cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

fun🤩& facts🤔

*memes, * facts *useful informations

Більше
Рекламні дописи
540
Підписники
-124 години
-57 днів
-1430 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

Фото недоступнеДивитись в Telegram
አንድ ጊዜ አንድ ሰው በአንድ ፎቅ ቤት ስር ተቀምጦ በተመስጦ ስልኩን እየነካካ ሳለ በድንገት ከላይ “የአንድ ብር ሳንቲም” ጭንቅላቱ ላይ ነጥራ አጠገቡ አረፈች፡፡ ይህ ሰው በጣም ስላመመው ጭንቅላቱን በማሻሸት ወደላይ በማየት የመታውን ሰው ለመሳደብ ሲቃጣው ጭንቅላቱን የመታችው የአንድ ብር ሳንቲም መሆኗን በማየቱ አንስቶ ኪሱ በመክተት ጸጥ አለ፡፡ እንደገና ተመሳሳይ ሁኔታ ሲከሰት አሁንም የለመዳት አንድ ብር በመሆኗ ቀና ብሎ ከመጮህ ይልቅ ህመሙን ታግሶ አንድ ብሯን በማንሳት ኪሱ ከተተ፡፡ ሁኔታው ለሶስተኛ ጊዜ ከተደገመ በኋላ በአራተኛው ጊዜ ጭንቅላቱ ላይ ያረፈው የለመደው የአንድ ብር ሳንቲም ሳይሆን ጠጠር ነበር፡፡ በዚያን ጊዜ ነበር፣ እጅግ በተቆጣ ድምጽ “ማን ነው የመታኝ? በማለት ወደላይ ቀና ያለው፡፡ በግል ሕይወታችንም ሆነ በማሕበራዊ ግንኑነታችን፣ “ጥቅም እስካገኘሁ ድረስ ምን ቸገረኝ” በማለት የምናልፋቸው ጎጂ ነገሮች አጉል ተጽእኖ መጠነ ሰፊ ነው፡፡ እኛ ጊዜያዊ ጥቅም ስላገኘን ብቻ የተውናቸው ጤና ቢስ ተግባሮች የእኛኑ አመለካከትና ባህሪይ እያበሰበሱ መሄዳቸው አይቀርም፡፡ በተጨማሪም፣ በእኛ ዝምታ ምክንያት ተግባሩን የሚፈጽሙት ሰዎች እርማት ስለማያገኙና፣የእነሱን አጉል ምሳሌነት በመከተል ያንኑ ተግባር ወደመፈጸም የሚሄዱ የሕብረተሰቡ ክፍሎች ስለሚበራከቱ የበሰበሰ ሕብረተሰብ መፍጠሩ አይቀርም፡፡** *** ምን አገባኝ ብለን የተውነው ስንት አለ? እናንብብ እንወያይ ነጻ እንውጣ ንበብ ለንባብ**
Показати все...
👍 3
የማሪያኔ ባችሜየር ልብ የሚነካ ታሪክ ማሪያኔ ባችሜየር ሰኔ 3 ቀን 1950 በጀርመን ተወለደች! ለልጇ አና በጣም አፍቃሪ እና ታማኝ እናት ነበረች። አና የማሪያን ህይወት ብርሃን ነበረች ደስተኛ እና ብሩህ ትንሽ ልጅ በዙሪያዋ ላሉ ​​ሰዎች ሁሉ ታላቅ ደስታን የምታመጣ ህፃን ነበረች ማሪያ ቤታቸውን በፍቅር እና በደስታ በመሙላት ለአና ጥሩ ሕይወት እንዲኖራት ጠንክራ ትሰራ ነበር የሚያሳዝነው ግን በ1981 ይሄ ሁሉ ነገር ተዘበራረቀ መጋቢት 5, 1981 አና የሰባት ዓመት ልጅ እያለች ክላውስ ግራቦቭስኪ በተባለ ሰው ተደፍራ ​​ተገደለች። ከዚያ በኋላ ያለው ህመም ለ ማሪያ በጣም ከባድ ነበር ማሪያን የምትወዳትን ሴት ልጅ በሞት ማጣቷን መቀበል አልቻለችም ! በ1981 በክላውስ ግራቦቭስኪ የፍርድ ሂደት ላይ ማሪያን ዓለምን ያስደነገጠ ነገር አደረገች የፍርድ ሂደቱ በተጀመረ በሶስተኛው ቀን ሽጉጡን በድብቅ ወደ ፍርድ ቤት ይዛ ገብታ ግራቦቭስኪን በጥይት 8 ጊዜ ተኩሳ ፍትህን በእጇ አስገባች ! ለድርጊቷ የእስር ቅጣት ቢፈረድባትም ነገር ግን ብዙ ሰዎች ለአና ብላ ያደረገችው ነገር ስለሆነ ብዙ ሰው ትክክለኛ ነገር እንዳደረገች አስበዋል ! ማሪያን በሴፕቴምበር 17፣ 1996 ከዚህ አለም በሞት የተለየች ሰሆን ነገር ግን የእናት ታሪክ የእናት ፍቅር ምን ያህል እንደሆነ በማርያን አይነተናል ልጇን በሞት በማጣቷ  የሚደርስባትን ጥልቅ ህመም የሚያሳይ ልብ የሚነካ ታሪክ ለ አለም አስተላልፋለች !
