cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

Voa Amharic

መረጃዎችን ለመላክ @Voa_News_Amharic_bot

Більше
Рекламні дописи
17 792
Підписники
+924 години
+777 днів
+49530 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

በእንግሊዝ እስር ቤቶች በመጨናነቃቸው በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞች ሊለቀቁ ነው! እስር ቤቶች በመጨናነቃቸው ምክንያት በእንግሊዝ እና በዌልስ በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞች እንደሚለቀቁ የአገሪቱ የፍትሕ መሥሪያ ቤት ባለሥልጣን አስታወቁ።ባለሥልጣኗ ሻባና ማህሙድ በእስረኞች የተጨናነቁ እስር ቤቶችን ጫና በአስቸኳይ ማቃለል ካልተቻለ የአገሪቱ “ሕግ እና ሥርዓት ሙሉ ለሙሉ የመፍረስ አደጋ ሊገጥመው ይችላል” በማለት የእርምጃውን አስፈላጊነት አሳስበዋል። በእንግሊዝ እና በዌልስ ውስጥ በሚገኙ እስር ቤቶች ያለውን የታሳሪዎች ብዛት ለማቅለል የፍትሕ መሥሪያ ቤቱ ባቀረበው ዕቅድ መሠረት ከተፈረደባቸው የእስር ጊዜ 40 በመቶውን ያጠናቀቁ የተወሰኑ እስረኞች የሚለቀቁ ይሆናል።በዚህም መሠረት በመጪው መስከረም ወር በሺዎች የሚቆጠሩ እስረኞች በመጀመሪያው ዙር የሚፈቱ ሲሆን፣ ከዚያ በኋላ ባሉ 18 ወራት ውስጥ ደግሞ ተጨማሪ እስረኞች ደረጃ በደረጃ የሚለቀቁ እንደሚሆን ባለሥልጣኗ አሳውቀዋል። በሚቀጥሉት 18 ወራት ተጨማሪ አራት ሺህ ወንድ እስረኞች እና ከአንድ ሺህ ያነሱ ሴት እስረኞች በአዲሱ ውሳኔ መሠረት ከእስር የሚወጡ መሆናቸውን የአገሪቱ የፍትሕ ሚኒስቴር ለቢቢሲ አረጋግጧል።ነገር ግን በዚህ ውሳኔ መሠረት የሚፈቱት እስረኞች በከባድ ወንጀል የተፈረደባቸው እንደማይሆኑ ተገልጿል። ከባድ ወንጀል ፈጽመው አራት ዓመት እና ከዚያ በላይ የተፈረደባቸው እንዲሁም ወሲባዊ ጥቃት ፈጻሚዎች ከሚፈቱት ውስጥ አይካተቱም ተብሏል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показати все...
አዲሱ የኢራን ፕሬዝደንት የአሜሪካን ጫና እንደማይቀበሉ ገለጹ ፔዝሽኪያን "ቻይና እና ሩሲያ ፈታኝ በሆነ ጊዜ ከጎናችን ቆመዋል" ብለዋል። አዲሱ የኢራን ፕሬዝደነት መሱድ ፔዝሽኪያን ኢራን ለአሜሪካ ጫና ሸብረክ እንደማትል ተናግረዋል። ሀገራቸው ከቻይና እና ሩሲያ ጋር ያላትን ግንኑነት ያነሱት ፕሬዝደንት መሱዱ ፔዝሺኪያን ኢራን ከአሜሪካ የሚመጣ ጫናን አትቀበልም ብለዋል። በሄሊኮተር አደጋ የመሞቱን ራይሲን ለመተካት በተካሄደው ምርጫ፣ ወግ አጥባቂውን ያሸነፉት እና በአንጻራዊነት ለዘብተኛ የተባሉት ፔዝሺኪያን ኢራን የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንደማትፈልግ እና ከጎረቤቶቿ እና አውሮፓ ጋር መነጋገር እንደምትፈልግ ተናግረዋል። "አሜሪካ...እውነታውን መቀበል አለባት፤ የኢራን መከላከያ አስተምህሮ የኑክሌር ጦር መሳሪያ እንደማያካትት ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጋዜ መረዳት አለባት" ብለዋል "ለመላው አለም የተላለፈ መእልክት" በሚል ርዕስ ባወጡት መግለጫ። የ69 አመቱ የልብ ጠጋኝ የሆኑት ፔዝሽኪያን ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት ያስገባ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እንደሚከተሉ እና በ2015 የኑክሌር ስምምነት ምክንያት ከኃያላን ሀገራት ጋር የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ እንደሚሰሩ ተናግረዋል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
