cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Getachew shiferaw

Більше
Рекламні дописи
44 567
Підписники
-2624 години
-2847 днів
-99330 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

የሚገርሙ፣ የሚያሳዝኑም ጉዳዮች ናቸው! 1) የጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደር ከመቀሌ ውጭ ተንቀሳቅሶ ስብሰባ ማድረግ እንደማይችል ራሱ ጌታቸው ለትግራይ ሕዝብ ተናግሯል። ትግራይን የሚያስተዳድረው ከጦርነቱ በፊት የነበረው፣ ወንጀለኛ የተባለው መዋቅር ነው። ይህን ጌታቸው ረዳ በሚዲያ ወጥቶ ያረጋገጠው ነው። ይህ ህገወጥ መዋቅር ስለሆነ ነው ጊዜያዊ አስተዳደር ማዋቀር ያስፈለገው። ትግራይ ውስጥ ከመቀሌ ውጭ ስብሰባ እንኳ ማድረግ የማይችለው የጌታቸው ረዳ አስተዳደር፣ በህጋዊ ስምምነት የተሰጠውን ትግራይን እንዳያስተዳድር ተደርጎ፣ በማያገባው ከትግራይ ውጭ ያሉትን የአማራ ግዛቶች እንዲያስተዳድር ነው የተደረገው። ሰሞኑን ትህነግ በወረራቸው የአማራ አካባቢዎች ጊዜያዊ አስተዳደሩ መዋቅሩን አሰማርቷል። ትህነግ ለጊዜያዊ አስተዳደሩ የፈቀደለት የወረራ አላማ ስለሆነ ነው። ትግራይ ውስጥ አንድም ቀበሌ እንዳያስተዳደር የተደረገው ጌታቸው የአማራን አካባቢዎች ግን በህገወጥ መንገድ እንዲይዝ ተደርጓል። 2) ሰሞኑን በትግራይ ፖለቲካ አጀንዳ የሆነ ጉዳይ አለ። ትህነግ የአማራ አካባቢዎች ተወልደው ያደጉትን አመራሮቹን "ትግሬ አይደላችሁም" እንዳላቸው የጊዜያዊ አስተዳደሩ አመራር ረዳኢ ሓለፎም ቃል በቃል ተናግሯል። የትግሬ ካባ የሚሰጠንም የሚቀማንም ሌላ ቡድን አለ ብሏል። የአድዋውን ቡድን ነው። ታዲያ ራያ ያደጉትን አመራሮቹን "ትግሬ አይደሉም። ባንዳ ናቸው።" ወዘተ እያለ የሚፈርጅ ራያን መሬቱንና መሬቱን ብቻ እንደሚፈልግ ግልፅ ነው። አመራሮቹን በጠላትነት የፈረጀ ለሕዝቡማ ያለው ጥላቻን መገመት ቀላል ነው። በተደጋጋሚ በተግባርም የታየ ነው። 3) ራያን የወረረው የትህነግ ታጣቂ "አርሚ 24" ይባላል። መከላከያን በመታበት ጥቅምት 24 የተሰየመ ነው። መከላከያ የተገደለበትን ቀን ማስታወሻ ያደረገውን ኃይል ነው እያገዘ የሚገኘው። 4) የሰላም ስምምነቱ ያለ ምንም ማወላዳት የደነገገው፣ የጊዜ መንዛዛት ያልተቀመጠበት የትጥቅ መፍታት ነው። በማያሻማ መልኩ በአንድ ወር ውስጥ ትጥቅ ይፍቱ ተብሎ ነበር። ጭራሽ አስታጠቋቸው። መከላከያ ትግራይን ይረከብ ተብሎ ነበር። ጭራሽ መከላከያ ከትግራይ ወጥቶ አማራ ላይ ዘምቶ፣ ትጥቅ መፍታት የነበረበት ትህነግ አማራ ክልልን በኃይል እንዲይዝ ተደረገ 5) ትህነግ ባለፉት ወረራዎች ዘረፋ የሚፈፅሙትን በየጦሩ አደራጅቶ አሰማርቷል። በዘረፉት ልክ ጥቅም አግኝተዋል። እንደ ጀግና ታይተዋል። ይህ ኃይል ግን ወደ ትግራይ ተመልሶ አረመኔ ሆነ። የአርሶ አደር በሬ አርዶ መብላት፣ የተቋማትን ብረታብረት መዝረፍ ወዘተ። ሰሞኑን የትግራይ ክልል ውሃ መሳቢያ ብረቶች እየተዘረፉ መሆኑ በስፋት እየተሰራጨ ነው። ይህን የራሴ የሚለውን ትግራይን እየዘረፈ ያለ ኃይል ነው ጠላቴ ወደሚለው አማራ ይዘውት የመጡት። ከራያ ብቻ ከ50 ሺህ በላይ ሕዝብ የተፈናቀለውም ይህ አረመኔ ኃይል በሚፈፅመው ወንጀል ምክንያት ነው። ይህ ሁሉ እየሆነ ያለው አማራ ላይ ነው!
Показати все...
