cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ዲ/ን አንተነህ ብርሐኔ

" የአባቶቻችን ትምህርት እናስተምራለን ፤ ተስፋቸውንም ተስፋ እናደርጋለን ፤ የተማርናት ፤ ተስፋ የምናደርጋት ይህች ናት:: እንኖርባታለን ፤ እንሞትባታለን ፤ በእግዚአብሔር ፍቃድ እንነሣባታለን " [ ሃይማኖተ አበው ] ♥ አስተያየት @antenehBrhaneይላኩልን

Більше
Рекламні дописи
267
Підписники
Немає даних24 години
+17 днів
+130 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

🌻 ብቸኝነት ፡ ከመላእክት ፡ ጋር ፡ ያዛምዳል። ረሃብ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ለመጥገብ ፡ ያበቃል። መራቆት ፡ ክርስቶስን ፡ ለመልበስ ፡ ያበቃል። መሰደድ ፡ ለርሥት ፡ መንግሥተ ፡ ሰማያት ፡ ያበቃል። 🌻 + አባ ፡ ገብረ ፡ ኪዳን ፡ ግርማ + 🌾 የሕይወት ፡ እናቱ ፡ ሆይ፤ ተቀዳሚ ፡ ተከታይ ፡ በሌለው ፡ በአንድ ፡ ልጅሽና ፡ በእኛ ፡ መካከል ፡ አስታርቂን። t.me/antenehbrhane
Показати все...
ዲ/ን አንተነህ ብርሐኔ

" የአባቶቻችን ትምህርት እናስተምራለን ፤ ተስፋቸውንም ተስፋ እናደርጋለን ፤ የተማርናት ፤ ተስፋ የምናደርጋት ይህች ናት:: እንኖርባታለን ፤ እንሞትባታለን ፤ በእግዚአብሔር ፍቃድ እንነሣባታለን " [ ሃይማኖተ አበው ] ♥ አስተያየት @antenehBrhaneይላኩልን

✟ ✍... ኦ ፡ ድንግል ፡ እመ ፡ በላእኩ ፡ መፅሐፈ ፡ ከመ ፡ ሕዝቅኤል ፡ ነብይ፣ ወእመ ፡ ሰተይኩ ፡ ፅዋ ፡ ልቡና ፡ ከመ ፡ ዕዝራ ፡ ሱቱኤል ፡ እይክል ፡ ፈፂሞ ፡ ውዳሴኪ። ✟ ✍... ድንግል ፡ ሆይ ፡ እንደ ፡ ሕዝቅኤል ፡ መፅሐፍን ፡ ብበላ፣ እንደ ፡ ዕዝራም ፡ የልቡና ፡ ፅዋ ፡ ብጠጣ ፡ ያንቺን ፡ ምስጋና ፡ እንዴት ፡ አድርጌ ፡ እጨርሰዋለሁ። ✟ ሊቁ ፡ ቅዱስ ፡ ኤፍሬም ፡ ሶርያዊ 🌾 የሕይወት ፡ እናቱ ፡ ሆይ፤ ተቀዳሚ ፡ ተከታይ ፡ በሌለው ፡ በአንድ ፡ ልጅሽና ፡ በእኛ ፡ መካከል ፡ አስታርቂን። 🌾
Показати все...
🎻 አጠገብህ ፡ ስለሌለው ፡ ሰው ፡ ድክመት ፡ በተናገርክ ፡ ቁጥር፤ ሰይጣን ፡ ይዘፍንበት ፡ ዘንድ ፡ ምላስህን ፡ በገና ፡ አድርገህ ፡ እንደሰጠህ ፡ ይቆጠራል። 🎻 ሊቁ ፡ ቅዱስ ፡ ኤፍሬም ፡ ሶርያዊ 🌾 የሕይወት ፡ እናቱ ፡ ሆይ፤ ተቀዳሚ ፡ ተከታይ ፡ በሌለው ፡ በአንድ ፡ ልጅሽና ፡ በእኛ ፡ መካከል ፡ አስታርቂን። 🌾
Показати все...
+።።። ተሸክሜህ ነው ።።።።።+ ... በበርሃ ይሄድ የነበረ ሰው ወደ ኋላው ዞሮ ሲያይ ከእርሱ ሌላ አንድ ጥላ ይመለከታል:: የዚህም ጥላ ነገር አሳስቦት የማን እንደ ሆነ ያመለክተው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ። እግዚአብሔርም :- "ከኋላህ የተመለከትከው ጥላ የእኔ ነው። አንተን እየጠበኩህ እንደሆነ ታውቅ ዘንድ ይህን ምልክት አሳየውህ" አለው። ያም ሰው ፈጣሪው ከእርሱ ጋር እንዳለ በመስማቱ እጅግ ደስ እያለው ጉዞውን ቀጠለ። ጥቂትም እንደተጔዘ ወጣ ገባ የሆነ በጣም አስቸጋሪ መንገድ አጋጠመው:: ሰውየውም ያን አስቸጋሪ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ለመውጣት ታገለ። በትግሉ መካከል ግን ወደ ኋላው ዞር ብሎ ቢመለከት ቀድሞ ያየውን ጥላ አጣው። ከዚያም ፈታኝ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ከወጣ በኋላ፣ በታላቅ ኃዘን ሆኖ እየተበሳጨ ፈጣሪውን እንዲህ ሲል ጠየቀው :- "ምንም ችግር ባልገጠመኝ በሰላሙ ጊዜ "ከአንተ ጋር ነኝ ስትል ጥላህን አሳየኸኝ፣ የአንተ እርዳታ በሚያስፈልገኝ ጊዜ ግን ራስህን ሰወርክብኝ:: ይከተለኝ የነበረውን ጥላም ዘወር ብዬ ባየው አጣኹት። ለምን ተውከኝ ?" :: እግዚአብሔርም :- "በመከራህ ጊዜ ጥላዬን ያጣኸው ትቼህ እኮ አይደለም። ተሸክሜህ ነው!" ብሎ መለሰለት። ክፉውን ዘመን በክንፈ ረድኤቱ ተሸክሞ የሚያሻግረን እግዚአብሔር ነው። እርሱ አይተወንም፤ አይንቀንም። እኛም ከእርሱ ውጭ ተስፋ የምናደርገው የለንም። ጌታ ሆይ ስንት ዘመን ተሸክመኸኝ ምነው ተውከኝ ብዬህ ይሆን? ደካማው ልጅህን ይቅር በለኝ t.me/antenehbirhane
Показати все...
መልካም ለማድረግ አትዘግይ ባሕታዊ አባ እስጢፍኖስ (ABBA STEPHANOS THE HERMIT) እንዲህ ይለናል በአል ፋዩም (El Fayoum) ምድረ በዳ ውስጥ እንዲህ ሆነ፦ በዐይኖቼ ያየሁትን በጆሮዎቼም የሰማሁትን እነግራችኋለሁና ወዳጆቼ ሆይ ልብ ብላችሁ አድምጡኝ፦ ከዕለታት አንድ ቀን በአልፋዩም ምድረ በዳ ውስጥ ስዘዋወር በዚያ ባሉት ሸለቆዎች፣ ተራራዎችና ሰውን እንደወዳጅ በሚንከባከቡ አራዊት ተደንቄ እግዚአብሔርን አመሰገንሁ፡፡ ወደ ምድረ በዳው እምብርት ዘልቄ ስገባ እጅግ ብዙ ምንጮችና ዛፎች መኖራቸውን አስተዋልሁ፡፡ ከአንዱ ዛፍ ሥር ከበረሃው ሙቀትና ቅዝቃዜ የተነሣ ነጭ ወደ መሆን የተቀየረ የራስ ቅል (Skull) አገኘሁ። በዚህም እግዚአብሔርን አመሰገንሁና ይህ የራስ ቅል የማን እንደሆነና ምን ዐይነት ሕይወት ይመራ እንደነበር ለማወቅ ፈለግሁ፡፡ አሁን የት እንደሚኖርና ምን ዐይነት ሕይወት ይመራ እንደነበር ይነግረኝ ዘንድ የራስ ቅሉ አንደበት ተሰጥቶት ቢያናግረኝ ተመኘሁ፡ ምሥጢሩን እንዲገልጥልኝ ፊቴን ወደ ምሥራቅ አዙሬ እግዚአብሔርን በጸሎት ጠየቅሁ። ጸሎቴን ከመጨረሴ በፊት እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፡- “አባ እስጢፋኖስ፣ አሁን የምነግርህ ለአንተም ለባልንጀሮችህም ማስጠንቀቂያ ነውና ልብ ብለህ አድምጠኝ፡፡ ስለዚያች አስፈሪ የፍርድ ቀን ለባልንጀሮችህ በሙሉ አስጠንቅቀህ ንገራቸው፤ ክርስቶስ ዳግመኛ በሚመጣባት በሙታን ትንሣኤ ዕለት ቸርነትን ማድረግና በእምነት በሚሠራ ሥራ ሰው ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ይቀርባል እንጂ ወንድም ወንድሙን፣ አባትም ልጁን አያድንምና በትጋትና በጸሎት ለማይኖሩ ወዮላቸው፡፡ በዚያች ዕለት ጸሎትህ ልክ እንደጧፍ ደምቃ ትበራለችና እንዳትሰለች ተጠንቀቅ፡፡ ብዙ ሥቃይ ወዳለበት፣ እሳተ ወደማይጠፋበት ትሉም ወደማያንቀላፋበት እኔ ወደምኖርበት ቦታ እንዳይመጡ የምነግርህን ሁሉ ለሰዎች ንገራቸው፡፡ በምድር ላይ የነበርኝን ሕይወት ልንገርህ ስማኝ፡- ምንም እንኳን ብዙ ገንዘብ ቢኖረኝም በማንኛውም ሰው ላይ የምቀናና ለድሆች የማልራራ ሲበዛ ስስታም ነጋዴ ነበርሁ፡፡ ጸሎት ጸልዬ የማላውቅና ለማንም የማልራራ ጨካኝ ነበርሁ፡፡ እግዚአብሔርን ለማመስገንም ይሁን እርሱን ለማስደሰት ምንም ያደረግሁት ነገር የለም። ሰውን ሁሉ የሚወዱና ብዙ የፍቅርና ቸርነት ሥራዎችን ይሠሩ የነበሩ ደጋግ ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፡፡ መልካም ሥራ እንድሠራ ይመክሩኝ ነበር፤ እኔ ግን አልሰማቸውም ነበር፤ ገንዘቤንም እንዳያገኙ አደርግ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ብዙ ሀብት ቢኖረኝም አንድም ቀን ግን ባለኝ ሀብትና ንብረት ደስ ብሎኝና ረክቼ ዐላውቅም፡፡ አንድ ቀን ለንግድ ወደ ሩቅ አገር ሔድሁ፡፡ ብዙ ግመሎችን ከሎሌዎቼ ጋር ይዤ በመጓዝ ላይ እያለሁ በአንድ በረሓ ውስጥ በሚገኝ ዛፍ ሥር ጥቂት ለማረፍ ተዘጋጀሁ። መንገድ የሚመራኝ ሰው አስከትዬ እጅግ ብዙ ገንዘብና ዕቃዎችን ለንግድ ይዤ ነበር፡፡ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓው ውስጥ ከተጓዝን በኋላ መንገድ የሚመራኝ ሰውዬ አቅጣጫው ጠፋበት ወደ የት እየሔድን እንደሆነ ሳናውቅ ለሦስት ቀናት ያህል ያን በረሓ ዞርነው፡፡ እግዚአብሔር የመንገዱ መሪ ያልሆነለት ሰው ወዮለት! የፀሓዩ ሙቀት ይለበልባል፤ ግመሎቼ ሞቱ፤ ሎሌዎቼም ትተውኝ ሔዱ፤ እኔ ብቻ ቀረሁ። በዚያ ምድረ በዳ ውስጥ እጄ ላይ የቀረውን ስንቅ እየተመገብሁ ለተጨማሪ ሦስት ቀናት ቆየሁ፡፡ እየሞትሁ እንደሆነ ተሰማኝ፤ ነፍሴን ሊያድን የሚችል ምንም መልካም ምግባር እንደሌለኝና አሁን ከደረሰብኝ መከራ መውጣት የሚያስችል ሥልጣን እንደሌለኝ በማሰብ ሕይወቴ እንዴት በፍጥነት እየጠፋች መሆኑን ሳይ በጣም ተጨነቅኩ። በቀጣዩ ቀን ዐይኖቼ ከበዱብኝ፤ ማየት ተሳነኝ፤ በሦስተኛው ቀን ዐይኖቼ ተከፈቱና ከአፉ እሳት የሚተፋ የእሳት ሰይፍ የያዘ እጅግ በጣም የሚያስፈራ መልአክ አየሁ፡፡ ነፍሴን ከሥጋዬ እንድትለይ አዘዛት፤ ነፍሴን በእጁ ጭፍልቅ አድርጎ ያዛትና ለዲያብሎስ ሰጠው፡፡ ከዚያም በሹካ መሳይ ሹል ነገር ወጓትና ብቻዬን ወደምኖርበት ወደዚህ የሥቃይ ቦታ አመጡኝ፡፡ ከዚህ እኔ ከምኖርበት የሥቃይ ቦታ አጠገብ መጨረሻው በማይታይ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ የሚኖር በዓለም የሚኖር በዓለም _ ሳለሁ _ የማውቀው ሥራዎቹም ልክ እንደእኔ የከፉ ሽማግሌ አየሁ። እርሱም በከባድ ሥቃይ ውስጥ ይኖራል። በምን ምክንያት ወደዚህ ቦታ እንደተጣለ ስጠይቀው “በመጥፎ ሥራዎቼ ምክንያት ..." አለኝ። ከሰውዬው ጋር እያወራሁ እያለ ድንገት ማንም በምድር ላይ የሚኖር ሰው ሰምቶት ሊቋቋመው የማይቻለው የመብረቅ ነጎድጓድ ሰማሁ፤ ድምፁም በዚህ ያለውን ሥቃይ የሚያስፈጽመው መልአክ ድምዕ ነበር፡፡ እርሱም ጭብጥ አድርጎ ይዞ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ወደምገኝበት ወደ ጥልቁ ወረወረኝ፡፡” እኔ እስጢፋኖስም “በገነት ያሉ ቅዱሳንን ማየት ትችላላችሁ?” በማለት ጠየቅሁት፡፡ እርሱም “በእነርሱና በእኛ መካከል ሊለካ የማይችል ርቀት ስላለ እነርሱን ማንም ሊያያቸው አይችልም። በዚያች በመጨረሻዋ ሰዓት ገንዘብም ቢሆን ሀብትም ቢሆን ወይም ልጆቼ ሊያድኑኝ ለማይቻላቸው ለእኔ ወዮልኝ፡፡ ስለዚህም አባ እስጢፋኖስ ሆይ፣ የነገርሁህን ሁሉ አስታውስ፤ ለመጸለይ ወይም መልካም ለማድረግ አትዘግይ፤ ቃሌንም ለሁሉም ሰው ንገር። እኔ ሁልጊዜ ለወላጆቼ የማልታዘዝና ዓለማዊ ፍላጎቶችን ወዳጅ ነበርሁ። በመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዛት መሠረት አልኖርሁም፡፡ ምንም እንኳን ወደዚህ ዓለም የመጣው ጌታ ከድንግል ማርያም እንደተወለደና በገዛ ፈቃዱ መከራን እንደተቀበለ ባውቅም በኢየሱስ ክርስቶስ ግን እምነት ኖሮኝ ዐያውቅም፡፡ ሰው በቅድስት ጥምቀትና በቅዱስ ቍርባን እንደሚድን ባውቅም በትዕቢቱ ምክንያት በእነርሱ መኖርንና ትእዛዛቱን መከተልን እምቢ አልሁ እነዚህን ጸጋዎች በፍጹም ቸል እንዳትል!” እነዚህን ቃላት ሦስት ጊዜ ደጋገመና “ይህን ሁሉ ለአንተ እንድነግርህ ታዘዤ ነው” ብሎኝ መናገሩን አቆመ፡፡ እኔ እስጢፋኖስም ያን የራስ ቅል ወደ አንድ ዋሻ ወሰድሁና ጉድጓድ ቆፍሬ ቀበርሁት፡፡ ከዚያም ወደ ወንድሞች ዘንድ ሔድሁና ሁሉንም ነገር ነገርኋቸው፡፡ ሁላችንም ጸለይን፤ ከሙታን ትንሣኤ በኋላ ቃል በተገባልን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘለዓለማዊ ተስፋ እንኖር ዘንድ እንደእግዚአብሔር ፈቃድ በታማኝነት ለመኖር የተገባን እንሆን ዘንድ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን በጸሎት ጠየቅን፡፡ ዘለዓለማዊ ምሥጋና ለእግዚአብሔር ይሁን፤ አሜን። ያጋሩት
Показати все...
ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻለን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻለናል።  ቅዱስ አትናቴዎስ
Показати все...
ምንም ነገር ከሞከርኽ አይሳካልኝም ብለህ ስንፍናን አትማር ፤ ይልቁንም አምላኩን ታግሎ ያሸነፈውን ቅዱስ ያዕቆብን አስበው እንጂ ። ከአባቶች ለሁላችንም የያዕቆብን  ልብ ይስጠን
Показати все...
ቤተክርስቲያን የፍግ እሳት ናት ፤ ጠፍታለች ስትባል ሕያው ትኾናለች ። ብፁዕ አብነ ቀለምንጦስ   እግዚአብሔር በቸርነቱ ቤተክርስቲያናችንን ይጠብቅልን
Показати все...
እንደ ቸርነትህ አቤቱ ማረን/2/ እንደ ምህረትህ ይቅርታን ስጠን/2/ ከኃጥያቴም አንጻኝ ከብዙ በደሌ/2/ ለዛች ክፉ ሀጥያት እንዳልሆናት ሎሌ/2/ እኔስ አበሳዬ በደሌን ሳውቀው/2/ ከቶ የሚያድነኝ ቸርነትህ ነው/2/ አንተን ብቻ በደልኩ ክፉም አደረግሁ/2/ አሁን ይቅር በለን ከፌትህ ወደቅን /2/ ከፊትህ ወድቄ ስለምን አንተን ስማጸን አንተን መውደቄን ተመልከት አምላከ ብርሀን አምላከ ሰላም 💚  💚 💛  💛 ❤️  ❤️
Показати все...
መልካም ለማድረግ አትዘግይ ባሕታዊ አባ እስጢፍኖስ (ABBA STEPHANOS THE HERMIT) እንዲህ ይለናል በአል ፋዩም (El Fayoum) ምድረ በዳ ውስጥ እንዲህ ሆነ፦ በዐይኖቼ ያየሁትን በጆሮዎቼም የሰማሁትን እነግራችኋለሁና ወዳጆቼ ሆይ ልብ ብላችሁ አድምጡኝ፦ ከዕለታት አንድ ቀን በአልፋዩም ምድረ በዳ ውስጥ ስዘዋወር በዚያ ባሉት ሸለቆዎች፣ ተራራዎችና ሰውን እንደወዳጅ በሚንከባከቡ አራዊት ተደንቄ እግዚአብሔርን አመሰገንሁ፡፡ ወደ ምድረ በዳው እምብርት ዘልቄ ስገባ እጅግ ብዙ ምንጮችና ዛፎች መኖራቸውን አስተዋልሁ፡፡ ከአንዱ ዛፍ ሥር ከበረሃው ሙቀትና ቅዝቃዜ የተነሣ ነጭ ወደ መሆን የተቀየረ የራስ ቅል (Skull) አገኘሁ። በዚህም እግዚአብሔርን አመሰገንሁና ይህ የራስ ቅል የማን እንደሆነና ምን ዐይነት ሕይወት ይመራ እንደነበር ለማወቅ ፈለግሁ፡፡ አሁን የት እንደሚኖርና ምን ዐይነት ሕይወት ይመራ እንደነበር ይነግረኝ ዘንድ የራስ ቅሉ አንደበት ተሰጥቶት ቢያናግረኝ ተመኘሁ፡ ምሥጢሩን እንዲገልጥልኝ ፊቴን ወደ ምሥራቅ አዙሬ እግዚአብሔርን በጸሎት ጠየቅሁ። ጸሎቴን ከመጨረሴ በፊት እንዲህ የሚል ድምፅ ሰማሁ፡- “አባ እስጢፋኖስ፣ አሁን የምነግርህ ለአንተም ለባልንጀሮችህም ማስጠንቀቂያ ነውና ልብ ብለህ አድምጠኝ፡፡ ስለዚያች አስፈሪ የፍርድ ቀን ለባልንጀሮችህ በሙሉ አስጠንቅቀህ ንገራቸው፤ ክርስቶስ ዳግመኛ በሚመጣባት በሙታን ትንሣኤ ዕለት ቸርነትን ማድረግና በእምነት በሚሠራ ሥራ ሰው ሁሉ ወደ እግዚአብሔር ይቀርባል እንጂ ወንድም ወንድሙን፣ አባትም ልጁን አያድንምና በትጋትና በጸሎት ለማይኖሩ ወዮላቸው፡፡ በዚያች ዕለት ጸሎትህ ልክ እንደጧፍ ደምቃ ትበራለችና እንዳትሰለች ተጠንቀቅ፡፡ ብዙ ሥቃይ ወዳለበት፣ እሳተ ወደማይጠፋበት ትሉም ወደማያንቀላፋበት እኔ ወደምኖርበት ቦታ እንዳይመጡ የምነግርህን ሁሉ ለሰዎች ንገራቸው፡፡ በምድር ላይ የነበርኝን ሕይወት ልንገርህ ስማኝ፡- ምንም እንኳን ብዙ ገንዘብ ቢኖረኝም በማንኛውም ሰው ላይ የምቀናና ለድሆች የማልራራ ሲበዛ ስስታም ነጋዴ ነበርሁ፡፡ ጸሎት ጸልዬ የማላውቅና ለማንም የማልራራ ጨካኝ ነበርሁ፡፡ እግዚአብሔርን ለማመስገንም ይሁን እርሱን ለማስደሰት ምንም ያደረግሁት ነገር የለም። ሰውን ሁሉ የሚወዱና ብዙ የፍቅርና ቸርነት ሥራዎችን ይሠሩ የነበሩ ደጋግ ወንዶች ልጆች ነበሩኝ፡፡ መልካም ሥራ እንድሠራ ይመክሩኝ ነበር፤ እኔ ግን አልሰማቸውም ነበር፤ ገንዘቤንም እንዳያገኙ አደርግ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ብዙ ሀብት ቢኖረኝም አንድም ቀን ግን ባለኝ ሀብትና ንብረት ደስ ብሎኝና ረክቼ ዐላውቅም፡፡ አንድ ቀን ለንግድ ወደ ሩቅ አገር ሔድሁ፡፡ ብዙ ግመሎችን ከሎሌዎቼ ጋር ይዤ በመጓዝ ላይ እያለሁ በአንድ በረሓ ውስጥ በሚገኝ ዛፍ ሥር ጥቂት ለማረፍ ተዘጋጀሁ። መንገድ የሚመራኝ ሰው አስከትዬ እጅግ ብዙ ገንዘብና ዕቃዎችን ለንግድ ይዤ ነበር፡፡ አንድ ቀን ሙሉ በበረሓው ውስጥ ከተጓዝን በኋላ መንገድ የሚመራኝ ሰውዬ አቅጣጫው ጠፋበት ወደ የት እየሔድን እንደሆነ ሳናውቅ ለሦስት ቀናት ያህል ያን በረሓ ዞርነው፡፡ እግዚአብሔር የመንገዱ መሪ ያልሆነለት ሰው ወዮለት! የፀሓዩ ሙቀት ይለበልባል፤ ግመሎቼ ሞቱ፤ ሎሌዎቼም ትተውኝ ሔዱ፤ እኔ ብቻ ቀረሁ። በዚያ ምድረ በዳ ውስጥ እጄ ላይ የቀረውን ስንቅ እየተመገብሁ ለተጨማሪ ሦስት ቀናት ቆየሁ፡፡ እየሞትሁ እንደሆነ ተሰማኝ፤ ነፍሴን ሊያድን የሚችል ምንም መልካም ምግባር እንደሌለኝና አሁን ከደረሰብኝ መከራ መውጣት የሚያስችል ሥልጣን እንደሌለኝ በማሰብ ሕይወቴ እንዴት በፍጥነት እየጠፋች መሆኑን ሳይ በጣም ተጨነቅኩ። በቀጣዩ ቀን ዐይኖቼ ከበዱብኝ፤ ማየት ተሳነኝ፤ በሦስተኛው ቀን ዐይኖቼ ተከፈቱና ከአፉ እሳት የሚተፋ የእሳት ሰይፍ የያዘ እጅግ በጣም የሚያስፈራ መልአክ አየሁ፡፡ ነፍሴን ከሥጋዬ እንድትለይ አዘዛት፤ ነፍሴን በእጁ ጭፍልቅ አድርጎ ያዛትና ለዲያብሎስ ሰጠው፡፡ ከዚያም በሹካ መሳይ ሹል ነገር ወጓትና ብቻዬን ወደምኖርበት ወደዚህ የሥቃይ ቦታ አመጡኝ፡፡ ከዚህ እኔ ከምኖርበት የሥቃይ ቦታ አጠገብ መጨረሻው በማይታይ ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ የሚኖር በዓለም የሚኖር በዓለም _ ሳለሁ _ የማውቀው ሥራዎቹም ልክ እንደእኔ የከፉ ሽማግሌ አየሁ። እርሱም በከባድ ሥቃይ ውስጥ ይኖራል። በምን ምክንያት ወደዚህ ቦታ እንደተጣለ ስጠይቀው “በመጥፎ ሥራዎቼ ምክንያት ..." አለኝ። ከሰውዬው ጋር እያወራሁ እያለ ድንገት ማንም በምድር ላይ የሚኖር ሰው ሰምቶት ሊቋቋመው የማይቻለው የመብረቅ ነጎድጓድ ሰማሁ፤ ድምፁም በዚህ ያለውን ሥቃይ የሚያስፈጽመው መልአክ ድምዕ ነበር፡፡ እርሱም ጭብጥ አድርጎ ይዞ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ ወደምገኝበት ወደ ጥልቁ ወረወረኝ፡፡” እኔ እስጢፋኖስም “በገነት ያሉ ቅዱሳንን ማየት ትችላላችሁ?” በማለት ጠየቅሁት፡፡ እርሱም “በእነርሱና በእኛ መካከል ሊለካ የማይችል ርቀት ስላለ እነርሱን ማንም ሊያያቸው አይችልም። በዚያች በመጨረሻዋ ሰዓት ገንዘብም ቢሆን ሀብትም ቢሆን ወይም ልጆቼ ሊያድኑኝ ለማይቻላቸው ለእኔ ወዮልኝ፡፡ ስለዚህም አባ እስጢፋኖስ ሆይ፣ የነገርሁህን ሁሉ አስታውስ፤ ለመጸለይ ወይም መልካም ለማድረግ አትዘግይ፤ ቃሌንም ለሁሉም ሰው ንገር። እኔ ሁልጊዜ ለወላጆቼ የማልታዘዝና ዓለማዊ ፍላጎቶችን ወዳጅ ነበርሁ። በመጽሐፍ ቅዱስ ትእዛዛት መሠረት አልኖርሁም፡፡ ምንም እንኳን ወደዚህ ዓለም የመጣው ጌታ ከድንግል ማርያም እንደተወለደና በገዛ ፈቃዱ መከራን እንደተቀበለ ባውቅም በኢየሱስ ክርስቶስ ግን እምነት ኖሮኝ ዐያውቅም፡፡ ሰው በቅድስት ጥምቀትና በቅዱስ ቍርባን እንደሚድን ባውቅም በትዕቢቱ ምክንያት በእነርሱ መኖርንና ትእዛዛቱን መከተልን እምቢ አልሁ እነዚህን ጸጋዎች በፍጹም ቸል እንዳትል!” እነዚህን ቃላት ሦስት ጊዜ ደጋገመና “ይህን ሁሉ ለአንተ እንድነግርህ ታዘዤ ነው” ብሎኝ መናገሩን አቆመ፡፡ እኔ እስጢፋኖስም ያን የራስ ቅል ወደ አንድ ዋሻ ወሰድሁና ጉድጓድ ቆፍሬ ቀበርሁት፡፡ ከዚያም ወደ ወንድሞች ዘንድ ሔድሁና ሁሉንም ነገር ነገርኋቸው፡፡ ሁላችንም ጸለይን፤ ከሙታን ትንሣኤ በኋላ ቃል በተገባልን በኢየሱስ ክርስቶስ ዘለዓለማዊ ተስፋ እንኖር ዘንድ እንደእግዚአብሔር ፈቃድ በታማኝነት ለመኖር የተገባን እንሆን ዘንድ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን በጸሎት ጠየቅን፡፡ ዘለዓለማዊ ምሥጋና ለእግዚአብሔር ይሁን፤ አሜን። ያጋሩት
Показати все...
👍 1
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.