cookie

Ми використовуємо файли cookie для покращення вашого досвіду перегляду. Натиснувши «Прийняти все», ви погоджуєтеся на використання файлів cookie.

avatar

ከፊደላት~መካከል📗📒📕

ስነ ፅሁፍ፣ስነ ጥበብ፣ሙዚቃ፣ፊልም፣መጽሐፍት(በPdf) ሁሉንም በአንድ ያገኛሉ!! ጥያቄና አስተያየት👉@fishgna 👉@byssinia ላይ ያድርሱን!! ለመቀላቀል + ለመጋበዝ t.me/Fidelat_Mekakel ''ሠውም በአምሳሉ መፃህፍትን ፈጠረ'' ***********ማክቱብ*****Mak tube************

Більше
Країна не вказанаМова не вказанаКатегорія не вказана
Рекламні дописи
205
Підписники
Немає даних24 години
Немає даних7 днів
Немає даних30 днів

Триває завантаження даних...

Приріст підписників

Триває завантаження даних...

.... ''ተተኸማ ወንድ ጠፋ እንዴ!? አጣደፍሽኝ'ኮ'' ''የከተማ ወንድ ሁሉ ሲጋራና ጫት አልፈስፍሶታል፤ ወንድ ያለውማ እዚህ ገጠር ነው'' አለች በድገመኝ አይነት እየተሽለጠለጠች። እኔና ጀለስ እኩል ድክም ብለን ሳቅን😂😂 ''አይ አማርኛ ፊልም'' አለና አስከትሎ ''ወጣቱ ሴት ሁሉ እምሰ ከልክልና ብር አሳዳጅ ሆኖ ታዲያ መደበሪያችን ከጫትና ሲጋራ ውጪ ምን ይሁን!?'' ብሎኝ መልስ ሳይጠብቅ ''ሰሞኑን አንዲት ሹገር ጠበስኩ'' አለኝ። ክው ብዬ ''እንዴት?'' ''እንዴት ማለት?'' ማለት እ ሰው ምን ይልሃል? ሰዉ ምን አገባው? ከትልቅ ሴት ጋር ተያይዘህ ስትሄድ ምን ይሉሃል? ደሞ በባህላችን...አላስጨረሰኝም ''ባህላችን ገደል ይግባ...እርቦኝ በየሆቴሉ ቱሩ ልመና ስንከራት ማን አይዞህ አለኝ? ለስንት ቀናት ጎዳና ላይ ዝናብ ሲደበድበኝ በባህላችን መሠረት ብሎ ማነው ከዝናብ ያስጣለኝ? ስንት ጊዜ ነው የሆቴል ሠራተኞች ተርፏቸው የሚጥሉትን ለውሻ የሚሠጡትን ትርፍራፊ ለምኜያቸው ሌባ ብለው ያባረሩኝ? ታዲያ አሁን ምን ተገኝቶ ነው ለሀሜትና ለመጠቋቆም ሲሆን የሠው አይን ውስጥ የምገባው? ስማኝ ልንገርህ ባህል ወግ ምናምን በሚል እፍረት ነው እንጂ ስንት ወንድ አለ እንደሴቶቹ አደባባይ ወጥቶ...ተወኝ በቃ አታስወራኝ ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ትቶኝ ሄደ። መናገር የምችለው ነገር ቢኖር አስቁሜ ሀሳቡን ባስለውጠው ደስ ባለኝ ነበር። ነገርግን ምንም የምለው ነገር የለም ምንም። ምክንያቱም እውነት ነዋ። መለስ ብዬ ወደ ራሴ ተመለከትኩ፤ በሰፈሬ ስንት ሰው ነው ደግ፣የዋህ፣ሩህሩህ የሚባሉት? እጅግ በጣም ጥቂት ናቸው። በእንደዚህ ጥቂትና በባትሪ ተፈልገው በሚገኙ ሰዎች ምክንያት ነው ኢትዮጵያን ደጋጎች ናቸው የሚባሉት። ሌላው ዝም ብሎ አስመሳይ፤ አንዳንዱ ደግሞ በግልፅ ክፋቱ የሚነበብበት...ኧረ ስንቱ ቤት ይቁጠረው.... 𝙖𝙗𝙞 𝙛ª𝙛 t.me/Fidelat_mekakel
Показати все...
ከፊደላት~መካከል📗📒📕

ስነ ፅሁፍ፣ስነ ጥበብ፣ሙዚቃ፣ፊልም፣መጽሐፍት(በPdf) ሁሉንም በአንድ ያገኛሉ!! ጥያቄና አስተያየት👉@fishgna 👉@byssinia ላይ ያድርሱን!! ለመቀላቀል + ለመጋበዝ t.me/Fidelat_Mekakel ''ሠውም በአምሳሉ መፃህፍትን ፈጠረ'' ***********ማክቱብ*****Mak tube************