የወረራ ዝግጅት! ራያን የወረረው ትህነግ ጠለምትንና ወልቃይትን ለመውረር ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ይገኛል። በዚህም መሰረት በሱዳን በኩል፣ አርሚ 11 ጠለምትን ለመውረር፣ አርሚ 17 ወልቃይትን ለመውረር ዝግጅት ላይ ነው፣ አርሚ 35 ከአክሱም ወደ ሽሬ የተንቀሳቀሰ ሲሆን ጥቅምት 24 መከላከያን የመቱበትን ማስታወሻ ያደረጉት "አርሚ 24" ደግሞ ራያን የወረረው ነው። ይህ በሆነበት ብልፅግና የአማራ አስተዳደሮችን በሕገወጥ መልኩ አፍርሶ በተፈናቃይ ስም የወረራ በር እየከፈተና እያገዘ ይገኛል። እንደ ገለልተኛ "ትጥቅ መፍታት አለባቸው" እያለ የሚቀልደውም ዝግጅታቸውን ስለማያውቅ አይደለም። ማዘናጊያ ነው። በሌላ በኩል በተቃዋሚም ሆነ በሌላ ስም ትህነግ ጋር ስምምነት ለመፈፀም የሚደረግን ሂደት የህዝብ ለህዝብ እያስመሰለ፣ የትህነግን ወረራ የሚያድበሰብስም የትህነግና ብልፅግናን የጓዳ ውልና የወረራ አላማ የሚያስፈፅም የአማራ ጠላት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
Показати все...
ያዘዝነውን ካላስፈፀመ መከላከያንም እናቀምሰዋለን ብለዋል! በአማርኛ ነው! ቀጥታ ትዕዛዝ ነው! ሰሞኑን ትህነግ ባደረገው ሰልፍ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር መከላከያ በተገኘበት በአማርኛ ጭምር ያስተላለው ዛቻ ነው። መከላከያ የምንፈልገውን ካላስተገበረ ሱሪያችን ያውቃታል። ይቀምሳል ተብሏል። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር የአማራን ርስቶች ለመያዝ ህፃናትና አዛውንቶች ይዘን እንደማንመጣ ይታወቃል ብሏል። እንዳሉት ተፈናቃይ ይዘው አልመጡም። ታጣቂ ነው ይዘው የመጡት። መከላከያም ባዘዝነህ መልኩ ካልሰራህ ሱሪያችን ታውቃታለህ ተብሏል። ይህ ጌታቸው ረዳ የሚያዘው ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር ነው።
Показати все...
ትህነግ የጓዳ ውሉን ይፋ አደረገው! ትህነግ በጀኔራል ታደሰ ወረደ በኩል የጓዳ ውሉን በማያሻማ መልኩ ይፋ አድርጓል። ብልፅግና ጠለምትና ራያን በቅርቡ፣ ከዛም ወልቃይትን አሳልፎ ለመስጠት የተዋዋለበትን በይፋ ተናግሯል። ከ50 ሺህ በላይ ንፁሃን በትህነግ ታጣቂ ከራያ የተፈናቀሉት በጓዳ ውሉ መሰረት እንደሆነ ይታወቃል። አማራ እየተወረረ ያለው በጓዳ ውሉ መሰረት ነው። የብልፅግና አመራሮች ስለ ትህነግ ትጥቁን መፍታት ወዘተ ሲያወሩ "ውሸታቸውን ነው" የምንለው በምክንያት ነው። ጦርነት የሚፈልግ ኃይል ወዘተ እያለ የሚያወግዙ የሚመስሉት ውሸት ነው። የአማራን ግዛቶች አሳልፈው ለመስጠት የተዋዋሉት በወረራ መሆኑ ይፋ ወጥቷል። ታደሰ ወረደ ብልፅግና አማራን በኃይል እንዲይዙ የሰጣቸውን ድጋፍና ፈቃድ በሚዲያ ወጥቶ ሲገልፅ ይህ ሁለተኛ ጊዜው ነው። እነ ተመስገን ጥሩነህ "ያፈነገጠ ወዘተ" እያሉ ሀሰት ሲናገሩ፣ ጀኔራል ታደሰ በይፋ መጥቶ ከብልፅግና ጋር የተዋዋሉት የጓዳ ውል መሆኑን እየገለፀ ነው። አማራን በትህነግ እያስወረረ የሚገኘው ብልፅግና ነው። ትህነግ ባለፈው በጌታቸው ረዳና ታደሰ ወረደ፣ ዛሬም በታደሰ ወረደ በኩል ወረራው ከብልፅግና ጋር በተስማሙት መሰረት የተደረገ እንደሆነና እንደሚቀጥል ሲገልፅ ብልፅግና ትንፍሽ አላለም። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደሮች ናቸው ወረራው በስምምነት የተፈፀመ መሆኑን የሚናገሩት። ያፈነገጠ ወዘተ የሚባለው ነጭ ውሸት ነው። ማዘናጊያ ነው። የጓዳ ውሉን ማድበስበሻ ነው!
Показати все...
ሬዲዮው የትህነግ/ህወሓት ባትሪ ሳይጎርስ!
Показати все...