Показати все...
👍 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ይደንቃል ይገርማል እነዚህን Abby Hensel እና Brittany Hensel የተሰኙ ተጣብቀው የተፈጠሩ መንትዮች (Conjoined twins) አስታወስካቸው ኣ? - Joshua Bowling የተባለ የWar Veteran ነርስ፣ ከአንደኛዋ ጋራ፣ ማለትም ከAbby Hensel ጋራ ባለፈው ጋብቻ ፈጽሟል። ሁለተኛዋ ግን አሁንም Single ናት። - አካላቸው አንድ ቢሆንም፣ ሁለቱም እህትማማቾች የተለያየ ጭንቅላት ስላላቸው፣ የተለያየ ቴስት፣ ባህሪ፣ አመለካከት፣ አቋም፣ ፍላጎት፣ እና ሙድ አላቸው። ግን ተግባብተው እና ተናብበው ተዋድደው ይኖራሉ። ሁለቱም ተምረው፣ ተመርቀው፣ መምህር ሆነው ያገለግላሉ። አንድ ደሞዝ ለሁለት ይበላሉ። - ይኸው አንዷ ደግሞ ከአንዱ ወንድ ጋራ ተዋውቃ፣ ተላምዳ፣ ተጀናጅና፣ ተዋድዳ፣ ተፋቅራ አገባችው። እንደፐፈጣሪ ፈቃድ በቅርቡ ልጅ ትወልዳለች። ጌታዬ። እነዚህ ሴቶች ተጋፍጠው ካሸነፉት ችግር እና Wierdoነት አንፃር። እነዚህ ተጣባቂዎች ጭራቅ መስለው፣ የሰዉን አፍ ችለው ከተቋቋሙት Challenge አንፃር ካየኸው - አንተን የሚያጋጥምህ መከራ፣ ዲፕረሽን ውስጥ የሚከትህ ጉዳይ፣ ሙድህን አጥፍቶ Down የሚያደርግህ ነገር Insignificant ነው። ምንም ማለት ነው። ◦ የሠው ልጅ ጠንካራ ነው። ◦ የሠው ልጅ የሚገርም ፍጥረት ነው። ◦ የሠው ልጅ የማይወጣው Challenge የለም። ©Eyob mihereteab @Amazing_Fact_433 @Amazing_Fact_433
Показати все...
👍 3
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ይህ ሰው ድሀ፣ ለማኝ ወይም ቤት አልባ አይደለም ይልቅስ በአለም ስነ-ጽሁፍ ገዝፎ የሚታየው ሊዮ ቶልስቶይ ነው። ቶልስቶይ በሩሲያ ውስጥ ሰፊ መሬት እና ትልቅ ሀብት የነበረው ቢሆንም፤ ሀብቱን ሁሉ ለድሆች፣ ለምስኪኖች፣ ለችግረኞች እና ለቤት ፈላጊዎች በመስጠት የራሱን ህይወት ባልተጋነነ መለኩ የኖረ ሰው ነው። ታዋቂ ከምንላቸው አባባሎችሁ መኃል፦ "ስለ ሀይማኖት ብዙ አትንገረኝ፣ ነገር ግን በድርጊትህ ውስጥ ሃይማኖትህን እንዳይህ ፍቀድልኝ።" “ህመም ከተሰማህ በህይወት አለህ፤ የሌሎችን ህመም ከተሰማህ ግን በውኑ አንተ ሰው ነህ”
Показати все...
