cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

Рекламні дописи
189
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ታላቅ እና በአይነቱ ልዩ የሆነ የዳዕዋ ድግስ ==========================      እነሆ የፊታችን እሁድ ማለትም በቀን 06-02-2015 በወረታ ከተማ በሰለፍዮች መስጂድ (በፎቋ መስጂድ) በታላላቅ መሻይኾች እና ዑስታዞች ደምቀን እንውላለን ✅ከቀኑ 9:00 ሰዐት ጀምሮ ታላቅ የሙሓደራ እና የፈትዋ ድግስ ተዘጋጅቶ  ይጠብቀወታል። ✅ለሴቶችም በቂ ቦታ አዘጋጅተናል    ♻️ስለሆነም ቤተሰብወን እና ወዳጅ ዘመድዎን ይዘው እንዲመጡ በአክብሮት ተጋብዘዋል።♻️ "ጠንካራ የሰለፎች ተከታይ ሁን"
Показати все...
Aslamu alykum yajma Endet nachihu Erft Endet Nebr Be alah fkad megnagna chin eydrse slhon Yewsdnewn kupon Ena Amana Eytewetan New? Endanresa lmastawes yakl new bechalnew Mesrat ynorbnal Adra leguadegnochachihum astawsuachew
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
9ኙ.ሚስጥሮች.tt 📚 ቁርኣንን ለመሓፈዝ 9 ሚስጥሮች 🌀1ኛው ሚስጥር : ለቁርኣን ሒፍዝ ከፍተኛ የሆነ ጉጉት ፣ ፍላጎትና ተነሳሽነት ሊኖርህ ይገባል ፣ 🌀 2ኛው ሚስጥር : ኢኽላስ (ለአሏህ ብቻ ብሎ መሐፈዝና) አሏህ ቁርኣን ሂፍዝን እንዲያገራልህ ሁሌም ዱዓ ማድረግ ፣ 🌀 3ኛው ሚስጥር : ሀላፊነቱን ራስህ ውሰድ ፣ ምክንያት አታብዙ (እድሜህ ቢገፋ ፣ የማስታወስ አቅምህ ቢያንስ...) 🌀 4ኛው ሚስጥር : በአቅምህ ልክ ሀፍዝ እንዲሁም በአንድ ሙስሓፍ (አንድ ተመሳሳይ ገፅ ያለው የቁርኣን እትም) ብቻ ተጠቀም። 🌀 5ኛው ሚስጥር : ለሒፍዝ ተስማሚማ ተዛማች ጊዜና ቦታ ምረጥ (ስሁርና ፈጅር ወቅቶች የተሻሉ ሲሆኑ ማታ አይመከርም ፣ ቦታም ፀጥታ ያለበት ብዙ ቀልብን ሳቢ የሆኑ ነገራቶች የሌሉበት ቢሆን ይመከራል) 🌀 6ኛው ሚስጥር : 3ቱንም ዋና የሒፍዝ ሞተሮችን አንቃቸው - አይንህን ጆሮህንና ልብህን ክፍትና ንቁ አድርገህ መሓፈዝ ይኖርብሀል ፣ አንድኛቸውንም ከተውካቸው መሀፈዝህ ትርጉም አልባ ይሆናል። 🌀 7ኛው ሚስጥር : በተደጋጋሚ ማጥናትና ሙራጀዓ ማድረግ አትዘንጋ ፣ (ቀኑን ሙሉ እና ከመኝታ በፊት በኦድዬ በማዳመጥ ፣ እንዲሁም በየ ትርፍ ሶላቶች ላይ በመቅራት ሙራጀዓ ላይ ተጠባከር) 🌀 8ኛው ሚስጥር : ቋሚማ ወጥ የሆነ ፕሮግራም ይኑርህ ፣ በየቀኑ ምን ያክል ተሀፍዛለህ? ምን ያክሉን ሙራጀኣ ታደርጋለህ? መቼ ሂፍዝ ትጨርሳለህ? ወጥ የሆነና ቋሚ ፕሮግራምና እቅድ ይኑርህ 🌀 9ኛው ሚስጥር : ከወንጀል ራስህን አርቅ እንዲሁም አሏህ እንዲያገራልህ ሁሌም ዱዓ በማድረግ ላይ አትስነፍ። ◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈ © ፉርቃን የቁርኣን ንባብ ማዕከል ✍ በOnline ተመዝግቦ ቁርኣን ለመማር በዚህ ሊንክ ያመልክቱ 👇 @FurqanOnlineQuran ⭕️ ስለ ቁርኣን የመሳሰሉ ፅሁፎችን ፣ ምስሎችንና ቪዲዬዎችን ለመከታተል ይቀላቀሉን ፣ ለሌሎችም በማካፈል የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ!! 🌀 https://t.me/furqan_school
Показати все...
