cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

እውነት እውነትን እንነጋገር Group

ውሸትን መስወጋድ፣ እውነትን መነጋገር እና ለተነጋገርነው እውነት መኖር ነው፡፡ በዚህ Group :- ✍️...አጫጭር ትምህርቶች ፣ ⚖️... ሚዛናዊ የሆነ ሀሳቦች ፣ 📖...ሕይወት ለዋጭ የሆነው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ፣ 🎥...አስተማሪ የሆኑ ፎቶግራፍና ሌሎችም ይለቀቃሉ ። 🈴... Join us...!

Більше
Рекламні дописи
195
Підписники
Немає даних24 години
+17 днів
-530 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

#ወሬ አሉባልታክፉ መናገር  ከእዚያ ሰው ፍቃድ ሳይኖር ስለ ሌላ ሰው የግለሰብ ተጨባጭ የሆነውንና ያልሆነውን ነገሮችን ወይም መረጃዎችን መካፈል። አንዳንዴም በግማሽ እውነት፣ ህዝብን ከእግዚአብሔር እና ከሁሉም ጥሩ ነገሮች ለማዞር #ሰይጣን ወሬን እና ጸብን ያባዛል፣ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል ? ✍...ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ መልስ ይሰጡበታል፣ "እኔ እላችኋለሁ፥ ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል፤ከቃልህ የተነሣ ትጸድቃለህና ከቃልህም የተነሣ ትኰነናለህ። የማቴ.12:36-37 ✍...ቅዱሳን የማይገባውንም እየተናገሩ፣ ለፍላፊዎችና በነገር ጣልቃ ገቢዎች እንዳይሆኑ ተገስጸዋል፣ “ከዚህም ጋር ቤት ለቤት እየዞሩ ሥራን መፍታት ደግሞ ይማራሉ፥ የማይገባውንም እየተናገሩ ለፍላፊዎችና በነገር ገቢዎች ይሆናሉ እንጂ፥ ሥራ ፈቶች ብቻ አይደሉም።” 1ኛ ጢሞቴዎስ 5፥13 በመጨረሻም #ወሬ #አሉባልታ #ክፉ ንግግር ግለሰብን፣ቤተሰብን፣ጎረቤትን፣አካባቢን...ሀገርን ፣ የግልንና የመንግሥት ተቋማትን፣ቤተክርስቲያንን...ሌሎችንም የሚያፈርስ አደገኛ መሳሪያ ነው!! #ወሬ #አሉባልታ #ክፉ ንግግር !! ይቀጥላል...!
Показати все...
የበጎ ተግባር !! በጎነት በየእለት እንቅስቃሲያችን የምንለማመደው እና ለጥቅም የምንለምደው ተግባር ነው።በህይወታችን ውስጥ ብዙ መልካም ነገርን ያደረጉልን ሰዎች አሉ እናም የግድ ያንን ላደረጉልን ሰዎች ወደኋላ ተመልሰን ለእነሱ የሆነ ነገር ማድረግ አይኖርብን ይሆናል ምን አልባትም እነዛ ሰዎች ከኛ የሚጠብቁት ነገርም ላይኖር ይችላል ያ ከሆነ መልካምነት ይጠፋ እና ውለታ መላሽ ትውልድ ብቻ ነው የምንፈጥረው እናም እኛም ትላንት ላይ ለተደረገልን ነገር ዛሬ ላይ ወደኋላ ዞረን ለነሱ ለመክፈል ከምንጣጣር ወደፊታችን ሄደን ዛሬን እና ነገን ሌሎችን ልክ እኛ እርዳታ አስፈልጎን ሰዎች ከጎናችን እንደነበሩበት እኛም የምናስፈልጋቸው ሰዎች አሉና እነሱን በመርዳት በተወሰነ ደረጃ አለማችንን የተሻለ እናድርግ። መልካምነትም ሆነ ደግነት እለት ተዕለት የምንለማመደው ተግባር ነው። “ልጆችን በማሳደግ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት በጎንም ሥራ ሁሉ በመከተል፥ ይህን መልካም ሥራ በማድረግ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።” — 1ኛ ጢሞቴዎስ 5፥10
Показати все...
“የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።” — 2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥15
Показати все...
👆...አንድ ሰው! ይህ ሰዉ ምን ዓይነት ሰው ነዉ ? ነጭ ወይስ ጥቁር? ሀብታም ወይስ ድሃ? ክርስቲያን ወይስ እስላም? አማራ ወይስ ኦሮሞ? ሃዲያ ወይስ ከንበታ ? መጤ ወይስ ተወላጅ? ምሁር ወይስ ገበሬ? ይህ ሁሉ ምን ያስፈልጋል? በቃ! አንድ ሰው። ሰው የሆነ ሰው። ቅጽሉ ወይም መገለጫው ሰውየውን ሰው አላደረገውም። ሰው ለመሆን የግድ ነጭነትን ወይም ጥቁርነትን ማሟላት አይጠይቅም። ሀብታም ስለሆነ ሰው፣ ድሃ ሰለሆነ ደግሞ ሌላ ነገር አይሆንም። ዘሩ፣ ሙያው፣ የትምህርት ደረጃው፣የታሰረበት ሱስ ወይም ሌላ ሁሉ መገለጫዎቹ እንጂ ማንነቱ አይደሉም። አንድ ሰው በአንድ ጊዜ ብዙ መገለጫዎች ሊኖሩት ይችላሉ። አንዳንዶቹ ጊዚያዊ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ዘላቂ ይሆናሉ። ለምሳሌ ዛሬ ተማሪ የሆነና በዚህ ማንነቱ ያወቅነው ሰው ሲመረቅ ምሩቅ፣ ሲቀጠር ሠራተኛ፣ ጡረታ ሲወጣ ጡረተኛ ይባልና መታወቂያ ይቀይራል። ዛሬ የዚህ ሃይማኖት ተከታይ የሆነ ሰው ነገ መረዳቱ ይለውጥና በሌላ መገለጫ ይከሰታል። ዛሬ በድህነት የፈረጅነው ሰው ነገ ቀንቶት ሀብታም ይሆንና አጠራራችንን ለመቀየር እንገደዳለን። በቀላሉ የሚቀየሩ የማይመስሉን እንደ ቆዳ ቀለምና እንደ ብሔር ያሉ ልዩነቶችም ቢሆኑ ውጪያዊና ገጻዊ ናቸው። ዛሬ ነጭ፣ ጥቁር፣ ቢጫ … ያልነውን ሰው በአንድ መጠሪያ አስከሬን ከዚያም አፈር … እንለዋለን። ሰው የቆዳ ቀለሙ ቢለያይም ደሙ አንድ ነው ማለትም ቀይ እንጂ የአንዱ ደም ሰማያዊ የሌላ ግራጫ ሊሆን አይችልም። የሰው ሁሉ ደም ቀይ ነው። ሰው ከአንድ ተፈጥሯልና በዓለም ላይ ሁለት ዓይነት ሰው የለም! “.... ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ ...።” — ሉቃስ 10፥27 (አዲሱ መ.ት)
Показати все...
#ጠቃሚ ሰው ✍️...ጠቃሚ ሰዉ ፊጹም የፍቅር ፣የይቅርታ፣ የእርቅና የመቀባበል ሕይወት ያለዉ ሰዉ ነዉና፡፡ለምን ብባል ጠቃሚ ሰዉ በወደቀባት የሚቀር ሰይሆን እንደገና ለመነሳት እንደ ንስር ኃይል የሚያድስ፣ከአባቱ ቤት እንደኮበለለ ልጅ ወደ ልቡ ተመልሶ ከተሳሰተበት የሚመለስ ፣በመልካም መሬት ላይ እንደወደቀ ዘር አንዱም መቶ፡አንዱም ስድሳ፡አንዱም ሠላሳ እንደሚያደርግ ፍሬ የሚያፋራ ነዉ፡፡ ምንጭ :- ጠቃሚ ሰው ከሚል ለሕትመት እየቀረበ ከለው መጽሐፌ
Показати все...
