uk
Feedback
የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን

Відкрити в Telegram

ይህ ሥለኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ትክክለኛ መረጃ የሚያገኙበት የባለሥልጣኑ የቴሌግራም አካውንት ነው።

Показати більше
1 411
Підписники
+224 години
+257 днів
+8530 днів
Архів дописів
የፀረ-ተባይና ማዳበሪያ ምዝገባ ስራ በበየነ መረብ በመታገዝ በኦንላይን በኢ-ዶዜር አገለግሎት መስጠት መጀመሩ ተገለጸ፡፡ ***** የኢትዮጲያ ግብርና ባለስልጣን የፀረ-ተባይና ማዳበሪያ ምዝገባ በኤሌክትሮኒክ አገልግሎት (በኢ-ሰርቪስ ) በበየነ መረብ በኩል ለተገልጋዮች ተደራሽ ለማድረግ ጥር 23 ቀን /2016 ዓ.ም በሂልተን ሆቴል ከባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ወርክ ሾፕ በማዘጋጀት ተገልጋዮች በተገኙበት በይፋ አገልግሎቱን አስጀምሯል፡፡ የኢትዮጲያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ሃላፊ የሆኑት አቶ መሰሉ ዋጋው የወርክ ሾፑን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ለግብርና ምርት እድገት ግብዓት ከሆኑት መካከል ፀረ-ተባይና ማዳበሪያ ሲሆኑ በሀገራችን በከፍተኛ ደረጃ ጥቅም ላይ እንደሚውሉና ወደ ሀገር ውስጥም በብዛት እንደሚገቡ ገልጸው አገልግሎት አሰጣጡን በዲጂታል የታገዘ በማድረግና ግልጽ የሆነ አሰራር በመዘርጋት ጊዜን ፣ ሃብትን ፣ ጉልበትን ከመቆጠብ ባሻር አሰራሩን ቀልጣፋና ተአማኒ ያደርገዋል ብለዋል፡፡ አቶ መሰሉ አክለውም የዚህ የኢ-ሰርቪስ አገልግሎት ዋና አላማም የፀረ-ተባይና ማዳበሪያ ምዝገባ አሰራርን ግልፅነትና ተጠያቂነት ባለው መልኩ አገልግሎት በመስጠት መልካም አስተዳደርን በማስፈን የተገልጋዮችን እንግልት በመቀነስ እርካታ መፍጠር ነው ብለዋል፡፡ የክሮፕ ላይፍ አፍሪካ እና የሚድል ኢስት ዋና ዳይሬክተር በሆኑት በወሮ ስቴላ ሲሚዩ የሌሎች አፍሪካ አገራትን ተሞክሮ ፣ በፔራጎ ኢንፎርሜሽን ሲስተም አስተባባሪ በወ/ሮ ማህሌት ሀይለማርያም አገራዊ የኢ-ሰርቪስ አገልግሎትን በተመለከተ ለተሳታፊዎች የቀረቡ ሲሆኑ በፔራጎ ኢንፎርሜሽን ሲስተም ባለሙያ በሆነው በአቶ አቤል ተክላይ ደግሞ የኢ-ዶዜር አጠቃቀምን በተመለከተ ለተገልጋዮች ስልጠና ተሰጥቷል::በቀረቡት ገለፃዎችና ስልጠና ላይ ከተሳታፊዎች የገልፅነት ጥያቄዎችና አስተያየቶች ተነስተው ሰፊ ውይይት ተካሂዶ መግባባት ተደርሶባቸዋል :: የፀረ-ተባይና ማዳበሪያ ሪጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈጻሚ ደክተር በየነ ንጋቱ በበኩላቸው የኢትዮጲያ ግብርና ባለስልጣን መስሪያ ቤት በአዋጅ ከተሰጡት ተግባርና ሀላፊነት ውስጥ ፀረ-ተባይና ማዳበሪያዎች ፍቱንነታቸው ፣ ደህንነታቸው እና ውጤታማነታቸው ተረጋግጦ እንድመዘገቡና ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው አርሶና -አርብቶ አደሩ እንድጠቀምባቸው ማድረግ የስራ ክፍሉ ዋና ተግባር ነው ብለዋል:: ዶክተር በየነ አክለውም ከዚህ በፊት ይሰጥ ከነበረው የአገልግሎት አሰጣጥ ስረዓት በመውጣትና አገልግሎቱን በማዘመን በመላዉ ሀገሪቱ ለሚገኙ ተገልጋዮች ቀልጣፋ በሆነ መንገድ በኦንላይን ሲይሰተም ተደራሽ ለማድረግ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ፣ ከክሮፕ ላይፍ አፍሪካና ሚድል ኢስቲ እንድሁም ከፔራጎ ኢንፎርሜሽን ሲስተም ጋር በመሆን የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውንና ከዛሬው ቀን ጀምሮ የፀረ-ተባይና ማዳበሪያ ምዝገባ አገልግሎትን በኢ-ሰርቪስ ስረዓት ውስጥ በማሰገባት አገልግሎቱን በበየነ መረብ በመታገዝ በኢ-ዶዜር መስጠት እንደተጀመረ ገልጸዋል ፡፡

photo content
+5

የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ለእንስሳት ውጤቶች ላብራቶሪ ፍተሻ ማዕከል ሴት ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፤ ****** የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ለእንስሳት ውጤቶች ላብራቶሪ ፍተሻ ማዕከል ሴት ሰራተኞች ስርዓተ ፆታን ማካተትና ፆታዊ ትንኮሳን እንዲሁም ጥቃትን መከላከል ላይ በተመለከተ በደብረ ዘይት ከተማ ያደን ሆቴል የግንዛቤ ማስበጫ ስልጠና ሰጠ ። የባለስልጣኑ የስራ አመራር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አበበ ገለታ ሴቶችን ማንቃት ህብረተሰቡን ማንቃት ማለት ነው በማለት ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን የስልጠናው ዋና ዓላማም ሴቶች በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ በሴቶች ላይ የሚደረሰውን ፆታዊ ጥቃትና ትንኮሳ መከላከል ወሳኝ መሆኑን ለማስገንዘብ ነው ብለዋል። በስልጠናውን የባለስልጣኑ የሴቶች ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ትግስት ወንድማገኝ ፆታና ስርዓተ ፆታን ማካተት በሚል ርዕስ ገለፃ ያቀረቡ ሲሆን የሴቶች ፣ወጣቶችና ህጻናት ጉዳዮች አካቶ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሰይድ ኡመር ደግሞ ፆታዊ ትንኮሳና ጥቃትን መከላከል በሚል ርዕስ ላይ ገለፃ አድርገዋል። በቀረቡት ገለፃዎች ላይ የውይይቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳቦችና አስተያየቶችን አቀርበው ሰፊ ውይይቶች ተካሂደዋል። የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መሰሉ ዋጋው በበኩላቸው በቀረቡት ሀሳቦችና ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተው በተሰብሳቢዎቹ መካከል መግባባት ተደርሶ ውይይቱ ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ለእንስሳት ውጤቶች ላብራቶሪ ፍተሻ ማዕከል ሴት ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጠ፤ ****** የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ለእንስሳት ውጤቶች ላብራቶሪ ፍተሻ ማዕከል ሴት ሰራተኞች ስርዓተ ፆታን ማካተትና ፆታዊ ትንኮሳን እንዲሁም ጥቃትን መከላከል ላይ በተመለከተ በደብረ ዘይት ከተማ ያደን ሆቴል የግንዛቤ ማስበጫ ስልጠና ሰጠ ። የባለስልጣኑ የስራ አመራር መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አበበ ገለታ ሴቶችን ማንቃት ህብረተሰቡን ማንቃት ማለት ነው በማለት ንግግራቸውን የጀመሩ ሲሆን የስልጠናው ዋና ዓላማም ሴቶች በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ በሴቶች ላይ የሚደረሰውን ፆታዊ ጥቃትና ትንኮሳ መከላከል ወሳኝ መሆኑን ለማስገንዘብ ነው ብለዋል። በስልጠናውን የባለስልጣኑ የሴቶች ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ትግስት ወንድማገኝ ፆታና ስርዓተ ፆታን ማካተት በሚል ርዕስ ገለፃ ያቀረቡ ሲሆን የሴቶች ፣ወጣቶችና ህጻናት ጉዳዮች አካቶ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሰይድ ኡመር ደግሞ ፆታዊ ትንኮሳና ጥቃትን መከላከል በሚል ርዕስ ላይ ገለፃ አድርገዋል። በቀረቡት ገለፃዎች ላይ የውይይቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳቦችና አስተያየቶችን አቀርበው ሰፊ ውይይቶች ተካሂደዋል። የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ መሰሉ ዋጋው በበኩላቸው በቀረቡት ሀሳቦችና ጥያቄዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተው በተሰብሳቢዎቹ መካከል መግባባት ተደርሶ ውይይቱ ተጠናቋል።