#መውሊድን_ከተለያዩ_ሸሪዓዊ ምክንያቶች አንጻር አላከብርም!    ከብዙው በጥቂቱ 20 (ሀያ)      ምክንያቶችን ልጥቀስ።       ➚➚➚➚➚➚➚ ❶ኛ, #መውሊድ በሸሪዓችን #መሠረት የሌሌለው ማለትም #ቁርኣንና_ሐዲሥ ላይ ያልተደነገገ አዲስ #መጤ ፈጠራ ስለሆነ፣ ❷ኛ, #መውሊድ መከበር ያለበት ጠቃሚ #ኢስላማዊ በዓል ሁኖ በነበር፤ ከእኛ #በፊት ያሉ ደጋግ የነቢዩ ﷺ ➼ ባለቤቶች፣ ➼ ባልደረቦች (ሶሐቦች)፤ ➼ ታቢዒዮችና ➼ አትባዑ ታቢዒዮች #ባከበሩት ነበር። #ስለዚህ ያኔ ለነርሱ #ዲን ያልነበረው፤ ዛሬ ለእኛ #ዲን አይሆንምና አላከብርም! ❸ኛ, ከነዚህ #ትውልዶች በኋላ የመጡ #ታላላቅ የኢስላም #ሊቃውንቶችና #ሙሐዲሦች ስላላከበሩት፣ ❹ኛ, #መውሊድን የጀመሩት ሶሐቦችን #በመሳደብ በግንባር ቀደምትነት የሚታወቁት #ሺዓዎች የሆኑት ፋጢሚዶች ስለሆኑ፣ ❺ኛ,  አንድ ነገር በራሱ #መልካም ከሆነና የተጀመረበት #አላማ ለመልካም ከሆነ፤ ምንም እንኳን #ጀማሪዎቹ መጥፎ ቢሆኑም ነገሩ #ያልተፈቀደ ላይሆን ይችላል። #መውሊድን እነዚህ የፋጢሚይያህ #ሺዓዎች የጀመሩበት ዐብይ ምክንያት ግን፤ #በዋናነት የራሳቸውን #ብልሹ እምነት በሌላው ላይ ለመጫን #መሸጋገሪያ ድልድይ ይሆናቸው ዘንድ እና ከሱንናው #ማኅበረሰብ ጋር ያለውን #ልዩነት አጥብበው በፖለቲካው ዘርፍም የስልጣን #አድማሳቸውን ለማስፋት ነበር። ስለዚህ ለዚህ እኩይ #የሺዓ አላማ የተጀመረን #መውሊድ አላከብርም! ❻ኛ, #መውሊድ በሸሪዓችን #መሠረት የሌለው #በዓል ስለሆነ፤ ከፊሉ #ሙስሊም አከብራለሁ ሲል፣ ከፊሉ ደግሞ አላከብርም ሲል፤ #አንድ መሆን የሚገባውን #ሙስሊም በዚህ ክፍተት ብቻ #እንዲከፋፈል ጉልህ ሚና የተጫወተ #መጤ በዓል ነው። #መልካም ነገር ቢሆን ኑሮ፤ #ሙስሊሙን አንድ ያደርጋል እንጅ አይከፋፍልም ነበር! ❼ኛ,  #እስልምናዬ ሙሉ መሆኑ ተነግሮኛል። #ስለሆነም በውስጡ ያልተደነገገን ነገር በራሴ እሳቤ #አልጨምርም! ❽ኛ, #መውሊድ ጠቃሚ በነበር #አላህና መልዕክተኛው ﷺ በነገሩን ነበር። እነርሱ ለእኛ ከእኛ ይልቅ #ይበልጥ ጠቃሚውን ያውቃሉና! ❾ኛ, #ከመልዕክተኛው ሱንና ውጭ የሆነን #ነገር መፈጸም፤ እርሳቸው #ባላዘዙበት ነገር ወደ ርሳቸው #ለመቃረብ መሞከር፤ #እርሳቸውን መውደድ ሳይሆን #መቃረን  ስለሆነ፣ ❿ኛ, #በሸሪዓው ውስጥ የሌለን #መውሊድን ማክበር፤ #ሸሪዓውን ጉድለት #ያለበት ስለሚያስመስል፣ ⓫ኛ, #በእስልምናችን ውስጥ የተደነገጉ ሁላችንንም መላውን #ሙስሊም አንድ የሚያደርጉን ሁለት እውቅ #አመታዊ ዒዶች ስላሉን፣ ⓬ኛ, #መውሊድ በራሱ ቢድዓ ከመሆኑም #ባሻገር፤ በሚከበርበት