ሰዋስው ☘☘☘☘
Відкрити в Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
Показати більше1 161
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
1 161
#ድል_አለ_በስምህ
በስልክ የተቀዳ
ድል አለ በስምህ
ድል አለ በቃልህ /2/
ተራራው ይናዳል አማኑኤል ስልህ
ባህር ይከፈላል መድሀኔዓለም ስልህ
ቃዴስን ታላቁን በርሀ
አለፍነው ሳንጠማ ውሀ
ፈርኦንን ከባህር የጣለው
ጌታዬ የጸና ስምህ ነው
አምላኬ የጸና ስምህ ነው
#አዝ
በእልልታ ቢፈርስ እያረኮ
ጠላትም ቢወድቅ ተማርኮ
ቢሰጠን ለእኛ ከተማው
የሆነው ሁሉ ካንተ ነው/2/
#አዝ
ከክፋት ሁሉ ብናመልጥ
የማረ ውሀ ቢጣፍጥ
ብንበላ መና ከሰማይ
ስለ ሆንክ ነው አ ዶናይ
ስለ ሆንክ ነው ሁሉን ቻይ
#አዝ
የቆምነው ዛሬ በህይወት
ሰምህን አድርገን ነው ጉልበት
ከሜዳ ተጠርተን ብንነግስ
ሆነኸን ነው ክብርና ሞገስ
#ሼር
https://t.me/EOTCWW
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ ሰኔ ፳፯ (27) ቀን።
❤ እንኳን ከሰባ ሁለቱ አርድእት አንዱ ለሆነው ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን ላጠመቀው ለሐዋርያው ቅዱስ ሐናንያ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል፣ ሰንደላት ከሚባል አገር ለሆነ ለቅዱስ ቶማስ፣ ከእርሱም ጋር አብረው ሰማዕትነት ለተቀበሉ ለሰባት መቶ ወንዶችና ዘጠኝ ሴቶች ለዕረፍታቸው መታሰቢያ በዓል፣ ጌታችን ስለ እርሱ ቅዱስ ሉቃስ በጻፈው በቅዱስ ወንጌል ለተናገረለት ለድኀው ለቅዱስ አልዓዛርም ለመታሰቢያው በዓሉና ለመድኃኔዓለም ለስቅለቱ ለወራዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከማማስና ከሲላስ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ ሐዋርያው ቅዱስ ሐናንያ፦ ይህንንም ቅዱስ ሐዋርያት በደማስቆ ከተማ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። በውስጧም ሕይወት ሰጭ የወንጌልን ትምህርት አስተማረ ዳግመኛም በቤተ ገብርኤል ውስጥ ሰብኮ ክብር ይግባውና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሆነች የቀናች ሃይማኖት ብዙዎቹን መለሳቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው እውነተኛውንም የሃይማኖት ብርሃን አበራላቸው።
❤ ይህም ሐናንያ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስን ይቅር ባይ ጌታችን በቸርነቱ ከክህደቱ በጠራውና ምርጥ ዕቃ በአደረገው ጊዜ ያጠመቀው እጁንም በራሱ ላይና በዐይኖቹ ላይ ጭኖ ያዳነው እርሱ ነው።
❤ ጌታችንም በእጆቹ ታላላቅ ድንቆችንና ተአምራቶችን አደረገ በስብከቱም ብዙዎች አሕዛብ አመኑ ከአይሁድም ብዙዎቹን ክብር ይግባውና ክርስቶስን ወደ ማመን መለሳቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ዐመፀኛው መኰንን ሉክያኖስ ይዞ ታላላቅና አስጨናቂ ሥቃይን አሠቃየው ጎኖቹንም ሠንጥቆ በእሳት መብራቶች አቃጠለው ከዚህም በኋላ ከከተማው አውጥተው በደንጊያ እንዲወግሩት አዘዘ በዚያም ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እጅ ነፍሱን