uk
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Відкрити в Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Показати більше
1 161
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
1/1/2015 ዓ.ም (፩/፩/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 አድኅነኒ እምእለ ሮዱኒ እስመ ይኄይሉኒ። ወአውጽኣ እሞቅሕ ለነፍስየ። ከመ እግነይ ለስምከ እግዚኦ፡፡ መዝ. 141፥6 🕯 ትርጉም በርትተውብኛልና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ። አቤቱ ስምህን አመሰግን ዘንድ። ነፍሴን ከወህኒ አውጣት። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ሉቃ. 4:16-23 "ወሖረ ናዝሬተ ኅበ ተሐጽነ" - "ወዳደገበትም፡ወደ፡ናዝሬት፡መጣ፤እንደ፡ልማዱም፡በሰንበት፡ቀን፡ወደ፡ምኵራብ፡ገባ፥ሊያነብም፡ ተነሣ። የነቢዩንም፡የኢሳይያስን፡መጽሐፍ፡ሰጡት፥መጽሐፉንም፡በተረተረ፡ጊዜ፦የጌታ፡መንፈስ፡በእኔ፡ላይ፡ነው፥ለድሃዎች፡ወንጌልን፡እሰብክ፡ዘንድ፡ቀብቶኛልና፤ለታሰሩትም፡መፈታትን፡ለዕውሮችም፡ማየትን፡እሰብክ፡ዘንድ፥የተጠቁትንም፡ነጻ፡አወጣ፡ዘንድ፡የተወደደችውንም፡የጌታን፡ዓመት፡እሰብክ፡ዘንድ፡ልኮኛል፡ተብሎ፡የተጻፈበትን፡ስፍራ፡አገኘ። መጽሐፉንም፡ጠቅሎ፟፡ለአገልጋዩ፡ሰጠውና፡ተቀመጠ፤በምኵራብም፡የነበሩት፡ዅሉ፡ትኵር፡ብለው፡ይመለከቱት፡ነበር። እርሱም፦ዛሬ፡ይህ፡መጽሐፍ፡በጆሯችሁ፡ተፈጸመ፡ይላቸው፡ጀመር። ሁሉም፡ይመሰክሩለት፡ነበር፡ከአፉም፡ከሚወጣው፡ከጸጋው፡ቃል፡የተነሣ፡እየተደነቁ፦ይህ፡የዮሴፍ፡ ልጅ፡አይደለምን?ይሉ፡ነበር። እርሱም፦ያለጥርጥር፡ይህን፡ምሳሌ፦ባለመድኀኒት፡ሆይ፥ራስህን፡ፈውስ፤በቅፍርናሖም፡እንዳደረግኸው፡የሰማነውን፡ሁሉ፡በዚህ፡በገዛ፡አገርህ፡ደግሞ፡አድርግ፡ትሉኛላችሁ፡አላቸው።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.22 KB

01/1/2015 ዓ.ም (፩/፩/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ። ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም። ወይረውዩ አድባረ በድው። መዝ.64÷11 🕯 ትርጉም በቸርነትህ ዓመትን ታቀዳጃለህ። ምድረ በዳውም ስብን ይጠግባል። የምድረ በዳ ተራራዎች ይረካሉ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

.... እስኪ በአዲሱ አመት አምላካችንን የልቦናችንን ቅን ሃሳብን እንዲፈጽምልን በንፁህ ልብ በቅኔ እንማጸነው.. አምላኪየ ኄር በዘወሀብከኒ እድሜ ሕይወትየ ቀስም በቅኔአበው አበሜ

ባሕረ_ሐሳብ_የ2014_ዓ_ም_አጿማትና_በዓላት_ቀን_01_01_14.m4a44.97 MB

photo content

photo content

photo content

photo content

