uk
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Відкрити в Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Показати більше
1 161
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
photo content

❤ በዚያንም ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱ የሐር ልብስ አስመጥቶ በክብር ገነዘው ወደ ቤተ ክርስቲያንም ወስደው ከሥጋው እስከሚባረኩ በቤተ መቅደስ አኖሩት። ካህናቱና ሕዝቡ ሁሉ ከዚህም በኋላ ብዙ በሽተኞች ዕውሮች ሐንካሶች ደንቆሮዎች ዲዳዎች መጥተው ከሥጋው በተሳለሙ ጊዜ ሁሉም ከደዌያቸው ዳኑ በዚያችም ቀን ታላቅ ደስታ ሆነ። ሕዝቡም በበዙ ጊዜ የልጁን የሙሴን ሥጋ ከዐልጋው ላይ እንዳይጥሉት አውፊምያኖስ ፈራ ብዙ ገንዘብም አምጥተው ይበትኑ ዘንድ አገልጋዮቹን አዘዛቸው። ሥጋውን ትተው ወደ ተበተነው ገንዘብ ይሔዳሉ ብሎ አስቦ ነበር ግን ከቶ አንድ እንኳ ወደ ገንዘብ የሔደ የለም። ❤ ከዚህም በኋላ ሥጋውን በታላቋ በሐዋርያት ጴጥሮስና ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን አኖሩ ከሥጋውም ብዙ ድንቆች ተአምራት ተደረጉ ዕውሮች አይተዋልና ሐንካሶችም ቀንተው ይሔዳሉና ደንቆሮዎችም ይሰማሉና ለምጻሞችም ይነጻሉና አጋንንት ያደሩባቸውም ይወጡላቸዋልና ሁሉም ካለባቸው ደዌ ይድናሉና። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ሙሴ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት 14 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለዘሚካኤል ዘተሰምየ አረጋዌ። እስመ ሑረቱ በጥበብ ወፍናዊሁ ልባዌ። ምስሌሁ ኅቡረ ዘበአሐዱ ህላዌ። ሰላም ለቅዱሳን ዘተሰነዓው ስንዓዌ። ከመ በጸሎት ይሥዓሩ ሥርዓቶ ለአርዌ"። ትርጉም፦ አረጋዊ ተብሎ የመጠሪያ ስም የወጣለት ለኾነ ለዘሚካኤል ሰላምታ ይገባል፤ አኪያኺያዱ በጥበብና ጐዳናውም በማስተዋል ነውና በጸሎት የአውሬ ዲያብሎስን ሥርዐቱን ይደመስሱ ዘንድ በአንድ አኗኗር ከርሱ ጋር አንድነት ስምምነትን ላደረጉ ለቅዱሳን ሰላምታ ይገባል። + + + ❤ "ሰላም ለገብረ ክርስቶስ እንተ አንደየ አባሎ። በዴዴ አቡሁ አክልብት እስከነ ለሐሱ ቊስሎ። አዕረፈ ዮም ለእግዚአብሔር ከመ ሰአሎ። እምእደ አግብርት ተኰንኖ ወእምእደ አእማት ተጽዕሎ። እምድኅረ ፈጸመ ወሠለጠ ገድሎ"። ትርጉም፦ ባባቱ ደጃፍ ውሾች ቊስሉን እስኪልሱት ድረስ ሰውነቱን ያደኸየ ለኾነ ለገብረ ክርስቶስ ሰላምታ ይገባል፤ በወንዶች አገልጋዮች እጅ ተሠቃይቶ፤ በሴት አገልጋዮችም ተዋርዶ (ተቃልሎ) ገድሉን ፈጽሞ ከአከናወነ በኋላ እግዚአብሔርን እንደለመነው ዛሬ ዐረፈ። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 14። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ ከዚህም በኋላ አውፊምያኖስ ባሮቹን ጠርቶ ብዙ ገንዘብን ሰጣቸው እንዲህም አላቸው "ልጄን እስከምታገኙት ድረስ ሁለት ሁለት እየሆናችሁ ወደ ሀገሩ ሁሉ ሒዱ ለድኆችና ለችግረኞች ምጽዋትን ስጡአቸው"። እነርሱም በሀገሩ ሁሉ ተበታተኑ። ከአባቱ አገልጋዮችም ሁለቱ አገኙት ግን አላወቁትም ምጽዋትንም ከድኆች ጋር ሰጡት ቅዱስ ሙሴም አውቋቸው እንዲህ ብሎ አመሰገነ "ጌታዬ ፈጣሪዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ስለ አንተ ፍቅር ከአባቴ ባሮች እጅ ምጽዋትን እቀበል ዘንድ ለዚህ ታላቅ ክብር አድለህኛልና አመሰግንሃለሁ"። የአባቱ አገልጋዮችም ብዙ ወራት በሁሉ አገሮች ሲዞሩ ኑረው ወደ አውፊምያኖስ ጌታቸው ተመለሱ። የእግዚአብሔር ሰው ቅዱስ ሙሴም ከሰንበት ቀኖች በቀር እህልን የማይቀምስ እስቲሆን ድረስ ተጋድሎውን በመጨመር በየሁለትና በየሦስት ቀኖች የሚጾም ሆነ። ❤ ከዚህም በኋላ እመቤታችን የከበረች ድንግል ማርያም ከዚያች ቤተ ክርስቲያን ካህናት ውስጥ ለአንድ ደግ ጻድቅ ቄስ ተገልጻ እንዲህ አለቸው "በጥዋት ወደ ቤተ ክርስቲያን ውጭ ውጣ ከምሰሶ አጠገብ ብቻውን ቁሞ የሚጸልይ ሰው ታገኛለህ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ወደ ቤተ ክርስቲያን ግባ በለው በውጭ አትተወው ጾሙ ጸሎቱ በእግዚአብሔር ፊት መዓዛው ጣፋጭ እንደሆነ ዕጣን ተቀባይነትን አግኝቷልና"። ሲነጋም ያ ቄስ ወደ ቅዱስ ሙሴ ሒዶ "የእግዚአብሔር ሰው ሆይ ወደ ቤተ ክርስቲያን ግባ" አለው ሙሴም "አባቴ ሆይ በከበረ ቦታ ላይ መቆም የማይገባኝ ኃጢአተኛ ነኝና ተወኝ" አለው ቄሱም "ወደ ቤተ መቅደስ አስገባህ ዘንድ ከቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ወዳንተ ተልኬአለሁ" ብሎ መለሰለት ወደ ቤተ መቅደስም ያስገባው ዘንድ እንዳዘዘችው ነገረው ከዚህም በኋላ አስገባው። ❤ ከዚህም በኋላ የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ ወደ ሀገረ ጠርሴስ ይሔድ ዘንድ አስቦ እርሷም የሐዋርያው ጳውሎስ አገር ናት እንዲህም አለ "እስከ ዕለተ ሞቴ በውስጥዋ እኖራለሁ ሥጋው ምንም በሮሜ አገር የሚኖር ቢሆንም የትውልድ አገሩ ናትና በረከትን እቀበላለሁ" ብሎ ነው። ❤ በሌሊትም ወጥቶ ወደ ባሕር ዳርቻ ሔደ ወደ ጠርሴስም ይሔድ ዘንድ በመርከብ ተጫነ በባሕር መካከልም ታላቅ ነፋስ ተነሣባቸው ባሕሩም ከነፋሱ ኃይል የተነሣ ታወከ ወደየትም እንደሚሔዱ አያውቁም ነበር ቀኑ ጨልሞባቸዋልና ስለ ነፍሳቸውም ድኅነት ወደ እግዚአብሔር ለመኑ በዚያንም ጊዜ ባሕሩ ጸጥ ብሎ ታላቅ ደስታ ሆነ ብርሃንም ታየ ወደ ሮሜ ሀገር ወደብም እንደ ደረሱ አወቁ። ❤ ቅዱስ ሙሴም ተነሥቶ በመርከብ ውስጥ ያሉትን በሰላምታ ተሰናብቷቸው ጉዞውን ጀመረ በልቡም እንዲህ አለ "ይህ ሁሉ በእግዚአብሔር ፈቃድ ሆነ እንግዲህ እስከ ዕለተ ሞቴ ራሴን ለማንም እንዳልገልጥ ሕያው ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያውቀኝ የለምና በአባቴ ደጅ እኖራለሁ" ይህንንም ብሎ ወደ አባቱ ቤት ተጓዘ። በመንገድም ላይ አባቱን ተገናኘው ብዙ ሰውም ተከትሎት ነበር የእግዚአብሔር ሰው ሙሴም ቀረብ ብሎ አባቱ የተቀመጠበትን ፈረስ ልጓሙን ያዘ እንዲህም አለው "እግዚአብሔር የባረከህ ያከበረህ አንተ ደግ ሰው እግዚአብሔርም ኃጢአትህን ይቅር ይበልህ የልብህንም ልመና ይስጥህ እኔም መጻተኛ ድኃ ሰው እንደ ሆንኩ እወቅ ለመጻተኛነቴና ለችግረኛነቴ የምትራራ ሁነህ ከማዕድህ ፍርፋሪ ልትመግበኝ ከወደድህ መኖሪያዬን በቤትህ አንጻር በደጃፍህ አድርግልኝ ዋጋህንም የሚሰጥህ እግዚአብሔር ነውና"።በዚያንም ጊዜ አውፊምያኖስ የልጁ የሙሴን ስደት አስታውሶ በተቃጠለ ልብ አለቀሰ መኖሪያውንም በቤቱ ደጅ እንዲሠሩለት አዘዘለት። ሁለተኛም ከአገልጋዮቹ አንዱን በሚያሻው ነገር ሁሉ እንዲአገለግለው አዘዘው። ❤ የእግዚአብሔር ሰው ሙሴም ያን የሚያገለግለውን "ወንድሜ ሆይ ከሰንበት ቀኖች በቀር መብልና መጠጥ እንዳታመጣልኝ እለምንሃለሁ ይኸውም ከቁርባን በኋላ ግማሽ እንጀራና የጽዋ ውኃ ብቻ ነው" አለው። በጾምና በጸሎትም እየተጋደለ በዚያ በአባቱ ደጅ ዐሥራ ሁለት ዓመት ኖረ። ❤ ሰውን የሚወድ ቸር ጌታችን ኢየሱስ ከዚህ ዓለም ድካም ሊአሳርፈው ወዶ ተገለጠለት እንዲህም አለው "የመረጥሁህ አንተ ብፁዕ ነህ አንተ ፈቃዴን ፈጽመሃልና በዚህ ዓለም ከደስታ ኃዘንን ከብልጽግና ድኅነትን መርጠሃልና እኔም የማይጠፋ ብልጽግናን እሰጥሃለሁ ዳግመኛም ስምህን የሚጠራ መታሰቢያህንም ለሚያደርግ የተራበውን ለሚያጠግብ የተጠማውን ለሚያጠጣ የተራቈተውን ለሚያለብስ ገድልህንም ለሚጽፍ ወይም ለሚያጽፍ ስለ ስምህ በጎ ሥራ ሁሉ ለሚሠራ ቃል ኪዳንን ሰጠሁህ። በሰማያዊት መንግሥትም በጎ ዋጋን እሰጠዋለሁ ተጠራጣሪ ካልሆነ በዚህ ዓለምም እጠብቀዋለሁ ከበጎ ነገር ሁሉ ምንም አላሳጣውም። አሁንም ከአራት ቀን በኋላ እወስድሃለሁ ምርጦቼ ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት ከአሉበትም አኖርሃለሁ" ይህንንም ብሎ ከእርሱ ዘንድ ወደ ሰማይ በታላቅ ክብር ዐረገ። ❤ ቅዱስ ሙሴም ከእግዚአብሔር ዘንድ ይህን ጸጋ በተሰጠ ጊዜ እጅግ ደስ አለው ያን የሚያገለግለውንም ወንድሜ ሆይ እንግዲህ "ስለ እኔ ከመድከም ታርፋለህና ወረቀትና ቀለም አምጣልኝ" አለው። ያ አገልጋይም ከአነጋገሩ የተነሣ አድንቆ ወረቀቱንና ቀለሙን አመጣለት የከበረ የእግዚአብሔር ሰው ሙሴም ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ገድሉን ሁሉ ጻፈ በአራተኛውም ቀን ያቺን የጻፋትን መጽሐፍ በእጁ ጨበጣት በእሑድ ቀንም በሰላም ዐረፈ። መላእክት "ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት ለሚያገለግሉት የዘላለም ተድላ ደስታ ለሚሰጥ ለነበረና ለሚኖር ፈጣሪያችን ምስጋና ይሁን" እያሉ ነፍሱን ተቀበሏት። ሕዝቡም ሁሉ በቅዳሴ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተሰብስበው እያሉ ከመሠዊያው በላይ "የጌታቸውን ሕጎቹንና ሥርዓቱን የሚያደርጉ ደጎች አገልጋዮች ባሮች የተመሰገኑ ናቸው እነርሱ ወደ ዘላለም ተድላ ደስታ ይገባሉና" የሚል ቃልን ሲጮህ ሰሙ ። ❤ ሊቀ ጳጳሳቱና ኤጲስቆጶሳቱ ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ሕዝብም ሁሉ በሰሙ ጊዜ በላያቸው ታላቅ ፍርሀት ወደቀባቸው። የቅዳሴውም ሥርዓት ከተፈጸመ በኋላ ይህን ምሥጢር ይገልጽላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ በመጸለይ ማለዱ በዚያንም ጊዜ "የእግዚአብሔርን ሰው በአውፊምያኖስ ቤት ፈልጉት እነሆ እርሱ ነፍሱን በእግዚአብሔር እጅ ሰጥቷልና" የሚል ቃልን ሰሙ። ሊቀ ጳጳሳቱም ይህን ነገር ሰምቶ አውፊምያኖስን ጠራውና "ይህ ታላቅ ጸጋ በቤትህ ውስጥ ሲኖር በሕይወቱ ሳለ እንድንጎበኘው በረከቱንም እንድንቀበል ለምን አልነገርከንም" አለው አውፊምያኖስም እንዲህ ብሎ መለሰ "ክቡር አባት ሆይ ቅድስናህ ይመስክር ይህን የሚመስል በቤቴ ውስጥ እንዳለ አላወቅሁም"። ❤ በዚያንም ጊዜ ሊቀ ጳጳሳቱ ከሁሉ ካህናትና ሕዝብ ጋር ተነሥቶ ወደ አውፊምያኖስ ቤት ሔደ የከበረ የእግዚአብሔር ሰው ሙሴንም በዐረፈበት ቦታ አገኙት ክርታሱም በእጁ ውስጥ ነው ሊቀ ጳጳሳቱም ያቺን ክርታስ አንሥቶ "የእግዚአብሔር ሰው ሙሴ የአውፊምያኖስ ልጅ እናቱም አግልያስ" እስከሚለው ስሙ እስቲደርስ በሕዝቡ ሁሉ ፊት አነበባት። እናትና አባቱም በሰሙ ጊዜ ደነገጡ መራር ልቅሶንም አለቀሱ ቤተሰቦቻቸውም ሁሉ ከዚህም በኋላ ሊቀ ጳጳሳቱ አጽናንቶ ጸጥ አደረጋቸው።

