ሰዋስው ☘☘☘☘
Відкрити в Telegram
በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።
Показати більше1 161
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ነሐሴ ፲፯ (17) ቀን።
❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ጻድቅ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት አባት ለአባታች ለካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን።
+ + +
❤ የካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ ዕረፍት፦ በዚያም ወራት ከሦስት መቶ ሠላሳ ሦስት ዘመን በኋላ በሐምሌ ሰባት ቀን እግዚአብሔር መንግሥትን ከዛጌ ወገን የእስራኤል ወገለሚሆን ለይኵኖ አምላክ መለሰ። በየሀገሩ ሁሉ ጸጥታ ፍቅር አንድነት ሆነ። ከጥቂት ቀን በኋላ እናቱ እግዚእ ኃረያ በነሐሴ 12 ቀን ዐረፈች እርሷም ባረፈች በአምስተኛው ቀን በነሐሴ 17 ቀን አባቱ ጸጋ ዘአብ ዐረፈ። የሁለቱ ቅዱሳን በረከት ብልህ አዋቂ የሚሆን የልጃቸውም በረከት በእኛ ላይ ትደር ለዘለዓለሙ በእውነት። ፍሰሓ ጽዮንም እናት አባቱ ስላረፉበት አዘነ ነገር ግን ፈቃደ እግዚአብሔር አጸናው። በሚናገረው ነገር በሚመራው ሥራ የሚቻለው ሆነ እግዚአብሔርንም የሚያገለግል ሆነ..."። ከአባታች ከካህኑ ቅዱስ ጸጋ ዘአብ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት 28፥1-3።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
💫⚜💫⚜💫⚜💫⚜💫⚜💫⚜
✨✨እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችኹ✨✨
"ፈለሰት ማርያም በስብሐት ውስተ ሰማያት መላእክት ወሊቃነ መላእክት ወረዱ ለተቀብሎታ።
እመቤታችን በምስጋና ወደዚያኛው ዓለም በተለየች ጊዜ ለአቀባበሏ መላእክትና ሊቃነ መላእክት ወረዱ፡፡"
ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድ
https://t.me/Eotcw
🔱🌿🔱🌿🔱🌿🔱🌿🔱🌿🔱
1 161
"ወዳጄ ሆይ ተነሺ ውበቴ ሆይ ነዪ"
መሓ መሓ ፪፥፲
🎊🎉 እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የእርገቷ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን🎊🎉
"አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና
የመቅደስህ ታቦት።"
መዝ ፻፴፩፥፰
https://t.me/Eotcw
1 161
#አእረግዋ
አእረግዋ መላእክት ውስተ ሰማያት (፪)
አእረግዋ መላእክት ውስተ ሰማያት(፪)
አሳረጓት መላእክት ወደ ሰማያት(፪)
አጀቧት መላእክት ወደ ሰማያት(፪)
https://t.me/Eotcw
1 161
✞ሞትማ ለመዋቲ ይገባል✞
ሞትማ ለመዋቲ ይገባል ይገባል(፪)
የድንግል አሟሟት እጅጉን ይደንቃል(፪)
ለልጇ ስትነግር ሞት እንደምትፈራ(፪)
ወሰዷት በሐሴት መላእክተ ሐራ(፪)
ጭንቀቱ ሳይገጥማት ሳታስብ ድንገት(፪)
እንደ እንቅልፍ ወሰዳት ያመልአከ ሞት፪)
አዝ= = = = =
ይገርማል ይደንቃል የድንግል ፍልሰታ(፪)
በምስጋና አረገች ከልጇ ተጠርታ
በይባቤ አረገች ከልጇ ተጠርታ
እያሸበሸቡ መላእክተ ሰማይ(፪)
ወስደው አቀረቧት ከልጇ መንበር ላይ(፪)
አዝ= = = = =
ሱባኤ እንደገቡ እንደ ሐዋርያት(፪)
እኔም ከቤት ወጣሁ አንቺኑ በመሻት(፪)
ትንሳኤሽን በክብር እንዳሳየሻቸው(፪)
እኔንም ለዚህ አብቂኝ ብርሃንሽን እንዳየው(፪)
መዝሙር
የኪነጥበብ ወልደቂርቆስ
በዲያቆን ፍጹም ሻምበልድምጽ
"አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና
የመቅደስህ ታቦት።"
መዝ ፻፴፩፥፰
https://t.me/Eotcw
1 161
#ዕርገታ_ተሰምዓ
ዕርገታ ተሰምዓ ውስተ ሰማያት ወበአታ(፪) ውስተ ገነት
ገነዝዋ ሐዋርያት
ገነዝዋ(፪) በስብሐት
#ትርጉም:-
