uk
Feedback
ሰዋስው ☘☘☘☘

ሰዋስው ☘☘☘☘

Відкрити в Telegram

በሰዋስወ ብርሀን ቅዱስ ዻውሎስ ገዳም እና ለተለያዩ ቤተክርስቲያን ለክብረ በአላት ማውጫ ። በተጨማሪም-ዋዜማ ሥርዓተ ማኅሌት - መዝሙራት ስንክሳር - የየእለቱን ምስባክ ቅኔያት ጥያቄዎች እንዲሁም የወቅታዊ ነገር መወያያ በተጨማሪም @eotcww ብለው ይቀላቀሉን ለወዳጅ ዘመድዎ share#Share#Share# ያድርጉ።

Показати більше
1 161
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
Архів дописів
✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በዕለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 18:15-21 "ወእመኒ አበሰ ለከ እኁከ"- "ወንድምህም፡ቢበድልህ፥ሄደህ፡አንተና፡ርሱ፡ብቻችሁን፡ሆናችሁ፡ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን፡ገንዘብ፡አደረግኸው፤ ባይሰማህ፡ግን፥በሁለት፡ወይም፡በሦስት፡ምስክር፡አፍ፡ነገር፡ሁሉ፡እንዲጸና፥ዳግመኛ፡አንድ፡ወይም፡ሁለት፡ከአንተ፡ጋራ፡ውሰድ፤እነርሱንም፡ባይሰማ፥ለቤተ፡ክርስቲያን፡ንገራት፤ደግሞም፡ቤተ፡ክርስቲያንን፡ባይሰማት፥እንደ፡አረመኔና፡ እንደ፡ቀራጭ፡ይሁንልህ። እውነት፡እላችኋለሁ፥በምድር፡የምታስሩት፡ሁሉ፡በሰማይ፡የታሰረ፡ይሆናል፥ በምድርም፡የምትፈቱት፡ሁሉ፡በሰማይ፡የተፈታ፡ይሆናል። ደግሞ፡እላችዃለኹ፥ከእናንተ፡ኹለቱ፡በምድር፡በማናቸውም፡በሚለምኑት፡ነገር፡ዅሉ፡ቢስማሙ፡በሰማያት፡ካለው፡ከአባቴ፡ዘንድ፡ይደረግላቸዋል። ሁለት፡ወይም፡ሦስት፡በስሜ፡በሚሰበሰቡበት፡በዚያ፡በመካከላቸው፡እሆናለሁና። በዚያን፡ጊዜ፡ጴጥሮስ፡ወደ፡እርሱ፡ቀርቦ፦ጌታ፡ሆይ፥ወንድሜ፡ቢበድለኝ፡ስንት፡ጊዜ፡ ልተውለት፧እስከ፡ሰባት፡ጊዜን፧አለው።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.57 KB

19/2/2015 ዓ.ም (፲፱/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ወሶበሂ ኢትዋቀሥ ይፃዕ ተመዊዖ። ወጸሎቱሂ ትኩኖ ጌጋየ። ወይኲና መዋዕሊሁ ኀዳጠ። መዝ. 108፥7 🕯 ትርጉም በተሟገተም ጊዜ ተረቶ ይውጣ። ጸሎቱም ኃጢአት ትሁንበት። ዘመኖቹም ጥቂትይሁኑ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ በዕለቱ በቅዳሴ ሰዓት የሚነበብ ወንጌል ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨ ማቴ. 18:15-21 "ወእመኒ አበሰ ለከ እኁከ"- "ወንድምህም፡ቢበድልህ፥ሄደህ፡አንተና፡ርሱ፡ብቻችሁን፡ሆናችሁ፡ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን፡ገንዘብ፡አደረግኸው፤ ባይሰማህ፡ግን፥በሁለት፡ወይም፡በሦስት፡ምስክር፡አፍ፡ነገር፡ሁሉ፡እንዲጸና፥ዳግመኛ፡አንድ፡ወይም፡ሁለት፡ከአንተ፡ጋራ፡ውሰድ፤እነርሱንም፡ባይሰማ፥ለቤተ፡ክርስቲያን፡ንገራት፤ደግሞም፡ቤተ፡ክርስቲያንን፡ባይሰማት፥እንደ፡አረመኔና፡ እንደ፡ቀራጭ፡ይሁንልህ። እውነት፡እላችኋለሁ፥በምድር፡የምታስሩት፡ሁሉ፡በሰማይ፡የታሰረ፡ይሆናል፥ በምድርም፡የምትፈቱት፡ሁሉ፡በሰማይ፡የተፈታ፡ይሆናል። ደግሞ፡እላችዃለኹ፥ከእናንተ፡ኹለቱ፡በምድር፡በማናቸውም፡በሚለምኑት፡ነገር፡ዅሉ፡ቢስማሙ፡በሰማያት፡ካለው፡ከአባቴ፡ዘንድ፡ይደረግላቸዋል። ሁለት፡ወይም፡ሦስት፡በስሜ፡በሚሰበሰቡበት፡በዚያ፡በመካከላቸው፡እሆናለሁና። በዚያን፡ጊዜ፡ጴጥሮስ፡ወደ፡እርሱ፡ቀርቦ፦ጌታ፡ሆይ፥ወንድሜ፡ቢበድለኝ፡ስንት፡ጊዜ፡ ልተውለት፧እስከ፡ሰባት፡ጊዜን፧አለው።" ✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨✨

1.57 KB

19/2/2015 ዓ.ም (፲፱/፪/፳፻፲፭ ዓ.ም) 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 በእለቱ በነግህ የሚባል ምስባክ 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯 ወእለሂ ይኤብሱ ኢያንሥኡ ቀርኖሙ። ወኢያንሥኡ ቀርኖሙ ውስተ አርያም፡፡ ወኢይንብቡ ዓመፃ ላዕለ እግዚአብሔር። መዝ. 74፥4 🕯 ትርጉም ኃጢአተኛዎችንም ቀንዳችሁን አታንሡ። ቀንዳችሁን እስከ ላይ አታንሡ። በእግዚአብሔርም ላይ ዐመፅን አትናገሩ። 🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯🕯

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ + + + ❤ "ሰላም ለክሙ ፍስሐ ወኃሤት ወተድላ። እለ ትረውጹ በሠረገላ። ነአኲቶ ለአብ ይምርሐ ገብረ ማርያም ወላሊበላ። እቀቡኒ ለበግክሙ እምአፈ አንበሳ ወተኩላ። እስመ ምስለ ሞት አልብዕየ መሓላ"። ትርጉም፦ በሠረገላ መንፈስ የምትፋጠኑ ደስታና ተድላ የተመላችሁ ቅዱሳን ነገሥታት ነአኲቶለአብ ይምርሐ ገብረ ማርያም ላሊበላ ሆይ ሰላም እላችኋለሁ እኔን የዋህ አገልጋያችሁን ከአንበሳና ከተኩላ አፍ ጠብቁኝ ከሞት ጋር ቃል ኪዳን የለኝምና። መልክአ ቅዱስ ላሊበላ። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ ከዚያም ተነሥቶ ወደ ሌላ አገር ሔደ። የአገር ሰዎችም ዛፎችን ሲያመልኩ አግኝቷቸው እርሱም ከክህደታቸው እንዲመለሱ አስተማራቸው ባልሰሙትም ጊዜ ምሳር ይዞ በሌሊት ወደ ዛፎቹ መካከል ገብቶ ክብር ይግባውና ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ምሳሩንም አንሥቶ "በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እቆርጣችኋለሁ" አለ። ወዲያውኑ በአንዲት ምት ዐሥር ሽህ ዛፎች ወደቁ የሀገር ሰዎችም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አመኑ ሁሉም ከሴቶችና ከልጆች ጋር ተጠመቁ። ❤ ከዚያም ዳግመኛ ወደ ሌላ አገር ሔደ ሰዎችንም እሳትን ሲያመልኩ አገኛቸው እርሱም ይህን ድንቊርናቸውን ይተዉ ዘንድ አስተማራቸው ገሠጻቸውም እነርሱም በእርሱ ላይ ተቆጥተው ከእሳት ጨመሩት። እርሱም በደኅና ወጣ ሦስት ጊዜም ጨምረውት በደኅና ወጣ ውኃቸውንም ደም አደረገባቸው የሚጠጡትም አጥተው በተጨነቁ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ሁሉም አመኑ። አራት መቶ ሽህ ሰዎችም በእጁ ተጠመቁ ቤተክርስቲያንም ሠራላቸው አስተምሮም በቀናች ሃይማኖት አጸናቸው ቁጥር የሌላቸው ድንቆች ተአምራትንም አደረገ እግዚአብሔርንም አገልግሎ ጥቅምት 19 ቀን በሰላም በፍቅር ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ዮሐንስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። ምንጭ፦ የጥቅምት 19 ስንክሳር። + + + ❤ "ሰላም ለዮሐንስ በሥልጣነ ቃሉ ዘአዘዛ። ይኩን ደመ ለፈለገ ጸይለም ውኂዛ። ወሰላም ለረድኡ ጽጉየ ሠናይ መዓዛ። እንደ ተውህበ ለሞት እንዘ ውእቱ ወሬዛ። ለነፍሰ አእላፍ ከመ ይኩን ቤዛ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 19። + + + ❤ "ሰላም ለይምርሐ ዓመተ ምሕረት ዓሙ። በቀብዓ፡ክህነት ወንግሥ ዘአባላቲሁ ተኀትሙ። እስከ ብዙኃን ሕዝብ እመንክራቲሁ ተደሙ። መንገለ ተክዕወ ወነጥበ ደሙ። በቈለ ወይን ዘመንክር ጣዕሙ"። ሊቁ አርከ ሥሉስ (አርኬ) የጥቅምት 19። + + + ❤ የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ፦ "ወእለሂ ይኤብሱ ኢያንሥኡ ቀርኖሙ። ወኢያንሥኡ ቀርኖሙ ውስተ አርያም። ወኢይንብቡ ዐመፃ ላዕለ እግዚአብሔር"። መዝ 74፥4-5። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 10፥32-ፍ.ም። + + + ❤ የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ፦ "ወሶበሂ ይትዋቀስ ይፃእ ተመዊዖ። ወጸሎቱሂ ትኩኖ ጌጋየ። መይኩና መዋዕሊሁ ኅዳጠ"። መዝ 108፥7-8። የሚነበቡት መልዕክታት ቲቶ 3፥8-12፣ 1ኛ ዮሐ 2፥22-ፍ.ም የሐዋ ሥራ 20፥28-31። የሚነበበው ወንጌል ማቴ 18፥15-21። የሚቀደሰው ቅዳሴ የእመቤታችን የማርያም ቅዳሴ ነው። መልካም የቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ የዕረፍት በዓል፣ የአቡነ ሐራ ድንግል የልደት በዓልና የጾም ጊዜ። ለሁላችንም ይሁንልን። ❤ በየቀኑ ይህን ቴሌግራም ላይ ማግት ከፈለጉ ከታች ያለውን ሊኩን ይጫኑት። https://t.me/Eotcw

