uk
Feedback
Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Construction Solution- @Consite Media[የግንባታ ሥራ ተቋራጮች]🏗

Відкрити в Telegram

Addis Ababa, Ethiopia Con-Site is a Comprehensive Construction Filed Works and Materials Reference Catalogue for Architects, Engineers, Consultants and Customer service. t.me/ConsitesolutionBot ☜|]Chat us! Buy ads: https://telega.io/c/consite

Показати більше
3 586
Підписники
-324 години
-227 днів
-930 днів
Архів дописів
🧱New Point Bricks factory 新点砖厂🧱Our Bricks:- Tough,Don't decay, warp or twist, resistance to water & harsh soils, don't fade
🧱New Point Bricks factory 新点砖厂🧱Our Bricks:- Tough,Don't decay, warp or twist, resistance to water & harsh soils, don't fade....🧱ጥራት ያላቸውን እና ለተለያዩ ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ የቀይ ሸክላ ጡቦችን እናመርታለን። 🧱 ለሙሉ የቤት ግንባታ፣ 🧱ለባንክ ቤት ካዝና፣ 🧱 ለግቢ አጥር ማጠሪያ፣ 🧱 ለመንገድ ዳር ጠርዞች፣ 🧱  ለሆቴሎች፣ሬስቶራንት፣እና ካፌዎች ማሳመሪያ ፣ 🧱 ለx-ray ክፍሎች፣ 🧱 ለፍሳሽ ማንዋሎች፣ 🧱 ለኪችን ሲንክ ማስቀመጫ ፣ 🧱 ለሻወር ገንዳ ማሰቀመጫ፣ 🧱 የPBC ፍሳሽ ማስወገጃ ለመሸፈን፣ 🧱 ለአበባ መትከያ 🧱 ለብረት ማቅለጫ ፈርኒስ፣ 🧱 ለፒዛ ኦቭን፣ 🧱 ለምድጃ፣ 🧱 ለቆሻሻ ማቃጠያ፣    NEW POINT BRICK FACTORY *We produced best quality clay bricks for various construction purposes. 🧱 For building construction, 🧱 For bank vaults, 🧱 Fence for the yard, 🧱 For road edges, 🧱 For Hotels,Restaurants,and Cafes decoration, 🧱 For x-ray rooms, 🧱 For manuals, 🧱 For kitchen, 🧱 For shower tray 🧱 To cover PBC drains, 🧱 For garden, 🧱 Furnace For steel factory, 🧱 For pizza oven, 🧱 For waste incinerator, ....."Build together the future" join our telegram channel For order 0912854327&0902378888

የዋጋ ጭማሬ (Price Increament) ስሌት
በተለይ በዚህ ዘመን የግንባታ ግብአቶች ዋጋ ከዕለት-ዕለት ተቀያያሪና ተገማች ያልሆነ ሆኗል። በኮንስትራክሽን ሥራዎች ደግሞ እንደ ውላቸው የጊዜ ገደብ (Period to adjust price as per the contract) የዋጋ ማስተካከያ ጥያቄ የሚበዛበት ዘመን ሆኖ ተስተውሏል። በመሆኑም የዋጋ ማስተካከያ (price adjustment) ለማድረግ የራሱ የሆነ ስሌት ያለው ሲሆን ምን ያህል እንደጨመረ (እንደቀነሰ) ለማስላት የሚከከተለውን መንገድ እንጠቀማለን። ~ የግንባታ ግበቶች ዋጋ ጭማሬ (ቅናሽ) መጠን ~ የሠራተኛ ዋጋ (ባለሙያ፣ የጉልበት አበል) ~ የደመወዝተኛ ክፍያ (መሐንዲስ፣ አስተዳደር) ~ ሥራ ተጀምሮ የታየ አስቸጋሪ ሁኔታ ~ የማሽነሪና መሳሪያዎች ኪራይ ዋጋ ~ ሀገሪቱ ያወጣቻቸው ተጽእኖ ፈጣሪ አዋጆች ~ የብር የምንዛሬ አቅም ~ ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ስሌት ማስተካከያ = የቀድሞው ዋጋ*[1+(ጭማሬ/100)] የቴግራም ቻናላችን: t.me/DSDConstruction ሊጽፉልን ካሰቡ t.me/DSDCon ቲክቶክ: www.tiktok.com/@dsdconstruction

