cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

በዩትዩብ ቻናላችን ሰብስክራይብ ያድርጉ 👉https://www.youtube.com/@Historicalheromedia ጥቆማ ለመስጠት 👇👇👇 @Tagemi_bot

Більше
Рекламні дописи
7 632
Підписники
-1224 години
-177 днів
-7230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

💚💛❤ ሰበር የድል ዜናዎች ከጎንደር..‼️‼️ ጀግኖቹ የቴዲ ልጆች የጎንደርን ምድር በጠላት የማይደፈር እሳት ረመጥ አድርገውታል።ሰሞኑን ጠላት ያለ የለለ ሀይሉን እያግተለተለ ቢያስገባም እንደጠበቀው ግን አላገኘውም።በማዐከላዊ ጎንደር ወገራ ወረዳ ከጀጀህ አንስቶ እስከ ሰንበትጌ ብራ ባሉ ቀበሌዎች ሶስተኛ ቀኑን የያዘ ወጊያ የነበር ቢሆንም በክንደ ነበልባሎቹ የአካባቢው ፋኖዎች ተቀጥቅጦ ወቷል። ▪️ ጎንደር ኪንፋዝ በገላ ..❗ ሶስተኛ ቀኑን በያዘው ውጊያ በጎንደር እዝ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር በአዲስ ያደራጃቸው አዳዲስ ሻምበሎች የወረዳውን ህዝብ በማስተባበር ጠላት ያለ የለለ ሀይሉን በከባድ መሳሪያ የታገዘ ሀይሉን ቢያስገባም ተቀጥቅጦ የተደመሰሰው ተደምስሶ የቀረውም እግሪ አውጭኝ ብሎ ወደ አምባጊዮርጊስ ከተማ ፈርጥጧል።በዚህ ቀጠና አርቢት፣ስላሬ፣ሮቢት በገላን እና አካባቢውን ከጠላት ሀይል በማፅዳት በፋኖ ቁጥጥር ስር መሆን ችለዋል ▪️ጎንደር አርባያ በለሳ ..❗ የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ ስር ውስጥ ያሉ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦርን ጨምሮ ሌሎች ክፍለ ጦሮች የተሳተፉበት ከጠዋት ጀምሮ ይህ መረጃ እስከ ተላለፈበት ድረስ ውጊያ ላይ ሲሆኑ በደጎማና በአርባያ መካከል በምትገኘው ወርሀላ በተሰኘች ቦታ የጠላት ሀይል ለመፈርጠጥ እንኳን እድሉን እንዳያገኝ ተደርጎ በክንደ ነበልባሎቹ እየተወቀጠ ይገኛል።  ▪️ጎንደር-ቋራ ..❗ በምዐራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ሶስተኛ ቀኑን በያዘው ውጊያ የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ ቋራ ኦሜድላ ክፍለ ጦር የጠላትን ሀይል አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ሽንፋ ደለጎ የተባሉ ከተሞችን ነፃ ማውጣት ችለዋል አሁንም ውጊያው የቀጠለ ሲሆን በተለይ ጠላት ኔትዎርክ በመዝጋት ለማጥቃት ቢሞክርም ከሽንፈት ግን አልታደገውም። ባጠቃላይ ጎንደር ላይ ትግሉ ህዝባዊ የሆነ ሲሆን ህዝቡ እጅግ በሚያስደምም ሁኔታ በነቂስ በመውጣት የጠላትን ሀይል መውጫ መግቢያ አሳጦታል። መረጃው የአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ አደረጃጀት ዘርፍ ሀላፊ ሻለቃ በላዬ ዘለቀ ነው። https://t.me/Historicalheromedia https://youtube.com/@historicalheromedia-qj9gj?si=3qwHotMUBIjaDEMa
Показати все...
