cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ተዋህዶ Pictures

“ፃድቅሰ ከመ በቀልት ይፈርኢ ወይበዝ ከመ ዝግባ ዘሊባኖስ ትኩላን እሙንቱ ውስተ ቤተ እግዚአብሔር። ፃድቅ እንደ ዘንባባ ያፈራል እንደ ሊባኖስ ዝግባም ይበዛል በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ተተክለዋልና። ይህ ገጽ መንፈሳዊና መሰረታዊ የሆነውን እና የቤተክርስቲያን የጀርባ አጥንት፣ የቤተ ክርስትያን ትምህርት የሚሰጥበት ነዉ።

Більше
Рекламні дописи
452
Підписники
+124 години
-17 днів
-230 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Показати все...
"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን /አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥

https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ። 📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼ ❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

❇እንኳን ለዐብይ ፆም የመጀመርያው ሳምንት ሰንበት ዘወረደ በሰላም አደረሰን። 📌 ዘወረደ ትርጕሙ ‹ከሰማየ ሰማያት የወረደ› ማለት ነው፡፡ ከሰማየ ሰማያት የወረደውን፣ ከድንግል ማርያም የተወለደውን በጥንት ስሙ ወልድ፣ ቃል በኋላ ስሙ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ አማኑኤል የተባለውን ሰው የኾነውን አምላክ ለማመስገን ርደቱን (ከሰማየ ሰማያት መውረዱን) ለመዘከር የሚጾም ጾም ነው፡፡ ጌታችን ጾመ ከማለት አስቀድሞ ከሰማየ ሰማያት መውረዱን ከድንግል ማርያም መወለዱን መናገር አስፈላጊ ነውና የመጀመሪያው ሳምንት ‹ዘወረደ› ተብሏል፡፡ ‹‹አንተ በሰማይ ወአንተ በምድር ወአንተ በባሕር ወአንተ በየብስ፤ አንተ በሰማይ አለህ፤ በምድር በባሕርም በየብስም አለህ፤››የተባለውን በሰማይ በምድር ምሉዕ የኾነውን አምላክ ‹ወረደ፤ መጣ› ብሎ መናገር ‹ሰው ኾነ› ማለት ነው፡፡ ሰው ኾኖ መገለጡን ለማስረዳት ነው እንጂ መውረድ መውጣት የሚባሉ ቃላት በዅሉ ምሉዕ ለኾነው መለኮት አይስማሙትም፡፡ ቃላቱ ሰውኛ አነጋገርን የሚያመለክቱ ናቸውና፡፡ መተርጕማን አበው ‹‹‹ዘወረደ› ማለት ‹ሰው የኾነ› ማለት ነው›› ብለው ይተረጕማሉ፡፡ አምላካችን ሰው ከኾነ በኋላ ‹መጣ፤ ሔደ፤ ወረደ፤ ዐረገ› የሚሉ ቃላት ይስማሙታል፡፡ ምልዓቱን ሳይለቅ በሰው አካል ተወስኖ ታይቷልና፡፡ ስለዚህ ‹ወረደ› እግዚአብሔር ሰው ኾኖ መገለጡን፤ ‹ዐረገ› ደግሞ የሰውነቱን ሥራ መፈጸሙን ያሳያል፡፡ ዐረገ ስንልም ቀድሞ በሰማይ የለም ለማለት አይደለም፤ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመለኮቱ በዓለሙ ዅሉ ምሉዕ ነውና፡፡ ይህ የመጀመሪያው ሳምንት ‹ጾመ ሕርቃል› እየተባለም ይጠራል፡፡ ሕርቃል (ኤራቅሊዮስ) በ614 ዓ.ም የነበረ የቤዛንታይን ንጉሥ ነው፡፡ ለክርስቲያኖች ባደረገው ርዳታ ምክንያት አንድ ሳምንት ጾመውለት ነበር፡፡ ያላወቁ ‹ጾመ ሕርቃል› ብለው አንድ ጊዜ ጾመው ትተውታል፡፡ ጥንቱን የቅዱሳን ሐዋርያት መኾኑን ያወቁ ምእመናን ግን ዅልጊዜ በየዓመቱ ይጾሙት ነበር፡፡ ዛሬም ድረስ ጾመ ሕርቃል እየተባለ ይጠራል፡፡ የበረከት የህይወት ፆም ያርግልን።
Показати все...