🏷ለባከነ የግንባታ ጊዜ ''የጊዜ የጉዳት መቀጫ'' /Liquidated damage/ ➡️በኮንስትራክሽን ውል ላይ የውሉ የግንባታ ስራ ተብሎ የተቀመጠውን በዲዛይኑ እና ዝርዝር ስፔስፊኬሽኑ መሰረት በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሰርቶ ማጠናቀቅ የተቋራጩ ሀላፊነት ነው፡፡              ➡️ተቋራጩ የውሉን የግናባታ ስራ በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በወቅቱ ሰርቶ ያላጠናቀቀ እንደሆነ ከውሉ ማጠናቀቂያ ጊዜ/completion date/ በኋላ ግንባታው እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ ለእያንዳንዱ ቀን ተቋራጩ የግንባታ መዘግየት ምክንያት ለአሰሪው የጊዜ የጉዳት መቀጫ/Liquidated damage/ የመክፈል ሀላፊነት ይኖርበታል፡፡ ⏭በውሉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ሲባል ምን ማለት ነው? ▶️አንዳንድ አሰሪዎች/client/ በግንዛቤ እጥረት በውሉ ላይ የተቀመጠው ተቋራጩና አሰሪው ለግናባታው ማጠናቀቂያ የተስማሙበትን የቀን ብዛት/የጊዜ እርዝማኔ/ መቆጠር የሚጀምረው ውሉ በግራ ቀኙ ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ እንደሆነ ይረዱታል፡፡ይሄ አረዳድ ስህተት ነው፡፡ ⏹በኮንስትራክሽን ውል ስለ ጊዜ አቆጣጠር በተለይ ⏺የግንባታ ውል የተደረገበት ቀን/contract signing date/ ፣ ⏺ሞቢላይዜሽን ፔሬድ/mobilization period/፣ ⏺የሳይት መረከቢያ ቀን/site handover/፣ ⏺የስራ መጀመሪያ ቀን/commencement date/ እና ⏺የስራ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ የሚሉትን መረዳት የግንባታ የጊዜ የጉዳት መቀጫ/Liquidated damage/ የሚለውን በአግባቡ ለማወቅ ይጠቅማል፡፡ ⏹በመሰረቱ በውሉ የተቀመጠው የስራ ማከናወኛ የጊዜ ገደብ መቆጠር የሚጀምረው ተቋራጩ የግናባታውን ሳይት ከአሰሪው ከተረከበ በኋላ ነው፡፡ይሄውም ከሳይት ርክክብ በኋላ የስራ መጀመሪያ ቀን /commencement date/ በመሀንዲሱ የሚወሰን እና ለተቋራጩ የሚገለጽለት ይሆናል፡፡ ⏹እንግዲህ  በመሀንዲሱ ከሚወሰነው የስራ መጀመሪያ ቀን ጀምሮ በውሉ ላይ የተቀመጠው ቀን ይቆጠርና የስራ ማጠናቀቂያ ቀን/completion date/ መቼ እንደሆነ ለማወቅ ያስችላል ማለት ነው፡፡ ➡️እዚህ ላይ ሊታወቅ የሚገባው ነገር በኮንስትራክሽን ውሉ ላይ የተወሰነውን የስራ ክፍል ከውሉ የማጠናቀቂያ ጊዜ አስቀድሞ ለማጠናቀቅ ውል ሊደረግ የሚችልበት እድልም አለ፡፡/Partial completion/ ማለት ነው፡፡የቀን አቆጣጠሩ ከላይ እንደተብራራው የሚሰላ ይሆናል፡፡ *⃣ስለሆነም የግንባታ መዘግየት ቅጣት የሚለው ጉዳይ የሚመጣው ተቋራጩ የውሉን የግንባታ ስራ በውሉ ስራ የማጠናቀቂያ ጊዜ /completion date/ ሳያጠናቅቅ የቀረ እንደሆነ ነው፡፡የገንዘብ ቅጣቱ የሚጣለው በተቋራጩ ላይ ነው፡፡ *⃣ተቋራጩ ግንባታውን ላዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን በውሉ የተቀመጠውን የጊዜ ኪሳራ መቀጫየሚከፍል ይሆናል፡፡በነገራችን ላይ እየተቀጡ መስራት ለተቋራጩ መብትም ጭምር ነው፡፡ይህ ማለት አሰሪው የውሉ ማጠናቀቂያ ጊዜ ስላለቀ ውል አቋርጣለሁ ማለት አይችልም፡፡በውሉ ላይ የተቀመጠው የመዘግየት ቅጣት ጣሪያ መጠን ከሞላ በኋላ ግን አሰሪው ውል ማቋረጥ ይችላል፡፡ውል ከተቋረጠ በኋላ የመዘግየት ቅጣት የሚባል ነገርም የለም፡፡ *⃣*⃣ሌላው ተቋራጩ ወደ መዘግየት ቅጣት እንዲገባ ከመደረጉ አስቀድሞ በአግባቡ መረጋገጥ ያለበት ነገር መሀንዲሱ ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ/Extension of Time / ፈቅዷል ወይስ አልፈቀደም የሚለው ነጥብ ነው፡፡ምክንያቱም ለተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ ተፈቅዶለት ከሆነ የግንባታ ማጠናቀቂያ ጊዜውም አብሮ ስለሚራዘምና ቀኑ ስለሚቀየር ነው፡፡ ▶️የሀገራችንን የህግ ማእቀፍ በዚህ ረገድ ምን ይላል? የሚለውን ለመመለስ በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1887 እስከ 1895 ድረስ የተደነገጉትን መዳሰስ ይጠይቃል፡፡ *⃣በፍትሀብሄር ህግ አንቀጽ 1889 ላይ ተዋዋዮች በውላቸው ምናልባት አንደኛው ወገን እንደውሉ ግዴታውን ያልፈጸመ እንደሆነ ወይም አጓድሎ የፈጸመ እንደሆነ ወይም አዘግይቶ የፈጸመ እንደሆነ የሚከፍለውን የመቀጮ መጠን አስቀድመው በውላቸው ለመወሰን እንደሚችሉ በሚፈቅድ መልኩ ተደንግጓል፡፡ *⃣እዚህ ላይ የውል ግዴታን አዘግይቶ መፈጸም ስለሚያስከትለው ቅጣት የሚዋዋሉት በተለይ የግንባታ ጊዜ የጉዳት መቀጫ/liquidated damage/ የሚመለከት ይሆናል፡፡ ▶️የመዘግየት ቅጣት ስምምነት ባለ ጊዜ አሰሪው የውሉ ስራ እንዲፈጸምና የቅጣት ገንዘቡንም ለመቀበል መብት እንደሚኖረው የፍ/ህ/ቁ 1890(2) ይደነግጋል፡፡ *⃣እንደዚሁም አሰሪው ኪሳራ ባይደርስበት እንኳ የመዘግየት ቅጣት ገንዘቡ ሊከፈለው እንደሚገባ የፍ/ህ/ቁ 1892(1) ይደነግጋል፡፡እንግዲህ ተቋራጩ ግንባታውን በወቅቱ ያላጠናቀቀው አሰሪውን ሆነ ብሎ ለመጉዳት አስቦ ጉልህ በሆነ ቸልተኝነት ወይም በከባድ ጥፋት መሆኑ የተረጋገጠ እንደሆነ አሰሪው በውሉ ከተቀመጠው የቅጣት ገንዘብ በላይ በደረሰበት ትክክለኛ ጉዳት መጠን ልክ ከተቋራጩ ላይ ኪሳራ ለመጠየቅ እንደሚችል የፍ/ህ/ቁ 1892(2) ይደነግጋል፡፡ ▶️ሌላው የመዘግየት ቅጣት መጠን በዳኞች ሊቀነስ የሚችልበት እድል ስለመኖሩ የፍ/ህ/ቁ 1893 ይደነግጋል፡፡ይሄውም ተቋራጩ ግዴታውን በከፊል የፈጸመ ሆኖ ሲገኝ ነው፡፡ *⃣ይህ ማለት ተቋራጩ ባከናወነው ስራ ሁሉ ቅጣት የሚጣልበት አይሆንም ማለት ነው፡፡ ▶️በዚህ ረገድ በሲቪል ግንባታ ስራዎች ቋሚ የውል መተዳደሪያ አንቀጽ 47(1) ላይ ተቋራጩ ስራውን በውሉ የማጠናቀቂያ ጊዜ ካላጠናቀቀ ለዘገየበት ለእያንዳንዱ ቀን የውሉን ዋጋ 1/1000 እንደሚከፍል እና ይሄውም አጠቃላይ መጠኑ ከውሉ ዋጋ ከ(10-20%)መብለጥ እንደማይችል ይደነግጋል፡፡ *⃣ሆኖም ግን በከፊል ለተከናወነው ስራ መሀንዲሱ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት በሰጠ ጊዜ የቅጣቱ መጠን የሚሰላው ባልተከናወነው ስራ መጠን ዋጋ ላይ በመመስረት ይሆናል ማለት ነው፡፡ ▶️በመጨረሻም የመዘግየት ቅጣት በኛ ሀገር ከላይ እንዳየነው እንደቅጣት የሚቆጠርና በህጉ ቅጣቱ እውቅና የሚሰጠው ሲሆን በኮመን ሎው የህግ ስርአት ግን ቅጣት አይደለም፡፡ *⃣በኮመን ሎው የጊዜ የጉዳት መቀጫ በአሰሪው ላይ ከደረሰው ጉዳት ጋር እኩል ሆኖ መመዛዘን የሚኖርበት ሲሆን የቅጣት አይነት ተመሳሳይ ባህሪ ካለው ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡ https://t.me/ptconstruction