እለት ደግሞ ከርሱ የባሱ #ቢድዓዎች ይፈጸማሉ። ⓭ኛ, #በመውሊድ እለት ከራሱ ተጨማሪ ከሚታከሉ #ቢድዓዎች ባሻገር፤ #ከእስልምና ሊያስወጡ የሚችሉ #ሽርኮች መፈጸሚያ #ማዕከል በመሆኑ፣ ⓮ኛ, መልዕክተኛውን ﷺ #መውደድ ማለት ሱናቸውን #በቀንጣጤ አጥብቆ መያዝና ትዕዛዛቸውን #መፈጸም እንጅ፤ ልደታቸውን #ማክበር ባለመሆኑ፣ ⓯ኛ, የርሳቸውን #ልደት ማክበር፤ #አላዋቂዎች ደግሞ የሚወዱትን ሰው #ልደት እንዲያከብሩ በር #ከፋች በመሆኑ፣ ⓰ኛ, እፁብ #ድንቅ የሆኑ #በሸሪዓችን የተደነገጉ ብዙ ኢስላማዊ #እሴቶች እያሉን፤ ቅንጣት #መሠረት የሌለውን በዓል መሠረት ያለውን #አስመስለን ስናከብር፤ #ሙስሊም ላልሆኑ ወገኖች መተላለፍ ያለበትን #መልዕክት ወደ ጎን በመተው #መተላለፍ የሌለበትን መልዕክት #እያስተላለፍንላቸው በመሆኑ፣ ⓱ኛ, #መውሊድ የሚከበርበት ረቢዑል አወል 12፤ #ትክክለኛው የልደት ቀናቸው ባለመሆኑ #እንዳውም ይህ ቀን በትክክል #የሞቱበት ቀን ነበር። ስለዚህ #ልደታቸውን ነው ወይስ #ሞታቸውን እያከበርን ያለነው?! #የሚከበርበት ቀን ራሱ የተገደበና በውል #የታወቀ አለመሆኑ በራሱ፤ #መውሊድ በሸሪዓችን #መሠረት የሌለው አዲስ #መጤ ቢድዓ ለመሆኑ #አመላካች ነው። #ሁሉም ሸሪዓዊ ትዕዛዛት #የአፈጻጸም ህግና ደንብ አላቸው። እርሱ (መውሊድ)ግን የለውም፣ #ምክንያቱም ሰዋዊ ስለሆነ!!! ⓲ኛ, #በመውሊድ ምክንያት ሙስሊሙ ማኅበረሰብ #ሲከፋፈል የሚያይ፤ በቂ #እውቀት የሌለው #ሙስሊም ማኅበረሰብ #በእስልምናው እንዲጠራጠር #ሰበብ ስለሚሆን። ⓳ኛ, #ሙስሊሞች በሸሪዓቸው ባልተደነገገው #የመውሊድ በዓል ሳቢያ ሲጨቃጨቁ፤ #አልፎም ለድብደባና ለሰፊ ልዩነት ሲዳረጉ የሚያይ፤ #እስልምናን ለመቀበል ጉጉት የነበረው #ሙስሊም ያልሆነ ወገን፤ #እስልምናን እንዲጠላና እንዲርቅ፣ እንዲሁም #ሙስሊሞችን በመጥፎ ምስል እንዲስል #ሰበብ ስለሚሆን፣ ⓴ኛ, #እስልምና እንድንተገብራቸው ያዘዘን ብዙ በጎ #ተግባራት አሉ። እንኳን አዲስ #ተጨማሪ ነገር ልፈጥር ይቅርና፤ እነዚያን #መሠረት ያላቸውን የታዘዝኳቸውን ሰናይ #ተግባራት አሟልቼ የማልፈጽም ስለሆንኩ እንኳን ፈጽሜ #የማልጨርሳቸውን ብጨርሳቸው እንኳን፤ እነርሱኑ #በተደጋጋሚ እፈጽማለሁ እንጅ ሌላ አዲስ #ፈሊጥ አላመጣም። ይህን የማደርገው #መልዕክተኛውን ﷺ ስለምወድ #እንጅ ስለምጠላ አይደለም። <===/====/====/====/===> https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy https://t.me/AbuImranAselefy <~~\\\~~>
Показати все...
