cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

አስኳላ💚💛❤

እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉና ያዝናናሉ ብዬ የማስባቸውን ማንኛውም አይነት ፅሁፎች ከተለያዩ ቦታዎች እየለቀምኩ አቀርባለሁ። ስታነብ ታውቃለህ፣እራስህን ትመለከታለህ፣ክፉና ደጉን ትለያለክ። እዚህ የሚለቀቁ ፅሁፎች እኔ የተናገርኳቸው እና የፃፍኳቸው ብቻ አይደሉም። ከመፃፍ፣ከሶሻል ሚዲያ እና ከተለያዩ ሰዎች የሰበሰብኳቸው ጭምር ናቸው። Comment▹ @Meklite21

Більше
Рекламні дописи
3 027
Підписники
+424 години
+477 днів
+6530 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

____________________________ የተገላቢጦሽ ሆኖ ጭካኔ እና እራስ ወዳድነት የጥንካሬ ምልክቶች፤ የዋህነትና፣ ይቅርባይነት የሞኝነት ባህሪ ይመስሉናል። እንደ መልካም ስራ ጥንካሬን የሚፈትን ምን ነገር አለ?? ▸ ይቅርታ መጠየቅ ቀላል አይደለም፤ ተበድሎ ይቅር ማለት ግን ይበልጥ ይከብዳል። በድለን መርሳቱ ላይከብደን ይችላል፤ ተበድለን መርሳት መቻል ግን ጥንካሬን ይሻል። እየተጠሉ መውደድ፤ እየተዋረዱ ክብር መስጠት፤ እየተገፉ አለሁኝ ማለት፤ ጠንካራ ማንነትን ይጠይቃል። ▸ ብዙዎቻችን ደግነትን እንደ ደካማ ጎን አድረገን እናየዋለን። ትዕግስት እንደ ፍርሃት፤ ይቅር ባይነት እንደ ውርደት፤ አክብሮት እንደማስመሰል እየተቆጠረ መልካምነት ከዘመኑ ጋር የማይሄድ ባህሪ እየመሰለን እየሸሸነው ነው። ▸ ዋሽተን ማሳመን ብልጠት፤ እራሳችንን ማስቀደም ብልህንት፤ ሌሎችን ማዋረድ ክብር የሚያስገኝልን እየመሰለን ከሰብዓዊው ማንነታችን ቀስ በቀስ እንሸሻለን። 🔹እውነታው ግን ይቅር እንደማለት፤ ሌሎችን እደማክበር፤ ፍቅር ለሚገባው ፍቅር እንደመስጠት ፈታኝ እና ጥንካሬን የሚጠይቁ ምን ነገሮች አሉ? (ካህሊል ጂብራን) .......የእናቴ ልጅ-(Tame).......... ...       .......        ........... @Meklite21 ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    Telegram channel 👇👇👇 ➱💚 https://t.me/Asresee ➱💛 https://t.me/Asresee ➱❤ https://t.me/Asresee
Показати все...
👏 1