ወደሰማይ ማረጓ ወደ ገነት መግባቷ ተሰማ:: ሐዋርያት በክብር ገነዝዋት።
https://t.me/Eotcw
1 161
#ሰላም_ለኪ
ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ
ወልድኪ ይጼውአኪ ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር/፪/
#ትርጉም:-
የአምላክ እናት ማርያም ሰላም እልሻለሁ
ወደ ሕይወትና ወደ ክብር ወዳለው ጌትነት ልጅሽ ይጠራሻል።
https://t.me/Eotcw
1 161
✞ማርያም አርጋለች✞
ማርያም አርጋለች ወደ ገነት(፪)
የሰማይ መላእክት እያረጋጓት
እርሷም እንደ ልጇ ተነስታለች
የአባቷን ዳዊት ትንቢት ልትፈፅም
ወርቁን ተጎናፅፋ በቀኙ ልትቆም
ወደ አምላክ ማደሪያ ወደ ሰማያት
አረገለች በእልልታ ድንግል የእኛ እናት
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
አዝ= = = = =
ሰማያት ይከፈት ደመናም ይዘርጋ
ዝምታም አይኖርም እመ አምላክ አርጋ
አንደበት ይከፈት ማርያምን ያመስግን
ከዘላለም ጥፋት በምልጃዋ እንድንድን
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
አዝ= = = = =
የአምላክ ማደሪያ ቅዱስ ስጋሽ
አምላክን ያቀፉት እነዚያ እጆችሽ
ሙስና መቃብር ይዞ አላስቀራቸው
ተነስተዋል በክብር በእምነት አየናቸው
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
አዝ= = = = =
ሐዋርያት አበው እንኳን ደስ አላችሁ
በክብር አረገች ማርያም ሞገሳችሁ
ወደ ዓለምም ውጡ ሰበኑዋን ይዛችሁ
የድንግል እርገቷን ንገሩ ተግታችሁ
አርጋለች ማርያም ተነስታለች
ዘማሪ
ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ
"በወርቅ ልብስ ተጐናጽፋና ተሸፋፍና
ንግሥቲቱ በቀኝህ ትቆማለች።"
መዝ ፵፬፥፱
https://t.me/Eotcw
1 161
#ጴጥሮስ
ጴጥሮስ ወጳውሎስ አጠኑ ሥጋሃ(፪)
ለማርያም(፪) በማእጠንተ ወርቅ
#ትርጉም
ጴጥሮስና ጳውሎስ የማርያምን ሥጋ
በወርቅ ማዕጠንት አጠኑ።
https://t.me/Eotcw
1 161
+ + +
❤ በዚህችም ዕለት የሰማዕታት አለቃ የቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋው ከፋርስ አገር ወደ አገሩ ልዳ በክብር የፈለሰበት ነው። የሥጋውም ፍልሰት ከእመቤታችን ድንግል ማርያም የሥጋ ፍልሰት ጋር አንድ ሆኗልና ስለዚህም እርሷን መውደዱን የሚያወቁ ሥዕሉን ከሥዕሏ አጠገብ ይሥላሉ በስሙ ለሚማፀኑ የድኅነት ወደብ ይሆን ዘንድ።
❤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን በኃያሉ ተጋዳይ በቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎት በእኛ ላይ ምሕረት ይቅርታ ቸርነት ይሁን ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ "ሰላም ለጌጋር ሰማዕት መስፍነ ሶርያ፤ ዘተጋደለ በቅድመ ሄሮድስ ረሲዕ በእንተ ማርያም ወሕፃና ኢየሱስ ኬንያ፤ እምድኅረ ተቀትለ በሰይፍ መጺኦ በፈረሰ እሳት ጸዐዳ፤ ዘጸፍኦ ለሄሮድስ ፫ተ ጽፍአተ ኵሎን አባላቲሁ እስከ ይርዕዳ ወእስከ ይውኅዝ ደም ወመግል እምአዕናፊሁ በኵሉ መዋዕሊሁ"። ትርጉም፦ ስለ ማርያምና ጠቢብ ስለኾነው ስለ ልጇ ኢየሱስ በከሓዲው ሄሮድስ ፊት የተጋደለ፤ በሰይፍ ከተገደለ በኋላም በነጭ የእሳት ፈረስ መጥቶ መላዎች፡ ውነቶቹን ኹሉ እስኪርዱ ድረስ ሄሮድስን ሦስት ጊዜ በጥፊ የተመታውና በዘመኖቹ ኹሉ ባፍንጮቹ ደምና መግል እንዲፈስስ ያደረገው ለኾነ ለሶርያው መስፍን ለሰማዕቱ ጌጋር ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ።
+ + +
❤ የሶሪያ መስፍን ሰማዕቱ ቅዱስ ጊጋር፦ ሰማዕት የሆነበትም ምክንያት ጌታችን ከእመቤታችን ከእናቱ ከድንግል ማርያም ጋራ በተሰደደ ጊዜ በሊባኖስ ተራራ ሳለ ኄሮድስ ሰምቶ ከበው ይዘው ይገድሏቸው ዘንድ ጭፍሮቹን ላከ ጊጋርም ጭፍሮች እንዳገኟቸው አሸሻቸው።
