለነበር በሀብተ ጽዮንም ቤት አድሮ ጠዋት ተነሥቶ ሲሄድ የእመቤታችንን ሥዕል በራስጌው እንዳኖራት እረስቶ ሄደ፡፡ ያንጊዜ ሕፃን የነበሩት አባ መብዓ ጽዮንም ሥዕሏን ወስደው ሳሟት፣ በእርሷም ደስ ተሰኙባት፡፡ ለሌላም ሰው አልሰጥም ብለው በአንገታቸው አሰሯት፡፡ ሀብተ ጽዮንም "ይህችን የእግዳው ካህን ንብረት የሆነች የእመቤታችንን ሥዕል ከቤት እንዳላስቀምጣት ኃጢአት ይሆንብኛል እንዳልሰጠውም ከየት አገኘዋለሁ" እያለ ሲቀጨነቅ ከዕለታት በአንደኛው ቀን ያንን እንግዳ አገኘው፡፡ ባገኘውም ጊዜ ከቤት የተዋትን የእመቤታችንን ሥዕል እንዲወስድ ነገረው፡፡ መጀመሪያ ሕፃን መብዓ ጽዮን እንዳገኛትና በጣም እንደወደዳት ለሌላ ሰውም አልሰጥም ብሎ በግድ ቀምቶ እንዳስቀመጣት ነገረው፡፡ እንግዳውም ይህን ሲሰማ "የሥዕሊቱ ባለቤት እርሷ የሕፃኑ እንድትሆን ፈቅዳለታለች፤ ከእኔ ዘንድ መሆኗን ፈቅዳ ቢሆንማ ኖሮ ባልተረሳችኝ ነበር ለዚያ ላገኛት ልጅህ የተገባች ናት" ካለው በኋላ እርስ በእርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጥተው ተለያዩ፡፡
❤ አቡነ መብዓ ጽዮን ዕድሜያቸው ከፍ ሲል ወላጆቻቸው ሚስት ሊድሩላቸው ሲሉ እርሳቸው ግን አላገባም ብለው የዚህን ዓለም ጣዕም ንቀው ነው የመነኑት፡፡ የምንኩስና ልብስ ከለበሱበት ጊዜ ጀምረው በበቅሎና በፈረስ ላይ ተቀምጠው አያውቁም፤ በአልጋም ሆነ በምንጣፍ ላይ አልተኙም ይልቁንም የአንድ ሰው ሸክም የሚያህል ትልቅ ድንጋይ በደረታቸው ተሸክመው ከአመድ ላይ ይተኙ ነበር እንጂ፡፡ ከሰንበት ቀናት ውጭ ሲቀመጡም ድንጋዩን በራሳቸው ላይ ይሸከሙታል፣ ሲሰግዱም በጀርባቸው ያዝሉት ነበር፡፡
❤ አባታችን ለቅዱስ ሥጋ ወደሙ እጅግ ትልቅ ክብር ስለነበራቸው የቆረበ ሰው ከቤተክርስቲያን ወጥቶ ሲሄድ እንቅፋት እንኳን ሲመታው ስለሥጋ ወደሙ ክብር ብለው እግሩ የደማበትን ሰው ደሙን ይጠጡት ነበር፣ ደሙ የፈሰሰበትንም አፈር ይልሱታል፡፡ ይህም የመድኃኔዓለምን ሥጋና ደም ከማክበራቸው የተነሣ ነው፡፡ ጻድቁ ጌታችን በዕለተ ዓርብ መራራ ሐሞት መጠጣቱን አስታውሰው ሁልጊዜ ዐርብ ዐርብ ኮሶ ይጠጡ ነበር፡፡ መድኃኔዓለምም በየጊዜው በሕፃን አምሳል ይገለጥላቸዋል፡፡ በዕለተ ዓርብም እንደተሰቀለ ሆኖ ይገለጥላቸው ነበር፡፡ ዳግመኛም ጌታችን ለአቡነ መባዓ ጽዮን በመሠዊያው ላይ በነጭ በግ አምሳል ይገለጥላቸው ነበር፡፡
❤ መከራ ሞቱን እያስታወሱ ሰውነታቸውን ይጎዱ እንደነበር በቅዱስ ገድላቸው ላይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡- "በተቀደሰች በዓርባ ጾምም የመድኃኔዓለምን ግርፋት እያሰበ ሰውነቱን በእጅጉ ገረፈ፡፡ ደሙ ከመሬት እስኪወርድ ድረስ ልቡንም አጥቶ ከምድር ላይ ወደቀ፡፡ የመድኃኔዓለምን መከራውን አስቦ እንደሞተም ሆነ፡፡ መድኃኔዓለምም ወደ እርሱ መጣና "ተነሥ እኔ ቁስልህን እፈውስሃለሁ" ብሎ የጀርባውን ቁስል ዳሰሰው፡፡ ምንም ሕማም እንዳላገኘውም ሆነ፡፡ መድኃኔዓለምም አባታችንን "በአንተው እጅ ትገደልን? እኔ እንኳ የተገደልኩት በአመፀኞች በአይሁድ እጅ ነው" አለው፡፡ በዚያችም ሰዓት ጌታ የመባዓ ጽዮንን ከንፈሮቹን ይዞ ሦስት ጊዜ እፍ አለበትና "የከበረ ትንፋሼም ከትንፋስህ ጋራ ይጨመር፣ ሥጋህም ከነፍስህ ጋራ የከበረ ይሁን› አለው፡፡ "አንተ በላዩ እፍ ያልህበትም የተቀደሰና የከበረ ይሁን" አለው"፡፡
❤ ጌታችን ለአቡነ መብዓ ጽዮን የወርቅ በትር ሰጥቷቸው በእርሷ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጡባት ነበር፡፡ መቋሚያዋም እሳቸው ካረፉ በኋላ የሚሞተውን ሰው እየለየች ትናገር ነበር፡፡ አባታችን እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም በመልአክ ተጥቀው ተወስደው የሥላሴን መንበር ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር አጥነዋል፡፡ ጌታችን ከተረገመችና ከተወገዘች ዕፅ ጋር በተገናኘ ለአቡነ ዘርዐ ቡሩክና ለአቡነ መብዓ ጽዮን ልዩ ምሥጢር እንደነገራቸው በሁለቱም ቅዱሳን ገድላት ላይ በሰፊው ተጽፏል፡፡
❤ አቡነ መብዓ ጽዮን በይበልጥ የሚታወቁት ሁልጊዜ ወር በገባ በሃያ ሰባት መድኃኔዓለምን አብልጠው በመዘከራቸው ነው፡፡ በዚህም ምክንያት "እንደ አንተም በየወሩ በሃያ ሰባት የሞቴ መታሰቢያ ለሚያደርግ ነፍሳትን ከሲኦል አወጣለታለሁ" የሚል ድንቅ ቃልኪዳን ከጌታችን ተቀብለውበታል፡፡ ይኸውም የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ የሚያድርግ ቢኖር ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ሲነግራቸው ነው፡፡ ቅዱስ አባታችን "ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ! በዓልህን አደርግ ዘንድ አንተ የምትወደውን ግለጥልኝ" ብለው ጌታችንን ሲጠይቁት እርሱም "የሞቴን መታሰቢያ ያደረገ እንደ እኔ ነፍሳትን ከደይን ያወጣል፣ "በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን ይሠራል፣ ከዚያም የበለጠ ይሠራል" ብዬ በወንጌሌ እንደተናገርሁ" አላቸው"፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን ለልጆቻቸው እንዲህ ብለው መከሯቸው፡- "ክርስቲያኖች ሁሉ የፈጣሪያችንን የመድኃኔዓለም ክርስቶስን የመታሰቢያ በዓሉን እናድርግ፡፡ የአባቶቻችን የሐዋርያት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የመላእክት መታሰቢያቸው ባረፉበት በተሾሙበት ቀን ይከበራል፡፡ እነርሱን የፈጠራቸው እርሱ መድኃኔዓለም ነው፣ ያከበራቸው፣ ከፍ ከፍ ያደረጋቸው፣ ስማቸውን ለጠራ መታሰቢያቸውን ያደረገ እንደሚድን ቃልኪዳን የሰጣቸው እርሱ ነው፡፡ የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ ያደረገ ግን የተኮነኑ ነፍሳትን ከደይን ያወጣል፣ በሞቱም ጊዜ