ቀልጣፋና የተጠናከረ የሪጉላቶሪ ስርዓት ለመዘርጋት የታቀዱ ተግባራትን በብቃት መፈፀም ወሳኝ መሆኑ ተገለፀ። የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የ2016 በጀት ዓመት የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞ በተገኙበት ጥር 17 ቀን 2016 ዓ/ም በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ግምገማ ተካሄደ፡፡ የባለስልጣኑ የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም በስትራቴጅክ ጉዳዮች ስራ አስፈጻሚ በወ/ሮ መሰረት አበባው አማካኝነት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡ በውይይቱም አብዛኞቹ መሪ ስራ አስፈፃሚዎች የተሻለ አፈጻጸም የታየባቸው ተግባራት ተጠናከረው መቀጠል እንዳለባቸው እንዲሁም አንዳንድ መሪ ስራ አስፈፃሚዎች ደግሞ ዝቅተኛ አፈፃፀም የተመዘገበባቸው ስራዎች እንዳሉ ለዚህ ደግሞ የሀገር ውስጥና የውጭ የገበያ ፍላጎት ተፅዕኖ እንዳሳደረ እንዲሁም በየደረጃው ባሉ አመራሮች ሊፈቱ ይገባቸዋል ያሏቸውን ችግሮች በውይይቱ ላይ ተነስቷል፡፡ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእንሰሳት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል የ6 ወር እቅድ አፈጻጸማችን የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት ቢሆንም በአንዳንድ ተግባራት ላይ የአፈጻጸም ክፍተት ታይቷል ያሉ ሲሆን ለቀጣይ ስራዎቻችን ጥሩ አፈፃፀም ያመጡትን በማስቀጠልና ዝቅተኛ አፈጻፀም የታየባቸውን ደግሞ የማካካሻ እቅድ በማውጣት እንዲሁም በቀጣይ እቅድ አካተን በመስራት የተቋማችንን አፈጻጸም ውጤታማ ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእፅዋት ሪጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዳለ ሀብታሙ በበኩላቸው የተቋሙ አፈጻጸም ባለው ግምገማ የተሻለ ቢሆንም እንደ ተቆጣጣሪ ተቋም አገልግሎት ስንሰጥ በፍትሃዊነትና በታማኝነት ከብልሹ አሰራር በጸዳ መልኩ ሁላችንም እየሰራን ነወይ በማለት እራሳችንን መፈተሸና የታዩ ክፍተቶችን በመሙላት ለቀጣይ ስራዎች ዝግጁ መሆን እንደሚገባ እንዲሁም ስራን ከንክኪ ነፃ ለማድረግ በኦን-ላይን ሲስተም ውስጥ ያልገቡ ስራዎችን ለማስገባት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተው ገልፀዋል፡፡ አቶ ወንዳለ አያይዘውም የኢንስፔክሽን ስራዎችን ለማጠናከር በመደጋገፍና በመግባባት መስራት እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡ በመጨረሻም የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ የቀረበው ሪፖርት አፈፃፀሙ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸሻለ የመጣ ቢሆንም በቀጣይ ቀልጣፋና የተጠናከረ የሪጉላቶሪ ስርዓት በመዘርጋት የታቀዱ ተግባራትን በብቃት መፈፀም እንደሚገባና ለዚህ ደግሞ እያንዳንዳችን ለአንድ ተቋማዊ ለውጥ እስከተሰለፍንና ሀላፊነት እስከተጣለብን ድረስ ያለንን ሀብት ተጠቅመን ክፍተት የታየባቸው ስራዎችን የቀጣይ እቅድ አካል በማድረግ በመደጋገፍ መስራት ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን በተጨማሪም ሪጉላቶሪ ስርዓቱ መሰረታዊ ለውጥ ማምጣትና ወደ ተግባር መግባት እንዳለበት ገልፀው በዚህም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ውይይቱ ተጠናቋል፡

የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ከእንስሳት መድኃኒትና ህክምና መሳሪያ አስመጪ፤አከፋፋይ ና ላኪ ድርጅቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ፤ ****** የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ከእንስሳት መድኃኒትና ህክምና መሳሪያ አስመጪ፤አከፋፋይ ና ላኪ ድርጅቶች ጋር በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲቱዩት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የምክክር መድረክ አካሂደ፡፡ የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ሲሆኑ የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማ ከእንስሳት መድኃኒትና ህክምና መሳሪያ አስመጪ፤አከፋፋይ ና ላኪ ድርጅቶች ምርቶቻቸው ላይ ጥራት፣ ደህንነትና ፈዋሽነትን በማስጠበቅ በሰው፣ በእንስሳትና በአካባቢ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እንዲያስችል ህግና መመሪያውን ተከትለው እንዲሰሩ ግንዛቤን ለመፍጠር ያለመ ስለሆነ ቀልጣፋና ዘመናዊ አሰራር እንዲኖር ደንበኞቻችን የተዘጋጁ መመሪያዎችንና ህጎችን አውቀው በተግባር ላይ ማዋል የሚገባ በመሆኑን አስገንዝበው የምክክር መድረኩ በይፋ የተጀመረ መሆኑን አብስረዋል፡፡ የእንስሳት መድኃኒት ሪጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሰለሞን ከበደ ከእንስሳት መድኃኒትና ህክምና መሳሪያ አስመጪ፤አከፋፋይ ና ላኪ ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያን ለምክክር መድረክ ተሳታፊዎች ያቀረቡ ሲሆን በዚህ ህግ እና መመሪያና መሰረት ባለስልጣን መ/ቤቱ የእንስሳት መድኃኒትና ህክምና መሳሪያ አስመጪ፤አከፋፋይ ና ላኪ ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ ውጪ ማስተናገድ እንደማይቻል አውቀው ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡ በተለይም አገር ውስጥ ለሚሸጡና ለሚያከፋፍሉ ድርጅቶች የአከመቻቸት ሂደት የሙቀትና የቅዝቃዜ መጠኑን መለኪያ ቴርሞ ሜትር ፣ መድኃኒቱ የተሰራበትንና የሚያበቃበትን ጊዜ የሚገለፅ ፅሑፍ መኖሩን፤ የሚወገዱ መድኃኒቶች አከመቻቸት እንዲሁም ንፅህና አጠባበቅን አስመልክቶ ህግና መመሪያውን ተከትለው መስራት እንዳለባቸው አስረድተው ከህግና መመሪያው ውጪ ለሚሰሩ ድርጅቶችና ባለሙያዎች የቃልና የፅሑፍ ማስጠንቀቂ፣ የእገዳ እንዲሁም የስረዛ ቅጣቶች እንደሚጣልባቸው አብራርተዋል፡፤ የእንስሳት ሪጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬከተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል በበኩላቸው ባለፉት የምክክር መድረረኮች ላይ ጥሩ ግንዛቤ የተወሰደበትና ተነሳሽነትን የፈጠረ መሆኑን ገልፀው በአሁኑ መድረክም በተሻለ ሆኔታ ቀጣይነት እንዲኖረው የሚያስችል መሆኑን በመግለፅ በተለይም በመድኃኒት አከመቻቸት ላይ ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባ አሳስበው ለስራ ማነቆ የሆኑና ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸውን ህግና መመሪያዎችንም ወስደን በማስተካከል የጋራ ተግባቦትን በመፍጠር ለቀጣይ ስራ ውጤታማነት በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም የቀረቡ ገለፃዎችን መሰረት በማድረግ በመድረኩ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን በተለይ ምላሽ ያስፈልጋቸዋል ለተባሉ ጥያቄዎች በገለፃ አቅራቢዎች ምላሽ ከተሰጠ በኋላ ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ከተሳታፊዎች