እርሱም "በእግዚአብሔር ዘንድ እተውሻለሁ እኔም ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስን ልከተለው እሔዳለሁ የአባቴ መንግሥት አላፊ ነውና አንቺም መሐላሽን አስቢ" አላት ያን ጊዜ መሐላዋን አስባ ዝም አለች። ❤ ለሠርጉም የታደሙት ሁሉ እንደተኙ በሌሊት ወጥቶ ሔደ ወደ ባሕርም ዳርቻ ደርሶ በመርከብ የሚጓዙ መንገደኞችን አገኘ የዓመት መንገድ ወደሚሆን አርማንያም እስከሚደርስ ከእነርሱ ጋር ተጓዘ። ነግቶ ወደ ሠርጉ አዳራሽ አባትና እናቱ በገቡ ጊዜ ሙሽራውን ልጃቸውን አላገኙትም ሙሽሪትንም "ልጃችን ወዴት አለ?" ብለው ጠየቋት እርሷም እንዲህ አለቻቸው። "በሌሊት ወደ እኔ ገባ መሐላን አማለኝ ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ ራሴንም ስሞኝ ከእኔ ዘንድ ወጣ እኔም እያለቀስኩ ብቻዬን አደርኩ" ነገርዋንም ሰምተው ወድቀው በመጮህ ታላቅ ልቅሶን አለቀሱ ። ❤ በዚያችም ጊዜ በሀገሮች ውስጥ ሁሉ ልጁን ገብረ ክርስቶስን ይፈልጉት ዘንድ ንጉሡ አምስት መቶ አገልጋዮቹን ላከ ለድኆችና ለምስኪኖችም ምጽዋት አድርገው የሚሰጥዋቸውን ብዙ ገንዘብን ሰጣቸው። ገብረ ክርስቶስ ግን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ስም በአርማንም አገር በተሠራች በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ደጅ የሚኖር ሆነ። አባቱ የላካቸውም ሁለቱ አገልጋዮች ከዚያ ደርሰው ስለርሱ መረመሩ ግን ወሬውን ማግኘት ተሳናቸው ለድኆችም ምጽዋትን ሰጡ እርሱም ከድኆችም ጋር ምጽዋትን ተቀበለ። ❤ በዚያም ዐሥራ አምስት ዓመት ከኖረ በኋላ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለአንድ ቄስ ተገለጸችለት ቦታውንም አመልክታ እንዲህ አለችው። "የእግዚአብሔር ሰው ገብረ ክርስቶስን ይዘህ ከቤተ ክርስቲያን ውስጥ አስገባው ከውጭ አትተወው" ቄሱም እመቤታችን እዳዘዘችው አደረገ። ❤ ከዚህም በኋላ የተመሰገነ ገብረ ክርስቶስ በሌሊት ተነሣ ከእመቤታችንም ሥዕል ፊት ቁም ጸለየ እንዲህም አላት "እመቤቴ ሆይ የተሠወረ ሥራዬን አንቺ ለምን ገለጥሽ አሁንም ወደሚሻለኝ ምሪኝ" ይህንንም ብሎ የእመቤታችንን ሥዕሏን ተሳልሞ በሌሊት ወጥቶ ወደ ባሕሩ ወደብ ደረሰ ወደሌላ ሀገርም ሊሔድ ወዶ በመርከብ ተሳፈረ። ግን በእግዚአብሔር ፈቃድ ከአባቱ አገር ደረሰ የአባቱና የእናቱም ባሮች እየናቁትና እየሰደቡት በአባቱ ደጅ ዐሥራ አምስት ዓመት ኖረ። ሲገቡና ሲወጡም ሽታው እንዳያስጨንቀን "ይህን ምስኪን አስወግዱልን" ይላሉ ወጭትና ድስትም አጥበው በላዩ ይደፉበታል ውሾችም እንዲናከሱበትና እንዲበሉት የሥጋ ትርፍራፊ ይጥሉበታል ውሾች ግን ቁስሉን ይልሱለት ነበር እንደዚህም አብዝተው አሠቃዪት ። ❤ ከዚህም በኋላ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ለመነ "ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለአባቴና ለእናቴ ባሮች በደል እንዳይሆንባቸው ወዳንተ ውሰደኝ"። በዚያንም ጊዜ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙን ለሚጠራ መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው። ከዚህም በኋላ ገድሉን ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ጻፈ በእጁም ጨብጧት ጥቅምት 14 ቀን ዐረፈ። ❤ በእሑድ ቀንም ሕዝቡ ሁሉና ካህናቱ ከሊቀ ጳጳሳቱ ጋር በቅዳሴ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሳሉ "የእግዚአብሔርን ሰው በንጉሥ ቴዎዶስዮስ ቤት ፈልጉት" የሚል ቃል ከሰማይ ሰሙ በዚያን ጊዜ ሔደው በአረፈበት ቦታ አገኙት። በእጁም ውስጥ የተጨበጠ ክርታስን አዩ ሊወስዷትም ሽተው መውሰድ ተሳናቸው ። ❤ በአንድነትም በጸለዩ ጊዜ እጁ ተፈትታ ወስደው አነበቧት አባትና እናቱም ልጃቸው እንደሆነ አወቁ ታላቅ ጩኸትም ሆነ መሪር ልቅሶንም አለቀሱ አክብረውም ቀበሩት መቃብሩም በሽተኞችን ሁሉ በመፈወስ ድንቆች የሆኑ ብዙ ተአምራትን የሚያደርግ ሆነ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ገብረ ክርስቶስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ከሮሜ ሀገር የሆነ የከበረ የእግዚአብሔር ሰው ቅዱስ ሙሴ፦ የዚህም ቅዱስ የአባቱ ስም አውፊምያኖስ የእናቱ አግልያስ ነው እነርሱም እግዚአብዘሔርን የሚፈሩ እጅግም ባለጸጎች ናቸው። አብዝተውም ይመጸውታሉ ሁልጊዜም ይጸልያሉ እስከ ዘጠኝ ሰዓትም ይጾማሉ ድኆችንና ችግረኞችንም ሳይይዙ አይበሉም። ❤ ነገር ግን ልጆች የሏቸውም ነበር የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ የተባረከ ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ እግዚአብሔርን ይለምኑት ነበር ጌታችንም ልመናቸውን ተቀብሎ ይህን መልኩ እጅግ ያማረ የከበረና የተባረከ ልጅን ሰጣቸው በወለዱትም ጊዜ በርሱ ደስ ብሏቸው ለድኆችና ለምስኪኖች ታላቅ ምሳ አደረጉ ስሙንም ሙሴ ብለው ሰየሙት ትርጓሜውም የእግዚአብሔር ሰው ማለት ነው ስለእርሱ እግዚአብሔር ልመናቸውን ሰምቷልና። ❤ ከዚህም በኋላ ሙሴን በመልካም አስተዳደግ አሳደጉት መንፈሳዊና ሥጋዊ ትምህርትን ጥበብን ሁሉ አስተማሩት። አድጎም በጎለመሰ ጊዜ አባቱ አውፊምያኖስ ሚስቱ አግልያስን "እነሆ ልጃችን ሙሴ አደገ ሚስትን ልናጋባውና በጋብቻውም ደስ ሊለን ለእኛ ይገባናል" አላት። የሙሴ እናት አግልያስም ሰምታ በዚህ ነገር ደስ አላት ከሮሜ አገር ታላላቆች ሰዎች ወገንም መልኳ እጅግ ያማረ አንዲት ብላቴና አጋቡት። ታላቅ ሠርግንም በማዘጋጀት ሸልመው አስጊጠው በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በጋብቻ ሥርዓት አክሊላትን አቀዳጇቸው። ከዚህ በኋላ ሥጋውንና ደሙንም ተቀብለው ወደሚሠረጉበት ቤት ገቡ። ❤ ከዚህም በኋላ በማግሥቱ አውፊምያኖስ ሚዜውን ጠርቶ እንዲህ አለው ሙሽራው ወደ ሙሽሪቷ ገብቶ የጋብቻውን ሕግ እንዲፈጽም ንገረው ያ ሚዜውም በነገረው ጊዜ ወደ ሙሽራዪቷ ገባ ድንቅ የሆነ ውበቷንና ደም ግባቷን ተመለከተ በልቡም አስቦ እንዲህ አለ "ይህ ሁሉ ውበትና ደም ግባት አላፊ ጠፊ አይደለምን"። ይህንንም ብሎ ወደ ሰማያዊት መንግሥቱ የሚደርስበትን መንገድ እንዲመራው እግዚአብሔርን ለመነው። ሙሽራዪቱንም እንዲህ አላት "የተባረክሽ እኅቴ ሰላም ይሁንልሽ የእግዚአብሔርም ፍቅር አንድነት ከአንቺ ጋር ይኑር ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ እስከምንገናኝ ደኅና ሁኚ"። ይህንንም በሚላት ጊዜ ልብሶቹን አውልቆ ሰጥቷት ከእርሷ ዘንድ ወጣ የተሞሸረበትንም ልብስ ለውጦ ከባሕር ዳርቻ እስከሚደርስ መንገዱን ተጓዘ። ልብሶቹንም ሁሉ ሽጦ ለድኆችና ለችግረኞች ምጽዋትን ሰጠ እርሱም ጨርቅ በመልበስ እንደ ድኃ ሁኖ ቁራሽ እንጀራ እየለመነ በየጥቂቱ እየተመገበ እስከ ሀገረ ሮሀ ድረስ ሔደ። ❤ ከዚያም በደረሰ ጊዜ ወደቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብቶ ለሮሀ ንጉሥ ለአቃርዮስ በስብከቱ ወራት የተላከለትን ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሥዕልና የእመቤታችንን የቅድስት ድንግል ማርያምን ሥዕል አግኝቶ ከሥዕሎቹ ተሳልሞ በረከትን ተቀበለ ወደ ልዑል እግዚአብሔርም ፈጽሞ እያመሰገነ ጸለየ። ወጥቶም ኑሮውን ከድኆችና ከምስኪኖች ጋር አደረገ። ❤ ከዚህም በኋላ መጸለይና መጾምን ጀመረ እስከ ምሽትም ይጾማል በቀንና በሌሊትም ጸሎቱን አያቋርጥም ምጽዋትንም ከድኆች ጋር ተቀብሎ እርሱ መልሶ ለሌሎች ይሰጣል። በዚያቺም ዕለት በነጋ ጊዜ ወደ ሠርጉ አዳራሽ አባትና እናቱ ሲገቡ ሙሽራው ልጃቸው ሙሴ በጫጉላው ቤት እንደ ሌለ ሰሙ ደስታቸውም ወደ ኀዘን የሠርጉም ዘፈን ወደ ልቅሶ ወደ ዋይታ ተለወጠ።