ሰጠ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሐናንያ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ ሰንደላት ከሚባል አገር የሆነው ሰማዕቱ ቅዱስ ቶማስ፦ ይህም ቅዱስ ዕድሜው ዐሥራ አንድ ዓመት በሆነው ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ወደ መንኰንኑ ሔዶ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይታመን ዘንድ አዘዘው።
❤ ያን ጊዜም ተነሥቶ የገመድ አለንጋ ይዞ ብቻውን ወደ እስክንድርያ አገር ሔደ በመኰንኑም ፊት ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ። መኰንኑም "ለአማልክት ሠዋ" አለው ጸሐፊውም ሊያደርገው ቃል ኪዳን ገባለት ቅዱስ ቶማስም ተቆጥቶ ያቺን አለንጋ አውጥቶ መኰንኑን ብዙ ግርፋት ገረፈው የመኰንኑን ሎሌዎችም ይዘው ጽኑ ሥቃይን አሠቃዩት ሥጋውንም በብረት መጋዝ ሠነጠቁ ክብር ይግባውና ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ርዳታ ለመነ ወዲያውኑም መልአኩን ልኮ አዳነው።
❤ ከዚህ በኋላ በእሥር ቤት አሠሩት የወህኒ ቤቱ ጠባቂም ስለ ታመመው ልጁ ለመነው እርሱም ያንን የገመድ አለንጋ ሰጠውና "ይህን አለንጋ በልጅህ ላይ አኑር" አለው እንዲሁም አደረገ። ያን ጊዜም ልጁ በእግዚአብሔር ኃይል ዳነ። መኰንኑም በሰማ ጊዜ ወደርሱ አቅርቦ "ለአማልክት ሠዋ" አለው ቅዱስ ቶማስም "በፊትህ ዕሠዋ ዘንድ ና እንሒድ" ብሎ መለሰለት። መኰንኑም ዕውነት መስሎት ደስ አለው ወደ ጣዖቶቹ ቤትም ወሰደው ያን ጊዜ ቅዱስ ቶማስ ጣዖታቱን ያጠፋቸው ዘንድ ወደ ጌታችን ለመነ። ወዲያውኑ ሁሉም ጣዖታት ተሰባበሩ ሰይጣኑም በመኰንኑ ላይ ተቀመጠ "ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ብሎ እስሚታመን ድረስ አነቀው።
❤ አሕዛብም ይህንን ድንቅ ነገር አይተው እጅግ አደነቁ "ክብር ይግባውና ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም" እያሉም ጮኹ በእርሱም አመኑ። ያላመኑ ግን በጨለማ ቤት ውስጥ አኖሩት ያለ መብልና ያለ መጠጥ ከብዙ ሥቃይም የተነሣ ከአፉ ደም እየፈሰሰ ዐሥራ አምስት ቀን በዚያ ተቀመጠ የእግዚአብሔር መልአክም ወርዶ ፈወሰው። አንዲት ሴት ዕውር ልጅ ነበራት ከዚያም ደም ወስዳ የልጅዋን ዐይን አስነካችው ወዲያውኑም አየ።
❤ ቅዱስ ቶማስንም ከወህኒ ቤት አውጥተው ሴት አንበሳ ሰደዱበት ወደርሱም በደረሰች ጊዜ እግሮቹን ላሰች ሰገደችለትም። ዳግመኛም በብረት መንደልቶ አፋ ላይ ደበደቡት በዚያን ጊዜም በሥቃይ ውስጥ ከእርሱ ጋራ ከበንደላ አገር ቅዱስ በብኑዳ ከበልኪም አገር ቅዱስ ሙሴ ነበሩ። እርስ በርሳቸው አንዱ አንዱን ያጽናናው ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ ቅባትና የነዳጅ ድፍድፍ አፍልተው በቅዱስ ቶማስ ራስ ላይ ደፉት ነገር ግን ምንም ምን ጉዳት አልደረሰበትም። እንደገናም አባለ ዘሩን ቈርጠው በአውድማ ውስጥ አበራዩት ደግመውም ታላቅ ደንጊያ በአንገቱ ላይ ሰቅለው አሠቃዩት።