Abu Imran Muhammed Mekonn

ዝም አንልም እኛ በህይወት እስካለን፤ ባለችው አቅማችን እንፋለማለን፤ ያበጠው ይፈንዳ ሲፈልግ ይተርተር፤ እውነት ይነገራል ቢጣፍጥም ቢመር። ያለወትን ሀሳብ 💡 ➢ @AbuImranAselefybot በሚለው ያድርሱኝ ⤵ ↪ እቀበላለሁ ↩ ⤴ ➻ በተለይ ስህተት ካዩ በፍጥነት ይጠቁሙኝ

Фото недоступнеДивитись в Telegram
"ጤነኞች አይደሉም" የምንለው በምክንያት ነው! ~ ኢማሙ ማሊክ ረሒመሁላህ “እኛ ዘንድ ሱፊያ የሚባሉ ሰዎች አሉ፡፡ በብዛት ይበሉና ከዚያ ያንጎራጉራሉ፡፡ ከዚያም ተነስተው ይጨፍራሉ” ተብለው ቢጠየቁ:– “ህፃናት ናቸው?” አሉ። “አይደሉም” አሏቸው፡፡ “እብዶች ናቸው?” ብለው ጠየቁ። “አይደሉም፣ ሸይኾች ናቸው” አሏቸው፡፡ ኢማሙ ማሊክ:– "እኔ ከኢስላም ሰዎች ይህን የሚሰራ አንድም አልሰማሁም” አሉ። [ተርቲቡል መዳሪክ: 2/53] • አልዒዝ ኢብኑ ዐብዲሰላም ረሒመሁላህ፡- “ጭፈራ ቢድዐ ነው፡፡ #አእምሮው_ጎደሎ_የሆነ እንጂ አይፈፅመውም” ብለዋል። [ፈታዋ አልዒዝ ኢብኒ ዐብዲሰላም፡ 318-319] ከስር የምትመለከቱት ሱፍዮች የሚጨፍሩበትን ድቤ የተሸከመ አሳዛኝ ፍጡር ነው። = የቴሌግራም ቻናል :- https://t.me/IbnuMunewor
Показати все...
የ “ዘመን መለወጫ” ኮተቶች ~ ኢትዮጵያ በምትከተለው ክርስቲያናዊው የዘመን አቆጣጠር መሰረት አዲስ አመት ሊገባ የያዝነው አመት እየተጠናቀቀ ነው። ታዲያ ይህን ክስተት ተከትሎ የሚፈፀሙ ከሃይማኖትችን ጋር የማይሄዱ በርካታ ጥፋቶች አሉ። ከነዚህም ውስጥ 1. ቀዳሚው ድግምትና ጥንቆላ ነው፡፡ በሃገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ነሀሴ ሊጠናቀቅ ሲል በየጠንቋዩ ቤት የሚልከሰከሱት እጅግ ብዙ ናቸው። ከዚያም አምስቱ ወይም ስድስቱ የጳጉሜ ቀናት መንገዶች በድግምት ስራዎች ይሞላሉ። በነዚህ ቀናት ማልዶ የወጣ ሰው እንዲራመዳቸው ታስቦ በጎረቤት መተላለፊያ እና ህዝብ በሚያዘወትራቸው መንገዶች ላይ ፍየሎች፣ ዶሮዎች፣ ድመቶች፣ ጥንቸሎች ወዘተ ታርደው ይጣላሉ። በደም የተነከሩ ሳንቲሞች፣ ብሮች፣ ጌጣ-ጌጦች፣ የተለያዩ ቁሳቁሶች እዚህም እዚያም ወድቀው ይታያሉ። ጥንቆላና ድግምት:- * ከኢስላም የሚያስወጡ ከባባድ ወንጀሎች ናቸው፡፡ وَاتَّبَعُوا مَا تَتْلُو