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፲፬ (14) ቀን። ❤ እንኳን ከዘጠኙ ቅዱሳን አንዱ ለሆኑት ለአባ ዘሚካኤል በሚሰሩት ስራቸው አረጋዊ ለተባሉት ለታላቁ አባት ለአቡነ አረጋዊ ከዚህ ዓለም ከሞት ለተሰወሩበት ቀን ለመታሰቢያ በዓል፣ ለቊስጥንጥንያ ንጉሥ ለቴዎዶስዮስ ልጅ ለሙሽራወ ለቅዱስ ለገብረ ክርስቶስና ከሮሜ ሀገር ለሆነ ለእግዚአብሔር ሰው ለቅዱስ ሙሴ ለዕረፍታቸው ዓመታዊ መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከመራክዋና ከእርሱ ጋር ካሉ ሰማዕታት፣ ከድማቴዎስና ከምራይስ ከአራት መቶ ሠላሳ አንድ ሰማዕታት ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዕለቱ አንገሪጋሪ ዜማ ግእዝ፦ ሃሌ ሉያ "ዘእምደብረ ደናግል አባ ኤልያስ ወትሩፈ ምግባር አርከሌድሰ አረጋዊ ጻድቅ ዘውገ ሙሴ ወገብረ ክርስቶስ አማን ዘቀደሰ መንፈስ ቅዱስ"። ትርጉም፦ ከደናግል ቦታ አባ ኤልያስ አረጋዊ አርኬሌድስ ሙሴ ምግባሩ የበዛ (የተመሰከረለት) ገብረ ክርስቶስ ዕውነተኛ መንፈስ ቅዱስ አክብሮታልና (አከበረው) ቀደስው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ አባ ዘሚካኤል (አቡነ አረጋዊ)፦ እኚህ አባት ከ9 ቅዱሳን አባቶች አንዱ ሲሆኑ አባታቸው ይስሐቅ የሮም ንጉሥ ነበሩ፡፡ እናታቸው ንግሥት እደና ይባሉ ነበር፡፡ የመጀመሪያ ስማቸው ዘሚካኤል ነው፡፡ ጥበብ መንፈሳ ሲማሩ አድገው ወደ እስክንድርያ ገዳም ገቡ፡፡ አበምኔቱ አባ ጳኵሚስ በፈቃደ እግዚአብሔር የመጡ መሆናቸውን አውቀው መዓረገ ምንኵስና ሰጥተዋቸዋል፡፡ ❤ የንጉሣዊ የቅንጦት ኑሮ ንቀው ትተው ገዳም ገብተው በምንኵስና ተወስነዋል፡፡ አባታችን በተጋድሏቸውም ከአባ እንጦንስ፣ ከአባ ጳውሊ እና ከአባ መቃርስ ቀጥሎ በአራተኛ ማዕረግ አበ መነኰሳት ሆነው ተመርጠዋል። ❤ በገዳመ ዳውናስ 7 ዓመት ከቆዩ በኋላ ወደ ሮም ተመልሰው ሲያስተምሩ የሀገራችን ኢትዮጵያን ዜና ሰምተው ለመምጣት በ480 ዓ.ም ከአባ ፍሬምናጦስ በኋላ መንገድ ጀመሩ፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም በክንፉ ተሸክሞ አክሱም አድርሷቸዋል፡፡ ተመልሰውም ሄደው ስለ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መስክረዋል፡፡ "ሐዋርያ ሳይላክላት በሃይማኖት በምግባር ጸንታ ትኖራለች" ብለው ለሰባቱ ዘመዶቻቸው አበው መነኰሳት ነገሯቸው፡፡ ስምንቱም ጓዛቸውን ጠቅልለው በሮም ነግሦ የነበሩ ይስሐቅን (አባ ገሪማን) ጨምረው ንጉሥ አልአሜዳ በነገሠ በአምስተኛ ዓመት ማለትም በ480 ዓ.ም ወደ ኢትዮጵያ ዘጠኝ ሆነው መጥተዋል፡፡ ❤ አባ አረጋዊ እናታቸው ቅድስት እድናን ደቀ መዝሙራቸውን ማትያስን አስከትለው እግረ መንገዳቸውን እያስተማሩና ድውያንን እየፈወሱ ደብረ ዳሞ ደረሰዋል፡፡ ከእግረ ደብር ሆነው አሁን "ይህን ተራራ በምን ልወጣው እችላለሁ" እያሉ ሲያወጡ ሲያወርዱ በንግግሩ ሐሰት የሌለበት አምላካችን በነቢዩ ዳዊት ላይ አድሮ በመዝ 90፥11-16 ላይ "በመንገድህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላእክቱን ስለ አንተ ያዝዛቸዋልና፤ እግርህም በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሡሃል። በተኵላና በእባብ ላይ ትጫማለህ፤ አንበሳውንና ዘንዶውን ትረግጣለህ"። እንዳለው የታዘዘ ዘንዶ መጥቶ ስደሳ ክንድ በሚያህል ጅራቱ ጠምጥሞ ቅዱስ ሚካኤል ሰይፈ እሳት ይዞ እየጠበቃቸው ከተራራው አናት አድርሷቸዋል፡፡ ❤ ወዲያው ሃሌ ሉያ ለአብ ሃሌ ሉያ ለወልድ ሃሌ ሉያ ለመንፈስ ቅዱስ ብለው አመስግነዋል፡፡ ቦታውም ደብረ ሃሌ ሉያ ተብሏል፡፡ በዚያ ዕለት ግማሽ ህብስት በልተው ጠገቡ፤ ከዚያ በኋላ ግን ምድራዊ ሕብስት አልተመገቡም፡፡ በሰንበተ ክርስታያን ከቅዳሴ በኋላ ሕብስተ ሰማያዊ እያመጡላቸው ይመገቡ ነበር እንጂ፡፡ ኋላም ዜና ጽድቃቸውን ሰምተው ከስድስት ሺህ ያላነሱ ደቀ መዛሙርት ተሰብስበውላቸዋል፡፡ ❤ ስለ አባታች አቡነ አረጋዊ መሰወር፦ የእርግና ዘመኑ ደረሰ ዘጠና ዘጠኝ ዓመት ሆነው። በነጋም ጊዜ ቆሞ ሲለምንና ጸሎትም ሲያደርግ ተመለከተው በምን ጊዜ ወይም ሰዓት ከነሱ እንደሚሠወር ደቀ መዝሙሩ አባ ማትያስ ይጠባበቅ ወይም በልቡ ያስቡ ነበርና። ❤ ጸሎት ያደርግ ዘንድ ቀድሞ ወደነበረበት ተመልሶ ገባ ወይም ሄደ። ዳግመኛም ሦስት ሰዓት በሆነ ጊዜ ተመልሶ መጣ ነገር ግን ከበዓቱ በደረሰ ጊዜ አላገኘውም እሱ ተሠውሯልና። በዚያም ከመቋሚያና ከመስቀል በስተቀር ምንም ያገኘው ነገር የለም ይህንኑም ለወንድምቹ ነገራቸው። እነርሱም ጮሁ ዋይ ዋይም አሉ እሱንም ያገኙ እየመሰላቸው መስቀሉንና መቋሚያውን ተሸክመው በመሳም መሪር ዕንባን አለቀሱ። ❤ ኀዘናቸውንና ልቅሶአቸውን ከፈጸሙ በኋላ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለክቡር አባታችን አቡነ አረጋዊ የተሰጠውን ቃል ኪዳን ደቀ መዝሙሩ አባ ማትያስ "ምድራዊ መንግስትህን ትተህ ስላገለገልከኝ ህልፈት ሽረት የሌለባት ሰማያዊ መንግስቴን አወርሰሃለሁ" ብሎ ቃልኪዳን እንደሰጠው፡፡ "በስምህ የተማጸነውን እስከ ዐሥራ አምስት ትውልድ ድረስ እምርልሃለሁ አንተም ከሞት ገጽ ትሰወራለህ" ብሎ ተስፋ እደነገራቸው፡፡ ነገራቸው ወንድሞቹም ይህን በሰሙ ጊዜ ፈጽመው ተደሰቱ ኀዘናቸውም ወደ ደስታ ተለወጠ ስለዚህም እግዚአብሔር አመሰገኑት። ❤ በዚያን ጊዜ ቀለምና ብራና አዘጋጅተው ማትያስና ዮሴፍ እየነገሯቸው ለልጅ ልጅ መታሰቢ ሆኖ ይኖር ዘንድ የገድሉንና የቃል ኪዳኑን መጽሐፍ ጻፈ። ❤ ከዚህም በኋላ በመነኰሳት ሥርዓት ማኅበር ሥርዓት ማኅበር ይኖሩ ዘንድ የሠራላቸውን ሥርዓት አሰቡ በሥርዓት ይመራቸው ዘንድ አባታቸው አረጋዊ ለሰጣቸው ለመንፈሳዊ አባታቸው ለአባ ማትያስም ራሳቸውን ዝቅ አደረጉ ሃሳባቸውንም የአባታቸው የአረጋዊዊን መታሰቢያ ወደማድረግ ተመለሱ። ❤ ክብር አባታችን አቡነ አሰጋዊ የተሠወረበት ቀን በኢትዮጵያ ወር አቆጣጠር በጥቅምት ዐሥራ ዐራት ቀን በዕብራውያን ደግሞ በታስሪን ዐሥራ አንድ ቀን በኢትዮጵያዊው ንጉሥ በዐፄ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት ነው። ከአባታች ከአቡነ አረጋዊ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ ገድለ አቡነ አረጋዊ። + + + ❤ የቊስጥንጥንያ ንጉሥ የቴዎዶስዮስ ልጅ መሽራው ቅዱስ ገብረ ክርስቶስ፦ ይህም ቴዎዶስዮስ እግዚአብሔርን የሚፈራ ነው ሚስቱም በጎ የምትሠራ እግዚአብሔርንም የምትፈራ ናት ስሟም መርኬዛ ነው። እነርሱም ልጅ ስለሌላቸው ያዝኑ ነበር ወደ ኢየሩሳሌምም ሒደው ስእለትን ተሳሉ ቸር መሐሪ ወደሆነ እግዚአብሔርም ለመኑ እርሱም ልመናቸውን ተቀበሎ ይህን ያማረ ልጅ ሰጣቸው ስሙንም "አብደልመሲህ" ብለው ሰየሙት ትርጓሜውም "ገብረ ክርስቶስ" ማለት ነው ። የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ የሥጋዊንም ትምህርት አስተማሩት ። ❤ አድጎ በጕለመሰም ጊዜ የሮሜውን ንጉሥ ልጅ አጭተው እንደ ሥርዓቱ አጋቡት ከሌሊቱ እኩሌታም በሆነ ጊዜ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ ተነሥቶ ወደሙሽራዪቱ ገባ እጅዋንም ይዞ ከእርስዋ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ። ከዚያም የሃይማኖት ጸሎት በአንድ አምላክ እናምናለን የሚለውን እስከ መጨረሻ ጸለየ የተሞሸረበትንም ልብስ ከላዩ አውልቆ የግምጃ ልብስን ለበሰ ወደ ሙሽሪቷም ሒዶ ራስዋን ሳማት እንዲህም እያለ ተሰናበታት "እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይኑር ከሰይጣን ሥራ ሁሉ ያድንሽ"። እርሷም አልቅሳ "ጌታዬ ወዴት ትሔዳለህ ለማንስ ትተወኛለህ" አለችው