❤ ስለዚህም ኄሮድስ ተቆጣ ጊጋርንም ይዞ ጽኑ ሥቃይን አሠቃየው ሕዋሳቱንም ሁሉ ቆራረጠ። ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገልጦለት ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ገድሉንም ለሚጽፍ ቃል ኪዳን ሰጠው ከዚህም በኋላ ራሱን በሰይፍ ቆረጡት በሦስት አክሊሎችም ተጋረደ ሦስት አክሊላትን ተቀዳጀ።
❤ ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ጊጋር በአማላጅነቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
+ + +
❤ የዕለቱ ዓራራይ ዜማ፦ "ደብተራ ፍጽምት ዘጳውሊ ወማሕደሩ በጽድቅ ዘገብራ ከሀሊ ፈለሰት እምዘ ይበሊ ኀበ ኢይበሊ በመሰንቆሁ እንዘ የሀሊ ዳዊት አሁሃ ዘወልደ ወዓሊ"፡፡ ትርጉም፦ የጳውሊ ያማረች ድንኳን ሁሉን ቻይ በእውነት የሰራት ማደሪያው ከሚያረጀው ወደ ማያረጀው ተሸጋገረች (ፈለሰች) የጳውሊ ልጅ አባቷ ዳዊት በመሰንቆው ሲዘምርላት። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
+ + +
❤ "ሰላም ለጊዮርጊስ ተውላጠ ፃማሁ ወሕማሙ። እንተ ተለዓለ ሞገሰ ስሙ። በፍልሰትኪ ድንግል (ዮም) ተቶስሐ ፍልሰተ ዓፅሙ። እንዘ ይብል ሶበ ጸለየ አሜሃ ቀዲሙ። ምስለ ፍልሰትኪ ደምርኒ እሙ"። መልክአ ፍልሰታ (አርከ ሥሉስ (አርኬ) የነሐሴ16።
+ + +
❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦"ወትቀውም ንግሥት በየማንከ። በአልባሰ ወርቅ ዑጽፍት ወኊብርት። ስምዒ ወለትየ ወርእዪ ወአጽምዒ ዕዝነኪ"። መዝ44፥9-10። የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 1፥39-57።
+ + +
❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል። እግዚአብሔር ውስተ ማእከላ ኢትትሀወክ። ወይረድኣ እግዚአብሔር ፍጽመ"። መዝ4፥4-5 ወይም መዝ 121፥6-7። የሚነበቡት መልዕክታት የሚነበበው ሮሜ 8፥31-ፍ.ም 2ኛ ዮሐ 1፥1-7 እና የሐዋ ሥራ 1፥12-15። ወንጌል ማቴ 26፥26-31። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ። መልካም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የትንሣኤዋና የዕረገቷ በዓልና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን።
❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት።
https://t.me/Eotcw
1 161
❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤
❤ ነሐሴ ፲፮ (16) ቀን።
❤ እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ለትንሣኤዋና ለዕርገቷ በዓል፣ ለሰማዕታት አለቃ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሥጋው ከፋርስ አገር ወደ አገሩ ልዳ በክብር ለፈለሰበት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከሶርያ መስፍን ከታላቁ ሰማዕት ከቅዱስ ጊጋር (በስደቷ ጊዜ እመቤታችንና ልጇን መድኀኔዓለምን ዮሴፍን ሰሎሜን አብሮ ወደቤቱ አስገብቶ በመደበቅ ከሄሮድስ ጭፍሮች ያዳናቸው ነው) ከዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን።
+ + +
❤ የዕለቱ አንገርጋሪ ግዕዝ ዜማ፦ ሃሌ ሉያ "ትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር ኀደረ ላዕሌሃ ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ሠናይትየ ፀቃውዕ ይዑኅዝ እምከናፍሪሃ"፡፡ትርጉም፦ የባሕርይ አምላክ መለኮት ክቡር ወልድ በርሷ አደረ፤ ሰሎሞንም በመሓልዩ የዋኂቷ መልካም ርግቤ የማር ወለላ ከከናፍሮቿ ይፈስሳል አላት።
+ + +