ሉዊስ ናኒ እና ንዋንኩ ካኑ አዲስ አበባ ገቡ ታዋቂዎቹ የእግር ኳስ ተጫዋቾች የፖርቹጋሉ ሉዊስ ናኒ እና ናይጄሪያዊው ንዋንኩ ካኑ ዛሬ ጠዋት አዲስ አበባ ገብተዋል። ሁለቱ ታዋቂ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የመቻል 80ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ላይ ተካፋይ እንዲሆኑ በተደረገላቸው ግብዣ መሠረት ነው። ተጫዋቾቹን የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ስለሺ ግርማ ፣የመቻል ስፖርት ክለብ ቦርድ ሰብሳቢ ሰይፈ ጌታሁን (ዶ/ር) እና የመከላከያ ሚዲያ ስራዎች ዳይሬክተር ብ/ጄ ኩማ ሚደቅሳ አቀባበል እንዳደረጉላቸው የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показати все...
የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ሥራቸውን ለቀቁ በሀገሪቱ በተቀጣጠለው ፀረ መንግሥት ተቃውሞ በርካቶች መሞታቸውን ተከትሎ ጠንካራ ትችት የተሰነዘረባቸው የፖሊስ አዛዥ ጃፌት ኮሜ በዛሬው ዕለት የስንብት ደብዳቤ አስገብተዋል። የኬንያ ፕሬዝደንት ጽሕፈት ቤት የኮሜን የስንብት ደብዳቤ ፕሬዝደንት ዊልያል ሩቶ መቀበላቸውን አረጋግጧል። ጽሕፈት ቤቱ አክሎም በቦታቸው ምክትል የኬንያ ፖሊስ አዛዥ የነበሩት ዳግላስ ካንጃ መተካታቸውን አስታውቋል። በሀገሪቱ የተካሄደውን ፀረ መንግሥት ተቃውሞ ያደራጀው ጀነሬሽን Z በአጭሩ ጄን Z የተሰኘው የኬንያ ወጣቶች ስብስብ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የኃይል እርምጃ ወስዷል ያሉት የኬንያ ፖሊስ አዛዥ ሥልጣናቸውን እንዲቀቁ ግፊት ሲያደርግ ነበር። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показати все...
<<...መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ...ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷ "የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ ሲኖዶሱ ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ገዳማት የምሕላ ጸሎት እንዲፈጸም አወጀ። በሀገር አስተማማኝ ሰላም ሲጠፋ በጾም በጸሎት በመወሰን ፣ ምሕላ ይታወጃል።ምሕላ የሚታወጀው ልባዊ በሆነ ተማሕጽኖ ለእግዚአብሔር ምልጃን ለማቅረብ ነው። "ውሎ ማደር፣ ወጥቶ መግባት በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች ስጋት ከሆነ ሰነባብቷል ። እግዚአብሔር  መተላለፋችንን ይቅር እንዲለን፣;ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ ለቤተ ክርስቲያናችን ፍቅር አንድነት፣ ለሕዝባችን ደኅንነት እንዲሰጥልን ከአንድነት ገዳማት ኅብረት በቀረበው ጥያቄ መነሻነት ምሕላ ማወጅ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል " ብሏል። በዚህም በመላ የሀገራችን ክፍልና ሌሎች አህጉራተ ዓለም የሚገኙ መነኰሳትና መነኰሳይያት ከሐምሌ 22 እስከ ሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት በቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት የገዳማት ኅብረቱን ጥሪ ተቀብለው የምሕላ ጸሎት እንዲያደርሱ ጥሪ አቅርቧል። በጤና ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀርም እስከ ዕርበተ ፀሐይ በመጾም