👉🏽 ነገ አመታዊ መታሰቢያ የንግስ ክብረ በዓል ነዉ ። ❗️❗️ጥቅምት 14 በዓለ እረፍቱ ለ ቅዱስ ፊልጶስ ዘ ኮልፌ 👉🏽 ወር በገባ በ 14 የቅድስት ሀገራችን የኢትዮጲያ የክርስትና አባት የሆነዉ የ ቅዱስ ፊልጶስ የእረፍት በዓል መታሰቢያ ነዉ ። 👉🏽 አባታችን ቁጥሩ ከ 12 ቅዱሳን ሐዋርያት ተርታ ያለ ሳይሆን ከ 72 አርድዕት በኋላም ከ 7 ዲያቆናት ከ ሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖስ በመቀጠል 2ኛዉ ዲያቆን የቅዱሳን ሐዋርያት ረዳት በመሆን እግዚአብሔር አምላክን አገልግሏል ፣ በኋላም የ ኢትዮጲያ ንግስት ህንደኬ ባለሟል ጃንደረባዉ ቅዱስ ፓኮስን የክርስትና ጥምቀትን አጥምቆ ለሀገራችን ከ ብሉይ ሥርዓት ወደ ክርስትና እምነት እና ሥርዓትን በማስጀመር ለእኛ ለኢትዮጲያዊያን ለሁላችን የክርስትና አባት ኾኖናል ። ❗️ የሐዋርያት ስራ ምዕራፍ 8 👉🏽 በ አዲስ አበባም ብቸኛዉ በቅዱስ ፊልጶስ ስም የታነፀ የእግዚአብሔር ቤተ- መቅደስ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ በ ኮልፌ አጠና ተራ ይገኛል ፤ በመሆኑም ኢትዮጲያዊያን ሁላችን መተን የክርስትና አባታችን እንጠይቅ ደጁን እንሳለም በረከትንም እንቀበል ። ❗️ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ፣ ❗️ ወለወላዲቱ ድንግል ፣ ❗️ ወለመስቀሉ ክቡር ።

photo content

photo content
+4

🌹ጥቅምት ፲፫ ምስባክ🌹 @EOTCW የዕለቱምስባክ፦ ጻድቅሰ ከመ በቀልት ይፈሪ ወይበዝኅ ከመ ዘግባ ዘሊባኖስ ትኩላን እሙንቱ ውስተ ቤተ እግዚአብሔር መዝ ፺፩፥፲፪ @EOTCW ትርጕም፦ ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል። እንደ ሊባኖስ ዝግባም ይበዛል። በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የተተከሉ ናቸው። #Share https://t.me/Eotcw #ሼር

መዝሙር ወመኑ መሐሪ (በ፫/ሙ) ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ (ወ) ምስለ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ (ወ) ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ (ወ) በጽጌያት ምድረ አሠርጐከ ወስነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ (ወ) ወከመ ወሬዛ ኀየል መላትሒሁ ጉርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ ዘወይጠል (ወ) ሰማየ ወምድረ ዘአንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ (ወ) በከዋክብት ሰማየ ዘከለልከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ (ወ) ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት ወአልዓላ እምኵሉ ዕለት ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወኵሉ ይሴፎ ኪያከ። ትርጕም፦ እንደ አንተ ያለ ይቅር ባይ ማነው? ከኖኅ ጋር ቃል ኪዳንን ያቆምህ/ያጸናህ፤ለእስራኤል ልጆች መናን ያወረድህ፤ ምድርን በአበቦች ያስጌጥህ እንደ አንተ ያለ ይቅር ባይ ማነው? የምድረ በዳ ውበት ከቅዱሳንህ ጋር ነው ጉንጮቹ እንደብርቱ ዋሊያ ናቸው ጉረሮው ጣፋጭ ነው ፌቆ ምሳሌው ነው ሰማይና ምድርን የፈጠርህ ፀሐይና ጨረቃን ያስማማህ አንተ ነህ በከዋክብት ሰማይን የጋረድህ በአበቦችም ምድርን ያስጌጥህ አንተ ነህ ሰንበትን ቀደሳት አከበራት ከዕለታት ሁሉ ከፍ ከፍ አደረጋት እንዳንተ ያለ ይቅር ባይ ማነው ሁሉ አንተን ተስፋ ያደርጋል። የዕለቱ ምንባባት፦ ፩ቆሮ ፲፥፩ - ፲፬፤ ራእይ ፲፬፥፩ - ፮፤ ግብ ፬፥፲፱ - ፴፩፤ የዕለቱ ወንጌል፦ ማቴ ፲፪፥፩ − ፳፪፤ ቅዳሴ፦ ዘእግዝእትነ ማርያም የዕለቱምስባክ፦ ጻድቅሰ ከመ በቀልት ይፈሪ ወይበዝኅ ከመ ዘግባ ዘሊባኖስ ትኩላን እሙንቱ ውስተ ቤተ እግዚአብሔር መዝ ፺፩፥፲፪ ትርጕም፦ ጻድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል። እንደ ሊባኖስ ዝግባም ይበዛል። በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የተተከሉ ናቸው። ምሥጢር፦ ጻድቅ ሕዝቅያስ እንደ ዘንባባ ያፈራል ማለት ትሞታለህ ከተባለ በኋላ ዕድሜ ተጨምሮለታልና። አንድም ኢዮብን ይመለከታል ከተፈተነ በኋላ ቀድሞ የነበረው ሁሉ በዕጥፍ ተመልሶለታልና። አንድም ሁሉንም ጻድቃን ይመለከታል ፍሬ በረከታቸው ብዙ ነውና ከነሱ አልፎ ለእኛ የሚጠቅም ሆኗልና። ለአብነት ሐዋርያና ወንጌላዊ የሆነ ቅዱስ ማቴዎስን ብናነሣ የጻፈልን ባለ ፳፰ ምዕራፍ ወንጌል ምን ያህል እንደጠቀመን ነፍሳችን ምን ያህል በቃሉ እየረካችና ከቁስለ ኃጢአት በየቀኑ እንዴት እንደምትፈወስ ስንመለከት እንደዘንባባ የበዛ የአገልግሎቱ ፍሬ ግልጥ ብሎ ይታየናል። እንደ ሊባኖስ ዝግባ ይበዛል ሲል ደግሞ ቅዱሳኑ የተሰጣቸውን ክብርና በእነሱ ተልእኮና ምልጃ ተጠቃሚው ምን ያህል ብዙ እንደሆነ ያሳያል። በእግዚአብሔር የተተከሉ ናቸው ሲልም በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ያለውን የቅዱሳን ድርሻ ያሳያል ማለት የማይጠፋ ስምና የዘለዓለም መታሰቢያ ያላቸው መሆኑን ያሳያል። ኢሳ ፶፮፥፭ #Share 👇👇 https://t.me/Eotcw

photo content

photo content

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፲፫ (13) ቀን። ❤ እንኳን ለመነኰስ ለአባ ዘካርያስ ለዕረፍት በዓል፣ ለታላቁ አባት ለቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ለመታሰቢያው በዓልና ለማኅሌተ ጽጌ ሦስተኛ ሳምንት በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ ከቀሲስ አብጥልማኮስና ከወንድሞቹ በሰማዕትነት ከዐረፋ፣ ከአውስኖ፣ ከአውሲኪስ፣ ከታኦድራስ፣ ከአብላስከ ወንድሞቹ፣ ከናውላውስና ከአቤላ ከመታሰቢያየው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ የዚህ ሳምንት መዝሙር፦ ሃሌ ሉያ በ ፫ "ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ምስለ፤ ኖኅ ኪዳነ ዘአቀምከ ለደቂቀ እስራኤል መና ዘአውረድከ፤ አዝ፣ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ ወስነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ፤ አዝ፣ ወከመ ወሬዛ ኀየል መላትሒሁ ጒርዔሁ መዐርዒር አምሳሉ ዘወይጠል፤ አዝ፣ ሰማየ ወምድረ ዘአንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ፤ አዝ፣ በከዋክብት ሰማየ ዘከለልከ ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ አዝ፣ ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት ወአልዓላ እምኲሉ ዕለት ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ወኲሉ ይሴፎ ኪያከ"። ትርጉም፦ እንደ አንተ ያለ ይቅር ባይ ማነው? ከኖኅ ጋር ቃል ኪዳንን ያቆምህ (ያጸናህ)፤ ለእስራኤል ልጆች መናን ያወረድህ፤ በአበቦች ውበት ምድርን ያስጌጥክ፣ የገዳምን ውበት ከቅዱሳንህ ጋር ነው አስጌጥክ እንደ ኃይለኛ ጎልማሳ እንደ ዋሊያ ጉረሮው ጣፋጭ ነው ሰማይና ምድርን የፈጠርህ፣ ፀሐይና ጨረቃን ያስማማህ፣ በከዋክብት ሰማይን የጋረድክ፣ በአበቦችን አሳየ፣ ቁጥር የሌለው ብዙ አበቦችን አሳይ፣ ለሕዝብህ በረከትን ስጥ፣ ሰንበትን ቀደሳት አከበራት ከዕለታት ሁሉ ከፍ ከፍ አደረጋት እንዳንተ ያለ ይቅር ባይ ማነው ሁሉ አንተን ተስፋ ያደርጋል። ሊቁ ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ። + + + ❤ መነኰስ አባ ዘካርያስ፦ የዚህም መስተጋድል የአባቱ ስም አቃርዮስ ነው። ይህም አቃርዮስ የምንኲስና ልብስ ሊለብስ ሽቶ ለሚስቱ ነገራት እርሷም በነገራት ነገር ተስማማች። ወንድና ሴት ሁለት ልጆች አሉአቸው እነርሱንም ከእናታቸው ዘንድ ትቶ እርሱ ወደ አስቄጥስ ገዳም ሔዶ ከአንድ አረጋዊ አባት መነኰስ ዘንድ በዚያ መነኰሰ። ❤ ከጥቂት ወራትም በኋላ በሀገር ውስጥ ረኃብ ሆነ ሚስቱም ልጆቿን ይዛ ወደ አስቄጥስ ገዳም ወደባሏ አቃርዮስ መጣች በረኃብም ስለ ሆነው ችግር ነገረችው አቃርዮስም "እነሆ እግዚአብሔር በመካከላችን ፍርድን አድርጎ ልጆቻችንን አካፈለን እኔም ወንዱን ልጄን እወስዳለሁ አንቺም ሴት ልጅሽን ውሰጂ" አላት ይህንንም ብሎ ልጁን ወሰደ ይኸውም ዘካርያስ ነው እርሷም ሴቷን ልጅዋን ይዛ ተመለሰች። ❤ ከዚህም በኋላ ልጁን ዘካርያስን ወደ ቅዱሳን አረጋውያን አቀረበው እነርሱም በላዩ ጸለዩ ባረኩትም እርሱ ፍጹም መነኲሴ እንደሚሆንም ትንቢት ተናገሩለት። ዘካርያስም ከበጎ ሥራ ጋር በገዳም ውስጥ አደገ መልኩም እጅግ ያማረ ነው ስለርሱም ጉርምርምታ ሆነ መነኰሳቱም እርስበርሳቸው "ይህ ወጣት ይህን ያህል እጅግ መልከ መልካም ሲሆን በገዳም ውስጥ በመነኰሳት መካከል እንዴት ይኖራል" ተባባሉ። ❤ ዘካርያስም ስለርሱ መነኰሳት እንዳንጐራጐሩ በሰማ ጊዜ ናጥራን ወደሚባል ተራራ ስር ወደአለች ዐዘቅት ሔደ ልብሱንም አውልቆ በረግረግ ውስጥ ተኛ ሥጋውም ተነፋፍቶ ጠቆረ ተመላልጦም ቈሰለ ብዙ ዘመንም በደዌ እንደኖረ ሆነ፤ ከዚህም በኋላ ልብሱን ለብሶ ወደ ገዳም መጣ ያወቀውም የለም። ከብዙ ቀኖችም በኋላ አባቱ አስተውሎ ልጁ ዘካርያስ እንደ ሆነ አወቀውና "መልክህን የለወጠው ምንድን ነው?" ብሎ ጠየቀው አርሱም ያደረገውን ሁሉ ነገረው። ❤ በእሑድ ቀንም ሥጋውንና ደሙን ሊቀበል ወደ ቤተ ክርስቲያን ገባ እግዚአብሔርም ያን ጊዜ ሥራውን ለአባ ኤስድሮስ ገለጸለት እርሱም ዘካርያስ የሠራውን ለወንድሞች መነኰሳት አስረዳቸው እነርሱም "አስቀድሞ እንደ ሰው ሁነህ መጣህ ዛሬ ግን እንደ እግዚአብሔር መልአክ ሁነህ መጣህ" አሉት። ❤ ይህ አባት ዘካርያስም በብዙ ገድል ሲጋደል ኖረ ትሕትናን ቅንነትን ያማረ የትሩፋትን ሥራ ሁሉ ገንዘብ አደረገ አባቱም ስለርሱ "እኔ በገድል ብዙ ደክሜአለሁ ነገር ግን ከልጄ ሥርዓተ ገድል አልደረስኩም" ብሎ ተናገረ። ❤ በዚህ ተጋድሎውም አርባ አምስት ዓመት ኑሮ እግዚአብሔርን ከአገለገለው በኋላ በፍቅር አንድነት ጥቅምት 13 ቀን ዐረፈ መላ ዘመኑም ሃምሳ ሁለት ነው። ከዚህም ሰባቱን ዓመት በወላጆቹ ቤት አርባ አምስቱን በገዳም ኖረ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዘካርያስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት 13 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለዘካርያስ ቡሩክ። በውስተ ዓምዓም ሰኪቦ አባላቲሁ ዘአስሐከ። እለ ነጸሩ ትጋሖ ወተጋድሎቶ ውሱከ። ይቤልዎ ኮነ እንዘ ብእሲ መልአከ። እምሕገ ሥጋ ዓዲዎ ከሀከ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 13። + + + ❤ የዕለቱ ምስባክ፦ "ጻድቅሰ ከመ በቀልት ይፈሪ። ወይበዝኅ ከመ ዘግባ ዘሊባኖስ። ትኩላን እሙንቱ ውስተ ቤተ እግዚአብሔር"። መዝ 91፥12-13። የሚነበቡት መልዕክታት 1ኛ ቆሮ 10፥1-14፣ ራዕ ዮሐ 14፥1-6 እና የሐዋ ሥራ 4፥19-31። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 12፥1-32። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የአባ ዘካርያስ የዕረፍት በዓል፣ የቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ የመታሰቢያው፣ የማኅሌተ ጽጌ ሦስተኛ ሳምንትና የጾም ጊዜ ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

#ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ሚካኤል (3) ነብሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ ፈጥነህ ተራዳኝ ዋስ ጠበቃዬ #አዝ አንተ ስለሆንክ ሚካኤል የአምላክ ባለሟል ሚካኤል ልመናቅ ፈጥኖ ሚካኤል ካምላክ ይቀርባል ሚካኤል የዋህ መልአክ ነህ አዛኝ ለሰው ምልጃህ ፈጣን ነው ለምናምነው (2) #አዝ ደዌ የጸናበት ሚካኤል ባንተ ይድናል ሚካኤል በአደባባይህ ሚካኤል ምስክር ሆኗል ሚካኤል ከቤትህ መጥቶ የተማፀነ በቃል ኪዳንህ ህይወቱ ዳነ (2) #አዝ ካምላክ ተሰጥቶህ ሚካኤል ክብርህ ያበራል ሚካኤል ለጎስቋላው ሰው ሚካኤል መጠጊያ ሆኗል ሚካኤል ትንሽ ትልቁ ደሀው ሀብታሙ ለምኖ አግኝቷል ካምላክ በስሙ (2) #አዝ በብሉይ ኪዳን ሚካኤል ከአምላክ ተልከህ ሚካኤል ሕዝበ እስራኤልን ሚካኤል ነጻ ያወጣህ ሚካኤል በአዲስ ኪዳንም ድንቅ ስራ አለህ በተአምራትህ ትፈውሳለህ (2) ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇        ★ @mezmurtenat ★

#ቅዱስ ሚካኤል ፈጥኖ ደረሰልኝ ቅዱስ ሚካኤል ፈጥኖ ደረሰልኝ ኦ ከሳሼን ረግጦ አዋረደልኝ ክንፉን ቀጥ አድርጐ ዙሪያየን ሰፈረ የጠላቴን መንገድ ወጥመድ ሰባበረ (2 ) #አዝ........ ሌጌዎን መከረኝ በሐሰት እንድቆም ሊያሳየኝ ፈልጐ የሙሴን መቃብር አይጠቅመኝምና ሰወረዉ ሚካኤል ፈርቶ ተመልሷል ተዋርዶ ሳጥናኤል (2 ) #አዝ....... ጽድቅን አስተማረኝ ሀጢአትን ሳበዛ ነፍሴ እንዳትኮነን በበረት ተይዛ ወደ ህይወት መንገድ ይዞ እየመራኝ የመዳኔን እራስ ጌታን አሳየኝ ( 2 ) #አዝ....... ከታናሽነቴ ተግቶ የጠበቀኝ ከአጋንንት እስራት ምልጃ የታደገኝ ዛሬም አለ ጐኔ በጐልማሳነቴ የልቤ ብርሀን ነው ሚካኤል አባቴ ( 2 ) #አዝ....... ፀጋዬ እንዳይጐድል ጠላት እንዳይረግመኝ ተራዳኢው መልአክ ከፊቴ ቆመልኝ በአህያ አንደበት ነቢዩን ገሰፀው እብደቱን አግቶ ከመንገድ መለሰው ( 2 ) ለመቀላቀል_ሰማያዊውን_ይጫኑ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇        ★ @mezmurtenat ★

ይህን ቢያንስ ለአስር ሰው በመላክ እና በመገኘት የበተከቱ ተካፋይ ይሁኑ የዛ ሰው ይበለን
ይህን ቢያንስ ለአስር ሰው በመላክ እና በመገኘት የበተከቱ ተካፋይ ይሁኑ የዛ ሰው ይበለን

