cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

የጥበብ ተግሳጽ

መዳን በኢየሱስ ብቻ ነው ሐዋ.ስራ4÷12 የሀገሬ ልጆች፦ በመልካሙ መንገድ እንዲጓዙ፤ የክፉውን አሰራርና ስራ ይተው ዘንድ እግዚአብሔርን በመፍራት በእውነት በፊቱ ይመላለሱ ዘንድ ይገባቸዋልና የአቅሜን መልካሙን መንገድ ለማሳየት እሞክራለሁ። @anechenashicaraka

Більше
Ефіопія10 795Амхарська9 225Категорія не вказана
Рекламні дописи
298
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

01:09
Відео недоступнеДивитись в Telegram
ይቅርታ የፍቅር መቀመጫ ዙፋን ነው!!! @Balerai_wetat @Balerai_wetat @Balerai_wetat
Показати все...
YouCut_20230207_163555390.mp432.92 MB
በሚበልጠው ልትሾም በሚያንሰው ትፈተናለህ!! ሰው ከፍ ያለ፣ ክብር ያለው፣ ትልቅ ቦታ ላይ መሾም ይፈልጋል፤ ይህ በንዲህ እንዳለ አሁንም ሰው በሚበልጠው ከእሱ በሚያንሰውና በሚንቀው ነገር መፈተን አይፈልግም። ይሄ የሰው በሃሪ ደግሞ ትልቅ ቦታና የከበረ ስፍራ እንዳንደርስ መጥፎ እንቅፋት ነው። ያገሬ ልጆች ከፍታችሁ የሚሰራው በሚበልጧችሁ ሰዎች ከናንተ በላይ በሆኑ ሰዎች አይደለም። እናንተ ከእናንተ በታች ያሉትን እንደምትንቁት ልክ እንደዛ የበላዮቻችሁ ከነሱ ስለምታንሱ የናንተ ነገር ለነሱ ምንም ነው ይንቋችኋል። የሚበልጧችሁ ሰዎች እንኳን ከፍታችሁን ሊሠሩላችሁ ቀርቶ በንቀታቸው የከፍታችሁን መሠረት ሊያፈርሱት ይደርሳሉ። "ሀብታም በድሃ ገንዘብ ይታከማል" እንደሚባለው፦ የእኛ ከፍታ የሚሰራው ባቀለልንው፣ ባልጠበቅንው፣ ዝቅ ዝቅ ባደረግንው፣ በናቅንው ነገር ነው። "ህይወትን ቀለል አድርገህ ኑራት" ያሉ ሰዎች ህይወት ከብዳባቸው ሲቸገሩ አይተናል። ስለዚህ የከፍታችንን ጥያቄ መልስ የምናገኘው ባነሰው፣ ዝቅ ባለውና በናቅንው ነገር ስንፈተን ነው። ያገሬ ልጆች ለመሞት መወለድ፤ ለመድረስ መሄድ፤ ለመጥገብ መብላት አስፈላጊና ወሳኝ ነገር እንደሆነው ሁሉ በሚበልጠው ለመሾም በሚያንሰው መፈተን ግድ ነው። ሰዎች ለጨለማዎቻቸው መብራት፤ ለጥያቄዎቻቸው መልስ፤ ለቁልፎቻቸው መክፈቻ ያላገኙ ሰዎች የነሱን ጨለማ የሚገፍ፤ ለጥያቄያቸው መልስ ለቁልፋቸው መክፈቻ ስለሌለ ሳይሆን ለጨለማቸው መብራትን፤ ለጥያቄያቸው መልስን፤ ለቁልፋቸው መክፈቻን ያላገኙት ወዳነሰውና ዝቅ ወዳለው ወደናቁት ነገር ጎንበስ ብለው ከመፈለግ ይልቅ ያላቅማቸው መንጠራራትን ስለመረጡ ነው። ሰው ቤት አሰርቶሲጨርስ ቁልፉን የሚቀበለው ከባለ ስልጣናት ሳይሆን ከቀጠረው ቅጥረኛ እንደሆነ ልክ እንደዛ ለጨለማ ብርሃንን፤ ለጥያቄ መልስን፤ ለተዘጉ በሮች ቁልፎችን የምናገኘው ያላቅማችን ተጠራርተን ሳይሆን ካነሰውና ዝቅ ካለው ከፈተኑን ነገሮች ውስጥ ነው። ✔ እንግዲህ ሰው ሁለት እግር አለኝ ብሎ ሁለት ዛፍ ላይ እንደማይወጣው ልክ እንደዛ በሚበልጠው መሾምን ወደን በሚያንሰው መፈተንን መጥላት አንችልም። ያገሬ ልጆች 💖❤እወዳችኋለሁ💖❤ @Balerai_wetat @Balerai_wetat @Balerai_wetat
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
01:41
Відео недоступнеДивитись в Telegram
# ስኬት ላይ ለመድረስ የሚያስፈልገው አቅም ሳይሆን አቋም ነው!!! # ስኬት እንደቀልድ የምንይዘው፤ የምንጨብጠው ተራ ነገር አይደለም!! ሼር➮➮➮ሼር➮➮➮ሼር➮➮➮ @Balerai_wetat @Balerai_wetat @Balerai_wetat
Показати все...