ከሰዎች ጠብቀሽ ላታገኚው ትችያለሽ፣ በወዳጆችሽ መባል ፈልገሽ አልተባልሽም ይሆናል፣ የተለየ ቦታ በሰጠሻቸው ሰዎች እንዲሁ የተለየ ስፍራ አልተሰጠሽም ይሆናል፡፡ ነገር ግን አንድ ነገር አስታውሺ የትም ሳትሔጂ፣ ማንንም ሳትመስዪ፣ ከማንም ሳትወዳጂ፣ ማንም ሳይኖርሽ፣ ምንም ሳትጨምሪ እንዲሁ ውብ ነሽ። ውበትሽም የግድ በሰዎች ሊነገርና ሊደነቅ አይገባም። ዛሬ ውብ እንደሆንሽ የነገረሽ ሰው ነገም ውብ ስለመሆንሽ እንደሚመሰክር እርግጠኛ መሆን አትችይም፡፡ አዳማቂ የማይፈልገው ውበትሽ ከትምህርት ደረጃሽ የመጣ አይደለም፣ ከስራሽ የመጣ አይደለም፣ ከቤተሰቦችሽ የመጣ አይደለም፣ ከጓደኞችሽ የመጣ አይደለም፡፡ የውበትሽ ምንጭ የአምላክሽ ልጅ መሆንሽ ነው፤ የውበትሽ መነሻ ሴትነትሽ፣ አንቺነትሽና ጥልቁ ማንነትሽ ነው። ልንገርሸ ውብ ነሽ! እስካከበርሽው ድረስ ሴት በመሆንሽ ብቻ ቆንጆ ነሽ፤ አሁን ያለሽበት ስፍራ በመገኘትሽ ብቻ ብርቱ ነሽ፣ እንዳቅምሽ ስለተንቀሳቀስሽ ብቻ ጠንካራ ሴት ነሽ፡፡ አለም የሚያደንቅልሽን ሳይሆን በአምላክሽ መንፈስ የተቃኘውን ውስጣዊ ውበትን የሚያዩ፣ የስብዕናሽን ጥልቀት የሚመረምሩ፣ እንዲሁ አይተው የሚማረኩብሽ ሰዎች እስኪከቡሽ ድረስ ውበትሽን ለእራስ ተናገሪ፣ ጥንካሬሽን ደጋግመሽ ለእራስሽ መስክሪ። የሚረዱሽን መምረጥ፣ የማይረዱሽንም የመተው ምርጫ አለሽ። ማንም እንዲያምንብሽ ዝቅ ብሎ የመለመን ግዴታ የለብሽም፡፡ አንደኛው ውበትሽ ክብርሽ እንደሆነ አስታውሺ፡፡ ለእራስሽ ብርታትና ሃይል መሆን ትችያለሽ፤ ለእራስሽ የሰጠሽውን ቦታ በመቀየር ብቻ አካባቢሽንና የተሰጠሽን ቦታ መቀየር ትችያለሽ። .......የእናቴ ልጅ-(Tame).......... ...       .......        ........... @Meklite21 ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    Telegram channel 👇👇👇 ➱💚 https://t.me/Asresee ➱💛 https://t.me/Asresee ➱❤ https://t.me/Asresee
Показати все...
5👍 3
📓ርዕስ :- ትዝታሽን ለእኔ ትዝታዬን ለአንቺ 📝ደራሲ :- እሱባለው አበራ 📅ዓ.ም :- 2012 📖የገፅ ብዛት :- 180 💚 https://t.me/Asresee 💛 https://t.me/Asreseehttps://t.me/Asresee
Показати все...
❤️እናቴ❤️… ➡እናቱን በሞት የተነጠቀው ህፃን መንደር ዳር ቆሞ ጭቃ እያቦካ ነው። አባቱ ከስራ ሲመለስ አፈርን ከውሀ እየለወሰ ሲያሽ ይመለከተዋል። #ልጄ ሆይ በጭቃ አትጫወት ልብስህ ይቆሽሻል ሰውነትም ይቦካል በል ና አሁን ተነስ ወደ ቤት ግባና ታጠብ #ልጅ አባቴ ሆይ እኛ ከጭቃ እንደተፈጠርን አልነገርከኝም ነበር ? #አባት አዎ ልጄ በሚገባ ከጭቃ ነው የተፈጠርነው #ልጅ እባክህ አባቴ እርዳኝ እና እናቴን እንደገና ልስራ ብሎ ያለቅሳል😭😭       ሁሌም ቢሆን የእናትን ዋጋ የሚያውቁ የሚያስቡት ልክ እንደ ህፃኑ ነው🙏🙏🙏 💚 https://t.me/Asresee 💛 https://t.me/Asreseehttps://t.me/Asresee
Показати все...