#ይቅርታ!! ”የማይበደልና ይቅር ለማለት የማይፈተን ሰው ያለ ከመሰላችሁ የሞተ ሰው ብቻ ነው፡፡” ✍...የፊልሞና መልዕክት 25 ቁጥሮች ሲኖሩት ለሰው ዓይን የማይመች ከሚመስል ቦታ የተጻፈ አጭር መልዕክት ቢሆንም እንኳን ለሰዉ ሁሉ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ዘላለማዊ መልዕክት ያለው እንዲሁም በአዲስ ኪዳን ሊገኝ የሚችል የይቅርታን ትርጉም ዉብ በሆነ መንገድ የያዘ ነዉ። የመልዕክቱ ማዕከላዊ ሀሳብ ይቅርታ ሲሆን አማኞች በደለኞችና ኃጢአተኞች ቢሆኑም እግዚአብሔር ይቅር እንዳላቸው ሌሎችን ይቅር ማለት እንዳለባቸው በጥብቅ ያስተምራል። አናሲሞስ በይቅርታ ምክንያት ለራሱ ህይወትና ለወንጌል ሥራም የተረፈ ሰው ነው። ይህ ይቅርታ ደግሞ የፍቅር ዉጤት ነዉና። #ፍቅር #ይቅርታ ይብዛላችሁ ይብዛልን !! ምንጭ :- ጠቃሚ ሰው ከሚል ለሕትመት እየቀረበ ከለው መጽሐፌ የተወሰደ!
Показати все...
✍...ሕዝቡ አይጎዳ...!!! የምሠራው ሥራ ለእኔ መተዳደሪያ የሚሆን ገቢ ቢያስገኝም አሻግሬ ማያት ያለብኝ ሌሎችን ባግባቡ እየጠቃምሁ ነው ወይስ እየጎዳሁ ? እኔ ብዙ ጥቅም እንደገኝ እነሱን አጉላላሁ ወይስ ሚዛናዊ መጠቃቀም አስባለሁ ? የሚሉትን መፈተሻዎች ነው። በኀብረተ ሰብ ውስብስብ ኢኮኖሚ ውስጥ አንዳንድ ጊዜ የአንዱ ጉዳት ለሌው ጥቅም የሆነ የሚመስልበት ጊዜ አለ። ዕቃና ባለሙያ ሲጠፋ ዕቃውና ሙያው ያላቸው ሰዎች የበለጠ የሚፈልጉበት አጋጣሚዎች ይፈጠራሉ። ያን ጊዜ እንደ ሠራተኛ ወይም ነጋዴ ሊኖረን የሚገባ አመለካከት በጥንቃቄ የተያዘ ሊሆን ያስፈልጋል ። “በድብቅ እህል የሚያከማቸውን ሕዝብ ይረግመዋል፤ አውጥቶ የሚሸጥ ግን በረከት ይጐናጸፋል።” ምሳሌ 11፥26 (አዲሱ መ.ት) 👌...በየትኛውም ሁኔታ ሕዝቡን ከጎዳን ትርፉ #መረገም ነውና!!
Показати все...