❤ "ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ደባትረ ብርሀን ኀበ ተተክሉ። ለገነተ ጽባሕ በማእከሉ ውድስት አንቲ ወስብሕት በአፈ ኵሉ። እምነ ጻድቃን ዘታሕቱ ወእምትጉሃን ዘላዕሉ። ማርያም ለኪ ስብሐተ አደሉ"። ትርጉም፦ እመቤቴ ማርያም ሆይ በምሥራቃዊ ተክለ ገነት መካከል የብርሃን ድንኳኖች ወደ ተተከሉበት ለዐረገ ሥጋሽ ሰላምታ ይገባል። ድንግል ሆይ በሁሉ አንደበት መመስገን የተገባሽ ስለሆነ። በሰማይ ካሉ መላእክትና በምድር ከሚኖሩ ደቂቀ አዳም። ሁል ጊዜ ምስጋና ይቀርብልሻል። መልክአ ማርያም።
+ + +
❤ በዚህች ቀን አምላክን የወለደች የእመቤታችን ድንግል ማርያም ሥጋዋ ወደ ሰማይ ያረገበት መታሰቢያዋ ሆነ ። ከዕረፍቷም በኋላ ከእርሳቸው ስለመለየቷ ሐዋርያት ፈጽሞ እያዘኑ ነበር ።
❤ ከዚህም በኋላ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ተገለጠላቸው እርሷን በሥጋ ያዩ ዘንድ እንዳላቸውም ተስፋ ሰጣቸው ። ወንጌላዊ ዮሐንስም እስያ በሚባል አገር እያስተማረ ሳለ በነሐሴ ወር ዐሥራ ስድስተኛ ቀን ተድላ ደስታ ወደአለባት ገነት በመንፈስ ቅዱስ ተነጠቀ። የክብር ባለቤት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ካለበት ከዕፀ ሕይወት ሥር ተቀምጦ አየው። የንጽሕት እናቱንም ሥጋ ታወጣ ዘንድ ምድርን እንዲጠሩዋት ሰባቱን የመላእክት አለቆች አዘዛቸው ። እነርሱም "የንጽሕት እናቱን ሥጋ ታወጪ ዘንድ እግዚአብሔር አዞሻል" አሏት ። ያን ጊዜም ከዕፀ ሕይወት በታች ካለ መቃብር የእመቤታችን ማርያም ሥጋዋ ወጣ ።
❤ የክብር ባለቤት ጌታችንም እንዲህ እያለ አረጋጋት "የተወደድሽ የወለድሽኝ እናቴ ሆይ ዘላለማዊ ወደ ሆነ መንግሥተ ሰማያት አሳርግሽ ዘንድ ነዪ"። ያን ጊዜም በገነት ያሉ ዕፀዋት ሁሉም አዘነበሉ መላእክት የመላእክት አለቆች ጻድቃን ሰማዕታትም እየሰገዱላትና ፈጽሞ እያመሰገኗት አሳረጓት ። አባቷ ዳዊትም "ንግሥት እመቤታችን ወርቀ ዘቦ ለብሳ ደርባ ደራርባ በቀኝህ ትቀመጣለች" እያለ በበገና አመሰገናት ። በኪሩቤል ሠረገላ ተቀምጣ ከዐረገች በኋላ በልጁዋና በፈጣሪዋ ቀኝ በታላቅ ክብር ተቀመጠች ።
❤ ወንጌላዊ ዮሐንስም ከእርሷ በረከትን ተቀብሎ ሰግዶላት ተመልሶ ከሰማይ ወረደ ሐዋርያትን ተሰብስበው ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥጋ ፈጽሞ ሲያዝኑና ሲተክዙ አገኛቸው ። እርሱም እንደ አየ እንደ ሰማ ሥጋዋንም በታላቅ ክብር በምስጋና እንደ አሳረጓት ነገራቸው ።
❤ ሐዋርያትም በሰሙ ጊዜ ዮሐንስ እንዳየና እንደሰማ ባለማየታቸውና ባለመስማታቸው እጅግ አዘኑ ። ከዚህም በኋላ እያዘኑ ሳሉ እነሆ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠላቸውና "የፍቅር አንድነት ልጆች ሰላም ይሁንላችሁ ስለ እናቴ ማርያም ሥጋ ለምን ታዝናላችሁ። እነሆ እኔ እርሷን በሥጋ ላሳያችሁ ልባችሁም ደስ ሊለው ይገባዋል" አላቸው ይህንንም ብሎ ከእርሳትው ዘንድ ወደ ሰማያት ዐረገ ።
❤ ሐዋርያትም ዓመት ሙሉ ቆዩ የነሐሴም ወር በባተ ቀን ሐዋርያት ዮሐንስ እንዲህ አላቸው "አምላክን የወለደች የእመቤታችንን ሥጋዋን ለማየት የተዘጋጀን አድርጎ ያሰየን ዘንድ ኑ ይህን ሁለት ሱባዔ በመጾም የክብር ባለቤት ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው በልጅዋ በወዳጅዋ ቀኝ ተቀምጣ አይተን በእርሷ ደስ እንዲለን"።
❤ በዚያን ጊዜም ዮሐንስ እንዳላቸው በጾም በጸሎት ሱባዔ ያዙ የነሐሴ ወር እንደ ዛሬ ዐሥራ ስድስተኛ ቀን በሆነ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉንም ሐዋርያት ወደ ሰማይ አወጣቸው። በታላቅ ክብር በተወደደ ልጅዋ ቀኝ ተቀምጣ ከሥጋዋ ተዋሕዳ ተነሥታ እመቤታችን ማርያምን አዩዋት። እጆቿንም ዘርግታ የከበሩ ሐዋርያትን እያንዳንዳቸውን ባረከቻቸው በልባቸውም እጅግ ደስ አላቸው።