በየነ ከሰሞኑ ምን ሆነ? (በእውቀቱ ስዩም) (ይህ ፅሁፍ ካስራ ስምን አመት በታች ለሆኑ አንባቢያን እርም ነው) እኛ ኮረና ፈርተን ባደፈጥንበት ጊዜ ጉዋደኛችን በየነ የገነት አበባ የመሰለች ልጅ ጠበሰ ፤ ልእልት ትባላለች! ለሁለት ወራት ያክል ደጅ ካስጠናችው በሁዋላ ድንግልናዋን ሰጠችው፤ ውሸቴን ነው! ድንግልናዋን የነበረበትን ቦታ አስጎበኘችው:: ከዚያ ጠፋች፤ በስንት መከራ እንደገና አገኛት፤ “በዩ ! ግልፅ እንድሆንልህ ትፈልጋለህ?” አለቺው ፤ “ አዎ! “ “ በጣም በጣም ግልፅ? ” “አ..ዎ “ አለ ልቡ እየፈራበት “ የምኝታው ነገር ይቅርብን! አልቻልክበትም ” ‘ እስካሁን እንዳልጎዳሽ ብየ ለኮፍ ለኮፍ ነው ያደረኩሽ ፤ አሁን አንድ እድል ብቻ ስጭኝ! ሌቱን ሙሉ በደስታ ላስለቅስሽ” አለ በየነ በልምምጥ! “ ርግጠኛ ነህ?” “ አቡነ ዘራብሩክን! ለክፉ ቀን ቆጥቤው ነው እንጂ የፍቅር ሸማኔ ነኝ” “ እስቲ እናያለን! ” ከዚያ ራት በሉ ፤ ተጫወቱ፤ ወይን ጠጡ፤ ሶፋ ላይ ተሳሳሙ! በየነ ከራባቱን አንስቶ ወረወረ፤ ሸሚዙን አውልቆ አሽቀነጠረ፤ ለመጀመርያ ቀን ውሃ ዳር የቆመ የዋና ተማሪ መስሎ ርቃኑን አልጋው ዳር ተገተረ፡፡ ልእልት ፤ አልጋው ላይ ጋለል ብላ ፤ አንድ እግሩዋን ወደ ምእራብ አንድ እግሩዋን ወደ ምስራቅ አሰማርታ የየወፍ መንደፍያ ባላ መስላ ጠበቀችው፡፡ በየነ ለሰኮንዶች ያክል ወልመጥ ወልመጥ አለና እንደ ተወጋ ሰው አአአአአአአ ብሎ ደረቱዋ መሀል ተገነደሰ! በረረረረጂሙ ተነፈሰችና " it is ok " አለቺው፤ በረጅም ትንፋሽዋ ውስጥ ካዳመጠው ቅሬታና ብግነት አንፃር it is ok የሚለው ቃሉዋ የሚያፅናና አልነበረም ፤ በየነ ለጥቂት ደቂቃ ያህል ድምጡን አጥፍቶ ከቆየ በሁዋላ ፤ አንጀት በሚበላ ድምፅ እንዲህ አለ፤ “ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ጉዳይ፤ የሰራ አከላቴን ሰቅዞ ይዞት ነው እንጂ፤ በደናው ቀንማ በድቼ በድቼ እማባራ ሰው አልነበርኩም” t.me/Fidelat_Mekakel
Показати все...
ከፊደላት~መካከል📗📒📕

ስነ ፅሁፍ፣ስነ ጥበብ፣ሙዚቃ፣ፊልም፣መጽሐፍት(በPdf) ሁሉንም በአንድ ያገኛሉ!! ጥያቄና አስተያየት👉@fishgna 👉@byssinia ላይ ያድርሱን!! ለመቀላቀል + ለመጋበዝ t.me/Fidelat_Mekakel ''ሠውም በአምሳሉ መፃህፍትን ፈጠረ'' ***********ማክቱብ*****Mak tube************

የእናቴ እናት ስትሞት እሪሪሪ ብዬ አለቀስኩ😭ኧረ እንደውም ራሴን ካላጠፋው ብዬ ያዙኝ ልቀቁኝ አልኩ😊(በርግጥ ይዘው ለቀቁኝ ምንም አላደረኩም) ተው ፈጣሪ የወደደውን ነው ሚወስደው፣ሁሉም ሰው ነገ ሟች ነው፣ ሀዘን አታብዛ፣የአያትህ ነብስ በሰላም ታርፍ ዘንድ ጸሎት አድርግ እንጂ እሷን እያሰብክ አትብከንከን ብላ ብላ ብለው ሊያጽናኑኝ ሞከሩ። የማይረሳ ነገር የለምና የአያቴም ሞት ተረስቶ ሁላችንም ወደ ቀድሞው ሳቅና ደስታ ተመልሰን ኑሮዋችንን ቀጠልን።(ስንኖር ስንኖር 😂) ደሞ ሌላ 😭ሀዘን የአያቶች ወረርሽኝ የተነሳ ይመስል ወንዱ አያቴ ማለትም በጣም የምወደው የአባቴ አባት ሞተ😭 አባቴን ጨምሮ ብዙዎቹ ቤተሰቦቼ አለቀሱ። እኔ ግን ወይ ፍንክች እንባ የሚባል አልወርድ አለኝ። ለቅሶ የመጣ ሁሉ በግልምጫ አላስቆም አላስቀምጥ አሉኝ።(ምን አለበት አርፈው አልቅሰው እንደለመዱት አልቅሰናል እዩን ብለው ሽርጉድ አብዝተው ቢሄዱ) ባህል ይመስል የኔም ቤተሰቦች የመጣና የሄደውን በአይነ_ቁራኛ እና (በአይነ አሞራኛ 😁) እየተከታተሉ ነበር። በሰለስት ማግስት ቤተሰብ ሰብሰብ ብለው ርዕስ መርጠው (#ሀዘናችንን_አቢ_ላይ_መወጣት መሠለኝ ርዕሱ 😊) ይወርዱብኝ ጀመር። አንተ ምን አይነት ድንጋይ ልብ ነው ያለህ!?😡 እንዴት እወደዋለሁ የምትለው አያትህ ሲሞት አታለቅስም!?😠(ወዮዮ ጭራሽ መውደዴንም ተጠራጥረው #እወደዋለሁ_የምትለው አሉኝ'ኮ ከነሱ በላይ እሱን እንደምወደው ልቦናቸው እያወቀው አስመሳይ ሊሉኝም ይቃጣቸዋል) በቃ ሁሉም የየራሳቸውን ስድብና እርግማን አውርደውብኝ ወደየስራቸው ሄዱ። ምንም ሳትል ዝም ብላ አይን አይኔን ስታይ የነበረችው አያቴ የአባቴ እናት ብቻ ናት። (እንዲህ ነው ቀጣይ አንተ ስትሆንና ስትፈራ ምንም ማለት አትመርጥም። አስታውሳለሁ ልጅ እያለን ት/ቤት መርፌ ልንወጋ ሰልፍ ይዘን እስኪደርሰን ድረስ እንዘላለን፣ እየተወጋ ያለውን ልጅ ፊቱን እያየን በድንጋጤው ስንስቅ እና ስንዝናና ቆይተን የኛ ተራ ሲደርስ ግን ዝምታን እንመርጣለን። አያቴ ፊት ላይ ያየሁት ይሄንን ነው። ምን አልባት ተረኛ ልትሆንም፡ላትሆንም ትችላለች። ግን ፊቷ ላይ ድንጋጤ ይታያል።) አሊያም ደግሞ ወደ ውስጥ ማልቀሴን፣ ውስጤ መጎዳቱን በአትኩሮት ተመልክታ አዝናልኝ ይሆናል። (#አልቋልም_አላለቀምም) ✍Abi F t.me/Fidelat_Mekakel
Показати все...
ከፊደላት~መካከል📗📒📕