ኢትዮ ተምሳሌት ሚድያ

በዩትዩብ ቻናላችን ሰብስክራይብ ያድርጉ 👉

https://www.youtube.com/@Historicalheromedia

ጥቆማ ለመስጠት 👇👇👇 @Tagemi_bot

3
💚💛❤ የድል ዜናዎች {።።።።} #ድል_አንድ ፦ የአማራ ፋኖ በጎጃም ቢትወደድ አያሌው ክፍለጦር በኮሎኔል ጌታሁን እየተመራ በአራዊት ሰራዊቱ 99ኛ ክፍለጦር በድን ላይ ተረማምደው የሰሜን አቸፈሯን የሊበን ከተማን ነፃ አውጥተዋል። #ድል_ሁለት ፦ በሸዋ በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ባልጪ በምትባል ከተማ ፋኖዎቻችን የአራዊት ሰራዊቱን ካምፖ በድንገት በመክበብ በፈፀሙት ኦፕሬሽን አራዊት ሰራዊቱ እንደ ቄጤማ መጎዝጎዙ ታውቋል። --- #ድል_ሶስት ፦ በአዲስ ቅዳም ድማማ በሚባል ቦታ የኤፍሬም አጥናፉ ብርጌድ እጅግ በርካታ ቁጥር ያለውን አራዊት ሰራዊት ከምድር በታች አድርጎታል፤ ክራንች አንጋች የሆነውም በርካታ እንደሆነ የአካባቢው ምንጮች ገልፀዋል። ዝርዝር ይኖረናል! https://t.me/Historicalheromedia https://youtube.com/@historicalheromedia-qj9gj?si=3qwHotMUBIjaDEMa
Показати все...
👍 4
💚💛❤ በፍጥነት ይዛመት‼️ በዛሬ ዕለት ደጀን ጉበያ ከአራዊት ሰራዊቱ ጋር  ዛንበራ በበቆል፣ ወብላትና ቆቁሃ ግንባሮች ውጊያ እየተደረገ ነው። የአካባቢው ያለህ ወገን ተናበህ፣ ውጠህ አስቀረው። አንዲትም ወታደር በህይወት እንዳይወጣ ተረባረብ፤ መረጃ በፍጥነት ወደ አካባቢውና አጎራባች አካባቢዎች አድርሱ። https://t.me/Historicalheromedia https://youtube.com/@historicalheromedia-qj9gj?si=3qwHotMUBIjaDEMa
Показати все...
👍 16 5👏 2
💚💛❤ ጎንደር ለማመን የሚከብድ ነገር ግን በነብሮች የተፈፀመ ጀብድ ‼️ የጭንቅ ቀን ጀግና ይፈጠራል የሚባለው ለዚህ ነው። ዛሬ 23/09/2016 በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ ልዩ ቦታው ሸሚት ከታባለው ቦታ የአብይ አህመድ የሸኔ ሰራዊት #ድሽቃ መሳርያ ፈትተው እያፀዱ እያለ የእስቴ ዴንሳ ብርጌድ 1ኛ ሻለቃ አባል የሆኑት 1ኛ .ሻንበል ውበቴ 2ኛ .ሳሚ ባንቴና 3ኛ .ገብርዬ ታደሰ የተባሉ ሶስት ጀግኖች በደረታቸው እየተሳቡ በመሄድ ድሽቃ መሳርያ ማርከው ለእስቴ ዴንሳ ብርጌድ መምርያ ገቢ አድርገዋል። አየህ ክፉ ቀን ጀግኖችን አምጦ ይወልዳል የሚባለው ለዚህ ነው። ይሄ ጀብድ ሲሰራ ምንም አይነት ኮሽ የሚል ውጊያ አልተካሄደም። ይህ የደፈጣ ውጊያ ዋናው አካሄድ ነው። ይህ ታሪክም ለትውልድ በወርቅ ቀለም ተከትቦ ይቀመጣል። የዜናው ምንጭ የእስቴ ዴንሳ ብርጌድ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ ማረው ክንዱ ነው ። #ድል ለፋኖ https://t.me/Historicalheromedia https://youtube.com/@historicalheromedia-qj9gj?si=3qwHotMUBIjaDEMa
Показати все...