الشَّيَاطِينُ عَلَى مُلْكِ سُلَيْمَانَ وَمَا كَفَرَ سُلَيْمَانُ وَلَكِنَّ الشَّيَاطِينَ كَفَرُوا يُعَلِّمُونَ النَّاسَ السِّحْرَ “በሱለይማን ዘመነ-መንግስት ሸይጧኖች የሚያነቡትንም (ድግምት) ተከተሉ። ሱለይማን ግን አልካደም (ድግምተኛ አልነበረምና።) ግና ሸይጧኖች ሰዎችን ድግምት የሚያስተምሩ ሲሆኑ ካዱ።” [በቀራህ፡ 102] ነብዩም ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ በሚናገረው ያመነ፣ በሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል።} [አሶሒሐህ፡ 3387] * ደጋሚዎችና ከነሱ ዘንድ የሚመላለሱ ሰዎች መቼም ቢሆን ስኬት የላቸውም። ጌታችን እንዲህ ይላል፡- “ድግምተኛም በመጣበት ስፍራ ሁሉ አይቀናውም።” [ጦሃ፡ 69] * ደጋሚዎች የሰዎችን ገንዘብ በማታለል የሚበዘብዙ መዥገሮች ናቸው። ገንዘቡን ለነሱ የሚሰጥ አካልም አላህ ፊት ተጠያቂ ነው። ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- {የኣደም ልጅ በቂያማህ ቀን አምስት ነገሮችን ሳይጠየቅ እግሮቹ አይንቀሳቀሱም። እድሜውን በምን እንዳጠፋው፤ ወጣትነቱን በምን እንደጨረሰው፤ ገንዘቡን ከየት እንዳመጣው፤ እንዲሁም በምን እንዳወጣው፤ ባወቀው ምን እንደሰራ።} [አሶሒሐህ፡ 946] * ደጋሚዎች የነገር ቋቶች የማህበራዊ ህይወት ጠንቆች ናቸው። የተቸገረ ደንበኛቸው መፍተሄ ፈልጎ ሲመጣባቸው በብዛት የችግሩ መንስኤ የሆነው ወይ ጎረቤቱ፣ ወይ ዘመዱ ወይ ደግሞ የቤተሰቡ አባል እንደሆነ በመጠቆም ሰዎች ውስጣቸው እንዲሻክር አለመተማመን እንዲነግስ ያደርጋሉ። በድግምቶቹ ምክንያት የጤና መጓደል፣ የትዳር መፍረስ፣ የዝምድና መቆራረጥ፣ የጎረቤቶች በጎሪጥ መተያየት አልፎም ደም የሚያቃባ ግጭት እንዲከሰት ሁሉ ሰበብ ሊሆኑ ይችላሉ። * ጠንቋይና ደጋሚ ዘንድ የሚሄድ ሰው የተነገረውን ባያምን እንኳን ከባድ ቅጣት ይከተለዋል። ነብዩ ﷺ እንዲህ ይላሉ፡- {ጠንቋይ ዘንድ ሄዶ ስለሆነ ነገር የጠየቀው የአርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም።} [ሙስሊም፡ 5957] 2. ሌላው በ “ዘመን መለወጫ” አካባቢ የሚፈፀመው ጥፋት በአንዳንድ አካባቢ ያለው ጳጉሜን ተከትሎ ለዱዓህ መሰባሰብ ነው። እነዚህ አካላት የጳጉሜ ዱዓህ “መቅቡል ነው” (ተቀባይነት ያለው ነው) በማለት ነው ወቅቱን በዱዓእ የሚያሳልፏት። በጣም የሚገርመው ለዱዓህ የሚጥጠሩት እስልምናን ያውቃሉ ሰዎችን ያስተምራሉ የሚባሉት ሰዎች መሆናቸው ነው። ነብዩ ﷺ “አላህ እውቀትን ከባሪያዎቹ መንጠቅን አይነጥቅም። ይልቁንም ዑለማዎችን በመውሰድ (በመግደል) እውቀትን ይወስዳል። ከዚያም ዓሊም እስከማይቀር ድረስ። በዚያኔ ሰዎች መሀይማንን መሪዎች አድርገው ይይዛሉ። ሲጠየቁም ያለ እውቀት ፈትዋ ይሰጣሉ። በዚህም ይጠማሉ፣ ያጠማሉም” ማለታቸው ምንኛ የሚደንቅ ሐቅ ነው?! ዲን ያስተምራሉ ተብለው የሚታሰቡት አካላት ክርስቲያናዊ አቆጣጠርን መሰረት ያደረገ ዒባዳህ እየፈፀሙ ሰዎችን ወደ ጥፋት ሲወስዱ በገሃድ ይታያሉ። 3. ሌላኛው የ “ዘመን መለወጫን” ተከትሎ የሚፈፀመው ጥፋት መስከረም አንድን ወይም እንቁጣጣሽን ማክበር ነው። አቆጣጠሩ ሀገራዊ እንጂ እምነታዊ መሰረት እንደሌለው ሊያሳምኑ በከንቱ የሚዳክሩ ሰዎች አሉ። ነገሩ ሲበዛ ግልፅ ከመሆኑ ጋር በዚህ ላይ የሚሸወድ መኖሩ እጅጉን የሚደንቅ ነው። ብቻ ለማንም እንደማይሰወር ባስብም ለማስታወስ ያክል:- * አቆጣጠሩ ወደ ሀገር ውስጥ የገባው በሚሲዮናውያን መሆኑ፣ * አመቱ ሲፃፍ መጨረሻ ላይ “ዓመተ ምህረት” መባሉ፣ * የነብዩ ዒሳን (ሰላም በሳቸው ላይ ይስፈንና) መወለድ መሰረት ያደረገ እንደሆነ መሞገታቸው * እንዲሁም ይበልጥ ለማረጋገጥ የ “ዘመን መለወጫ” ወቅት ላይ ለምሳሌ “እንኳን ከዘመነ ማቲዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ፣ ከዘመነ ሉቃስ ወደ ዘመነ ዮሐንስ፣ ... አደረሳችሁ” ማለታቸው አቆጣጠሩና በአሉ ሃይማኖታዊ መሆናቸውን አጉልተው የሚያሳዩ ነጥቦች ናቸው፡፡ ይህንን ስንል የሚደብራቸው ክርስቲያኖች አሉ። እኛኮ ዒድን አብራችሁን ካላከበራችሁ አላልንም። ሰው እንዴት የኔን እምነት ካልተከተላችሁ ብሎ ሌሎችን በአክራሪነት ይፈርጃል?! የእምነታችንን ጉዳይ ለኛ ብትተውልን። እምነታችን ሌሎች ህዝቦች በሚልለዩባቸው እምነቶች፣ ባህሎችና ልማዶች መመሳሰልን አይፈቅድም። ነብያችን ﷺ “በሰዎች የተመሳሰለ ከነሱው ነው” ብለዋል። = (ኢብኑ ሙነወር፣ ነሐሴ 26/2007) የቴሌግራም ቻናል https://t.me/IbnuMunewor
Показати все...