❤ ከማሠቃየቱ የተነሣ በደከመው ጊዜ መኰንኑ አርያኖስ ወደ እንዴናው ከተማ ሊወስደው ይዞት ተነሣ ጣው ወደሚባል አገርም በደረሱ ጊዜ የቅዱስ ቶማስን ራስ ቆረጡት በዚያም ምስክርነቱን ፈጸሙ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ ከእርሱ ጋራ መከራ ተቀበለው የሞቱ ሰባት መቶ ወንዶችና ዘጠኝ ሴቶችም እርሱ ሥቃይ በተቀበለበት ወራት የሰማዕትነት እክሊል ተቀበሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን ሰማዕታት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 27 ሰንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ለከ ሐናንያ ኵኑን። በዝብጠተ ድንቡስ ክቡድ እንተ አፍአሁ ኀፂን። ዘእንበለ እድ መጺአ እምኀበ ሀሎ መካን። ይቀጥቀጥ ከመ ልሕኵት ርእስ ፀርየ ሰይጣን። ውስተ ክሣድከ ዘተአሥረ ዕብን"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 27።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦"ነዳይ፡ወቊሱል አነ። መድኃኔ ገጽየ እግዚአብሔር ተወክፈኒ። እሴብሕ ለስመ አምላኪየ በማኅሌት"። መዝ 68፥29-30። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 12፥28-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 2፥9-27 እና የሐዋ ሥራ 9፥10-20። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 16፥19-31። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዳሴ ነው። መልካም የሐዋርያው የቅዱስ ሐናንያ የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
መዝሙር ዘሰንበት
በ2 ሀሌታ-
ደምፀ እገሪሁ ለዝናም፤ ሶበ ይገስስ ዝናመ ይፀግቡ ርኁባን፤ ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ሶበ ይዘንም ዝናም ይትፌሥሑ ነዳያን ፤ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ወሠርዓ ሠንበተ ለሰብዐ ዕረፍተ፤ ማ፦ ደምፀ እገሪሁ ለዝናም፤ ደምፀ እገሪሁ ለዝናም
አመላለስ፦
ደምፀ እገሪሁ ለዝናም/2/
ደምፀ እገሪሁ ለዝናም/4/
https://t.me/Eotcw
#ይቀላቀሉ & #ለወዳጅዎ_ሼር_ያርጉ
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ እንኳን ለዘመነ ክረምት መግቢያ ለሚታሰብበት ለመጀመሪያ ዕለተ ሰንበት (እሑድ) እግዚአብሔር አምላክ በሰላምና በጤና አደረን።
+ + +
❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ፪ "ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ሶበ ይዘንም ዝናም ይጸግቡ ርኁባን፤ ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ይትፌሥሑ ነዳያን፤ አዝ፣ ወሠርዐ ሰንበት ለሰብእ ዕረፍት ደምፀ እገሪሁ ለዝናም ደምፀ እገሪሁ ለዝናም"። ትርጉም፦ የዝናም ኮቴው ተሰማ ዝናብ በሚዘንብ ጊዜ ረኀብተኞች ይጠግባሉ፤ ዝናብ በዘነበ ጊዜ ድኆዎች ደስ ይሰኛሉ፤ ሰንበትን ለሰው ዕረፍት ፈጠረ የዝናም ኮቴው ተሰማ። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ ዘመነ ክረምት፦ "ክረምት" የሚለው ቃል ከርመ፣ ከረመ ሰነበተ ኖረ ከሚለው የግእዝ ቃል የተገኘ ሲሆን ሁለት ትርጉም አለው የመጀመሪያው ብዙ ዓመት መቆየትን፣ መሰንበትንና ወቅትን ዘመንን የሚያመለክት ሊኾን ሁለተኛም ትርጓሜ መዝነምን መፍሰስን የሚያመለክት ነው።
