uk
Feedback
Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Відкрити в Telegram

Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Comments Construction Solution Official Service

Показати більше
3 584
Підписники
Немає даних24 години
-57 днів
+5330 день
Архів дописів
+1
የተለያዩ የመንገድ ግንባታና ጥገና አገልግሎት የሚውል የሚዲባስ ተሽከርካሪ ኪራይ ጨረታ

በኮንስትራክሽን Site🏗 ስራ ላይ ውጤታማ ለመሆን የሚያስፈልጉ COTM/ ሲቪል ኢንጅነር ሊያውቃቸው የሚገቡ 10 ወሳኝ ነጥቦች:-
1) የግንባታ እቃዎች ፍተሻ( TESTS OF BUILDING MATERIALS) አንድ ጥሩ ኢንጅነር በሳይት ላይ የሚሰሩ የግንባታ እቃዎችን ለመፈተሽ የሚጠቅሙ የፍተሻ ስራዎችን የግድ ማወቅ ይጠበቅበታል። ከታች የተለያዩ አይነት የፍተሻ ቴክኒኮች ተጠቅሰዋል የኮንክሪት ፍተሻ(Concrete Test): ✅️Slump test, ✅️compression test (cubic or cylindrical test), ✅️split tensile test, soundness etc. የአፈር ፍተሻ (Soil Test): ✅️Core cutter test, ✅️compactiontest,sand replacement test, triaxial test, consolidation test etc. Bitumen Test: ✅️Ductility test, softening point test, gravity test, penetration test etc. (በእርግጥ እነዚህን ሁሉ እውቀቶች በየዮንቨርስቲዎች ውስጥ አንማር ይሆናል ነገር ግን ዘመኑ የቴክኖሎጂ ነው ተወዳዳሪ ሆኖ ለመቅረብ የግድ መማር ማወቅ አለብን ዩ ቲዩብ ገብተን ብንፈልግ በቪድዮ የተደገፉቁም ነገሮችን እናገኛለን ጥቆማችን ነው 2) የአፈር ጥናት (INVESTIGATION OF SOIL) የተለያዩ አይነት የፍተሻ ቴክኒኮችን ተጠቅመን የአፈሩን የመሸከም አቅም እና ርጉእነት (settlement and stability ) የምንገነባው አካል ከመገንባቱ በፊት ልናውቅ እንችላለን። እንደ ኢንጅነር የአፈር ጥናት ለማድረግ የሚጠቅሙ በሳይት ላይ የሚከወኑ የፍተሻ ቴክኒኮችን ማወቅ ግዴታችን ነው። 3 የተለያዩ የሰርቬይን መሳሪያዎች አጠቃቀም ማወቅ(USES OF SURVEYING INSTRUMENTS) በእርግጥ በብዙ የኮንስትራክሽን ስራዎች ላይ ራሱን የቻለ የሰርቬይ ባለሞያ መቅጠር አሁን አሁን የተለመደ ቢሆንም ነገር ግን መሰረታዊ የሚባሉ የሰርቬይ መሳራያዎች ለምሳሌ ቶታል ስቴሽን እና ቴዎዶላይት አጠቃቀማቸውን አንድ ኢንጅነር የግድ ማወቅ አለበት። የግድ ! 4). የተለያዩ የግንባታ ስታንዳርድ ኮዶች (STANDARD CODES USED IN CONSTRUCTION) ኢትዮጵያን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ከመልካ ምድራቸው የአየር፣ የንፋስ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ከባቢያዊ ፀባያቸው አንፃር የሚያዘጋጁት የግንባታ መርህ (Construction codes) አላቸው። አንድ ኢንጅንየር ግንባታ የሚያደርግበት ሃገርን ስታንዳርድ ኮድ የማወቅ ግዴታ አለበት ምክንያቱም የሚገነባው ቁስሃገሪቱ ባላት ተፈጥሯዊ መሰናክል እንዳይሰናከል እና እንዳይወድም። እነዚህን ኮዶች ወይም መመሪያዎች ሳይከተል የሚገነባ የትኛውም ግንባታ የመፍረስአቅሙ በእጥፍ የጨመረ ነው። 5) BAR BENDING SCHEDULE ባር ቤንዲንግ ስኬጁል ለኢንጅነየሮች ጠቃሚ የሆነ ቻርት (በተለይ ኮንስትራክሽኑ ሬንፎርስመንት ካለው)። ይህ ቻርት ሬንፎርስድ የሆነው የግንባታ አካል ማለትም ቢም፣ ኮለን፣ ስላብ፣ ዋል... የሚጠቀማቸውን ቤረቶች የሚቆረጥበት ርዝመት ፣ በምን ያህል ርዝመት እንደሚታጠፉ እና ምን ያክል ተመሳሳይ እጥፋትና ርዝመት ያላቸው ባሮች በዛ አካል ውስጥ እንደሚኖሩ በግልፅ ይነግረናል ። ይህ ቻርት ብረትን ያለብክነት እንድንጠቀም እና የስትራክቸሩን ደህንነት (safety) እንድንጠብቅ ይጠቅመናል 6) የንድፍ እና ዲዛይን ንባብ (DRAWING AND DESIGN) አንድ ሳይት ኢንጅነር ከምንም ከምንም በላይ የግንባታን ንድፍ የማንበብ በጣም ትልቅ እውቀት ሊኖረው ይገባል። ዲዛይን እና ንድፎችን በትክክል ማንበብ እናመተርጎም ከቻለ ለሳይት ኢንጂንየርነት የሚያበቃውን 60% እውቀት አካብቷል ማለት ነው። ስለዚህ በተለይ ተማሪዎች ለቴክኒካል ድራዊንግ እና አውቶካድ እውቀቶች የምትሰጡትን ክሬዲት ከፍ አርጉ የፔጃችን መልእክት ነው:: 7) ግምት እና ክፍያ ( ESTIMATION AND BILLS) ግንባታው ምን ያህል ገንዘብ እንደሚያወጣ ግምቱን የሚያስቀምጠው የሳይት ኢንጅንየሩ ነው። (እንዴት መገመት እንዳለብን ፎርማቱን ወደፊት እንፖስታለን) 8 የጥራት ቁጥጥር (QUALITY CONTROL) ከኢንጅነሪንግ መርሆች ውስጥ አንዱ ጥራት ነው። ጥራቱን የጠበቀ ግንባታ ለተጠቃሚው አካል ገንብቶ ማቅረብ ግዴታችን ነው። አንዳንዴ ለሆዳቸው ያደሩኢንጂንየሮች ጥራቱን ባልጠበቀ የግንባታ መሳሪያ ገንብተው ያስረከቡት ህንፃ ምን አይነት ጉዳቶች እንዳደረሰ የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው። አንድ ሳይት ኢንጅነር የሚጠቀመውን የግንባታ ቁስ ጥራት የማወቅ ግዴታ አለበት ኋላ በሃገርም በግለሰብም ላይ የሚደርስን አደጋ ለመከላከል። 9) የሳይት ላይ አመራሮች (ON FIELD MANAGEMENT) እንዴት ፎርም ወርክ መታሰር እንዳለበት፣ የኮንክሪት አሰራር፣ ለጥንቃቄ የምንሰራቸው ስራዎችን ጨምሮ የተለያዩ ነገሮች ማወቅ ግዴታችን ነው 10) ከጉልበት ሰራተኞች ጋር ያለን መናበብ መቀራረብ (COORDINATION WITH LABOR) የጉልበት ሰራተኞችን ጨምሮ ሌሎች የተማሩ እና ያልተማሩ ሰራተኞችን እንዴትማስተዳደር እንዳለብን እውቀቱ ሊኖረን ይገባል። ትዛዝ ማስተላለፍ ብቻሳይሆን ወርዶ መስራትም ይጠበቅብናል። ለስራችን መቀላጠፍ ከሁሉምጋ ተናቦና በፍቅር መስራት ወሳኝ እና ወሳኝ ነው

ወጥነት ያለው የጨረታ ሂደት ዕውን ለማድረግ ያለመ ውይይት ተደረገ🏗 የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ከጨረታ ግብዣ ማስታወቂያ ጀምሮ ባለው አጠቃላይ የግንባታ ጨረታ ሂደት ዙሪያ በተደረገ
ወጥነት ያለው የጨረታ ሂደት ዕውን ለማድረግ ያለመ ውይይት ተደረገ🏗
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ከጨረታ ግብዣ ማስታወቂያ ጀምሮ ባለው አጠቃላይ የግንባታ ጨረታ ሂደት ዙሪያ በተደረገ ጥናት መነሻነት ከተለያዩ ክፍለከተሞች ከተውጣጡ የዲዛይንና ግንባታ ጽ/ቤት ተወካዮች ጋር  ውይይት አድርጓል፡፡  የውይይቱ አላማ በግንባታ ጨረታ ሂደት ከመነሻው ጀምሮ የሚስተዋሉ የአፈፃፀም ችግሮችን ለመለየት ተደረገውን ጥናት መነሻ በማድረግ እነዚህን ችግሮች ህጎች ላይ መሰረት ያደረገ እና ግልፅነት እንዲሁም ፍትሀዊነት የተረጋገጠበት የጨረታ ስርዓት በኢንዱስትሪው ላይ ለመተግበር ያለመ እንደሆነ ውይይቱን የመሩት የቢሮው ቴክኒካል አማካሪ ኢ/ር አብነት አለነ በመድረኩ ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም በመመሪያ አተረጓጎም ልዩነት ሳቢያ ወጥነት በሌለው መልኩ ጨረታዎች ሲዘጋጁና ችግሮች ሲስተዋሉ መቆየታቸው ተጠቅሶ ይህም ለጨረታዎች በተደጋጋሚ መሰረዝ ምክንያት ሆኖ እንደቆየ በመድረኩ የተነሳ ሲሆን የዛሬው ውይይትም ቢሮው በዕቅድ ከያዛቸውና ይህን ችግር ከመሰረቱ በመቅረፍ ግልፅ፣አሳታፊና ወጥነት ያለው የጨረታ ስርዓት ለመዘርጋት ከሚያስችሉ ተከታታይነት ያላቸው ተግባራት ውስጥ አንዱ መሆኑ ተነስቷል።
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ @con_site 🏗

የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች የጊዜና የዋጋ መገመቻ ማንዋልና ሶፍትዌር ረቂቅ ሰነድ ላይ ውይይት ተካሂዷል🏗
የኢት/ኮንስትራክሽን ባለስልጣን  የግንባታ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ እንዲሁም  በተገቢ ዋጋ ተፈጻሚ እንዲሆኑ የሚያስችል ሀገር አቀፍ አሰራርን ለመዘርጋት አልሞ እየሰራ ይገኛል። በዚሁ መሰረትም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሲያስጠናው የነበረው የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች የጊዜና የዋጋ መገመቻ ማንዋልና ሶፍትዌር ተቋሙ ሲያስጠና ቆይቷል ፡፡  በጥናቱ ረቂቅ ሰነድ ላይ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት ጥቅምት 14/2017ዓ.ም ምክክር ተካሂዶበታል። የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የሆኑት ተስፋሁን ንጋቱ እና በጋሻው ወርቁ በቀረበው የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች የዋጋና የጊዜ መገመቻ ረቂቅ ሰነድ ላይ መካተት ስላሉባቸው ሳይንሳዊ፣ ቴክኖሎጂያዊ እና ሀገራዊ ነባራዊ ሁኔታዎች ላይ ግብረ መልሶች ቀርበዋል፡፡ አሁን ላይ ያለውን የግንባታ ፕሮጀክቶች የዋጋና የጊዜ ግመታ አሰራር ክፍቶችን በአግባቡ የመለየት፣ የማንዋሉና የሶፍትዌሩ ዝርዝር እና ጥቅል ይዘቶችን ግልፅ የማድረግ እና በአተገባበር ሂደት ላይ የተሳታፊ አካላትን ሃላፊነትና ሚና የማሳየት ጉዳዮች መካተት እንዳለባቸው ተሳታፊዎች ሙያዊ ግብረ መልስ ሰጥተዋል፡፡ እንዲሁም ማንዋሉና ሶፍትዌሩ ከግንባታ መረጃ ማናጅመንት/ BIM / ጋር የሚናበብ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ትኩረት እንዲሰጥ፣ በቀጣይም ወደ ትግበራ ከመገባቱ አስቀድሞ በተመረጡ ፕሮጀክቶች ላይ የማሳያ ትግበራ እንዲካሄድም ግብረ መልስ ተሰጥቷል፡፡ የጥናት ሰነድ አቅራቢዉ ተስፋሁን ንጋቱ በተሰጡ ግብረ መልሶች ላይ ምሁራዊና ሳይንሳዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በቀጣይም የጥናት ረቂቅ ሰነዶቹ በፍጥነት ዳብረው ለትግበራ እንደሚዘጋጁም ገልፀዋል፡፡ በውይይቱ ማጠቃለያ ላይ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ ረቂቅ ሰነዶቹ ማለፍ የሚገቧቸውን ሂደቶችና ደረጃዎች እንዲያልፉ ጥረት እንዲደረግ አሳስበዋል፡፡ በዋናነትም ለጥናቱ ግብአት የሚዉሉ የመረጃ አሰባሰብ ላይ ትኩረት እንዲደረግ አስገንዝበዋል፡፡ የጥናት ሰነዶቹ ሲገባደዱ ከትግበራ አስቀድሞ የሙከራ ትግበራ እንዲሁም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ደረጃዎችን ያልፋል ያሉት ኢ/ር መስፍን ነገዎ የወደፊት አሰራሩ በቀጣይ ትግበራ እያደረገ እንደሚሄድ ገልፀዋል፡፡ 
 Via~ (ኢኮባ) @con_site 🏗