የተነሱ ገንቢ ሃሳቦችን በግብዓትነት በመውሰድ የቀጣይ ስራችን አካል አድርገን የምንሰራቸው መሆኑን በመግለፅ የተቋማችንን የእንስሳት መድኃኒትና ህክምና መሳሪያ አስመጪ፤አከፋፋይ ና ላኪ ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያን ማወቅና በተግባር ላይ በማዋል የበኩላችሁን ኃላፊነት መወጣጥ ይገባል ብለዋል፡፡ በዚህ ማጠቃለያ ሃሳብ ላይ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ከእንስሳት መድኃኒትና ህክምና መሳሪያ አስመጪ፤አከፋፋይ ና ላኪ ድርጅቶች ጋር የምክክር መድረክ አካሄደ፤ ****** የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ከእንስሳት መድኃኒትና ህክምና መሳሪያ አስመጪ፤አከፋፋይ ና ላኪ ድርጅቶች ጋር በኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲቱዩት የመሰብሰቢያ አዳራሽ የምክክር መድረክ አካሂደ፡፡ የምክክር መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ሲሆኑ የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማ ከእንስሳት መድኃኒትና ህክምና መሳሪያ አስመጪ፤አከፋፋይ ና ላኪ ድርጅቶች ምርቶቻቸው ላይ ጥራት፣ ደህንነትና ፈዋሽነትን በማስጠበቅ በሰው፣ በእንስሳትና በአካባቢ ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ እንዲያስችል ህግና መመሪያውን ተከትለው እንዲሰሩ ግንዛቤን ለመፍጠር ያለመ ስለሆነ ቀልጣፋና ዘመናዊ አሰራር እንዲኖር ደንበኞቻችን የተዘጋጁ መመሪያዎችንና ህጎችን አውቀው በተግባር ላይ ማዋል የሚገባ በመሆኑን አስገንዝበው የምክክር መድረኩ በይፋ የተጀመረ መሆኑን አብስረዋል፡፡ የእንስሳት መድኃኒት ሪጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሰለሞን ከበደ ከእንስሳት መድኃኒትና ህክምና መሳሪያ አስመጪ፤አከፋፋይ ና ላኪ ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያን ለምክክር መድረክ ተሳታፊዎች ያቀረቡ ሲሆን በዚህ ህግ እና መመሪያና መሰረት ባለስልጣን መ/ቤቱ የእንስሳት መድኃኒትና ህክምና መሳሪያ አስመጪ፤አከፋፋይ ና ላኪ ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያ ውጪ ማስተናገድ እንደማይቻል አውቀው ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ አብራርተዋል፡፡ በተለይም አገር ውስጥ ለሚሸጡና ለሚያከፋፍሉ ድርጅቶች የአከመቻቸት ሂደት የሙቀትና የቅዝቃዜ መጠኑን መለኪያ ቴርሞ ሜትር ፣ መድኃኒቱ የተሰራበትንና የሚያበቃበትን ጊዜ የሚገለፅ ፅሑፍ መኖሩን፤ የሚወገዱ መድኃኒቶች አከመቻቸት እንዲሁም ንፅህና አጠባበቅን አስመልክቶ ህግና መመሪያውን ተከትለው መስራት እንዳለባቸው አስረድተው ከህግና መመሪያው ውጪ ለሚሰሩ ድርጅቶችና ባለሙያዎች የቃልና የፅሑፍ ማስጠንቀቂ፣ የእገዳ እንዲሁም የስረዛ ቅጣቶች እንደሚጣልባቸው አብራርተዋል፡፤ የእንስሳት ሪጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬከተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል በበኩላቸው ባለፉት የምክክር መድረረኮች ላይ ጥሩ ግንዛቤ የተወሰደበትና ተነሳሽነትን የፈጠረ መሆኑን ገልፀው በአሁኑ መድረክም በተሻለ ሆኔታ ቀጣይነት እንዲኖረው የሚያስችል መሆኑን በመግለፅ በተለይም በመድኃኒት አከመቻቸት ላይ ትኩረት ሊደረግበት እንደሚገባ አሳስበው ለስራ ማነቆ የሆኑና ማስተካከያ የሚያስፈልጋቸውን ህግና መመሪያዎችንም ወስደን በማስተካከል የጋራ ተግባቦትን በመፍጠር ለቀጣይ ስራ ውጤታማነት በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡ በመጨረሻም የቀረቡ ገለፃዎችን መሰረት በማድረግ በመድረኩ ተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች የተሰጡ ሲሆን በተለይ ምላሽ ያስፈልጋቸዋል ለተባሉ ጥያቄዎች በገለፃ አቅራቢዎች ምላሽ ከተሰጠ በኋላ ክቡር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ከተሳታፊዎች የተነሱ ገንቢ ሃሳቦችን በግብዓትነት በመውሰድ የቀጣይ ስራችን አካል አድርገን የምንሰራቸው መሆኑን በመግለፅ የተቋማችንን የእንስሳት መድኃኒትና ህክምና መሳሪያ አስመጪ፤አከፋፋይ ና ላኪ ድርጅቶች የብቃት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት አሰጣጥና ቁጥጥር መመሪያን ማወቅና በተግባር ላይ በማዋል የበኩላችሁን ኃላፊነት መወጣጥ ይገባል ብለዋል፡፡ በዚህ ማጠቃለያ ሃሳብ ላይ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች! እንኳን ለጌታችን፣ ለመድኃኒታችን፣ ለእየሱስ ክርስቶስ ለከተራና ለጥምቀት በዓል በሠላምና በጤና አደረሳችሁ በማለት በዓሉ የሠላም፣ የደስታ፣ የፍቅርና የመተሳሰብ እንዲሆንላችሁ ይመኛል፡፡ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን

ቅንጅታዊ አሰራር ለአበባ እርሻ ልማት ምርታማነትና ለአካባቢ አያያዝ ስርዓት ውጤታማነት ጉልህ አስተዋፅዖ አለው፡፡ /አዳማ፣ ታህሳስ 30 ቀን 2016 ዓ.ም፣ ግብርና ሚኒስቴር/ የትግበራ ኦዲት ግኝትን መሰረት በማድረግ የአበባ እርሻ ልማት ምርታማነትና የአካባቢ አያያዝ ስርዓት ውጤታማነት ለማሻሻል በግብርና ሚኒስቴር እና በፕላንና ልማት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች አስተባባሪነት ባለድርሻ አካላት ተወያዩ፡፡ የአበባ እርሻ ልማት ምርታማነትና የአካባቢ አያያዝ ሥርዓት ውጤታማነት የትግበራ ኦዲት ግኝት ሪፖርት እና የባለድርሻ አካላት (የግብርና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን፣ የአካባቢ ባለስልጣን፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር፣ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን) ሚና ዙሪያ ፅሁፍ ቀርቦ ተሳታፊዎች በስፋት ተወያይተውበታል፡፡ በውይይቱም ላይ ብዙ ክፍተቶች የተነሱ ሲሆን ባለድርሻ አካላት በቅንጅት አለመስራት፤ አንዳንድ አካላት የስራቸው አካል አድረገው አለመውሰድ፤ ለአበባ ልማት የሚውሉ ግብዓቶችን በአግባቡ አለመጠቀም፤ እንዲሁም የፖሊሲ፣ ኢኮኖሚያዊና ቴክኒካል ጉዳዮችን ሀገርን በሚጠቅም አግባብ መፈፀም አለመቻል በዋናነት ተነስተዋል፡፡ በግብርና ሚኒስቴር የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መለስ መኮንን (ደ/ር) ሆርቲካልቸር ለውጪ ምንዘሬ ግኝት፣ ለኢንዱስትሪ ግብዓት እና ለስራ ዕድል ፈጠራ ጉልህ አስተዋፅዖ የሚያበረክት ዘርፍ በመሆኑ በትኩረት መስራት አለብን ብለዋል፡፡ ዘርፉን በቀጣይነት ውጤታማ ለማድረግ በኦዲት ግኝቶችና በተቀመጡ አቅጣጫዎች መሰረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው የድርሻቸውን እንዲወጡ አሳስበው በጋራ የሚሰራባቸውን ጉዳዮች የሚለይ የቴክኒክ ኮሚቴም እንደሚቋቋም ሚኒስትር ዴኤታው ገልፀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ በበኩላቸው ለቅንጅታዊ አሰራር ውድቀት በጋራ የሚሰራበት ጉዳይ ከመደበኛ ስራ ተለይቶ አለመቀመጥ መሆኑንና የአበባ እርሻ ልማት ብዙ ተለፍቶበት እዚህ መድረሱን አንስተው በኦዲት ግኝት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የድርሻቸውን በቁርጠኝነት እንደሚወጡ ተናግረዋል፡፡ ካሜራ፥- ዮዲት እንዳለው ዘጋቢ፥- ሸምስህድን ዩሱፍ

ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ !
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ !