cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ሀ ረ ጋ ት🎋

መሙላትን የሚያስንቁ ጎደሎ ሀረጎች likely ur Thoughts are hear🍃 TICKTOK :@Samiya.311 Facebook :samiya Tuha ለ ሀሳብ አስተያየት tg@samiya311

Більше
Ефіопія9 267Амхарська8 270Категорія не вказана
Рекламні дописи
382
Підписники
Немає даних24 години
-47 днів
-230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
🥺🥺🥺
Показати все...
Repost from N/a
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Violence languages 🤗
Показати все...
እማ ፡እና ፡የጠዋት ፡ቡና🖤(1).mp36.89 MB
ሁሉ ሁሉ ሲወደኝ ደስ አይልም ፡ ሁሉ ሁሉ እኔን ሲል የሚደብር ነገር አለዉ አ ደስ አይልም ሁሉም በየቀኑ መሀል ሳስፈልገዉ ሳይ ለኔስ መች በቃሁና ነዉ እላለሁ ። ባለፈዉ ለታ  ሁሌ ሁሌ ሰአት ቀኑን የሚያጋራኝ 'እሱ' ሲቀር ብቻየን ቀረሁ ና እዛ የምወደዉ ካፌ ሄጄ ቁጭ ስል ኪል ኪል አልኩኝ (ባዶ እንደሆንኩ) አሁን ከኔ ምን አለ እላለሁ ማለት በመቀራረብ ስም የቀኔን ሁለት ሰአት ቅርጥፍጥፍ እያደረገ ቁጭ አርጎ ያወራኛል እሰማዋለሁ  እህ እህ እላለሁ አወራለሁ እህ እህ ይላል ። ብዙ ብዙ ተጋርተን ይሆናልል ብዙ ተቀብየም ይሆናል ኮ ግን ምን ይሰማኛል እንደበራድ ከሞላ  እኔነት ወደኔ ለሚመጡ ስኒወች ሁሉ ቀድቸ ቀድቸ የጨረስኩ ይመስለኝና ቅድም ስቀመጥ እንደሆንኩት የሆነ ቀን ላይ ኪል ኪል ያልኩ ይመስለኛል ። አንዳንድዴ ምን ይሰማኛል ለምንድን ነዉ ይሄን ያህል በዚ መጠን የሚወዱኝ አለ አ ያስፈራል ይሄ ወጣትነቴ ሲጠነዛ ሁሉ ሁሉ ሲያልፍ አጀብ ሲደበዝዝ ፣ ሲቀዘቅዝ በሆይሆይታ የተንቆጠቆጠዉ እኔነቴ እንከን (ከሰዉ ስህተት ከብረት ዝገት እንደዛ እንደዛ እንዳሉት )የሆነ በእድሜ ብዛት መዛግ ስጀምር ከኔ የሚነጠሉ መዋቦች እንዳሉ ወደኔ የሚያፈጡ እንከኖችም ያይላሉና የዛኔ ስሚመጣዉ  ጉድለት ዛሬን  ጨንቆኝ ሀያ ላይ ሆኜ ስለሸበቶ ዘመኔ እብሰለሰላለሁ ። ማፍጠጥ ስል ማለቴ እንደዛ ብየ ሳስብ አስተናጋጁ ፊቴ ቆሞ ፈገገግ ብሎ ያየኛል ። ደንግጨ ማኪዪቶ ብየዉ ወደ ሀሳቤ ምልስ..... . እዛ ካፌ ቁጭ ስል ለምን እፈልገዋለሁ ?እሱን ከባዶነቴ ጋር ምን ያያይዘዋል በረህማን ⁈ አሁን በዚች ባለ አበባ ቀሚሴ ስር ሾልካ የምትዳብሰኝ ነፋስ እያለች ስለምን ክንዶቹን እናፍቃለሁ? ናፍቆት ራሱ ምንድን ነዉ? (ይሄ አስጠቂ ብሽቅ) እንዲ ሲናፍቀኝ የራበኝ እየመሰለኝ ምግብ አዛለሁ(አንጀቴ ጠብ አይልም )። ማንንን ነበር ምናፍቀዉ ግን እእእእ አወ እንደዛ ለምን ወደደኝ ቆይ ያ ልጅ እያልኩ ነዋ ?