ስነ ፅሁፍ፣ስነ ጥበብ፣ሙዚቃ፣ፊልም፣መጽሐፍት(በPdf) ሁሉንም በአንድ ያገኛሉ!! ጥያቄና አስተያየት👉@fishgna 👉@byssinia ላይ ያድርሱን!! ለመቀላቀል + ለመጋበዝ t.me/Fidelat_Mekakel ''ሠውም በአምሳሉ መፃህፍትን ፈጠረ'' ***********ማክቱብ*****Mak tube************

የእናቴ እናት አያቴ ስትሞት እሪሪሪ ብዬ አለቀስኩ😭ኧረ እንደውም ራሴን ካላጠፋው ብዬ ያዙኝ ልቀቁኝ አልኩ😊(በርግጥ ይዘው ለቀቁኝ ምንም አላደረኩም) ተው ፈጣሪ የወደደውን ነው ሚወስደው፣ሁሉም ሰው ነገ ሟች ነው፣ ሀዘን አታብዛ፣የአያትህ ነብስ በሰላም ታርፍ ዘንድ ጸሎት አድርግ እንጂ እሷን እያሰብክ አትብከንከን ብላ ብላ ብለው ሊያጽናኑኝ ሞከሩ። የማይረሳ ነገር የለምና የአያቴም ሞት ተረስቶ ሁላችንም ወደ ቀድሞው ሳቅና ደስታ ተመልሰን ኑሮዋችንን ቀጠልን።(ስንኖር ስንኖር 😂) ደሞ ሌላ 😭ሀዘን የአያቶች ወረርሽኝ የተነሳ ይመስል ወንዱ አያቴ ማለትም በጣም የምወደው የአባቴ አባት ሞተ😭 አባቴን ጨምሮ ብዙዎቹ ቤተሰቦቼ አለቀሱ። እኔ ግን ወይ ፍንክች እንባ የሚባል አልወርድ አለኝ። ለቅሶ የመጣ ሁሉ በግልምጫ አላስቆም አላስቀምጥ አሉኝ።(ምን አለበት አርፈው አልቅሰው እንደለመዱት አልቅሰናል እዩን ብለው ሽርጉድ አብዝተው ቢሄዱ) ባህል ይመስል የኔም ቤተሰቦች የመጣና የሄደውን በአይነ_ቁራኛ እና (በአይነ አሞራኛ 😁) እየተከታተሉ ነበር። በሰለስት ማግስት ቤተሰብ ሰብሰብ ብለው ርዕስ መርጠው (#ሀዘናችንን_አቢ_ላይ_መወጣት መሠለኝ ርዕሱ 😊) ይወርዱብኝ ጀመር። አንተ ምን አይነት ድንጋይ ልብ ነው ያለህ!?😡 እንዴት እወደዋለሁ የምትለው አያትህ ሲሞት አታለቅስም!?😠(ወዮዮ ጭራሽ መውደዴንም ተጠራጥረው #እወደዋለሁ_የምትለው አሉኝ'ኮ ከነሱ በላይ እሱን እንደምወደው ልቦናቸው እያወቀው አስመሳይ ሊሉኝም ይቃጣቸዋል) በቃ ሁሉም የየራሳቸውን ስድብና እርግማን አውርደውብኝ ወደየስራቸው ሄዱ። ምንም ሳትል ዝም ብላ አይን አይኔን ስታይ የነበረችው አያቴ የአባቴ እናት ብቻ ናት። (እንዲህ ነው ቀጣይ አንተ ስትሆንና ስትፈራ ምንም ማለት አትመርጥም። አስታውሳለሁ ልጅ እያለን ት/ቤት መርፌ ልንወጋ ሰልፍ ይዘን እስኪደርሰን ድረስ እንዘላለን፣ እየተወጋ ያለውን ልጅ ፊቱን እያየን በድንጋጤው ስንስቅ እና ስንዝናና ቆይተን የኛ ተራ ሲደርስ ግን ዝምታን እንመርጣለን። አያቴ ፊት ላይ ያየሁት ይሄንን ነው። ምን አልባት ተረኛ ልትሆንም፡ላትሆንም ትችላለች። ግን ፊቷ ላይ ድንጋጤ ይታያል።) አሊያም ደግሞ ወደ ውስጥ ማልቀሴን፣ ውስጤ መጎዳቱን በአትኩሮት ተመልክታ አዝናልኝ ይሆናል። (አልቋልም_አላለቀምም) t.me/Fidelat_Mekakel
Показати все...
ከፊደላት~መካከል📗📒📕