❤ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በከበረ ሥጋውና ደሙ ላይ ሠራዒ ካህን ሆነ ። እስጢፋኖስም አዘጋጀ ዮሐንስም "በመፍራት ቁሙ" አለ። ሁሉም ሐዋርያት በመሠዊያው ዙሪያ ቆሙ በዚያን ጊዜ ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ ታላቅ ደስታ ሆነ።
❤ ጌታችንም የቅዳሴውን ሥርዓት በፈጸመ ጊዜ ሥጋውንና ደሙን አቀበላቸው። ከዚያም በኪሩቤልና በሱራፌል ሠረገላ ተቀምጣ በምታርግ ጊዜ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እናቱ እመቤታችን ማርያምን እንዲህ ብሎ ተናገራት "በዚች ቀን የሆነ የዕርገትሽን መታሰቢያ በዓለም ውስጥ እንዲሰብኩ ልጆችሽ ሐዋርያትን እዘዣቸው። መታሰቢያሽን የሚያደርገውን ሁሉ ተጠብቆም በዚች ቀን ቅዱስ ቁርባንን የሚቀበለውን ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ። የእሳትን ሥቃይ ከቶ አያያትም መታሰቢያሽን ለሚያደርግ ሁሉ በዚች ቀን ለድኆች በስምሽ ለሚመጸውት ቸርነቴ ትገናኘዋለች ይህም ሥጋሽ ወደ ሰማይ ያረገበት ነው"።
❤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምም ክብር ይግባውና ጌታችንን እንዲህ አለችው "ልጄ ሆይ እነሆ በዐይኖቻቸው አዩ በጆሮቻቸውም ሰሙ በእጆቻቸውም ያዙ ሌሎችም ታላላቅ ደንቆች ሥራዎችን አዩ"። እመቤታችንም ይህን ስትናገር ጌታችን ሰላምታ ሰጥቷቸው በታላቅ ደስታ ወደ ደብረ ዘይት ተመለሱ።
❤ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ በፍጹም ደስታ መታሰቢያዋን እናደርግ ዘንድ ይገባናል እርሷ ስለእኛ ወደ ተወደደ ልጅዋ ሁልጊዜ ትማልዳለችና። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ይማረን ። በረከቷም ከርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ከአባ መርቆሬዎስና ከአባ ማትያስ ከሁሉም ሊቃነ ጳጳሳትና ኤጲስቆጶሳት ጋራ ሐዋርያት ከሰበሰቧት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች ከሁላችን ጋራ ይኑር ለዘላለሙ አሜን።
+ + +
❤ የዕለቱ ምልጣን፦ ሃሌ ሉያ "በኃይለ አጥናን ዘሞዖ ለሰይጣን አሐዱ ቅዱስ እምቅዱሳን ጊዮርጊስ ረባን ሰባኬ ትንሣኤሃ ለእመ ብርሃን አማን ምዑዝ ከመ ዕጣን"። ትርጉም፡- በቅድስት ሥላሴ ኃይል (በሰባቱ ሀብታት ኃይል ሰይጣንን ያሸነፈው) ከቅዱሳን አንዱ ቅዱስ ጊዮርጊስ መኰንን (የነገሥታት ዘር) ለብርሃን እናት ትንሣኤዋን የሚመሰክር በእውነት እንደ ዕጣን መዓዛው ያማረ ነው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ።
1 161
✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️✴️
ሥርዓተ ማኅሌት ዘነሐሴ ፲፮ በዓለ ቅድስት ኪዳነምህረት
🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡🟡
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።
@EOTCW
@EOTCW
❣መልክአ ሥላሴ፦
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
@EOTCW
@EOTCW
❣ዚቅ፦
ወታስተሥርዩ ኃጥያተ ህዝብኪ ተበውሐ ለኪ፤ እም አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ከመ ትኲኒ ተንከተመ ለውሉደ ሰብእ፤ ለሕይወት ዘለዓለም፤ ለኪ ይደሉ ከመ ትኵኒ መድኀኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ፤ ኦ መድኃኒተ ኩሉ ዓለም ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰዓሊ ለነ ቅድስት
@EOTCW
@EOTCW
❣ነግስ፦
እምጌቴሴማኒ ፈለሰት ኀበ ዘሉዓሌ መካን፤ውስተ ቤተ መቅደስ ረባቢ ዘመሳከዊሁ ብርሃን፤ አንቀጸ አድኅኖ ማርያም ጽላተ ኪዳን፤ኵሉ ይብልዋ በአኅብሮ ዘበዕብራይስጢ ልሳን፤ ዕፀ ጳጦስ ይዕቲ እንተ በአማን ቅድስተ ቅዱሳን፤ እመቅድሐ ከርሣ ተቀድሐ አስራባተ ወይን ወውስቴታ ተሠርዓ ቁርባን።