ቆይ ለምን ብሎ ልቤን በዛ መጠን ገመተዉ  እኔስ እሺ ብየ እንዴት በዛ መጠን ተገተትኩ ነዉ ጥያቄዉ አ ? ያኛዉስ ለምን ጊዜየን ቀረጠፈ ምናምን ለምንድን ነዉ እንዲ ሚወዱኝ ? የምር ደስ አይልም አ መወደድ ሲመጣ መረሳትም ያስፈራኝ ና እንቀጠቀጣለሁ ብርድ ብርድ ሲለኝ ጋቢየን እስባለሁ ። የሚያጎሉኝ ይመስለኛል በመዉደድ ስም ። በማድነቅ ስም የልጅነት  ዉበቴን ፣ ወዜን በአይናቸዉ የሚያስቀሩት ይመስለኝና በሀሳቤ ጋቢየ ዉስጥ መጥፋት ያምረኛል። ልጁ ማኪያቶየን ሰጥቶኝ ዞር አለ ማለት ምንድን ነዉ ያልገባኝ ልጅ ሆኜ ወይ ጅል ..አላዉቅም ግን ምን አለፈኝ ..? አሁን የሚወዱኝ ብቻ ሳይሆን  የምወዳቸዉ ነገሮች ምን ቀን ድረስ ነዉ ደስ እንዳለኝ የሚቀጥለዉ ዉስጤ ሲቀጣጠል የሚሰማኝን የምወደዉን አሳት መችና በምኔ ነዉ የምቸልሰዉ ?አጣዋለሁ ወይስ እንዲ የሚቀጥሉሉ ብዙዙዙ ነገሮች አሉኝ ...? ኡፍፍፍፍፍ  እንጃ ከካፌዉ ወንበር ተነስቸ ሄድኩ ብዙ ብዙ ማሰብ ባዶ ያደርጋል ቢሉ ማን ያምናል  (ከራስ ስለሚያነታርክ ) ሂሳቤን ከፍየ ወጣሁ እንዳረገ ያርገኝ ያለችዉ ማን ነበረች (ማ ዘፋኝ ?)ዘፈንም የሆነ አመቴ ላይ ይደብረኛል አ ግጥምስ ''  አአአአአአአ ኧረ መንገድሽን ስሞት ሆ መኪና ኮ ነዉ የምነዳዉ ምን ትላለች እቺ እብድ''  የሆነ ጯሂ ድምፅ ...! ©Samiya  T
Показати все...
Repost from Lidocaine
Фото недоступнеДивитись в Telegram
the quiet ones are the most chaotic. ساکت ترین مردم، آشفته ترین ها هستند. @Lidocaine
Показати все...
Repost from N/a
"ምንድን ነበር ህልምሽ?" አለቺኝ ልትጋብዘኝ ቃል የገባችልኝን የናና ሻይ ወደ ጠረፔዛዉ እያቀረበች። "ቆንጆ የ ቢዝነስ ሰዉ መሆን!" ደግሜ ማሰብ አላስፈለገኝም።ፊትለፊቴ የምኞቷን እኔ ካሁኗ እኔ ጋር እያወዳደርኩ ከንፈሬን መጠጥኩ። ሰሙ የ እህቴ ጓደኛ እና የ የሳይኮሎጂ ምሩቅ ናት።ሰበቡን በማልደራደርበት የ ናና ሻይ አርጋ ጠራቺነኝ እንጂ እህትየዉ "እስቲ አንቺ መላ በያት...እኔስ አቃተቺኝ!" ብላት እንደጠራቺኝ ገብቶኛል። "አሁን ምን ይሰማሻል?" አለቺኝ ወንበሯን አስተካክላ ከተቀመጠች በኃላ "የባከነ እድሜ፣ከሁሉም ወደኃላ የመቅረት ድባዜ..." አይምሮዬ ላይ የተከመሩ ቃላቶቼን ማዉጣት አቃተኝ። "የተሰማሽን ሁሉ ተናገሪ...እስትጨርሺ ድረስ እሰማሻለሁ" እንዳነቀኝ የገባዉ አይኗን ሳትነቅል አይዞሽ በሚል አስተያየት ገረመመቺኝ። "ምኑን ላስረዳሽ ሰሙ? አብረዉኝ ቢዝነስ የተማሩ ጓደኞቼ በሙሉ አሁን የሆነ ነገር እየሰሩበት ነዉ።ሀይስኩል 'ዉይ እቺንስ ከየት ነዉ ያበቀሏት!' እምንላት ያቺ ፀባይም መልክም ጣል ያላረገባት ልጅ እንኳን ቆንጆ ባል አግብታ ሁለት እሱን አፍርታለች። ሁሉም ህይወቱ ላይ የሆነ መሰረት ገንብቶ እየለሰነ ነዉ።