ነዚያን ደንጊያዎች ሰይጣንን አሸክሞ ወደ ገዳሙ አደረሰው በገዳሙም ደጃፍ አጠገብ እንዲአስቀምጣቸው አዘዘው እስከዛሬም በዚያ ይኖራሉ። ሰይጣንንም ዳግመኛ ወጥቶ እንዳይፈትነው በዓለት ዋሻ ውስጥ ዘግቶ በመስቀል ምልክት ለዘላለሙ አሸገው። ❤ አባ ሚልኪም ከመነኰሰ አርባ አምስት ዓመታት ሲሆነው እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ ወደርሱ መጣ "እነሆ የምታርፍበት ቀን ቀርቧል ከሦስት ቀን በቀር አልቀረህም ወደ ዘላለምም ተድላ ደስታ ትሔዳለህ"። ያን ጊዜም ልጆቹን ሁለ ጠርቶ ሰይጣን ከሚያመጣው ስሕተት እንዲርቁና እንዲጠብቁ በፍርሃትም ሁነው እግዚአብሔርን እንዲአገለግሉ አዘዛቸው። ከሦስት ቀንም በኋላ ቅዱሳን አባቶች መነኰሳት አባ እንጦንስ አባ መቃርስ አባ ሲኖዳ አባ ብሶይ አባ ጳኵሚስ ወደርሱ መጥተው እንዲህ አሉት "ወንድማችን ወደእኛ ና ከእኛ ጋርም ፍጹም ተድላ ደስታ ባለበት በእግዚአብሔር መንግሥት ደስ ይበልህ" ይህንንም ሲሉት ነፍሱ ከሥጋው ወጣች። መላእክትም "በዓለም ውስጥ በገድል በትሩፋት የደከመ ለዘላለሙ በሕይወት ይኖራል" እያሉ በክብር በምስጋና ወደ ኢየሩሳሌም ሰማያዊት አወጡት። ❤ ከዚህም በኋላ ጳጳሳት ኤጲስቆጶሳት ሁሉም ካህናት ተሰብስበው ገነዙት በቤተ ክርስቲያንም ውስጥ ቀበሩት ከመቃብሩም ቍጥር የሌላቸው ታላላቅ የሆኑ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጻድቁ አባ ሚሊኪ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የታላቂቱ አገር የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ሜልዮስ፦ እርሱም ለአባታችን ሐዋርያና ወንጌላዊ ለሆነ ማርቆስ ሦስተኛ ነው። ❤ ይህም አባት የሮሜ ንጉሥ አስባስያኖስ በነገሠ በዐሥራ አምስት ዓመት ተሾመ ይኸውም የክብር ባለቤት ጌታችን በዐረገ በአርባ ዓመት ነው ክብር ይግባውና የክርስቶስን መንጋዎች በበጎ አጠባበቅ ጠበቃቸው በሹመቱም ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ። እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም በፍቅር አንድነት ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ሚልዮስ ጸሎት ይማረን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የመስከረም 1 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለምልኪ እምዐቢይተ ቊልዝም ዘኮነ። ዘሠናየ ልሕቀ ወዘአዳመ ተሐፅነ። እምእግዚአብሔር ከሀሊ ነሢኦ ሥልጣነ። በኃይለ ጸሎቱ ቀነየ ሰይጣነ። እንዘ ያፀውሮ ገብላተ ወስቊረ ዕብነ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የመስከረም 1። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

ግን ከዓለም ሸሽቶ ያመልጥ ዘንድ ያስባል። ❤ ከዚህም በኋላ አባቱን እንዲህ አለው "አባቴ ሆይ ከእኔ ጋራ ለተማሩ ልጆች ለባልንጀሮቼም ምሳ ላደርግላቸው እሻለሁ ምሳንም በባልንጀሮቹ ያዘጋጅላቸው ዘንድ አባቱ አንድ ሺህ የወርቅ ዲናርን ሰጠው። ዳግመኛም ለሚያስፈልገው ሥራ እንዲገለግሉ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችን አዘዘለት። ❤ ከዚህም በኋላ በፈረስ ተቀምጦ ከአባቱ ፊት ወጣ ሎሌዎቹንም እንዲህ አላቸው "መቶ የወርቅ ዲናርን ወስዳችሁ በፍጥነት ምሳ አዘጋጁልን ልጆች ባልንጀሮቼን እኔ ብቻዬን ሒጄ እጠራቸዋለሁ"። ዘመዶቹም ሰምተው ተመለሱ እርሱም ብቻውን ሒዶ ያንን ወርቅ ለድኖችና ለምስኪኖች በተነ ፈረሱንም ለአንድ ድኃ ሰጠ በላዩ ካለ ልብስ በቀር ምንም ምን አላስቀረም። ❤ መምጣቱም በዘገየ ጊዜ ፈለጉት ግን አላገኙትም። እያለቀሱም ተመልሰው ለአባቱና ለእናቱ ነገሩአቸው እነርሱም የመረረ ልቅሶን አለቀሱ ከለቅሶ ብዛትም የተነሣ የእናቱ ዐይኖቿ ታወሩ ለሞትም አደረሳት። ይህ አባ ሚልኪ ግን ጡር ወደምትባል ገዳም ሔደ ይቺም ስሙ አባ አውጊን ለሚባል ለእናቱ ወንድም ገዳሙ ናት። ❤ ይህም አባ አውጊን ብዙ ትሩፋትን የሚሠራ ጻድቅ ሰው ነው በእርሱም ሥር የተመረጡ ሰባ ሁለት መነኰሳት ነዋሪዎች አሉ። አባ ሚልኪም ከእግሩ በታች ሰግዶ "አባቴ ሆይ በጥላህ ሥር እንድኖር የምንኲስናንም ልብስ ታለብሰኝ ዘንድ እሻለሁ" አለው። አባ አውጊንም ከወዴት አገር ነህ ብሎ ጠየቀው እርሱ አባ ሚልኪም አገሩ ቊልዝም ለአባ አውጊንም የእኀቱ ልጅ መሆኑን ነገረው ሰምቶም ፈጽሞ ደስ አለው። ❤ ሦስት ዓመትም በአመክሮ አቆየው ከዚህም በኋላ የምንኲስናን ልብስ አለበሰው ዜናው በፋርስ አገር ሁሉ እስቲሰማ ትጋትንና ተጋድሎን አበዛ። እግዚአብሔርም የመፈወስን ሀብት ሰጥቶት አጋንንትን ከሰዎች ላይ አሰወጥቶ ይሰዳቸዋል። ❤ ከዕለታትም በአንዲቱ ዕለት የዳዊትን መዝሙር እያነበበ ብቻውን ሲጓዝ ታላቅ ጒድጓድ ወዳለበት ደረሰ በአጠገቡም የበለስ ዛፍ አለ ብዙ እረኞችም በዚያ ያለቅሱ ነበር። አባ ሚልኪም "ምን ያስለቅሳችኋል" አላቸው። እረኞችም እንዲህ ብለው መለሱለት "የአገረ ገዢው ልጅ ከእኛ ጋራ ከበለስ ፍሬ ሲበላ ታላቅ ዘንዶ ወጥቶ ልጁን ውጦ ወደ ጒድጓድ ተመለሰ" አሉት። እረኞችም እየነገሩት ሳለ የሕፃኑ አባት ልብሱን በመቅደድ ፊቱንም በመጽፋት ከብዙ ሰዎች ጋር መጣ ቅዱስ ሚልኪንም ስለ ልጁ ማለደው። አባ ሚልኪም "ልጄ ሆይ በእግዚአብሔር ታመን እንጂ አትፍራ የጌትነቱንም ድንቅ ሥራ ታያለህ" አለው። ❤ ያን ጊዜም ፈቱን ወደ ምሥራቅ መልሶ ረጅም ጸሎትን ጸለየ ጸሎቱንም በጨርሰ ጊዜ ዘንዶውን ጠርቶ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሕፃኑን ይተፋው ዘንድ አዘዘው ምንም ሕማም ሳይነካው ጒዳትም ከቶ ሳያገኘው ወዲያውኑ ተፋው በከይሲውም አድሮ ያለ ሰይጣን እንዲህ ብሎ ጮኸ "የቊልዝም ሰው ሚልኪ ከአንተ የተነሣ ወዴት ልሒድ" ይህንንም ብሎ እንደ ጢስ ተበተነ። ❤ የሕፃኑም አባት ይህን ድንቅ ሥራ ልጁም እንደ ዳነ በአየ ጊዜ እጅግ ደስ አለው። ለቅዱስ አባ ሚልኪም ብዙ ወርቅትና ብር አመጣ አባ ሚልኪም "መቀበልን አይሆንም" አለ "ግን በጽድቅ ሥራ አንድ እንድንሆን ገዳምን ሥራ" አለው። አገር ገዢው የሕፃኑ አባትም ደስ አለው ሦስት መቶ የመነኰሳት ቤቶችን ሠራ ዙሪያውንም በግንብ አጠረ መዝጊያውንም ከብረት ሠራ። ❤ ቤተክርስቲያንንም ሲሠሩ ሦስት መቶ ሰዎች ሊአንቀሳቅሷት የማይችሉ ለማዕዘን የምትሆን ደንጊያን አገኙ በጻድቁ በአባ ሚልኪ ጸሎትም ራስዋ ተነሥታ እንደሚፈልጓት ሁና ተሠራች። ❤ ከዚህም በኋላ በዚያ ገዳም ሦስት መቶ ሰዎች ተሰብስበው የተመረጡ መነኰሳትን ሆኑ። የቅዱስ አባ ሚልኪም