uk
Feedback
የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን

የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን

Відкрити в Telegram

ይህ ሥለኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን ትክክለኛ መረጃ የሚያገኙበት የባለሥልጣኑ የቴሌግራም አካውንት ነው።

Показати більше
1 411
Підписники
+224 години
+257 днів
+8530 днів
Архів дописів
አቶ መሰሉ : እኔም አመሰግናለሁ

ህዝብ ግንኙነት፡- ባለስልጣን መ/ቤቱ የህግ ማዕቀፎችን አካቶ ከመስራት አኳያ ያለው አሰራር ምን ይመስላል ? አቶ መሰሉ፡- የባለስልጣኑ ሥራዎች በሕግ አግባብ እንዲሰሩ ግብ ተይዞ የህግ ረቂቅ ማዘጋጀት፣ የህግ ረቂቅ ማጸደቅ፣ የህግ ግንዛቤ ማሳደግ፣ ውጤታማ የህግ አፈጻጸም፣ ውጤታማ የህግ ድጋፍ፤ ግምገማና ክትትል፣ እየተሰራ ይገኛል፡፡ የባለስልጣኑን የሀግ ማዕቀፍ ፍላጎቶችን እና ክፈተቶችን በመለየት ከተለያዩ ስራ አስፈጻሚዎች ጋር በመቀናጀት አዋጅ፣ ደንብና መመሪያ አስፈጻሚ የህግ ድጋፍ እንዲደርግ እገዛ እያደረገ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት 2 አዋጅ፣ 1 ደንብ እና 3 መመሪያ ለማጸደቅ በእቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ህዝብ ግንኙነት፡- የተቋሙን ተልዕኮ ከማሳካትና ችግሮችን ከመለየት እንዲሁም መፍትሔ እንዲያገኙ ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ ከማድረግ አኳያ እየሰራ ያለው ስራ ምን ይመስላል? አቶ መሰሉ፡- የተቋሙ ተልዕኮ የአካባቢን ደህነነት በማስጠበቅ የግብርና ምርት፤ ግብዓት፣ ቴክኖሎጂ የግብርና ኤክስቴንሽን አገለግሎት ጥራት፣ ደህንነት፣ ጤናማነት እና ፍቱንነት ማረጋገጥ፣ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ገበያን ለማሻሻል ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓትን በመገንባት ለአገሪቱ የሚበጀውን ጥቅም ማስጠበቅ ስለሆነ ከሚመለከታቸው ስራ አስፈጻሚዎች ሲረቀቅ ከህግ አገልግሎት ስራ ጋር በመሆን ችግሮች እየተለዩ በስራ አመራር ማናጅመንት ውሳኔ እየተሰጠባቸው የተፈቱ ብዙ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የማዕከላትና የጣቢያ ኃላፊዎች ምደባ፤ ምደባ ያላገኙ ሰራተኞች እንዲመደቡ፣ የተቋሙን ሀብት በአግባብ መጠቀም ለምሳሌ የነዳጅና የተሸከርካሪ አጠቃቀም፤ የእንስሳት ኳራንቲን አገልግሎት አሰጣጥ የመሳሰሉት ችግሮች መፍትሄ እንዲሰጣቸው ተደርጓል፡፡ ህዝብ ግንኙነት፡- በባለስልጣን መ/ቤቱ የሚፈጠሩ ህግ -ጥሰቶችንና ብልሹ አሰራሮችን ከመከላከልና በተለይም ለሙስናና ለብልሹ አሰራር የሚያጋልጡ የአሰራር ሂደቶችን ወደ ግልፅና ተጠያቂነት ከማምጣት አኳያ ምን እየተሰራ ነው ? አቶ መሰሉ፡- በባለስልጣን መ/ቤቱ የሥነ ምግባር ደንቦች እና የፀረ ሙስና ሕጎች በማክበር ከሙስና የፀዳ አሰራርና መልካም አስተዳዳር እንዲሰፍን ግብ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ይህን ለማሳካት በ3 ቁልፍ ውጤት አመልካች ታቅዶ እየተሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት የሥነ ምግባር የሙስና ተጋላጭነት ስጋትን መቀነስ እና የሙስና መረጃ አስተዳዳር ውጤታማነትን የማረጋገጥ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ፡፡ ህዝብ ግንኙነት፡- የተቋሙ ተልዕኮ ውጤታማ እንዲሆን ከሚመለከታቸው የውስጥና የውጭ አካላት ጋር ተናቦ ከመስራት አኳያ ያለው ሚና ምን ይመስላል? አቶ መሰሉ፡- የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት ከባለድርሻ አካላትና ተገልጋዮች ጋር የምክክር መድረክ ተካሂዷል፡፡ ውይይት መድረኩ ቀጣይ መሆን ስላለበት ላኪና ተቀባይአገራትን፣ ባለድርሻ አካላትንና ተገልገዮችን በመለየት የተቋሙን ራዕይ፤ ተልዕኮ እና የአሰራር የህግ ማዕቀፍ ማስተዋወቅ ቅድሚያ ሚሰጠው ስራ ነው፡፡ በመሆኑም ወደ ኢትዮጵያ ላኪ አገራት ቁጥር 45 እና ከኢትዮጵያ ተቀባይ አገራት ቁጥር 28 አገሮች እንደሆኑ ተለይተዋል፡፡ ከተገልጋዮች አንጻር ሲታይ አምራች 105፣ ላኪ 150 እና አስመጭ 249 ተቋማት ተለይተዋል፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ ለተቋሙ ስራ ጉልህ ድርሻ ያላቸው 32 ዋና ባለድርሻ አካላት፣ 14 መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ 12 የሙያ ማህበራትና 2 አገልግሎት ሰጭ ደርጅቶች ተለይተዋል፡፡ ከእነዚህ ድርችቶች ጋር የውይይት መድረክ ለማዘጋጀት በሂደት ላይ እንገኛለን፡፡ ህዝብ ግንኙነት፡- ጽ/ቤቱ በስሩ ለሚገኙ ስራ አስፈፃሚዎች ድጋፍና ክትትል ከማድረግ አኳያ ያለው የስራ እንቅስቃሴ ምን ይመስላል? አቶ መሰሉ፡- በፅ/ቤት ስር ያሉ ስራ አስፈጻሚዎች የበጀት አመቱ እቅድ ቁልፍ ውጤት አመልካች እቅድ መሰረት ተደርጎ እንዲታቀድ መነሻ ሀሳብ በጽሁፍ የመስጠት ስራ ተሰርቷል፡፡ በስራ አስፈጻሚዎች የታቀደው እቅድ በስትራቴጅክ ጉዳዮች ሥራ አስፈጻሚ አስተያይት እንዲሰጥበት በማድረግ በጋር በመገምገም ጸድቆ ወደ ስራ እንዲገባ ሆኖል፡፡ አፈጻጸሙም በ1ኛው እና በ2ኛው ሩብ ዓመት ከስራ አስፈጻሚዎች ጋር በመገምገም ለቀጣይ አቅጣጫ አስቀምጠናል፡፡ ስራ አስፈጻሚዎች የተሰጣቸውን ተግባርና ኃላፊነት ከተጠያቂነት ጋር ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ያልተማከለ አሰራር እንዲከተሉ የማድረግ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ከሌሎች ስራ አስፈጻሚዎች ጋር በቅንጅት ስራ ለመስራት የጽ/ቤት ኃላፊውን እገዛ በሚጠይቁ ስራዎች ላይ ድጋፍ እየተሰጠ ይገኛል፡፡ ህዝብ ግንኙነት፡- በመጨረሻ ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልዕክት ካለ ? አቶ መሰሉ፡- የአንድ ተቋም ስራ ውጤታማ የሚሆነው ሁሉም በተመደበበት ስራ በትብብር መንፈስ በትጋት ሲሰራ መሆኑ ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ሁላችንም ከአድሎአዊ አሰራር ነጻ በመሆን፤ ብልሹ አሰራርን በመጸየፍና ሀብትን በቁጠባ በመጠቀም ለውጤት እንስራ፡፡ ህዝብ ግንኙነት፡- ስነበረን ቆይታ ከልብ እናመሰግናለን፡፡

"የአንድ ተቋም ስራ ውጤታማ የሚሆነው ሁሉም በተመደበበት የስራ መስክ በትብብር መንፈስ በትጋት ሲሰራ ነው!" ******** አቶ መሰሉ ዋጋው ግብርና ባለስልጣን ጽ/ቤት ሀላፊ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በግብርና ዘርፉ የተጠናከረ ሬጉላቶሪ ስርዓት በመዘርጋትና በመተግበር በዓለም አቀፍና በአገር አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ በሰው፣ በእንስሳትና በእጽዋት ጤና እንዲሁም በአካባቢ ላይ የሚደርሰውን ጉዳትና ተጽዕኖ እንዲቀንስ ወይም እንዲወገድ የማስቻል ዓላማ ይዞ የፌደራል መንግስት የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር በመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1263/2014 አንቀፅ 45 ንኡስ አንቀፅ 1 መሰረት የተቋቋመ የፌደራል መ/ቤት ነው፡፡ በዚህም መሰረት ይህንን ዓላማና ተልዕኮ ከግብ ለማድረስ የህግ ማዕቀፎችን አካቶ መስራት፣ ሴቶች በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ እንዲሁም በፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ማሳደግ፣ የተቋሙ የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነት የሚያረጋግጥ የረዥም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ የውስጥ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ዕቅድ እንዲዘጋጅ በማድረግ ፤አፈጻጸሙንም መከታተል፤ ለብልሹ አሰራር የሚዳርጉ የአሠራር ዘዴዎችን ለማስተካከል / ለመድፈን/ የሚያስችሉ የአሰራር ዘዴዎችና ስልቶች በማጥናት ለዋና ዳይሬክተሩ ማቅረብ፣ ሲወሰንም ተግባራዊ ማድረግ እንዲሁም የባለስልጣን መሥሪያ ቤቱን የህዝብ ግንኙነትና ስርዐተ ተግባቦት (communication) ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ራዕይ፤ተልዕኮና አላማ/ግብ ጋር በተስማማ መንገድ ለመከወን የሚያስችል መርሃ ግብር መዘጋጀቱን የመከታተልና የማስተባበር ስራዎችን የሚሰሩት የባለስልጣኑ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መሰሉ ዋጋው በዚህ ወር የጋዜጣ እትማችን ላይ መረጃዎችን እያካፈሉን እንግዳችን ሆነው ቆይተዋል፡፡ መልካም ንባብ ፡፡ ህዝብ ግንኙነት፡- የባለስልጣኑ ፅ/ቤት ሀላፊ የሚያከናውናቸው ዋና ዋና ተግባራት ምንድን ናቸው ? አቶ መሰሉ፡- የጽ/ቤት ሀላፊ ተጠሪነቱ ለዋና ዳይሬክተር ሲሆን ጽ/ቤቱ በርካታ ስራዎችን ያከናውናል፡፡ ከነዚህም መካከል በዓመታዊ ዕቅዱ ላይ በአፈጻጸም ሂደት ውስጥ የሚያስፈልግ በጀትና ግብዓቶች የዕቅድ አካል ተደርገው መዘርዘራቸውን ያረጋግጣል፤ የባለሥልጣኑን የእለት ተእለት ተግባራት ለማከናወን ከተለያዩ የዋና እና ደጋፊ ሥራ ሂደቶች/ ስራ አስፈፃሚዎች/ እንዲሁም የተገልጋይ ጉዳዮችን ማስተናገጃ ሥርአት ይዘረጋል፣ በመስሪያ ቤቱ የሚወጡ አዋጆችን፤ደንቦች ፤ መመሪያዎች እና ስምምነቶች ከሀገሪቱ ህጎች ጋር የማይጋጩ መሆኑን ያረጋግጣል፤ የህግ ማእቀፎችን እና የአሰራር ስርዓቶችን ዝግጅት በማስተባበር ይመራል፣ የተቋሙን ተልዕኮ ከማሳካት አንጻር ችግሮችን በመለየት ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ችግሩ እንዲፈታ ያደርጋል፣ ከኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ቁጥጥር ዓላማ አንጻር ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ተግባራት በመለየትና የስጋት ተጋላጭነት ያላቸውን በማስቀመጥ የስጋት ማምከኛ ስርአት አዘጋጅቶ ለዋና ዳይሬክተሩ ያቀርባል፤ የመሥሪያ ቤቱን የህዝብ ግንኙነትና ስርዐተ- ተግባቦት(communication) ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ራዕይ፤ተልዕኮና አላማ/ግብ ጋር በተስማማ መንገድ ለመከወን የሚያስችል መርሃ ግብር መዘጋጀቱን ይከታተላል፤ ተቋሙን የሚመለከቱ፤ በአገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጁ ሁነቶችንና መድረ ኮችን(ሲምፓዚየሞች፣ኤግዚቢሽኖች፣ ኮንፍረንሶች፣ የምክክር መድረኮች ወዘተ) በቅድሚያ ለይቶ በዕቅድ እንዲያዙ በማድረግ መድረኮቹንም ለተቋማዊ የገጽታ ግንባታ ሥራ ጠቀሜታ መዋላቸውን ያረጋግጣል፤ የተቋሙ የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነት የሚያረጋግጥ የረዥም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ የውስጥ ኦዲትና ኢንስፔክሽን ዕቅድ እንዲዘጋጅ በማድረግ ፤አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤ ለብልሹ አሰራር የሚዳርጉ የአሠራር ዘዴዎችን ለማስተካከል / ለመድፈን/ የሚያስችሉ የአሰራር ዘዴዎችና ስልቶችን በማጥናት ለዋና ዳይሬክተሩ ያቀርባል፣ ሲወሰንም ተግባራዊ ያደርጋል፤ የባለስልጣን መ/ቤቱ ሴቶች፣ወጣቶችና አካል ጉዳተኞች በሀገሪቱ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማኀበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ በንቃት ለመሳተፍ የሚያስችሏቸው ዕድሎች የተመቻቹላቸው መሆኑን ለማረጋገጥ የሚያስችል ስትራቴጂካዊ ዕቅድ ይነድፋል፣ ያስፈጽማል፤ ከዚህ ባለፈም ሴት ሠራተኞችን ለማብቃትና በውሳኔ ሰጪ የሥራ ቦታዎች ላይ እንዲመደቡ ለማድረግ የሚያስችሉ ስልቶችን ይቀይሳል፣ በቅጥር፣ በደረጃ እድገት፣ በዝውውር፣ በድልድል፣ በትምህርትና ሥልጠና አፈጻጸም የተጨማሪ ድጋፍ እርምጃዎች ተጠቃሚ የሚያደርጉ የአሰራር ስርአቶችን መተግበራቸውን ይከታተላል፤ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ በተለይም ወላጆቻቸውን ያጡና ተንከባካቢ የሌላቸው ሕጻናት ፍቅር፣ ክብካቤ፣ ድጋፍ እና ጥበቃ አግኝተውና መሠረታዊ ፍላጎታቸው ተሟልቶ እንዲያድጉ በሴክተሩ ድጋፍ የሚያገኙበትን ሁኔታዎችን ያመቻቻል፤ በባለስልጣኑ ምቹ የህጻናት ማቆያ እንዲኖር፤ አስፈላጊ መገልገያ ቁሳቁሶችና ተንከባካቢዎች እንዲሟሉ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤ ተፈጻሚነቱንም ይቆጣጠራል፤ በበላይ አመራሩ ውሳኔ የሚያስፈልጋቸውን ጉዳዮች ከህግና መ/ቤቱ ከተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት አንፃር በመለየት በማስረጃ ተደግፎ እንዲቀርብ በማድረግ፣ ተፈጻሚነቱን ይከታተላል፣ ውጤቱንም ለአመራሩ ያቀርባል፣ ከዚህ ባለፈም የበላይ አመራሩ ለሚካፈሉባቸው ብሔራዊና ዓለም አቀፋዊ ስብሰባዎች የሚያስፈለጉ መረጃዎችንና መግለጫዎችን ከሚመለከታቸው ጋር በመሆን ተጠናቅረው እንዲቀርቡ ያደርጋል፣ የአደረጃጀትና የአሰራር ሥርዓት እንዲሻሻል አህጉራዊና አለማቀፋዊ ልምዶችና ነባራዊ እውነታዎች ተዳሰው የሚቀመሩበትንና ከነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በማዛመድ ምርጥ ተሞክሮዎችን ይቀምራል፣ ያስፋፋል። የባለስልጣኑ ተልዕኮ ውጤታማ እንዲሆን ከሚመለከታቸው የውስጥና የውጭ አካላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ውጤታማ ስራ ይሰራል፤ በተጨማሪም የባለስልጣኑ ተልዕኮ ውጤታማ እንዲሆን ከሚመለከታቸው የውስጥና የውጭ አካላት ጋር ግንኙነት በመፍጠር ውጤታማ ስራ ይሰራል፤ በተጨማሪም ባለሥልጣኑ ከመንግሥት፣ ከፕሬስ፣ ከባለድርሻ አካላት፤ ከተገልጋዮች እና ከማኅበረሰብ ጋር ያለውን የግኙነት በመከታተል፤ ውጤቱንም ለዋና ዳይሬክተሩ ያቀርባል፤ የዕቅድና ፕሮግራም ክንውን እና አጠቃላይ የበጀት አጠቃቀምን አስመልክቶ አፈጻጸሙን በጋራ ገምግሞ፣ አፈጻጸሙንም ያረጋግጣል፤ እንዲሁም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለሚቀርቡ ጥቆማዎችና ቅሬታዎች ወቅታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ለባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር በማቅረብ፤ ወቅታዊና ትክክለኛ ምላሽ እንዲሰጥበት በማድረግ አፈፃጸሙን ይከታተላል፤ ጽ/ ቤቱን አስመልክቶ በየጊዜው ለበላይ አካላትና ለተለያዩ መ/ ቤቶች የሚቀርቡ ዕቅዶችና ሪፖርቶች ወቅታቸውን ጠብቀው መቅረባቸውን በመከታተል፣ ተፈጻሚ እንዲሆን ያደርጋል፤ በባለስልጣን መ/ቤቱና በባለድርሻ አካላት የሚደረጉ የፕሮቶኮል ስምምነት ሰነዶችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን ያዘጋጃል፣ ያስፈጽማል፣ የባለስልጣን መ/ቤቱ ስራ ማስፈጸሚያ መመሪያዎችና ስምምነቶች ተግባራዊ መሆናቸውን ይከታተላል እንዲሁም በሥራ ክፍሉ ውስጥ ጠንካራ የስራ ባህልና ተነሳሽነት እንዲፈጠርና በዘላቂነት እንዲቀጥል ተገቢውን አመራር በመስጠት የክፍሉን ሠራተኞች የሥራ አፈፃፀም በየምዕራፉ ይገመግማል ፣የተጠቃለለ የግምገማ ሪፖርቶችን ያቀርባል ማለት ነው ::