ስነ ፅሁፍ፣ስነ ጥበብ፣ሙዚቃ፣ፊልም፣መጽሐፍት(በPdf) ሁሉንም በአንድ ያገኛሉ!! ጥያቄና አስተያየት👉@fishgna 👉@byssinia ላይ ያድርሱን!! ለመቀላቀል + ለመጋበዝ t.me/Fidelat_Mekakel ''ሠውም በአምሳሉ መፃህፍትን ፈጠረ'' ***********ማክቱብ*****Mak tube************

ለአንዴ ሴት ባረገኝ የልጅነት ወዝ ደም ግባቴ፣ ለአይን ሞልቶ ውበቴ፣ በሴትነት በተማሪ፣ ተፈቅሬ በASSተማሪ፣ በእውቀት ሳይሆን በውበቴ፣ ሰቃይ ተብዬ በትምህርቴ፣ ተምሬ ሳላውቅ ሳይገባኝ፣ የጎበዝ ክብር እንዲ'ገባኝ፣ በቀሚሴ በኩል በሚታየው ጭኔ፣ በጥብቆዬ ቀዳዳ በሚታየው ጡቴ፣ ለተማሩት የሆነውን ያንን ጥቁር ካባ ጥቁር ልብስ፣ እኔም ሳልማር እንድለብስ፣ ለባለ-ጠመኔው ምሁር፣ ለዛ ትንሽ መምህር፣ እንጥልጥል ውበቴ ወንድነቴ ቀርቶ፣ እኔን በሴትነት እንደገና ሰርቶ፣ አይነግቡ ውበት ቁንጅናን ሳይነፍገኝ፣ ለ''A+''Grade ለአንዴ ሴት ባረገኝ። (በእውቀታቸው ሳይሆን በተግባራቸው ላነሱ ቅሌታም መምህራን) ✍ገጣሚ ዘላለም ተሾመ (የሳጥን ወርቅ) ከእፀሳቤቅ መጽሐፍ የተወሰደ
Показати все...
#የመዲባ_ኡሪ (አዳም ረታ) ከዕለታት አንድ ቀን ‘ጣይቱ’ የተባሉ እተጌ እዛች ፍልውሃ የምትባለው የምትጤስ ቦታ፣ እዛች እርጥብ ፊንፊኔ ገላቸውን ተጣጥበው ጨርሰው፣ ከተቀመጡበት በርጩማ ብድግ ሲሉ፣ እንደ ደንግ የምታበራ የሕልም እንቁላላቸው የምትሞቅ ግልገል ኩሬ ውስጥ ወደቀች፡፡ ከዛም ወደ ተሰራላቸው ማረፊያ ጎጆ አቀበቱን ሲያዘግሙ፣ ስሟ የተጠራ ከተማ የመቆርቆር ምኞታቸው በሚያልፉበት ጎዳና ላይ ከአንደበታቸውና ከረጠበ ጉንጉናቸው ተንጠባጠበ፡፡ ባለቤታቸው ንጉሠ ነገሥት ሚኒሊክን ጨምሮ ሕዝቦች ያን ከፍል ውሐ ጉም እስከ ባዕታ ወይራዎች ድረስ የተዘራውን የእመቤታቸውን ምኞት አተኩረው እንደ ጥሬ ለቀሙ (ምንም እኳን በንግርት ባላቸው እንጦጦ ላይ የታፈረ መንግስት እንዲያቆሙ ንግርት አለ ቢልም)፡፡ ቅጠል በልቶ ከተነበየ ባሕታዊና አውቃለሁ ባይ የአምደ ፅዮን ዘመን ደብተራ ይልቅ ጎርጎራ ከተማ በጣና ዳር በመረጋጋት የሰለጠነ የንግሥት ጣይቱ ድምቡሼ ገላ ትንቢትን አሸነፈ፡፡ ብዙም ሳይቆይ ምኒሊክ እንጦጦ ማሪያም ግቢ ጉባኤ ጠርተው መኳንንቶቻቸውን እንዲህ አሉ፡ “አዲስ አባን እንካችሁ፡፡ ተጠራርታችሁ ሙሏት” እነሱም እንደ ተባሉት ሠራዊቶቻቸውን እየመሩ ፍል ውሃ ዙሪያ ሳርና ጭቃ ላይ እንደ ጨርቅ ተጣፉ፤ እንደ ድንጋይ ተኮለኮሉ፡ ሸጎሌ፣ አባ ኮራን፣ ጉለሌ፣ ጎላ፣ ተረት ሰፈር፣ ሠራተኛ ሰፈር፣ አራዳ…… እንዲያ እንዲያ እያለ በጅረት እና በወንዝ የተሸረሸረች፣ አፈርና ሳር የነበረችው የፊንፊኔ ሜዳ በሰውና በጎጆ፣ በሰንሰልና በባሕር ዛፍ ሞላች፡፡ ዘመናዊ ለመሆን ማሽቃበጥ ስትጀምር በ1928 ጣሊያን ገባና በሲሚንቶ፣ በዘረኛነት፣ በአስፋልት…… ይሄንንም እንዲያዳምቁ ጦርነት የበተናቸውን ወይዛዝርት ሰብስቦና አደፋፍሮ በመለኮ (እዝራ እንዳለው) አጎለበታት፡፡ በ1933 አ.