❤ አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመዝገበ ቃላቸው ላይ ስለክረምት ሲያብራሩ "ክረምት በቁሙ ዝናም የዝናም ወራት፤ በጸደይና በመጸው መካከል ያለ ክፍለ ዓመት፤ ከሰኔ 25 እስከ መስከረም 25 ዓመት ድረስ ያለ ወቅት ነው"። ብለው ገልጸውታል። ስለዚህ ክረምት ወርኃ ዝናም፣ ወርኃ ነጎድጓድ፣ ዘመነ ባሕር፣ ዘመነ ነጎድጓድ፣ ዘመነ አፍላግ፣ ዘመነ ጠል፣ ዘመነ ደመና፣ ዘመነ መብረቅ ማለት ነው።
❤ በዘመነ ከረምት ውኃ ይሠለጥናል፣ ዝናም አፈርን ያጥባል፣ እሳትን ያጠፋል። ሆኖም ግን በብሩህነቱ ከእሳት፤ በቀዝቃዛነቱ ነፍስ፤ በእርጥብነቱ ከመሬት ጋር አስማምቶ ከሦስቱ ባሕርያት ጋር ይኖራል። ይህ ወቅት ስለ ሥነ ፍጥረት መግቦት ዘርዘር ባለ መልኩ የሚነገርበት ወቅት ስለሆነ ፍጡርን ከፈጣሪ ምግብን ከመጋቢ ለይቶ የሚያሳይና የሚያሳውቅ ወቅት ነው። ወርኃ ክረምት የዝናም፣ የዘርና የአዝመራ ወቅት በመሆኑ ምድር በጠልና በዝናም ትረካለች።
❤ ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድ ሲዘምር በድጓው ላይ "አንተ ኬንያሁ ለኵሉ ፍጥረት አንተ ሠራዕከ ክረምተ ወወሀብከ ለዝናማት ወሠራዕከ መፀወ ወወሀብከ ለጽጌያት። የፍረት ሁሉ ተጠባቢው አንተ ነህ፤ አንተ ክረምትን ሠራህ የሠራኸውንም ክረምት ለዝናም ሰጠኽ፤ አንተ መፀውን ሠራህ የሠራኸውም መፀው ለአበቦችም ሰጠኽ"። ሲል አመስጥሯል። ምንጭ፦ ኆኅተ ስብከት ዘቅዱስ ያሬድ ቅጽ ፪ ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ዘይገለብቦ ለሰማይ በደመና። ወያስተዴሉ ክረምተ ለምድር። ዘያበቊል ሣዕረ ውስተ አድባር"። መዝ 146፥8። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 15፥33-51፣ ያዕ 5፥16-ፍ.ም እና የሐዋ ሥራ 27፥11-21። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 8፥1-22። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱስ ኤጲፋንዮስ ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ገብርኤል በዓል፣ የነቢዩ የኢያሱ የዕረፍት በዓል፣ የክረምት መግቢያ (ሰንበት)ና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ ሰኔ ፳፮ (26) ቀን።
❤ እንኳን ለከበረ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ገብርኤል ለበዓሉ መታሰቢያ እንዲሁም ኔቅሎን በሚባል አገር በፍዩም ገዳም ቤተ ክርስቲያኑ ለተከበረችበትና ለታላቁ ነቢይና መስፍን ለነቢያት አለቃ ለሙሴ ደቀ መዝሙር ለነዌ ልጅ ለቅዱስ ኢያሱ ለዕረፍቱ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። ረድኤትና፡በረከትን፡ያሳትፈን።
+ + +
❤ በዚች ቀን የከበረ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤል በዓሉ ነው እንዲሁም ኔቅሎን በሚባል አገር በፍዩም ገዳም ቤተ ክርስቲያኑ የተከበረችበት ነው። በውስጧም ከቤተ ክርስቲያንዋ የጣራ ዕንጨት ብዙ ተአምር ይገለጽ ነበር ጽጋብ በሚሆንባት በዚያች ዓመት ውኃ ይንጠፈጠፋል ረሀብ ከሆነ ግን ላብ እንኳ አይታይም ነበር።