ዜናው በሀገሩ ሁሉ ተሰምቶ በየዓይነቱ ደዌ ያለባቸውን በክፉዎች አጋንንትም የተያዙትን ወደርሱ የሚያመጡአቸው ሆኑ ሁሉም በጸሎቱ ይፈወሱ ነበር። በዚሁ ጻድቅ ጸሎትና ምልጃ የፋርስና የሮም ሰዎች ተጠብቀው የሚኖሩ ሆኑ። ❤ ከዚህም በኋላ አባ ሚልኪ ከዋሻ ውስጥ ገብቶ የዋሻውን በር ዘጋ በልቡም "እስከ ዕድሜዬ ፍጻሜ ከዚህ ዋሻ አልወጣም" ብሎ ቃል ገባ። የበጎ ሥራ ጠላት ሰይጣንም እንዲህ ብሎ ዛተበት "ጠብቀኝ እኔ ከዚህ ከበዓትህ አስወጥቼ የተሳልከውን ቃል አፈርሳለሁ" ይህንንም ብሎ ሒዶ በሮም ንጉሥ ልጅ ላይ አድሮ አሳበዳት እርሷም እየጮኸች እንዲህ አለች "ከቊልዝማዊው ሚልኪ በቀር የሚያድነኝ የለም"። ❤ ንጉሥ አባቷም ሰምቶ ከወታደሮቹ ውስጥ አራት መቶ ሰዎችን ላከ እንዲህም ብሎ አዘዛቸው "በሁሉ ቦታ ተግታችሁ አባ ሚልኪን ፈልጋችሁ ወደ እኔ አምጡት እኔም በጎ የሆነ ዋጋችሁን እከፍላችኋለሁ። ይህ ካልሆነ ግን ራሶቻችሁን በሰይፍ ልቆርጥ ምያለሁ"። ❤ የተላኩ ወታደሮችም ፈልገው በጭንቅ አገኙትና ለብፁዕ አባ ሚልኪ የንጉሡን መልእክት ልጁን ጋኔን እንደአደረባት የምትናገረውንም ነገር ነገሩት። እርሱም "እኔ ሽማግሌ ሰው ነኝ ወደ ሮም አገር ለመሔድ አልችልም" አላቸው። እነርሱም "አባታችን ሆይ አንተ ከእኛ ጋር ካልሔድክ ንጉሥ በሰይፍ ቆርጦ እንደሚገድለን ነግሮናል" አሉት። ሰምቶም እጅግ አዘነ እንዲህም አላቸው "ልጆቼ ሒዱ እኛ እርስ በርሳችን በሮም ከተማ መግቢያ እንገናኛለን"። ❤ ቃሉንም ሰምተው ሔዱ በዓመቱም ፍጻሜ ከሮሜ ከተማ መግቢያ መድረሳቸውን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ያን ጊዜም ደመና ተሸክማ ከሮሜ ከተማ መግቢያ አደረሰችው። የንጉሥ መልእክተኞችም በአዩት ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው። ለንጉሡም የከበረ አባ ሚልኪ መምጣቱን ነገሩት። እርሱም ወጥቶ በክብር ተቀብሎ ወደ እልፍኙ አስገባው ስለ ልጁ ስለ ደዌዋ ነገረው ቅዱስ አባ ሚልኪም አምጧት ብሎ አዘዘ። በአመጧትም ጊዜ ጋኔኑ ጥሎ አረፋ አስደፈቃት ሞተች ብለው እስከሚጠራጠሩ። ያን ጊዜም አባ ሚልኪ ተነሥቶ ጸለየ በፊቷ ላይም ውኃን ረጨ ዘይትንም ቀባት ሰይጣንንም ከርሷ ይወጣ ዘንድ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዘዘው። ያን ጊዜም በጥቁር ባርያ አምሳል ከእርሷ ወጣ። ❤ ቅዱስ አባ ሚልኪም ሰይጣንን በሥውር ይዞ በቤት ውስጥ ዘጋበት በዚያም አሠረው። ንጉሡም ይህን ድንቅ ሥራ አይቶ ከእግሩ በታች ሰገደ ለገዳሙ ለሚአስፈልገው ነገር እንዲሆነው ብሎ ብዙ ወርቅና ብርን አመጣለት እርሱም መቀበልን እምቢ አለ። ንጉሡም "አባቴ ሆይ ከዚህ ተቀመጥ እኔም ገዳም እሠራልሃለሁ" አለው አባ ሚልኪም "ልጆቼን መተው አይሆንልኝም" አለው ግን በሽተኞችን እየፈወሰ በሮሜ ከተማ ጥቂት ቀኖች ተቀመጠ። ❤ ወደ አገሩ ይመለስ ዘንድ ተነሥቶ በወጣ ጊዜ ንጉሡም ከመኳንንቱ ጋራ ሊሸኘው ተነሣ። ከንጉሥ ግቢ በስተውጭ የንጉሥ ፈረሶች የሚጠጡበት ታላቅ የደንጊያ ገንዳ የተበሳ ታላቅ ደንጊያን አባ ሚልኪ አይቶ ንጉሡን "ይህን ገንዳ ይህንንም የተበሳ ታላቅ ደንጊያ ለገዳም አገልግሎት እሻዋለሁና ስጠኝ" አለው። ንጉሡም "ዐሥራ አራት ሰዎች ከምድር ከፍ ሊአደርጉት የማይቻላቸው ወደ ገዳምህ እንዴት ይደርሳል ተሸክሞ ወደ ፈለግከው ቦታ የሚያደርስ ኃይል ካለህ እኔ ሰጠሁህ" አለው። ❤ ያን ጊዜም ቅዱስ አባ ሚልኪ ሰይጣንን ከአሠረበት ቦታ አምጥቶ ያንን የተበሳ ደንጊያ በአንገቱ ውስጥ አንጠለጠለ ገንዳውንም ተሸክሞ በፊት በፊቱ ተገልጦ እንዲጓዝ አዘዘው። ሰይጣንም እነዚያን ገንዳዎች የተበሳውንም ደንጊያ ተሸክሞ በፊት በፊቱ ይጓዝ ጀመረ። ንጉሡና የተሰበሰቡት ሕዝብ አይተው እጅግ አደነቁ ለሚፈሩት ለሚያመልኩት ይህን ያህል ጸጋ የሚሰጥ ምስጉን እግዚአብሔርንም አመሰገኑት። ❤ የከበረ አባ ሚልኪም እ

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ የተባረከ የመስከረም ወር የግብፅና የኢትዮጵያ ዓመታት ወሮች ርእስ ነው። የቀኑ ሰዓትም ከሌሊት ሰዓት የተስተካከለ ዐሥራ ሁለት ነው። ከዚህ በኋላ እያነሰ ይሔዳል። ❤ መስከረም ፩ (1) ቀን። ❤ እንኳን ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ራጉኤል ለበዓለ ሲመቱ፣ ለሐዋርያው ለቅዱስ በርተሎሜዎስ ለዕረፍቱ በዓል፣ ለቅዱስ ኢዮብ በፈሳሽ ውኃ ታጥቦ ከደዌው ሁሉ ለዳነበት ቀን፣ ለታላቁ አባት ለቊልዝም ሰው ለሆነ ፍፁም ጻድቅ ሰይጣን አስሮ ዐሥራ አራት ሰዎች ሊይዙት የማችሉትን ድንጊያ ላሸከመው ለአባ ሚልኪ ለዕረፍት በዓል በጤና በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰበው፦ ከሦስተኛ የእስክድርያ ሊቀ ጳጳስ ከአባ ሚልዮስ በዓለ ዕረፍትና ከቅዱስ ቀን እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ "ሰላም ለራጉኤል ወለሳቁኤል፤ ለአፍኒን ወለራሙኤል እለ የዐውዱ መንበሮ ለልዑል"። ትርጉም፦ የልዑል ዙፋኑን ለሚዞሩ ለራጉኤልና ለሳቁኤል፤ ለአፍኒንና ለራሙኤል ሰላምታ ይገባል፡፡ ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ በዚችም ቀን ከተስዓቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ የከበረ መልአክ ራጉኤል የበዓሉ መታሰቢያ ነው። እርሱም ስለሚነድ እሳትና ስለ ኃጥአን ሁሉ በጥፋት ውኃ መደምሰስ ለሄኖክ ያስገነዘበው ነው። የዚህም ብርሃናዊ መልአክ የቅዱስ ራጉኤል አማላጅነቱ ከእኛ ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ "ሰአሉ ለነ ሐዋርያት አስራብ ዘወርቅ ወሐይዝተ ጽድቅ ወዘሐረገ ወይን አዕጹቅ ሰአሉ ለነ አስተምሕሩ"። ትርጉም፦ የወርቅ ፏፏቴዎች የጽድቅ ፈሳሽና የወይን ሐረግ ቅርጫፎች ሐዋርያት ለምኑልን አማልዱን። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ በሰዓታቱ ላይ። + + + ❤ ሐዋርያው ቅዱስ በርተሎሜዎስ፦ ለዚህም ሐዋርያ ሒዶ ያስተምር ዘንድ እልዋህ በሚባል አገር ዕጣው ወጣ። እርሱም ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር በአንድነት ሔደ የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተማሩ ልባቸውንም የሚያስደነግጥ ድንቆች ተአምራትን በፊታቸው ከአደረጉ በኋላ እግዚአብሔር ወደ ማወቅ መለሷቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ከተማው ውስጥ ገብቶ ያስተምር ዘንድ ምክንያት አደረገ ቅዱስ ጴጥሮስም እንደ ባሪያ ሸጠው። ባለ ጸጋ ለሆነ መኰንንም በወይን አትክልት ውስጥ የሚያገለግል ሆነ ድንቅ ተአምርን በማድረግ የተቆረጡ የወይን ቅርጫፎች በሠራተኞች እጅ ላይ ሳሉ አፈሩ። የአገረ ገዥውም ልጅ በሞተ ጊዜ ከሞተ አሥነሣው የአገር ሰዎችም ሁሉ አመኑ እግዚአብሔርንም ወደ ማወቅ ተመለሱ። ❤ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በርበር ወደሚባል አገር ሔዶ ያስተምር ዘንድ ሐዋርያ ቅዱስ በርተሎሜዎስን አዘዘው እንዲረዳውም ሐዋርያ ቅዱስ እንድርያስን ከደቀ መዝሙሩ ጋር ላከለት። የዚያች አገር ሰዎች ግን እጅግ የከፉ ስለሆኑ በፊታቸው ድንቆች ተአምራቶችን እያደረጉላቸው ሐዋርያትን አልተቀበሏቸውም። ❤ ጌታችንም ሰውን ከሚበሉ አገር አንዱን ገጸ ከልብ ይታዘዝላቸው ዘንድ በሚያዙት ሁሉ ትእዛዛቸውን እንዳይተላለፍ አዘዘው። ሐዋርያትም ወደዚያች አገር ሁለተኛ ይዘውት ገቡ የአገር ሰዎችም ሐዋርያትን ይበሏቸው ዘንድ ነጣቂዎች የሆኑ አራዊትን አወጡ። ያን ጊዜም ያ ገጸ ከልብ በአራዊቱ ላይ ተነሥቶ እየነጠቀ በላቸው ይህንንም ገጸ ከልብ ከመፍራት የተነሣ ከሰዎች በድንጋጤ የሞቱ ብዙዎች ናቸው። ❤ የአገሩ ሰዎች ሁሉም የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ከሐዋርያትም እግር በታች ሰገዱ የሚሉአቸው ሁሉ የሚደርጉ ታዛዦች ሆኑ። ሐዋርያትም ቤተ ክርስቲያን ሠርተውላቸው ካህናትንም ሹመውላቸው ከእነርሱም ዘንድ ወጥተው እግዚአብሔር እያመሰገኑ ሔዱ። ❤ ሐዋርያ ቅዱስ በርተሎሜዎስም እግዚአብሔርን የማያውቁ ሰዎች ወደሚኖሩበት በባሕር ዳርቻ ወዳሉ አገሮች ሔዶ የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ሰበከላቸው በፊታቸውም ተአምራትን አደረገ ሁሉም የጌታችን በሆነች በቀናች ሃይማኖት አመኑ። ❤ ሐዋርያ ቅዱስ በርተሎሜዎስም ከዝሙት ርቀው ንጹሐን እንዲሆኑ ሰዎችን የሚያዝዝ ሆነ። ንጉሥ አግሪጳም ስለርሱ በሰማ ጊዜ በከበረ ሐዋርያ በቅዱስ በርተሎሜዎስ ላይ እጅግ ተቆጣ። በማቅ ከረጢት ውስጥ እንዲአደርጉትና አሸዋ ሞልተው ከባሕር እንዲጥሉት አዘወ። እንዲሁም ይህን አደረጉበት ምስክርነቱንና ተጋድሎውንም መስከረም 1 ቀን ፈጸመ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባታችን በሐዋርያ ቅዱስ በርተሎሜዎስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ "ሰላም ለኢዮብ ምኩር ወተዓጋሢ በመከራሁ ወበሕማሙ እስከ ይዝሕቅ ቊሰሊሁ በገልዕ፤ መጋቤ ምጽዋት ላዕለ ጽኑሳን ለለጽባሑ"። ትርጉም፦ በየጧቱ ለተቸገሩ ምጽዋትን ይሰጥ የነበረ ለሚኾን፤ በሸክላ ስባሪ ቊስሉ እስኪላጥ (እስኪገሸለጥ) ድረስ ያክ ለነበረው በመከራውና በሕማሙ ታጋሽ ለኾነው ለተፈተነው ለኢዮብ ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ በዚችም ዕለት ኢዮብ በፈሳሽ ውኃ ታጥቦ ከደዌው ሁሉ ተፈወሰ። ይህም ለሰዎች ልማዳቸው