👍 34 4
👍 1
💚💛❤ የክልል የፀጥታ ሀይሎችን የጦርነት ተሳትፎ አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ጎንደር እዝ የተሰጠ መግለጫ..‼️ አማራ በ21ኛ ክፍለ ዘመን በአለም ላይ የጠፉ መከራዎች እየተፈራረቀበት የሚገኝ እና ላለመጥፋት ተጋድሎ እያደረገ ያለ ህዝብ እንደሆነ ለማንም ጤነኛ አዕምሮ ያለው ሰው የተደበቀ አይደለም። ይህ ስርዓት የአማራን ህዝብ ለመጨረሻ ጊዜ ለመስበር እና ለማጥፋት የሚንቀሳቀስ መሆኑ ለማንም የሚታይና የሚዳሰስ ሐቅ ነው። ይህን የምንለው ያለምክንያት አይደለም። ቀደም ባሉት ጊዚያት የማሸነፍ ስነልቦና ላይ የነበረው  የብልፅግና ሐይልም ሆነ እሱን የወለደው ስርዓት ለአማራው ምንም አይነት ርህራሔ እንደሌለው እና አማራ ተሸንፎ ሊኖር እንደማይችል በተግባር አሳይቶን እንጅ። በመሆኑም  የአማራ ህዝብ ህልውናውን ለማረጋገጥ ካባከናቸው ዕንቁ እድሎች ውስጥ ይህ የመጨረሻው እድል ነው ብሎ በማመን ይህን ስርዓት እና ስርዓቱ የወለዳቸውን ችግሮች ነቅሎ ለመጣል ውድ ህይወቱን መገበር ከጀመረ አንድ አመት አስቆጥሯል። በዚህ የአማራ ህዝብ  እያደረገ ባለው ህዝባዊ ተጋድሎ የመከላከያ ሀይሉ ሙት እና ቁስለኛ የሆነበትና የተረፈው ተማርኮ እና ከድቶ ያለቀበት የብልፅግና መንግስት የሌሎች ክልል ታጣቂዎችን ለውጊያ ማሰለፍ መጀመሩን ለመረዳት ችለናል::  ይህም የብልፅግና መንግስት ሊደብቅ እየሞከረ ያለውን ሀቅ በገሀድ ያሳየና የብልፅግና ጦር እውነትም ግብዓተ መሬቱ መቃረቡን ያረጋገጠ ክስተት ነው:: የብልፅግና መንግስት እንኳን የክልል የፀጥታ ሀይሎች፤ ቅጥር ነብሰ ገዳይ የሚያዋጋበት የሞራል ዝቅጠት ላይ በመሆኑ   ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት እና መደበቂያ ለመፈለግ ያደረገው ድርጊት ብዙም  ባያስገርመንም በዚህ ዘመናዊ የሸፍጥ ፖለቲካ የሰዎችን ግብረገብነት ቦታ ባሳጣበት ወቅት፤ ቡድኖችንና ግለሰቦች  ሸንግለውና አታለው እራስን ለመጥቀም በመፈለግ የኦሮሞ ህዝብ የዚህ ታሪካዊ ጠባሳ አጋር ለማድረግ የተሔደበት እርቀት እጅግ በጣም አሳዝኖናል። በመሆኑም የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ለሚከተሉት አካላት መልዕክት እና ማሳሰቢያ መስጠት ይፈልጋል፦ 1. ለኦሮሚያ እና ለሌሎች የክልል ፀጥታ ሐይሎች፦ ይህ  ስርዓት ስልጣኑ የተደላደለለት ሲመስለው ማንንም ለማጥቃት የማይራራ መሆኑን ከአማራ ክልል ልዩ ሐይል እና ከለውጥ አመራሮች በላይ አስተማሪ የለም።  