cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Bensa Fm 91.9🔓

ምን ይፈልጋሉ :- New job opportunity አዳድስ መረጃ scholarship Advertising አድስ የስራ ማስታወቂያ sport mereja All university information ❤❤❤

Більше
Рекламні дописи
236
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
-130 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

#ExitExam ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ምን አሉ ? የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተናን በተመለከተ ለፋና ቴሌቪዥን ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል። በማብራሪያቸው ምን አሉ ? - የፈተናው አይነት " የምርጫ ጥያቄ " መሆኑን ገልፀዋል። - የፈተናው ጥያቄ ብዛት በተመለከተ ጊዜው ሲደርስ እንደሚገለፅ፤ የጥየቄው ብዛት ግን ከ50 በላይ እንደሆነ ፤ በአብዛኛው ፕሮግራም 100 ጥያቄ እንደሚኖር አሳውቀዋል። - በአብዛኛው ፕሮግራም 100 ጥያቄ ነው ፈተናው ፤ በተወሰኑ መስኮች ምርጫውን ለመሙላት ብዙ ሂሳብ ስለሚሰሩ የጥያቄ ቁጥሩ ከ100 ሊያንስ ይችላል። - ተማሪዎች ፈተናውን እንደተፈተኑ ውጤታቸውን ወዲያው መላክ የሚያስችል ቴክኖሎጂ ቢሮርም የመጀመሪያ ቀን የተፈተኑ ተማሪዎች ውጤት ቢገለፅ ሌሎች ላይ ከሚያሳድረው ጫና አንፃር ወይም ፈተናው ቀለል / ከባድ ነው ብሎ እንዳይዘናጋ / እንዳይጨነቅ ወዲያው አይገለፅም። የፈተናው ውጤት የሚገለፀው የመጨረሻው ፈተና ከተሰጠ ከአንድ ቀን በኃላ ነው። - ውጤት አልፏል ወድቋል ብቻ ሳይሆን ተማሪው ያመጣው ውጤት ይገለፃል። - የጤና ተማሪዎች ፈተና ሰኔ 30 ይጀምራል እስከ ሐምሌ 8 ድረስ ይዘልቃል። የጤና ተማሪዎች ቀድመው የሚፈተኑበት ምክንያት ቀኑን ሙሉ ፈተናውን ስለሚወስዱ ነው። ጥዋት ላይ ከሙያቸው ጋር የተያያዘውን ይፈታናሉ ፤ ከሰዓት ላይ የመውጫውን ፈተና ይወስዳሉ / በተቃራኒው / ። - ፈተናው በከፍተኛ ጥንቃቄ ነው የተዘጋጀው ፤ በውስን ኃላፊዎች ብቻ እንዲታወቅ ተደርጓል፤ ስለማይታተም፣ እጅም ስለሌለበት ደህንነቱ አያሰጋንም። - ፈተናውን ከመስጫው ሰከንድ በፊት ማየት የሚችል ሰው አይኖርም። ፈተናው ካለቀበት ሰከንድ በኃላ መስራት የሚችል ሰው አይኖርም። ይህ በማዕከል ነው ቁጥጥር የሚደረገው። - የማለፊያው ነጥብ 50 % እና በላይ ሲሆን ይህን ያላለፉ (ኮርስ ያልጨረሱ) ከ5 / ከ6 ወር በኃላ ጥር እና የካቲት ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና መውሰድ ይችለሉ። በዚህም ከለተሳካ ከቀጣይ አመት ተፈታኞች ጋር መውሰድ ይቻላል። በዓመት ሁለት ጊዜ ለመስጠት ታቅዷል። - አብዛኛው ተማሪ በመጀመሪያው ዙር ያልፋል የሚል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል፤ ካልሆነ ግን በሁለተኛው ዙር ተፈትኖ ያልፋል። ሁለቴ ተፈትኖ ማለፍ ያልቻለ እስከሚያልፍ / 50 % እና ከዚያ በላይ ማምጣቱ እስኪረጋገጥ ፈተናውን መውሰድ ይችላል። - ፈተናው ተማሪዎች አልተሳካላቸውም ብሎ የማሸማቀቅ ዓለማ ስለሌለው እስኪያልፉ ድረስ መፈተን ይችላሉ። - ምናልባት ያላለፉ ተማሪዎች ዳግም ፈተና ለመውሰድ መጀመሪያ ሲማሩበት ወደነበረበት ተቋም መሄድ አይጠበቅባቸውም ፤ ባሉበት አካባቢ ባሉ ተቋማት ፈተናውን እንደሚወስዱ የሚደረግበት ሁኔታ ይኖራል። - ከ50 በመቶ በታች  ያመጡ ተማሪዎች በምረቃ ፕሮግራም ላይ ይሳተፋሉ ? ትምህርት ሚኒስቴር የምረቃ ፕሮግራም በተመለከተ በፖሊሲው ላይ እንደማይፅፍ ገልፀዋል። ጉዳዩ የተቋማት ነው ብለዋል። ሚኒስቴሩ በፖሊሲ የሚያስገድደው ግን የመውጫ ፈተናው የስርዓተ ትምህርቱ አካል ስለሆነ ይህን ያላለፈ ዲግሪ/ጊዜያዊ ጭምር፣  ትራንስክሪብት አይሰጠውም። የምረቃ ፕሮግራም ከማዕከል አይመራም ይህ የተቋማቱ ጉዳይ ነው። እኛ የምንከታተለው ፈተናውን ሳያልፉ ዲግሪ እንዳይሰጣቸው ነው። - የምረቃ ጉዳይ እና በዕለቱ በምረቃ ላይ የሚሳተፉ ተማሪዎች ጉዳይ የሴኔት ነው ትምህርት ሚኒስቴር አይመለከተውም። ነገር ግን የመውጫ ፈተናው እየተሰጠ/ ሳይሰጥ በፊት ምረቃ ማድረግ በፍፁም አይቻልም። - የመውጫ ፈተና ያላለፈ ተማሪ በፍፁም ዲግሪ፣ ቴምፖራሪ ዲግሪ፣ ሰርተፊኬት እንደማይሰጠው አስገንዝበዋል። @dbensa
Показати все...
#Update የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ትላንት " ኦነግ ሸኔ " እያለ ከሚጠሩት የታጠቀ ቡድን ጋር ነገ ማክሰኞ በታንዛንያ ድርድር እንደሚጀመር ማሳወቃቸው ይታወሳል። ይህንን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር የታጣቂው ቡድን /የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት / ማረጋገጫ ሰጥቶ ድርድር እንደሚጀመር አሳውቋል። ታጣቂ ቡድኑ ከፌደራል መንግሥቱ ጋር ልዩነቶችን በንግግር ለመፍታት ከስምምነቱ መደረሱን ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል። " የኢትዮጵያ መንግሥት ለድርድር ያስቀመጥነውን ቅድመ ሁኔታ ተቀብሏል " ያለው ታጣቂው ቡድን " ገለልተኛ ሦስተኛ ወገን ባለበት በድርድሩ ወቅት በዘላቂነት ግልጸኝነት እንዲኖር ተስማምተናል " ብሏል። በሌላ በኩል የታጣቂ ቡድኑ መንግሥት ድርጅቱን  " ሸኔ " ብሎ ከመጥራት እንዲቆጠብ አሳስቧል። " የድርጅታችን መጠሪያ፤ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ነው ፡ ሌላ ስያሜ ስህተት ከመሆኑም በላይ ማንነታችንን እና ዓላማችንን የሚወክል አይሆንም " ሲል ገልጿል። ካመንግሥት ይህን አይነት የተሳሳተ መረጃ ከማሰራጨት ሊቆጠብ ይገባልም ብሏል። የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከመንግስት ጋር ያለውም ልዩነቶች በንግግር ለመፍታት ቀጠሮ መያዙ " ለፍትሕ፣ እኩልነት እና የራስን እድል በራስ ለመወሰን የለውጥ ምዕራፍ ጅማሮ ነው " ብሏል። ከዚሁ ከድርድር ጋር በተያያዘ መረጃ ፤ የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከፍተኛ አዛዥ አማካሪ ነኝ ያሉት አቶ ጅሬኛ ጉዳታ ለኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ በሰጡት ቃለ ምልልስ በታንዛኒያ የሚደረገው ድርድር ረቡዕ እንደሚጀምር አረጋግጣለሁኝ ብለዋል። በታንዛኒያ የሚደረገው መድረክ የሂደት ማበጀት መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ መድረክ ማነው ሶስተኛው ወገን፣ በምን መልኩ ነው ሂደቱ የሚካሄደው ፣ የደህንነት ማረጋገጫ የሚያደርገው ማነው ? የሚሉና መሰል ጉዳዮች የሚወሰንበት ነው ብለዋል። አቶ ጅሬኛ ድርድሩን እያማቻቹ ያሉ አካላት የኖርዌይ እና ኬንያ መንግሥታት መሆናቸውን ገልጸው ከአውሮፓም በሂደቱ ውስጥ እየተሳተፉ ያሉ ዲፕሎማቶች መኖራቸውን ጠቁመዋል። አሜሪካ እና የአውሮፓ ህብረትም በሂደቱ የመሳተፍ ፍላጎት እንዳላቸው እኙሁ የሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዥ አማካሪ እንደሆኑ የገለፁት አቶ ጅሬኛ አሳውቀዋል። " ድርድር መደረጉ እና ሰላም እንዲሰፍን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት ከፍተኛ ፍላጎት አለው " ያሉት አቶ ጅሬኛ ፤ " ሂደቱ ተስፋ ሰጪ ነው " ብለዋል። @tikvahethiopia
Показати все...