❤ አባታችን አቡነ ሐራ ድንግልም በክብር ካረፉ በኋላ በመካነ መቃብራቸው ላይ ለ40 ቀን ብርሃን ሲወርድ በገሃድ ታይቷል፡፡ አፅማቸውም ከዚያው ከገዳማቸው በክብር አርፎ ይገኛል፡፡ በጸሎታቸው ያፈለቁት ጸበልና የመቃብራቸው አፈር ሕመምተኞችን ከተለያዩ ደውያት ሰውንም እንስሳትንም እየፈወሰ ይገኛል፡፡ አፈራቸውና ጸበላቸው ለሥጋ ደዌ፣ ለእብጠት፣ለቁስል፣ ለለምፅና ለመሳሰሉት ፍቱን መድኃኒት ነው፡፡ በዓለ ዕረፍታቸው ጥር 11 ቀን 1624 ዓ.ም ነው፡፡ ከአቡነ ሐራ ድንግል እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከትን ያሳትፈን። በጸሎታቸው ይማረን!። ምንጭ፦ መዝገበ ቅዱሳን ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ። + + + ❤ ሰማዕቱ ቅዱስ በርቶሎሜዎስና ሚስቱ፦ እሊህ ቅዱሳንም የግብጽ ምዕራብ ከሆነ ፍዩም ከሚባል አገር ናቸው ክርስቲያኖችም እንደሆኑ በመኰንኑ ዘንድ ወነጀሏቸው መኰንኑም ልኮ አስቀረባቸውና ስለ ሃይማኖት ጠየቃቸው እነርሱም ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በፊቱ ታመኑ። ❤ መኰንኑም ጥልቅ ጒድጓድ እንዲቆፍሩላቸው በዚያም እንዲጨምሩአቸውና በሕይወታቸው እንዲደፍኑባቸው አዘዘ። መኰንኑም እንዳዘዘ አደረጉባቸው በዚህም ምስክርነታቸውን ፈጽመው የሰማዕትነት አክሊልን በመንግሥተ ሰማያት ተቀበሉ።ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም ቅዱስ በርቶሎሜዎስና ሚስቱ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ ስለ ጳውሎስ ሳምሳጢ በአንጾኪያ አገር የቤተ ክርስቲያን የአንድነት ስብሰባ ስለመደረጉ፦ ይህ ጳውሎስም ከአንጾኪያ አገሮች በአንዲቱ አገር ኤጲስቆጶስነት በተሾመ ጊዜ ክፉ ዘርን ሰይጣን በልቡ ውስጥ ዘራበት አካላዊ ቃልን አካል እንደሌለ የክርስቶስም ጥንት መገኛው ከማርያም እንደሆነ እርሱም አለምን ያድንበት ዘንድ እግዚአብሔር የፈጠረው እንደሆነ ከመለኮትም ጋር ያልተዋሐደ በላዩ ወርዶ በእግዚአብሔር ፈቃድ አደረበት እንጂ ብሎ የሚያምን ሆነ በወልድም ቢሆን በመንፈስ ቅዱስም ቢሆን የሚያምን አልሆነም። ❤ ስለዚህም ኤጲስቆጶሳት አንድነት ተሰበሰቡ የእስክንድርያ አባ ዲዮናስ የሮሜ አባ ዲዮናስዮስ እሊህ ሊቃነ ጳጳሳት ስለ እርጅናቸው ከዚያ ደርሰው ከእርሳቸው ጋር ሊሰበሰቡ አልቻሉም ነገር ግን መልእክትን ጻፉ። የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት አባ ዲዮናስም እንዲህ የሚል መልእክትን ጻፈ ። "የእግዚአብሔር ልጁም ቃሉም የሆነ ክርስቶስ በመለኮቱም ከእርሱ ጋር ትክክል የሆነ እርሱም ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ ስለእኛ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ዘር ስጋንና ነፍስን ነሥቶ ፍጹም ሰው የሆነ በመለኮቱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ሲሆን እንደእኛ ፊጹም ሰው ሁኗል ከተዋሕዶውም በኋላ ያለ መለያየትና ያለ መቀላቀል ሁለቱ ባሕርያት አንድ ሁነዋል" ከብሉይና ከሐዲስ መጻሕፍት ምስክሮችን ጠቅሶ እያስረዳ ጽፎ ይቺንም መልእክት ከሁለት ምሁራን ቀሳውስት ጋር ላካት። ❤ በዚያንም ጊዜ አሥራ ሦስቱ ኤጲስቆጶሳትና እሊህ ሁለቱ ቀሳውስት ጉባኤ አድርገው ይህን ጳውሊ ሳምሳጢን አቅርበው የአባ ዲዮናስን መልእክት በፊቱ አነበቡ። ዳግመኛም ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጁም ቃሉም የሆነ የጌትነቱ ነጸብራቅ ነው የሚለውን የሐዋርያ ጳውሎስን ቃል በመጥቀስ እርሱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በትክክልነት እንደሚኖር አስረዱት እርሱ ግን ቃላቸውን አልተቀበለም። ❤ ከዚህም በኋላ በእርሱ ትምህርት የሚያምኑትን ሁሉ አውግዘው ከምእመናን ለይተው አሳደዱት። ለምእመናንም ሥርዓትን ሠሩ። ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሳን አባቶቻችን በጸሎታቸው ከስሕተት ይጠብቀን በረከታቸውም ትድረሰ ለዘላለሙ አሜን። + + + ❤ የጸይለም አገር የከበረ አባት ቅዱስ ዮሐንስ፦ የዚህም ቅዱስ ወላጆቹ ከሀገሩ ታላላቆች ወገን ናቸው የአባቱም ስም አብርሃም የእናቱም ስም ሣራ ነው እነርሱም ልጆች ስለ ሌሏቸው ብዙ ዘመን ወደ እግዚአብሔር እየለመኑ ኖሩ። ❤ በአንዲትም ዕለት ሁለት መነኰሳት ወደ እነርሱ እንግድነት መጡ እነርሱም በክብር ተቀብለው አሳደሩአቸው። እሊህ መነኰሳትም አብርሃምን "ልጅ የለህምን?" አሉት እርሱም እንባውን እየአፈሰሰ "አባቶቼ ልጅ የለኝም አሁንማ እኔ አረጀሁ የሚስቴም የልጅነቷ ወራት አለፈ" ብሎ መለሰላቸው። እሊህ መነኰሳትም ስለ እርሳቸው ጸለዩላቸው ባርከዋቸውም ጎዳናቸውን ተጓዙ። ❤ ከጥቂትም ቀን በኋላ ሣራ ፀነሰች ደስ የሚያሰኝም ልጅን ወለደች ስሙንም ዮሐንስ ብለው ሰየሙት በእርሱም ደስ አላቸው የቤተ ክርስቲያንንም ትምህርት እየአስተማሩ አሳደጉት። ዐሥራ ሰባት ዓመትም በሆነው ጊዜ ወደ መምህሩ ቤት መነኰሳት መጡ ዮሐንስም ከእርሳቸው ጋር እንዲወስዱት ለመናቸው እነርሱም "አባትህን እንፈራለንና እኛ አንወስድህም" አሉት። መነኰሳቱም ወደቦታቸው እየሔዱ ሳሉ ወደ መረጠው ጎዳና ይመራው ዘንድ ዮሐንስ ተነሥቶ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ከመምህሩም ቤት ወጥቶ ሊደርስባቸው ወዶ መነኰሳቱን በኋላቸው ተከተላቸው ወደ ታላቅ ወንዝም ደረሰ ብቻውንም መሻገር ፈርቶ ቆመ ከዚያም ሳለ ዓረቦች ከግመሎቻቸው ጋር መጡ ያሻገሩትም ዘንድ ለመናቸው እነርሱም ከእርሳቸው ጋር አሻገሩት አንወስድህም ወደአሉት መነኰሳት ወደ ገዳማቸው በእግዚአብሔር ፈቃድ ደረሰ። ❤ ከእርሳቸውም አንዱ አባ ስምዖን የሚባለው ዮሐንስን ወስዶ ደቀ መዝሙሩ አድርጎ ከሁለቱ ደቀ መዛሙርቱ ጋር አኖረው። አባ ስምዖን የሚሞትበት ጊዜ እንደቀረበ በአወቀ ጊዜ ልጆቹን ጠርቶ "ከሞትኩ በኋላ በእናንተ ላይ የሚሆነውን እግዚአብሔር ያሳየኝን እነግራችሁ ዘንድ ልጆቼ ኑ" አላቸውና "ከእናንተ አንዱን ጅብ ነጥቆ ይወስደዋል። ሁለተኛው ወደ ዓለም ተመልሶ ይባክናል። የሦስተኛው ግን ዜናው በዓለሙ ሁሉ ይሰማል" አላቸው። ❤ ከዚህም በኋላ አረጋዊው ስምዖን ወደ ዮሐንስ ተመልክቶ "ልጄ ሆይ በክርስቶስ ፍቅር ጽና ለብዙዎች አባት ልትሆን እርሱ መርጦሃልና" አለው። አባ ስምዖንም ከዐረፈ በኋላ በሦስተኛው ቀን አንዱ ረድዕ ወደ ዓለም ተመልሶ ሚስት አገባ ሁለተኛው ወዴት እንደ ደረሰ አልታወቀም። አባ ዮሐንስም ብቻውን ቀረ ፈጽሞ አዘነ በልቡ እንዲህ አለ "የጓደኞቼን ወሬ እጠይቅ ዘንድ ከገዳም ወጥቼ ልውረድ" ይህንንም ብሎ ከገዳሙ ወጥቶ ሲወርድ የጸይለም ጦረኞች ተቀበሉት ደም ግባታቸው ከሚአምር ከሁለት ሴቶች ጋር አሥረው ወሰዱት በጒዞም ላይ እያሉ ለእንስሶቻቸውና ለራሳቸው የሚጠጡት ውኃ አጡ። አባ ዮሐንስም "ከዚህ በረሀ ውስጥ ፈጣሪዬ ውኃን ቢአወጣላችሁ ትለቁኛላችሁን" አላቸው "አዎን" አሉት። በዚያንም ጊዜ አባ ዮሐንስ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ" ብሎ በምድር ላይ አማተበ ውኃም ፈልቆላቸው ጠጥተው ረኩ። ❤ የከበረ ዮሐንስም "ቃል ኪዳን እንደ ገባችሁልኝ አሰናብቱኝ" አላቸው እነርሱም "እንዳንተ ያለ አናገኝምና ከቶ አንለቅህም" አሉት። ይህንንም ብለው ወደ አገራቸው ወደ ጸይለም አደረሱት። በዚያንም ወራት በጸይለም አገር ታላቅ መቅሠፍት ወረደ የአበ ዮሐንስም ጌታው ከቤተሰቦቹ ሁሉና ከልጆቹ ጋር ሞተ ሚስቱም ከአንዲት ልጅዋ ጋር ብቻዋን ቀረች። የጌታውም ሚስት ቅዱስ ዮሐንስን መሠርይ እንደ ሆነ አሰበች በማደሪያውም ውስጥ እያለ ሊአቃጥሉት እሳት ለቀቁበት እግዚአብሔርም ከእሳት ውስጥ በደኅና አወጣው የጸይለም ሰዎችም ይህን ድንቅ ተአምር አይተው ሴቶችም ወንዶችም በጌታችን አምነው በእጆቹ ተጠመቁ።

