cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

The Jubair || The ጁበይር

ሀሳብ አስተያየታቹን በ @thejubair ያድርሱኝ ይህ የ The Jubair official የቴሌግራም ገፅ ነው በቻናላችን አጫጫር ዳዕዋዎችን | ፈጣን መረጃዎችን | አጫጭር የቁረዐን አያቶችን| እንዲሁም ሌሎች እጅግ አስተማሪ ነገሮችን በአላህ ፍቃድ ያገኛሉ . ይህን ሁሉ ቻናላችንን Join በማድረግ ብቻ ሀያ ቢስሚላህ 😊 ሹክረን ;)

Більше
Рекламні дописи
2 633
Підписники
+224 години
-57 днів
-1730 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

🛑👉የደስታ ቁልፍ! ~ የሰው ልጆች በዱንያም በአኺራም የተሳካ፣ አስደሳች እና ያማረ ሕይወት መኖርን ይመኛሉ።  ደስታና ስኬትን ለማግኘትም ገንዘባቸውን፣ ጊዜያቸውንና የህይወታቸውን ውድ ነገር ሳይቀር ይገብራሉ።  ነገር ግን ብዙውን ጊዜ የፈለጉትን ደስታ አያገኙም፤ ቢያገኙም ጊዜያዊ ነው። ምክንያቱም ዘላለማዊ ደስታ በደስታም ሆነ በችግር ውስጥ ያለ ደስታ ሲሆን ይህን የሚያገኘው ደግሞ ሙእሚን ብቻ ነው። ይህን አስመልክቶ ሙስሊምና ሌሎችም በዘገቡት ከሱሐይብ በተወራዉ ሐዲስ ረሱል صلى الله عليه وسلم እንዲህ ይላሉ፦ " عَجَبًا لأمرِ المؤمنِ إِنَّ أمْرَه كُلَّهُ لهُ خَيرٌ وليسَ ذلكَ لأحَدٍ إلا للمُؤْمنِ إِنْ أصَابتهُ سَرَّاءُ شَكَرَ فكانتْ خَيرًا لهُ وإنْ أصَابتهُ ضَرَّاءُ صَبرَ فكانتْ خَيرًا لهُ ". رواهُ مُسْلِمٌ. "የሙዕሚን ነገር ይገርማል፤ የሙዕሚን ሁሉ ነገሩ መልካም ነው ይህ ለማንም አይሆንም  ለሙዕሚን እንጂ። መልካም ነገር ከገጠመው አላህን ያመሰግናል በዚህም መልካም ይሆንለታል። አስቸጋሪ ነገር ቢገጥመው ይታገሳል ይህም መልካም ይሆንለታል።" የዱንያ አዙሪት ከነዚህ ሁለት ነገሮች የማይወጣ መሆኑ የታወቀ ነው! " ተድላና ችግር" ሁለቱም ለሙእሚን መልካም ከሆኑ ታዲያ የሰው ልጆች ደስታና ስኬትን ለማግኘት ሙዕሚን ከመሆን ሌላ ምን አማራጭ አላቸው? 🛑👉ጥያቄው  ደስታን እንዴት ማግኘት እንችላለን? አላህ ዐዘ ወጀል በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል፡ قال الله تعالى: (مَنْ عَمِلَ صَالِحًا مِنْ ذَكَرٍ أَوْ أُنْثَى وَهُوَ مُؤْمِنٌ فَلَنُحْيِيَنَّهُ حَيَاةً طَيِّبَةً وَلَنَجْزِيَنَّهُمْ أَجْرَهُمْ بِأَحْسَنِ مَا كَانُوا يَعْمَلُونَ)، النحل ٩٧ "ከወንድ ወይም ከሴት እርሱ አማኝ ሆኖ በጎን የሰራ መልካም ኑሮን በእርግጥ እናኖረዋለን፡፡ ይሠሩትም ከነበሩት ነገር በመልካሙ ምንዳቸውን እንመነዳቸዋለን።" (ነህል :97) ﴿ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ طُوبَى لَهُمْ وَحُسْنُ مَآبٍ ﴾ [الرعد: 29]. "እነዚያ ያመኑትና መልካም ሥራዎችን የሠሩት ለእነሱ ደግ ኑሮ መልካም መመለሻም አላቸው።" (ረዕድ :29) 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
Показати все...
4
🔴   ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 إِنَّ السَّاعَةَ لَآتِيَةٌ لَّا رَيْبَ فِيهَا وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يُؤْمِنُونَ ሰዓቲቱ በእርግጥ መጪ ናት፡፡ በእርሷ ጥርጥር የለም፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም፡፡ وَقَالَ رَبُّكُمُ ادْعُونِي أَسْتَجِبْ لَكُمْ ۚ إِنَّ الَّذِينَ يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِي سَيَدْخُلُونَ جَهَنَّمَ دَاخِرِينَ ጌታችሁም አለ «ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡ እነዚያ እኔን ከመግገዛት የሚኮሩት ተዋራጆች ኾነው ገሀነምን በእርግጥ ይገባሉ፡፡ اللَّهُ الَّذِي جَعَلَ لَكُمُ اللَّيْلَ لِتَسْكُنُوا فِيهِ وَالنَّهَارَ مُبْصِرًا ۚ إِنَّ اللَّهَ لَذُو فَضْلٍ عَلَى النَّاسِ وَلَٰكِنَّ أَكْثَرَ النَّاسِ لَا يَشْكُرُونَ አላህ ያ ለእናንተ ሌሊትን በውስጡ ልታርፉበት (ጨለማ) ቀንንም (ልትሠሩበት) የሚያሳይ ያደረገላችሁ ነው፡፡ አላህ በሰዎች ላይ በእርግጥ የችሮታ ባለቤት ነውና፡፡ ግን አብዛኛዎቹ ሰዎች አያመሰግኑም፡፡ ذَٰلِكُمُ اللَّهُ رَبُّكُمْ خَالِقُ كُلِّ شَيْءٍ لَّا إِلَٰهَ إِلَّا هُوَ ۖ فَأَنَّىٰ تُؤْفَكُونَ ይሃችሁ ጌታችሁ አላህ ነው፤ የነገሩ ሁሉ ፈጣሪ ነው፤ ከርሱ ሌላ አምላክ የለም፤ ታዲያ (ከእምነት) ወዴት ትመለሳላችሁ፡፡ •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_318 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
Показати все...
🥰 1
ፈገግታ ~ "በወንድምህ ፊት ፈገግ ማለትህ ምፅዋት ነው" ''ፈገግታ የህይወት ማጣፈጫ ቅመም ነው። ''የፈገግተኛ ሰዎች አቃ ፈገግተኛ ካልሆኑት በብዙ አጥፍ የተሻለ ይሸጣል። ''ፈገግታኞች የተጋጋሉ የቁጣ እሳቶችን ያበርዳሉ። "ፈገግተኛ ሰው አብሮ ሲኖር ሰዎች ይደሰቱበታል፣ሲጠፋ ይናፍቁታል። "ፈገግተኛን ሰው ሰዎች ቶሎ ይቀርቡታል። ስለዚህ ፈገግታን እንደ ልብስ ገዝተህም ቢሆን ተላበሰው! 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
Показати все...
🥰 5
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ጌታህ የምተወደውን ነገር ሲከለክልህ የተከለከልክበትን ምክንያት አታውቅም #ሲተካህ ቢሆን እንጂ *በማታውቀው ነገር ላይ ብዙ አትበል ለማለት ነው። 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
Показати все...
👍 4
🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 يَا أَبَتِ لَا تَعْبُدِ الشَّيْطَانَ ۖ إِنَّ الشَّيْطَانَ كَانَ لِلرَّحْمَٰنِ عَصِيًّا «አባቴ ሆይ! ሰይጣንን አትግገዛ፡፡ ሰይጣን ለአልረሕማን አመጸኛ ነውና፡፡ يَا أَبَتِ إِنِّي أَخَافُ أَن يَمَسَّكَ عَذَابٌ مِّنَ الرَّحْمَٰنِ فَتَكُونَ لِلشَّيْطَانِ وَلِيًّا «አባቴ ሆይ! እኔ ከአልረሕማን ቅጣት ሊያገኝህ ለሰይጣንም ጓደኛ ልትኾን እፈራለሁ፡፡» قَالَ أَرَاغِبٌ أَنتَ عَنْ آلِهَتِي يَا إِبْرَاهِيمُ ۖ لَئِن لَّمْ تَنتَهِ لَأَرْجُمَنَّكَ ۖ وَاهْجُرْنِي مَلِيًّا (አባቱም) «ኢብራሂም ሆይ! አንተ አምላኮቼን ትተህ የምትዞር ነህን ባትከለከል በእርግጥ እወግርሃለሁ፡፡ ረዥም ጊዜንም ተወኝ» አለ፡፡ قَالَ سَلَامٌ عَلَيْكَ ۖ سَأَسْتَغْفِرُ لَكَ رَبِّي ۖ إِنَّهُ كَانَ بِي حَفِيًّا «ደህና ኹን፡፡ ወደፊት ከጌታዬ ምሕረትን እለምንልሃለሁ፡፡ እርሱ ለኔ በጣም ርኅሩኅ ነውና» አለ፡፡ [ ሱረቱል መርየም : 44-47] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_317 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ      ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ቀን 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
Показати все...
🥰 1
🔴  ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 قُل لَّن يُصِيبَنَا إِلَّا مَا كَتَبَ اللَّهُ لَنَا هُوَ مَوْلَانَا ۚ وَعَلَى اللَّهِ فَلْيَتَوَكَّلِ الْمُؤْمِنُونَ «አላህ ለኛ የጻፈልን (ጥቅም) እንጂ ሌላ አይነካንም፡፡ እርሱ ረዳታችን ነው፡፡ በአላህ ላይም ምእመናን ይመኩ» በላቸው፡፡ [ሱረቱ ተውባ - 51] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_316 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ       ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽታችንን 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
Показати все...
🔴  ቀናችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ቀናችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 أَإِذَا مِتْنَا وَكُنَّا تُرَابًا وَعِظَامًا أَإِنَّا لَمَدِينُونَ «በሞትንና ዐፈር አጥንቶችም በሆን ጊዜ እኛ በእርግጥ እንመረመራለን?» (የሚል)፡፡ قَالَ هَلْ أَنتُم مُّطَّلِعُونَ እናንተ ተመልካቾች ናችሁን? ይላል፡፡ فَاطَّلَعَ فَرَآهُ فِي سَوَاءِ الْجَحِيمِ ይመለከታልም፤ በገሀነም መካከልም (ጓደኛውን) ያየዋል፡፡ قَالَ تَاللَّهِ إِن كِدتَّ لَتُرْدِينِ ይላል «በአላህ እምላለሁ፤ በእርግጥ ልታጠፋኝ ቀርበህ ነበር፡፡ وَلَوْلَا نِعْمَةُ رَبِّي لَكُنتُ مِنَ الْمُحْضَرِينَ «የጌታየም ጸጋ ባልነበረ ኖሮ ወደ እሳት ከሚቀርቡት እሆን ነበር፡፡» أَفَمَا نَحْنُ بِمَيِّتِينَ (የገነት ሰዎች ይላሉ) «እኛ የምንሞት አይደለንምን? إِلَّا مَوْتَتَنَا الْأُولَىٰ وَمَا نَحْنُ بِمُعَذَّبِينَ «የመጀመሪያይቱ መሞታችን ብቻ ስትቀር፡፡ እኛም የምንቅቀጣ አይደለንምን?» (ይላሉ)፡፡ إِنَّ هَٰذَا لَهُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ ይህ (ለገነት ሰዎች የተወሳው) እርሱ በእርግጥ ታላቅ ዕድል ነው፡፡ لِمِثْلِ هَٰذَا فَلْيَعْمَلِ الْعَامِلُونَ ለዚህ ብጤ ሠሪዎች ይሥሩ፡፡ [ሱረቱ ሷፋት 53-61] •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_315 •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ       ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ቀን🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
🔖ቤት ውስጥ መሆን ለሴት ልጅ ራሱን የቻለ ዒባደህ ነው። ተገዳ ወይም አማራጭ አጥታ ካልሆነ በስተቀር ሙስሊም ሴት ወጣ-ገባ ማለት ልታበዛ አይገባም። ከደጋግ ቀደምት ሴቶች መካከል አንዷ የሆኑት ፋጢመህ ቢንቱልዓጣር በህይወታቸው 3 ጊዜ ብቻ እንጂ ከቤት ወጥተው አያውቁም ነበር፤ ⓵- ያገቡ ቀን፣ ⓶- ሐጅ ያደረጉ ቀንና ⓷- የሞቱ ቀን ብቻ!:: 👉አንቺስ እህቴ! በቀን ስንቴ ነው የምትወጪው!? 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
Показати все...
👍 6
🔴  ምሽታችንን ቁርዐን በማስተንተን እንጀምር        አላህ ምሽታችንን ሰላማዊ ያድርግልን 🤍 •●° ውስጠ-ሰላም #ክፍል_314 يَوْمَ تَرَى الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ يَسْعَىٰ نُورُهُم بَيْنَ أَيْدِيهِمْ وَبِأَيْمَانِهِم بُشْرَاكُمُ الْيَوْمَ جَنَّاتٌ تَجْرِي مِن تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا ۚ ذَٰلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ ምእመናንንና ምእምናትን በስተፊቶቻቸው፣ በቀኞቻቸውም ብርሃናቸው የሚሮጥ ሲኾን በምታያቸው ቀን (ምንዳ አልላቸው)፡፡ ዛሬ ብስራታችሁ በውስጦቻቸው ዘውታሪዎች ስትኾኑ ከሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈስሱባቸው ገነቶች ናቸው (ይባላሉ)፡፡ ይህ እርሱ ታላቁ ዕድል ነው፡፡ [አል-ሐዲድ - 12] •●° ውዱን የቁርዐን ስጦታ       ለውድ ሰዎች አድርሱልኝ ↪😊 •●° መልካም ምሽት 🤍 🟥 Tg : https://t.me/Thejubair00 .
Показати все...
4
~አብዝተው ኢስቲغፋር ማድረግ . የገራላቸው ሰዎች አላህ ከቅጣቱ  ሊጠብቃቸው የፈለጋቸው ሰዎች ናቸው። : وَمَا كَانَ اللَّهُ مُعَذِّبَهُمْ وَهُمْ يَسْتَغْفِرُونَ «መሓርታን እየጠየቁት አላህ የሚቀጣቸው አይደለም።» ኢስቲግፋር እያበዛን ሀባይቢ ! 🟥 Telegram : https://t.me/Thejubair00 .
Показати все...
👍 1