ክፉ እና ተንኮለኛ ፍላጎቱ ድል አስኪደረግ ድረስ እንጅ የእናንተም እጣ ፋንታ ከእነሱ የተለየ እንደማይሆን ውስጣችሁ ያውቀዋል። በመሆኑም በጥቅም ፍርፋሪ ተገዝተው በሚያዙዋችሁ አለቆቻችሁ ተመርታችሁ የአማራን ህዝብ ለማጥፋት ከሚደረግ ዘመቻ እንድትታቀቡ ጥሪያችን እናስተላልፋለን። ይህ ሳይሆን ቀርቶ በፈቃዳችሁ  የብልፅግና መንግስትን ጭፍጨፋ ለመደገፍ እስከመጣችሁ ደረስ ግን ለሚደርስባችሁ ነገር በሙሉ ሀላፊነቱ የእናንተ እና የላካችሁ አካል መሆኑን እናሳውቃለን:: ፋኖ የአማራ ህዝብን ህልውና ለማስከበርና ሀገራችንን ከዚህ አሳፋሪ ስርዓት ለማላቀቅ በሚያደርገው ትግል የሚወስድባችሁ እርምጃም በጦርነት ህግ ሁሉ የተፈቀደ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን። 2. ለኦሮሞ ህዝብ፦ የብልፅግና አመራሮች እና አፈ-ቀላጤዎች የኦሮሞ ህዝብ በአማራ ህዝብ ላይ እንዲዘምት ቅስቀሳ ማድረግ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። እነዚህ የብልፅግና ካድሬዎች በአማራ እና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ለማስታወስ የሚዘገንን በደልና ስቃይ ሲፈፅሙ የነበሩ ሌቦችና ጨካኞች እንደሆኑ ይታወቃል። ባለፉት 27 አመታት በኢትዮጵያ ሰማይ ስር የተፈፀመውን ቅጥ-ያጣ ዘረፋና ጭካኔ የሞላው ተግባር በብዙ እጥፍ አሳድገው በመፈፀማቸው ለውርደትና ውድቀት የተዳረጉ፤ ከህግና የህሊና ፍርድ ለማምለጥ  የኦሮሞ ህዝብ ውስጥ ለመደበቅ ጥረት እያደረጉ ያሉ አካሎች ናቸው። በመሆኑም በብዙ መከራ እንግልት ውስጥ አልፋችሁ ያሳደጋችኋቸው ልጆች የውሻ ሞት እንዲሞቱ እየተጠሩ እና እየሞቱ ስላለ ያልገቡት እንዳይገቡ የገቡትም ወደቤታቸው እንዲመለሱ ጥሪ እንድታደርጉ  በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ጥሪያችንን እናስተላልፋለ። በዚህ የሕልውና ትግል የአማራ ህዝብ በጠላትነት የፈረጅነው ሕዝብ የለም፡፡ ነገር ግን በየትኛውም ሁኔታ የአማራን ሕዝብ ሕልውናን የማይቀበሉ፣ ሰብአዊ ክብራችን ተገፎና ተዋርደን እንድንኖር አበክረው የሚሠሩ የትኞቹንም ኃይሎች ያለምህረት እንታገላለን። በዚህ ሒደት ለሚደርሰው ማንኛውም ኪሳራ የአማራ ህዝብ ተጠያቂ እንደማይሆን እናሳውቃለን። 3.  ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ፦ ፋኖ ይህ ድርጊት የሰላማዊው የኢትዮጲያ ህዝብ ፍላጎት ይገልፃል ብሎ አያምንም:: የነበረውን ሰላማዊ የህዝብ- ለህዝብ ግንኙነት ማስቀጠል ለሁሉም የሚያዋጣ  እና የሀገራችንን ቀጣይነት የሚያረጋግጥ መሆኑንም ያምናል:: ድርጊቱ ብልፅግና ጦርነቱን ከእሱ በማዞርና የብሄር ግጭት በማድረግ ስልጣኑን ለማራዘም የቆፈረው ጉድጓድ በመሆኑ ከአማራ ህዝብ ጋር ያላችሁን መልካም ግንኙነት እንድታስቀጥሉ እንዲሁም  ይሄንን ድርጊት ለጋራ ጥቅም ስትሉ እንድታወግዙ፣ ተሳታፊም