❤ ከጠንጠውድምም ሞት በኋላ ማንም እንዳልነገሠ ሲያረጋግጡ የማን ልጅ እንደሆነ እንዲነግራቸው በእግዚአብሔር ስም ለመኑትና "የጠንጠውድም የታናሽ ወንድምና የዣን ስዩም ታላቅ ወንድም የሆነው የግርማ ስዩም ልጅ ነኝ" አላቸው፡፡ እነርሱም "የተነገረው ትንቢት ደርሷልና ሳንዘገይ እናንግሠው" ብለው ሥርዓተ መንግሥቱን ፈጽመው በዙፋን ላይ አስቀመጡት፡፡ ለቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ቅዱስ መስቀልና ሰማያዊውን ኅብስት ከሰማይ ይወርድለት ነበር፡፡ ❤ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ በትረ መንግሥቱንም ከያዘ በኋላ ሁሉም ሰው እንደወንጌሉ ቃል በአንድ ለአንድ ጋብቻ ብቻ ተወስኖ እንዲኖር በግዛቱ ሁሉ አወጀ፡፡ እግዚአብሔርም የሚመሰገንበት ቤት መሥራት አሰበና የተፈቀደለትን ቦታ እንኪያገኝ ድረስ ዛዚያ በምትባል ልዩ በሆነች ስፍራ ድንኳን ተክሎ እንደሙሴ እግዚአብሔርን ማገልገል ጀመረ፡፡ ዘጸ 33፡7። ሰኔ 21 ቀንም ቀድሶ ሕዝቡን ከማቁረቡ በፊት ኅብስቱንና ጽዋውን የእግዚአብሔር መልአክ ሕዝቡን ከሚባርክበት ሰማያዊ መስቀል ጋር ከሰማይ አምጥቶለታል፡፡ በዚህ ዓይነት ሁኔታ ሕዝቡን ከሰማይ በወረደለት መስቀል እየባረከና ሰማያዊውን ኅብስትና ጽዋ እያቆረበ ለ22 ዓመት በድንኳኗ ውስጥ ኖሯል፡፡ ዛሬም ድረስ ያንን ሰማያዊው መስቀል በቤተመቅደሱ የሚያገለግሉት ካህናት አባቶች ቤተመቅደሱን ለመሳለም የሚመጣውን ሕዝበ ክርስቲያን በበዓል ቀን ይባርኩበታል፡፡ ❤ ለቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ጌታችን ተገልጦለት ቤተ መቅደሱን በባሕር ላይ እንዲሠራ ነግሮታል፡፡ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ እየወረደለት ለ22 ዓመት በድንኳኗ ውስጥ ካገለገለ በኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በክብር ተገልጦለት እንዲህ አለው፡- "ወዳጄ ይምርሃነ ክርስቶስ ይህን ሥፍራ (ዛዚያን) ልቀቅ፣ ከእንግዲህ ወዲህ በዚህ ቦታ ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ አይወርድልህም፡፡ ወደማሳይህ ቦታ ተነሥተህ ሂድ፣ በዚያም እስከ ዕረፍትህ ቀን ድረስ ሰማያዊ ኅብስትና ሰማያዊ ጽዋ ይወርድልሀል፡፡ ይህን ዓለም ለማሳለፍ እስከምመጣበት እስከ ዕለተ ምፅዓት ድረስ የእኔ ጌትነት የአንተም የቅድስና ሕይወት የሚነገርበት፣ የሥጋህ የዕረፍት ቦታ የሚሆንበት፣ ለምትሠራው መቅደስ ክዳን የሚሆን ሣር የማይፈልግ ሰፊ ዋሻ አለ፣ በዚያ ቤተ መቅደሴን ሥራ፣ እኔም በምትሠራው ቤተ መቅደስ ከአንተ ጋር ለዘለዓለም ቃልኪዳኔን አቆማለሁ፡፡ በምታንጸው ቤተ መቅደስ ውስጥ "አቤቱ የይምርሃነ ክርስቶስ አምላክ ሆይ! ስለወዳጅህ ስለ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ብለህ ይቅር በለኝ" እያለ "አባታችን ሆይ!" የሚለውን ጸሎት የሚጸልይ ዕለቱን እንደተጠመቀ አደርገዋለሁ፡፡ ነገ ማለዳ ተነሥተህ ወግረ ስሂን ወደሚባለው የዕረፍትህ ቦታ ወደሚሆነው ዋሻ ሕዝብህን አስከትለህ ሂድ፤ በዚያም ቤተ መቅደሴን ሥራ" ብሎ ጌታችን ቃልኪዳን ከሰጠው በኋላ ሰላምታ ሰጥቶት በክብር ወደ ሰማይ ዐርገ፡፡ በዚች ቦታ እስከመጫረሻው በገድል ተጠምዶ ኖሮ ከእግዚአብሔር አምላኩ ብዙ ቃል ኪዳንን ተቀብሎ ጥቅምት 19 ቀን በክብር ዐረፈ። ከጻድቁ ንጉሥ ከቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ እግዚአብሔር አምላክ ረድኤት በረከቱ ያሳትፈን፣ በጸሎቱ ይማረን!። + + + ❤ አቡነ ሐራ ድንግል፡- ጻድቁ ከአባታቸው ከሬማው ካህን ከቅዱስ ዮሐንስ ከእናታቸው ብፅዕት ወለተ ጊዮርጊስ የተወለዱት ጥቅምት 19 ቀን 1534 ዓ.ም ነው፡፡ የትውልድ ሀገራቸው ጥንት በጌምድር ደብረ ታቦር አውራጃ ደራ ወረዳ ይባል በነበረው አሁን በምዕራብ ጎጃም ዞን ባሕር ዳር ዙሪያ ወረዳ ላጉና ቀበሌ ነው፡፡ ቅዱሳን የሆኑ ወላጆቻቸውም አባታችንን ከልጅነታቸው ጀምሮ በሃይማኖት በምግባር ኮትኩተው አሳደጓቸው፡፡ አባታችንም የቤተ ክርስቲያንን መጻሕፍት በሙሉ ተምረው በታላቅ መንፈሳዊ ተጋድሎና አገልግሎት ከኖሩ በኋላ ዓለምን ፍጹም ንቀው መንነው ወደ ሸዋ ተጉዘው ግራርያ ከሚባል አገር ደረሱ፡፡ ❤ በዚያም ዘመዶቻቸው ፈልገው ስላገኙዋቸውና ወደ ሀገራቸው ስለመለሷቸው በሌላ ጊዜ ጥቅጥቅ ያለውን ጫካ አቋርጠው አሁን ገዳማቸው ካለበት ጫካ ውስጥ ገቡና ገዳመ ወንያትን መሠረቱ፡፡ በዚያም ፈተናውን ሁሉ ድምጸ አራዊቱን፣ ግርማ ሌሊቱን፣ ብርዱን፣ ሐሩሩን፣ ረሃብ፣ ጥማቱን ታግሰው በታላቅ ተጋድሎ ኖሩ፡፡ ሰይጣንም በፈተና ሊጥላቸው አንድ ጊዜ በተዋበች ቆንጆ ሴት እየተመሰለ አንድ ጊዜ ደግሞ በሞተ ሰው እየተመሰለ እስከ ሰባት ተከታታይ ቀናት ድረስ ቢፈትናቸውም ድል አድርገውታል፡፡ አባታችን ቀን ላይ ጸሎት እያደረጉ እያለ ነብር የሚያባርራት አንዲት ሚዳቋ መጥታ ከቤት ገብታ ከአቡነ ሐራ ድንግል እግር ስር አረፈች፡፡ ነብሩም ደርሶ ከደጅ እየተቆጣ ቆመ፡፡ ይህን ጊዜ አባታችን "እርሷን ገድለህ ትበላ ዘንድ እግዚአብሔር አልሰጠህምና ሂድ" ባሉት ጊዜ ቃላቸውን ሰምቶ ሄደ፡፡ ሚዳቋዋም እዛው አድራ ሲነጋ በሰላም አሰናብተዋታል። ❤ አባታችን መንኵሰው በገዳማቸው ከገቡበት ፈጽመው ሳይወጡ ለ14 ዓመት በተአቅቦ ተቀምጠዋል፡፡ በአንድ ወቅት ጠላት ተነስቶ አካባቢውን በሙሉ በመውረር ሁሉን ሲማርኩ ገዳሟን አይተው ወደ እርሷም ሊገቡ ሲሉ በተአምራት ባሉበት ተይዘው ቆመው በመቅረታቸው ጉዳት ሳይደርሱባት ተመልሰዋል፡፡ ሱስንዮስ "ሁለት ባሕርይ ሁለት አካል" የሚለውን የሮማን የረከሰ ሃይማኖት በሀገራችን ላይ አውጆ ብዙዎች ሰማዕትንትን ሲቀበሉ አቡነ ሐራ ድንግል በገዳማቸው ለብዙዎች መጠጊያ ሆነው ሃይማኖታቸውን ሲያስተምሯቸውና ሲያፀኗቸው ነበር፡፡ በንጉሡም ፊት ቀርበው በድፍረት "አንድ አካልና አንድ ባሕርይ የሆነውን መለኮትና ትስብእትን ለምን ከሁለት ወገን ትከፍለዋለህ?" ብለው ሲገስፁት ፈርቶ አሽከሮቹን "ይህን መነኵሴ ከቤቴ አውጥታችሁ በፍጥነት ወደ ገዳሙ አድርሱልኝ" ብሏቸዋል፡፡ ❤ እመቤታችንን እጅግ አድርገው ይወዷት ነበርና ምስጋናዋን ሲያደርሱ ሦስት ክንድ ከምድር ከፍ ይሉ ነበር፡፡ ቅዱስ ገብርኤልም የሁልጊዜ ጠባቂያቸው ነበር፡፡ በ1574 ዓ.ም አሁን በስማቸው ወደሚጠራው ገዳመ ወንያት መንነው ገቡ፡፡ በዚያም ወንጌልን እያስተማሩ፣እጅግ ድንቅ ድንቅ የሆኑ ተአምራትን እያደረጉ፣ ሙት እያስነሱ፣ ድውያንን እየፈወሱ እግዚአብሔርን ሲያገለገሉ ኖረዋል። ❤ አባታችን ሐራ ድንግል "የማነ ብርሃን" የሚባል ታማኝ አገልጋይ አህያ ነበራቸው፡፡ አህያውም ጸሎታቸው ይጠብቀው ነበር እንጂ እረኛ አልነበረውም፡፡ አንገቱ ላይ ቃጭል አስረው ወደ ገበሬው አውድማ ይልኩትና አህያውም ቃጭሉን እያጮኸ ወደ አውድማው ሁሉ ሄዶ እየዞረ "ማርያም ባርኪ" በረከት ሰፍረው ይጭኑታል፡፡ አህያውም ከገበሬው ሁሉ የሰበሰበውን እህል ይዞ ወደ አቡነ ሐራ ድንግል ይገባል፡፡ በፈለጉትም ሰዓት ራሱ አውቆ ይመጣላቸው ነበር፡፡ አህያውም አርጅቶ ሲሞት እንደ ሰው አልቅሰውና በአዲስ ጨርቅ ጠቅልለው ቀብረውታል፡፡ አህያቸው የማነ ብርሃን ከተቀበረበት ቦታ ላይ ጸበል ፈልቆ አስደናቂ ተአምራትን አድርጓል፡፡ የቅዱሳኑ በረከታቸው እስከምን ድረስ እንደሆነ ልብ ይሏል፡፡ ታላላቆቹ ቅዱሳን እንደነ በትረ ማርያም፣ ጽጌ ድንግል፣ ወለተጴጥሮስ ያሉ ሌሎችም በርካታ ደጋግ ቅዱሳን ዝናቸውን እየሰሙ ከያሉበት እየሄዱ ይጎበኙዋቸውና በረከታቸውን ይቀበሉ ነበር፡፡

❤ "በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"። ❤ ❤ ጥቅምት ፲፱ (19) ቀን። ❤ እንኳን ለኢትዮጵያዊው ንጉሥ ክህነት ከንግስና ጋር አስተባብሮ ለያዘው 40 ዓመት ሙሉ ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ ከሰማይ እየወረደለት ለቀደሰው ለጻድቁ ለቅዱስ ለይምርሐነ ክርስቶስ ለዕረፍት በዓልና ለታላቁ አባት ከመቃብራቸው በሚወጠው በእምነታቸውና በጠበል ፈዋሽነታቸው ለመታወቁት ለአቡነ ሐራ ድንግል ለልደታቸው በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕትነት ለተቀበሉ ለቅዱስ በርተሎሜዎስና ለሚስቱ ለዕረፍታቸው በዓል፣ ስለ ጳውሎስ ሳምሳጢ በአንጾኪያ የቤተ ክርስቲያ አንድነት ስብሰባ ለተደረገበትና ለጸይለም አገር ለሆነ ለከበረ አባት አቡነ ዮሐንስ ለዕረፍት ለዕረፍታቸው በዓል፣ በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ቀን ከሚታሰቡ፦ እንደ በግ ከታረዱ ከመጥራ ጻድቃ ከመታሰቢያቸው እግዚአብሔር አምላክ ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። + + + ❤ ጻድቁ ንጉሥ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ፡- ከላስታ (ከዛጉዌ) ነገሥታት መካከል ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ፣ ቅዱስ ገብረ ማርያም፣ ቅዱስ ላሊበላና ቅዱስ ነአኵቶለአብ እነዚህ አራቱ ነገሥታት እንደ መልከጼዴቅ (ዘፍ 14፡18) ክህነትን ከንግሥና፣ ቅድስናን ከንጽሕና ጋር አንድ አድርገው በመያዝ እግዚአብሔርንም ሰውንም በቅድስና አገልግለው አልፈዋል፡፡ በንግሥናቸው ሀገርን በመልካም ሥራና በቅድስና ከማስተዳደራቸው በተጨማሪ ቅዱሳን ጻድቃን ሆነው እግዚአብሔርን በብዙ ድካም በመልካም ተጋድሎአቸው ያገለገሉና አገልግሎታቸውም ሆነ ቅድስናቸው በእግዚአብሔር ዘንድ የተመሰከረላቸው ቅዱሳን ናቸው፡፡ ❤ ከእነርሱም ውስጥ ሞትን ሳያይ እንደነ ሄኖክና ኤልያስ የተሰወረ አለ፤ ከእነርሱም ውስጥ በባሕር ላይ ቤተ መቅደሱን ያነጸ አለ፤ ከእነርሱም ውስጥ የታዘዘ መልአክ መጥቶ ወደ ሰማይ ነጥቆ ወስዶት የቤተ መቅደሶቹን አሠራር ራሱ ጌታችን በቃሉ ያስረዳው አለ፡፡ ከእነርሱም ውስጥ በክህነቱ ሲቀድስ 40 ዓመት ሙሉ ቅዱስ ቁርባኑን መላእክት ከሰማይ እያመጡለት የነበረ አለ፡፡ እነዚህ ቅዱሳን ነገሥታት ገድላቸውና ትሩፋታቸው፣ ምግባር ሃይማኖታቸው እጅግ ድንቅ ነው፡፡ የእነዚህ ቅዱሳን ነገሥታቱን የዘር ሐረጋቸው ከሰሎሞን ዘር ሲያያዝ የመጣ ነው፡፡ከ10ኛው እስከ 13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን (920-1253 ዓ.ም ገደማ) በላስታ ቡግና ምድር የነገሡ የላስታ ቡግና ተወላጅ የሆኑ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ነገሥታት የንግሥናቸው መጠሪያ "የዛጉዌ ሥርወ መንግሥት" ወይም "የላስታ መንግሥት" በመባል ይታወቃል፡፡ ከዛጉዌ ነገሥታት ውስጥ የመጀመሪያው ንጉሥ መራ ተክለሃይማኖት የዐፄ ድልነአድን ልጅ መሶበወርቅን አግብቶ አራት ልጆችን ወልዷል፡፡ ሦስቱ ወንዶች ጠንጠውድም፣ ግርማ ስዩምና ዣን ስዩም ይባላሉ፡፡ ጠንጠውድም ገብረ መስቀልን ወለደ፣ ግርማ ስዩም ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ወለደ፣ ዣን ስዩም ደግሞ ቅዱስ ገብረማርያምንና ቅዱስ ላሊበላን ወለደ፡፡ ገብረ መስቀልም ጣራው ክፍት ሆኖ ዝናብ የማያስገባውን ገዳም የመሠረቱትን የመቄቱን ታላቁን አባት አቡነ አሮንን ወለደ፡፡ ቅዱስ ገብረማርያም ደግሞ ቅዱስ ነዓኵለአብን ወለደ፡፡ ❤ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ በቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ሳለ መልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል "ከጠንጠውድም በኋላ የምትነግሠው አንተ ነህ" በማለት ከነገረው በኋላ በመንገዱ ሁሉ እየተራዳው ወደ ኢትዮጵያ ይዞት መጥቷል፡፡ በቤተ መቅደስ ገብቶ ሲቀድስ መላእክት ሰማያዊ ኅብስትንና ጽዋን አምጥተው እየሰጡት እርሱም ለሕዝቡ ሁሉ ያቆርባቸው ነበር፡፡ ሕዝቡን የሚባርክበትም መስቀል ከሰማይ ነው የወረደለት፡፡ ዛሬም ድረስ አለ፣ በዓል ሲሆን ካህናት አባቶች እያወጡ ሕዝበ ክርስቲያኑን ይባርኩበታል፡፡ ጌታችን ለይምርሃነ ክርስቶስ በአካል ተገልጦለት እስከ ዕለተ ምፅዓት ድረስ አካሉ እንደማይፈርስ ቃልኪዳን የሰጠውንና አሁን በላስታ ላሊበላ ያለውን ቤተመቅደሱን በባሕር ላይ እንዲሠራ ነግሮት በኋላም በቦታው ላይ እጅግ አስደናቂ ቃልኪዳን ሰጥቶታል፡፡ ❤ ቅዱስ ይምርሃነ ክርስቶስ ግንቦት 19 ቀን ሲወለድ እንደነ አቡነ ተክለሃይማኖትና እንደነ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ ምሥራቅ ዞሮ አምላኩን ያመሰገነ ሲሆን ቤቱም በብርሃን ተሞልቶ ታይቶ አዋላጆቹን ሁሉ አስገርሟል፡፡ እርሱ ገና ሳይወለድ በፊት አጎቱ ጠንጠውድም በንግሥና ላይ ሳለ "ከአንተ በኋላ የሚነግሠው ይምርሃነ ክርስቶስ የሚባል ሰው ነው" ተብሎ ሲነገረው "እንዲህ የሚባል ሰው በቤተ መንግሥቴ አለን?" በማለት ቢጠይቅም እንደነቢዩ ኤርሚያስ ከእናቱ ማኅፀን ጀምሮ የተመረጠ ሕፃን እንደሚወለድ ነግረውታል፡፡ አርባ ዓመት የነገሠው ጠንጠውድም ቀድሞ በትንቢት እንደተነገረው "ይምርሃነ ክርስቶስ" የሚባል የወንድሙ ልጅ መወለዱን ሲሰማ "የወንድሜን ልጅ አየው ዘንድ አምጡልኝ" ብሎ ላከ፡፡ ባየውም ጊዜ ደም ግባቱ እጅግ ያምር ስለነበር "ይህስ መንግሥቴን ይውረስ፣ በእውነት ልጄ ነው" ብሎ ባረከው፡፡ ሆኖም ከእርሱ ጋር ስምንት ቀን ተቀምጦ በወለዳቸው ልጆቹ መካከል በተመለከተው ጊዜ በልቡ ሰይጣን አደረበትና በቅናት ሆኖ "እርሱ ነግሦ ልጆቼ ወታደሮቹ ሊሆኑ ነው" በማለት ይገድለው ዘንድ አሰበ፡፡ሆኖም ግን "ለጊዜው ምንም አያውቅም ለወደፊቱም የንግሥና ምሥጢር እንዳያውቅ ወደ እናቱና አባቱ ዘንድ መልሰው በዚያ ከብት ሲያግድ ያድጋል እንጂ ሥርዓተ ንግሥናን አያውቅም" በማለት ስለተመከረ ወደ እናቱ ላከው፡፡ በኋላም በጥበብና በብልሃት አስተዋይ ሆኖ ማደጉን በሰማ ጊዜ ሊገድለው አሽከሮቹን ላከ፡፡ እናቱም ለተላኩት አሽከሮች ምግብ አቅርባ እርሷ ግን ነገሩን እንዲገልጽላት እግዚአብሔርን በስውር አልቅሳ ስትለምን የንጉሡ ተንኮል ስለተገለጠላት ልጇን ደበቀችው፡፡ በስውርም ወስዳ ከጳጳሱ ዘንድ ዲቁና እንዲቀበል ካደረገችው በኋላ "ልጄ ሆይ! አጎትህ ሊገድልህ ይፈልግሃልና በፊቴ ከሚገድልህ ርቀህ ብትሄድ ይሻላል፣ ያዕቆብን ከኤሳው የጠበቀ አንተንም ይጠብቅህ" ብላ ሸኘችው፡፡ ❤ ንጉሡ አጎቱም "ይምርሃነ ክርስቶስን ፈልጎ ላገኘልኝ የመንግሥቴን እኩሌታ እሰጣለሁ" ብሎ ቢያውጅም ይምርሃነ ክርስቶስ ግን ወደ ኢየሩሳሌም ተሰደደ፡፡ በዚያም የሌዋውያን ወገን የምትሆን ቅድስት ሕዝባን አግብቶ ቅስናም ተቀብሎ ሥጋዊውንና መንፈሳዊውን ጥበብ ተምሮ ካጠናቀቀ በኋላ ወንጌልን እየሰበከ፣ በተአምራቱም ሕመምተኞችን እየፈወሰ እግዚአብሔር እያገለገለ ኖረ፡፡ እግዚአብሔርም አጎቱ ንጉሥ መሞቱንና በንጉሡም ዙፋን እርሱ እንደሚነግሥ ነግሮት በመልአኩ ቅዱስ ሩፋኤል መሪነት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሶ መጥቶ በላስታ ወረዳ ሳይ (ዛሬ ሸጐላ ማርያም) ከምትባል ሀገር ደርሶ በዚያ ወንጌልን እያስተማረ፣ ድውያንን እየፈወሰ ተቀመጠ፡፡ ትምህርቱንና ተአምራቱን ያዩት የአካባቢው ሰዎች "ነፃነትና ፍቅር የሚገኝብህ የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! እኛ ሰላማዊ ብርሃናዊ ብለን ስም አወጣንልህ፣ ያንተ ግን ስምህ ማን ይባላል ንገረን" አሉት፡፡ እርሱም "ስሜ ይምርሃነ ክርስቶስ ነው" ባላቸው ሰዓት ሕዝቡ ሁሉ በሹክሹክታ "ይምርሃነ ክርስቶስ የሚባል ሲነግሥ ሃይማኖት ይቀናል፣ ፍርድ ይስተካከላል፣ በዘመኑም የሮም ሰዎች ለኢትዮጵያ ይገዛሉ" ሲሉ አባቶቻችን ሰምተናል አሉ፡፡