cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ኸይር ኡማ ልማትና መረዳጃ ዕድር

ያለብን ሀላፊነት ከተሰጠን ጊዜ በላይ ነው

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
278
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

ከአዲስ የኸይር ኡማ ቤተሰቦች ጋር ትውውቅ ተደረገ በቀን 24/4/14 በኸንደቅ ላይብረሪ የኸይር ኡማ ልማትና መረዳጃ እድር አዲስ ከተቀላቀሉ አባላት ጋር የትውውቅ እና አጭር የስራ ገለፃ የተደረገ ሲሆን በፕሮግራሙም ላይ ነባር አባላት ስለ እድሩ የተለያዩ ገለፃዎችን አድረገዋል። ከአዲስ የኸይር ኡማ ቤተሰቦችም የተለያዩ የግልፅነት ጥያቄዎች የተጠየቁ ሲሆን ከመድረክ በተብራራ ሁኔታ ምላሽ ተሰጥቷል። ከዚህ ጋር ተያይዞ አባሉ ብሰራ ውጤታማ እሆናለው በሚልበትና እውቀትና ፍላጎቱን ባማከለ መልኩ የስራ ክፍፍል ተደርጎ በፍጥነት ወደተግባር እነደሚገቡ መልክት ተላልፏል። በስተመጨረሻም የእድሩ ስራ አስኪያጅ አብድልአዚዝ አብደላ ጊዜያቸውን መስዋት አድረገው የህብረተሰቡ ችግር ያገባኛል ይመለከተኛል አቅሜ በፈቀደ መልኩ ማገልገል አለብኝ ብለው የእድሩን አብረን እንስራ ጥሪ ተቀብለው በመድረኩ ላይ ለተገኙ አዲስ የኸይር ኡማ ቤተሰቦች የከበረ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ስለ እድሩ የተለያዩ መረጃዎችና ተጨማሪ መልክት ለማግኘት ከስር የተቀመጠውን ሊንክ/ ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ጆይን፣ ላይክ፣ ሼር እና ኮሜንት ያድርጉ የፌስቡክ ገፅ https://m.facebook.com/groups/479099122550352/?tsid=0.021813917365587798&source=result የቴሌግራም ገፅ https://t.me/kheiruma
Показати все...
#የስኬት_መንገድ ✍ #እንዴት_ስኬታማ_እሆናለው? አንድ ወጣት በጣም የተማረ አንድ ሳይኮሎጂስት ጋር ይሄድና እንዴት ስኬታማ መሆን እንደሚችል ጠየቀው፡፡ ሳይኮሎጂስቱም ወጣቱን ይዞ ወደ ወንዝ አመራ፡፡ በዛም እንደደረሱ የወጣቱን አንገት ከወደ ኀላ ይዞ ከወንዙ ውስጥ ደፈቀው፡፡ ሰከንዶች ተቆጠሩ፤ ከተወሰነ ሰከንዶች በኀላ ከተደፈቀበት ውሃ አወጣው፡፡ በዚህ ወቅት ወጣቱ በአፍንጫውም በአፋም ንፁ አየር ለመሳባ ተቻኮለ፡፡ ነፍሱ መለስ ካለችለት በኀላ በጣም በመናደድ ሳይኮሎጂሰሸቱ ላይ ጮኸበት፡፡ ሳይኮሎጂስቱም "አየህ ሁሌም አንድን ነገር አጥብቀህ ከፈለከው ታገኘዋለህ፤ አሁን ለመኖር የግድ ንፁ አየር ያስፈልግህ ስለነበር አተነፋፈስክን ጨምረክ ቶሎ ቶሎ ንፁ አየር አገኘክ፡፡ ስኬትም እንደዚው ናት፡፡ አጥብቀህ ከፈለካትና እሷን ለማግኘት ከለፋክ ስኬት ሁሌም በዙሪያህ ነች፡፡" አለው፡፡ #ጭብጥ ፡- በህይወታችን ልናሳካው የምንፈልገው ነገር ካለ ሁሌም መፈለግና መልፋት ይጠበቅብናል፡፡ እዚህ ጋር ግን #መመኘትና #መፈለግ ይለያያል፡፡ መፈለግ እየለፉ፣ እየሰሩ ነው፡፡
Показати все...
የትስስርና የልምድ ልውውጥ መድረክ ተካሄደ የኸይር ኡማ የልማትና መረዳጃ እድር በቀን 17/4/14 ዓ•ል በከተማችን ከሚገኙ እድሮች እና ጋር የልምድ ልውውጥ አደረገ። የኸይር ኡማ የልማትና መረዳጃ እድር በዘንድሮው በጀት ዓመት ሊሰራቸው ካሰባቸው ተግባራት አንዱ የሆነውን የትስስርና የልምድ ልውውጥ መድረክ በዛሬው እለት ፒያሳ በሚገኘው ኸንደቅ ላይብረሪ የተለያዩ እድሮች አባላት በተገኙበት ተከናውኗል። በውይይቱም ላይ ኡስታዝ ማህሙድ ተገኝተው መልክት ያስተላለፉ ሲሆን ሁሉም ትልቅ አላማ መያዝ እነዳለበት እና ትንንሽ አጀንዳዎችን ወደ ጎን በመተው በአንድነት ትልቅ አላማ ያለው ትልቅ ተፅኖ ፈጣሮ ተቋም በሂደት መገንባት እንደሚገባ ገልፀዋል። የውይይቱ መሪና የኸይር ኡማ ልማትና መረዳጃ እድር ስራ አስኪያጅ የሆኑት አብድል አዚዝ አብደላህ እነደገለፁት መድረኩ የመጀመሪያ እንደመሆኑ በውስን ተቋማት ብቻ የተካሄደ ቢሆንም ከታሰበው በላይ የተሳካ እንደነበር ገልፀዋል ከዚህም ጋር ተያይዞ ተመሳሳይ አላማ ተይዞ ተበታትኖ መስራት አቅምን ከመበታተንም በላይ አላማን ለማሳካት ተግዳሮት ሊሆን ስለሚችል አንድ በሚያደርጉ አጀንዳዎች ላይ በጋራ በመስራት የተሻለ አቅም መፍጠር እንደሚገባና ተቋማዊ አሰራርን ጠብቆ መሄድ ላይ የማይተካ ሚና መጫወት እንዳለብን መልክት አስተላልፈዋል። መድረኩ ላይ የተለያዩ እድርና ማህበራትን ወክለው የተገኙ ተሳታፊዎችን ለማነጋገር እንደሞከርነው በመጀመሪያ ደረጃ ሀሳቡ የሚደነቅ መሆኑን ገልፀው ቋሚ የግንኙነት ጊዜ ተቀምጦለት ዛሬ እድሉን ያላገኙ ሎሎች እድሮችና መሀበራት በተገኙበት ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባ ገለፀው መድረኩም አሳታፊና አንዳንችን ከአንዳችን ትምህርት የቀሰምንበት ለችግሮቻችን ደግሞ የመፍትሄ አቀጣጫ ያገኘንበት ነው ብለዋል ። ስለ እድሩ የተለያዩ መረጃዎችና ተጨማሪ መልክት ለማግኘት ከስር የተቀመጠውን ሊንክ/ ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ጆይን፣ ላይክ፣ ሼር እና ኮሜንት ያድርጉ https://m.facebook.com/groups/479099122550352/?tsid=0.899542983400428&source=result https://t.me/kheiruma
Показати все...
Log in or sign up to view

See posts, photos and more on Facebook.

ለኢንጅነሪንግ ተማሪዎች አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ውድ የኸይር ኡማ ልማትና መረዳጃ እድር ቤተሰቦች እንደሚታወቀው ኸይር ኡማ የልማት እና መረዳጃ እድር በትምህርት፣በማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ ሀይማኖታዊ እና መሰል ማህበረሰቡን በሚጠቅሙ ተግባራት ላይ ላለፉት 5 አመታት ሲሳተፍ ቆይቷል። ሆኖም በትምህርት ዘርፍ ከዚህ ቀደም ከሰራቸው ስራዎች የቀጠለ ለኢንጅነሪንግ ተማሪዎች የሚከተሉትን ስልጠናዎች በአጭር ጊዜ ለማሰልጠን ዝግጅቱን ጨርሷል ። ስለዚህ ከዚህ በታች ያሉትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ እና ፍላጎት ያላቹ መመዝገብ እና መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን። የስልጠናዎቹ አይነት 1 AutoCAD 2 archiCAD 3 Quantity ስልጠናው በሁለት ዙር የሚሰጥ ሲሆን በሁሉም ዘርፍ 50 ሰልጣኞች በአጠቃላይ 150 የምንቀበል ሲሆን በሁሉም ዘርፍ ቀድመው የተመዘገቡ 25 ሰልጣኞች በመጀመሪያ ዙር እና መጨረሻ የተመዘገቡ 25 ሰልጣኞች በሁለተኛ ዙር የሚሳተፉ ይሆናል። ለመመዝገብ በስልክ ቁጥር #0964726464 #0964736464 ሙሉ ስም፣ ስልክ ቁጥር፣ የትምህርት ደረጃ እና የሚፈልጉትን ዘርፍ/ ኮርስ በመጥቀስ መልክት ይላኩ ። ስለ እድሩ የተለያዩ መረጃዎችና ተጨማሪ መልክት ለማግኘት ከስር የተቀመጠውን ሊንክ/ ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ጆይን፣ ላይክ፣ ሼር እና ኮሜንት ያድርጉ ። ለሌሎች እንዲደርስ መልክቱን ሼር ያድርጉ https://m.facebook.com/groups/479099122550352/?tsid=0.899542983400428&source=result https://t.me/kheiruma
Показати все...
👆👆👆👆 ይሄኛው ሳዳም ነው ወደ 5000 የተቀየረው
Показати все...
Sadam 5000 birr tekbeeeer Mejid 500
Показати все...
ወርሀዊ መዋጮ 350 ብር
Показати все...
A.aziz 1000
Показати все...
Abdu tes 500
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.