👉🏻 _ሁለተኛ ሚስት ማግባት ያሰኘው ሰው ለሚስ_ ቱ ይቺን ( _የኢብኑ ባዝ) መልክት እንድታነብ ይስጣት ፡፡_ _ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ) ይሄን ጥያቄ ተጠየቁ ፡⏬ 👉🏻ጥያቄ፡- ክቡር ሸኽ አንዲት ሚስት አለችኝ፡ ከእሷም ልጆች አሉኝ፡ ሁለተኛ ሚስት ለማግባት በጣም እፈልጋለው፡ ግን ስለዚህ ጉዳይና ማግባት እንደምፈልግ ሚስቴን በነገርኳት ቁጥር አይሆንም ትለኛለች ፡ ካገባህ ትቼህ እሄዳለው ልጆችህንም ጭምር እያለች ትዝትብኛለች፡ ሸይኽ እኔንም እሷንም ምን ትመክሩናላችሁ ❓ 👉🏻መልስ፡- አንቺ የአላህ ባሪያ ሆይ ! በዚህ ተግባርሽ አላህን ልትፈሪው ይገባል፡ ማግባት የባል መብት (ሃቅ) እንጂ የሚስት አይደለም ፡ ባል ሁለተኛም፣ ሶስተኛም፣ አራተኛም ማግባት ቢፈልግ ሚስት መከልከል አትችልም ፡፡ ይሄን የደነገገው ከሰባት ሰማያት በላይ ያለው (አላህ ሱብሃነሁ ወተኣላ) ነው፡፡ አላህ ለወንዶችም ሆነ ለሴቶች የሚበጀውን ያውቃል፡፡ ለዚህም ነው አላህ ይሄን የፈቀደው ለብዙ ጥቅሞች ሲል ነው፡ ከፊሎቹ ጥቅሞች ለራሷ ለሚስት ሲሆኑ ፡ ...... ከዚህ ሁሉ ዋናውና አሳሳቢው ነገር ግን ባልሽ ሁለተኛ ማግባቱን መጥላትሽ ይህ በአንቺ ላይ በጣም ከባድ የሆነ አደጋ ነው ፡ አላህ በቁርአኑ ላይ ካወረደው ህግ ከፊሉን በመጥላትሽ መልካም ስራወችሽ እንዳይታበሱብሽ የሚያስፈራ ከባድ አደጋ ነው፡ ምክኒያቱም አላህ ግልፅ በሆነ የቁርአን አንቀፅ እስከ አራት ድረስ ሚስትን መደጋገም አዟል ፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡- (وَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تُقْسِطُوا فِي الْيَتَامَىٰ فَانْكِحُوا مَا طَابَ لَكُمْ مِنَ النِّسَاءِ مَثْنَىٰ وَثُلَاثَ وَرُبَاعَ ۖ فَإِنْ خِفْتُمْ أَلَّا تَعْدِلُوا فَوَاحِدَةً أَوْ مَا مَلَكَتْ أَيْمَانُكُمْ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَلَّا تَعُولُوا " ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን ሁለት ሁለት፣ ሶስት ሶስትም፣ አራት አራትም አግቡ ፡ [ ምዕራፍ፡ ኒሳዕ፣ አንቀፅ 3 ] አላህ በቁርአን ላይ ያወረደውን ህግ መጥለት መልካም ስራወችን የግድ ያሳብሳል፡፡ አላህ እንዲህ ይላል፡- " ይህ እነርሱ አላህ ያወረደውን ስለጠሉ ነው ስለዚህ ስራወቻቸውን አበላሸባቸው " [ምዕራፍ፡ ሙሃመድ፣ አንቀፅ 9] መልካም ስራን ለማሳበስ የግድ ሁሉንም አላህ ያወረደውን ማስተባበል አይጠበቅብሽም፡ አንዲትም ብትሆን በቂ ናት፡፡ ( _ፈትዋ ኑሩን አለ - ደርብ_ https://t.me/yesunawakonjobetwuhidyabebech
Показати все...
የሱናዋ ቆንጆ በተውሂድ ያበበች

የሀቅ ዘበኛ የቢደዓ ጥላት እውነተኛ ቆንጆ አምሳያ የሌላት አቋሟ ቀጥ ያለ እንደ ወሀ ሙላት💎💎

https://t.me/yesunawakonjobetwuhidyabebech

https://t.me/yesunawakonjobetwuhidyabebech