👍 6 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሁላችንም ቤተሰቦቻችን ጠዋት ተነስተው ካርቶን ቀደው ግማሹን እሳት ግማሹን ማራገቢያ ያደርጉታል። በምስሉ ላይ ያለችው የ67 አመት ሴትም ማራገቢያ የሚያስፈልጋት እሳት የጎረሰች እናት ትመስለው ይሆናል ምናልባት የቀዩ ጦር አባል የነበረው መቶአለቃ አባቷ የወታደር ልጅ ስለሆነች ይሆናል። ✅️ለ7 ወንድም እና እህቶቿ ታላቅ እህታቸው ነች ህፃን እያለች አባቷ እስርቤት በመግባቱ ነበር ገና በልጅነቷ ነበር ወደስራ ለመግባት የተገደደችው። የችግርን ብፌ በያይነት ያነሳችው ሴት በአንድ ጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ውስጥ የመፅሃፍት ክፍል ጠባቂነት ብትቀጠርም ስራዋ ቀኑን ሙሉ በመሆኑ ተጨማሪ ገቢ ማግኘት አልቻለችም ነበር። ታዲያ በነዚህ መሃል በአሰሪዋ የግል ችግር ስራዋን አጥታ ስራ በፈታችበት ወቅት ወረቀቶችን በመሰብሰብ ለምን ወደ ምርት አልቀይርም ብላ የተነሳችው። በሰፈሯ የተጣሉ ወረቀቶችን ከመሰብሰብ እስከ በኪሎ ግዢ እየታገዘች ምርቷን ማስተዋወቅ የጀመረችው። ከተጣሉ ወረቀቶች የሚገኘውም ምርት ቲቪ ፣ ፍሪጅ ፣ ምግቦችን ከፋብሪካ ስንገዛ የሚታሸግበት ካርቶን ነበር አዎ ካርቶን ማምረት። ⭐ዛሬ ላይ ቢሊየነር ነች እሷ ብቻ አይደለችም ወንድሟ እንዲሁም ባሏ እሷ በመሰረተችው ፋብሪካ ውስጥ ማኔጀር ሲሆኑ እነሱም ሳይቀር ቢሊየነር አድርጋቸዋለች። አባቴ አጠገብህ ያሉ ነገሮችን ተመልከት.ትላለች ዙሪያህ ያሉ ነገሮችን አትናቅ ዛሬ ቻይና ላይ ውስጥ ተገኝተህ "የቆሻሻዋ ንግስት ማነች?" ብትል ቻይኖች "张茵,你想要什么?" ዣንግ ዪን ትባላለች ምን ፈልገህ ነው? ማለት ነው።
Показати все...
👍 2
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ጂኒየሶች እና እንግዳ ጠባያቸው ክፍል ሁለት ፪) ቪንሰንት ቫን ጎግ ዝነኛ የደች ሰአሊ ነው። ዝነኛ የሆነው ግን ከሞተ በኋላ ነበር። ጎግ የአእምሮ ህመም ተጠቂና በማህበራዊ ህይወቱም ደካማ ነበር። ታድያ ጎግ አንዲት ሴት አፈቀረ። ይቺ ያፈቀራት ሴት ደግሞ ጆሮውን እንደወደደችው ነገረችው። በምላሹ ጎግ ከጆሮግንዱ ላይ ቆርጦ ጆሮውን ልኮላታል። @Amazing_Fact_433 @Amazing_Fact_433
Показати все...