3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Фото недоступнеДивитись в Telegram
Фото недоступнеДивитись в Telegram
እንኳን ለነነዌ ጾም አደረሳችሁ።✝ ✝✞✝በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ :: አሜን :: ✝✞✝ +*" ጾመ ነነዌ ወቅዱስ ዮናስ ነቢይ "*+ =>ዮናስ ማለት 'ርግብ: የዋህ' ማለት ሲሆን ከ12ቱ ደቂቀ ነቢያት አንዱ ነው:: በሰራፕታ ተወልዶ ያደገው ነቢዩ በልጅነቱ ታሞ ሙቶ ነበር:: ታላቁ ነቢይ ኤልያስ ግን 7 ጊዜ ጸሎት አድርጐ ከሞት አስነስቶታል:: (1ነገ. 17:17) እናቱ የሰራፕታዋ መበለትም ደግ ሴት ነበረች:: +ቅዱስ ዮናስ በእድሜው ከፍ ሲል የቅዱስ ኤልያስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: የነ ኤልሳዕና አብድዩም ባልንጀራ ነበረ:: ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስ ካረገ በሁዋላ: ቅ/ል/ክርስቶስ በ800 ዓመት አካባቢ የነነዌ ሰዎች ኃጢአት ከመሥፈርቱ በማለፉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ መጣ:: +"ሒድና ለነነዌ ሰዎች ንስሃን ስበክላቸው" አለው:: ከነቢያት ወገን ከሙሴና ከዳዊት ቀጥሎ የዮናስን ያህል የዋህ (ገራገር) የለምና እንቢ አለ (ሰምቶ ዝም አለ):: እግዚአብሔር እየደጋገመ ሲናገረው ግን "እንዲህ የሚዘበዝበኝ ከፊቱ ብቀመጥ አይደል!" ብሎ ወደ ተርሴስ ኮበለለ:: +ወገኖቼ አንድ ነገርን ልብ እንበል:: እንኩዋን ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዮናስ እኛ ክፉዎችም ከጌታ ፊት መሸሸት እንደማይቻል ጠንቅቀን እናውቃለን:: ታዲያ ለምን ሸሸ ቢሉ:- ጥበበ እግዚአብሔር በውስጡ ስለ ነበረበት ነው:: +ምክንያቱም ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ 3 ቀን ሌሊት ኖሮ: ሙስና (ጥፋት) ሳያገኘው መውጣቱ ለጌታ ትንሳኤ ጥላ (ምሳሌ) ነው:: ለዚህም ምስክሩ ራሱ ጌታችን ነው:: "ወበከመ ነበረ ዮናስ ውስተ ከርሠ አንበሪ ሠሉሰ ዕለተ ወሠሉሰ ለያልየ: ከማሁ ይነብር ወልደ እጉዋለ እመ ሕያው ውስተ ልበ ምድር ሠሉሰ ዕለተ: ወሠሉሰ ለያልየ" እንዲል:: (ማቴ. 12:39) +ቅዱስ ዮናስ በገንዘቡ ዋጅቶ ወደ መርከብ በገባ ጊዜ ታላቅ ማዕበል ሆነ:: የእምነት ሰው ነውና እንዲያ እየተናወጡ እርሱ በእርጋታ ተኝቷል:: እነርሱ ግን ቀስቅሰው ቢጠይቁት (እጣ ወድቆበታልና) "የእኔ ጥፋት ስለ ሆነ ወደ ማዕበሉ ጣሉኝ" አላቸው:: +እያዘኑ ቢጥሉት ታላቅ ጸጥታ ሆነ:: እነዚያ አሕዛብም እግዚአብሔርን በመስዋዕትና በስዕለት አከበሩ:: ዮናስ ግን በማዕበልና በአሣ አንበሪ ሆድ ውስጥ ለ3 ቀናት ጸለየ:: አሣ አንበሪው በ3ኛው ቀን ወደ ነነዌ ተፋው:: +ቅዱሱም "እስከ ሠሉስ ዕለት ትትገፈታእ #ነነዌ ዐባይ ሃገር" እያለ ንስሃን ሰበከ:: የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸውን አምነው ቢጸጸቱ ከሰማይ ወርዶ ከደመና ደርሶ የነበረው የእሳት ማዕበል ተመልሶላቸዋል:: +የነቢዩ ትንቢት ግን አልቀረምና ታላቁዋ ነነዌ ከ300 ዓመታት በሁዋላ ጠፍታለች:: ቅዱስ ዮናስ ግን በቀሪ ዘመኑ ፈጣሪውን እያገለገለ ኑሯል:: ጠቅላላ እድሜውም 170 ዓመት ነው:: +ዛሬ ያለን ሁላችን ሃገራችን ነነዌን ሕዝቦቿም ሕዝቦቻቸውን ከመሰልን ሰንብተናል:: በእርግጥ እንደ ነነዌ እሳት አይዘንብብን ይሆናል:: ግን የዘለዓለም እሳት ይጠብቀናል:: ንስሃ ካልገባን የሚመጣብን ቅጣት የሚከፋ ይሆናል:: =>አምላከ ቅዱስ ዮናስ እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሃ አይንሳን:: ጾሙንም የበረከት ያድርግልን:: =>+"+ ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል:: ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም:: ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ: እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል:: የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዱበታል:: በዮናስ ስብከት ንስሃ ገብተዋልና:: እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ:: +"+ (ማቴ. 12:39)    <<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
Показати все...