👍 1
✍️...ሰው ሁሉ ? 🔑 ለልጆች ስልክ ፣ ቴሌቭዥን አጠቃቀም፣ ከሶሻል ሚዲያ ጋር እንዴት ማሳለፍ እንዳለባቸው፣ ከእንስሶች ጋር እንዴት መኖር እንዳለባቸው መንገድ እናሳያቸዋለን እና ትራንስፖርት አጠቃቀም ሁሉ እንደ ቤተሰብ እናስተምራቸዋለን፤ በትምህርት ቤት እና በተለያየ መንገድ ደግሞ ገንዘብ ማግኛ መንገድን (ማንንም እና ምንንም ባላማከለ መንገድ)፣ ከማሽኖች ጋር እንዴት መስራት እንዳለባቸው በተለያየ መንገድ ይሰለጥናሉ። 🔑 ሰው እንደመሆናችን ግን በተለይ እድሚያችን እያደገ ብዙም የማናድግበት የህይወት ክፍል ከሰው ጋር እንዴት መኖር አለብን (ከሰው ጋር እንዴት እንኑር?) በሚለው ነው። ✨ ምክንያቱም በሚጠላሉ ሰዎች መካከል ከሚፈጠረው የጥላቻ መጎዳዳት ይልቅ በሚዋደዱ መካከልም እየተፈጠረ ያለው ጥላቻ የሌለበት የግጭት ቁስል እየፈጠረ ያለው ጥላቻ እየበለጠ ነው። ✨ ባለትዳሮች ሳይጠሉ አብረው መኖር አቃታቸው! ✨ ልጆች እየተፈላለጉ አብረው ማሳለፍ አልቻሉም! ✨ ወላጆች ከልጆች ጋር እየተዋደዱ መግባባት አቃታቸው! ✨ ጓደኛማቾች እየተሰበሰቡ ተጎዳድተው ይጨርሳሉ! 📌 ብዙ ወይም ሁሉም ሰው በሰው አዝኗል፣ እንደሌላው በሽታ በሐኪም ትዕዛዝ አይድንም። ለነገም እንዳይጎዳ የሚያደርግ መድሃኒት ማግኘት አልቻለም። 🔑 የቤተሰብ ስልጠና እና የማህበረሰብ ግንባታ ያስፈልገናል! ይሄንን የሚሰሩ ድርጅቶች ያስፈልጋሉ፣ እስከዛው ግን ምክሬን ስሙልኝ። 📌 የዘመኑ ትልቅ በሽታ መገለጫው ወይንም ምልክቱ: "ስማኝማ" "ስሚኝማ" "ስሙኝማ" የሚል ነው። እስኪ እኛም እራሳችን እንስማ። ከዚህ እንጀምር። ሌላው የበሽታው ምልክት ብዙ ነው። ግን እስኪ መጀመሪያ ይሄንን እናርም። ምንም አንናገር ሳይሆን፣ እስኪ ለመስማት ደግሞ ጆሯችንን ብቻ ሳይሆን ልባችንንም እንክፈት፣ ስክን እንበል። ደግሞ ስንሰማ ለወሬው የምንመልሰውን እያሰብን ሳይሆን ከልባችን እናዳምጥ። እንዴ... እኛ ብቻ እኮ አይደለንም ሐሳብ፣ አስተያየት፣ አመለካከት፣ ምክር ... ያለን። 📌 ይህንን አትርሱ እናንተ ብቻ አይደለም በመከራ እና በተለያየ መጎዳት የምታልፉት ምናልባትም እናንተ ከምታስቡት እና ከምታወሩት የበለጠ የሰው ጉድ አለ፤ ግዴላችሁም አንዳንዴ የሌላውን ቁስል እያከሙ መታከም አለ፤ እስኪ እንስማ። እስኪ ይሄንን ሰሞን ሰውን መስማት ተለማመዱ። በዛውም ሰው የመስማት አቅማችሁንም ተመልከቱ። ከቅዱስ ቃሉም እንካችሁ:- 💎 “የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ይህን አስተውሉ፤ 👉 ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፣ 👉 ለመናገር የዘገየ፣ 👉 ለቊጣም የዘገየ ይሁን፤” 📖 (ያዕቆብ 1፥19) ምንጭ:- ከpost
Показати все...
👏 1
✍...እንጀራን መተው! እንጀራ ሆነና የሰው ቁም ነገሩ አልቀመጥ አለ የሰው ልጅ በሀገሩ። "...እንጀራም ብር እያለ ለይገኘ ይችላል ፤ ግን የኑሮ መሠረት በእግዚአብሔር ላይ ከተገነባ እንጀራ በእግሩ ይመጣል። እግዚአብሔር ከሆነ የሰው ቁም ነገሩ ሊያገኝ ይመጣል እንጀራ ካገሩ። ምንጭ:- ደረጄ ሙላቱ ከጻፈው መተው ከሚተል የተወሰደ!
Показати все...
🥰 1
AYIKERM
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.