እንዳትሆኑ እንጠይቃለን:: የክልሎች በጦርነቱ መሳተፍ ግጭቱ ከአማራ ክልል ተሻግሮ ወደ አጎራባች ክልሎች እንዲስፋፋ የማድረግ እድሉ ከፍተኛ ነው :: ፋኖም የታጣቂዎችን መነሻ ከምንጩ ለማድረቅ በክልሎቹ ውስጥ ተልዕኮ እንዲሰራ ሊያስገድደው እንደሚችል እናሳውቃለን:: በመሆኑም የትኛውም የፋኖ እንቅስቃሴ ወንጀለኞችን ለመያዝ እና ጨፍጫፊውን ሀይል ለመምታት ብቻ ያለመ መሆኑን ለማሳወቅ እንፈልጋለን:: 4. ለአማራ ህዝበ፦ ዛሬ ላይ ለሌላው ሰው ህይወት እራሳቸውን አሳልፈው የሚሰጡ  ከፍተኛ የሰውነት ባህሪ ያላቸው ልጆችን አምጠህ ወልደሐል። ይሁን እንጅ ይህ የታሪክ እጥፋት ለ60  በላይ አመታት የፖለቲካ ስብራት በኋላ የተገኘ እድል ነው። ጎሽ እንደሰው ማሰብ ማንሰላሰል የሚያስችል አዕምሮ ሳይኖራት በደመነብሳዊ እሳቤ ለልጇ ስትል ከማትመጣጠነው ትልቅ አውሬ ጋር የምትጋፈጠው ዝርያዋን ለማስቀጠል ነው። ስለዚህ እያደረግነው ያለው ትግል እንስሳት እንኳን የሚያደርጉትን ዘርን የማስቀጠል ትግል ነው። ለዚህ ደግሞ መማር ወይም አለመማር አይጠይቅም፤ አይከለክልም። በመሆኑም እየተሞከሩ ያሉ አዝማሚያወች በዚሁ የሚቀጥሉ ከሆነ እንደ ህዝብ እራሳችን ለመከላከል ስለምንገደ ከእሰካሁኑ የተለየ የትግል ስልት እንከተላለን። ለዚህም  መላው የአማራ ህዝብ እራሱን ለሁሉ ነገር ዝግጁ እንዲያደርግ ከወዲሁ እንጠይቃለን። ድል ለአማራ ፋኖ! ድል ለአማራ ህዝብ!                           የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ                 ዋና አዛዥ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ                                 ጎንደር-አማራ-ኢትዮጵያ                         ግንቦት  23/2016 ዓ.ም https://t.me/Historicalheromedia https://youtube.com/@historicalheromedia-qj9gj?si=3qwHotMUBIjaDEMa
Показати все...
👍 13 2
Показати все...
በአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ መብረቁ ክፍለጦር የተማረኩ የአንድ ግለሰብ ስልጣን አስጠባቂ ሠራዊት

👍 9
💚💛❤ ሸዋ በረኸት ‼️ ሸዋ በረኸት ከንጋት 9:00 የጀመረ ከፍተኛ ትንቅንቅ እየተደረገ ነው ። በአጎራባች ያላችሁ የህዝብ ልጆች ለበረኸት ፋኖ ሽፋን በመስጠት እዲያግዙ መረጃውን አድርሱ። #ድል ፋኖ https://t.me/Historicalheromedia https://youtube.com/@historicalheromedia-qj9gj?si=3qwHotMUBIjaDEMa
Показати все...
