cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ሰዉነት ምንድነዉ???🤔🤔🤔🤔🤔

ዛሬ አዲስ ቀን አዲስ ተስፍ አዲስ ፍሬ ይህ የመልካምነት ቻናል ነዉ በዚ ቻናል ዉስጥ የሚለቀቁት እራሳችንን እንድንፈትሽ የሚያደርጉ ናቸዉ እናም በተቻላችሁ መጠን ተቀላቀሉን ስለ መልካም ምላሻችሁ እናመሰግናለን😍😍😍እንወዳችዋለን

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
249
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

የተበላሸ አፕል ቀምሰህ ከላወቅክ በጤነኘው አፕል ጣዕም አትደነቅም፤ ህይወትን ለመረዳትም መጥፎ ጊዜያት አስፈላጊ ናቸው!
Показати все...
እያንዳንዱ አጋጣሚ ምንም መጥፎ ቢመስልም እንኳን በውስጡ የያዘው ጠቃሚ ነገር አለ፤ ጉዳዩ እሱን ማግኘት ነው!
Показати все...
.................አድዋ.............. ✍🏽.አጤ ዮሐንስ ካረፋ በኋላ ግዛታቸውን እያስፋፉ ውጫሌው በተባለው ስፍራ ላይ ሰፍረው ሳለ ሚያዚያ 25 ቀን 1881 ከኢጣሊያ መንግስት ጋር 20 አንቀፆችን ተዋዋሉ ውሉም "የውጫሌው ውል" ተባለ።ይሄንንም ሲፈርሙ ገና አልነገሱም ነበር።ከእነዚህም 20 አንቀፆች ውስጥ በአንቀፅ 17 አለመስማማት ተፈጠረ።ይህም አንቀፅ በሁለት ግልባጭ የተፃፈ ነበር በአማርኛ እና በጣሊያነኛ። 1.በአማርኛ የተፃፈው "የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ከውጭ ሀገር መንግስታት ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት 'ፈቃዱ ከሆነ' በኢጣሊያ መንግስት በኩል ሊያደርግ ይቻለዋል" 2.ነገር ግን በኢጣሊ "የኢትዮጵያ መንግስት ከውጭ ሀገር መንግስታት ጋር የሚያደርገውን ግንኙነት በኢጣሊያ መንግስት አማካኝነት ማድረግ ይገባዋል"የሚል ነበር። ✍🏽.አጤ ምኒሊክ እንደዚህ ተብሎ መተርጎሙን ያወቁት ንጉሠ ነገሥት ከሆኑ በኋላ የደስታ መልዕክታቸውን ለአውሮፓ መንግስት ሊልኩ ሲል አይ ደብዳቤ ቢሆንም በእኛ በኩል ነው ማለፍ ያለበት ባሉ ጊዜ ነው። ✍🏽.ጣልያኖችም በዮሐንስ ጊዜ ሲያደርጉት እንደነበረው አሁንም የተለያዩ መኳንቶች ከእነ ራስ አሉላ ጋር ተጣልተው ወደ እነሱ እንዲመጡ አደረጉ የጣሊያን ጦር በእነዚህ መኳንት እየተመራ ብዙ ቦታዎችን ተቆጣጠረ ✍🏽.አጤ ምኒሊክም ለቀው እንዲወጡ ቢያስጠነቅቁም አሻፈረኝ አሉ።አጤ ምኒሊክም አዋጅ አሰነገሩ አዋጁም"የሐገሬ ሰው ከአሁን ቀደም የበደልኩህ አይመስለኝም።አንተም እስከ አሁን አላስቀየምከኝም።አሁንም ጉልበት ያለህ በጉልበትህ ጉልበትየሌለህ ለልጅህ:ለሚስትህ:ለሀይማኖትህ እና ለሐገርህ ስትል በሐዘንህ እርዳኝ ።የወሰለትክ እንደሆነ ግን ትጣላኛለህ አልተውህም ።እግዝዕትነ ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም ዘመቻዬም በጥቅምት ነውና የሸዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ድረስ ወረይሉ ከተህ ላግኝህ"ብለው የክተት አዋጅ መስከረም 7 ቀን 1988 ዓ.ም አወጁ። ✍🏽."እኔ ሴት ነኝ ጦርነት አልወድም ግን እንዲህ መሳዩን ውል አልቀበልም እኛ የናንተን የበላይነት አንፈልግም አንፈራችሁም።"እቴጌ ጣይቱ ብርሐን ዘኢትዮጵያ የውጫሌውን ውል በተመለከተ የተናገሩት። -ጥቅምት 2 ቀን 1888 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ሲነሱ እቴጌ ጣይቱ አብረው ተነሱ ።ራስ መኮንን የጦር አበጋዝ ሆነው ራስ ወሌን :ራስ ሚካኤልን:ራስ መንገሻን ወ.ዘ.ተ ይዘው ጣሊያኖች በመሸጉት አምባላጌ ተራራ ላይ ሠፈሩ። -ህዳር 28 አምባላጌ ላይ የተደረገው ጦርነት 2 ሰዓት ፈጅቶ ራስ መኮንን በመሩት ጦር የኢጣሊያ ጦር ወደ መቀሌ ሸሸ።ራስ መኮንን እየገሰገሱ ወደ መቀሌ ከተጓዙ በኋላ መቀሌ ላይ የተካሄደው ጦርነት ብዙ ሰዓት ከፈጀ በኋላ የውሃ ጥም ተጨምሮባቸው ብዙ መሳሪያዎችን አስረክበው ሸሹ። -ከእነዚህ ጦርነቶች በኋላ ዋና የጦር አዝማቹ ባራቴሪ የቀረውን ጦር በ4 አቅጣጫ ከፍሎ አሰለፉ። 1.ጄ/ል አርሞንዲ 2.ጄ/ል ዳቦርሚዳን 3.ጄ:ል አልበርቶኒ 4.ጄ/ል ኤሌና የጦር ካርታ አዘጋጅቶ አሰለፋቸው።አጠቃላይ የኢጣሊ ጦር ከ20 ሺህ የበለጠ እና በዘመናዊ የጦር መሳሪያ የተሞላ እና 60 መድፎችን ታጥቀው ቀረቡ። -የኢትዮጵያ ሰራዊት ደግሞ በ10 ጀነራሎች የተዋቀረ ነበር። 1.ምኒሊክ ከአድዋ አጠገብ ከ30,000 ሰራዊት ጋር 2.ጣይቱ በዚሁ ስፍራ ከ3000 ወታደር ጋር 3.ተክለ ሐይማኖት በዚሁ ስፍራ ከ3000 ወታደር ጋር 4.ፊት አውራሪ ገበየው ገቦ ከአሰም ወንዝ ተሻግሮ ከ6000 ወታደር ጋር 5.ንጉስ ሚካኤል ከ8000 ወታደር ጋር 6.ራስ መኮንን ከ8000 ወታደር ጋር 7.ራስ መንገሻ ዮሐንስ ከራስ አሉላ እና ከራስ ሐጎስ ጋር ከ3000 ወታደር 8.ዋግስዩም ከ6000 ወታደር ጋር 9.ራስ ወሌ ከ3000 ወታደር ጋር 10.ራስ መንገሻ አቲከም ከ3000 ወታደር ጋር በድምሩ 73,000 የኢትዮጵያ ሰራዊት ለውጊያ ተሰልፎ ነበር በዚህ ሰዓት የጊወርጊስ ዕለት ስለነበር ታቦቱን ይዘው እንደ ተሰለፉ ይተረካል።በጦርነቱ ጊዜም ቅዱስ ጊዎርጊስም ወርዶ ተዋግቷል ይባላል።ጦርነቱም ከተጀመረ በኋላ በሁለቱም ወገን ብዙ እልቂት ደረሰ።ጦርነቱም አንድ ሙሉ ቀን ወሰደ። -ከኢጣሊ ወገን 5000 ነጭ:2000 ከኤርትራ የተመለመሉ ወታደሮች ሲሞቱ:2400 የሚሆኑት ከ60 መድፍ እና ከብዙ መሳሪያዎች ጋር ተማርከዋል። -በኢትዮጵያ በኩል ህዝቡ ተኝቶ መታኮስ የፈሪ ነው እያለ ቆሞ በጀግንነት ሲዋጋ ስለነበር ለጥይት የተጋለጠ ስለነበር ብዙ ሰው አልቋል።በአጠቃላይ 10,000 እንደነበር ብዙዎች ይስማማሉ። -ከ4ቱ መሪዎች 2ቱ ጄ/ል ዳቦር እና አርሞንዲን ተገደሉ።ጄ/ል አሌና ቆሰለ :አልበርቶኒ ተማረከ።በዚህም ጦርነት ትልቁን ድርሻ ባሻይ አውኣሎም በስለላ ተወጧል። ✍🏽.ጦርነቱም በባሻይ አውኣሎም ብልሀትነት:በምኒሊክ የጦር አደረጃጀት:በጣይቱ የተለየ ዘዴ እና በእነ ራስ መኮንን የጦር መሪነት እንዲሁም በኢትዮጵያ ህዝብ ወኔ እና ጀግንነት ጦርነቱን በድል አጠናቀቀች። ✍🏽.የዓለም ህዝብም ጉድ አለ።ኢጣሊ አንገተቷን ደፋች መላው የአፍሪካ ህዝብ አንገት ደግሞ ቀና አለ በዚሁም በወቅቱ የነበረው የኢጣሊ ጠ/ሚ ፍራንቺስኮ ክርስፒ ከስልጣናቸው ወረዱ።ለመላው አፍሪካዊያን ደግሞ የብርሃን ጮራ ብቅ አለች።ከድሉም በኋላ "ምኒሊክ ተወልዶ በያነሳ ጋሻ ግብሩ እንቁላል ነበር ይህን ጊዜ ሐበሻ" እየተባለ ተዘመረለት። 🙏🏾.ክብር አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍሰው ይቺን ሀገር ላቆሙ የኢትዮጵያ ነገስታት እና ህዝቦች
Показати все...
ያንተ ዋጋ ጥቅምህን ማየት ባልቻሉ ሰዎች ምክኒያት አይቀንስም!
Показати все...
ሁሌም ትክክል እንደሆንክ የሚሰማህ ከሆነ፤ ከሕይወት ምንም አትማርም።
Показати все...
ትችት ሁልግዜ የሚመጣው አንተ ማድረግ ስላልቻልከው ነገር ብቻ ሳይሆን አንዳንዴም አንተ በሚገባ ሰርተህው ሌሎች ስላልቻሉት ሊሆን ይችላል !
Показати все...
አንዳንድ ሰዎች ንግግርህን እነርሱ እንደፈለጉት አጣመው ይፈቱታል፤ ያን ጊዜ ለማቃናት መሞከር ከንቱ ልፋት ነው ሚሆነው፤ እንደውም እነርሱን በመተው ከጠማማነታቸው መዳን ሳይሻል አይቀርም!!!
Показати все...
ደስተኛ መሆን ማለት አሁን ያለህበትን መቀበል ከዛ እያንዳንዱን ቅፅበት ማጣጣም ነው። ለማን ብለሀ ነው ስላለፈው የምትናደደው? ስለሚመጣው የምትጨነቀው? ወዳጄ ስለ ነገ አላማ ይኑርህ በተረፈ ዛሬን አጣጥመው፤ ከዚህ ውጪ ካደረክ ነፋስ እየተከተልክ ነው!
Показати все...
እባብ በህይወት እያለ ጉንዳንን ይበላል እባብ ሲሞት ጉንዳኖች ይበሉታል ጊዜ በማንኛውም ሰአት ይለወጣል በህይወትህ የማንንም ዋጋ አታሳንስ ምንአልባት ሀይለኛ ትሆን ይሆናል ነገር ግን ጊዜ ካንተ ያበለጠ ሀያል ነው አንድ ዛፍ መቶ ሺህ ክብሪቶችን ሲሰራ አንድ ክብሪት ግን መቶ ሺህ ዛፎችን ታቃጥላለች አንድ መጥፎ ስራ ጥሩ ድረጊቶችን ታጠፉለች ዋናው ነገር ሰዎችን የምታከብር በአስተሳስብ ዘመናዊ እና ሁል ጊዜ ጥሩ አመለካከት ያላህ ሁን !
Показати все...
💛❤ይህ ነዉ ፍቅር 1. የፍቅር ምንጭ-------ፈጣሪ 2. የፍቅር መገለጫ-----ድርጊት 3. የፍቅር ልጅ----------ነፃነት 4. የፍቅር ውጤት------ደስታ 5. የፍቅር ላብራቶሪ-----ልብ 6. የፍቅር መለኪያ------መሥዋዕት 7. የፍቅር ጓደኞች------እምነትና ተስፋ 8. የፍቅር ዙፋን--------ትዕግስት 9. የፍቅር ቋንቋ-------ትህትና 10. የፍቅር መንገድ---ሰላም ሰናይ ዉሎ 😍😍😍😍😍😍😍😍😍
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.