😱 4👍 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
#አንዲት ሴት ቆንጆ ስለሆነች ብቻ የምትወዷት ከሆነ ፍቅራችሁ እውነተኛ ፍቅር አይደለም። ነገ ያቺ ያፈቀራችሃት ሴት ታረጅና ፣ ድንገት ትታመምና አስቀያሚ ልትሆን ትችላለች። ምናልባትም አፍንጫዋ ላይ ቀዶ ጥገና ይደረግላት ይሆናል። ያን ጊዜ ፍቅራችሁን ምን ይውጠዋል? ፍቅር ውስጥ ያስገባችሁ ውቧ አፍንጫዋ ነበር። አሁን ያ አፍንጫዋ የለምና ፍቅራችሁም ይጠፋል። ሴትዬዋ ሸክም ትሆንባችኋለች። በምክንያት ባልተሞላ ልብ የሚመጣው ፍቅር ግን በነገሮች ላይ ጥገኛ አይደለም። ይህን ፍቅር ከሰውዬው ውበት ወይም እውቀት ወይም ተሰጥኦ ጋር የሚያገናኘው ምንም ነገር አይኖረውም። በፍቅር ትምሉና ያን ፍቅር ማካፈል ትፈልጋላችሁ። እናም ለመቀበል ዝግጁ ለሆነው ሁሉ አመስግናችሁ ትሰጡታላችሁ። ስጦታ ነው የምትሰጡት ስለ ሞላችሁ ስለተረፋችሁ ነው። #ኦሾ /Osho
Показати все...
👍 4 1
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በ 1915 በሳውዝ ካሎሪና Essie Dunbar የተባለች ሴት ሰዎች እንደመሰላቸው በ Epilepsy ሕመሟ ምክንያት በደረሰባት አደጋ ሕየወቷ ያልፋል። መሞቷንም ለማረጋገጥ Dr.briggs የተባሉ ግለሰብ በቦታው ተገኝተው ከመረመሯት በኋላ There is no signs of life not breathing, nor pulse. በማለት መሞቷን ያረጋግጣሉ። በቀጣዩ ቀን በተደረገው የቀብር ስነስርዓት መገባደጃ ላይ የሬሳ ሳጥኑ ላይ አፈር እየተመለሰ ሳለ ለቀብሩ አርፍዳ የደረሰችው የሟች እህት እህቴን ለመጨረሻ ጊዜ በዓይኔ ሳላያት አትቀብሯትም ብላ አጥብቃ በመለመኗ የሬሳ ሳጥኑ እንደገና ወጥቶ ሲከፈት Essie Dunbar ቀና ብላ እህቷን በፈገግታ ተመለከተቻት። በዚህ ጊዜ ሶስት ቀብር አስፈጻሚዎች በድንጋጤ የቀብር ጉድጓድ ውስጥ የወደቁ ሲሆን ብዙዎች የሙት መንፈስ መስላቸው ከመቃብር ቦታው ፈርጥጠው ሮጠዋል። የእህቷ አጥብቆ መለመን ከተቆፈረላት ጉድጓድ ባያስወጣት ኖሮ Essie Dunbar በተቀበረችበት ትነቃ ነበር ወይስ የመንቃቷ ምክንያት እህቷ ናት???
Показати все...
🤩 3 1
ኮሊንዳ ጋርበር የክሮሽያ ፕሬዝደንት ኮሊንዳ ጋርበር ነች ። እና ፈታ ማለት ስለምትወድ ፡ ካሪቢያን ደሴቶች ላይ እንዲህ በጡት ማስያዣ እና በፓንት ሆና ዝንትንት እያለች ባገኛትና ሰላም ብላት ብለህ አስበው ..... ሃይ እንዴት ነሽ ስትላት እሷም ደስ ከሚል ፈገግታ ጋር ሰላም እንዴት ነህ ትልሃለች ፡ ከዛ በቁምጣ ሆነህ ከባህሩ ዳር ከሷ እርምጃ እኩል እየተራመድህ ወሬ ለመጀመር ያህል እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ ፡ ትንሽ ስራዬ ውጥረት የሚበዛው በመሆኑ መዝናናቱ ላይ ብዙም አይደለሁም ፡ ስትላት ኦው ጥሩ ነው ኢትዮጵያን በስራ አጋጣሚ አውቃታለሁ ትልህና ፡ ምን ላይ እየሰራህ ነው ብላ ትጠይቅሃለች ፡ እኔ የግብርና ምርቶችን ኤክስፖርት አደርጋለሁ ፡ አንቺስ ? ቅድም ኢትዮጵያን በስራ አጋጣሚ አውቃታለሁ ስትይ ሰምቻለሁና ፡ ስራሽ ምንድነው ? ብለህ ስትጠይቃት ልብን በሚያሞቅ ፈገግታ ተሞልታ ፡ እኔማ የክሮሽያ ፕሬዝደንት ነኝ ፡ በዛ አጋጣሚ ነው ሃገራችሁን የማውቃት ብላ ዞር ስትል አንተ ፌንት አርገህ ወድቀሃል. .... አትሰማትም ። .............. 🔵ኮሊንዳ በርገር ፡ በዩናይተድ ስቴትስ አሜሪካ የክሮሽያ አምባሳደር ሆና ሃገሯን አገልግላለች ከዚያም የመጀመሪያዋ ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የክሮሽያ የአውሮፓ ጉዳዮች ሃላፊ በመጨረሻም እስከባለፉት ሁለት አመታት ድረስ ለአምስት አመታት ሃገሯን በፕሬዝደንትነት ያገለገለች ለሃገሯ ፡ ለልጆቿ ለቤተሰቦቿ አሁን አሁን ደግሞ ለአለምም ጭምር በጎ ነገር ለማውረስ የምትጥር ጠንካራ ሴት ናት ። ከፕሬዝደንቷ ከለቀቀች በኋላም በተለያዩ አጋጣሚዎች ሃገሯን እየወከለች ትገኛለች ፡ ከሁለት ወራት በፊት በዱባይ ኤክስፖ ላይ ክሮሽያን ወክላ ሄዳ ነበር ፡ ደግሞ ለአለም ዋንጫ ማጣሪያ ሃገሯ ከፈረንሳይ የነበራትን ጨዋታ ለመመልከት ፓሪስ ተገኝታ ነበር ፡ ይህ ጨዋታ ፈረንሳይን 1-0 ያሸነፍንበት ምርጥ ጨዋታ ነበር በተይም የ 2018 የአለም ዋንጫ ላይ በደንብ ትታወቃለች ። ....... እና ያንን ጨዋታ ለመመልከት አንተ የክሮሽያ ደጋፊ ሆነህ በፈረንሳይ ስታዲየም እንዳጋጣሚ አጠገቧ ብትቀመጥና ፡ ልክ ተጨዋቾች ለረፍት ሲወጡ አጠገብህ ነጭና ቀይ ስኩየር ማልያ ለብሳ ቁጭ ያለችውን ቀለል የምትል ሴት ዞር ብለህ አየት አድርገሃት ፡ የትም እንደማታውቃት ልብህ እያወቀው ለወሬ መክፈቻ. . የሆነ ቦታ አውቅሻለሁ ልበል ? ስትላት ፡ ተግባቢዋ ኮሊንዳ ..አይደል ? እኔምኮ ገርሞኝ የት ነው የማውቀው እያልኩ ሳስብ ነበር አሁን ነው ትዝ ያለኝ. ... ከሁለት አመት በፊት የክሮሽያ ፕሬዝደንት ሆኜ ካሪቢያን ደሴቶች ላይ ተገናኝተን ፌንት ያረከው ግን ምን ሆነህ ነው ብትልህ. .. ሁለተኛውን የጨዋታ አጋማሽ ፡ በሃፍረት ጥለህ ትወጣለህ ? ወይስ በምን አይነት ሙድ ሆነህ ኳሱን እንደምትከታተል ብቻ እግዜር ይወቅ ። .................. እንዲህ አይነት ራሳቸውን ሰማይ ጥግ የማይቆልሉ ፡ ተጫዋች ተግባቢ ፡ ሰው ሰው የሚሸቱ ፡ እኔ ብሆን ኖሮስ ብለው ራሳቸውን በህዝብ ቦታ የሚያስቀምጡ. .. ሁሉም የሚቀናባት ባለስልጣናት
Показати все...
7
የ42 አመቱ መምህር ዶ/ር አብዱልማሊክ በኬራላ ግዛት ወደምትገኘው በመምህራን እጦት ወደ ምትሰቃየው ትንሽ ትምህርት ቤት የሚሄደው በየቀኑ እስከአንገቱ ድረስ በሚያሰምጥ ጭቃማ ወንዝ ውስጥ በመዋኘት እያቋረጠ ነው! በውጤቱም ለአንድም ቀን ቀርቶም ሆነ አርፍዶ አያውቅም! እስኪ አንዴ ለ ዶ/ር አብዱልማሊክ በኬራላ👍👍 @Amazing_Fact_433 @Amazing_Fact_433
Показати все...
12
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.