❤ የዚህ የከበረ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ገብርኤል ተአምራቶቹ ብዙዎች ናቸው። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ገብርኤል በአማላጅነቱ ይማረን ረድኤቱም ከእኛ ጋራ ትሁን ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ የነዌ ልጅ ነቢዩና መስፍን ቅዱስ ኢያሱ፦ ይህም ከታናሽነቱ ጀምሮ ለሙሴ አንገቱን ዝቅ አድርጎ የሚታዘዝ ፍጹም ትሑት ሆነ ስለዚህም በሙሴ ላይ ያደረ መንፈስ ቅዱስ አደረበት። ነቢዩ ሙሴም ከአረፈ በኋላ በእግዚአብሔር ትእዛዝ የእስራኤልን ሕዝብ ተረከባቸው።
❤ እግዚአብሔርም ኢያሱን እንዲህ አለው "ከሙሴ ጋራ እንደኖርሁ ከአንተም ጋራ እኖራለሁ ጽና በርታ ለባለሟሌ ሙሴ ያዘዝሁትን ሕጌን ጠብቅ ከእርሱም ፈቀቅ አትበል ሕጉንም ትጠብቀውና በሱም ትጸና ዘንድ በውስጡም የተጻፈውን ታደርገው ዘንድ በቀንም በሌሊትም አንደበትህ ማንበብን አያቋርጥ"። ኢያሱም ሌቡ ጸና ሰላዮችንም ወደ ኢያሪኮ ላከ ሀገሪቱንም አይተው ሲመለሱ የኢያሪኮ ሰዎች አዩአቸው ሰላዮችም እንደሆኑ አውቀው ተከተሏቸው። እነርሱም ረዓብ በሚሏት አመንዝራ ሴት ዘንድ ተሸሸጉ እርሷም ሠወረቻቸው እነርሱም በሚመጡ ጊዜ ከቤተ ሰቦቿና ከዘመዶቿ ጋራ እንደሚያድኗት ቃል ገቡላት በደኅናም ሸኘቻቸው።
❤ ከዚህም በኋላ ኢያሱ ሕዝቡን ሁሉ የዮርዳኖስን ወንዝ አሻገረ ካህናቱ የእግዚአብሔርን ታቦት ሕግ ተሸክመው በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ቆመው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እስከሚሻገሩ ድረስ የወንዙን ውኃ እግዚአብሔር እንደ ግድግዳ አቁሞት ነበርና።
❤ ከዚህም በኋላ ደግሞ በግንብ የተከበበች ኢያሪኮን ሰባት ቀን ዞራት ከእርሱም ጋራ የልዑል ታቦተ ሕጉ ነበረች ቅጽሮቿንም አፈረሰ በውሷም የሚኖሩ አሕዛብን ሁሉ ከንጉሥዋ ጋር ገደለ ሁሉንም አጠፋቸው። አሕዛብ ሁሉ የእስራኤልን ልጆች ፈሩአቸው ከመፍራታቸውም ጽናት የተነሣ የገባዖን ሰዎች ተንኰል አደረጉ ስንቃቸውን ሰንቀውና አዘጋጅተው መጡ አሮጌ አቁማዶቻቸውን ያረጁና የተቀደዱ የተጠቀሙም የወይን ረዋቶችን በትክሻቸው ተሸክሙ። ጫማቸውም ያረጀና የተተበተበ ነበር። ለስንቅም የያዙት እንጀራ የደረቀና የሻገተ ነበር።
❤ ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤል ወደ ገልገላ መጥተው "እኛ ከሩቅ አገር መጥተናል አሁንም ለእኛ ማሉልን" አሏቸው። የእስራኤልም ልጆች ኤዎያውያንን "ከእናንተ ጋራ እንዴት መሐሊን እንማማላለን አሁንም በአቅራቢያችን ትኖሩ እንደሆነ ተጠንቀቁ" አሏቸው። ኢያሱንም "እኛ ከሩቅ አገር የመጣን ባሮችህ ነን" አሉት እርሱም "ከወዴት ናችሁ ከወዴትስ አገር መጣችሁ" አላቸው። እነርሱም "እኛ ባሮችህ በፈጣሪህ እግዚአብሔር ስም እጅግ ከራቀ አገር መጣን በግብጻውያን ያደረገውን ሁሉ በዮርዳኖስ ማዶ በሚኖሩ በሁሉቱ በአሞሬዎን ነገሥታትም ያደረገውን ሁሉ ሰምተን መጥተናል" አሉት።
❤ "የአገራችን ሰዎች ሁሉና አለቆቻችን ለመንገድ ስንቅ ያዙ ትቀበሏቸውም ዘንድ ሒዱ እኛ ባሮቻችን ነን አሁንም ለእኛ ማሉልን በሉአቸው" አሉን። "እነሆ ወደ እናንተ እንመጣ ዘንድ ከቤታችን በወጣንበት ቀን ይህ እንጀራችን ትኩስ ነበር አሁን ግን ሻግቷል ደርቋልም ይህም የወይን ረዋት አዲስ ሳለ መላንበት አሁን ግን ተራቁቷል አርጅቶም ተቀድዷል መንገዳችን እጅግ የራቀ ነውና ይህም ልብሳችን ይህም ጫማችን አርጅቷል" አሏቸው።
❤ መኳንንቱንም ስንቃቸውን ተቀብለው አዩ የእግዚአብሔርንም ቃል አልጠየቁም ኢያሱም ከነሱ ጋራ ሰላምን አደረገ ሊያድናቸውም ከእነርሱ ጋራ ቃል ኪዳን አደረገ የሕዝቡም አለቆች ማሉላቸው። ከሦስት ቀን በኋላም እስራኤል ከቅርብ እንደሆኑ ሰሙ። ኢያሱም በቅርብ እንደሆኑ በሰማ ጊዜ "በሽንገላ ለምን ወደእኛ መጣችሁ አሁንም እግዚአብሔር ቤትና ለእኛ ባሮች ትሆናላችሁ" አላቸው።
❤ የአሞሬዎን ነገሥታትም የገባዖን ሰዎች ሔደው ለእስራኤልና ለኢያሱ እንደ ተገዙ በሰሙ ጊዜ እነዚህ አምስቱ የኢየሩሳሌም ንጉሥ፣ የኬሮሮን ንጉሥ፣ የኢያሪሞት ንጉሥ፣ የለኪሶን ንጉሥና የአዶላም ንጉሥ ተሰብስበው ዘመቱ መጥተውም ገባዖንን ከበቡአት ሊዋጉም ጀመሩ።
❤ የገባዖን ሰዎችን በገልገላ ውስጥ ወደ እስራኤል ሰፈር ወደ ኢያሱ ልከው "ባሮችህን ለመርዳት እጅህ አትስነፍ ከተራሮች ላይ የሚኖሩ የአሞሬዎን ነገሥታት ሁሉ ተሰብስበውብናልና ወደ እኛ መጥተህ ርዳን ፈጥነህ አድነንም" አሉ። ኢያሱም ከጌልገላ ወጣ ሰልፈኞችም የሆኑ ሕዝብ ሁሉ ከእርሱ ጋር ነበሩ። እግዚአብሔርም ኢያሱን አለው "በእጅህ እጥላቸዋለሁና በፊታችሁም አንድ ስንኳ የሚቀር የለምና አትፍሯቸው" አለው ኢያሱም ሲገሠግሥ አድሮ ድንገት በሌሊት ደረሰባቸው።
❤ እግዚአብሔርም ከእስራኤል ፊት የተነሣ አስደነገጣቸው ኢያሱም ብርቱ ጥፋትን አጠፋቸው ከእርሱም ወደ ቢቶሮን ቊልቊለት በሸሹትም እግዚአብሔር የበረድ ድንጋይ ከሰማ አውርዶ ጨረሳቸው። የእስራኤል ልጆች በጦራቸው ከገደሏቸው በደንጊያ በረዶ የሞቱ በዙ። ያንጊዜም እግዚአብሔር አሞሬዎንን በእስራኤል ልጆች እጅ አሳልፎ በሰጣቸው ጊዜ ኢያሱ ፀሐይ በገባዖን ጨረቃም በኤሎም ቈላ ትቁም ብሎ ከእግዚአብሔር ጋር ተነጋገረ ፀሐይና ጨረቃም ቆሙ። ጠላቶችንም ሁሉንም አጠፋቸው ከእነርሱም የቀረ የለም።
❤ ከዚህም በኋላ ለእስራኤል ልጆች ሁሉ ርስትን አካፈላቸው ያለ ዕውቀት በስሕተት ሰው የገደለ በውስጡ ይማጠን ዘንድ ሰባት መማጸኛ ከተሞችን እግዚአብሔር እንደ አዘዘው ሠራ።
❤ ዕድሜውም መቶ ሃያ በሆነው ጊዜ የእስራኤልን ልጆች ሰበሰባቸው የኦሪትን ሕግ እንዲጠብቁ በአምኮተ እግዚአብሔርም እንዲጸኑ ትእዛዞቹንም እንዳይተላለፋ አዘዛቸው። እንዲህም አላቸው "እርሱ ፈጣሪያችን ቀናተኛ ነውና ጣዖት ብታመልኩ ያጠፋችኋል ሕጉን ብትጠብቁ ግን የበረከት ልጆች ትሆናላችሁ። ከዚህም በኋላ ሰኔ 26 ቀን በሰላም ዐረፈ ያዕቆብ ከኤሞርልጆች በመቶ በጎች በገዛው ናብሎስ በሚባል ቦታም ተቀበረ ሠላሳ ቀኖችም ያህል ታላቅ ልቅሶ አለቀሱለት። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩና በመስፍኑ ቅዱስ ኢያሱ በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 26 ሰንክሳር።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
መጋቤ ስብሐት ዓለሙ አጋ ሰዋስወ ብርሃን ይመጣሉ።
ሰንበት ትምህርት ቤታችን ለ፲፪ኛ ዙር ለ፰ ወራት የበገና መሠረታዊ ትምህርት ሲያሰለጥላቸው የቆያቸውን ተማሪዎች የፊታችን እሑድ በ26-10-2014 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ በመንፈሳዊ ኮሌጅ አዳራሽ ያስመርቃል። ኹላችኹም እንድትገኙልን፣ ሌሎችንም እንድትጠሩልን በልዑል እግዚአብሔር ስም እንጠይቃለን።
የሰዋስወ ብርሃን ቅዱስ ጳውሎስ ገዳም ሰንበት ትምህርት ቤት