የፀረ -ተባይና ማዳበሪያ የበየነ መረብ ምዝገባ አገልግሎት ለማግኘት E-dossier/E-SERVICE/:www .e-services.gov.et

በኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣናት የእንስሳት ምርትና ግብዓት ጥራትምርመራ ማዕከል አመራሮችና ሠራተኞች ከዕዳ ወደ ምንዳ በሚል ወቅታዊና አገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተጀመረ

"ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል መሪ ሃሳብ ሲሰጥ የነበረው ስልጠና ተጠናቀቀ ፡፡ ********* የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች "ከዕዳ ወደ ምንዳ" በሚል መሪ ሃሳብ ጥር 29/2016 ዓ/ም በተቋሙ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የጀመሩትን ስልጠናና መግባባት ላይ በመድረስ በውጤት አጠናቀቁ ። የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሰሉ ዋጋው ሀብት በመፍጠር ጉዟችን የተመዘገቡ ስኬቶች ፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች የሚለውን የመወያያ ሰነድ በገለጻ ያቀረቡ ሲሆን የባለስልጣኑ የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ አቶ አዲስ እጅጉ ደግሞ በኢትዮጵያ አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት በተደረገው ጥረት የመንግስት ሰራተኛው ሚና የሚለውን የመወያያ ሰነድ በተመሳሳይ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡ የስልጣናው ተሳታፊዎችም በበኩላቸው በሁለቱም የስልጠና ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ተዘጋጅቶ የቀረበው ሰነድ ከአቀራረቡ ጀምሮ ጥሩና ወቅታዊ መሆኑን ገልጸው መንግሰት እንደዚህ አይነት ስልጠናዎችን በየጊዜው ለሰራተኛው እያወረደ ብንወያይባቸው መልካም ነው ብለው በቀረቡ ሰነዶች ላይ ሰፋ ያለ አስተያየቶችና ጥያቄዎችን አንስተው መግባባት ላይ ተደርሷል ፡፡ በተነሱት አሰተያየቶች ላይ የሚመለከታቸው የባለስልጣኑ የስራ ኃላፊዎች ምላሽና አስተያየት የሰጡ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ የሚያጋጥሟትን ፈተናዎች ተቋቁማ በለውጥ ጎዳና ወደ ብልፅግና ልማት ለመሸጋገር ጥረት እያደረገች መሆኑን ገልጸው የባለስልጣኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በዚህ የለውጥ ሂደት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊያደርጉ እንደሚገባ ገልጸዋል:: በመጨረሻም የባለስልጣኑ የእንስሳት ሪጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል ለተነሱ ሀሳቦች ምላሽ በመስጠት መንግስት ማለት እኛ ነን የሚለውን አስተሳሰብ በመያዝ በሀገራችን የተጀመረውን የለውጥ ጉዞ አጠናክሮ በማስቀጠል እና ያለንን ጸጋና ሀብት ጥቅም ላይ እንድውል ማድረግና በአግባቡ በመጠቀም ለቀጣዩ ትውልድ ዕዳን ሳይሆን ምንዳን ለማስተላለፍ በቁርጠኝነት መስራት የሁላችንም ኃላፊነት ነው ብለዋል፡፡ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ጨምረውም የሬጉላቶሪ ተቋም ታማኝነትን ስለሚፈልግ አገልግሎት አሰጣጣችንን ከቅሬታ ነጻ በማድረግ የተሰጠንን ሀላፊነት በአግባቡ ለመወጣት በታማኝነት ማገልገል አለብን በማለት አሳስበውና መግባባት ላይ ተደረሶ ስልጠናው በውጤት ተጠናቋል።

