cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

✨ኢትዮ ትንሳኤ✨🌍

The best channel ever የጥንት ኢትዮጵያውያን የህዋ ስልጣኔና የሚስጥር ሳጥን በጥበብ ቁልፍ ሲከፈት 👇 👇 👇 👇 👉@✨ኢትዮ ትንሳኤ✨🌍👈 Join በሉ ኑ ከጥበብ መአድ ተካፈሉ 👆 👆 👆 👆

Більше
Рекламні дописи
209
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

✍️የቀጠለ ➪ከዚህ በፊት እንደተገለጸው ቅርብ የሚባሉ ከዋክብት አሉ ስንል ቅርበቱ እንዲህ በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ ስለ ቅርብ ከዋክብት ስናወራ ለእኛ የመጀመሪያ ቅርብ ከሆነችው ፀሐይ ውጭ ያሉትን መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህ አካሄድ ታዲያ ቅርብ ብለን ያነሣነው “ፕሮክሲማ ሴንታውሪ” 4.2 የብርሃን ዓመት ርቀት ነው ስንል ኮከቡ ጋ ለመድረስ በብርሃን ፍጥነት ብንጓዝ 4.2 ዓመት ይፈጃል ማለት ነው። ➩የሰው ልጅ በሠራቸው አሁን ባሉት ፈጣን መንኰራኵሮች እንጓዝ ያልን እንደሆነ ደግሞ ወደ 70,000 ዓመታትን ነው የሚፈጀው፡፡ ይህ እንግዲህ ቅርብ እንኳን ብለን የወሰድነው ኮከብ ምን ያህል ሩቅ እንደሆነ ከማሳየቱም በተጨማሪ  ዩኒቨርስ ምን ያህል ሰፊ እንደሆነም የሚጠቁም ነው፡፡ ሁለተኛ ቅርብ የሚባለው "በርናንድ" የሚባለው ኮከብ እንኳን 5.9 የብርሃን ርቀት ላይ ነው የሚገኘው። ➩መጠናቸውንም በተመለከተ በከዋክብት መሓከል እጅግ የሰፋ ልዩነት አለ፡፡ ማታ ላይ በዐይናችን የምናያቸው ከዋክብት ሁሉ በመጠናቸውና ደማቅነታቸው ከፀሐይ ይበልጣሉ፡፡ እጅግ ግዙፍ ከሚባሉት ውስጥ “ዩ ዋይ ስኩቲ" (UY Scuti) የሚባለው የፀሐይን ሬዲየስ 1700 እጥፍ ሲሆን “ቪ ዋይ ካኒስ ማጆሪስ" (VY Canis Majoris) የሚባለው ደግሞ ከ1,400 እስከ 2,000 እጥፍ የፀሐይን ሬዲየስ እንዳለው ታውቋል።እንደ ኒውትሮን ኮከብ ያሉት ደግሞ በጣም ትንሽ መጠን ያላቸው ሲሆን ሬዲየሳቸው 10 ኪ.ሜ. ብቻ ነው። ➩ማታ ላይ ከምናያቸው ከዋክብት ውስጥ እጅግ ደማቅ የሚባለው “ሳይረስ” (Sirius) የሚባለው ሲሆን የፀሐይን 20 እጥፍ ድምቀት አለው፡፡ ነገር ግን በጣም ሩቅ ስለሆነ ድምቀቱ አነስ ብሎ ይታያል፡፡ ተቆጥረው የማያልቁት ከዋክብት የብዛታቸውም ግምት በሳይንስ ተሰልቷል፡፡ በእኛ ጋላክሲ ውስጥ ከ100 እስከ 200 ቢሊዮን ከዋክብት እንዳሉ ይታመናል። በዩኒቨርስ ውስጥ ያሉት ጋላክሲዎች ብዛት ደግሞ ወደ 200 ቢሊዮን ስለሚገመት በዩኒቨርስ ውስጥ ያሉት ከዋክብት ብዛት ከ10 ሴክስቲሊየን (10²¹) እስከ 10 ሴፕቲሊየን (10²⁴) እንደሆነ ሒሳቡ ያመለክታል።                            ምንጭ፦አንድሮሜዳ መፅሀፍ ✍️ ሀሳብ አስተያየታችሁን ከስር ፃፋልኝ
Показати все...
👉የከዋክብት ልዩነት ➪ሌላው የተወሰነውን በዐይናችንም አይተን እንደምንመሰክረው በከዋክብት መሓከል ብዙ ዓይነት ልዩነቶች አሉ፡፡ የከዋክብትርቀት፣ ክብደት፣ ይዘት፣ ቀለም፣ሙቀት፣ደማቅነት የተለያየ ነው፡፡ የእፍጋት መጠናቸው፣ ብሩህነታቸው፣ ዕድሜአቸው፣ ውስጣዊ ሥሪታቸው እና የሚንቀሳቀሱበት አቅጣጫ ሌላው መለያቸው ነው፡፡ እንደ ፀሐይ ያሉ ከዋክብት ብቻቸውን ተገንጥለው የሚገኙ ሲሆን ጥንድ ሆነው፣ ሦስት ወይም አራት ሆነውም በስበታቸው ተያይዘው የሚኖሩ ከዋክብትም እንዳሉ የሳይንስ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ ➩በእርግጥ ከኀምሳ ፐርሰንት በላይ የሚሆኑት በምሽት የምናያቸው ከዋክብት ጥንድ እና ከዚያ በላይ ናቸው፡፡ ለምሳሌ ቅርብ የሚባለው “ፕሮክሲማ ሴንታውሪ” ብቸኛ ሳይሆን የሦስት ከዋክብት (አልፋ ሴንታውሪ ኤ፣ አልፋ ሴንታውሪ ቢ እና ፕሮክሲማ ሴንታውሪ) ውጤት ነው፡፡ እንደ ፀሐይ በዙሪያቸው ፕላኔት ያላቸውም አሉ፡፡ አንዳንድ ከዋክብት ደግሞ የራሱ ቃና ያለው ድምፅ እንደሚያወጡ ሳይንስ አረጋግጧል፡፡ ➩ከዋክብት እንደየሙቀት መጠናቸው ሰማያዊ፣ ቀይ ወይም ቢጫ ቀለም ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ሳይንስ ከዋክብት አረንጓዴ ቀለም በፍጹም ሊኖራቸው እንደማይችል ግን አረጋግጧል። ከዋክብት ይወለዳሉ፣ የተወሰነ ዘመን ይኖሩና ከዛም ይሞታሉ።ለምሳሌ አሁን ይህን ጽሑፍ እያነበብን ባለንበት ቅጽበት እንኳን ከዋክብት እየተወለዱ ነው፡፡ መጠነ ቁሳቸው በጣም ትልቅ የሆኑ ከዋክብት ዕድሜያቸው ዐጭር ሲሆን እንደ ፀሐይ አነስ ያሉት ግን ዕድሜአቸው ረጅም ነው። ሰማዩን ሞልተው በብዛት የሚገኙት የከዋክብት ዓይነቶች “ቀይ ድንኮች” (red dwarf) ይባላሉ፡፡ ለምሳሌ እኛ የምንኖርበትን ጋላክሲ (ፍኖተ ሐሊብ) ብንወስድ 85 ፐርስንቱ ከዋክብት ቀይ ድንኮች ናቸው፡፡                     ምንጭ፦አንድሮሜዳ መፅሀፍ ሀሳብ አስተያየታችውን ከስር አስቀምጡልኝ         👇👇
Показати все...
👉ኮከብ⭐💫✨          👇👇👇 ➪እንደ ሳይንሱ ጥናት ኮከብ ማለት በብዛት የሀይድሮጂን እና ሒልየም ሥሪት የሆነ፣ በራሱ የስበት ኀይል ሉል ቅርጽ ሠርቶ ያለና የራሱን ብርሃን የሚያመነጭ ጋዛማ ሰማያዊ አካል ነው፡፡ ወደ ዐምስት ሺሕ የሚሆኑ ከዋክብት በዐይን መታየት የሚችሉ ሲሆን፤ ግማሹ የመሬት ክፍል ቀን ስለሚሆን አንድ ስው ጨረቃ በሌለበት ሰማይ ላይ በምሽት ሁለት ሺሕ ዐምስተ መቶ ከዋክብትን ማየትን ይችላል፡፡ ➪በእርግጥ ማታ ላይ የምናያቸውና ሰማይ ላይ የሚያንጸባርቁ ሁሉ hዋክብት አይደሉም፡፡ ምክንያቱም ፕላኔቶችም በዐይን ሲታዩ ኮከብ መስለው ስለሚታዩ መለየት ይገባል፡፡ ከዋክብትን እና ፕላኔቶችን ከምንለይባቸው መንገዶች ዋናው ከዋክብትን ትኩር ብለን ስናያቸው ብርሃናቸው የመርገብገብ ዐይነት ባሕርይ ያሳያል፡፡በሳይንሳዊ አጠራሩ ይህ "ቲዊንክሊንግ"(twinkling) ይባላል። ይህ መርገብገብ ግን ኮከቡ ጋር ያለ ባሕርይ  ሳይሆን የመሬት ከባቢ አየር የፈጠረው ነው፡፡ ፕላኔቶችን ስናይ ግን ይህ የመርገብገብ ሁኔታ ስለማይታይባቸው በቀላሉ እንለያችዋለን ማለት ነው፡፡ ➪እንደ ሳይንስ ጥናት ከዋክብትን ስናይ ከጊዜ አንጻር ወደ ኋላ ተጉዘን በፊት የነበሩበትን ሁኔታ ነው የምናየው፡፡ ለምሳሌ ፀሐይን እየተመለከትን እያለን የፀሐይ ሁኔታ እየተመለከትንበት ባለንበት ቅጽበት ሳይሆን ከ8.2 ደቂቃ በፊት የነበረችበትን ሁኔታ ነው የምናየው፡ ይህም የሚሆነው የፀሐይ ብርሃን መሬት ላይ ለመድረስ 8.2 ደቂቃ ስለሚፈጅ ነው፡፡ ➩በተመሳሳይ ለመሬት ቅርብ የሆነውንና ከመሬት በ4.2 የብርሃን ዓመት ርቀት ላይ ያለውን “ፕሮክሲማ ሴንታውሪ” ስናይ የምንመለከተው ኮከቡ ከ4.2 የብርሃን ዓመት በፊት የነበረበትን ሁኔታ ነው። ሀሳብ አስተያየታቸውን ከስር Comment ላይ ፃፉልኝ።
Показати все...
Показати все...
✨ዘደሸት አስትሮኖሚ🪐️

አስደናቂ የአስሮኖሚ ምርምሮችን፣የታላቋ ኢትዮጵያ መገለጫ እሳቤዎች እንዲሁም በማይታየው ዓለም ወደ95ቱ የስሜት ህዋሳት የሚነጥቅ ድንቅ ጥናቶችና ምርምሮቹን የሚያገኙበት ቻናል።

👀 ተወያዩበት!!
Показати все...
00:58
Відео недоступнеДивитись в Telegram
10.44 MB
ምን አልባት ይሄ አስፈሪ ድምፅ በኤፍራጠስ ወንዝ ስር የታሰሩት የአራቱ መናፍስት ይሆን!!
Показати все...
የኤፍራጥስ ወንዝ መድረቅ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የተፈጠሩ ዋሻዎችን ተመልከቱ፦
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.