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን" ❤
❤ ሰኔ ፳፬ (24) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ አስቀድሞ ገዳይ ቀማኛ፣ ዘማዊና ያላመኑ ለነበሩ በንስሐ ተመልሰው በአባ መቃርስ እጅ ከተጠመቁ ከመነኰሱ በኋላ በግብፅ በአስቆጥስ ገዳም ታላቅ ተጋድሎ አድርገው በሰማዕነት ለዐረፉ ለአባ ሙሴ ጸሊም ለዕረፍቱ በዓል መታሰቢያ፣ ለአባታችን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖትና ለእናታች ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ለወራዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ አባ ሙሴ ጸሊም፦ ሰዎች ከገድሉ የተነሣ ይህን ቅዱስ ያደንቁታል እርሱ አስቀድሞ መንግሥተ ሰማያትን ገፍቷት ነበርና እርሱ በሥጋው ጠንካራ በሥራውም ኃይለኛ ነበር ይበላና ይጠጣ፣ ይቀማና ያመነዝር ነበር ይገድልም ነበር ማንም ሊቋቋመው አይችልም ነበር። አንድ በግ በአንድ ጊዜ ጨርሶ እንደሚበላና አንድ ፊቀን ወይን ጠጅ እንደ ሚጠጣ ስለ እርሱ ተነግሮአል። እርሱም ፀሐይን ለሚያመልኩ ሰዎች አገልጋይ ነበር ብዙ ጊዜም ወደ ፀሐይ እያንጋጠጠ "ፀሐይ ሆይ አንተ አምላክ ከሆንክ አነጋግረኝ" ይል ነበር ደግሞም በልቡ "የማላውቅህ ሆይ ራስህን አሳውቀኝ" ይል ነበር።
❤ ከዚህም በኋላ በአስቄጥስ ገዳም ያሉ መነኰሳት እግዚአብሔርን ያውቁታል ያዩታልም እያሉ ሲነጋገሩ ሰዎችን ሰማቸው። ያን ጊዜም ተነሣ ሰይፉንም ታጥቆ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ በደረሰም ጊዜ አባ ኤስድሮስን አገኘው። አባ ኤስድሮስም ፈራው ሙሴ ጸሊምም "እውነተኛውን አምላክ ታሳውቁኝና ታስረዱኝ ዘንድ ወደ እናንተ መጣሁ" አለው። አባ ኤስድሮስም ወደ አባ መቃርስ ወስዶ አገናኘው። እርሱም ተቀብሎ ሃይማኖትን አስተማረው እንዲለህም አለው "ታግሠህ የማስተምርህን ከጠበቅህ እግዚአብሔርን ታየዋለህ።
❤ ከዚህም በኋላ የክርስትና ጥምቀትን አጥምቆ አመነኰሰው ከብዙዎች ገድለኞች ቅዱሳን ይልቅ ብዙና ጽኑዕ ገድልን መጋደል ጀመረ። ሰይጣንም ቀድሞ ሲሠራው በነበረ በመብሉና በመጠጡ መዝሙቱም ይዋጋው ነበረ እርሱም በራሱ ላይ የሚደርስበትን ሁሉ ለአባ ኤስድሮስ ይነግረው ነበር እርሱም አጽናንቶ ሊሠራው የሚገባውን ያስተምረው ነበር።
❤ ከገድሉ ብዛትም የተነሣ አረጋውያን መነኰሳት በሚተኙ ጊዜ ቤቶቻቸውን በመዞር ውኃ መቅጃዎችን ወስዶ ውኃ መልቶ በየቤታቸው ደጃፍ ያኖር ነበር። ውኃው ከእርሱ ሩቅ ነበረና እንዲም እያደረገ በመጋደል በብዙ ዘመናት ኖረ። ሰይጣንም በእርሱ ቀንቶ በእግሩ ውስጥ አስጨናቂ የሆነ አመታትን መታው ተኝቶም እየተጨነቀ ብዙ ቀን ታመመ።
❤ ከዚህም በኋላ የመታውና የሚፈታተነው ሰይጣን እንደሆነ ዐውቆ ሥጋው በእሳት ተለብልቦ እንደ ደረቀ ዕንጨት እስቲሆን ድረስ ተጋድሎውንና አገልግሎቱን አበዛ። እግዚአብሔርም ትዕግሥቱን አይቶ ከደዌው ፈወሰው የሰይጣንንም ጦር ከእርሱ አራቀለት የመንፈስም ጸጋ አደረበት ወደርሱም አምስት መቶ ወንድሞች መነኰሳት ተሰበሰቡ በእነርሱም ላይ አበ ምኔት ሆነ።