@EOTCW
@EOTCW
❣ዚቅ፦
ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን መዝገቡ ለቃል፤ ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን አንቀጸ ብርሃን፤ዕፀ ጳጦስ እንተ በአማን ጽጌ ደንጉላት፤ ሐረገ ወይን ዘእምነገደ ይሁዳ፤ እንተ ሠረፀት ለሕይወት።
@EOTCW
@EOTCW
❣መልክዓ ኪዳነምህረት፦
ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ኀበ ሕንጻ ሕይወት ዘተሐደሰ፤ እምቅድመ ዝኒ ኀቤሁ ሥጋ ወልድኪ ፈለሰ፤ ቤዛዊተ ዓለም ማርያም አስተበቁዓኪ አንሰ፤ ትቤዝዊ በኪዳንኪ ዘዚዓየ ነፍሰ፤ እስመ በሥራያ ይዕቲ ቀብዓተኒ ፈውሰ።
@EOTCW
❣ዚቅ፦
ደብተራ ፍጽምት ዘጳዉሊ፤ወማኅደሩ በጽድቅ ዘገብራ ከሃሊ፤ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ፤በመሰንቆሁ እንዘ የኃሊ፤ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ ወዓሊ።
@EOTCW
❣ወረብ፦
ደብተራ ፍጽምት ዘጳዉሊ ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ/፪/
በመሰንቆሁ እንዘ የኃሊ ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ ወዓሊ/፪/
@EOTCW
@EOTCW
❣መልክአ ማርያም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፣እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፣ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትዕዛዝ፣ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፣ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።
@EOTCW
❣ዚቅ
ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ፤ወልድኪ ይጼዉዓኪ፤ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር።
@EOTCW
❣ወረብ፦
ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ ማኅደረ መለኮት/፪/
"ወልድኪ"/፪/ይጼዉዓኪ ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር/፪/
@EOTCW
@EOTCW
❣መልክዓ ማርያም፦
ሰላም ለእስትፋስኪ ዘመዓዛሁ ሕይወት፤ከመ መዓዛ ዕፀ ኅሩይ ዘውስተ ገነት፤ማርያም ድንግል ቤተ ቅድሳት፤ ጽንሕኒ ውስተ ሠናይ ወሰውርኒ እሞት፤በአክናፍኪ ርግብየ ኅሪት
@EOTCW
❣ዚቅ፦
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ ፤መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል፤ ወኵሉ ነገራ በሰላም
@EOTCW
❣ወረብ፦
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ/፪/
መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል/፬/
@EOTCW
❣መልክዓ ፍልሰታ
ሰላም ለፍልሰተ ሥጋኪ ዘኢይቀብል ሞገሱ፤ ወዘኢይነጸፍ ባሕርየ ተውዳሱ፤ ማርያም ታዕካ ለእግዚአብሔር ጽርሐ መቅደሱ፤ተበሃሉ በሰማያት እለ ኪያኪ አፍለሱ፤ ማርያምሰ በምድር ታንሶሱ።
@EOTCW
❣ዚቅ፦
ማርያም ጽርሕ ንጽሕት፤ማሕደረ መለኮት፤እኅቶሙ ለመላእክት ሰመያ፤ ሰማያዊት እንተ በምድር ታንሶሱ
@EOTCW
❣አመላለስ፦
ማርያም ጽርሕ ንጽሕት/፪/
ጽርሕ ንጽሕት ማሕደረ መለኮት/፪/
@EOTCW
❣ምልጣን፦
ትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር፤ኀደረ ላዕሌሃ፤ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ሠናይትየ፤ፀቃውዕ ይውኅዝ እምከናፍሪሃ
@EOTCWW
❣አመላለስ፦
ፀቃውዕ ይውኅዝ/፪/
ይውኅዝ እምከናፍሪሃ/፬/
@EOTCW
❣ወረብ፦
ትርሢተ ወልድ መለኮት ወፍቅር ኀደረ ላዕሌሃ/፪/
ይቤላ ርግብየ ወይቤላ ሠናይትየ/፪/
@EOTCW
@EOTCW
❣እስመ ለዓለም ፦
በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወኁብርት፤እኅትየ መርዓት አዳም አጥባትኪ እምወይን፤ መዓዛ ዕፍረትኪ እምኲሉ አፈው፤እትፌሳሕ ወእትሐሠይ ብኪ፤ናፍቅር አጥባትኪ እምወይን፤ርቱዕ አፍቅሮትኪ ኵለንታኪ ሠናይት እንተ እምኃቤየ፤ማ፦ አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ በላዕሌኪ፤ፃኢ እምሊባኖስ እኅትየ መርዓት።
@EOTCW
@EOTCW
❣አመላለስ፦
አልብኪ ነውር ወኢምንትኒ በላዕሌኪ/፪/
ፃኢ እምሊባኖስ እኅትየ መርዓት/፬/
@EOTCW
@EOTCW
❣ወረብ፦
"በአልባሰ ወርቅ"/፪/ዑፅፍት ወኁብርት/፪/
እኅትየ መርዓት አዳም አጥባትኪ/፪/
@EOTCWW
ሰላም፦
ንዒ ኀቤየ እንቲአየ ሠናይት ርግብየ ፤መዓዛ አፉሃ ከመ ኮል፤ ወኵሉ ነገራ በሰላም
@EOTCWW
#ይቀላቀሉ & #ለወዳጅዎ_ሼር_ያርጉ
1 161
🍀🍀🍀🍀🍀🍀☘☘☘☘☘☘
አመ ፲፮ ለነሐሴ በዓለ ቅድስት ኪዳነምህረት ስርዓተ ዋዜማ
❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️❄️
ዋዜማ በ፩
ሃሌ ሉያ
እግዝእትየ እብለኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ፤ወተወልደ እምኔኪ ቃለ ጽድቁ ለአብ፤ማርያምሰ ተሐቱ ዉስተ ከርሡ ለአዳም፤ከመ ባሕርይ ፀዓዳ፤ ፆረቶ እግዝእቱ ለአዳም፤
@EOTCW
@EOTCW
❣ማርያምሰ ተሐቱ፤ ዉስተ ከርሡ ለአዳም፤ከመ ባሕርይ ፀዓዳ፤ድንግል ተሐቱ በከርሠ አዳም፤ድንግል ተሐቱ በከርሠ አዳም።
@EOTCW
❣አመላለስ፦
ድንግል ተሐቱ በከርሠ አዳም/፪/
ድንግል ተሐቱ በከርሠ አዳም/፬/
@EOTCWW
@EOTCWW
❣ለእግዚአብሔር በምላዕ፦
ሰአሊ ለነ ማርያም እንተ እግዚእ ኀርያ ሰአሊ ለነ ማርያም
@EOTCWW
@EOTCWW
❣እግዚአብሔር ነግሠ፦
ደብተራ ፍጽምት ዘጳዉሊ፤ወማኅደሩ በጽድቅ ዘገብራ ከሃሊ፤ፈለሰት እምዘይበሊ ኀበ ኢይበሊ፤በመሰንቆሁ እንዘ የኃሊ፤ዳዊት አቡሃ ዘወልዳ ወዓሊ።
@EOTCW
@EOTCWW
❣እግዚኦ ጸራዕኩ ኀቤከ
ዕፀ ጳጦስ ይዕቲ እንተ በአማን ይብልዋ ቅድስተ ቅዱሳን ዕፀ ጳጦስ ይዕቲ እንተ በአማን
@EOTCWW
@EOTCWW
❣ይትባረክ
እግዝእትየ እብለኪ ወእሙ ለእግዚእየ እብለኪ ቃል ቅዱስ ኀደረ ላዕሌኪ።
@EOTCWW
@EOTCWW
❣ሰላም
ሃሌ ሉያ (፫) ፃኢ እምሊባኖስ ስነ ሕይወት፤ ርቱዕ አፍቅሮትኪ፤ ቡርክት አንቲ እምአንስት ማኅደረ መለኮት ፃኢ እምሊባኖስ ስነ ሕይወት ሰላም ለኪ ማርያም እመ አምላክ፤ ወልድኪ ይጼዉዓኪ፤
ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር።
@EOTCWW
@EOTCWW
❣አመላለስ፦
ወልድኪ ይጼዉዓኪ ወልድኪ ይጼዉዓኪ/፪/
ውስተ ሕይወት ወመንግሥተ ክብር/፬/
@EOTCWW
#ይቀላቀሉ & #ለወዳጅዎ_ሼር_ያርጉ
1 161
🥖 ደብረ ታቦር 🥖
ክፍል ሦስት
ከዚህ በኋላ ጴጥሮስ "ጌታ ሆይ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው" ሲል ተደምጧል፡፡ ይህም የተለያየ ትርጉም አለው፡፡ ቃል በቃል (Literaly) ስናየው ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታ ሆይ በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው ማለቱ "አንተ እያበላኸን እየፈወስከን፣ ሙሴ እነዚህ መከራ ያደርሱቡኛል ይገድሉኛል ያልካቸውን ጸሐፍትና ፈሪሳውያን እንዳይመጡ በደመና እየጋረደ፣ ቢመጡም አልያስ እሳት እያዘነመ እያባረራቸው በዚህ መኖር ለእኛ መልካም ነው" ማለቱ ሲሆን ምሥጢራዊው መልእክቱ ግን "የኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት በሚታመንበት፣ ወልድ ዋሕድ በምትለው ሃይማኖት መኖር ለእኛ መልካም ነው፡፡
ሰይጣን ድል በተደረገባት በታቦር ተራራ ምሳሌም በምትሆን በወንጌል ሕይወት፣ አንድም በቤተ ክርስቲያን መኖር ለእኛ መልካም ነው"ማለቱ ነው፡፡
ታቦር ተራራ የወንጌል ምሳሌ ነው!
ተራራ ሲወጡት ያደክማል፣ ከወጡት በኋላ ግን ጭንጫውን፣ ግጫውን ሲያሳይ ደስ ያሰኛል፡፡ ወንጌልም ሲማሯት ትከብዳለች በኋላ ግን ጽድቅን እና ኃጢአትን ለይታ ስታሳውቅ ደስ ታሰኛለች፡፡
ታቦር ተራራ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ነው!
ሀ/⏩ በታቦር ተራራ ከብሉይ ኪዳን ነቢያት ኤልያስና ሙሴን፣ ከሐዲስ ኪዳን ሦስቱን ሐዋርያት እንደተገኙ በቤተክርስቲያን ብሉይ ከሐዲስ እንዲነገር ያጠይቃል ፤ ሐዋርያት የሰበኩት ወንጌል አስቀድመው ነቢያት በምሳሌና በትንቢት የተናገሩት እንደሆነ ያስረዳል፡፡ "ነቢያት በቀየሱ ሐዋርያት ገሰገሱ" እንዲል ጳውሎስም "በሐዋርያት በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል" ይላልና ኤፌ ፪፥፳
ለ/⏩ በታቦር ተራራ ከመዓስባን (ባለትዳር) ሙሴን ከደናግል ደግሞ ኤልያስ እንደተገኙ በቤተክርስቲያን በድንግልና የሚኖሩ መናንያን መነኮሳት፣ በሕግ በሥርዓት የሚኖሩ ባለትዳሮችም ይገኛሉና፡፡
ታቦር ተራራ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው!
1/➡️ ተራራ በብዙ ችግር እንዲወጡት ወደ እግዚአብሔር መንግሥትም በብዙ መከራ እንገባ ዘንድ ያስፈልገናልና
ሐዋ ፲፬፥፳፪
2/⏩ በታቦር ተራራ የብሉይ ኪዳን ነቢያት ከሐዲስ ኪዳንም ሐዋርያት እንደተገኙ መንግሥተ ሰማያትን ነቢያትም፣ ሐዋርያትም አንድ ሆነው ይወርሷታልና፡፡
3/⏩ በታቦር ተራራ ከመዓስባን ሙሴ ከደናግል ደግሞ ኤልያስ እንደተገኙ መንግሥተ ሰማያትንም ደናግልም መዓስባንም በአንድ ላይ ይወርሷታልና፡፡
4/⏩ በታቦር ተራራ ሞተው ከተቀበሩት መካከል ሙሴን በብሔረ ሕያዋን ካሉት ደግሞ ኤልያስን እንደመጡ መንግሥተ
ሰማያትንም ሞተው የተቀበሩትም በብሔረ ሕያዋን ያሉትም በአንድነት ይወርሷታልና፡፡
5/⏩ ደብረ ታቦር የቤተ መቅደስ ምሳሌ ናት በቅድስት ቤተክርስቲያን ለሥርዓተ ቅዳሴ የሚሰየሙ ካህናት (ልዑካን)
አምስት ናቸው ሙሴና ኤልያስ የካህናት ጴጥሮስ ፣ዮሐንስ፣ያዕቆብ የዲያቆናት ምሳሌ ጌታችን አምላካችን
የሊቀካህናት ምሳሌ ናቸው።
6/⏩ ደብረ ታቦር የቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት በብሉይ የክርስቶስን መገለጥ የተናገሩ ነብያት በሐዲስ ኪዳን የተገለጠውን የእግዚአብሔር አብ የባህርይ ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ለዓለም የሰበኩ ሐዋርያት በአንድ ሆነው የተገኙባት ጌታቸውንበአንድነት ያመሰገኑባት ናት።
በአጠቃላይ ታቦር ተራራ የክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት የተመሠከረበት፣ የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት የተሰጠበት፤ ፈጣሪ ከቅዱሳን ሰዎቹ ጋር የተገኘበት፤ በልበ ሐዋርያት የነበረ ሰይጣን ድል የተደረገበት፤ የሐዋርያት በተለይም የሦስቱ ባለሟልነት የተገለጠበት፤ አሉባልታና ተራ ወሬ የከሸፈበት፤ የቅዱሳንን ክብር ለሚያናንቁ ተራራም እንኳን "ቅዱስ" እንደሚባል የተማርንበት፤ የብሔረ ሕያዋን መኖር የተመሰከበረበት፤ የትንሣኤ ሙታን ዋስትና የተገለጠበት የክብር ሰገነት፣ የምሥጢር መቅደስ፣ ታላቅ ትምህርት ቤትም ጭምር ነው፡፡
ፈጣሪያችን እግዚአብሔር እስከ መጨረሻዋ ሕቅታ ድረስ በታቦር ተራራ በተመሰለች ቤተ ክርስቲያን በሃይማኖታችን ጸንተን የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች የስሙ ቀዳሾች እንድንሆን የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን፡፡ አሜን!!
ወስብሐት ለእግዚብሔር
በዲ/ን የአብስራ ጌታሁን
~ተፈጸመ~
https://t.me/Eotcw