👍 5 2🥰 2
የሆነ መንደር ውስጥ አንድ ጅል ይኖራል። የመጨረሻ ጅል ከመሆኑ የተነሳ አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም መለየት አይችልም። እና የመንደሩ ነዋሪዎች ይመጡና "አንተ ጅል ና እስቲ ከዚህ ምረጥና ውስድ" ብለው አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም ሲያስቀምጡለት አስሯን ያነሳል። "ይሄ (አምሳውን) ይሻልሃል" ሲሉት "እምቢ ብሎ ያለቅሳል። "አይ ይሄ ጅል … ኑ ጉድ እዩ፤ ኑ ጉድ እዩ" ይሉና አስር ሳንቲም እና አምሳ ሳንቲም ድጋሚ ያስቀምጡለታል። አሁንም አስሯን ያነሳል። ኧረ ይሄ ይሻልሃል ሲሉት "እምቢ፣ እምቢ" ብሎ ያለቅሳል። በኋላ በዚህ ጅል ዘመዶቹ እያፈሩ ሄዱ። አንዱ ዘመዱ መጣና "አንተ ጅል … ሁሌ ባንተ እንዳፈርን እንቅር? ኧረ ተው ግድ የለህም፣ ተው ግድ የለህም። አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም መለየት አቅቶህ አምሳ ሳንቲም ሲሰጡህ በአስር ሳንቲም ታለቅሳለህ? ኧንደው ምናለ አምሳውን ብታነሳ?" ብሎ ሲመክረው። "ጅልስ አንተ ነህ! አምሳውን ያነሳው ቀን እኮ አያስመርጡኝም። ፧ ማነው ጅል? እነሱ ወይስ ጅል ብለው የሚያስቡት? አያችሁ እሱ ብልጥ ጅል ነው፤ እስከ ኖረ ድረስ አስር፣ አስር ሳንቲሟን እየመረጠ የተጃጃለ መስሎ ያጃጅላቸዋል፤ ምክንያቱም አምሳዋ አንዴ ነች፤ አስሯ እስካለ ትቀጥላለች። እንደነሱ ከሆነ አምሳ ሳንቲሟን የብልጠቱ፣ አስር ሳንቲሟን ደግሞ የጅልነቱ መገለጫ አድርገዋታል። ለሱ ግን አስር ሳንቲሟ የብልጠቱ መሰወሪያ፣ መደበቂያ ነች። አምሳዋን የመረጠ ቀን ጅልነቱ ያበቃል፤ ማንም አያስመርጠውማ። ምክንያቱም አውቋል፤ ነቅቷል ይሉታላ። © ዓለማየሁ ገላጋይ ........የእናቴ ልጅ-(Tame).......... ...       .......        ........... @Meklite21 ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    Telegram channel 👇👇👇 ➱💚 https://t.me/Asresee ➱💛 https://t.me/Asresee ➱❤ https://t.me/Asresee
Показати все...
4👍 3😁 2
....... ...... ጭቃ ውስጥ ሆነህ ጭቃው አበላሸኝ አይይይይ ብትል ፤ ጭቃው አይለቅህም ወጥተህ ካላታጠብክ፤ በጣም ብዙ ሰው ከጭቃው ለመውጣት ከመታገል እዛው ቆሞ ማለቃቀስ ይቀለዋል። ለተበላሹ ነገሮች አብዝቶ መጨነቅና ማሰብ ለቀጣይ እርምጃ እግራችን እንዳይነሳ አጣብቆ ይይዛል እንጂ ማስተካከያ አይሆንም፡፡ ያለፉትን እርግፍ አድርገህ ተዋቸው ለቀጣይ ህይወትህ ራስህን አዘጋጅ በፀፀት ራስህን አትቅጣ። ..........የእናቴ ልጅ(Tame) ...       .......        ........... @Meklite21 ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    Telegram channel 👇👇👇 ➱💚 https://t.me/Asresee ➱💛 https://t.me/Asresee ➱❤ https://t.me/Asresee
Показати все...