YouCut_20230116_192415537.mp495.06 MB
04:33
Відео недоступнеДивитись в Telegram
ባለራዕይ ትውልድ፦ ሆኖ የሚያስመሠክር እንጂ ለመባል የሚያስመስል አይደለም። ሼር➮➮➮ @Balerai_wetat @Balerai_wetat @Balerai_wetat
Показати все...
YouCut_20230115_045334817.mp4124.41 MB
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ቃሉን ጠብቁ የጠበቃችሁት እርሱ ይጠብቃችኋል ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ለእናንተ ይሁን (መጽሐፈ ምሳሌ 7 ) ------------ 1፤ ልጄ ሆይ፥ ቃሌን ጠብቅ ትእዛዜንም በአንተ ዘንድ ሸሽግ። 2፤ ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ፤ ሕጌንም እንደ ዓይንህ ብሌን ጠብቅ፤ 3፤ በጣቶችህ እሰራቸው፤ በልብህ ጽላት ጻፋቸው። 4፤ ጥበብን። አንቺ እኅቴ ነሽ በላት፥ ማስተማውልንም። ወዳጄ ብለህ ጥራት፥ 5፤ ከጋለሞታ ሴት ትጠብቅህ ዘንድ ቃልዋን ካለዘበች ከሌላይቱ ሴት። 6፤ በቤቴ መስኮት ሆኜ ወደ አደባባይ ተመለከትሁ፤ 7፤ ከአላዋቂዎች መካከል አስተዋልሁ፤ ከጐበዛዝትም መካከል ብላቴናውን አእምሮ ጐድሎት አየሁ፥ 8፤ በአደባባይ ሲሄድ በቤትዋም አቅራቢያ ሲያልፍ፤ የቤትዋን መንገድ ይዞ ወደ እርስዋ አቀና፥ 9፤ ማታ ሲመሽ፥ ውድቅትም ሲሆን፥ በሌሊትም በጽኑ ጨለማ። 10፤ እነሆ፥ ሴት ተገናኘችው የጋለሞታ ልብስ የለበሰች፥ ነፍሳትን ለማጥመድ የተዘጋጀች። 11፤ ሁከተኛና አባያ ናት፥ እግሮችዋም በቤትዋ አይቀመጡም፤ 12፤ አንድ ጊዜ በጎዳና፥ አንድ ጊዜ በአደባባይ፥ በማዕዘኑም ሁሉ። ታደባለች። 13፤ ያዘችውም ሳመችውም፤ ፊትዋም ያለ እፍረት ሆኖ እንዲህ አለችው። 14፤ መሥዋዕትንና የደኅንነት ቍርባንን ማቅረብ ነበረብኝ፤ ዛሬ ስእለቴን ፈጸምሁ። 15፤ ስለዚህ እንድገናኝህ፥ ፊትህንም በትጋት ለመሻት ወጥቻለሁ፥ አግኝቼሃለሁም። 16፤ በአልጋዬ ላይ ማለፊያ ሰርፍ ዘርግቼበታለሁ፥ የግብጽንም ሽመልመሌ ለሀፍ። 17፤ በመኝታዬ ከርቤንና ዓልሙን ቀረፋም ረጭቼበታለሁ። 18፤ ና፥ እስኪነጋ ድረስ በፍቅር እንርካ፥ በተወደደ መተቃቀፍም ደስ ይበለን። 