👍 2 1🙏 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ትዳር ✅ ትዳር ማለት 1 ወንድ 1 ሴት ማለት ነው ። ✅ ትዳር ማለት 1 እምነት 1 እውነት ማለት ነው ። ✅ ትዳር ማለት 1 እሳት 1 ውሀ ማለት ነው ። ✅ ትዳር ማለት 1 ሙሉ 1 ጎዶሎ ማለት ነው ። ✅ ትዳር ማለት 1 መጥፎ 1 ጥሩ ማለት ነው ። ✅ ትዳር ማለት 1 ጉልቻ 1 ድስት ማለት ነው ። ✅ ትዳር ማለት 1 ወንዝ 1 ውሀ የሚቀዳበት ቢሆንም ካልተንከባክበውና ካልተቻቻልንበት ሊደርቅ የሚችል ወራጅ ወንዝ ነው ፡፡ አስተውሉ ✅ ሴት ልጅን ባሏ ያመሰግናታል ። ✅ የሕይወት ዘመኑም እጥፍ ይሆናል ። ✅ ቅን ሴት ባሏን ደስ ታሰኘዋለች ። ✅ ዘመኑም በሰላም ይጨርሳል ። ✅ ደግ ሴት ዕድሏ ያማረ ነው ። ✅ እግዝአብሔርን የሚፈራ ሰውንም ወደ ዕድሉ ታደርሰዋለች መፅሐፈ ሲራክ 26፥1_3 ፈጣሪ ለሁላችን በፍቅር ያማረ ትዳር ሠላም ያለው እውነተኛ ፍቅር ይስጠን አሜን  ለዚህ ክብር ያልበቃችሁ እሱ ያብቃችሁ # እግዚአብሔር ያጣመረውን ማንም አይለየውም ።
Показати все...
1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
❤#ትዳር😘 ✅ ትዳር ማለት 1 ወንድ 1 ሴት ማለት ነው ። ✅ ትዳር ማለት 1 እምነት 1 እውነት ማለት ነው ።💕 ✅ ትዳር ማለት 1 እሳት 1 ውሀ ማለት ነው ።💞 ✅ ትዳር ማለት 1 ሙሉ 1 ጎዶሎ ማለት ነው ። ✅ ትዳር ማለት 1 መጥፎ 1 ጥሩ ማለት ነው ።❤ ✅ ትዳር ማለት 1 ጉልቻ 1 ድስት ማለት ነው ።😘 ✅ ትዳር ማለት 1 ወንዝ 1 ውሀ የሚቀዳበት ቢሆንም ካልተንከባክበውና💞 ካልተቻቻልንበት ሊደርቅ የሚችል #ወራጅ ወንዝ ነው ፡፡ #አስተውሉ ✅ ሴት ልጅን ባሏ ያመሰግናታል ። ✅ የሕይወት ዘመኑም እጥፍ ይሆናል ። ✅ ቅን ሴት ባሏን ደስ ታሰኘዋለች ። ✅ ዘመኑም በሰላም ይጨርሳል ። ✅ ደግ ሴት ዕድሏ ያማረ ነው ። ✅ እግዝአብሔርን የሚፈራ ሰውንም ወደ ዕድሉ ታደርሰዋለች #መፅሐፈ ሲራክ 26፥1_3 ❤ፈጣሪ ለሁላችን በፍቅር ያማረ ትዳር ሠላም ያለው እውነተኛ ፍቅር ይስጠን አሜን ለዚህ ክብር ያልበቃችሁ እሱ ያብቃችሁ # እግዚአብሔር ያጣመረውን ማንም አይለየውም ። ═════════❁✿❁ ═════════
Показати все...
እሱ የፈቀደ ቀን ላይ ግን ፈጣሪ ፍርዱን ይሰጣል
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
"...እንደማይሰማ ቸል ይላል፤ እንደማያይ ዝም ይላል፤ እንደማያዉቅ ይታገሣል፤ እንደማይሰጥ ያዘገያል...' ( ቅዳሴ ሠለስቱ ምዕት)
Показати все...
👍 2
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.