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 9፥9-32 "ወሐሊፎ እየሱስ እምህየ" - "ኢየሱስም፡ከዚያ፡ዐልፎ፡በመቅረጫው፡ተቀምጦ፡የነበረ፡ማቴዎስ፡የሚባል፡አንድ፡ሰው፡ አየና፦ተከተለኝ፡አለው።ተነሥቶም፡ተከተለው። በቤቱም፡በማእዱ፡ተቀምጦ ሳለ፥እንሆ፥ብዙ፡ቀራጮችና፡ኀጢአተኛዎች፡መጥተው፡ከኢየሱስና፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ጋራ፡ዐብረው፡ተቀመጡ። ፈሪሳውያንም፡አይተው፡ደቀ፡መዛሙርቱን፦መምህራችኹ፡ከቀራጮችና ከኀጢአተኛዎች፡ጋራ፡ዐብሮ፡ ስለ፡ምን፡ይበላል፧አሏቸው። ኢየሱስም፡ሰምቶ፦ሕመምተኛዎች፡እንጂ፡ባለጤናዎች፡ባለመድኀኒት፡አያስፈልጋቸውም፤ ነገር፡ግን፥ሄዳችሁ፦ምሕረትን፡እወዳለሁ፡መሥዋዕትንም፡አይደለም፡ያለው፡ምን፡እንደ፡ሆነ፡ተማሩ፤ኃጢአተኛዎችን፡ወደ፡ንስሓ፡እንጂ፡ጻድቃንን፡ልጠራ፡አልመጣሁምና፡አላቸው። በዚያን፡ጊዜ፡የዮሐንስ፡ደቀ፡መዛሙርት፡ወደ፡እርሱ፡ቀርበው፦እኛና፡ፈሪሳውያን፥ብዙ፡ጊዜ፡ የምንጦመው፥ደቀ፡መዛሙርትህ፡ግን፡የማይጦሙት፡ስለ፡ምንድር፡ነው፧አሉት። ኢየሱስም፡እንዲህ፡አላቸው፦ሚዜዎች፡ሙሽራው፡ከእነርሱ፡ጋራ፡ሳለ፡ሊያዝኑ፡ይችላሉን፧ነገር፡ግን፡ሙሽራው፡ከእነርሱ፡የሚወሰድበት፡ወራት፡ይመጣል፥በዚያ፡ጊዜም፡ይጦማሉ። በአረጀ፡ልብስ፡ዐዲስ፡ዕራፊ፡የሚያኖር፡የለም፤መጣፊያው፡ልብሱን፡ይቦጭቀዋልና፥መቀደዱም፡የባሰ፡ይሆናል። በአረጀ፡አቍማዳ፡ዐዲስ፡የወይን፡ጠጅ፡የሚያኖር፡የለም፤ቢደረግ፡ግን፥አቊማዳው፡ይፈነዳል፥የወይን፡ጠጁም፡ይፈሳል፡አቍማዳውም፡ይጠፋል፤ነገር፡ግን፥ዐዲሱን፡የወይን፡ጠጅ፡በዐዲስ፡አቍማዳ፡ ያኖረዋል፥ሁለቱም፡ይጠባበቃሉ። ይህንም፡ሲነግራቸው፥አንድ፡መኰንን፡መጥቶ፦ልጄ፡አሁን፡ሞተች፤ነገር፡ግን፥መጥተህ፡እጅህን፡ጫንባት፥በሕይወትም፡ትኖራለች፡እያለ፡ሰገደለት። ኢየሱስም፡ተነሥቶ፡ከደቀ፡መዛሙርቱ፡ጋራ፡ተከተለው። እንሆም፥ከዐሥራ፡ሁለት፡ዓመት፡ጀምሮ፡ደም፡የሚፈሳት፡ሴት፡በኋላው፡ቀርባ፡የልብሱን፡ጫፍ፡ዳሰሰች፤ በልቧ፦ልብሱን፡ብቻ፡የዳሰስሁ፡እንደ፡ሆነ፥እድናለሁ፡ትል፡ነበርና። ኢየሱስም፡ዘወር፡ብሎ፡አያትና፦ልጄ፡ሆይ፥አይዞሽ፤እምነትሽ፡አድኖሻል፡አላት።ሴቲቱም፡ከዚያች፡ሰዓት፡ጀምራ፡ዳነች። ኢየሱስም፡ወደመኰንኑ፡ቤት፡በደረሰ፡ጊዜ፥እንቢልተኛዎችንና፡የሚንጫጫውን፡ሕዝብ፡አይቶ፦ ብላቴናዪቱ፡ተኝታለች፡እንጂ፡አልሞተችምና፡ፈቀቅ፡በሉ፡አላቸው።በጣምም፡ሣቁበት። ሕዝቡን፡ግን፡ከአስወጡ፡በኋላ፡ገብቶ፡እጇን፡ያዛት፥ብላቴናዪቱም፡ተነሣች። ያም፡ዝና፡ወደዚያ፡አገር፡ሁሉ፡ወጣ። ኢየሱስም፡ከዚያ፡ሲያልፍ፡ሁለት፡ዕውሮች፦የዳዊት፡ልጅ፡ሆይ፥ማረን፡ብለው፡እየጮሁ፡ተከተሉት። ወደ፡ቤትም፡በገባ፡ጊዜ፡ዕውሮቹ፡ወደ፡እርሱ፡ቀረቡ፥ኢየሱስም፦ይህን፡ማድረግ፡እንድችል፡ታምናላችሁን፧አላቸው፦አዎን፥ጌታ፡ሆይ፡አሉት። በዚያን፡ጊዜ፦እንደ፡እምነታችሁ፡ይሁንላችሁ፡ብሎ፡ዐይኖቻቸውን፡ዳሰሰ። ዐይኖቻቸውም፡ተከፈቱ። ኢየሱስም፦ማንም፡እንዳያውቅ፡ተጠንቀቁ፡ብሎ፡በብርቱ፡አዘዛቸው።እነርሱ፡ግን፡ወጥተው፡በዚያ፡ አገር፡ሁሉ፡ስለ፡እርሱ፡አወሩ። እነርሱም፡ሲወጡ፥እንሆ፥ጋኔን፡ያደረበትን፡ዲዳ፡ሰው፡ወደ፡እርሱ፡አመጡ።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.54 KB

12/2/2015 ዓ.ም (፲፪/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 እስመ መምህረ ሕግ ይሁብ በረከተ። ወየሐውር እምኀይል ውስተ ኃይል። ወያስተርኢ አምላከ አማልክት በጽዮን፡፡ መዝ. 83፥5 🕯 ትርጉም የሕግ መምህር በረከትን ይሰጣልና። ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳል። የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል፡፡ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በእለቱ በነግህ የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 19:1-16፡ "ወኮነ እምዘፈጸመ ኢየሱስ" - "ኢየሱስም፡ይህን፡ነገር፡ከፈጸመ፡በኋላ፥ከገሊላ፡ኼዶ፡ወደይሁዳ፡አውራጃ፡ወደዮርዳኖስ፡ማዶ፡መጣ። ብዙ፡ሕዝብም፡ተከተሉት፥በዚያም፡ፈወሳቸው። ፈሪሳውያንም፡ወደ፡ርሱ፡ቀረቡና፡ሲፈትኑት፦ሰው፡በሆነው፡ምክንያት፡ሁሉ፡ሚስቱን፡ሊፈታ፡ተፈቅዶለታልን? አሉት። እርሱ፡ግን፡መልሶ፡እንዲህ፡አለ፦ፈጣሪ፡በመጀመሪያ፡ወንድና፡ሴት፡አደረጋቸው፥ አለም፦ስለዚህ፡ሰው፡አባቱንና፡እናቱን፡ይተዋል፥ከሚስቱም፡ጋራ፡ይተባበራል፥ሁለቱም፡አንድ፡ሥጋ፡ይሆናሉ፡የሚለውን፡ቃል፡አላነበባችኹምን? ስለዚህ፥አንድ፡ሥጋ፡ናቸው፡እንጂ፡ወደ፡ፊት፡ሁለት፡አይደሉም።እግዚአብሔር፡ያጣመረውን፡እንግዲህ፡ሰው፡አይለየው። እነርሱም፦እንኪያስ፡ሙሴ፡የፍቿን፡ጽሕፈት፡ሰጥተው፡እንዲፈቷት፡ስለ፡ምን፡አዘዘ፧አሉት። እርሱም፦ሙሴስ፡ስለልባችሁ፡ጥንካሬ፡ሚስቶቻችሁን፡ትፈቱ፡ዘንድ፡ፈቀደላችሁ፤ከጥንት፡ግን፡እንዲህ፡አልነበረም።እኔ፡ግን፡እላችኋለሀ፥ያለዝሙት፡ምክንያት፡ሚስቱን፡ፈቶ፟፡ሌላዪቱን፡የሚያገባ፡ሁሉ፡ያመነዝራል፥የተፈታችውንም፡የሚያገባ፡ያመነዝራል፡አላቸው። ደቀ፡መዛሙርቱም፦የባልና፡የሚስት፡ሥርዐት፡እንዲህ፡ከሆውነ፡መጋባት፡አይጠቅምም፡አሉት። እርሱ፡ግን፦ይህ፡ነገር፡ለተሰጣቸው፡ነው፡እንጂ፡ለሁሉ፡አይደለም፤ በእናት፡ማሕፀን፡ጃን፡ደረባዎች፡ሆነው፡የተወለዱ፡አሉ፥ሰውም፡የሰለባቸው፡ጃን፡ደረባዎች፡አሉ፥ስለ፡መንግሥተ፡ሰማያትም፡ራሳቸውን፡የሰለቡ፡ጃን፡ደረባዎች፡አሉ፦ሊቀበለው፡የሚችል፡ይቀበለው፡አላቸው። በዚያን፡ጊዜ፡እጁን፡እንዲጭንባቸውና፡እንዲጸልይ፡ሕፃናትን፡ወደ፡ርሱ፡አመጡ፤ደቀ፡መዛሙርቱም፡ገሠጿቸው። ነገር፡ግን፥ኢየሱስ፦ሕፃናትን፡ተዉአቸው፥ወደ፡እኔም፡ይመጡ፡ዘንድ፡አትከልክሏቸው፤መንግሥተ፡ሰማያት፡እንደነዚህ፡ላሉ፡ናትና፥አለ፤እጁንም፡ጫነባቸውና፡ከዚያ፡ሄደ። እንሆም፥አንድ፡ሰው፡ቀርቦ፦መምህር፡ሆይ፥የዘለዓለምን፡ሕይወት፡እንዳገኝ፡ምን፡መልካም፡ነገር፡ላድርግ? አለው።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