ያኔ አብረዉኝ ካፌ ሚሰለፉት እንዳለ ተሰልፈዉ ዉጪ ሄደዋል።ቅዳሜ እና እሁድ ፌስቡኬ እና ኢንስታግራሜ አለምን በኔ መስኮት ነዉ ሚቃኘዉ።ሁሉም ትሪፕ ላይ ነዉ።ሁሉም የሀያዎቹን adventure እያሟሟቀ ነዉ።" በረጅሙ ተነፈስኩ።አንድ ቁምነገር ሳልሰራ ሀያዎቼን አጋምሻቸዋለዉ። "በዲግሪሽ ስራ አገኘሽ?" "ለምን አታገቢም?" "ያቺ ጓደኛሽ ምን ሆነች?" "ለምን ማስተርስ አትቀጥዪም?" "እንዴት እስከዛሬ ከ አዲስአበባ ሳትወጪ?" ... ... .. እነዚህ ጥያቄዎች ታክተዉኛል።እነሱን ላለመጋፈጥ ስል ከክፍሌ ሳልወጣ ዉሎ ማንጋት ደክሞኛል።ያኔ የሰለቸኝ ትምህርት እራሱ ናፍቆኛል።የተሰጠኝን አንብቤ በተቀረፀልኝ መንገድ ተጉዤ ስኬት ላይ መቆም የለመደዉ እግሬ ካርታዉ በጠፋበት ዉጥንቅጥ አለም ላይ መጓዝ አቅቶታል። "ለምን የጀመርሽዉን ስራ አቆምሽ?" "ፀሀፊነቱን?" ሳስበዉ ገና ሳቄ መጣ። "የእድሜዬን ሶስት አመት ቡና ለመቅዳት ስላልተማርኩ!እኩል ተምረን ቢሮዋቸዉ ላይ ፀሀፊ ቀጥረዉ የሚሰሩ ሰዎች ፊት ቆሜ' ምንድነዉ ስራሽ ሲሉኝ 'ፀሀፊ ነኝ" ማለት ስለደከመኝ። are you getting what i said ግን?" አልኳት።ስለፈልፍ በተመስጦ እያዳመጠቺኝ መሆኑ ገርሞኝ።በአንገቷ አዎንታዋን መልሳ የቀረኝ ሀሳብ እንዳለ ሁሉ አፈጠጠችብኘኝ። "ዉቅያኖስ ላይ እየዋኘዉ ይመስለኛል...አለ አይደል መድረሻዉዐየማይታወቅ ከንቱ ድካም።" "የምኞቷ የ25 አመት አንቺ ምን ትመስላለች?" አለቺኝ ከረጅም ዝምታ በኃላ "ዲኗ ላይ ጠንካራ፣ የራሷን ቢዝነስ የምትመራ፣ቆንጆ ኦፊስ እና ፀሀፊ ያላት፣በ የሀገሩ እየዞረች ድንቅ ተፈጥሮን የምታደንቅ ፣ ቆንጆ እና ወንዳወንድ ባል እና ደሞ አንድ ድንቡሽቡሽ ልጅ ያላት.." "እያወራን ያለነዉ ስለ 25 ነዋ?" አለቺኝ ፈገግ እያለች።"ሀያዎቹ ላንቺ ምን አይነት እድሜ ነዉ?" "አለምን ማጣጣሚያ፣ህይወትን መስመር ማስያዣ...በቃ! ገንዘብ መሰብሰብ፣የምወደዉን ማግባት፣ቤት መግዛት ፣ መዉለድ ፣ቤተሰቤን መርዳት...እንደዛ አይደል? " " አይደለም! ሀያዎቹ እዉቀት እና ልምድ መሰብሰቢያ ጊዜ ነዉ።የመንገድሽን ጥግ ሳታቂ በድፍረት የምትጓዢበት፤ የምትፈልጊዉን ስራ ለማግኘት የማትፈልጊዉን ስራ የምትጋፈጪበት ፤ የምትወጂዉን ሳይሆን የምትስማሚዉን የምታገቢበት ፤ ገንዘብሽን እና ጊዜሽን የሰጠሽዉን ስራ የምትከስሪበት፤እንክት ብለሽ የምትወድቂበት፤ከዉድቀትሽ የምትማሪበት፤ተመልሰሽ የምትነሺበት ነዉ። belive me ዛሬ የዘራሽዉ እያንዳንዱ ስንዴን ነገ ማሳ ሆኖ ታጭጂዋለሽ።" "እና ምን ላድርግ?ካርታ የሌለዉ ቦታ እንዴት ነዉ ሚጎበኘዉ?" "ቱሪስት ነዉ የመጣዉ እነዛን ቦታዎች ለመቃኘት ብቻ ስለሆነ ሚጎበኘዉ።መንገደኛ እያንዳንዱን እርምጃ explore ነዉ ሚያረገዉ።በእያንዳንዱ እርምጃ የነከሰችዉን ጉንዳን አክሞ ፣ ሲጠማዉ ያጠጡትን እጅ ስሞ ዉድቀቱንም ከፍታዉንም እያጣጣመ ነዉ ሚጓዘዉ።