#Update የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በክልሉ ለሚገኙ መገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። በዚህም መግለጫቸው ፤ " የትግራይ ህዝብ እራሱን ከጥፋትና ውድመት ለማዳን ሁሉንም አይነት መስዋዕትነት ከፍሏል። " ያሉ ሲሆን " ጊዜያዊ አስተዳደሩም የትግራይ ህዝብ የታገለለትንና መስዋእትነት የከፈለበትን ዓላማ ለማሳካት ይሰራል " ብለዋል። አቶ ጌታቸው አስተዳደራቸው የትግራይን ግዛታዊ አንድነትን ማረጋገጥ፣ የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቄያቸው መመለስ እና የህዝቡን ሁለንተናዊ ችግሮች በፍጥነት መፍታት ዋነኛው አላማው አድርጎ እንደሚሰራ በሰጡት መግለጫ መናገራቸውን ከክልሉ ቴሌቪዥን ያገኘነው መረጃ ያሳያል። አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን እንዲመሩ በህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ አብላጫ ድምፅ አግኝተው ከተመረጡ በኃላ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ክልሉን እንዲያስተዳድሩ ርዕሰ መስተዳደር አድርገው እንደሾሟቸው ትላንት የጠ/ሚ ፅ/ቤት ማሳወቁ ይታወሳል። ተጨማሪ መረጃዎች ይኖራሉ። @tikvahethiopia
Показати все...
#NewsAlert የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፤ አቶ ጌታቸው ረዳን የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳደር አድርገው መሾማቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አሳውቋል። ርዕሰ መስተዳደሩ በክልሉ የሚንቀሳቀሱ የተለያዩ የፖለቲካ ሃይሎችን ውክልና የሚያረጋገጥና አካታች የሆነ አስተዳደር በማዋቀር የክልሉን አስፈፃሚ አካል የመምራትና የማስተባበር ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል ተብሏል። @tikvahethiopia
Показати все...
#Tigray አቶ ጌታቸው ረዳ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ በህወሓት ማዕከላይ ኮሚቴ አብላጫ ድምፅ ማግኘታቸው ተነገረ። የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አድርጎ ነበር። በዚህም #አቶ_ጌታቸው_ረዳን በትግራይ ክልል ለሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንታዊ እጩ አድርጎ አብላጫ ድምጽ መስጠቱን ቅርበት ያላቸው የፓርቲው ምንጮች እንደገለፁለት የአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ (ቪኦኤ) የትግርኛው አገልግሎት ክፍል ዘግቧል። የአቶ ጌታቸው ረዳና ሌሎች የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ ኣባላት ሹመት፣ የክልሉ አመራሮች ከፌደራሉ መንግሥት ጋር በጊዜያዊ አስተዳደሩ አወቃቀር ጉዳይ ተወያይተው #ካፀደቁት በኋላ ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሥራ እንደሚጀምር ነው ' ቪኦኤ ትግርኛ ' ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ በዘገባው ያመለከተው። @tikvahethiopia
Показати все...