በአዲስ አበባ ሁለተኛው ምዕራፍ የ ኮሪደር ልማት እየተከናዎኑ ያሉ ስራዎች ::
በአዲስ አበባ ሁለተኛው ምዕራፍ የ ኮሪደር ልማት እየተከናዎኑ ያሉ ስራዎች ::

ማስታወቂያ:- NAYHAf Construction Metal Trading- አቅራቢ🏗 ጥራትና ታማኝነትን የተላበሰ አገልግሎት" ከደንበኞች አብዛኛሆቻችሁ ታውቁታላችሁ መገኛ አድራሻው ቦታ:- 📍- ተክለሃይ
+3
ማስታወቂያ:-
NAYHAf Construction Metal Trading- አቅራቢ🏗 ጥራትና ታማኝነትን የተላበሰ አገልግሎት" ከደንበኞች አብዛኛሆቻችሁ ታውቁታላችሁ
መገኛ አድራሻው ቦታ:-
📍- ተክለሃይማኖት በርበሬ በረንዳ
ስልክ ቁጥር:-
🔺📞+251- 944454610 🔺📞+251- 952730999 #LTZ 28 #LTZ 38 #LTZ 48 #CHS ከ ባለ 12mm ጀምሮ .... #RHS #I BEAM #U CHANNEL #H BEAM #Mesh Wire #የ ኣጥር ሽቦ #Galvanized Pipe #Angle #Aluminium Sheet #D ብረት#8 ቁጥር #ፌርሞችን በጥራትና በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ! ስትፈልጉ በቀጥታ ይደውሉ.. .

👉በአደይ አበባ ፋብሪካ የቀን ሰራተኛ ላይ ግድግዳ ተንዶበት ህይወቱ አለፈ 🏷ዛሬ ዓርብ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋድ 4ሰአት ከ25 ላይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አደይ አ
👉በአደይ አበባ ፋብሪካ የቀን ሰራተኛ ላይ ግድግዳ ተንዶበት ህይወቱ አለፈ 🏷ዛሬ ዓርብ ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከረፋድ 4ሰአት ከ25 ላይ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አደይ አበባ ግቢ ዉስጥ በደረሰ የስራ ላይ አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል። ህይወቱ ያለፈዉ ግለሰብ ዕድሜዉ 32 ዓመት የተገመተ የቀን ሰራተኛ ሲሆን በፋብሪካዉ ምድር ቤት ዉስጥ የነበረ የቀድሞ የዉሀ ገንዳን ግድግዳ በማፍረስ ላይ እያለ ግድግዳዉ ተንዶበት በደሰበት ከፍተኛ ጉዳት ህይወቱ ማለፉን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና የፖሊስ አባላት እንዲሁም የፋብሪካዉ ሰራተኞች የግለሰቡን አስከሬን ማዉጣት ችለዋል። 💫በትላንትናዉ ዕለት በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ፊጋ መብራት ሀይል እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በህንጻ ግንባታ ስራ ላይ የነበረ የ27 ዓመት ወጣት ህይወቱ ማለፉ ብስራት መዘገቡ ይታወሳል። በማናቸዉም የህንጻና መሰል ግንባታዎች መሰል አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊዉን የደህንነት መርሆዎችን መከተል የሚገባ ሲሆን ለዚሁም ከባለሞያዎች ባሻገር አሰሪዎች ከፍተኛ ኃላፊነት አለባቸዉም ተብሏል። Via ዳጉ ጆርናል @etconp

✅አስር[10] ጊዜ x📏 ለካ= አንድ ጊዜ ቁረጥ- ይላል!🤔🤔🤔 ------------------------------------------------ በስራ ላይ~ ብሩህ ቀን ተመኘን!🤚 ቻናሉን አጋሩ!
አስር[10] ጊዜ x📏 ለካ= አንድ ጊዜ ቁረጥ- ይላል!🤔🤔🤔 ------------------------------------------------ በስራ ላይ~ ብሩህ ቀን ተመኘን!🤚
ቻናሉን አጋሩ! Share ይደረግ!
➡️@Con_site🏗💠

የአርማታ ብረታ ብረት አቅራቢ🏗🇪🇹 Ethio-Base Business Group💠 • 18-24 • Grade75 • የሀገር ውስጥ እና የቱርክ    የአርማታ ብረታ ብረት • በጅምላና በችርቻሮ • በተመጣጣኝ ዋጋ እናቀርባለን
📍አድራሻ፦ ከጋዜቦ አደባባይ ወደ ቡልጋሪያ በሚወስደው ድልድይ ጫፍ ላይ ያገኙናል
Ethio-Base Business Group ☎️+251911731977 📞+251972670787

Share waterworks-and-sewerage-713-eng.pdf

✨️✨️አዲስ ነገር ለኮንትራክተሮች እና ህንጻ ገንቢውች የተለያዮ ሴራሚኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ✨️✨️ ከግላንስ ሴራሚክ ና ግራናይት 🎯 ለህንጻዎ ወለል ና ግድግዳ ተጨማሪ ውበትን የሚያላብሱ 🎯 ከተለያ
+9
✨️✨️አዲስ ነገር ለኮንትራክተሮች እና ህንጻ ገንቢውች የተለያዮ ሴራሚኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ✨️✨️ ከግላንስ ሴራሚክ ና ግራናይት 🎯 ለህንጻዎ ወለል ና ግድግዳ ተጨማሪ ውበትን የሚያላብሱ 🎯 ከተለያዮ የሳይዝ ና ከለር አማራጭ ጋር 120×60 60×60 30x60 30×30 🎯 የውጭ ሀገር ሴራሚኮችን በተመጣጣኝ ዋጋ ይዘንለወት ቀረበናል ⚡️ በተጨማሪም የሀገር ዉስጥ ሴራሚክ አስገብተናል ይምጡና ይጎብኙን 📍 አድራሻ ፡ ከፊጋ መብራት ወደ ማርያም በሚወስደው መንገድ በእርሱ ሱፐር ማርኬት ፊት ለፊት/ ዲ ኤች ገዳ አጠገብ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮቻችን 🤳 ይደውሉልን ☎️ 0911676967 ☎️ 0970111177 𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐞𝐫𝐚𝐦: https://t.me/Glancegraniteandceramic 𝐓𝐢𝐤𝐓𝐨𝐤: @glanceceramicgranite

