Poems❤️
Ye fkr❤️ Ye nafkot 😔 Ye tzta 💔 Getmochen tagengalacehu
БільшеКраїна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
189
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів
- Підписники
- Перегляди допису
- ER - коефіцієнт залучення
Триває завантаження даних...
Приріст підписників
Триває завантаження даних...
ምን ይጠቅማል
ከንፋሱ ቀደምክ
ከብርሀን ፈጠንክ
ተጣደፍክ ለመሄድ
ሳትፈላ ለመብረድ
ብለህ ቀደም ቀደም
እኔ ነኝ ያንቺ አለም
ካፋፉ ላይ ቆመህ
ቸኮለ እኮ ልብህ
ጊዜ እንዳገናኘን
ጊዜ ነው ሚለየን
ብለህ ነግረኸኛል
ታድያ...ምን ያሸብረኛል
የዝምታ ጥጉ
የፍቅር መስረጉ
ከቃል ካልዘለለ
ልብህ ካልከጀለ
ወሬህ ወድያ ማዶ
ተግባርህ በረዶ
ታድያ ምን ይጠቅማል
እማ አባ መባባል
ሆነን እስካልኖርነው
ውሸት ነው በል ተወው
✍️ ሪታ
ነዒ
16ቱን ቀን ቆሜ ልለምንሽ
እመቤቴ የልቤ ነሽ
ልጥራሽ ብዬ በርከክ አንገቴን ቀልብሼ
በሀጥያት አረንቋ ከሰው ልጅ አንሼ
እልሻለሁ ነዒ
ስጋዬን አንፅቼ ልብሴን አጣጥቤ ብቆምም ከደጅሽ
በየሰዓታቱ ሰላም ለኪ ብልሽ
ነፍሴ ግን አድፋ ወድቃለች ከደጅሽ
ነዒ ድንግልዬ
እስኪ ወዬ በይኝ
ልጄ ብለሽ ጥሪኝ
በእንተ ማርያም ብዬ ልለምን ልጅሽን
ከነ ሀፍረቴ ልርገጠው ደጅሽን
ከገረገራው ስር ቁጭ ብዬ ላልቅስ
በድጋሚ ውለጅኝ ህይወቴንም ላድስ
🙏🙏🙏
አስተማሪ አጭር ታሪክ .!
አንድ ቤተሰብ ውስጥ አባት ከሞተ በኋላ የሚመገቡት እስኪያሳስባቸው ድረስ ይቸገራሉ ። አንድ ጌጣጌጥ መሸጫ ሱቅ ያለው ዘመድ አላቸው እና እናትየው ለልጇ ያላትን ለረጅም ጊዜ የተቀመጠ የአንገት እና የጣት ዳይመንድ ጌጥ ሰጥታው እዛ ሱቅ ሄዶ እንዲሸጠው ትሰጠዋለች፡፡
ልጁ የተባለው የዘመድ ጌጣ ጌጥ ሱቅ ሄዶ እናቱ እንደላከችው አስረድቶ እንዲገዛው ይጠይቃል፡፡ ሰውየውም ከመረመረው በኋላ "አሁን ገበያው ወድቋል ትንሽ ግዜ ጠብቀን በጥሩ ዋጋ
እንሸጠዋለን፡፡" ብሎ ይመልስለትና የተወሰነ ገንዘብ ከሰጠው በኋላ ለልጁም እስከዛው በየጊዜው እየመጣ እዛው ሱቅ ስራ እንዲሰራ ያደርጋል ።
ልጁ በየግዜው እየሄደ የጌጣጌጥአሰራር ጥበብ ተካነ ፡፡ የገበያም እውቀት አካበተ በስራውም ታዋቂም ለመሆን ቻለ ፡፡
ይሄኔ ባለሱቁ "የሆነ ግዜ ልትሸጠው አምጠተኸው የነበረውን ጌጥ አሁን አምጣው አሁን ገበያው ጣራ ነክቷል እና ታተርፋላችሁ ፡፡ ብሎ ይልከዋል ፡፡ ልጁ እንደተባለው እቤት ሄዶ ጌጣጌጡን በአይኑ በማየት ብቻ አርቴፊሻል ሆኖ ያገኘዋል፡፡
ወደ ሱቅ ይመለሳል ፡፡ባለቤቱ ይጠይቃል "ዳይመንዱስ ?" ልጁም "አርቴፊሻል ነው ግን እያወክ ያን ጊዜ ለምን አልገርከኝም ?አሁንስ ለምን ላከኝ?ሲል ጠየቀው፡፡ ዘመዱም "ያን ጊዜ ለረጅም ዘመን ዳይመንድ ነው ብላችሁ ያመናችሁትን ነበር ይዘህ የመጣኸው ፡፡ያለምንም እውቀት፤ ባዶህን እና በሙሉ እምነት ብቻ ! በሰዓቱ ባለህበት ሁኔታ ልክ ያልሆነ ነገር ለማስረዳት ይከብዳል፡፡ ምናልባት ላታምኑኝ ትችሉ ነበር ፡፡ምናልባትም ባለመግባባት የሚፈጠሩ የቃላት ልውውጥ አሁን ላይ መጥፎ ስሜት ሊያሳድርብን በቻለ ነበር ።" ብሎ በትህትና መለሰለት፡፡
@ritaspoems
◉ Join us share◉●••
═════❥━━━❥═════
🌾ነገ መልካም ይሆናል !
ከንቱ አንሆንም ነበር !
ከቶ አንቀርም መና!!
ሰው ያየኛል ሳንል፤
ቢዳኘን ህሊና።
---------😏😏😏😏
@ ritaspoems
Оберіть інший тариф
На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.