ወጥነት ያለው የጨረታ ሂደት ዕውን ለማድረግ ያለመ ውይይት ተደረገ🏗 የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ከጨረታ ግብዣ ማስታወቂያ ጀምሮ ባለው አጠቃላይ የግንባታ ጨረታ ሂደት ዙሪያ በተደረገ
ወጥነት ያለው የጨረታ ሂደት ዕውን ለማድረግ ያለመ ውይይት ተደረገ🏗
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ከጨረታ ግብዣ ማስታወቂያ ጀምሮ ባለው አጠቃላይ የግንባታ ጨረታ ሂደት ዙሪያ በተደረገ ጥናት መነሻነት ከተለያዩ ክፍለከተሞች ከተውጣጡ የዲዛይንና ግንባታ ጽ/ቤት ተወካዮች ጋር  ውይይት አድርጓል፡፡  የውይይቱ አላማ በግንባታ ጨረታ ሂደት ከመነሻው ጀምሮ የሚስተዋሉ የአፈፃፀም ችግሮችን ለመለየት ተደረገውን ጥናት መነሻ በማድረግ እነዚህን ችግሮች ህጎች ላይ መሰረት ያደረገ እና ግልፅነት እንዲሁም ፍትሀዊነት የተረጋገጠበት የጨረታ ስርዓት በኢንዱስትሪው ላይ ለመተግበር ያለመ እንደሆነ ውይይቱን የመሩት የቢሮው ቴክኒካል አማካሪ ኢ/ር አብነት አለነ በመድረኩ ገልፀዋል። ከዚህ ቀደም በመመሪያ አተረጓጎም ልዩነት ሳቢያ ወጥነት በሌለው መልኩ ጨረታዎች ሲዘጋጁና ችግሮች ሲስተዋሉ መቆየታቸው ተጠቅሶ ይህም ለጨረታዎች በተደጋጋሚ መሰረዝ ምክንያት ሆኖ እንደቆየ በመድረኩ የተነሳ ሲሆን የዛሬው ውይይትም ቢሮው በዕቅድ ከያዛቸውና ይህን ችግር ከመሰረቱ በመቅረፍ ግልፅ፣አሳታፊና ወጥነት ያለው የጨረታ ስርዓት ለመዘርጋት ከሚያስችሉ ተከታታይነት ያላቸው ተግባራት ውስጥ አንዱ መሆኑ ተነስቷል።
የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ

#TOP_URGENT #አስቸኳይ_ማስታወቂያ_ለማህበራት የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በተለያዩ ጊዜያት ባከናወናቸው በርካታ የግንባታ ስራዎች ላይ በመሳተፍ የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገባችሁና
+5
#TOP_URGENT #አስቸኳይ_ማስታወቂያ_ለማህበራት የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በተለያዩ ጊዜያት ባከናወናቸው በርካታ የግንባታ ስራዎች ላይ በመሳተፍ የተሻለ አፈፃፀም ያስመዘገባችሁና ስማችሁ የተያያዘ ማሕበራት በቀጣይ በተለያዩ ሳይቶች በሚከናወኑ አስቸኳይ የቤቶች ልማት ፕሮጀክቶች ዕድሳት ስራዎች ላይ ለማሳተፍ በነገው ዕለት ማለትም ዓርብ ጥቅምት 15/2017 ዓ/ም የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት ይካሄዳል። ስለሆነም ስማችሁ የተዘረዘረ ማሕበራት ተወካዮች ከላይ በተጠቀሰው ቀን ከጠዋቱ በ1:00 ሰዓት መገናኛ በሚገኘው የካ ክፍለከተማ አስተዳደር ትልቁ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ ጥብቅ ጥሪ ተላልፏል። የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ጥቅምት 14/2017 ዓ/ም 👉ማሳሰቢያ-በተጠቀሰው ቀን፣ቦታ እና ሰዓት በማይገኝ ማሕበር ላይ ቢሮው ኃላፊነቱን አይወስድም!!!! 💥መረጃው ለሁሉም እንዲደርስ ሼር ያድርጉ 💥ይህን ተከትለው በተከታታይ የሚወጡትን መሰል መረጃዎች በወቅቱ እንዲያገኙ ከታች የተቀመጡትን የቢሮውን #ይፋዊ የማሕበራዊ ሚዲያ ገፆች #መከታተልዎን እርግጠኛ ይሁኑ..... ፌስቡክ https://www.facebook.com/AddisConstruction/ ቴሌግራም https://t.me/AddisCityCon ትዊተር https://twitter.com/AddisCity ዩቲዩብ https://www.youtube.com/channel/UCwuES6TQUZmVlUT8tazLHmg ቲክቶክ https://tiktok.com/@design_and_construction1 ዋትሳፕ https://whatsapp.com/channel/0029Vani9gI0lwgzDJ1eFH1x ነፃ የስልክ መስመር 9426

🏗የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ የሴፍቲ ማቴሪያሎች ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ሌሎች ዕቃዎችን ይፈልጋል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት @con_site 🏗
🏗የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የሴፍቲ ማቴሪያሎች ፣ ኤሌክትሮኒክስ እና ሌሎች ዕቃዎችን ይፈልጋል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ጽ/ቤት @con_site 🏗