ም. ላይ ትቷት ሲሄድ የምንወደውን፣ የሚቀርበንንና የምንችልበትን ጠበቅን፡ ጥቂት ትምህርት ቤቶችን፣ አልሞት ያለ የአስፋልት መንገዱን፣ ለገሃርን፣ ፖፖላሬን፣ ካዛንቺስን፣ ፒያሳን፣ መርካቶን አረቄና ሽርሙጥናን (ልጅን ሲወዱ ከነንፍጡ)፡፡ ያኔ ይሄ ሁሉ ሲሆን ሽሮሜዳ፡ በእግር መንገዶች የተሸነሸኑ አረንጓዴ አራዳ ሜዳዎች የገነኑባት፤ ጥቁርና ቀይ አፈራቸው በዝናብና በጎርፍ የፈረሱ ተረተሮች አረሆ የተቀረፁባት፣ በጋ በጋ የሚደርቁ ጭቃማ ጅረቶች የሚሰርቡባት፣ ሚዳቋዎች ከተራራው እየዘለሉ መጥተው እየዘለሉ የሚሸሿት፣ በአጋም፣ በቀጋ፣ በቁጥቋጦና በፅድ ደኖች መሃል አሾልከው የሚያዩ ጎጆዎች የፈሉባት፣ ዝግባ ዛፍ ስር ያደፈጡ መንገደኛ መቀበያ ኮሳሳ ማደሪያዎች የተጎለቱባት፣ የቄስ የደብተራና የገበሬ ቅልሳቶች ያፈጠጡባት፣ የገግና የበሬ ነጋዴዎች ጉሮኖዎች የተነቀሱባት፣ ልብሳቸውን ሳር ላይ የሚያሰጡ ወይዘሮዎች የሚያንጎራጉሩባት፣ ጠዋት ማታ የሚንጋጋ ጅብ እዚህና እዚያ በነጭ ኩሱ የነቀሳት ቦታ ነበረች፡፡ እኔም ነጋ ጠባ ባሳፈፈ የእንጨት ጭስና የባሕር ዛፍ ድምድማት ተከልሎ ይኑር አይኑር በማይታወቀው የአዲስ አባ ማዕከልና በዝናብ እየታጠበ፣ የሌሊት ዝምታው ቋጠሮ አሁንም አሁንም በጅብ እሙኝታ፣ በውሾች የሌሊት ሃዝ ሃዝ፣ በሚፈታው የእንጦጦ ተራራ መሃል፣ ከኋለኛው ቀርቤ ከፊተኛው ዕርቄ ተወለድኩ፡፡ የከተማችን ቀያሾች ‘መዲባ’ ይሏታል፡፡ በመዲናና በባላገር መሃል ናችሁ ሲሉን፡፡ እየሰደቡን ይሆን እየመደቡን ይህቺ ማርያም ታውቃለች፡፡ ሽሮሜዳ ‘ሽሮሜዳ’ የተባለችው የአረጋሽ ባል ጋሼ ሰይፉ ሲያወራ እንደሰማሁት እዚህ አካባቢ በድሮ በድሮ ጊዜ ሰፈሩን አፈሩን ሽሮ መስሎአቸው ወጥ ሰርተው በልተውታል ተብሎ ነው አሉ፡፡ ስለ የድንጋይ ዳቦ ዘመን ከተወራ ስለ የአፈር ሽሮ ዘመን አይቻልም? ሽሮን (ስናቆላምጣት) የአዲስአባ ፕላን አውጪዎች ከሚያዳሉላቸው ቦሌና አሮጌው አይሮፕላን ማረፊያ ውበቷ ይበልጣል፡፡ የመስከረም አረንጓዴና ቢጫነቷን? በየመንገዶች ግራና ቀኝ ከእንጦጦ የሚወርደውን ወርቅማ ውሃዋን…… እንጦጦ ወጥተን በላስቲክ ኮሮጆ ሰብስበን የምናመጣቸውን አጋምና ቀጋዋን ማን ይስተካከላታል? ሽሮሜዳ እያደገች ብዙ ሰዎች ሊኖሩባትና ሊሰሩባት መጡ፡፡ የአልማዝ ጉርጉሱም ሆቴልና ተራራ ካፊቴሪያ ተከፈቱ፡፡ ግራና ቀኝ በየመንገዱ ዳርና ዳር ቡና፣ ጠላና አረቄ ቤቶች ተደረደሩ፡፡ ጥቂት ልብስ ሰፊዎችና የልብስ ሱቆች እዛ እዛ ተተከሉ፣ የሚያምር አጂፕ ነዳጅ ማደያ ከተራራ ሆቴል ዝቅ ብሎ ተከፈተ፡፡ ጫማ ሰሪዎች ትናንሽ መጠለያቸው ውስጥ መዶሻቸውን ይዘው ተቀመጡ፡፡ በዚች ጥቁር ሰረሰር በመሰለች አስፋልት መንገዳችን ጠርዝ ሸንኮራ ሻጩ ዋሕድ እየተጎማለለ መዘየር ጀመረ፡፡ የዚህ ሰፈር ሰዎች ሕብስት አያምራቸው፣ አጅሬ ሸንኮራ ገብቶ ከቤታቸው!! ቅልብጭ ባለችው ለግላጋ የመንደራችን ካርታ ላይ ሰካራም በረታ፡፡ እኔም እንደ አካባቢዬና እንደ ከባቢዬ ብዙ አለማዊ ዕውቀት ተማርኩ፡፡ ጊዜ አልወሰደብኝም በጉጉቴ ስፋትና በቀልቃላነቴ ጥልቀት ከከተማውም ከገጠሩም የደባለቀ የመዲባ ዜጋ፣ ደህና ዲቃላ ሆንኩ፡፡ መረቅ፣ ገጽ 11 – 13 t.me/Fidelat_Mekakel
Показати все...
ከፊደላት~መካከል📗📒📕