⭕️ የሙስሊም ወንድሙ ጭንቀት ለሚያሳስበው ሁሉ የእርዳታ ጥሪ📢 አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ ውድ ሙስሊም ወንድምና እህቶች እነሆ "በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም/በአኺራ/ የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ ﷺ ነግረውናል ። የሱና ወንድማችን አብዱ ሰይድ ይባላል። በልጅነቱ በሆነ አጋጣሚ በተፈጠረ አደጋ አንድ አይኑን አጥቶ ሲኖር የነበረና በችግርና በመከራ ውስጥም ቢሆን አግብቶ ሁለት ልጆችን ወልዷል።አላህ አግርቶሎት በቀረችው በአንድ አይኑ #ቁረአንም_ሀፍዟል እስካሁን በቆየበትም ጊዜ ለሱና ባለው ጉጉትና ፍላጎት የተነሳ ከቤተሰቦቹ ተገሎና ርቆ ምንም እገዛ እንኳን የማያደርጉለትና ዘወር ብለው የማያዩት ሲሆን ስራም ትንሽም ቢሆን የቀን ስራ እየሰራ ቤተሰቦችን ያስተዳድር ነበር ። አሁን ግን መስጊድ ቁጭ ብሎ ቁረአን ሲቀራ ነው የሚውለው ። ሆኖም አሁን ደግሞ የአሏህ ውሳኔ ሆነና በሚኖርበት ግቢ በተፈጠረ የእሳት አደጋ ምክንያት እሳቱን ለመከላከል ጥረት በሚያደርግበት ወቅት የኤሌክትሪክ መብራት ይዞት ጭንቅላቱን ክፉኛ የተመታ ሲሆን ይህ አደጋም የቀረችው አንድኛው አይኑ ላይም ተፅእኖ በመፍጠሩ ከፍተኛ ህመም ሲፈጥርበት ዶክተሮችም በፍጥነት አድስ አበባ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በመሄድ ህክምና ካልወሰድክ የአይንህ ነርቭ በመነካቱ ሁለተኛውንም አይንህን ልታጣው ትችላለህ ብለውታል። 📌📌📌 ስለዚህ ይህ የሱና ወንድማችን የቀረችውን አንድ አይኑን ለማትረፍ ህክምናውን ለመጀመር በትንሹ 70,000ሺ ብር( ሰባ ሺ ብር) እንደሚያስፈልገው በዶክተሮች ተነግሮታል ።ይሄንን ብር ደግሞ አይደለም በአንድ ጊዜ በአንድ አመትም ማገኘት ስለማይችል የኛ የወንድምና የእህቶቹ እገዛና እርዳታ ያስፈልገዋል❓❓❓ 📌 ያ አሏህ... ተመልኩቱ አንዷንም የተረፈችዋንም አይኑን ሊያጣት ነው⁉️ ሲደመር ችግር ፣ ድህነት ፣ ልጆች ማሳደግ ፣ ስራ ማጣት ፣ ከቤተሰብ መገለል እያሰቃየው ነው። ✅ እኛ ደግሞ ሁለቱም አይኖች አሉን። #አልሀምዱሊላህ ፣ አሏህም በቁረአኑ እንዲህ ብሎናል (أَلَمْ نَجْعَل لَّهُۥ عَيْنَيْنِ) "ለእርሱ(ለሰው ልጅ) ሁለት አይኖችን አላደረግንለትምን?"( ሱረቱል በለድ ፣ 8) ይላል። ታዲያ አሏህ እንዲህ አይነት ፀጋ ሲውልልን ምስጋናችን ከምንገልፅባቸው መንገዶች መካከል አንዱ እንዲህ በአይናቸው የተፈተኑ ሰዎችን በማገዝና በመርዳት አሏህ የኛንም አይኖች እንዲጠብቅልን ዱዓ በማድረግ ነው። ውድ ኸይር ፈላጊ ወንድምና እህቶች ፣ ለዚህ ለተጨነቀ ወንድማችን ትንሽ ትልቅ ሳንል የህክምና ወጪውን በመሸፈን ካለበት ጭንቀት ወጥቶ ለቤተሰቡም ለድኑም የሚያገለግል ወንድማችን እንዲሆን የአቅማቹህን እንድታበረክቱ ስንል ለሁሉም ኸይር ፈላጊ ወንድምና እህቶች የእርዳታ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። በገንዘብ መርዳት ባትችሉ share በማድረግ ተባበሩት። ወንድማችንን ለመርዳት የተቋቋመ የባንክ አካውንት ቁጥር :- የኢትዮ ንግድ ባንክ #1000034096008 #የአካውንቱ ስም :- አብዱ ሰይድ መሀመድ ለበለጠ መረጃ የወንድማችን ስልክ ስልክ: #0914324157 "በዚህች ምድር የወንድሙን ጭንቀት ያስወገደ አላህ በመጪው አለም/በአኺራ/ የሱን ጭንቀት ያስወግድለታል" ሲሉ አዛኙ ነብይ ﷺ ነግረውናል ። ይሄንን ፅሁፍ ያነበባችሁ ሁሉ በአላህ ስም እጠይቃችኋለሁ በተለያዩ ቻናሎች ግሩፖች ሸር እንዲታደርጉልን ።
Показати все...
Aslamu alykum yajma Endet nachihu Erft Endet new Yewsdnewn Amana Eytewetan New? Endanresa lmastawes yakl new bechalnew mesrat ynorbnal
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.