በጎረቤት መሬት ውስጥ ወሰን አልፎ ግንባታ ስለመፈጸም -- (የሕግ አግባብ)
ከግንባታ ሥራ ጋር ተያይዞ በሀገራችን ፍርድ ቤቶች ከቀረቡ ሪፖርቶች መካከል ሰፊውን ቦታ የያዘው «ጎረቤት ወሰን አልፎ አጥር ማጠር፣ እጽዋት መትከል እና በመሬት ውስጥ ወይም በአየር ላይ ግንባታ መፈጸም» በሚሉ ጉዳዮች የቀረቡ አቤቱታዎች ናቸው። በመሆኑም አንድ ሰው የይዞታ ማረጋገጫ ከተሰጠበት የይዞታ ድንበር መስመሮች ውጪ በመሬት ውስጥም ይሁን ከመሬት በላይ (በአየር ላይ አንጠልጥሎ) ግንባታ መፈጸም አይችልም። ግንባታ ይቅርና ባለይዞታው ካልፈቀደ በቀር እና በህግ ትእዛዝ ካልተሰጠ በቀር ማንም ሰው በሌላ ይዞታ ላይ አልፎ መግባት (መራመድ፣ መቆም) አይችልም (ፍ/ብ ሕ/ቁ 1216)። አንድ ጎረቤት በራሱ ይዞታ ላይ ዛፍ ቢተክልና ዛፉ እያደገ ሲሄድ የዛፉ ሥሮች በመሬት ውስጥ ወደሌላኛው ባለይዞታ መሬት ውስጥ ቢገቡ አልፈው የገቡትን የዛፉን ሥሮች የመቁረጥ ግዴታ አለበት፣ የዛፉ ቅርንጫፎችም በአየር ላይ በሰው ይዞታ ላይ ከገቡ ወይም ቅርንጫፎቹ ወደሌላ ጎረቤት ይዞታ ውስጥ ከተስፋፉ እነዚያን ቅርንጫፎች የመቁረጥ ግዴታ አለበት (ፍ/ብ ሕ/ቁ 1212) በመሆኑም በፍትሐብሔር ህግ ላይ በግልጽ እንደተቀመጠው አንድ ሰው በጎረቤቱ ይዞታ ላይ ግንባታ የፈጸመ ከሆነ (በመሬት ውስጥ መሰረት ግንባታ Foundation፣ በመሬት ላይ ወለል ወይም በአየር ላይ ተንጠልጣይ ውቅር Cantliver Structure ሊሆን ይችላል) ይዞታ የተጣሰበት አካል የባለቤትነት አቤቱታ በፍትሐ ብሔር /ሕ/ቁ 1206 መሰረት በማዘጋጀት ስልጣን ላለው ፍ/ቤት የማመልከት መብት አለው፡፡ አቤቱታው ይዞታው በሚገኝበት አካባቢ ባለ ፍርድ ቤት ቢሆን የተመረጠ ሲሆን በይዘት ደረጃ የይዞታው ባለቤትነት ማረጋገጫ ሰነድ የተያያዘበት፣ ግንባታ የፈጸመው አካል ምን ያህል ካሬሜትር አልፎ እንደገባ፣ እና ያለአግባብ የተፈጸመውን የግንባታ አይነት በመጥቀስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። የአቤቱታው ፍሬ ነገር (ፍላጎት ደግሞ) ግንባታ የፈጸመው አካል አልፎ የገነባውን የግንባታ አይነት በራሱ ወጪ አፍርሶ ይዞታውን ቀድሞ በነበረበት ይዘት እንዲያስረክብ ውሳኔ እንዲወሰን የሚጠይቅ መሆን አለበት።