ስነ ፅሁፍ፣ስነ ጥበብ፣ሙዚቃ፣ፊልም፣መጽሐፍት(በPdf) ሁሉንም በአንድ ያገኛሉ!! ጥያቄና አስተያየት👉@fishgna 👉@byssinia ላይ ያድርሱን!! ለመቀላቀል + ለመጋበዝ t.me/Fidelat_Mekakel ''ሠውም በአምሳሉ መፃህፍትን ፈጠረ'' ***********ማክቱብ*****Mak tube************

ለሰይጣን የተፃፈ ደብዳቤ ! በአሌክስ አብርሀም ሞት ለሰው አቅራቢው ጠቅልለህ በእንቁ እንዴት ነህ ሳጥናኤል ሉሲፈር የጥልቁ ያው መቸም ውሸት ነው ያንተ ቃል ከጥንቱ ግዴለም ለመልሱ አትድከም በከንቱ ! እኛማ…. ያው እንደምታውቀው ከማይዋሸው ቃል ነው እውነት የምንጠልቀው ! እና መፅሃፉ እንዳለው ከሆነ የውበት ፍፃሜ በሃይል የገነነ እምቢልታ ከበሮ በገና ዋሽንቱ ከፊቱ ተቀምጦ ላምልኮ የተጠራ ልብሱ እንደፀሃይ ለጉድ የሚያበራ አርጎህ ነበር አሉ ሁሉን ቻይ ሲፈጥርህ ያንን መልካም ዘመን አጉል አስታወስኩህ ! እኔ ምልህ ሰይጣን . . . ከዘፍጥረት በፊት የቀደመው ልደት ገና ሳይታወጅ ኪሩብ ነበርክ አሉ በሃያሉ እግዚአብሔር በመጋረጃው ደጅ ! እንግዲህ ዛሬ ላይ አንተም የግር እሳት የሆነብህ ጣጣ ትቢት አስገፍትሮህ ወዳለም ስትመጣ በተልካሻ ተንኮል ሁነህ ነብስ ሸቃጭ ሰውን ከራሱ ጋር ስታናጭ ስታጋጭ እዚህ ዘረኝነት አዛ ስልጣን ፀጋ ደግሞ ወዲያ ውበት… ለማይሽጥ ነገር የመሸጫ ዋጋ !! ህላዌን ስትለይ ከከበረው እጣ ዳግመኛው ውርደትህ ዳግመኛ ሊመጣ ቀኑ እየባጀ ነው ጭንቀትህ እንዴት ነው ? እኛማ ይሄውልህ … አለቀልን ብለን የዘላለም ህይወት የዘላለም ተስፋ ሙት ሚስኪን ነፍሳችን ተራዋ እስከሚደርስ ሲኦል ተሰልፋ ያንተን ክስ ተቀባይ ባንተ ተሸናፊ እንዳንተው ውሸታም እንዳንተ አገር አጥፊ ሁነን ስንሻኮት ፍርሃት አንግሰን ከላይ የግዜርን ስም ከውስጥ አንተን ለብሰን በሰውኛ ቁማር ነብሳችን ተበልታ አንተን ተከትላ ላንተው ተርቲብ ገብታ ታድናለህ ሲሉህ መቆስቆሻ ይዘህ ወደ እሳት ጉድጓድ የገፋኸን ለታ ትዝ ይልሃል አይደል . . .? ዓለም ዳር ስከዳር በሚጨንቅ ፅልመት እንደጨላለመ እንደሰራዊት ድምፅ በፍቅር ተጭኖ እያስገመገመ ከተፍ አለ ቃሉ በቃ ተፈፀመ …. ተ ፈ ፀ መ !! ያ ነው የፍቅር ልክ ያ ነው የኛ ዋጋ በትንሳኤው ጉልበት ሞትን የሚወጋ !! እኔ ምልህ ሰይጣን . . . መቸም ለነጣቂ በዚች በኛ ምድር ራስ ይሉት ዋጋ አወራርዶ ሚያድን መቃብሩን ከፍቶ ሞትን የሚከድን ከልካይ በሌለበት መንጋውን ወደሳት ተኩላው ሲነዳ የረኛው መከሰት መርዶ ነው ዱብ እዳ! እኔ ምልህ ሰይጣን . . . በፍጥረት አእምሮ እኔነት ሲነግስ ሰው ልቡን ሲያመልክ ለራሱ ሲገዛ አንድየ ልጆቹን ለክፉ ገብሮ የተወ እንደዋዛ መስሎህ ነበር አይደል …..?? ምን ታደርገዋለህ የሰላም አለቃ የሞት አዋጅ ዘመን በቃ ሲል አበቃ !! ((( ቅንጣት ዋጋ ሳንከፍል ያውም እየካድነው የክስህን ፋይል በፍቅሩ ከደነው !! ))) ያው በምድር ቋንቋ ‹‹በጭማሬ ሰአት›› እንደምትራወጥ ነግሮናል ልኡሉ ቃልህ ቢብረቀረቅ ድምፅህ ምን ቢገዝፍ አይበልጥም ከቃሉ !! እመጣለሁ ብሏል ይመጣል ንጉሱ ሳቅ በዛ ይሆናል በግፍ ላለቀሱ ሰማይ በመለከት ቃጤ ልትሆን ቀርቧል የፅድቅ ሰራዊት አጀቡን ሽቅብ ሊያይ ምፅአት ተርቧል ! ማነው የሚመጣው . . . ? ባክህ አታስመስል እውነት አታምታታ ዳንኪራ ቢረገጥ ከበሮ ቢመታ ከነውሸት ደስታህ ክብርህ ተደቁሷል በደሙ ጠብታ ! ታውቀዋለህ አይደል …..? ያንን ህያው ትንታግ የጌቶቹን ጌታ አፈር ድሜ በልተህ ያቆምከውን መንግስት ባንድ ቀን ሲንደው በደሙ ጠብታ ! ታውቀዋለህ አይደል …? የበሰበሰ አጥንት ልታፍስ ስትገባ ባዶ መቃብር ውስጥ ህይዎት ፍንትው ሲል እንደዱር አበባ ! በጭፍሮችህ አመፅ ያሰርከው ሰንሰለት ከልጆቹ እጅ ላይ እንደሳር ሲበጠስ ግሳቱ ሚያስፈራ የፅልመት ውቂያኖስ በቃሉ ሲገመስ በደረቅ እንጨት ላይ የልጆቹን ስቃይ በፍቅር የቻለ የሞትን ፍላፃ ጅራፍ በበጨቀው ስጋው የከለለ የሃፂያትን እዳ በደሙ ያነፃ ያንተን የነብስ ንግድ ፀያፍ ያደረገው ያዳነን በነፃ !! ትቢተኛ ንጉስ ሳር ሲግጥ ተዋርዶ ያ የምትፈራው ስም ልጆቹን ከእሳት ሲነጥቃቸው ወርዶ እሱ ነው ሚመጣው !! ታውቀዋለህ አይደል …. መቸም ከሃዲ ነህ ግዴለም ሸምጥጠው ያንተ ቤት ነጋዴ ነብስን ያህል ነገር በውሻሸት ኮተት አታሎ ሚሸጠው ካንተ የነፍስ እስር በሱ ነው ሚያመልጠው !! ባክህ ታውቀዋለህ …. በሁለት አሳና በአምስት እንጀራ በምድረበዳ ላይ አምስት ሽ አጥግቦ ተአምር የሰራ ይመጣል ልኡሉ አይቆይም ይመጣል ያኔ ያንተ ጭፍራ መደበቂያ ያጣል ያለም እንቶፈንቶ ያለም ግሳንግሱ ጥራጊ ይሆናል ሲገለጥ ንጉሱ !! ታውቀዋለህ አይደል . . .? በብርሃን ተከቦ በመልአክ አጀብ ሰማዩን ሲሞላው የመለከቱ ድምፅ ምድሩን ሲንጠው ያኔ ነው ያንተ ቤት የሚደነግጠው ! ያኔ ነው ጭፍሮችህ ታድናቸው ይመስል ላንተ የሚጮሁት ጥፍርህ ውስጥ ገብተህ አንሰህ አሳናሽ ጉድ መሆንክን የሚያውቁት ራቁት !! ከልካይ በሌለበት መንጋውን ወደሳት ተኩላው ሲነዳ የረኛው መከሰት መርዶ ነው ዱብ እዳ! ቅንጣት ዋጋ ሳንከፍል ያውም እ የ ካ ድ ነ ው የክስህን ፋይል በ ፍ ቅ ሩ ከደነው !! ይህን ታላቅ እውነት ዘመን ሊያደበዝዝ ጉልበቱ ተሰልቧል የመቃብር ክዳን እንደመፀሃፍ ገፅ እየተገለጠ ትንሳኤ ተነቧል !! በቃ ተ ፈ ፀ መ !! ┉┉✽̶»̶̥ĵøïņ✿śĥăŕę»̶̥✽̶┉┉ @fOr_DReaMEr @OnLY_for_dREaMEr ┉┉✽̶»̶̥🔥✿🔥»̶̥✽̶┉┉              
Показати все...
የስርዓተ ማህበሮች ትርጓሜ ----- ከሀይሉ ገብረ ዮሐንስ (ገሞራው) ----- የየዘመኑን ስርዓተ ማህበር ምንነት ቅልጥጥ አድርጎ ለማሳየትና የማያሻማ ፍቺ ለመስጠት የየሀገሩ የቱርጁማን ጠበብት ያልቧጠጡት የሃሳብ ኮረኮንችና ያልዳሰሱት ሸካራ ብሂል የለም፡፡ በየዘመኑ ለተከሰቱ የማህበረሰብ አስተሳሰቦች ከተለያዩ ምሁራን የተለያየ ፍቺና ትርጓሜ ተሰጥቷል፡፡ ምሁራኑ በዘመናችን ከደረሱበት መተርጉም አንዱ በሁለት ላሞች ተምሳሌትነት የቀረበው ነው፡፡ የነጠረውን ፍጹማዊ መተርጉም እስኪያገኙ ድረስ የፈረንጅ ሊቃውንት ይህንን በሁለት ላሞች ላይ የተመሰረተ ተምሳሌታዊ መተርጉም ሰጥተዋልና ከግልዎ ግምገማ ጋር በማያያዝ ይህችን አጭር ሐተታ ያነጻጽሩት ዘንድ እነሆ ብለናል፡፡ 1. ሶሻሊዝም እርስዎ ሁለት ላሞች ይኖርዎታል እንበል፡፡ በሶሻሊዝም ስርዓተ-ህይወት እስካሉ ድረስ አንዲቷን ላም ለራስዎ መድበው ሌላይቱን ለጎረቤትዎ መዳረግ ግዴታዎ ነው፡፡ 2. ኮሚኒዝም እርስዎ ሁለት ላሞች ይኖርዎታል እንበል፡፡ በኮሚኒዝም ስርዓተ ማህበር ውስጥ እስካሉ ድረስ መንግሥታዊው የኮሚኒስት ፓርቲ ሁለቱንም ላሞችዎን ይወስድብዎትና የድርሻዎን ያህል ብቻ ወተት ያድልዎታል፡፡ 3. ፋሺዝም እርስዎ መንታ ላሞች አሉዎት እንበል፡፡ በፋሺዝም ስርዓ-ህይወት እስካሉ ድረስ የሚገዛዎ የመንግሥት ቁንጮ ሁለቱንም ላሞችዎን ይነጥቅና የሚያልበውን ወተት ለራስዎ ይሸጥልዎታል፡፡ 4. ናዚዝም እርስዎ መንታ ላሞች አሉዎት እንበል፡፡ በናዚዝም ስርዓተ-ሕይወት እስካሉ ድረስ ጨካኙ መንግስት ሁለቱንም ላሞችዎን ዘርፎ ከወሰዳቸው በኋላ ራስዎን ጭምር ያርድዎታል፡፡ 5. ቢሮክራሲዝም እርስዎ ጥንድ ላሞች አሉዎት እንበል፡፡ የሚኖሩበት ስርዓተ ማህበር ቢሮክራሲዝም እስከሆነ ድረስ ሁለቱንም ላሞች ይወስድብዎትና አንደኛይቱን ያርዳታል፤ ሌላይቱን ግን እያለበ ወተቷን እመቅ ያፈሰዋል፡፡ 6. ካፒታሊዝም እርስዎ የሁለት ላሞች ባለቤት ነዎት እንበል፡፡ የሚኖሩበት ስርዓተ ማህበር ካፒታሊዝም እስከሆነ ድረስ በዘዴ ይወስድብዎና አንዲቷን ላም ከሸጠ በኋላ ለገዛ ራሱ ለማራባት ሲል በተሸጠችው ላም ገንዘብ ኮርማ ይገዛበታል፡፡ ማን ቀረ? ማኦይዝም፤…ሌኒንዘም፣. ራዲካሊዝም፣… ሊብራሊዝም፣ ኒኦ-ሊብራሊዝም፣ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ወዘተ… አሉ፡፡ እስቲ በዚህ የሁለት ላሞች ቀመር መሰረት ራስዎ የሚኖሩበትን ስርዓተ ማህበር ለመተርጎም ይሞክሩ፡፡ * ሃይሉ ገብረ ዮሐንስ፣ መስከረም 1994
Показати все...
ጎጃም አዘነው የት ሄደ??..(ክፍል 4) በዮናስ ኪዳኔ ትምህርት ቤት ተዘግቷል። ክረምት ነበር፤ እውቀት ቀርቶ የምንራገጥበት ወቅት። ለዚያ ነው ወላጆች አንጠልጥለው ለየኔታ ያስረከቡን። እንድንማር ፈልገው አይመስለኝም። ቢሆንማ አምና የተማርነውን “ሀ ሁ…” ባልደገምን ነበር። የኔታ ከግቢው ቅጥር ወዲህ አዛዥ ናቸው። ግቢው ውስጥ እስካለህ ድረስ፣ በልምጭ ቢሉህ ጠያቂ የላቸውም። “ሰፈር ከሚያውደለድሉ…” ተብሎ ነው እሳቸው ጋር መዋላችን… ‘ጥሩ ልጆች’ እንድንሆን! ብቻ ፊደል እየደገሙም ቢሆን አዲስ ትምህርት አይጠፋም። ከመሃላችን አዲስ ክር ያሰረ ሰው የኔታ ጋር ሄዶ ያስባርካል። የተለመደ ነው። ቤተሰብ ማእተብ ይገዛልሃል፣ የኔታ ፈንጅ የሚያስስ ጥበቃ ይመስል፣ በመስቀላቸው ሰውነትህ ላይ እያንዣበቡ፣ የግዕዝ ቃላት ያነበንባሉ። አበቃ። ስምንት ሰከንድ አይወስድም ሂደቱ። እንዲያውም አንዳንዴ በመሃል አቋርጠው “አንተኛው አታርፍም ዎይ?” ይሉ ነበር… አንዱን ረባሽ እያዩ… አንድ ቀን ይህን ተማርን። ከመሃላችን አንዱ፣ የኔታ ዘወትር እንደሚያሳስቡን ጥቁር ክር ሳይሆን፣ የወርቅ ሃብል አስሮ መጣ… ባለመስቀል ነው ደግሞ… “ምናለ በሉ… የኔታ ይቆጡታል” አለ ናዖድ በሹክሹክታ… “ለምን?” የሰፈር ጓደኛው… “ከጥቁር ክር ሌላ አታድርጉ ብለዋላ!” ዝም። “ሄደህ አስባርክ” አለው እሱን ደግሞ ጮክ ብሎ። የኔታ ግን ሌሎቻችን እንደምናደርገው፣ ሄዶ እስኪጠይቃቸው አልጠበቁም። መጡና እንደ ጓደኛ አቅፈውት ከአዳራሹ ወጡ። “ወዴት ነው የሚወስዱት? ለምን አቀፉት? አባ ተማሪ ያቅፋሉ ወይ?” ናዖድ “የሱ ማእተብ ለየት ስለሚል ነው!” ጓደኛው… “የኔታ ያዳላሉ ማለት ነው?” ““ማእተብህ ውድ ከሆነ…” “አሃ?… ታድያ ለምን ‘አታዳሉ’ ይሉናል?” ዝም። የወጡት መስቀልና ልምጫቸውን ይዘው ነበር ደግነቱ፣ ትምህርቱን ትተን እናያቸው ጀመራ። እየተጋፋን በአዳራሹ ግድግዳ እናጮልቅ ያዝን። ልጁን ይዘውት ራቅ አሉ። መስቀላቸውን አወጡና ለረጅም ደቂቃዎች አንገቱ ላይ ያለውን የወርቅ ሃብል ሲባርኩ ቆዩ። “እንንዴ?" አለ ናዖድ “የኔን ማእተብ ሲባርኩ እንዲህ ቆይተው ነበር?” “ያንተ ማእተብማ ጥቁር ክር ነው!” ጓደኛው “እኮ… ልክ እሳቸው እንደነገሩን…” “እሱን ተወው” ዝም። የኔታና የወርቅ ሃብሉን ያስባረከው ልጅ ተያይዘው ሲመለሱ፣ ናዖድ አንገቱ ላይ የነበረውን ክር ይዞ ይጎትት ነበር። ናዖድ በነጋታው ሲመጣ፣ አንገቱ ላይ ማእተብ አልነበረም።
Показати все...
የስፓርት አፍቃሪ ነወት??እንግዲያውስ የሚከተለውን ቻናል ሠብስክራይብ በማረግ ስፓርትን በሳይንሳዊ መንገድ ይከታተሉ👇👇👇👇👇👇 https://m.youtube.com/channel/UCxL51xKeu0DQ_28LSXqs0Qg/featured?f=co
Показати все...
Оберіть інший тариф

На вашому тарифі доступна аналітика тільки для 5 каналів. Щоб отримати більше — оберіть інший тариф.