" የሰላም ስምምነቱ ሙሉ በሙሉና ዘላቂነት ባለው መልኩ ተግባራዊ ሲደረግም አሜሪካ የኢትዮጵያን የአጎዋ ተጠቃሚነት ዳግም ለመመለሾ ቁርጠኛ ናት " - አንቶኒ ብሊንከን ብሊንከን ኢትዮጵያን ወደ አጎዋ ለመመለሾ ሀገራቸው ቁርጠኛ መሆኗን ገለፁ። አሜሪካ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ሙሉ ተግባራዊነት ተከትሎ ኢትዮጵያን ወደ አጎዋ እድል ተጠቃሚነት ለመመለሾ ቁርጠኛ መሆኗን በአዲስ አበባ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን መናገራቸውን ፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት ዘግቧል። ብሊንከን ለፋና በሰጡት ቃለመጠይቅ አሜሪካ በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር  በቅንጅት እየሰራች ነው ብለዋል። ይህም አሜሪካ፥ ከኢትዮጵያ ጋር በኢኮኖሚ እና በሌሎች ዘርፎች ላይ  ያላትን አጋርነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚያበረታታ ተናግረዋል። የሰላም ስምምነቱ በሚመለከታቸው አካላት ሙሉ በሙሉና ዘላቂነት ባለው መልኩ ተግባራዊ ሲደረግም አሜሪካ ኢትዮጵያን  ምርቶቿን ከኮታና ቀረጥ ነፃ ወደ አሜሪካ እንድታስገባ ወደ ሚፈቅደው የአጎዋ ተጠቃሚነት ዳግም ለመመለሾ ቁርጠኛ ናት ብለዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በቃለ መጠይቁ ወቅት " ኢትዮጵያ የሽግግር ፍትሕን ለመተግበር የጀመረችውን ጥረት አድንቀዋል ያለው " ፋና ብሮድካስት " የሰላም ስምምነቱ ትግበራ ሒደት በጥሩ ሁኔታ እየተፈጸመ መሆኑን ገልፀዋል ብሏል። @tikvahethiopia
Показати все...
#Update ብሊንከን አዲስ አበባ ደርሰዋል። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል። ብሊንከን ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ምስጋኑ አርጋ አቀባበል አድርገውላቸዋል። የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በይፋዊ ጉብኝታቸው ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል። @tikvahethiopia
Показати все...
#Update የሲዳማ እና ኦሮሚያ ክልል አዋሣኝ ከሆነው ከምዕራብ አርሲ ዞን ነሰቦ ወረዳ የተፈናቀሉ ዜጎች የሚመለከተው የመንግሥት አካል ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርግላቸው መጠየቃቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል። ተፈናቃዮቹ በሺዎች የሚቆጠሩ ናቸው ያለው ዘገባው፤ ይኖሩበት በነበረው የምዕራብ አርሲ ዞን ነሰቦ ወረዳ - ቦርጮሳ ቀበሌ ባለፈው ዓርብ መሣሪያ የታጠቁ ሰዎች ግድያ መፈጸማቸውን ተከትሎ ወደ ሲዳማ ክልል ጭሪ ወረዳ ሸሽተው መጠለላቸውን ገልጿል። የወረዳዎች መስተዳድር ባለሥልጣናት በበኩላቸው ነዋሪዎቹን በአጭር ጊዜ ወደ ቦታቸው ለመመለሾ በቅንጅት እየሠራን እንገኛለን ብለዋል። ተጎጂዎች እንዳሉት ከሆነ ዓርብ መሣሪያ የታጠቁ ሰዎች ለስብሰባ በተጠራው ነዋሪ ላይ ተኩሰው 12 ከገደሉና ሌሎች 38 ሰዎችን ካቆሰሉ በኋላ አብዛኛው የቀበሌ ነዋሪ በፍርሃት አካባቢውን ለቆ ወጥቷል። ከግድያ በተጨማሪ የመኖሪያ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን በዚህም በርካቶች ሸሽተው የሲዳማ ክልል ጭሪ ወረዳ መገባታቸውና በትምህርት ቤቶችና በቀበሌ ጽህፈት ቤቶች ቅጥር ግቢ የተቀሩት ደግሞ በየዘመዶቻቸው ቤት ተጠግተው እንደሚገኙ ተመላክቷል። ተፈናቃይ ወገኖች ፤ የኢትዮጵ ቀይ መስቀል ማህበር ውስን የዕለት ድጋፍ እንዳቀረበለቸው ከዚህ በስተቀር ግን የደገፋቸው አካል እንደሌለ በመግለፅ ድጋፍ እንዲደረግላቸው ጥሪ አቅርበዋል። በምዕራብ አርሲ ዞን የነሰቦ ወረዳንና በሲዳማ ክልል የጭሪ ወረዳ አመራሮች  የጋራ ምክክር ተደርጎ መግባባት ላይ እስኪደረስ የተናጠል መግለጫ እንዳይሰጥ ስምምነት በመኖሩ ዝርዝር ማብራሪያ ለመስጠት እንደሚቸገሩ እንደገለፁ ሬድዮ ጣቢያው አመልክቷል። አሁን ላይ አመራሮቹ ከመንደራቸው ለቀው የወጡ ነዋሪዎችን በአጭር ጊዜ ወደቦታቸው ለመመለሾ ከመግባባት ላይ መድረሳቸውንና ሂደቱ እንደተጠቃለለ የጋራ መግለጫ እንደሚሰጥ እንዳሳወቁ ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ በዘገባው ጠቅሷል። @dbensa
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.