❤ ከዚህም በኋላ ቅስና ሊሾሙት መረጡት በቤተ መቅደስም ሊቀ ጳጳሳቱ ዘንድ በአቆሙት ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱም አልፈቀደም ነበር አረጋውያኑንም "ይህን ጠቋራ ለምን አመጣችሁት ከዚህ አውጡት" አላቸው እነርሱም "መልክህ የከፋ ጠቋራ ሆይ መካም አደረጉብህ" በማለት ራሱን እየገሠጸ ወጣ ከዚህ በኋላ ዳግመኛ ሊቀ ጳጳሳቱ ጠራውና እጁን በላዩ ጭኖ ቅስና ሾመው እንዲህም አለው "ሙሴ ሆይ እነሆ በውስጥም በውጭም ሁለመናህ ነጭ ሆነ"።
❤ በአንዲትም ዕለት ቅዱሳን አረጋውያን ወደርሱ መጡ በእርሱም ዘንድ ውኃ አልነበረም እርሱም ከበዓቱ ብዙ ጊዜ ወጣ ገባ ይል ነበር ከዚህም በኋላም ብዙ ዝናም ዘንሞ ጒድጓዶችን ሁሉ ሞላ። አረጋውያንም ለምን ብዙ ጊዜ ወጣ ገባ ትል ነበር ብለው ጠየቁት እርሱም "እግዚአብሔርን ውኃ ካልሰጠኸኝ ቅዱሳን አገልጋዮችህን ምን አጠጣቸዋለሁ እለው ነበር በቸርነቱም ዝናምን ልኮልን ውኃን አገኘን" አላቸው።
❤ በአንዲት ዕለት አባ ሙሴ ከአረጋውያን ጋር ወደ አባ መቃርስ ሔደ አባ መቃርስም የሰማዕትነት አክሊል ያለው ከእናንተ ውስጥ አንዱን እነሆ አያለሁ" አላቸው አባ ሙሴም "አባቴ ሆይ ምናልባት እኔ እሆናለሁ በሰይፍ የገደለ በሰይፍ ይገደል ዘንድ አለው የሚል ጽሑፍ አለና" ብሎ መለሰ።
❤ ከዚህም በኋላ የበርበር ሰዎች መጡ አባ ሙሴም ከእርሱ ጋራ ያሉትን መነኰሳት "እነሆ የበርበር ሰዎች ደረሱ መሸሽ የሚፈልግ ይሽሽ" አላቸው እነርሱም "አባታችን አንተስ አትሸሽምን" አሉት እርሱም "በሰይፍ የገደለ በሰይፍ ይገደላል ስለ ሚለው የእግዚአብሔር ቃል እነሆ ያቺን ቀን ለብዙ ዘመናት ስጠብቃት ኖሬአለሁ" አላቸው። ወዲያውኑም የበርበር ሰዎች ገብተው በሰይፍ ገደሉት መሸሽ ስለ አልፈለጉ ከእርሱ ጋር ሰባት መነኰሳትም ተገደሉ አንዱ ግን ከምንጣፍ ውስጥ ተሠወረ የእግዚአብሔርንም መላአክ አየ በእጁም አክሊል ነበር እርሱም ቆሞ ይጠብቅ ነበር። ይህንንም በአየ ጊዜ ከተሠወረበት ወጣ የበርበር ሰዎችም ገደሉት የሰማዕታትንም አክሊል ተቀበለ።
❤ ወንድሞች ሆይ ከሀዲና ነፍሰ ገዳይ ቀማኛና ዘማዊ የነበረውን ለውጣ ደግ አባት መምህርና የሚያጽናና ለመነኰሳትም ሥርዓትን የሠራ ካህን እንዳደረገችው በሁሉም አብያተ ክርስቲያን ስሙ እንዲጠራ እንዳደረገችው የንስሐን ኃይሏን ተመልከቱ።
❤ ሥጋው በአስቄጥስ ገዳም ደርምስ በተባለ ቦታ ለዘላለም ይኖራል ከእርሱም ብዙዎች ድንቆችና ተአምራት ይታያሉ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሙሴ ጸሊም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የሰኔ 24 ስንክሳር።
+ + +
❤ "ሰላም ዕብል ለሙሴ ጸሊም። እንተ ነበረ ዕጉሠ ውስጤ ገዳም። ሶበ ተዘከረ ኵሎ እከያቲሁ ዘቅድም እትቀተል ይቤ በመጥባሕተ በርበር ዮም። ዘእንበለ ደም ኢይነጽሕ ደም"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የሰኔ 24።
+ + +
❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ኃጢአትየ ነገርኩ ወአበሳየ ኢኀባዕኩ። ወእቤ አስተዋዲ ርእስየ ኀበ እግዚአብሔር በእንተ ኃጢአትየ። ወአንተ ኅድግ ጽልሑቶ ለልብየ"። መዝ 31፥5። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 10፥46-ፍ.ም፣ 1ኛ ዮሐ 1፥4-ፍ.ም፣ የሐዋ ሥራ 14፥1-7። የሚነበበው ወንጌል ዮሐ 12፥20-27። የሚቀደሰው ቅዳሴ የሠለስቱ ምዕት ቅዳሴ ነው። መልካም የአባ ሙሴ ጸሊም የዕረፍት በዓልና የጾም ጊዜ ሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