አንቺ መንገደኛ እንጂ ቱሪስት አይደለሽም። " "ግን ከምን እንደምጀምር እራሱ እኮ አላቅም ሰሙ።የቱ ጋር ነዉ የቆምኩት? ምንድነዉ ማድረግ ያለብኝ?" "ማወቅ አይጠበቅብሽም እያልኩሽ ነዉ።ሁሉም ለመታየት እያስመሰለ እንጂ ህይወቱ 100% የገባዉ የለም።ይሄ የራስሽ መንገድ ነዉ።ወደ ስራሽ ተመለሺ።ወደ ማርኬቱ ምታድጊበትን መንገዶች ፈልጊ።አዲስ ሰዉ ተዋወቂ።የምታዉቂያቸዉን ሰዎች ለእርዳታ እጅሽን ለመዘርጋት አትፈሪ።አሁን የማፈሪያ እና የመፍሪያ እድሜሽ ላይ አይደለሽም።ብዙ ስራ ሞክሪ።ዉደቂ።በእርምጃዎችሽ ተማሪበት።ስትሞክሪዉ ነዉ ሚሳካልሽ።ያልሞከርሻቸዉን እድሎች 100% አጥተሻቸዋል።ሌላዉ ቢቀር የ ሀያዎችሽ ማብቂያ ላይ ቆንጆ ባል እና ስራ እንደ መና እንዲወርድላት እየጠበቀች ከጨረሰችዉ ልጅ ይልቅ የህይወቷን ጥሪ ለመሙላት እየተጋች ብዙ ልምዶችን የተካፈለች ሴት ትሆኛለሽ።ሰላሳዎችሽ ላይ የምትነግሪዉ የራስሽ ታሪክ ይኖርሻል።ህይወት ላይ ደሞ ወድቆ መነሳት ካለመዉደቅ በላይ ጠአም አለዉ።" ለመጀመሪያ ጊዜ የሆነ ነገር ብልጭ አለልኝ።መንገዴን ሳላዉቅ መጓዝ እንደምችል...ለመራመድ እግር እንጂ ካርታ ግዴታ እንዳልሆነ "ነገ እደዉልና ካላባረሩኝ እመለሳለሁ።" አልኳት።
Показати все...
የደመቁ ገፆች . . . . እቺን የፃፋት ሩሚ የተባለው እጅግ የተወደደው የፋርስ ገጣሚ ባለቅኔና መንፈሳዊ መምህር ነው። "የሰዋሰው ሊቁ እና ጀልባ ቀዛፊው " ትላለች  ርዕስዋ  ' አንድ የታወቁ የሰዋሰው ሊቀ ሊቃውንት የሆኑ አዛውንት በጀልባ እየሄዱ እያለ የሚቀዝፈውን ሰውዬ  " ሰዋሰው ታውቃለህ ? " ሲሉ ጠየቁት " አረ ደሀ ነኝ አላውቅም ጌታዬ " ሲል መለሰ ሰውዬው ጀልባውን እየቀዘፈ  " እንግዲያው ወዳጄ ግማሽ እድሜህን የኖርከው በከንቱ ነው !" ብለው አንኳሰሱት።  ጀልባዋ ወደ ባህሩ እርቃ ከገባች ብሃላ ሀይለኛ አውሎ ንፋስ ተነስቶ ከባድ መዓበል ቀሰቀሰ በዚህ ግዜ ጀልባ ቀዛፊው የሰዋሰው ሊቁን አዛውንት እንዲህ ሲል ጠየቃቸው "ዋና ይችላሉ? " "አረ አልችልም " ሲሉ መለሱ " እንግዲያው ጌታዬ አብዛኛውን እድሜ የኖሩት በከንቱ ነው ! " የሰዋሰው ሊቁም አፍረው ሳይሆን ፈርተው ቅል አከሉ መዓበሉም በርትቶ ህይወታቸውን አጡ ። ' በአጭሩ ምን ለማለት ነው (ሰው አይናቅም) ሰላም እደሩልኝ ካሊድ አቅሉ✍
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
I hope you find someone who enjoys your energy but understands your quiet phases too. امیدوارم کسی را پیدا کنید که از انرژی شما لذت ببرد، اما فاز سکوتتان را هم درک کند.
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.