ፌሮ ብረት Vs የአርማታ [Reinforcement bar Vs Concrete mix]
የኮንክሬት መዋቅር (Concrete Skeletons) የተለያዩ የግንባታ ግብአቶችን የሚጠቀሙ ቢሆንም በአብዛኛው የተለመደው የፌሮ ብረት እና የአርማታ ሙሌት ያለው መዋቅር ነው። ይህ አይነቱ ስትራክቸር «Reinforced Concrete Structure ወይም ባለፌሮብረት የአርማታ ውቅር» ተብሎ ይጠራል። በመሆኑም እነዚህ ሁለት ዋና ዋና የግንባታ ግብአቶች (ፌሮ ብረት እና አርማታ) ለውቅሩ የየራሳቸው የሆነ አስፈላጊ ጥቅም አላቸው። ከዚህ አንጻር፦ የፌሮ ብረት (Reinforcement bar) በባህርዩ ተለጣጭ አይነት ባህርይ ስላለው በኮንክሬት ውቅሩ ላይ የሚተገበረውን ጫና (load) በቀላሉ እንዳይፈረካከስ በማድረግ እና ባለው ወጥነት የተነሳቭየተወሰነ የመለጠጥ ነጻነትን (Ductile Property) በማበልጸግ የመለጠጥ ጥንካሬን (Tensile Strength) እንዲኖረው ያደርጋል። በዚህ አግባብ የአርማታ ውቅሩ Tension ላይ ልዩ የመቻል አቅም እንዲኖረው የሚያደርግ ግብአት ነው፡ አርማታ (Concrete Mix) በፌሮ ብረት መዋቅሩ ውስጥ እና ዙሪያ የሚሞላው አርማታ ደግሞ የኮንክሬት መዋቅሩ (Concrete Structure) የመኮማተር አቅም (Compressive Strength) እንዲኖረው የሚያደርግ ነው። በመሆኑም አርማታ በመዋቅሩ ላይ የሚተገበረው ጫና በአንጻራዊ ስፋት ላይ አርፎ ማዕከላዊ የፍሰት ሥርዓትን (Centerline load transfer system) ተከትሎ እንዲፈስ የሚያስችል የመድረቅ ወይም የመኮማተር ሂደትን የሚይዝ ነው። ማጠቃለያ አርማታ ጠንካራ የማይለጠጥ ጸባይ ስላለው ፌሮ ካልገባበት ጫና ሲበዛበት የመሰበር ወይም የመቀንጠስ አደጋ ይገጥመዋል። ፌሮ ብረትም ብቻውን ቢሆን የመለጠጥ ጸባይ ስላለው አርማታ ባይኖርበት ተጣጥፎ ይተኛል ወይም ጎብጦ ይቀራል እንጂ ራሱን ችሎ ደረቅ መዋቅር የመሆን አቅሙን አያስቀጥልም። በመሆኑም አርማታ ብቻውን ቢሆን ወይም አርማታው በዝቶ ፌሮ ብረት ካነሰ የመለጠጥ አስፈላጊ ባህርዩን ስለሚያጣ «Tensile Failure» ይገጥማል። በተቃራኒው ፌሮ ብቻውን ከሆነ ወይም ፌሮ በዝቶ አርማታ ካነሰ "Compressive Failure" ይከሰታል ማለት ነው። የቴግራም ቻናላችን: t.me/DSDConstruction ሊጽፉልን ካሰቡ t.me/DSDCon ቲክቶክ: www.tiktok.com/@dsdconstruction

ስለመሬት፣ ስለግንባታ እና ስለውሎች የሚደነግገውን ክፍል ቢያነቡት እንመክራለን!

አስቸኳይ የስራ ማስታወቂያ 🚧ቢውልደርስአፕ ኮንስትራክሽን ማቴሪያል ማምረቻ ኃላ/የተ/የግ/ማህበር 🏷በኢንዱስትሪያል ማሽን ኦፐሬተር መቅጠር ይፈልጋል የት/ደረጃ በዲፕሎማ ማሽን ኦፐሬቶር ወይም በአውቶ መካኒክ የተመረቀ የስራ ልምድ በኢንዱስትሪ ማሽን ኦፕሬተርነት ወይም በተመሳሳይ የስራ ዘርፍ  2 ዓመት ያገለገለ የስራ ቦታ፡ ዱከም ስ.ቁ 0930105927 ወይም @Ch1bn ፃፉልን

የተለያዩ አይነት ላፕቶፕ ኮምፒተሮች፣ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች እና ታብሌት ግዥ ጨረታ
የተለያዩ አይነት ላፕቶፕ ኮምፒተሮች፣ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች እና ታብሌት ግዥ ጨረታ

በስራ ላይ~ ቀናችሁ ያማር ይሁን!🤚
ቻናሉን አጋሩ!➡️Share ይደረግ!
➡️@Con_site🏗💠 🤝🤝🤝🤝