ሱባኤ እንዲይዙ ፣ ቋሚ ሲኖዶስ ከአደራ ጋር አሳስቧል። ከዚህ በተጨማሪ ሁሉም የቤተክርስቲያን አገልጋዮች እና ምእመናን ሀገራዊ ሰላምን፣  መረጋጋትን እና ፍቅር አንድነትን ለማስፈን ጾምና ጸሎት በታወጀበት የምሕላ ሳምንት ለገዳማውያኑ ፀጥታ ሲባል ወደ ገዳማት የሚያደርጉትን ጉዞ ለጊዜው እንዲቆይ መልዕክት ተላልፏል፡፡ https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት በ8ኛ ክፍል ማለፊያ ውጤት ዙሪያ ውይይት በማድረግ የማለፊያ ነጥቡን ይፋ አደረጉ፡፡ በዚሁ መሰረት የ2016 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን÷ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 እንዲሆን አባላቱ በሙሉ ድምጽ አጽድቀዋል። ተማሪዎችም ይህን ማስፈንጠሪያ https://aa.ministry.et/#/result በመጫን መለያ ቁጥርና ስም በማስገባት ውጤታቸውን መመልከት ይችላሉ ተብሏል፡፡ በቀጣይ ጥቂት ቀናትም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ እንደሚደረግ ተጠቁሟል፡፡ https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሊላንድ ወታደሮች ለሥልጠና ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገለጸ! በሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሊላንድ ወታደሮች ወታደራዊ ሥልጠና ለመውሰድ ትናንት ሐሙስ ሐምሌ 4/2016 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸው ተገለጸ።በመንግሥት የሚተዳደረው የሶማሊላንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ ለወታደራዊ ሥልጠና ወደ ኢትዮጵያ የሚጓዙ ናቸው ያላቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ የሠራዊት አባላት በተሽከርካሪዎች ጉዞ ሲጀምሩ አሳይቷል። “የሶማሊላንድ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሜጀር ጄኔራል ኑህ እስማኢል ለሥልጠና የሚጓዙትን ሠልጣኞች ሸኝተዋል” ብሏል መንግሥታዊው የሶማሊላንድ ቴሌቪዥን ጣቢያ በዘገባው። ወታደራዊ ሥልጠናውን በተመለከተ ከኢትዮጵያ መንግሥት በኩል የተባለ ነገር የለም። ከሶማሊላንድ በኩልም እንዲሁም የሠራዊት አባላቱ ቁጥር “በሺዎች የሚቆጠሩ” ከማለት ውጪ ምን ዓይነት ሥልጠና እንደሚወሰዱ የተገለጸ ነገር የለም። ቴሌቪዥን ጣቢያው በበርካታ አውቶብሶች እና የደረቅ ጭነት ተሸከርካሪዎች ከሶማሊላንድ ተነስተው ዋጃሌ የተባለች የድንበር ከተማን አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ ሲገቡ አሳይቷል።ይህንን ጉዳይ በተመለከተ ከኢትዮጵያ እና ከሶማሊያ መንግሥታት በኩል አስካሁን የተባለ ነገር የለም። ከስድስት ወራት በፊት የሶማሊላንድ ከፍተኛ የጦር መኮንኖች አዲስ አበባ ተገኝተው በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ ከኢትዮጵያ አቻዎቻቸው ጋር ውይይት አድርገው እንደነበረ ይታወሳል።በወቅቱ የኢፌድሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሶማሊላንድ ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ሜጄር ጄኔራል ኑህ ኢስማኢል ታኒ ጋር ዝርዝሩ ይፋ ባልተደረገ ወታደራዊ ትብብር ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጾ ነበር። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показати все...
Фото недоступнеДивитись в Telegram
በ424 ሚሊዮን ዶላር የሚተገበር ሁለተኛው ዙር የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ! የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር በስምንት ክልሎች ተግባራዊ የሚደረገውን ሁለተኛ ዙር የቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።ለፕሮጀክቱ ማስፈጸሚያ 424 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በጀት እንደተያዘለት በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ተጠቁሟል። የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ የአርብቶ አደሩንና ከፊል አርብቶ አደሩን ኑሮ ለማሻሻል የተዘጋጀው ፕሮጀክት ተግባራዊ የሚደረገው በስምንት ክልሎች ነው።የፕሮጀክቱ ዓላማ በሀገሪቷ ቆላማ አካባቢዎች የሚገኙ የአርብቶ አደሩን ማህበረሰብ ህይወት ለማሻሻል የሚያግዙ ተግባራትን ማጠናከር መሆኑን ጠቅሰዋል። በተለይም የመሬት ለምነትን በዘላቂነት በመጠበቅ የእንስሳት መኖ ልማት፣ የሰብል እና የአትክልት ምርታማነት ማሻሻል የሚረዱ ተግባራት እንደሚገኙበት ተናግረዋል።በፕሮጀክቱ 600 ሺህ አባወራዎችን ጨምሮ ሦስት ሚሊየን ቤተሰቦቻቸው ቀጥታ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ የመስኖና ቆላማ አካባቢዎች ሚኒስቴር መረጃ አመልክቷል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показати все...
"ተማሪዎቹ ተለቋል!" የኦሮሚያ ክልል "ልጆቻችን አልተለቀቁም!" ወላጆች የታገቱት ተማሪዎች፤ የመንግሥት መግለጫና ቤተሰቦች ባለፈው ሳምንት ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ አካባቢ በታጣቂዎች ከታገቱት 167 የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች 160ዎቹ መለቀቃቸውን የመንግሥት ባለሥልጣናት ቢናገሩም ቤተሰቦች ግን እስካሁን ልጆቹ እንዳልተለቀቁ አስታወቁ። ዶቼ ቬለ ካነጋገራቸው መካከል እህታቸውን እስከትናንት ድረስ በስልክ አግኝተው ማነጋገራቸውና አሁን እዚያው በአጋቾቹ ቁጥጥር ስር መሆኗን የገለጹልን ቤተሰብ የተለየ ነገር አለመኖሩን አረጋግጠዋል። ዛሬ ጠዋትም እህታቸውን እንዲያነጋግሩ ከሚያገናኟቸው አጋቾች አንዱን በስልክ አግኝተው እንደነበር የገለጹት እኒሁ እማኝ እህታቸውን ወዲያው ማነጋገር ያልቻሉት ግለሰቡ ታጋቾቹ ከሚገኙበት አካባቢ ባለመሆኑ ከ30 ደቂቃ በኋላ እንዲደውሉ እንደነገራቸውም አክለው ገልጸዋል። ትናንት ማምሻውን የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ «በተደረገ ጥብቅ ኦፕሬሽን ከ167 ታጋች ተማሪዎች መካከል 160ዎቹ ተለቀዋል» ማለታቸውን የመንግሥት መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። ዜናውን መስማታቸውን ለዶቼ ቬለ የገለጹት እህታቸው የታገተችባቸው የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ «በጣም ይገርማል በእውነት፤ እኔ እኮ በእራሳቸው ስልክ (በአጋቾቹ ማለታቸው ነው) ትናንት ጠዋትም ከሰአት በኋላም እራሴ አግኝቻታለሁ በድምፅ፣ ሰዎቹንም አግኝቻቸዋለሁ። ልጆቹ አሁንም እዚያው ነው ያሉት፤ ተፈተዋል ምናም የሚባለው ነገር ውሸት ነው። ማታ ዜና ስንሰማ ነበር። እንዴት እንዲዚህ ያለ ነገር ይሰራል እስኪ?» በማለት ጠይቀዋል። በተመሳሳይ ከሀዋሳ ያነጋገርናቸው የታጋች ተማሪ ቤተሰብ ምንም የተለየ ነገር እንደሌለ ነው የተናገሩት። እሳቸውም እንዲሁ የታገተችው እህታቸው መሆኗን በመግለጽ እስካሁን ያለችበትን እንዳላወቁ ሆኖም ግን 700,000 ብር ቤዛ መጠየቃቸውን ለዶቼ ቬለ ገልጸዋል። በመንግሥት መገናኛ ብዙሃን «ተለቀዋል» የሚለው ዜና መስማታቸውን የገለጹት የሀዋሳው ነዋሪ ካለፉት ሦስት ቀናት ወዲህ ግን ከአጋቾቹ ወገን ስልክ እንዳልተደወለላቸው አመልክተዋል። ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ጠዋት ከአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባሕር ዳር መኪና ተራ የተነሱት ሦስት አውቶብሶች እንደነበሩ፤ ቀድመው በወጡት ሁለት አውቶብሶች ውስጥ የተሳፈሩት አብዛኞቹ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደነበሩ ነው ከእገታው ካመለጡ ተማሪዎች ያገኘነው መረጃ የሚያመለክተው። በሦስተኛው አውቶብስ ውስጥም እንዲሁ የተሳፈሩት አብዛኞቹ ተማሪዎች ነበሩ ነው የተባለው። በጉዞ ላይ ሳሉም ብዛታቸው ከ25 እስከ 30 የሚገመት ክላሽና አንዳንዶቹም ስናይፐር የታጠቁ አጋቾች ከፊት ያሉት አውቶብሶች እንዲቆሙ አስገድደው የተወሰኑት ለማምለጥ መሞከራቸውን፤ በዚህ ጊዜም ወደ ሰማይ ጥይት መተኮሳቸውንም ዘርዝረዋል። አጋቾች ለታጋቾቹ ቤተሰቦች ስልክ በማስደወል ገንዘብ የጠየቁ ሲሆን ቤተሰቦች የተጣለባቸውን የቤዛ ገንዘብ ለመክፈል መጨነቃቸውን እየተናገሩ ነው። የታጋቾቹ ጉዳይ የሀገር ውስጥ እና የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ተቋማት ቀልብ የሳበ ሲሆን በአዲስ አበባ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ በተለይም በኦሮሚያ እና አማራ ክልል እገታ መደጋገሙ እንዳሳሰበው የሚያመለክት መግለጫ አውጥቷል። በዚህ መሃል ከመንግሥት ባለሥልጣናት የአብዛኞቹ ታጋቾችን መለቀቅ የሚያመለክት መግለጫ ቢሰጡም ቤተሰቦቻቸው እንደሚሉት ግን እስካሁን የተለየ ነገር የለም። በ2012 ዓ,ም ጥር ወር በተመሳሳይ የደምቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የሆኑ ከ17 በላይ ሴት ተማሪዎች ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በታጣቂዎች ታግተው መወሰዳቸው ይታወሳል። በወቅቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕረስ ሴክረታሪ የነበሩት አቶ ንጉሡ ጥላሁን «በመንግሥት ብርቱ ጥረት» ተማሪዎቹ መለቀቃቸውን የገለጹ ሲሆን የተባለውን ቤተሰቦቻቸውም ሆነ ልጆቹ ወጥተው አላረጋገጡም። እስከዛሬ ድረስም የታገቱት ሴት ተማሪዎችን ዕጣ ፈንታ የሚያመለክት ነገር አልተሰማም። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показати все...
አማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት፣ ባለፈው ሳምንት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ገርበ ጉራቻ ከተማ አካባቢ በተፈጸመው የበርካታ ሰዎች እገታ "የመንግሥት የደኅንነት አካላት" እና "የበታች የፓርቲ ካድሬዎች" እጅ አለበት ብሎ እንደሚያምን አስታውቋል። ቡድኑ በክልሉ እየተበራከተ ለመጣው እገታ በክልሉ መንግሥት ሥር ተመስርቷል ያለውን ኢመደበኛ የጸጥታ ኮሚቴ ተጠያቂ አድርጓል። ገዥው መንግሥት የሰላማዊ ሰዎችን እገታ የፖለቲካ ተቀናቃኞችን ለማሸማቀቅ በፖለቲካ መሳሪያነት ይጠቀምበታል በማለትም ቡድኑ ከሷል። ቡድኑ፣ ከመንግሥታዊ አካላትና ከበታች ካድሬዎች ሌላ፣ በመንግሥት ተስፋ የቆረጡ ሥራ አጥ ወጣቶችም የመንግሥት የጸጥታ መዋቅር መዳከሙን እንደ ጥሩ አጋጣሚ በመጠቀም የታጋች ማስለቀቂያ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ሰላማዊ ሰዎችን ያግታሉ ብሏል። https://t.me/voa_amharic1 https://t.me/voa_amharic1
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.