10👍 3
ዛሬም ሰላም መሆን ይቻላል! ፨፨፨፨፨፨/////////፨፨፨፨፨፨ ዛሬም ሰላምን ማውረድ፣ በሰላም መቆየት፣ በሰላም መነጋገር ይቻላል። ያለፉት መልካም የአብሮነት ጊዜያት ቢያበቁም ዛሬ በሰላማዊና ጥሩ ሁኔታ ግንኙነትን ማስኬድ ይቻላል። በተበደልኩ ስሜት ለበዛ ጥላቻ መሰናዳት አያስፈልግም፣ የማይረባ እልህ መገባት አያዋጣም። መለያየቱ የተሻለ ምርጫ እስከሆነ ድረስ ያለፉትን አስደሳች ጊዜያት በመዘንጋት ክፋትን ብቻ መቁጠር፣ በአሉታዊ መንገድ ብቻ መፈረጅ ጤነኛ አመለካከት አይደለም። መሆን ስላለበት ሆኖልና ያለፈ ግንኙነትን እንከን ብቻ መፈለግ ዋጋ የለውም። አዎ! ጀግኒት..! ምንም ቢሆን የሆነ ጊዜ የደስታሽ ምክንያት እርሱ ነበር፤ ሲንከባከብሽ፣ ሲያዝንልሽ የነበረው ሰው እርሱ ነው። ሁኔታዎች የግንኙነቱን ቀጣይነት ባለመፍቀዳቸው ማብቃቱ እንዳለ ሆኖ፣ ልዩነቱም በስምምነትና በፍቅር መሆን ይችላል። ከዛም ቦሃላ ሰላማዊ ግንኙነት መፍጠር፣ ከተበዳይነት ስሜት መውጣትና የተረጋጋ ሰላማዊ ግንኙነት መፍጠሩ ለሁለቱም አካል እጅግ ተመራጭ አካሔድ ነው። አዎ! በውስጥህ ቂምን አዝለህ፣ ለበቀል እየተንደረደርክ መቼም የተረጋጋ ህይወት ሊኖርህ አይችልም። በዳይ ሆንክ ተበዳይ፣ ጎጂም ሆንክ ተጎጂ ከፀፀት የምትድነው፣ ወደፊት የምታስበው፣ የተሻለ የምታደርገው፣ ጥሩ ተማሪ የምትሆነው በይቀርባይነት ስትታነፅ፣ በደልን ስትተውና ቂምን ስትረሳ ብቻ ነው። አብራቹ በነበራቹ ሰዓት የሚደረግልህን ነገር ካልጠበክ ስላም የማትሆንበትና ነፃ የማትሆንበት ምክንያት የለም። ሰው ተጎዳድቶ በይቅርታ ይታረቃል፤ ምንም ታሪክ አብሮ ያላሳለፈ ሰው በሰዓታት ግጪት ቢጣላ አንድ የሚያደርገውን፣ የሚያስማማውን ነገር ላያገኝ ይችላል። ለረጅም ጊዜ አብሮ የቆየ፣ ብዙ ነገር አብሮ ያሳለፈ ሰው ግን ቢያንስ አንድ የሚያስማማውና የሚያስታርቀው ነገር አያጣም። ዳግም መስማማት በምትችለው ቁርሾ ሰላምህን አትጣ። ዛሬም ሰላም መሆን ይቻላልና ልዩነትን በፀጋ፣ ጉዳትንም በይቅርታ ማለፉን ለእራስህ ብለህ እወቅበት። ማንም ሁን ብሎ ቢበድለህ ከበዳይነት ነፃ እስከሆንክ ድረስ እራስህን አረጋጋ፣ ህሊናህን ነፃ አውጣ፣ ተጠያቂነትን ከእራስህ ላይ አውርድ። (Epha A.) ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    Telegram channel 👇👇👇 ➱💚 https://t.me/Asresee ➱💛 https://t.me/Asresee ➱❤ https://t.me/Asresee
Показати все...
👍 4
ርዕስ📓 እንዴት ነሽ አራዳ ደራሲ✍  ስርግው ሀብለ ስላሴ ማጋራት መተሳሰብ ነው! ........አስኳላ💚💛❤️ ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    Telegram channel 👇👇👇 ➱💚 https://t.me/Asresee ➱💛 https://t.me/Asresee ➱❤ https://t.me/Asresee
Показати все...
👍 4
ብር ስታገኝ ገንዘብ ያጣህባቸውን ጊዚያቶች አስታውስ ያኔ ብሩን በአግባቡ ትጠቀምበታለህ !   ከልቡ እሚወድህ ሰው ስታገኝ አታስቀይመው ሰው ፈልገህ ሰው ያጣህባቸውን ጊዚያቶች መለስ ብለህ አስታውስ !    ህይወትህም ሙሉ እንዲሆን እምታመሰግንበት ምክንያት ፈልገህ አመስግን…ሁሉም ነገር ከፈጣሪ ሲሆን ነው እና ደስ እሚለው ሁሉን ነገር ከፈጣሪ ጠብቅ !            እኔ እንዲህ ነው እማምነው :)          ........አስኳላ💚💛❤️ ➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢    Telegram channel 👇👇👇 ➱💚 https://t.me/Asresee ➱💛 https://t.me/Asresee ➱❤ https://t.me/Asresee
Показати все...
👍 4 2🔥 1👏 1