ሆኖ ዓመቱ ዙሮ ሲመጣ ፈሳሹ ውኃም በመላ ጊዜ በአዲስ ውኃ ይጠመቃሉ በእርሱም ይባረካሉ። የጻድቁ ኢዮብ በረከትም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ፍጽም ጻድቅ አባ ሚልኪ፦ የዚህም ጻድቅ ወላጆቹ ከቊልዝም አገር ከታላላቆች ወገን ናቸው። እርሷም ከላይኛው ግብጹ አውራጃ ውስጥ ናት እነርሱም በብርና በወርቅ የበለጸጉ ናቸው ለድኖችና ለችግረኞች ምጽዋትን የሚሰጡ እግዚአብሔርንም እጅግ የሚወዱ ናቸው። ❤ ነገር ግን ልጅ አልነበራቸውም ከዕለታትም በአንዲቱ ከመምህር ዘንድ የሚማሩ ልጆችን አዩ በእጆቻቸውም ሠሌዳዎችን ይዘዋል። በሠሌዳዎቹም ውስጥ እንዲህ የሚል ጽሑፍ አለ "እኛ የሕያው እግዚአብሔር ልጆች እንድንሆን በሕይወታቸው ሳሉ ያስተማሩን አባቶቻችንን አስባቸው አቤቱ ነፍሶቻቸውንም ከተመረጡ ቅዱሳን ጻድቃንና ሰማዕት አሳርፍ"። የአባ ሚልኪ አባትም ከልጆች አንደበት ይህን ቃል በሰማ ጊዜ "ከዚህ ዓለም ከሔድኩ በኋላ ልጅ የሌለኝ እኔን ማን ያስበኛል ወዮልኝ" እያለ እጅግ በማዘን ተከዘ። ❤ ከዚህም በኋላ በጾም በጸሎት ምጽዋትንም በመስጠት ከሚስቱ ጋር ምህላ ያዘ። የክብር ባለቤት እግዚአብሔርም ልመናቸውን ሰምቶ ወንድና ሴት ሁለት ልጆችን በአንዲት ጊዜ ሰጣቸው በእነርሱም ፈጽሞ ደስ አላቸው። ወደ ክርስትናም በአስገቧቸው ጊዜ ወንዱን ልጅ ሚልኪ አሉት እኀቱን ስፍና አሏት ትርጓሜዋ ርግብ ማለት ነው በመልካም አስተዳደግ አሳደጓቸው። ❤ ለሚልኪ ሰባት ዓመት ሲሆነው አባቱ ወስዶ ለመምህር ሰጠው የብሊያትንና የሐዲሳት መጻሕፍትን ሁሉ ተማረ መንፈስ ቅዱስም አደረበት። ከሕፃናቱም ጋር አይጫወትም አይስቅም በቀንም በሌሊትም አዘውትሮ መጸሕፍትን ያነባል እንጂ። ❤ ዕድሜውም ዐሥራ ዘጠኝ ዓመት በሆነው ጊዜ ወላጆቹ ጠርተው ስለ ጋብቻ ሚስት አብግቶ መታሰቢያችው ይሆን ዘንድ ተናገሩት። እርሱም ይህን አልወደደም ነገር ግን በተንኰል "እሺ ቃላችሁን ተቀብዬ ያዘዛችሁኝን ሁሉ አደርጋለሁ" አላቸው እርሱ

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልደ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ የተባረከ የመስከረም ወር የግብፅና የኢትዮጵያ ዓመታት ወሮች ርእስ ነው። የቀኑ ሰዓትም ከሌሊት ሰዓት የተስተካከለ ዐሥራ ሁለት ነው። ከዚህ በኋላ እያነሰ ይሔዳል። ❤ መስከረም ፩ (1) ቀን። ❤ እንኳን ለርእሰ ዐውደ ዓመት ለቅዱስ ዮሐንስ፤ ከዘመነ ቅዱስ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ቅዱስ ማርቆስ አሸጋግሮ እግዚአብሔር አምላክን በጤና በሰላም አደረሰን። + + + ❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግእዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ወአንተኒ ሕጻን ነቢየ ልዑል ትሰመይ ዓርኩ ለመርዓዊ ትሰመይ ወአዝማዱ በሥጋ ትሰመይ ተፈኖከ ታርኁ አናቅጸ ጽድቅ"። ትርጉም፦ አንተም ሕጻን የልዑል ነቢይ ትባላለህ፡፡ ለሙሽራው ሚዜ ትባላለህ የሥጋ ዘመዱ ትባላለህ የጽድቅ በሮች እንድተፍት ተልከሃል። ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ የዕለቱ መዝሙር፦ "ባርክ ለነ እግዚኦ ዘንተ ዓመተ ምሕረትነ በብዝሃ ኂሩትከ ለሕዝብከ ኢትዮጵያ ከመ ንግነይ ለስምከ ቅዱስ። ወከመ ይኩን ንብረተነ በሰላም ወባዳኅና በዝንቱ ዓመት"። ትርጉም፦ ባርክልን አቤቱ ይህንን የምሕረት ዓመታችን በቸርነትህ ብዛት ለሕዝቦችህ ኢትዮጵያ እንድንገዛ ለቅዱስ ስምህ። እንዲሆንም ኑሮዋችን በሰላም በደኅና በዚህ ዓመት። + + + ❤ የተባረከ የመስከረም ወር የግብፅና የኢትዮጵያ ዓመታት ወሮች ርእስ ነው። የቀኑ ሰዓትም ከሌሊት ሰዓት የተስተካከለ ዐሥራ ሁለት ነው። ከዚህ በኋላ እያነሰ ይሔዳል። አሁንም በፍጹም ንጽሕና ታላቅ በዓልን አድርገን ልናከብር ይገባናል። ❤ ይህች ዕለት ከሌሎች ዕለታት ተለይታ የተባረከች ናትና ከክፉ ሥራዎችም ሁሉ ተለይተን እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝባቸውን አዳዲስ የሆኑ በጎ ሥራዎችን እንሥራ። ሐዋርያ ቅዱስ ጳውሎስ "እነሆ የቀደሙት ሥራዎች አልፈው ሁሉ በክርስቶስ ሐዲስ ሆነ" እንዳለ። ይህም ከእግዚአብሔር ዘንድ እንዲሁ የጐላ የተረዳ ሆነ እርሱም በክርስቶስ ልጅነትን በመስጠት ይቅርታውንና ቸርነቱን አደለን። ❤ ኢሳይያስም እንዲህ አለ "በኔ ህልውና ያለ ያዋሐደኝ ሕይወቴ መንፈስ ቅዱስ ስለርሱ ድኆችን በልብ ያዘኑ ሰዎችን ደስ አሰኛቸው ዘንድ ለተማረኩም ሰዎች ነፃ መውጣትን አስተምራቸው ዘንድ ዕውሮችም ያዩ ዘንድ እግዚአብሔር የወሰነውን ዘመን የተመረጠ እለው ዘንድ ፍዳ የሚደረግባትንም ቀን ደግ እላት ዘንድ ያዘኑትንም ሰዎች ደስ አሰኛቸው ዘንድ ላከኝ"። ❤ ነቢዩ ዳዊትም ዳግመኛ እንዲህ አለ "የምሕረትህንም ዓመት እህል ትባርካለህ። ምድረ በዳዎችም ከበረከትህ ጠሎችን ይጠግባሉ። ምንጭ፦ የመስከረም 1 ስንክሳር። + + + ❤ የዕለቱ ዓራራይ ዜማ፦ "አባ ዮሐንስ ባርከ ፍሬሃ ለምድር ቀዳማዌ ሣዕረ ደኃራዌ ሰብለ ዕተብ ወጸሊ ፍሬሃ ለምድር"። ትርጉም፦ አባ ዮሐንስ የምድርን ፍሬዋን ባርክ፡፡ መጀመሪያ ሳርን ሁለተኛም ሰብልን ባርክ ስለምድር ፍሬ ጸልይ። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወትባረክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ። ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም። ወይረውዩ አድባረ በድው"። መዝ 64፥11-12። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 4፥17-23። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "አድኅነኒ እምእለ ሮዱኒ እስመ ይኄይሉኒ። ወአውፅአ እሞቅሕ ለነፍስየ። ከመ እግነይ ለስምከ እግዚኦ"። መዝ 141፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት 2ኛ ቆሮ 6፥1-11፣ ያዕ 5፥8-13 እና የሐዋ ሥራ 5፥12-17። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 11፥1-20። የሚቀደሰው ቅዳሴ የቅዱሳን ሐዋርያት ቅዳሴ ነው። መልካም አዲስ ዓመትና በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw