uk
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Відкрити в Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Показати більше
1 161
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
photo content

photo content

❤ ጌታ ኢየሱስም ወደ ቅርጺቱ መለስ ብሎ እንዲህ አላት "አብርሃምን እንዳነጋገርኩት አላመኑምና ሔደሽ እንዲህ በይው። አስቀድሞ አዳምን የፈጠረው፣ አንተንም ወዳጁ ያደረገህ፣ አንተ ልጆችህ ይስሐቅና ያዕቆብን ይዘህ ተነሥ ከመቃብርም ወጥተህ ወደዚህ ኑ የካህናት አለቆችን ትወቅሱአቸው ዘንድ እኔ የማውቃችሁና የተነጋገርኳችሁ መሆኔን አስረዷቸው"። ቅርጺቱም ሥዕል ይህን ሰምታ እያየናት ሔደች ወደ አብርሃምም መቃብር ደርሳ በውጭ ቁማ ጠራቻቸው። ወዲያውኑ ከሦስቱ አርእስተ አበው ጋር ዐሥራ ሁለቱ ወጡ ከእኛ ውስጥ "ወደ ማን ነው የተላክሽ" አሏት። ቅርጺቱም እንዲህ ብላ መለሰች ወደ "ሦስቱ የአባቶች አለቆች ነው እናንተ ግን እስከ ትንሣኤ ሙታን ድረስ ተኙ" ያን ጊዜም ወደ መቃብራቸው ተመለሱ። እሊህ ሦስቱ አባቶችም የካህናት አለቆችና እኛ ወደ አለንበት ከቅርጺቱ ሥዕል ጋር መጥተው ወቀሷቸው የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነም ነገሩአቸው። ❤ ከዚህም በኋላ ጌታችን አባቶችን "ወደቦታችሁ ሒዱ" አላቸው ወዲያው ተመለሱ ቅርጺቱንም "ወደቦታሽ ተመለሽ" አላት እርሷም ወደ ቀደመው አኗኗርዋ ተመለሰች "ይህንንም አይተው የካህናት አለቆች አላመኑም ሌላም ብዙ አለ ብነግርህ መወሰን አትችልም ነገር ግን ለብልህ ጥቂት ቃል ትበቃዋለች ለሰነፍ ግን ቢነግሩት በቁም ነገር ላይ አይታመንም"። ❤ ከዚህም በኋላ ጌታችን ማነጋገሩን ገታ ራሱንም እንደሚያንቀላፋ አደረገ እንድርያስም አንቀላፋ እንድርያስንና ደቀ መዛሙርቱን እንዲሸከሙአቸውና ሊገቡበት ወደሚሹት አገር በውጭ እንዲአኖሩዋቸው መላእክትን አዘዛቸው። ❤ ከዚህም በኋላ እንድርያስ በነቃ ጊዜ ዐይኖቹን ገለጠ የከተማውንም በር ተመለከተ በየብስም ላይ እንዳለ አውቆ ደነገጠ አደነቀም። ደቀ መዛሙርቱንም አነቃቸውና እንዲህ አላቸው "ጌታችንን በባሕር ላይ ሳለን ያላወቅነው ምን አደረገብን ሲፈትነን መልኩን ለውጦ እንደ ሰው ሁኖ ታይቶናልና"። ደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አሉት "እኛም በጌትነቱ ዙፋን ላይ ሁኖ የመላእክት ሠራዊት ሁሉ በዙሪያው ሁነው ጌታችንን አየነው አብርሃምን፣ ይስሐቅን፣ ያዕቆብንም ቅዱሳንን ሁሉ አየናቸው ንጉሥ ዳዊትም በመሰንቆ ይዘምር ነበር። እናንተንም ዐሥራ ሁለት ሐዋርያት በፊቱ ቁማችሁ ዐሥራ ሁለቱንም የመላእክት አለቆች በፊታችሁ ሌሎች መላእክት በኋላችሁ ሁነው አየናችሁ። እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስንም መላእክትን እንዲህ ብሎ ሲያዛቸው ሰማነው የሚሉአችሁን ሁሉ ሐዋርያትን ስሟቸው"። ❤ እንድርያስም በሰማ ጊዜ እጅግ ደስ አለው ይህን ድንቅ ምሥጢር ያዩ ዘንድ ደቀ መዛሙርቱ የሚገባቸው ሆነዋልና። ከዚህም በኋላ እንድርያስ ዐይኖቹን ወደ ሰማይ አቅንቶ እንዲህ ብሎ በታላቅ ድምጽ ጮኸ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ከእኛ ከባሮችህ ሩቅ እንዳልሆንክ አወቅሁ። ነገር ግን በመርከብ ላይ እኔ እንደማስተምረው ሰው መስለኸኝ በድፍረት ተናግሬሃለሁና ጌታዬ ይቅር በለኝ"። ❤ በዚያንም ጊዜ የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእንድርያስ ዳግመኛ ተገለጠለት እንዲህም አለው። "አዎን እኔ ነኝ በሊቀ ሐመር አምሳል በባሕር ውስጥ የተገለጥኩልህና መርከቡን የቀዘፍኩልህ። አትፍራ አትደንግጥ እኔ ከአንተ ጋራ እኖራለሁ ይህንንም ብሎ ወደ ሰማያት በክብር ዐረገ እንድርያስም መንገዱን ሄደ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጌቶቻችን ሐዋርያት በጸሎታቸው ይማረን በረከታቸውም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ❤ በነሐሴ ወር የሚበብ ንባብ በእግዚአብሔር ቸርነት ደረሰ ተፈጸመ። ክብር ጌትነት ገንዘቡ ለሆነ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የዕለቱ አራራይ ዜማ፦ "መላእክት ፆርዎ ለእንድርያስ ወአብጽሕዎ ሀገረ በላዕተ ሰብዕ ወይቤልዎ መኑ አንተ ወመኑ ስመከ ወምነ ታመልክ አውስአ እንድርያስ ወይቤሎሙ አንሰ አመልኮ ለእግእዚእየ ኢየሱ ፡ክርስቶስ ለዘገብረ ብርሃናተ ዐበይተ ባሕቲቱ"፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እስመ ኀቤከ እጼሊ እግዚኦ። በጽብሐ ስምዐኒ ቃልየ። በጽብሐ እቀውም ቅድሚከ ወአስተርኢ ለከ"። መዝ 5፥2-3። የሚነበቡት መልዕክታት ሮሜ 13፥1-ፍ.ም፣ 1ጴጥ 2፥2-11 እና የሐዋ ሥራ 27፥33-ፍ.ም። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 4፥12-17። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የነቢዩ ቅዱስ ሚልክያስ የዕረፍት በዓልና የዚህ ዓመት የመጨረሻ ዕለተ ሰንበት ለሁላችንንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ነሐሴ ፴ (30) ቀን። ❤ እንኳን ከዐሥራ ሁለቱ ደቂቅ ነቢያት አንዱ ለሆነው ለታላቁ ነቢይ ለቅዱስ ሚልክያስ ለዕረፍት በዓል፣ ጌታችን በባሕር ውስጥ በሊቀ ሐመር አምሳል ለሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ ለተገለጠለትና ድንቅ ተአምር ላደረገበት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ከሀገረ ፈርማ ኤጲስቆጶስ ከአባ ሙሴ ዕረፍት እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ "ጽርሕ ንጽሕት ዘሚልክያስ።" ትርጉም፦ የሚልክያስ ንጽሕት አዳራሽ አንቺ ነሽ። ሊቁ አባ ሕርያቆስ በቅዳሴ ማርያም። + + + ❤ "ሰአሉ ለነ ነቢያት ስኩራነ መንፈስ ምሉኣን ሞገስ አቅርንተ ሥሉስ ቅዱስ"። ትርጉም፦ የሥላሴ ነጋሪቶች (ዐዋጅ፡ነጋሪዎች) የምትኾኑ ክብርን የተመላችኊ በመንፈስ ቅዱስ የተቃኛችኊ ነቢያት ለምኑልን ለእኛ አማልዱን። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በሰዓታቱ ላይ። + + + ❤ ነቢዩ ቅዱስ ሚልክያስ፦ ይህም ነቢይ የእስራኤል ልጆች ከተሰደዱበት ከባቢሎን ሀገር በተመለሱ ጊዜ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመተላለፋቸው ገሥጿቸዋል። ❤ ሁለተኛም ነቋር ስለሆነ መሥዋዕት ስለ አሥራትና በኵራት ገሥጿቸዋል። በዚህ ነቢይ አንደበት እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሯልና "ርኅራኄ አድርጋችሁ ምጽዋትን መጽውቱ፣ ዐሥራቴንና በኵራቴንም አስገቡና እስቲ ፈትኑኝ እኔ ከሰማይ ዝናሙን ባላወርድላችሁ በረከትንም አስቲበቃችሁ ባልጨምርላችሁ የምድራችሁንም ፍሬ ነቀዝና መሰክ እንዳይበሉት እከለክላለሁ"። ❤ ዳግመኛም ከክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ አስቀድሞ መጥምቁ ዮሐንስ ስለ መምጣቱ ስለ ነቢዩ ኤልያስም ተናገረ። ደግሞ ስለ አይሁድ የሥርዓተ ክህነት ፍጻሜ ተናገረ በአሕዛብም አገር ውስጥ ለእግዚአብሔር የሚቀበላቸውን መሥዋዕት የሚያሳርጉ ዕውነተኞች ንጹሐን ካህናት እንዳሉ ገለጠላቸው። ❤ በበጎ ተጋድሎውም እግዚአብሔርን ከአገለገለ በኋላ ከዚህ ዓለም በመፍለስ በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በነቢዩ ቅዱስ ሚልክያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የዕለቱ እስመ ለዓለም፦ "እስመ ለዓለም ምሕረቱ ይቤሎ ኢየሱስ ለእንድርያስ ምንተ ገብረ እግዚእከ ኃይለ ዘአራየከ ወይቤሎ አንሰ ርኢኩ ጊሜ ወፀዳለ ዐቢየ ነጎድጓደ ወሎቱ ማኅለቅተ ብርሃን"። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ ጌታችን በባሕር ውስጥ ለሐዋርያ እንድርያስ በሊቀ ሐመር አምሳል ተገልጦ ድንቅ ተአምር እዳደረገለት፦ "እንድርያስም ጌታችንን በመርከብህ አሳፍረን ነገር ግን የምንከፍልህ የመርከብ ዋጋ የለንም" አለው። በሊቀ ሐመር የተመሰለ ጌታችንም "ስለምን የላችሁም" አለው። እንድርያስም "በከረጢታችን ወርቅን፣ ብርን እንዳንይዝ ስለአዘዘን ነው" አለው። ጌታችንም "እንዲህ ከሆነ ወደ መርከቤ ወጥታችሁ ተሳፈሩ" አላቸው ያንጊዜም ወደ መርከብ ወጥተው ተሳፈሩ። ❤ ከዚህም በኋላ ጌታችን እንድርያስንና ደቀ መዛሙርቱን "ከባሕሩ ማዕበል የተነሣ መታገሥ እንድትችሉ ተነሥታችሁ እንጀራ ብሉ" አለ። አንድርያስም አድንቆ እንዲህ አለው "በመንግሥተ ሰማያት የሕይወት እንጀራ እግዚአብሔር ይስጥህ"። ደቀ መዛሙርቱ ግን በባሕር ላይ ጉዞ ስለአልለመዱ ከባሕሩ ማዕበል ፍርሀት የተነሣ መብላት መነጋገርም ተሳናቸው ። ❤ ጌታችንም እንድርያስን "ደቀ መዛሙርትህን ወደ ምድር እንዲወርዱ እዘዛቸው ሲፈሩ አያቸዋለሁና ይህ ካልሆነ እንዳይፈሩ አንተ የኢየሱስ ደቀ መዝሙሩ ከሆንክ ጣዕም ባለው ቃል አስተምራቸው እነሆ ከየብስ ርቀናልና" አለው። ጌታችንም መርከቡን መቅዘፍ ጀመረ እንድርያስም ማስተማርና ማጽናናት ያዘ በልቡም ጸለየ ያን ጊዜም ከባድ እንቅልፍን አንቀላፉ ስለተኙለትም እንድርያስ ደስ አለው። ❤ እንድርያስም ወደ ጌታችን ተመልሶ እንዲህ አለው "ዐሥራ አራት ጊዜ በባሕር ላይ ጒዞ አድርጌአለሁ እንዳንተ የሚቀዝፍ አላገኘሁም"። ጌታም መልሶ እንዲህ አለው "እኛስ በባሕር ላይ ስንጓዝ ሁል ጊዜ እንቸገራለን። ነገር ግን አንተ የክብር ባለቤት የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዝሙር እንደሆንክ ባሕር ስለአወቀችህ ማዕበሏን በአንተ ላይ አላነሣችም" እንድርያስም በታላቅ ቃል እንዲህ ብሎ ጮኸ። "የክብር ባለቤት ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ አመሰግንሃለሁ ከሚያከብርህ ሰው ጋር ተገናኝቼ ተነጋግሬአለሁና"። ❤ ከዚህም በኋላ ጌታችን እንድርያስን እንዲህ አለው "አንተ የክርስቶስ ደቀ መዝሙሩ ነህና ንገረኝ። አይሁድ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ስለምን አላመኑም የሠራውን ብዙ ድንቅ ተአምርን ሰምተናልና" አለው። እንድርያስም እንዲህ አለው "አዎን ወንድሜ እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ገልጦልናል አንካሶችንም በትክክል እንዲሔዱ አድርጓልና፣ ደንቆሮዎችንም አሰምቷልና፣ ዲዳዎችንም አናግሮአልና፣ ለምጻሞችንም አንጽቷልና፣ ውኃውንም ወይን አድርጓልና፣ አምስት እንጀራና ሁለት ዓሣን አንሥቶ ያዘ ሕዝቡንም በመስክ ሣር ላይ እንዲቀመጡ አዘዘ ሣሩም እንጀራ እስቲለብስ ድረስ በልተው ጠገቡ የተረፈውንም በብዙ ቅርጫቶች አነሣን ይህም ሁሉ ሲሆን አላመኑም"። ❤ ጌታ ኢየሱስም እንዲህ አለው "ይህን ያደረገ በግልጥ ነው ወይስ በሥውር"። እንድርያስም እንዲህ አለው "ይህንስ በግልጥ ነው ያደረገ በሥውር ያደረገውም አለ ግን የምትፈትነኝ መሰለኝ" ጌታችንም እንዲህ አለው "ወንድሜ ሆይ ልቤን ደስ ስለሚላት ነውና ንገረኝ"። እንድርያስም እንዲህ አለው "ልጄ ሆይ በጎ ሥራህን ሀሉ እግዚአብሔር ይፈጽምልህ አሁንም ስማ ጌታችን ያደረገውን ተአምር እኛ ዐሥራ ሁለታችን ሐዋርያቶቹ ከእርሱ ጋራ ስንጓዝ ከሊቃነ ካህናትና ከሕዝቡ ብዙዎች አሉ። ወደ ምኵራብም ደረስን ጌታችንም እንዲህ አለ "በሰማይ ባሉ በኪሩቤልና በሱራፌል አምሳል በምድር ላይ ሰው የሠራትን ይቺን የተቀረጸች ሥዕል ታያላችሁን"። ❤ ከዚህም በኋላ ወደሥዕሊቱ ተመልሶ "ብልህ ሰው የተጠበበብሽ የሰማያውያን መልክን ያደረግሽ አንቺን እላለሁ ከቦታሽ ተነቅለሽ ውረጂ የካህናት አለቆችንም ውቀሻቸው እኔም ዕሩቅ ብእሲ ወይም እግዚአብሔር እንደሆንኩ መስክሪ" አላት። ወዲያውኑ ከቦታዋ ተነቅላ ወረደች እንደሰውም በመናገር እንዲህ አለች "እናንተ የደነቆራችሁ አይሁድ የራሳችሁ መደንቆር ያልበቃችሁ ሌሎችንም ለማደንቆር የምትሹ ለድኅነታችሁ ሰው የሆነ እግዚአብሔርን እንዴት ዕሩቅ ብእሲ ትሉታላችሁ አስቀድሞ ሰውን የፈጠረው በንፍሐት ልጅነትንም የሰጠው ይህ ነው። አብርሃምን የተናገረው፣ ይስሐቅንም ከመታረድ ያዳነው፣ ያዕቆብንም ወደ አገሩ ያስገባው ይህ ነው ለሚፈሩት በረከትን የሚሰጥ ለማይታዘዙለት ቅጣትን የሚያዘጋጅ ይህ ነው ። ❤ እውነት እነግራችኋላሁ እናንተ ስለምትክዱት ሕጉንና ሥርዓቱንም ትለውጣላችሁና ስለዚህ እነሆ መስዋዕታችሁ ይሻራል ምኵራቦቻችሁም በዋሕድ ወልደ እግዚአብሔር ስም አብያተ ክርስቲያናት ይሆናሉ"። ይህንንና የሚመስለውን ተናግራ ዝም አለች። እኛም የካህናት አለቆችን መልሰን እንዲህ አልናቸው "እነሆ ቅርጺቱ ሥዕል ተናግራ ወቀሰቻችሁ ታምኑ ዘንድ ይገባችኋል"። የካህናት አለቆችና አይሁድም እንዲህ አሉን "ይህ የሚያናግረው በሥራይ ነው አብርሃምን በወዴት አገኘው ከሞተ ዘመኑ ብዙ ነውና"።

ጥብቅ ማሳሰቢያ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!! ነሐሴ ፳፯ ቀን ፳፻ ፲፬ ዓ.ም """"""""""""""""""""""""""""" አዲስ አበበ -ኢትዮጵያ """""""""""""""""""""" , ሰምኑን የቤተክርስቲያናችን ባልሆኑ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን አማካኝነት የቤተክርስቲያናችንን አርማ በመጠቀምና የቤተክርስቲያናችን ማኅበራዊ መገናኛዎች በማስመሰል ልዩ ልዩ ዜናዎችን በመሥራት ሕዝበ ክርስቲያኑን ለማደናገር የሚሞክሩ ድረ ገጾች እየተሰራጩ መሆኑን ደርሰንበታል። እነዚሁ ድረ ገጾች ላይም በተለይ የቤተክርስቲያናችን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የሰጡት መግለጫ በማስመሰል የሚያስተላልፏቸው ዘገባዎች ሐሰተኞች ከመሆናቸውም በላይ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ስም የተከፈቱ የቲዩተርም ሆነ የፌስ ቡክ አካውንት የሌለ መሆኑን እየገለጽን ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልዕክት ካለ በቤተክርስቲያናችን መገናኛ ብዙሃንና በሕዝብ ግንኙነት ድረ ገጾች ብቻ የሚያስተላለፉ መሆኑን እየገለጽን ሕዝበ ክርስቲያኑ ከነዚህ ህጋዊ የቤተክርስቲያናችን መገናኛ ዘዴዎች ውጪ የሚተላለፉ መልእክቶች ሁሉ የሐሰት መረጃዎች መሆናቸውን በመረዳት ህዝበ ክርስቲያኑን ለማደናገር ከተከፈቱ ሐሰተኛ የማኅበራዊ ድረ ገጾች ራሱን በመጠበቅና ለክፉ ዓላማ ማሳኪያ ተብለው የተከፈቱ መገናኛ አውታሮችን እንዲጋለጡ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መልዕክቷን ታስተላልፋለች። መረጃው ለሁሉም እንዲዳረስ ሼር በማድረግ እንዲተባበሩን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች። የኢኦተቤክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ❤❤❤

photo content

☘☘☘☘ መዝሙር ዘሰንበት ✨✨✨✨ በ 5 - አምላኪየ ኄር አንሥአኒ በትንሣኤከ;ጎሐ ጽባሕ ዘአንተ ሠራዕከ:አምላኪየ ኄር አንሥአኒ በትንሣኤከ ከመ ኢይርሳዕ ሰብሖ ስምከ:አምላኪየ ኄር አንሥአኒ በትንሣኤከ ከመ ትጽገብ ምድር እምፍሬ ተግባርከ አምላኪየ ኄር አንሥአኒ በትንሣኤከ ዓይነ ኩሉ ነፍስ ይሴፎ ኪያከ: አምላኪየ ኄር አንሥአኒ በትንሣኤከ እስመ በእንተ ሰብአ ሰንበተ ሠራዕከ:አምላኪየ ኄር አንሥአኒ በትንሣኤከ፤መሐሪ ወትረ ስቡሕ ስምከ https://t.me/Eotcw # Join & share

photo content

photo content

ሙ ለቅዱሳን። ወለድኩከ እምከርሥ እምቅድመ ኮከበ ጽባሕ"። መዝ109፥3።የሚነበበው ወንጌል ሉቃ 2፥1-8። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "እዜም ወእሌቡ ፍኖተ ንጹሐ። ማእዜ ትመጽእ ኀቤየ። ወአሐውር በየዋሃተ ልብየ ማእከለ ቤትየ"። መዝ 100፥1-2። የሚነበቡ መልዕክታት ገላ 3፥15-21፣ 1 ዮሐ 4፥9-18 እና የሐዋ ሥራ 20፥28-31 የሚነበበው ወንጌል ማቴ 5፥1-17። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የአባ ዮሐንስ ሐጺር የፍልሰት ሥጋ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ነሐሴ ፳፱ (29) ቀን። ❤ እንኳን ለታላቁ ለትሑቱና ለትዕግስተኛው አባት ለዮሐንስ ሐጺር የአባ እንጦንዮስ በሆነ በቁልዝም ገዳም ከዐረፈ በኋላ ወደ አስቄጥስ ገዳም ለሥጋው ለፈለሰት በዓልና ለሰማዕቱ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ አትናቴዎስ ለሁለቱ አገልጋዮች ቅዱሳን ሰማዕታት ገርሲሞስና ቴዎዶጦስ ለዕረፍታቸው በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰበው፦ ለክብር ባለቤት ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ከእመቤታች ቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ ለተወለደበት ለልደቱ (ከበዓለ ወልድ) ከወራዊ መታሰቢያ በዓል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ "ሰላም ለዮሐንስ ሐጺር ትሩፈ ምግባር፤ ዘአጥረየ ትሕትና ወወረሰ ልዕልና"። ትርጉም፦ ትሕትናን ገንዘብ አድርጎ ልዕልናን የወረሰ መልካም ሥራው የበዛ ለኾነ ለዮሐንስ ሐጺር ሰላምታ ይገባል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በተአምኆ ቅዱሳን ላይ። + + + ❤ አባ ዮሐንስ ሐጺር የሥጋው ፍልሰት፦ ይህም የአባ እንጦንዮስ በሆነ በቊልዝም ገዳም ከዐረፈ በኋላ ነው። ለእስክንድርያ አባ ዮሐንስ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ እርሱም ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት አርባ ስምንተኛ የሆነ ነው። እርሱም ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔደ የከበሩ መነኰሳትም እንዲህ አሉት "የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ሥጋ በዚህ በቤተ ክርስቲያኑ ቢሆን እኛም ሥጋው በአለበት ለፈጣሪያችን እግዚአብሔር እንሰግድ ዘንድ እንሻ ነበር"። ❤ ያን ጊዜ የእግዚአብሔር ቸርነት አነሣሣችውና ስሙ ቆዝሞስ ለሚባል ለአንድ አበ ምኔት መልእክትን ጻፈ ከእርሱም ጋር የቊልዝም አገር የሆነ አረጋዊ አለ በደረሱም ጊዜ በዚያን ሰዓት ሥጋውን መውሰድ አልተቻላቸውም። የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ሥጋ የኬልቄዶንን ጉባኤ በተቀበሉ መለካውያን ዘንድ ይጠበቅ ስለነበረ ነገር ግን ቦታውን አወቁ ተረዱ ወደ ቦታቸውም ተመልሰው ሃይማኖታቸው የቀና ምእመናን ሰዎችን አገኙ እነርሱም በዚያች አገር የሚኖሩ ናቸው ስለርሱ የመጡበትን ነገሩአቸው። ❤ ከጥቂት ቀኖች በኋላም ከታላላቅ ዐረቦች ወገን ለቊልዝም አገር መኰንን ተሾመ እርሱም ለኤጲስቆጶስ አባ ሚካኤል ወዳጁ ነው ሊቀ ጳጳሳት አባ ዮሐንስም ስለ ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺር ሥጋ ወደ ኤጲስቆጶሱ መልእክትን ጻፈ፤ በመልእክቱም የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ሥጋ ከከሐድያን መለካውያን እጅ እስከ አፈለሱት ድረስ መልእክተኞች አእሩግ መነኰሳትን ምክንያት ፈልጎ እንዲረዳቸው በማሳሰብ አዘዘው። ❤ ኤጲስቆጶሱም በሰማ ጊዜ ፈጽሞ ደስ አለው ሒዶም ወዳጁ ለሆነ ለመኰንኑ ጸሐፊ ነገረው። ጸሐፊውም ለመኰንኑ ነገረው። እነሆ መኰንኑም ከመነኰሳቱ ጋራ ሔደ ጸሐፊውም "መነኰሳቱ ወደዚያ ቦታ እንዲገቡ ምክንያት እንዴት እናገኛለን" አለ ። መኰንኑም "በልብሶቻቸው ላይ የዓረቦችን ልብሶች ያልብሱአቸውና ከእኔ ጋራ ወደዚያ ቦታ ይምጡ" አለ እንዲሁም እንዳላቸው አደረጉ። ❤ ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሔደ ከእርሱም ጋራ ብዙ ፈረሰኞች ሰዎች ብዙ ሕዝብም የአስቄጥስ ገዳም የከበሩ አረጋውያን አሉ ወደቊልዝም ገዳምም ደረሱ። መኰንኑም በዚያ የሚኖራውን የመለካውያን ኤጲስቆጶስ እንዲህ ብሎ አዘዘው "ያንተን ሰዎች ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ አስወጣቸው በዚች ሌሊት እኔ በውስጧ አድራለሁና" ያ መለካዊም መኰንኑ እንዳዘዘው አደረገ። ❤ መነኰሳቱም እንስሶቻቸውን ከከተማ ውጭ አዘጋጅተው በሌሊት ወደዚያ ገብተው የቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርን ሥጋ ይዘው ወደ ምስር ደረሱ ከዚያም ወደ አስቄጥስ ገዳም ደረሱ የአባ መቃርስ ገዳም መነኰሳትም መስቀሎችን፣ ወንጌሎችን፣ ማዕጠንቶችንና መብራቶችን በመያዝ እየዘመሩና እያመሰገኑ ተቀበሏቸው ወደ አባት መቃርስ ሥጋም አቀረቡትና ከእርሱ ተባረኩ በላዩም ብዙ ሽቱዎችን ነሰነሱ የቊርባን ቅዳሴንም ቀደሱ የከበረ ወንጌልም በሚነበብ ጊዜ ታላቅ ድንቅ ተአምር ተገለጠ ቤተ ክርስቲያኒቱ ሁለመናዋ በሰማያዊ ብርሃን በራች። ከቶ እንደርሱ ሆኖ የማያውቅ በጎ መዓዛ ሸተተ ታላቅ ደስታም ሆነ በዚያም ቦታ ሰባት ቀን ኖረ። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ ራሱ ቤተ ክርስቲያን ተሸክመው ወሰዱት ዕብራውያንም "በእግዚአብሔር ስም የሚመጣ የተባረከ" ነው እያሉ መድኃኒታችንን እንደተቀበሉት ልጆቹ መነኰሳት ተቀበሉትና ወደ ቦታው አኖሩት ከእርሱም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሊቀ ጳጳሳት አባ ማርቆስ በወጣ ጊዜ ወደ አባ ዮሐንስ ሐጺር ቤተ ክርስቲያን ገባ። ከእርሱም ጋር ብዙዎች ኤጲስቆጶሳትና የእስክንድርያ አገር ታላላቆች ከግብጽ አገር ሁሉ አሉ። የአባ ዮሐንስ ሐጺር ሥጋ የተጠቀለለበትን ሰሌን ገልጦ ከእርሱ ተባረከ መሪር ልቅሶንም አለቀሰ ያን ጊዜ ሥጋው ሲገለጥ መብረቅና ነጐድጓድ ሆነ። በቤተ ክርስቲያኑም ውስጥ ያሉት ሁሉም ደንግጠው ወደቁ ሊቀ ጳጳሳቱም ሰሌኑን መልሶ በፍጥነት ሥጋውን ጠቀለለ በሽብሸባ እየዘመሩና እያመሰገኑ እንደቀድሞው ሸፈነው። ❤ ከዚህም በኋላ ዳግመኛ እንዲህ እያሉ ሊያመሰግኑ ጀመሩ "ፈጣን ደመና ሁነህ የመንፈስ ቅዱስን ዝናም የተሸከምክ ሠለስቱ ደቂቅ ወዳሉበት ወደ ባቢሎን የሔድክ በላይህ በአደረ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ወደ እስከንድርያ አገር የተመለስክ ሁለተኛም ወደ ቊልዝም የሔድክ የጣዖታትን ቤቶች አፍርሰህ ሃይማኖትን የሰበክ በሽተኞችን የፈወስክ አጋንንትን ያስወጣህ ወደርስትህም የተመለስክ አንተ የበረከት ማደሪያ ነህና"። ❤ የአባ ዮሐንስ ሐጺር የሥጋው ፍልሰት ከንጹሐን ሰማዕታት ዘመን በአምስት መቶ ሃያ ዓመት ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሐንስ ሐጺር ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ሰማዕቱ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ አትናቴዎስ ሁለቱ አገልጋዮች ቅዱሳን ሰማዕታት ገርሲሞስና ቴዎዶጦስ፦ ይህንንም ቅዱስ አትናቴዎስን የእንጦኒቆስን የጭፍራ አለቃውን ልጅ እርሱ እንዳጠመቃት በንጉሥ ዘንድ ወነጀሉትና ንጉሥ አርስያኖስ ያዘው እርሱም ክርስቲያን እንደሆነ ታመነ ብዙ ሥቃይንም አሠቃየው። ❤ በሃይማኖቱም ጸና እንጂ ሃይማኖቱን ባልካደ ጊዜ ራሱን በሰይፍ ይቆርጡ ዘንድ አዘዘ እንዲሁም እሊህን ሁለቱን አገልጋዮች ገርሲሞስንና ቴዎዶጦስን በግርፋትና በስቅላት ከቀጣቸው በኋላ ራሶቻቸውን በሰይፍ አስቆረጠ ሦስቱም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበሉ። ❤ አማንያን ሰዎችም መጡ ለወታደሮችም ገንዘብ ሰጥተው የቅዱሳኑን ሥጋቸውን ወሰዱ በአማሩ ልብሶችም ገንዘው በሣጥን ውስጥ አኖሩአቸው ከሥጋቸውም ታላላቅ ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎታቸው ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በሰማዕቱ ኤጲስቆጶስ ቅዱስ አትናቴዎስ ሁለቱ አገልጋዮች ቅዱሳን ሰማዕታት ገርሲሞስና ቴዎዶጦስ ጸሎት ይማረን። በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የነሐሴ 29 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለልደትከ ዘተለዓለ ዓቅሙ። እምልደተ ጻድቃን ድኀርት ወእለ ቀደሙ። በይቡስ ጌጋይ እስመ አባላትየ ሐሙ። ይትከዐው በአሥራውየ ለምሕረትከ ዝናሙ። ወበአምትንትየ ገቦከ ደሙ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የነሐሴ29። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ምስሌከ ቀዳማዊ በዕለ ኃይል። ወብርሃኖ

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 22:23-34 "ወበይእቲ ዕለት መጽኡ ኀቤሁ ሰዱቃውያን" - "በዚያን፡ቀን፦ትንሣኤ፡ሙታን፡የለም፡የሚሉ፡ሰዱቃውያን፡ወደ፡እርሱ፡ቀረቡ፥እንዲህም፡ብለው፡ጠየቁት፦መምህር፡ሆይ፥ሙሴ፡አንድ፡ሰው፡ልጅ፡ሳይወልድ፡ሲሞት፡ወንድሙ፡ሚስቱን፡አግብቶ፡ለወንድሙ፡ዘር፡ይተካ፡አለ። ሰባት፡ወንድማማች፡በእኛ፡ዘንድ፡ነበሩ፤ፊተኛውም፡ሚስት፡አግብቶ፡ሞተ፥ዘርም፡ስለሌለው፡ሚስቱን፡ለወንድሙ፡ተወለት፤ እንዲሁ፡ደግሞ፡ሁለተኛው፡ሦስተኛውም፥እስከ፡ሰባተኛው፡ድረስ። ከሁሉም፡በኋላ፡ሴቲቱ፡ሞተች። ሁሉ፡አግብተዋታልና፥በትንሣኤ፡ቀንስ፥ከሰባቱ፡ለማናቸው፡ሚስት፡ትሆናለች? ኢየሱስም፡መልሶ፡እንዲህ፡አላቸው፦መጻሕፍትንና፡የእግዚአብሔርን፡ኃይል፡አታውቁምና፡ትስታላችሁ። በትንሣኤስ፡እንደእግዚአብሔር፡መላእክት፡በሰማይ፡ይሆናሉ፡እንጂ፡አያገቡም፡አይጋቡምም። ስለ፡ትንሣኤ፡ሙታን፡ግን፦እኔ፡የአብርሃም፡አምላክ፥የይሥሐቅም፡አምላክ፡የያዕቆብም፡አምላክ፡ነኝ፡የሚል፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ወደ፡እናንተ፡የተባለውን፡አላነበባችሁምን፧የሕያዋን፡አምላክ፡ነው፡እንጂ፡የሙታን፡አይደለም። ሕዝቡም፡ይህን፡ሰምተው፡በትምህርቱ፡ተገረሙ። ፈሪሳውያንም፡ሰዱቃውያንን፡ዝም፡እንዳሠኛቸው፡በሰሙ፡ጊዜ፡አብረው፡ተሰበሰቡ።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.35 KB

28/12/2014 ዓ.ም (፳፰/፲፪/፳፻፲፬ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 አንሣእኩ አዕይንትየ መንገለ አድባር። እምአይቴ ይምጻእ ረድኤትየ። ረድኤትየሰ እምኀበ እግዚአብሔር፡፡ መዝ. 120÷1 🕯 ትርጉም ዓይኖቼን ወደ ተራሮች አነሣሁ። ረዳቴ ከወዴት ይምጣ? ረዳቴ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነው። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 1:1-18 "መጽሐፈ ልደቱ ለእግዚእነ" - "የዳዊት፡ልጅ፡የአብርሃም፡ልጅ፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ትውልድ፡መጽሐፍ። አብርሃም፡ይሥሐቅን፡ወለደ፤ይሥሐቅም፡ያዕቆብን፡ወለደ፤ያዕቆብም፡ይሁዳንና፡ወንድሞቹን፡ወለደ፤ ይሁዳም፡ከትዕማር፡ፋሬስንና፡ዛራን፡ወለደ፤ፋሬስም፡ኤስሮምን፡ወለደ፤ ኤስሮምም፡አራምን፡ወለደ፤አራምም፡ዐሚናዳብን፡ወለደ፤ዐሚናዳብም፡ነአሶንን፡ወለደ፤ነአሶንም፡ ሰልሞንን፡ወለደ፤ ሰልሞንም፡ከራኬብ፡ቦኤዝን፡ወለደ፤ቦኤዝም፡ከሩት፡ኢዮቤድን፡ወለደ፤ኢዮቤድም፡እሴይን፡ወለደ፤ እሴይም፡ንጉሥ፡ዳዊትን፡ወለደ። ሰሎሞንም፡ሮብዓምን፡ወለደ፤ሮብዓምም፡አቢያን፡ወለደ፤አቢያም፡አሣፍን፡ወለደ፤ አሣፍም፡ኢዮሳፍጥን፡ወለደ፤ኢዮሳፍጥም፡ኢዮራምን፡ወለደ፤ኢዮራምም፡ዖዝያንን፡ወለደ፤ ዖዝያንም፡ኢዮአታምን፡ወለደ፤ኢዮአታምም፡አካዝን፡ወለደ፤ አካዝም፡ሕዝቅያስን፡ወለደ፤ሕዝቅያስም፡ምናሴን፡ወለደ፤ምናሴም፡አሞፅን፡ወለደ፤ አሞፅም፡ኢዮስያስን፡ወለደ፤ኢዮስያስም፡በባቢሎን፡ምርኮ፡ጊዜ፡ኢኮንያንንና፡ወንድሞቹን፡ወለደ። ከባቢሎንም፡ምርኮ፡በዃላ፡ኢኮንያን፡ሰላትያልን፡ወለደ፤ሰላትያልም፡ዘሩባቤልን፡ወለደ፤ ዘሩባቤልም፡አብዩድን፡ወለደ፤አብዩድም፡ኤልያቄምን፡ወለደ፤ኤልያቄምም፡አዛርን፡ወለደ፤ አዛርም፡ሳዶቅን፡ወለደ፤ሳዶቅም፡አኪምን፡ወለደ፤አኪምም፡ኤልዩድን፡ወለደ፤ ኤልዩድም፡አልዓዛርን፡ወለደ፤አልዓዛርም፡ማታንን፡ወለደ፤ማታንም፡ያዕቆብን፡ወለደ፤ ያዕቆብም፡ክርስቶስ፡የተባለውን፡ኢየሱስን፡የወለደች፡የማርያምን፡ዕጮኛ፡ዮሴፍን፡ወለደ። እንግዲህ፡ትውልድ፡ሁሉ፡ከአብርሃም፡እስከ፡ዳዊት፡አሥራ፡አራት፡ትውልድ፥ከዳዊትም፡እስከባቢሎን፡ምርኮ፡ዐሥራ፡አራት፡ትውልድ፥ከባቢሎንም፡ምርኮ፡እስከ፡ክርስቶስ፡አሥራ፡አራት፡ትውልድ፡ነው። የኢየሱስ፡ክርስቶስም፡ልደት፡እንዲህ፡ነበረ። እናቱ፡ማርያም፡ለዮሴፍ፡በታጨች፡ጊዜ፥ሳይገናኙ፡ከመንፈስ፡ቅዱስ፡ፀንሳ፡ተገኘች።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

0.90 KB

28/12/2014 ዓ.ም (፳፰/፲፪/፳፻፲፬ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ዘሠርዓ ለአብርሃም። ወመሐለ ለይስሐቅ። ወዐቀመ ስምዐ ለያዕቆብ፡፡ መዝ. 104፥9 🕯 ትርጉም ለአብርሃም ያደረገውን። ለይስሐቅም የማለውን። ለያዕቆብ ሕግ የሆነውን አቆመ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

photo content