በእንስሳት መኖ ጥራትና ደህንነት የላቦራቶሪ ፍተሸ ውጤትና ኢንስፔክሽን ግኝት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ በኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእንስሳት መኖ ሬጉላቶሪ መሪ ስራ አስፈፃሚ ባዘጋጀው መድረክ ከእንስሳት መኖ አቀናባሪዎች፤ ከእንስሳት መኖ አምራቾች ማህበር፤ ከዶሮ አርቢዎች፤ከወተት አርቢዎችና ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ለተውጣጡ ባለድርሻ አካላት በአዳማ ከተማ የውይይት መድረክ አካሄደ፡፡ ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእንስሳት ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ዋና ዳይረተክተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል ሲሆኑ የውይይት መድረኩ ዋና ዓለማ በተገኙት የኢንስፔክሽን ግኝቶችና የእንስሳት መኖ ምርመራ ውጤት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት በማካሄድ በቀጣይ የእንስሳት መኖ ጥራት ቁጥጥር የሚጠናከርበትንና ጥራትና ደህንነቱ የተጠበቀ የእንስሳት መኖ የሚቀርብበትን መንገድ ለመፍጠር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ አያይዘውም ስለ ሰው ልጆች ጤንነት እና ደህንነት የምናስብ ከሆነ ቅድሚያ የእንስሳትን ጤንነት ለመጠበቅ የእንስሳትን መኖ ጥራትና ደህንነት መጠበቅ አስፈላጊ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡ በውይይት መድረኩ ላይም በእንስሳት መኖ ጥራትና ደህንነት የላቦራቶሪ ፍተሸ ውጤትና ኢንስፔክሽን ግኝት፤ የወተትና የእንስሳት መኖ የላቦራቶሪ ፍተሻ ውጤት ነባራዊ ሁኔታ እና የምግብ ጥራትና ደህንነት ጉዳዮች በሚሉ ርዕሶች ላይ በተለያዩ አቅራቢዎች ገለፃ ቀርቦ ከቤቱ የተለያዩ ጥያቄዎች፤ አስተያየቶችና ሀሳቦች ተነስተዉ ሰፊ ዉይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ በመጨረሻም የቀረቡ የኢንስፔክሽን ግኝቶችና የላቦራቶሪ ውጤቶች ከአለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፀር መሻሻሎች የታዩበትን ያህል የተወሰኑ ተቋማት ደግሞ ይበልጥ መሻሻል ማሳየት ሲገባቸው ከነበራቸው አፈፃፀም የቀነሱ እንዳሉ ተነስቶ ለቀጣይ ባለስልጣኑ ከስራ እስከማገድ እርምጃ ከመውሰዱ በፊት አሉ የተባሉ ችግሮችን ከወዲሁ ማረምና ማስተካከል እንደሚገባና ለሁሉም ተቋማት የፅሁፍ ግብረ መልስ እንደሚደርስ የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ የውይይት መድረኩ ተጠናቋል፡፡

የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ለስራ ኃላላዎችና ለመላው ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከጥር 29 እሰከ 30/ 2016 ዓ/ም በባለስልጣኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ <<ከእዳ ወደ ምንዳ>> በሚል መሪ ቃል ስልጠና መስጠት ጀመረ፤ *********** የባለስልጣኑ የእንስሳት ሪጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል የስልጠናውን ዓላማ አስመልክቶ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም ድህነትን ለማጥፋት ሀብት መፍጠር የዚህ ትውልድ ዋና ተግባር ሊሆን እደሚገባ ገልጸው የሚሰጠው ስልጠና በመንግስት ተዘጋጅቶ ለህዝብ ውይይት የወረደ ሰነድን መነሻ በማድረግ ሲሆን ሀብት በመፍጠር ጉዟችን የተመዘገቡ ስኬቶች ፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችና ቀጣይ አቅጣጫዎች እና በኢትዮጵያ አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቪስ ለመገንባት በተደረገው ጥረት የመንግስት ሰራተኛው ሚና የሚሉ ርዕሰ-ጉዳዮችን ያካተተ ነው ብለዋል፡፡ በስልጠናው በሚኖረው የውይይት ቆይታ ሰልጣኞች በሁለቱ የስልጠና ርዕሰ-ጉዳዮች ላይ ሰፊ ግንዛቤና ዕውቀት እንደሚጨብጡ ፣ ጥልቅና ዝርዝር ጉዳዮች እንደሚዳሰሱና ሰፊ ውይይት እንደሚደረግ ገልጸዉ ተሳታፊዎችም የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው መልእክታቸውን አስተላልፈው የስልጠና መድረኩ ተጀምሯል፡፡ የስልጠናውን ቀጣይ ክፍልና ማጠቃለያ በሚቀጥለው ዜናችን የምንለቅ ይሆናል፡፡ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል መረጃዎችን ያግኙ ዌብሳይት http://www.eaa.gov.et ፌስቡክ: የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣናት /Ethiopian Agricultural Authority / ቴሌግራም eaa_123 የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን

የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን በማዕከላዊ ማስተባበሪያ ፅ/ቤት አደረጃጀት ላይ አጭር ገለፃ አካሄደ:: ****** የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የማዕከላዊ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አደረጃጀት፣ ተግባርና ሀላፊነትን በተመለከተ የባለስልጣኑ ሀላፊዎችና የማዕከሉ የቅርንጫፍ ፅ/ቤት ዘርፍ ሀላፊዎች በተገኙበት በአዳማ ከተማ ኤፋታህ ሆቴል ገለፃ አካሄደ ። የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን የእንስሳት ሪጉላቶሪ ዘርፋ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሀሚድ ጀማል የዚህ መድረክ ዋና ዓላማ የባለስልጣኑ ማዕከላዊ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አደረጃጀት ለይ ግልፀኝነት በመፋጠር የተቋሙን አላማ ፣ ተልዕኮና ግብ ለማሳካት የራሳችንን ሀላፊነተና ተግባር የምንወስድበት ነው ብለዋል። የማዕከላዊ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ገመዳ ቢነግዴ በበኩላቸው የማስተባበሪያ ማዕከሉ የአራቱን አቅጥጫ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አካቶ የሚሰራ ሲሆን አደረጃጀቱንና የአሰራር ሂደቱን ግልፅ ለማድረግ የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን ገልፀው በዚህም ላይ ሰፊ ገለፃ አካሂደዋል። ከዚህ በተጨማሪም የሰዉ ሀይል ብቃትና አስተዳደር መሪ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ብርቱካን ቦጋለ የማዕከላዊ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሀላፊነትና ተግባርን በተመለከተ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል። በመጨረሻም በቀረበው ገለፃ ላይ በተሳታፊዎች ሰፊ ውይይቶችና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን በእነዚህ ሀሳቦች ላይ የባለስልጣኑ የእንስሳት ሬጉላቶሬ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶር ሀሚድና የክፋሉ ስራ አስፈሚ ምላሽ ሰጥተውባቸው መግባባት ከተደረሰ በኋላ ውይይቱ ተጠናቋል።