🔺የግንባታ ወጪን ለመቀነሰ የሚረዱ አማራጭ ዘዴዎች:-🏗
ለህንፃ ግንባታ የሚያስፈልጉ እንደ ብረት፣ ሲሚንቶ፣ ብሎኬት፣ ጠጠር ያሉ ጥሬ ዕቃዎች ዋጋ እ.ኤ.አ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ ከ1000 ፐርሰንት በበለጠ ዋጋ እየጨመረ የመሄዱ ጉዳይ ከማንም የተሰወረ አይደለም፡፡ ለዚህ መንስኤ በዋነኝነት የሚጠቀሱት የማምረቻ፣ የሠራተኛ ጉልበት፣ የትራንፖርት ዋጋ መጨመር እና ተያያዥነት ያለው የዋጋ ግሽበት ናቸው፡፡ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ ልዩ ባህሪ ደግሞ ጥሬ ዕቃዎችን በመግዛት እና በመደባለቅ፣ ጠንካራ ረጅም ዕድሜ የሚኖረው እና ውብ የሆኑ ህንፃዎችን መገንባት ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት የኮንስትራክሽን ኤክስፐርቶች የጥሬ ዋጋ ንረትን በመቋቋም ወጪን ለመቀነስ ያስችላሉ ብለው በቀዳሚነት ያስቀመጧቸውን አሠራሮች መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፡፡ 🚧 ጠንካራ የዕቅድ ፕላን መዘርጋት እንደ ማንኛውም የንግድ ዘርፍ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ የመጨረሻ ልብ ማትረፍ ነው፡፡ ይህንን ትርፍ ለማግኘት ለግንባታው የሚያስፈልገውን በጀት እና ዝርዝር የግንባታ ሂደቶች የተመለከተ ጠንካር ያለ የዕቅድ ፕላን መቀየር ነው፡፡ ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከሚያስችሉ ጠንካር ያሉ የዕቅድ ፕላኖች ውስጥ ጥሬ ዕቃዎችን ካለው  ነባራዊ ሁኔታ በመመርመር ቀደም ብሎ ማከማቸት በእያንዳንዱ የግንባታ ሂደት የሚያስፈልጉ ግብዕቶችን ቀደም ብሎ ማዘጋጀት ናቸው፡፡ 🚧 መደበኛ የሆነ እና የሚደጋገም ዲዛይን አንድ ህንፃ ከመሬት ተነስቶ እያደገ በሄደ ቁጥር፣ የሚይዛቸው የክፍል ገፅታዎች መደበኛ የሆነ ስፋት እና ገፅታ የተለበሱ እንደሆኑ ማድረግ ዋጋን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ ህንፃው ባደገ ቁጥር የውስጥ ገፅታ ዲዛይን የሚለዋወጥ ከሆነ፣ የጥሬ ቁስ ብክነት ያስከትላል፡፡ ለተለዋጭ ዲዛይን የሚሆን ሌላ ጥሩ ቁስ መግዛትን ይጠይቃል፡፡ እስከ ዘለቄታው ለግንባታ የሚያገለግሉ ቁሶችን ቀደም ብሎ ማከማቸት እንዳይቻል ያደርጋል፡፡ ለግንባታ የሚያስፈልጉ መሣሪያዎች በየጊዜው እንዲለዋወጡ ያደርጋል፡፡ የሥራ ፍጥነት እና ሂደትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ጋሬጣ ይፈጥራል፡፡ 🚧 አማራጭ ቁሶችን መጠቀም በህንፃ ግንባታ ህንፃው ለወደፊት የሚሰጠውን አገልግሎት ከግምት በማስገባት ረሳይክልድ የሆኑ ብረቶችን ከጂፕሰም እና ከጣውላ የሚዘጋጀ የውስጥ ማከፋፈያ ግርግዳዎችን መጠቀም፣ ተገጣማሚ ብሎኬቶች እና ግርግዳዎችን መጠቀም የህንፃው የግንባታ ዋጋ እንዲቀነስ ያደርጋሉ:: 🚧 የግንባታ ባለሙያዎች ወጪን መቀነስ የግንባታ ሂደትን በጊዜ ሰሌዳ ሸንሽኖ አስፈላጊውን ቁስ ቀደም ብሎ በማሟላት፣ ለግንባታው የሚያስፈልገውን ባለሙያ በጊዜው በመቅጠር ግንባታ የሚያስፈልግ የጉልበት (የሙያ) ክፍያ ወጪን በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ ይረዳል:: 🚧 ጊዜ እና ገንዘብን መቆጠብ ለግንባታ የሚያስፈልጉ እና ሥራን የሚያቀላጥፉ እንደ ሎደር፣ ኤክስካቫተር፣ ፓሌት (የብረት ምንጣፍ) የኮንክሪት ምንጣፍ ተሻካሚ፣ ተገጣጣሚ ብረቶችን፣ ግንባታው ሳይቋረጥ በሚፈለግበት ጊዜ ወዲያው የሚቀርቡበትን ቀደም ያለ ዝግጅት ማድረግ ለግንባታ የሚያስፈልግ ጊዜ በመቆጠብ፣ በፍጥነት ወደሚፈለገው ትርፋማ ጉዞ ለማምራት በተዛማጅነትም ወጪን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ ብርሃን የሚያስገቡ መስታወቶችን እና የፀሀይ ብርሃንን ወደ ኤሌክትሪክ የሚለውጡ ግርግዳዎችን ማካተት፣ ህንፃው ከተጠናቀቀ በኃላ ዘላቂ የኃይል ፍጆታ (ገንዘብ) እንዲቆጠብ ያደርጋል፡

+2
የኮንስትራክሽን_ስራዎች_የጋራ_ማህበር_መመሪያ.pdf8.44 MB

የውጭ አገር ለኮንስትራክሽን ባለሞያዎች🏗- በሀገራችን በኮንስትራክሽን ዘርፍ ለመሰማራት የሚያስችላቸውን ፍቃድ እንዲያገኙ የድጋፍ ደብዳቤ የሚያገኙበትን ሁኔታ ለመወሰን በወጣው መመሪያ ቁጥር 29/2012 ዓ.ም መሰረት አገልግሎቱን በግንባር ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ የድጋፍ ደብዳቤ አሰጣጥ አገልግሎት ቀልጣፋና የተገልጋዩን ፍላጎት የሚያረካ ይሆን ዘንድ በቴክኖሎጂ እንዲታገዝ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ ቆይቷል ፡፡ በዚሁ መሰረት የአገልግሎት አሰጣጡን ከጥቅምት 1 ቀን2017ዓ.ም ጀምሮ ባሉጉዳዩች ካሉበት ቦታ ሆነው በ online አገልግሎት የሚያገኙበት  ሁኔታ ስለተመቻቸ አገልግሎቱን የምትፈልጉ በ www.Eservice.gov.et ማግኝት የምትችል መሆኑን እንገልፃለን ። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +25115541285 | +25115541254 ደውለው መረጃ ማግኘት ይቻላል የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር @con_site 🏗