👍 21
💚💛❤ መረጃ ጎንደር ⨳⨳⨳⨳ የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ዕዝ በአራቱም አቅጣጫ አየያደረገ ያለውን ተጋድሎ አጠናክሮ የቀጠለ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በደንቢያ፣በእብናት፣በበለሳ፣ በአርማጭሆ፣በሰቀልት እና በመተማ ውጊያዎች እየተደረጉ ነው ሲል የዕዙ ዋና አዛዥ ሻለቃ ሀብቴ ወልዴ ተናገረ። የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር በወገራ ወረዳ ከገደብየ ጀምሮ እስከ ጨዋ ቀበሌ ድረስ ባለው ቀጠና በእያንዳንዱ ቀበሌ ሐይለኛ ውጊያ እየተደረገ እንደሆነም ተናግሯል። ውጊው ከሌሊቱ ዘጠኝ ሰዓት የጀመረ ሲሆን መረጃው አስከተሰጠበት ሰዓት ቀጥሏል ብሏል። ለቁጥር የሚያታክት የጠላት ጦር የገባ ቢሆንም ከቆይታወች በኋላ ለቁጥር የሚያታክት አስክሬን ሆኗል ሲል ዋና አዛዡ ተናግሯል። ድል ለአማራ ህዝብ! ድል ለአማራ ፋኖ የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ https://t.me/Historicalheromedia https://youtube.com/@historicalheromedia-qj9gj?si=3qwHotMUBIjaDEMa
Показати все...
👍 27
💚💛❤ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ‼️ ነበልባሉን የአማራ ፋኖ ከበባ አድርጎ ጥቃት ለመፈፀም ያቀደው የአብይ አህመድ ወታደር እንደእባብ ተቀጥቅጦ ተመልሰ። ግንቦት 22/2016 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ከደብረብርሀን 13 ኪ.ሜ ርቀት ላይበእምዬ ምኒልክ ቀዬ በአንኮበር መስመር ልዩ ቦታው ዲቡት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኙ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ጀግኖች ላይ የህልም እንጀራ ለመብላት ከአንኮበር እና ከደብረብርሀን ከተማ ተሰባስቦ ያለውን ሁሉ ሜካናይዝድ የጦር መሳሪያ በመያዝ ጥቃት ለመፈፀም እሳቱን የሸዋ ምድር የረገጠው የብርሀኑ ጁላ ፀረ አማራ ፍዝ መንጋ ቡድን በጀግናው የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በተለያዩ የብርጌድ ሻለቆች በደረሰበት መብረቃዊ የመልሶ ማጥቃት ምት አስከሬኑን ሳይሰበስብ እግሬን በሰበረኝ እያለ ወደ መጣበት ፈርጥጧል። ግንቦት 21/2016 ዓ.ም ከሌሊቱ 9:00 ጀምሮ ጥቃት እንዲፈፀምበት በሸዋ ባንዳዎች ሴራ የተሸረበት የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ለልዩ ኦፕሬሽን የተዘጋጁ የተለያየ የብርጌድ ሻለቆች በየአቅጣጫው ዲሽቃና ዙ-23 ተሸክሞ በሁለት አቅጣጫ የመጣውን የአብይ አህመድ አሽከር ባደረጉት አስደማሚ እና ተወርዋሪ የማጥቃት ኦፕሬሽን ፀረ አማራው የአገዛዙ ወንበር ጠባቂ የጠላት ሀይል ጥቁር አስፓልቱን ተከትሎ ወደ ደብረብርሃን ከተማ ፈርጥጦ የተመለሰ ሲሆን ሀቅን ከህዝባቸው፣ ጀግንነትን ከአባታቸው የወረሱት የአማራ ፋኖ የሸዋ አናብስቶችም ታላቅ ጀብዱ በመጎናፀፍ የጠላትን ሀይል እግር በእግር እየተከተሉ ወደ ደብረብርሃን እየገሰገሱ ይገኛሉ። ድል ለአማራ ፋኖ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት ክፍል https://t.me/Historicalheromedia https://youtube.com/@historicalheromedia-qj9gj?si=3qwHotMUBIjaDEMa
Показати все...
👍 21🙏 1