19፤ ባለቤቴ በቤቱ የለምና፥ ወደ ሩቅ መንገድ ሄዶአልና፤ 20፤ በእጁም የብር ከረጢት ወስዶአል፤ ሙሉ ጨረቃ በሆነች ጊዜ ወደ ቤቱ ይመለሳል። 21፤ በብዙ ጨዋታዋ እንዲስት ታደርገዋለች፤ በከንፈርዋ ልዝብነት ትጐትተዋለች። 22፤ እርሱ እንዲህ ስቶ ይከተላታል፥ በሬ ለመታረድ እንዲነዳ፥ ውሻም ወደ እስራት እንዲሄድ፥ 23፤ ወፍ ወደ ወጥመድ እንደሚቸኩል፥ ለነፍሱ ጥፋት እንደሚሆን ሳያውቅ፥ ፍላጻ ጕበቱን እስኪሰነጥቀው ድረስ። 24፤ ልጆቼ ሆይ፥ አሁን እንግዲህ ስሙኝ ወደ አፌም ቃል አድምጡኝ። 25፤ ልብህ ወደ መንገድዋ አያዘንብል በጎዳናዋ አትሳት። 26፤ ወግታ የጣለቻቸው ብዙ ናቸውና፤ እርስዋም የገደለቻቸው እጅግ ብዙ ናቸው። 27፤ ቤትዋ የሲኦል መንገድ ነው፤ ወደ ሞት ማጀት የሚወርድ ነው። ያገሬ ልጆች በክርስትና ህይወት ከሰይጣን ጋር ያላችሁ መንፈሳዊ ውጊያ በሳምንት አንዴ እሁድ እሁድ ብቻ አይደለም። በቀን 24ስአት በሳምንት 7ቀን በወር 30ቀን በአመት 365ቀን ነው አጋንንት ቅዱሳኖችን የሚዋጋው ። በዚህ ምዕራፍ ላይ ያለውልጅ በሚያልፍበት መንገድ ብዙዎች አልፈዋል አሳቿም ሴት የተቀባባችው የለበሰችው ልብስ ትኩረት እዲያገኝ ወደሷ እዲመጡም ጩሀለች ነገር ግን እነሱ የእግዚአብሔር ቃል ስለጠበቁ የጠበቁትም እርሱ ስለጠበቃቸው ተላልፈው ለጠላት ሀሳብ አልተሰጡም። ይህ ወጣት ግን ቃሉን ስላልጠበቀ ማስተዋልም ስለጎደለው ጩኸቷንም ሰማ ውበቷንም አየ ወደቤቷ ገባ ወጋችው ወደቀ ሞተ። የታጠቀን አጋንንት የእግዚአብሔርን ቃል ታጥቃችሁ እንጂ ቃሉን ጥላችሁ አታሸንፉትም። ስለዚች ሴት ምዕራፉሲናገር እደዚህ ይላል ወግታ የጣለቻቸው ብዙ ናቸው፤ እርሷ የገደለቻቸው እጅግ ብዙ ናቸው። አልቀጠረችውም አይተዋወቁም በመንገድ ሲሄድ ማስተዋል የጎደለው እንደሆነ አየች ወደቤቷ ወስዳ ገደለችው። የእግዚአብሔርን ቃል የጠበቁ የታጠቁም እያዮአት እዳለፏት ልክ እደዛ ቃሉን ብንጠብቅ ብንታጠቅም የጨለማው መንፈስ መዋቅር ያዘጋጀብንን ወጥመድ እያየንው እናልፈዋለን። ❤💖እወዳችኋለሁ ❤💖 @anechenashicaraka @anechenashicaraka @anechenashicaraka
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.